ና እንቀደስ
እኔና አንተ ማለት
የዓለም መንገደኛ ብንሆንም ደካማ
አይተወን ጌታችን ለሱም ባንስማማ
ብንኳትንም በምድር ብንል ወጣ ገባ
ዛሬስ እንመለስ ከመቅደሱ እንግባ
ና እንቀደስ ነጩን ልብስ እንልበስ
አለን እንበለው ሳትሞት ረቂቋ ነብስ
አያውረን ስጋ አይተብትበን ምቾት
ከእርሱ ዘንድ ብቻ ነው እውነተኛው ህይወት
ዓለም አታላይ ናት እንዳትወስደን ቀድማ
ከአውደምህረቱ ስር ወንጌሉን እንስማ
ና እንቀደስ ነጩን ልብስ እንልበስ
አለን እንበለው ሳትሞት ረቂቋ ነብስ
ፍቅር ማለት ጌታ ፍቅር ማለት እውነት
በፍቃድ በህጉ እንዲኖረን ጥምረት
የዓለምን ስርዓት እንተው እንዘንጋ
በፍቃዱ ያጣምረን እንሂድ እርሱ ጋ
ና እንቀደስ ነጩን ልብስ እንልበስ
አለን እንበለው ሳትሞት ረቂቋ ነብስ
እንታጭ ለትዳር ለተክሊሉ ሞገስ
እስኪያደርሰን ለዚያ ምግባር እንላበስ
ሁለትነት ቀርቶ አንድ እስክንሆን ድረስ
በቤቱ እየሄድን ዘውትር እንቀደስ
✍️የተክልዬዋ
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
🥰ሄዋኖች ለአዳሞቻቹ ሼር አድርጉ🥰
✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️
1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 50 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 25 ብር ካርድ
➡️ ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇
✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️
1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ
2️⃣ ለወጣ 50 ብር ካርድ
3️⃣ ለወጣ 25 ብር ካርድ
➡️ ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇
ዘመነ አስተምህ(ሕ)ሮ እና ዘመነ ስብከት
በቤተክርስቲያናችን አንድ ዓመት በመጽሐፍ ቅዱስና በቅዱስ ያሬድ የድጓ መጽሐፍ መሠረት ለብዙ ዘመናት ይከፋፈላል። ጾመ ነቢያት ኹለት ዘመናት አሉት - ዘመነ አስተምህሮ እና ዘመነ ስብከት። ዘመናቱን፥ የሰንበቶቻቸውን ስያሜ እና ለምን እንደዚያ እንደተሰየሙ በጥቂቱ ለማሳየት ሞክረናል።
“መድኃኒት የኾነ #ልጁን እንሰብካለን፤ ከዓለም በፊት ያለ በኦሪት የተሰበከ፥ የሰማዕታት አክሊል፥ የካህናት ሿሚያቸው፥ የመነኮሳት ተስፋቸው የኾነ መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን፤ #መድኃኒት ልጁን እንሰብካለን።” - ቅዱስ ያሬድ