ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3540

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

¤የኔታ እንዲህ አሉኝ:-

" የራስህ ልብ ጠላት እንዳይሆንብህ አጥብቀህ
ቆልፈው:: ግን ልብህን በባዶው አትቆልፈው:: ፈጣሪህን
ክርስቶስን : ድንግል እመቤትህን : ቅዱሳን ወዳጆችህን
ካስገባህ በሁዋላ ነው እንጂ . . .

. . . ለምን ትለኝ እንደሁ . . . ዓለም ብትናወጽ : ተራራው
ቢነቀል : ማዕበላት ቢማቱ . . . በሰላም ልብህ ከታተመ
ምንም አይመስልህም::

. . . 3ቱ ሰላሞች ደግሞ የክርስቶስ ሰላም (ዮሐ. ፲፬:፳፯) :
የድንግል ማርያም ሰላም (ሉቃ. ፩:፵፩) የቅዱሳን ሰላም (ማቴ. ፲:፲፫)
ናቸው::

. . . ይህ ካልሆነ ግን . . . ልብህን በባዶው ብትቆልፈው
ከልካይ ያጣ ሰባሪ (ሰይጣን) ገብቶ ይመላብሃል:: ወዲህ
ደግሞ 'የክርስቶስ ሰላም ብቻ ይበቃኛል' ብለህ ብትናገር
የቅዱስ መጽሐፍ ተቃዋሚና ግብዝ መሆንህ ነው::
. . . እና ደግሞ የትኛውንም ጠላት ትሸሸዋለህ:: ግን
ጠላትህ ልብህ ከሆነ (ልብህ ውስጥ ካደረ) የትም
ሸሽተህ አታመልጠውምና ልጄ ሆይ! ልብህን ለሚገባቸው
ከፍተህ : ለማይገባቸው ቆልፍ::"

"' አባቶቻችን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን:: '"

ምንጭ :- Dn Yordanos Abebe

✝ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር✝

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ምን እናግዝዎት

✓ CV
✓Assignment
✓Seminar
✓proposal
✓research
✓Business plan
✓practical attachment
✓power point for presentation
Etc..
Contact us via inbox
ስልክ ቁጥር (0799941004) Eyob እና ጓደኞቹ በ አጭር ስአት ውስጥ እናደርሳለን

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሁለተኛው ጥያቄ መልሱ ትክክል ነው

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ድሮም መጽሐፍ ቅዱስን እንደማታውቅ ታሳየናለህ? አፍ መክፈት ብቻ ነው የምታውቀው።

እስኪ እውነት መጽሐፍ ቅዱስን የምታውቅ ከኾነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች "ያድናሉ" ተብሎ ይነገርላቸዋል?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን
ይቻልናል።››
/ቅዱስ አትናቴዎስ/

#መልዕክት

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ቤዛ_ለምንድነው?

ሙሴ ቤዛ ቢባል ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ነው እሱም በጊዜና በቦታ የተገደበ ነው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው
#ሙሴ ቤዛ ቢባል ለሥጋዊ ነው #ለምድራዊ #ለእህል ነው
#ማርምያምም ቤዛ ብትባል እንኳን ከዚህ ያለፈ ለምንም ነው ምክንያቱም ፍጡር ነች ግን አንድም ቦታ ቤዛ አልተባለችም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ

#እኛ እያወራን ያለነው ስለ ሐጥያተኞች የተከፈለ ቤዛነት ነው ለምድራዊ ቅራቅንቦ ወይም ለሥጋዊ የተደረገ መሰዋትነት አይደለም፡፡
ለዘላለም ሕይወት የማይሆን ቤዛነት ለኛ ለምንም አይጠቅመንም

#የሙሴ ቤዛ መባል ከኢየሱስ ቤዛነት ጋር በፍፁም ልነፃፃር አይችልም፡፡
የሙሴ ቤዛነት ከዮርዳኖስ አላለፈም
ሙሴ ቤዛ ስለተባለ ፍጡር ሁሉ ቤዛ ሊባልም አይችልም

#የኢየሱስ_ቤዛነት
"ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
"ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ነው
"ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው
"ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ነው
"ለምግብ ሳይሆን ለኃጢአት ነው የኢየሱስ ቤዛነት፡፡

#ማርያም የሔዋን ምትክ ስለሆነች ቤዛ ነች ይሉኛል
ማርያም የሔዋን ምትክ ናት የሚል አንድም ጥቅስ የለም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከየት አምጥታችሁ ነው ለካስ እናንተ ውዳሴ ማርያም ላይ አለላችሁ😃😃😃

የሔዋን ምትክ ብትባልስ ሔዋን የቱ ጋ ነው ቤዛ ተብላ የተጠቀሰችው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ

እናት ስለሆነች😃😃😃
እናትና ልጅ ስለሆኑ😃😃😃
እምላክን ስለወለደች??😃😃

#ማርያም ይህን ሁሉ አድርጋ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታዲያ እንዴት ቤዛ ተብላ አልተጠቀሰችም???ይገርማል😃😃

#እኛ በ Logic ሳይሆን የምናምነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው አራት ነጥብ፡፡

#መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጫማም ቤዛ ተብሎ ተፅፏል ይላሉ #ቤዛ ትርጉሙ ጥላ ወይም ከለላ ወይም ምትክ ማለት ሲሆን ጫማም ቤዛ የተባለው እግርን ከተለያዩ አደጋዎች ስለምጠብቅ እና ለእግር የምመጣው ድንጋይ ሆነ አደጋ ጫማው ላይ ስለሚያርፍ ነው ጫማ ለእግር ቤዛ የተባለው
#ጫማ ቤዛ ተብሏልና ቤዛችን ጫማ ነው ማለት ነው?

#የኢየሱስ ቤዛነት ልክ እንደጫማው ልያጠፋን የመጣውን በደላችን በራሱ አሳርፎ በኛ ምትክ ሞታችን ሞቶ ነው ያዳነን ቤዛችን ኢየሱስ ነው፡፡

#በደሙ የፈረመልን ቤዛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው

#የዓለም_ቤዛ_ኢየሱስ!!
ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጣ
“እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
— ማቴዎስ20፥28

#የድነት_ቤዛ!!
የዳንነው የፀድቅነው በእርሱ ቤዛነት ነው በፀጋው
“በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።”
— ሮሜ 3፥24

#በደም_የተደረገ_ቤዛነት!!
ደም ሳይፈስ ቤዛነት የለም
“በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።”
— ኤፌሶን 1፥7

#ለኃጢአት_የተከፈለ_ቤዛነት!!
“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”
— ቆላስይስ 1፥13-14

#ዘላለማዊ_ቤዛነት...
የኢየሱስ ቤዛነት ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
“የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።”
— ዕብራውያን 9፥12

በደሙ የፈረመልኝ ቤዛዬ ኢየሱስ ነው
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳናት ቤዛዬ ኢየሱስ

🙏🙏🙏🙏🙏
#ጌታን_መቀበል...
ይህ እውነት የገባችሁ ጌታን መቀበል እፈልጋለሁ በውስጥ መስመር አናግሩን ።

ኢየሱስ ሁለም ይወራል Jesus all time

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እንዲሁ ተመልከቷቸው ፥ ሀፍስ ላይ ከታች የተደረገው ትንሽ መስመር "ቃሉን" ላይ ደግሞ ከላይ ነው የተደረገው። ከዚያ "ቃሉን" ላይ ሌላ ተመሳሳይ ትንሽ መስመር ተጨምሯል። በዐይናችሁ ራሱ ልዩነት እንዳለ መመልከት ትችላላችሁ።

ይሄኛው ለየት የሚያደርገው ትርጉምና ሥርዓት ራሱ ይለውጣል።

እንደሐፍስ ከኾነ አንድ ሰው ካበላችሁ ትእዛዙን ፈጸማችሁ ማለት ነው ፥ እንደ"ቃሉን" ግን ገና ትእዛዙን አልፈጸማችሁም። "ቃሉን" እንደሐፍስ ደሃ (ዐረብኛ፡ ሚስኪኒን) ሳይኾን ድኾች (ዐረብኛ፡ መሰኪን) ነው የሚለው። ስለዚህ በአንድ ብቻ ሳይኾን ብዙ በማብላት ነው ትእዛዙን የምትፈጽሙት ማለት ነው።

ከዚህ ኹሉ ግን መረዳት ያለባችሁ ነገር አንድ ነው ፥ ቁርአን ተአምራዊ በኾነ አጠባበቅ ስለተጠበቀ ምንም ልዩነት የላቸውም። ኹለቱም አንድ ናቸው።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🔻ሰላም Old Group ማለትም የቆየ የቴሌግራም ግሩፕ ያላችሁ በከፍተኝ ዋጋ እየገዛን ነው በነዚ አመተምህረት የተከፈተ ካላችሁ አናግሩን⬇️
✅2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣1️⃣8️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣1️⃣9️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣0️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣1️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣2️⃣💵💵💵


📥📥ማሳሰቢያ ❌‼️
⏬ የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ሆነ ''1000'' ሆነ '10,000'' ዋጋው እኩል ነው
እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ😘😍
😑 clear history ያልተደረገ ግሩፕ ነው የምንፈልገው


⏺ Dm

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥ ፈለግሁት፤ አላገኘሁትም። — #ክፍል_አንድ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት ከበድ የሚለው - አስተሳሰባችን ከተበላሸም በመጥፎ መልኩ የምንተረጉመው - አንድ መጽሐፍ አለ፤ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን። ይኽ መጽሐፍ ከአምስቱ የሰሎሞን የጥበብ መጻሕፍት አንዱ ነው። ሰሎሞን መጽሐፉን ከሌሎቹ መጻሕፍቱ በተለየ መልኩ ክርስቶስን፥ ቤተክርስቲያንንና እመቤታችንን በዘይቤያዊ መንገድ እያቆራኘ ይጽፋል። መጽሐፉን ከማንበባችን በፊት ግን Fr. Zakaria Butros (የCoptic Church ካህን ናቸው፤ በእስልምናው ላይ በመሥራት በስፋት ይታወቃሉ) በመጽሐፉ ዙሪያ ከጻፉት በትንሹ ላስነብባችኹ።

Actually, approaching to the book of Song of the Songs is similar to approaching a flaming tree, flamed with the holy fire that had been seen by prophet Moses, as the lord said to him O Moses, ‛Take your shoes off your feet, for the place where you are standing is a holy ground’ (Acts 7:33) ... So when we approach the book of Song of the Songs, with its sublimity of meanings and symbols, we have to take off the shoes of materialism, and lusty thoughts, and go forward in the holiness of meditation and purity of heart, as: "To the pure, all things are pure; but to those who are defiled and unbelieving, nothing is pure; but both their mind and their conscience are defiled." (Titus 1:15)


መኃልየ መኃልይን ማንበብ ለሙሴ እንደታየው አይነት በቅዱስ እሳት የሚቃጠል ቁጥቋጦን እንደ መቅረብ ያለ ነው፤ ጌታ ለሙሴ እንዲኽ ሲል እንደተናገረው “የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና የእግርህን ጫማ አውልቅ።” (ሐዋ. 7፥33) ... ስለዚኽ እኛም መኃልየ መኃልይን ስናነብ፥ [ያሉትን ጥልቅ ትርጉሞችና ምልክቶችንም ለመረዳት] የmaterialism፥ የዝሙት ሐሳቦችን ጫማ አውልቀን፥ በቅድስና መንፈስ እና በንጹሕ ልብ መኾን አለበት፤ እንዲኽ እንደተጻፈ፦ “ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፥ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሷል።” (ቲቶ 1፥15)

(Fr. Zakaria Butros, The challenges against The book of Song of the Songs And their answers, Introduction.) [materialism ለሚለው የአማርኛ አቻ ቃል አልመጣልኽ አለኝ። ያው ትርጉሙን በትክክል እንዳልተረጎምኹት አውቃለኹ.. እንዲኹ ከምተወው ብዬ ነው።]

እሳቸው እንዳሉት ነው፤ የምጨምረው የለኝም። ግን ስለ መጽሐፉ በጥቂቱ ልንገራችኹ። መጽሐፉን የጥንት አባቶችን ትርጉም ሳትይዙ (እንዴት እንደተረጎሙት ሳትረዱ) ባታነቡት እመክራለኹ፤ እናንብበው ካላችኹ ግን ከላይ እንደ ተጻፈው ልባችንን ንጹሕ አድርገን ወደ መጽሐፉ መቅረብ ይገባናል።

መጽሐፉ በሴትና በወንድ መካከል ያለ ግንኙነትን ተመሥርቶ የተጻፈ ነው፤ ነገር ግን በውስጡ ያዘለው መልእክት እጅግ ጥልቅ ነው - ከጾታዊ ግንኙነቱ በዘለለ ብዙ ነገሮችን በቅኔያዊ መልኩ ይይዛል። በቤተክርስቲያናችን የቀዳም ስዑር ዕለት ከሚነበቡ መጻሕፍት አንዱ ነው፤ “በዘቢብም አጽናኑኝ፥ በእንኮይ አበረታቱኝ፥ በፍቅሩ ተነድፌ ታምሜያለሁና። ግራው ከራሴ በታች ናት፥ ቀኙም ታቅፈኛለች። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ፥ ፍቅርን እንዳታስነሱትና እንዳታነሣሡት፥ በሚዳቋ በምድረ በዳም ዋላ አምላችኋለሁ።” (2፥5-7)

ውዷ ጠፍቷትም ስትፈልገው ነበር። “ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፤ ‛#ነፍሴ_የወደደችውን_አያችሁትን?’ አልኋቸውም። ከእነርሱም ጥቂት እልፍ ብዬ፥ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት።” (3፥3-4 — ውዷ የተባልነው እኛ ነን በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን።)

ስለ እመቤታችንም እንዲኽ ሲል ይናገራል፤ “ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ፥ ከአማና ራስ ከሳኔርና ከኤርሞን ራስ፥ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች።” (4፥8) ስለ ክርስቶስም “ውዴ #ነጭና_ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው። ... ” እያለ በትንቢት መነጽር እያየ ይናገራል። (5፥10 — ይኼን ምዕራፍ ሙሉውን በቀጣዮቹ ክፍሎች ስለምናየው ስለ ክርስቶስ የሚናገረውንም በዚያው አብረን እናየዋለን። የተጠቀምኳቸውን መጻሕፍት እንዲኹም የአበውን የዚኽ መጽሐፍ የትርጉም ሥራዎች አስቀምጥላችዃለኹ።)

[ክፍል ኹለት ይቀጥላል...]

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ከስንክሳር_ገጾች አንድ ቅዱስ - ግንቦት 5

ቅዱስ ኤርምያስ


ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ከዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በስድስት መቶ አካባቢ የነበረ ነቢይ ነው። አባቱ ኬልቅዩ ይባላል። ከካህናተ እስራኤል አንዱ ነበር። እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕፃንነቱ ነበር። "ከእናትህ ማኅጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ፥ ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል። (ኤር. 1፥5) ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም። ከሰባ ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል።

ዘመኑ ዘመነ-ኃጢአት (ዘመነ ዐጸባ) ነበር። እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም። ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት። እግዚአብሔር ግን በኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው። የተሰበከላቸውን የንስሐ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር የሚባል የአሕዛብ ንጉሥ መጥቶ አሥሩን ነገድ ማርኮ በ722 አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው። በኋላ ደግሞ በኃይለኝነቱ የታወቀው የባቢሎን ንጉሥ ይማርካቸው ዘንድ ወደ ሁለቱ ነገድ ኢየሩሳሌም ደረሰ። ኤርምያስ ወደ ከተማዋ ዳር ወጥቶ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አለቀሰ።

ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው። ነቢዩ የተናገረው አይቀርምና ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ፥ እኩሉንም ማርኮ፥ ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ፥ የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጐ በ586 ባቢሎን አወረዳቸው። ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብጽ ወረዱ እንጂ አልተማረከም።

በዚያም ተአምራትን አድርጐ አራዊትን አጥፍቷቸዋል። ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት፥ ነቢይ፥ መምህርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወረደ። በዚያም ትንቢትን እየተናገረ፥ ሕዝቡን ከሰባ ዓመታት በኋላ ወደ ሐገራቸው እንደሚመለሱ እያስተማራቸው በባቢሎን ቆይቷል። ያለ በደሉም በመከራቸው ተካፋይ ሆኗል። ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው።

በዚህ ተበሳጭተው ሊወግሩት ሲሉ ጸጋ በዝቶለት፥ ምሥጢርም ሰፍቶለት ስለ ነገረ ሥጋዌ (ስለ ክርስቶስ የማዳን ሥራ) አምልቶና አጉልቶ ትንቢት ተናገረ። አንዴ ልቡናቸው ታውሮ ኤርምያስ ነው ብለው ድንጋዩን በድንጋይ ሲወግሩት ውለዋል። ዘግይቶ ግን ኤርምያስ ራሱን ገለጠላቸው። ስለ እነርሱ ሲል ሰባ ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት። ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤርምያስ ሃምሳ ሁለት ምዕራፎች ያሉት ሐረገ ትንቢት ተናግሯል/ ጽፏል።

ግንቦት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ (ከታላላቆቹ ነቢያት አንዱ)
ወርኃዊ በዓላት

1. ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2. ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
3. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ
5. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።››
/ቅዱስ እንጦስ/

#መልዕክት

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የቁርአን ግጭት #1

በፍጥረት ሰማይ ይቀድማል ወይስ ምድር?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

“ጥበብ ቤትዋን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።”
— ምሳሌ 9፥1

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#አንድ መነኩሴ ወደ ገዳሙ አበ ምኔት ቀርቦ በምሬት እንዲህ አለ :-
"አባቴ በዚህ ገዳም ምንም ጸጋ ምንም ትሩፋት የሌለኝ መነኩሴ እኔ ብቻ ነኝ:: አባ እገሌን እዩት እንደ እርሱ የዋህ የለም! አባ እገሌን እዩአቸው እንደርሳቸው ታጋሽ ማን አለ? አባ እገሌን እዩአቸው ለሁሉ ፍቅር አላቸው!
እኔ ግን ምንም የለኝም አልረባም አባቴ እባክዎ ይጸልዩልኝ የእኔ ጸጋ የእኔ ፍሬ ምንድር ነው?" አለ እያለቀሰ::
አበምኔቱም አይዞህ ጸልይ ብለው አሰናበቱት::
እሱ ከወጣ በኁዋላ ግን አብረዋቸው ላሉት መነኮሳት እንዲህ አሉ :-
"ይህ መነኩሴ በዚህ ገዳም ካሉ ሁሉ የሚበልጥ ጸጋ ተሠጥቶታል:: የወንድሞቹ ኃጢአት አይታየውም
ጽድቃቸውን ግን በትሕትና ሲቆጥር ይውላል:: ከዚህ በላይ ምን ጸጋ አለ? ዝም ያልኩት ይህንን ብነግረው ክብሩን አሳንስበታለሁ ብዬ ነው" አሉ::
"ነፍሳችሁን ተመልከቱ የወንድማችሁንም ኃጢአት አትመልከቱ እግዚአብሔር ያያል"

#ቅዳሴ እግዚእ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#እንዲ እናምናለን አንታመናለን አብ ወልድ መንፋስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብለን

#እንኲን ለወርሐዊው የአብርሀሙ ሥላሴ በዓል አደረሳቹ አደረሰን

📖📖📖📖📖📖📖📖📖.

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Mekdes Lije:
አባ ጥያቄ አለኝ

1,የዮሀንስ ጥምቀት ከምድር ናት ከሰማይ

2,እመቤታችን መቼ ተጠመቀች

    መልስ
1
እመቤታችን ጥምቀት አያስፈልጋትም ምክንያቱም እርሷን ኀጢአት የለባትም መጠመቅ የሚገባው የዘር ኀጢአት ያለበት ነው እርሷ ደግሞ ከኀጢአት ነጻ ተደርጋ የተፈጠረች ናት

2
የዮሐንስ ጥምቀት የንስሐ ጥምቀት ነውና ንስሐ የሚገባ ከኀጢአት የሚነጻበት ታላቁ የእግዚአብሔር ስጦታ ሲሆን የሚያሰጠው ግን የሥጋ ሥርየትን እንጂ የነፍስን አያሰጥም ነበር

ስለዚህ ምድራዊ ክብርን የሥጋ ሥርየትን ብቻ ነው የሚሰጠው  ልጅነትን የሚያሰጥ ሰማያዊ አይደለም

ማቴዎስ 3÷1-2: በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።  👇

መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡ ማለት መንግስተ ሰማያት በሰማይ ያለች እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያዘጋጃት ታላቅ ስጦታ ነች ስለዚህ ይህ የንስሐ ጥምቀት ነው በእርሱ ተጠመቁ ከሥጋ ኀጢአታችሁ ነጽታችሁ ጠብቁ

ማቴዎስ 3÷11
እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤

ቀሲስ ዓለሙ ሲሳይ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ከቅዳሴ ጋር በተያያዘ፣ የልጅነት ትዝታዬ ከሆኑት መካከል፣ ከጓደኞቼ ጋር ተሰብስበን  ወደ ደብራችን ለቅዳሴ ስንሄድ ደወል ከሰማን “አሐዱ” ሳይባል ቤተ መቅደስ ውስጥ ለመግባት የምንሮጠው ሩጫ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስላድግን ነው መሰለኝ፣ ለቅዳሴ የተለየ ፍቅር አለኝ፡፡ ሠራዒው ካህን መጽሐፈ ቅዳሴው በሚያዝዘው መሠረት ሁለቱን “እጆቹን ዘርግቶ፣ ቀጥ ብሎ በመቆምና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ”:-

አሐዱ አብ ቅዱስ (አንዱ አብ ቅዱስ ነው)፤
አሐዱ ወልድ ቅዱስ (አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው)፤
አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ (አንዱ [መንፈስም] ቅዱስ ነው)፤


እያለ ሲያዜም (በተለይ ድምጻዊ ከሆነ) እጅግ የሚመስጥና ሕሊናዬን ሰማይ አድርሶ የሚመልስ ስሜት ይሰማኛል፡፡ “አሐዱ” ሳይባል ቤተ መቅደስ ውስጥ ለመግባት ከጓደኞቼ ጋር እንሮጥ የነበረውን የልጅነት ሩጫ ሳስታውስ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ እኛ እየሮጥን ካህኑ በድምጽ ማጉያ “አሐዱ” ሲል ከሰማን፣ ዜማውን እስኪጨርስ ድረስ ባለንበት ቦታ ቀጥ ብለን እንቆማለን፡፡ ለምን እንደምንቆም የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራኖቻችንን ስንጠይቅ "ካህኑ አሐዱ በሚልበት ሰዓት ኅብስቱና ወይኑ ወደ ጌታ ሥጋና ደም ስለሚለወጥ ነው” የሚል መልስ እንደሰጡን አስታውሳለሁ፡፡ ቀሲስ ፍቅረ መለኮት ስለ ቅዳሴ ሲያስተምሩን፣ ይህ ጥያቄ ተነስቶ የሰማሁትን መልስ ስነግራቸው የሚከተለውን አስደናቂ ማብራሪያ ሰጡኝ፡-

"አይ ፍቅርተ ኢየሱስ! ምክንያቱ ይህ አይደለም፤ ኅብስቱና ወይኑ የጌታ ሥጋና ደም ወደ መሆን የሚለወጡት በቅዳሴው ሦስተኛ ከፍል (የአማንያን ቅዳሴ/አኰቴተ ቊርባን) ካህኑ ወደ እግዚአብሔር አብ መንፈስ ቅዱስን በኅብስቱና በወይኑ ላይ (እንዲሁም በሁላችን ላይ) እንዲልክ በሚጸልይበት ሰዓት ነው እንጂ አሐዱ ሲባል አይደለም፡፡ እንዲያውም ግሪኮች ይህን ጸሎት Epiklësis (ጽዋዔ መንፈስ ቅዱስ) በማለት ይጠሩታል፡፡ ካህኑ አሐዱ ሲል ቆመን የምንሰማው፣ የእምነት ምስክርነት እየሰጠ ስለሆነ ያን ለማዳመጥ ነው፡፡ ሲጨርስም የእርሱ እምነት እምነታቸው ነውና ምእመናን (ሕዝቡ) ‘በአማን አብ ቅዱስ (አብ በእውነት ቅዱስ ነው)፣ በአማን ወልድ ቅዱስ፣ በአማን ውእቱ መንፈስ ቅዱስ' በማለት ይመልሱለታል፡፡"

ቅዳሴ
በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ
ገፅ 26-27

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በገና፣ ክራር እና መሰንቆ መግዛት የምትፈልጉ inbox አድርጉልኝ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ቤዛ_ለምንድነው?

ሙሴ ቤዛ ቢባል ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ነው እሱም በጊዜና በቦታ የተገደበ ነው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው
#ሙሴ ቤዛ ቢባል ለሥጋዊ ነው #ለምድራዊ #ለእህል ነው
#ማርምያምም ቤዛ ብትባል እንኳን ከዚህ ያለፈ ለምንም ነው ምክንያቱም ፍጡር ነች ግን አንድም ቦታ ቤዛ አልተባለችም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ

#እኛ እያወራን ያለነው ስለ ሐጥያተኞች የተከፈለ ቤዛነት ነው ለምድራዊ ቅራቅንቦ ወይም ለሥጋዊ የተደረገ መሰዋትነት አይደለም፡፡
ለዘላለም ሕይወት የማይሆን ቤዛነት ለኛ ለምንም አይጠቅመንም

#የሙሴ ቤዛ መባል ከኢየሱስ ቤዛነት ጋር በፍፁም ልነፃፃር አይችልም፡፡
የሙሴ ቤዛነት ከዮርዳኖስ አላለፈም
ሙሴ ቤዛ ስለተባለ ፍጡር ሁሉ ቤዛ ሊባልም አይችልም

#የኢየሱስ_ቤዛነት
"ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
"ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ነው
"ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው
"ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ነው
"ለምግብ ሳይሆን ለኃጢአት ነው የኢየሱስ ቤዛነት፡፡

#ማርያም የሔዋን ምትክ ስለሆነች ቤዛ ነች ይሉኛል
ማርያም የሔዋን ምትክ ናት የሚል አንድም ጥቅስ የለም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከየት አምጥታችሁ ነው ለካስ እናንተ ውዳሴ ማርያም ላይ አለላችሁ😃😃😃

የሔዋን ምትክ ብትባልስ ሔዋን የቱ ጋ ነው ቤዛ ተብላ የተጠቀሰችው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ

እናት ስለሆነች😃😃😃
እናትና ልጅ ስለሆኑ😃😃😃
እምላክን ስለወለደች??😃😃

#ማርያም ይህን ሁሉ አድርጋ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታዲያ እንዴት ቤዛ ተብላ አልተጠቀሰችም???ይገርማል😃😃

#እኛ በ Logic ሳይሆን የምናምነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው አራት ነጥብ፡፡

#መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጫማም ቤዛ ተብሎ ተፅፏል ይላሉ #ቤዛ ትርጉሙ ጥላ ወይም ከለላ ወይም ምትክ ማለት ሲሆን ጫማም ቤዛ የተባለው እግርን ከተለያዩ አደጋዎች ስለምጠብቅ እና ለእግር የምመጣው ድንጋይ ሆነ አደጋ ጫማው ላይ ስለሚያርፍ ነው ጫማ ለእግር ቤዛ የተባለው
#ጫማ ቤዛ ተብሏልና ቤዛችን ጫማ ነው ማለት ነው?

#የኢየሱስ ቤዛነት ልክ እንደጫማው ልያጠፋን የመጣውን በደላችን በራሱ አሳርፎ በኛ ምትክ ሞታችን ሞቶ ነው ያዳነን ቤዛችን ኢየሱስ ነው፡፡

#በደሙ የፈረመልን ቤዛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው

#የዓለም_ቤዛ_ኢየሱስ!!
ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጣ
“እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
  — ማቴዎስ20፥28

#የድነት_ቤዛ!!
የዳንነው የፀድቅነው በእርሱ ቤዛነት ነው በፀጋው
“በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።”
  — ሮሜ 3፥24

#በደም_የተደረገ_ቤዛነት!!
ደም ሳይፈስ ቤዛነት የለም
“በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።”
  — ኤፌሶን 1፥7

#ለኃጢአት_የተከፈለ_ቤዛነት!!
“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”
  — ቆላስይስ 1፥13-14

#ዘላለማዊ_ቤዛነት...
የኢየሱስ ቤዛነት ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
“የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።”
  — ዕብራውያን 9፥12

በደሙ የፈረመልኝ ቤዛዬ ኢየሱስ ነው
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳናት ቤዛዬ ኢየሱስ

🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ቤዛ_ለምንድነው?

ሙሴ ቤዛ ቢባል ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ነው እሱም በጊዜና በቦታ የተገደበ ነው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው
#ሙሴ ቤዛ ቢባል ለሥጋዊ ነው #ለምድራዊ #ለእህል ነው
#ማርምያምም ቤዛ ብትባል እንኳን ከዚህ ያለፈ ለምንም ነው ምክንያቱም ፍጡር ነች ግን አንድም ቦታ ቤዛ አልተባለችም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ

#እኛ እያወራን ያለነው ስለ ሐጥያተኞች የተከፈለ ቤዛነት ነው ለምድራዊ ቅራቅንቦ ወይም ለሥጋዊ የተደረገ መሰዋትነት አይደለም፡፡
ለዘላለም ሕይወት የማይሆን ቤዛነት ለኛ ለምንም አይጠቅመንም

#የሙሴ ቤዛ መባል ከኢየሱስ ቤዛነት ጋር በፍፁም ልነፃፃር አይችልም፡፡
የሙሴ ቤዛነት ከዮርዳኖስ አላለፈም
ሙሴ ቤዛ ስለተባለ ፍጡር ሁሉ ቤዛ ሊባልም አይችልም

#የኢየሱስ_ቤዛነት
"ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
"ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ነው
"ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው
"ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ነው
"ለምግብ ሳይሆን ለኃጢአት ነው የኢየሱስ ቤዛነት፡፡

#ማርያም የሔዋን ምትክ ስለሆነች ቤዛ ነች ይሉኛል
ማርያም የሔዋን ምትክ ናት የሚል አንድም ጥቅስ የለም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከየት አምጥታችሁ ነው ለካስ እናንተ ውዳሴ ማርያም ላይ አለላችሁ😃😃😃

የሔዋን ምትክ ብትባልስ ሔዋን የቱ ጋ ነው ቤዛ ተብላ የተጠቀሰችው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ

እናት ስለሆነች😃😃😃
እናትና ልጅ ስለሆኑ😃😃😃
እምላክን ስለወለደች??😃😃

#ማርያም ይህን ሁሉ አድርጋ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታዲያ እንዴት ቤዛ ተብላ አልተጠቀሰችም???ይገርማል😃😃

#እኛ በ Logic ሳይሆን የምናምነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው አራት ነጥብ፡፡

#መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጫማም ቤዛ ተብሎ ተፅፏል ይላሉ #ቤዛ ትርጉሙ ጥላ ወይም ከለላ ወይም ምትክ ማለት ሲሆን ጫማም ቤዛ የተባለው እግርን ከተለያዩ አደጋዎች ስለምጠብቅ እና ለእግር የምመጣው ድንጋይ ሆነ አደጋ ጫማው ላይ ስለሚያርፍ ነው ጫማ ለእግር ቤዛ የተባለው
#ጫማ ቤዛ ተብሏልና ቤዛችን ጫማ ነው ማለት ነው?

#የኢየሱስ ቤዛነት ልክ እንደጫማው ልያጠፋን የመጣውን በደላችን በራሱ አሳርፎ በኛ ምትክ ሞታችን ሞቶ ነው ያዳነን ቤዛችን ኢየሱስ ነው፡፡

#በደሙ የፈረመልን ቤዛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው

#የዓለም_ቤዛ_ኢየሱስ!!
ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጣ
“እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
— ማቴዎስ20፥28

#የድነት_ቤዛ!!
የዳንነው የፀድቅነው በእርሱ ቤዛነት ነው በፀጋው
“በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።”
— ሮሜ 3፥24

#በደም_የተደረገ_ቤዛነት!!
ደም ሳይፈስ ቤዛነት የለም
“በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።”
— ኤፌሶን 1፥7

#ለኃጢአት_የተከፈለ_ቤዛነት!!
“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”
— ቆላስይስ 1፥13-14

#ዘላለማዊ_ቤዛነት...
የኢየሱስ ቤዛነት ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
“የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።”
— ዕብራውያን 9፥12

በደሙ የፈረመልኝ ቤዛዬ ኢየሱስ ነው
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳናት ቤዛዬ ኢየሱስ

🙏🙏🙏🙏🙏
#ጌታን_መቀበል...
ይህ እውነት የገባችሁ ጌታን መቀበል እፈልጋለሁ በውስጥ መስመር አናግሩን ።

ኢየሱስ ሁለም ይወራል Jesus all time

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

አልገባኝም ማነህ ወንድሜ በስምሙ (በስሙም) ለምያምኑት አማላጅ ሆነሃል። ስሙን ምን ብለው ላመኑት ነው አማላጅ የሆነው?።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በገና፣ ክራር እና መሰንቆ መግዛት የምትፈልጉ inbox አድርጉልኝ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

@mary21God

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ንብ መቼ እንደምትሞት አይታችሁ ታውቃላችሁ?

የምትሞተው ሌላውን ስትናደፍ ነው፡፡
እግዚአብሔር በዚህች ፍጥረት በወንድሞቻችን ላይ ልንቆጣ እንዳይገባ ያስተምረናል፡፡
እኛው የምንቆጣ (የምንናደፍ) ከሆነ ግን ቀድመን የምንሞተው እኛው ነን፡፡
ስንቈጣቸው የጎዳናቸው ይመስለን ይሆናል፤ ነገር ግን እንደዚያች ንብ ተጐጂዎቹ እኛው ነን፡፡

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እባካችሁ መልሱልኝ በሙስሊም የታረደ ስጋ ማንበላበት ምክንያት የመፅሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ስለተጠየኩ ነዉ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

SOURCE: Jalaludin Suyuti, Al-Itqan fi Ulum al-Qur’an, Nasikh and Mansukh, p. 12

እንደነገርኳችሁ ብዙ የሚመጡ ጥሩ ጥሩ ታሪኮች ይኖራሉ ፥ እነዚህን ካጠናችኋቸው በኋላ "በየትኛው ዓለም ውስጥ እየኖሩ ነው ቁርአን ተጠበቀ የሚሉን?" ማለት ትጀምራላችሁ።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

1-እምነ በሐ(የዘወትር)

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ከስንክሳር_ገጾች አንድ ቅዱስ - ግንቦት 4

አቡነ መልከ ጼዴቅ


አቡነ መልከ ጼዴቅ በሸዋ ነገሥታት ዘመን የነበሩ፥ የንጉሱ ዓምደ ጽዮን የቅርብ ዘመድ ነበሩ። የጻድቁ ወላጆች ፍሬ ጽዮንና ዐመተ ማርያም ይባላሉ። አቡነ መልከ ጼዴቅ ገና በሕጻንነታቸው ሥርዓተ መንግስትን አጥንተዋል። በኋላ ከመምህር ዘንድ ገብተው ብሉይ ከሐዲስ ተምረው ሲያጠናቅቁ ይህንን ዓለም ንቀው ከቤተ መንግስቱ አካባቢ ጠፍተው ወደ አቡነ አሮን መንክራዊ ዘንድ ሔደው መንኩሰዋል።

ነገሩ በቤተ መንግስት አካባቢ ሲሰማ ወላጆች አለቀሱ። አቡነ አሮንም ተከሰው ነበር። ነገሩ ግን ከእግዚአብሔር ነበርና አቡነ መልከ ጼዴቅን መልዐክ እየመራ አምጥቶ አሁን ገዳማቸው ያለበት ሸዋ (ሚዳ) አደረሳቸው። በዚያ ትንሽ በዓት ሰርተው ለዘመናት ተጋድለዋል። ዋሻዋም ደብረ መድኃኒት ትባላለች። ጻድቁ ከጾምና ጸሎታቸው በተረፈ ዓርብ ዓርብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሕማማት በማሰብ ጀርባቸውን 300 ጊዜ ይገርፉ፥ ደቀ መዛሙርቱንም ግረፉኝ ይሉ ነበር። አንድ ጊዜም እጃቸውንና እግራቸውን በትልልቅ ችንካሮች ቸንክረውት ደማቸው ሲፈስ ተገኝቷል።

በመጨረሻ አቡነ መልከ ጼዴቅ ጌታን ኢትዮጵያውያንን ማርልኝ አሉት። ጌታችንም መለሰ፦ “በስምህ ያመኑትን፥ በቃል ኪዳንህ የተማጸኑትን፥ ገዳምህን የተሳለሙትን እምርልሃለሁ።” ጻድቁም ብዙ ተአምራትን ሰርተው በዚሕች ቀን አርፈዋል። አቡነ አምሃ ኢየሱስም በክብር ገንዘው በበዓታቸው ውስጥ ቀብሯቸዋል። አምላካችን እግዚአብሔር ከጻድቁ ዋጋና በረከት አይለየን።

ግንቦት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. አቡነ መልከ ጼዴቅ ካህን (ኢትዮጵያዊ ጻድቅ)
2. አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት
3. ቅዱሳን ሶሲማና ኖዳ ሰማዕታት (የታላቁ ፊቅጦር ተከታዮች የነበሩ)
ወርኃዊ በዓላት

1. ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ወንጌላዊው)
2. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ከሽማግሌዎቹም፡አንዱ አታልቅስ እንሆ ከይሁዳ ነገድ የኾነው አንበሳ ርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቷል አለኝ።

ራዕይ 5፥5

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.

Читать полностью…
Subscribe to a channel