ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo
ዕንባቆም 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
¹⁸ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።
@mary21God
የተፈጠርንለትን አላማ ጠንቅቆ ማወቅ ብዙ ሰዎች ደስተኛ ያደርገናል ሲሉ ይሰማሉ።
እውነታቸውን ነው ደስተኛ ያደርጋል.... ግን...የተፈጠሩበትን አላማ ተሰውሮባቸው ለማግኘት የማይቆፍሩት የማይወጡ ዳገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ከዚ ሁሉ አድካሚ የህይወት ጉዞ በኋላ ከፊሎቹ ሳያገኙት በሀዘን ይመለሳሉ ግማሾቹ ደግሞ የነፍስያችንን ጥሪ አገኘናት ልባችን አረፈች ይላሉ።
እውን ግን የተፈጠርንለት አላማ ምንድነው የነፍሳችንስ ጥሪ???
እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው እንዲያመሰግነው ነው!!!!! የነፍሳችን ጥሪም እሱን ለማመስገን የልባችን ማረፍያዋም እሱ ብቻ ነው።
አለም ላይ እንደሚያመሰግን ያለ ደስተኛ ሰው የለም!!!
ንጉስ ዳዊት ግሩም እና ድንቅ አድርገህ ፈጥረሀኛል ብሎ ለአምላኩ ምስጋናን የሰዋ እረኛ ሳለ ነበር።ያከበረው እግዚአብሔር ጊዜ ጠብቆ አክብሮት አይተናል።
እኛም ዛሬ የህይወታችን ትላልቅ ችግሮች በማማረር አይፈቱም ብቸኝነታችን ብቸኛ ነን ስላልን ትቶን አይሄድም።
በትክክል ለተፈጠርንለት አላማ እንኑር እናመስግነው ያኔ የህይወታችንን ማእበል በቃሉ ይገስፅልናል ። ነፍስያችን ጥሪዋን ታገኛለች።
#መልዕክት ✍
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
💵የለምን ክፍያ በቤታቹ ሆናቹ የምተሰሩትን በጣም አትራፊ የ Online ስራ ላስተዋውቃችሁ💵 👇👇
Smart phone እና Internet ያላችሁ ከኛ ጋር መስራት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ
@kali19K
☎️0965282217
07991074 51
በተለይ እቤት የምትዉሉ እህቶች በጣም ታተርፉበታላቹ 🙌
ለውጥ ለማየት ሳምንት በቂ ነው
ሰላም ውድ ኦርቶዶክሳውያን የክርስቶስ ፀጋ ከሁላችን ጋር ይሁን
ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ የስርዓተ ቅዳሴ የዜማ ትምሕርቱ የሚለቀቅ ሲሆን
፩-ትምሕርቱ የሚለቀቀው በሁለት ዓይነት ሲሆን የመጀመሪያው የዜማውን ድምፅ ከንባቡ ምስል ጋር አንድ ላይ በ video ሲሆን(ይኸኛው ግን ምናልባት package ገዝታቹህ የምትከታተሉ ካላቹህ MB መጠን ሊበዛባቹህ ይችላል) ስለዚህ ሁለተኛው የዜማው ድምፅ ብቻውን ከንባቡ ምስል ጋር ይለቀቃል።
፪-ሙሉውን የቅዳሴ ስርዓት(ማለትም ምስባኩን፣የወንጌል ንባቡን ሁሉንም) ከላይ በተያያዙት PDF files የሚያገኙ ሲሆን የዜማ ትምህርቱ ግን ሙሉው እዚህ ይለቀቃል።
ይ.ሕ(ሕዝብ)- የሚለው ይበል ሕዝብ ማለት ሲሆን እኛ የምናጠናውም ይሄንን ነው።
ይ.ካ እና ይ.ዲ(ካህን እና ዲያቆን)- የሚሉት የካህናት ስለሆኑ የምንዘላቸው በመሆኑ በማስተዋል እናጥና።
ሰላም የተዋህዶ ቤተሰቦች የቅድስ ድንግል ማርያም ልጆች እንደምን ናቹ እኔ እግዚያብሄር የተመሰገነ ይሁን ደህና ነኝ ዛሬ ቢጨንቀኝ አማራጭ ሳጣ ላስቸግራቹ እርዳታቹን ፍለጋ ከፊታቹ ቆሚያለዉ በዚህ መልክ ባይሆን ደስ ባለኝ ግን ምን አባቴ ላድርግ አማራጭ ሳጣ በዚህ መልክ እርዳታቹን ለማግኘት መጥቻለዉ እናቴ አልጋ ለይ ከዋለች ድፍን አምስት አመት አለፏታል በነዚህ የጭንቅ ግዚያቶች በተለያየ ሆስፒታል ከአምስት ግዜ በላይ ሰርጀሪ ተሰርታለች ያለኝን ነገር ሁሉ በወጣትነቴ የቋጠርኳትን ሁሉ በእክምና ጨርሼ አሁንም ሰርጀሪ መሰራት አለባት ሲሉኝ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ወደ ቤት ይዣት ተመልሼ ምን እንደማደር ግራ ገብቶኝ በጭንቀቴ ቁጭ ብያለዉ ግን አንድ ነገር ሀሳብ መቶልኝ ነበር ብዙም ሰዉ ሲለኝ ስለነበር ስዉሯ ማርያም ፀብል ይዣት ለሜሄድ አስቤ ነበር ግን ያለሁበት ቦታ ትንሽ ስለሚርቅ ሌላዉን ነገር እግዚያብሄር ያቃል ግን የትንራንስፓርቱን እንኳን ካገዛቹኝ ብዬ እናንተን የሀገሬን ልጆች እጅ ማየት ግድ ሆኖብኘል የእዉነት ጭንቄ የገባቹ እና የእናትን ነገር ምታቁ ሁሉ ለነብስ ይሆናቹሀል ስለ እመብርሀን አግዙኝ ካለ እናቴ የእዉነት ማንም የለኝም እንዲ ነዉ ብዬ ማዋየዉ ዘመድ እንኳን የለኝም ተስፋዬ እናቴ ስዉሯ ማርያም ነች እሷን ልጠጋ እና አዛኝቱ አዝናልኝ እናቴን ትማርልኝ አነሰ በዛ ሳትሉ ለትራንስፓር ሚሆነን አግዙን እግዚያብሄር በማትችሉት አይፈትናቹ ማንም የምቶዱት ሰዉ አይታመምባቹ አመሰግናለዉ 1000409905246 ኢሄ የንግድ ባንክ አካዉንቴ ነዉ ወገኖቼ እባካቹ በቻላቹት ሁሉ እርዳታቹን እንሻለን በፀሎትም🙏🙏🙏 0974460145 ኢሄ ስልክ ቁጥሬ🙏🙏
Читать полностью…የመዳናችን መንገድ ፤ ሕይወትን የስጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።
===============
ኢየሱስ ኢየሱስ የምንለው በምክኒያት ነው ፡-
1, እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ስለሆነ ። ሐዋ 4፥12 ""መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና ።
2, ጉልበት ሁሉ የሚበረከክለት ስም ስለሆነ ።ፊሊ2፥10
""ይህም በስማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ።
3, የመግቢያው በር ስለሆነ ።ዮሐ10፥9
"በሩ እኔ ነኝ ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል ይገባልም ይወጣልም መስማሪያም ይገኛል ።
4, የአለም ቤዛ ስለሆነ ። ማር 10፥45 ኤፍ 1፥7 1ጢሞ2፥5-6 ዕብ 9፥12
5, ሕይወት ስለሆነ ።1ዮሐ 5፥12 "ልጁ ያለው ሕይወት አለው ፤የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም ።
6, ትንሳኤና ሕይወት ስለሆነ ።ዮሐ 11፥25
"ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ ።
7, የዘላለም ሕይወት ስለሆነ ።ዮሐ 3፥36
"በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው ።
8, የአለም ኃጢአት የሚያስወግድ ስለሆነ ። ዮሐ 1፥9 ""የአለም ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ።
9, መልካም እረኛ ስለሆነ ።ዮሐ10፥14
""መልካም እረኛ እኔ ነኝ ።
10, የአለም ብርሃን ስለሆነ ። ዮሐ8፥12
""እኔ የአለም ብርሃን ነኝ ።
ይህ ነው እውነቱ በእግዚአብሔር ቃል እንመራ ። የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል ፡-እምነት በመስማት ነው መስማትም የእግዚአብሔር ቃል ነው ። ሮሜ 10፥17 ስለሆነም የእምነት መስረቱ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው ። እኛም በዚህ እውነት መቆም መኖር ያስፈልጋል ። ሳጠቃልልም ""ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመስክር እግዚአብሔር ከሙታን እንዳነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ ።
ሮሜ 10፥9
💵የለምን ክፍያ በቤታቹ ሆናቹ የምተሰሩትን በጣም አትራፊ የ Online ስራ ላስተዋውቃችሁ💵 👇👇
Smart phone እና Internet ያላችሁ ከኛ ጋር መስራት የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ
@kali19K
☎️0965282217
07991074 51
በተለይ እቤት የምትዉሉ እህቶች በጣም ታተርፉበታላቹ 🙌
ለውጥ ለማየት ሳምንት በቂ ነው
📌📌📌
❤️🩹መዝሙረ ዳዊት ልብን የሚያፅናኑ ጥቅሶች❤️🩹
“አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።”
➕መዝሙር 27፥8
“እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።”
➕መዝሙር 28፥7
"መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።"
➕መዝሙር 37፥5
"ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፤ ለዘላለምም ትኖራለህ።"
➕መዝሙር 37፥27
"አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።"
➕መዝሙር 51፥10
"እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።"
➕መዝሙር 34፥18
"መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።"
➕መዝሙር 62፥7
“አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።”
➕መዝሙር 39፥7
"ዓመፃን ተስፋ አታድርጉ፥ ቅሚያንም አትተማመኑት፤ ባለጠግነት ቢበዛ ልባችሁ አይኵራ።"
➕መዝሙር 62፥10
“ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።”
➕መዝሙር 42፥5
📙 ይድረስ ለውዷ ፊያሜታ ጊላይ... እንደምን አለሽልኝ..? እኔ በልጅነቴ ፍቅር እስከ መቃብር ነው ሲሉ ሰምቼ ዙቤይዳን እስከማገኝ ድረስ ኦሮማይን የሙጥኝ ብየ ነበር የቆየሁት። ሳድግ የፍርድ ቀን ዘመቻ ላይ ሆኜ በትኩሳት እየተንቀጠቀጥኩኝ... መልህቅ እንደሌለው መርከብ እየተናወጥኩኝ... ሌቱም አይነጋልኝ ስል ተገኘሁ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአመጓ እስከ ዝጎራ እያካለልኩ መርበብትና ሰበዝን ይዤ በጠበኛ እውነቶች ስም አንፈርስም አንታደስም የሚል መፈክር ማሰማት ጀመርኩኝ። አይይይ... ይሄ ነገሬ እንኳን ለኔም አልገባኝም... ብቻ ሌላ ሰው ላይ ስፎክር እንደ ኢያሪኮ ግንብ በቅፅበት ለመፍረስ እንዳይሆንብኝ ሁሉቱ ጊዮርጊሶች ይጠብቁኝ።
📙 ይገርምሻል አንዳንድ ቀንና ህይወት ርዕስ የለውም ይባላል። ብዙ ሰው የሚስማማበት ሃሳብ ግን ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ ልክ እንደ መንደሪን ጣፋጭ መድሃኒት መሆኑን ነው። ከዕለታት ግማሽ ቀን ቤተልሄምን ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ እያልኳት ሀገር ያጣ ሞት ድንገት በጠቢባን መንገድ በኩል ሲመጣብኝ ምንሽሮን ዋስ ጠርቼ አመለጥኩት። በሰሞነ ህማማት ደግሞ ገላና ገላዬ ሲታመሙብኝ ትዝታሽን ለኔ ትዝታየን ለአንቺ እያሰብኩኝ አሳለፍኩ።
📙 አንቺዬ ደግሞ ያልተነገረ ተረክና ያልተፃፈ ኑረት ታሪክ አይሆንምና አንድ ቀን ሜሎሪናን ህልምሽን አጫውችኝ ብያት ስታወጋኝ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮችን አስታወሰችኝ። እግረ መንገድ ይሁን እንጅ ዶክተር አሸብር የታካሚውንና የልብ ጠጋኙን ማስታወሻ እያገላበጠ ፊት ለፊቱ አሳንቲ የሰማይ ላይ ስዕል መስላ እንደተሰየመች በምናቤ ውል አለችብኝ። በመጨረሻም ከዚህ በላይ የነገርኩሽን ታሪክ ጨምሮ የአና ማስታወሻ፣ ዮቶርና ፖፒዮ የተሰኙትን ዜማዎች ከወንድም ሐሽማል ጋር ጋብዠሻለሁ።
.
.
ያንቺው ጠኃ ባላደራ ...!
የመፅሃፍት ስምና ገፀባህርያትን በመጠቀም የተፃፈ ታሪካዊ ደብዳቤ::
✍️ መሳይ አርቀው
ፊያሜታ ተናፍቀሻል🥰
ስንቶችን አንብበዋል?😊
a.a wust huneh edmeh ke 18 amet eske 23 amet kehonk yerasihn business lemesirat ready kehonk Inbox lay ene alehu belegn mnm adrgeh hiwothn lemekeyer ready kehonk
Читать полностью…ለእስልምና መልሰ መስጠት አፈልጋለዉ ተጠይቄነዉ 2ዜና 22:2 እና 2ኛ ነገስት 8:26
Читать полностью…#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
ከሰማዕቷ ከቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ምልጃ ጸሎት ቃል ኪዳን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳትፈን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ። ለዘለዓለሙ አሜን ።
@mary21God
አንድ አባት ልጆቹን ወደ መናፈሻ ይዟቸው ይገባል
ልጆቹም ደስ ብሏቸው እየተጫወቱ ከቦታ ቦታ መሯሯጥ ጀመሩ
ህፃናቱ በደስታ ስለሆነ በጣም እየጮሁ እየዘለሉ ስለነበር በአከባቢያቸው የነበረን አንድ ሰው አበሳጩት ሰውየውም ተናዶ
"ምን አይነት አባት ነው ልጆቹን ሰብስቦ አይዝ" እያለ በውስጡ ማጉረምረም ጀመረ......
አባትየው ግን ይህ ሁሉ ሲካሄድ ምንም እያየ አልነበረም በሀሳብ ብቻ ተወስዶ ተክዟል!
ይባሱንም ልጆቹ ሲቃለዱ ይጠጣ የነበረውን ሻይ ሰውየው ላይ ሳያስቡ ደፉበት
በዚህም ተበሳጭቶ አባትየው ጋር በንዴት ሄደ ግዴለሽነት ነው ብሎም ሊጮህበትና ሊተናነቀው ተጠጋው
አባት ግን በተሰበረ ድምፅ "ከጥቂት ደቂቃ በፊት የልጅነት ሚስቴና የልጆቼም እናት ሆስፒታል ተኝታ ስለነበር አሁን ሕይወቷ እንዳለፈ ነገሩኝ እንዴት ብዬ ለልጆቼ እንደምነግር ግራ ገብቶኝ ነው በዝምታ ያለውት" አለው
አንዳንዴ ስሜታቸውን ሳንረዳ እንፈርድና ስህተት እንሰራለን ቀድሞ ከመፈረጅ እንቆጠብ!
#መልዕክት🙏
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
Mnm kehaymanot gar yemiyagenagnew yelm
Читать полностью…ሰዎች ፤ አልገባ ያለኝ ነገር አለ።
አላህ፡ ይሄ ጳውሎስ ያለውን እወስደዋለሁ
ኢብኒ ከቲር፡ ጳውሎስ ከአላህ የተላከ መልእክተኛ ነው
ሙስሊሞች፡ ጳውሎስ ሐሰተኛ መልእክተኛ ነው
አላህ፡ መጻሕፍቶቻችሁን አረጋግጫለሁኝ
ሙስሊሞች፡ መጻሕፍቶቻችሁ የተበረዙ ናቸው
አላህ፡ የመጽሐፍን አንድ ክፍል መርጣችሁ ሌላውን አትተዉ
ሙስሊሞች፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰነውን መርጣችሁ ሌላውን መተው አለባችሁ
!!! ሙስሊሞች ለምንድን ነው ኹልጊዜ ከአማላካቸው ተቃራኒ ጂሃድ መዝመት የሚወዱት? !!!
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፻፴፪ ኛው መደበኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
"በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
#ሐዋርያት ፳፥፳፰
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
#ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
“ናሁ ውስተ አድባር እገሪሆሙ ለሰብአ ዜና ወይዜንዉ ሰላመ እነሆ የምሥራችን የሚሰብክ ሰላምን የሚያወራ (ሚጠትን የሚናገር) ሰው እግሮች በተራሮች ላይ ናቸው"
(ትን.ናሆም 1፣15 ትርጓሜ ቅዱስ ዮሐንስ አወፈርቅ)
በውጭ አህጉረ ስብከት ተመድበው ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በመፈጸም ላይ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ 1 ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (ዶ/ር) የሰሜን ካሊፎርኒያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጅያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ወደ ሀገር ቤት በመግባት ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን እንዲሳተፉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ጥያቄ ማቅረቧ ይታወቃል፡፡
መንግሥትም ሀገራዊ ተቋማትን ለማጠናከር ያለው ቁርጠኝነት የጸና መሆኑን በገለጸበት መግለጫ እንደተመለከትነው የሀገራችንን ሰላም ለማጽናት፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን የታሪክ ገጽታ ለመጠበቅ ተቀራርቦ መነጋገር የተሻለ መፍትሔ መሆኑን ተረድቶ ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገር ገብተው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን እንዲሳተፉ መፍቀዱን ተረድተናል፡፡
በመሆኑም መንግሥት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያቀረበችውን ጥያቄ ተቀብሎ ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ሀገር እንዲገቡ በመፍቀዱና ተግባራዊ ምላሽ በመስጠቱ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ወደፊትም እግዚአብሔር በሰጠን ምድር፣ አባቶቻችን ባቆዩልን ሀገር አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ለሀገራችንና ለሕዝባችን በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ግንኙነታችንን በማጠናከር በጋራ : ለመሥራት ዝግጁዎች መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
Mnm kehaymano gar yemayagnagne new mokirut taterfubetalchu
Читать полностью…ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት፥ ፈለግሁት፤ አላገኘሁትም። — #ክፍል_አንድ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት ከበድ የሚለው - አስተሳሰባችን ከተበላሸም በመጥፎ መልኩ የምንተረጉመው - አንድ መጽሐፍ አለ፤ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን። ይኽ መጽሐፍ ከአምስቱ የሰሎሞን የጥበብ መጻሕፍት አንዱ ነው። ሰሎሞን መጽሐፉን ከሌሎቹ መጻሕፍቱ በተለየ መልኩ ክርስቶስን፥ ቤተክርስቲያንንና እመቤታችንን በዘይቤያዊ መንገድ እያቆራኘ ይጽፋል። መጽሐፉን ከማንበባችን በፊት ግን Fr. Zakaria Butros (የCoptic Church ካህን ናቸው፤ በእስልምናው ላይ በመሥራት በስፋት ይታወቃሉ) በመጽሐፉ ዙሪያ ከጻፉት በትንሹ ላስነብባችኹ።
Actually, approaching to the book of Song of the Songs is similar to approaching a flaming tree, flamed with the holy fire that had been seen by prophet Moses, as the lord said to him O Moses, ‛Take your shoes off your feet, for the place where you are standing is a holy ground’ (Acts 7:33) ... So when we approach the book of Song of the Songs, with its sublimity of meanings and symbols, we have to take off the shoes of materialism, and lusty thoughts, and go forward in the holiness of meditation and purity of heart, as: "To the pure, all things are pure; but to those who are defiled and unbelieving, nothing is pure; but both their mind and their conscience are defiled." (Titus 1:15)
መኃልየ መኃልይን ማንበብ ለሙሴ እንደታየው አይነት በቅዱስ እሳት የሚቃጠል ቁጥቋጦን እንደ መቅረብ ያለ ነው፤ ጌታ ለሙሴ እንዲኽ ሲል እንደተናገረው “የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና የእግርህን ጫማ አውልቅ።” (ሐዋ. 7፥33) ... ስለዚኽ እኛም መኃልየ መኃልይን ስናነብ፥ [ያሉትን ጥልቅ ትርጉሞችና ምልክቶችንም ለመረዳት] የmaterialism፥ የዝሙት ሐሳቦችን ጫማ አውልቀን፥ በቅድስና መንፈስ እና በንጹሕ ልብ መኾን አለበት፤ እንዲኽ እንደተጻፈ፦ “ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፥ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሷል።” (ቲቶ 1፥15)
በገና፣ ክራር እና መሰንቆ መግዛት የምትፈልጉ inbox አድርጉልኝ
Читать полностью…#ቤዛ_ለምንድነው?
ሙሴ ቤዛ ቢባል ለእስራኤል ሕዝብ ብቻ ነው እሱም በጊዜና በቦታ የተገደበ ነው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው
#ሙሴ ቤዛ ቢባል ለሥጋዊ ነው #ለምድራዊ #ለእህል ነው
#ማርምያምም ቤዛ ብትባል እንኳን ከዚህ ያለፈ ለምንም ነው ምክንያቱም ፍጡር ነች ግን አንድም ቦታ ቤዛ አልተባለችም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ
#እኛ እያወራን ያለነው ስለ ሐጥያተኞች የተከፈለ ቤዛነት ነው ለምድራዊ ቅራቅንቦ ወይም ለሥጋዊ የተደረገ መሰዋትነት አይደለም፡፡
ለዘላለም ሕይወት የማይሆን ቤዛነት ለኛ ለምንም አይጠቅመንም
#የሙሴ ቤዛ መባል ከኢየሱስ ቤዛነት ጋር በፍፁም ልነፃፃር አይችልም፡፡
የሙሴ ቤዛነት ከዮርዳኖስ አላለፈም
ሙሴ ቤዛ ስለተባለ ፍጡር ሁሉ ቤዛ ሊባልም አይችልም
#የኢየሱስ_ቤዛነት
"ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
"ሥጋዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ነው
"ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው
"ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ነው
"ለምግብ ሳይሆን ለኃጢአት ነው የኢየሱስ ቤዛነት፡፡
#ማርያም የሔዋን ምትክ ስለሆነች ቤዛ ነች ይሉኛል
ማርያም የሔዋን ምትክ ናት የሚል አንድም ጥቅስ የለም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከየት አምጥታችሁ ነው ለካስ እናንተ ውዳሴ ማርያም ላይ አለላችሁ😃😃😃
የሔዋን ምትክ ብትባልስ ሔዋን የቱ ጋ ነው ቤዛ ተብላ የተጠቀሰችው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ
እናት ስለሆነች😃😃😃
እናትና ልጅ ስለሆኑ😃😃😃
እምላክን ስለወለደች??😃😃
#ማርያም ይህን ሁሉ አድርጋ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታዲያ እንዴት ቤዛ ተብላ አልተጠቀሰችም???ይገርማል😃😃
#እኛ በ Logic ሳይሆን የምናምነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው አራት ነጥብ፡፡
#መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ጫማም ቤዛ ተብሎ ተፅፏል ይላሉ #ቤዛ ትርጉሙ ጥላ ወይም ከለላ ወይም ምትክ ማለት ሲሆን ጫማም ቤዛ የተባለው እግርን ከተለያዩ አደጋዎች ስለምጠብቅ እና ለእግር የምመጣው ድንጋይ ሆነ አደጋ ጫማው ላይ ስለሚያርፍ ነው ጫማ ለእግር ቤዛ የተባለው
#ጫማ ቤዛ ተብሏልና ቤዛችን ጫማ ነው ማለት ነው?
#የኢየሱስ ቤዛነት ልክ እንደጫማው ልያጠፋን የመጣውን በደላችን በራሱ አሳርፎ በኛ ምትክ ሞታችን ሞቶ ነው ያዳነን ቤዛችን ኢየሱስ ነው፡፡
#በደሙ የፈረመልን ቤዛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው
#የዓለም_ቤዛ_ኢየሱስ!!
ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ መጣ
“እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
— ማቴዎስ20፥28
#የድነት_ቤዛ!!
የዳንነው የፀድቅነው በእርሱ ቤዛነት ነው በፀጋው
“በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።”
— ሮሜ 3፥24
#በደም_የተደረገ_ቤዛነት!!
ደም ሳይፈስ ቤዛነት የለም
“በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።”
— ኤፌሶን 1፥7
#ለኃጢአት_የተከፈለ_ቤዛነት!!
“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”
— ቆላስይስ 1፥13-14
#ዘላለማዊ_ቤዛነት...
የኢየሱስ ቤዛነት ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው
“የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።”
— ዕብራውያን 9፥12
በደሙ የፈረመልኝ ቤዛዬ ኢየሱስ ነው
እርሱ ነው ነፍሴን ያዳናት ቤዛዬ ኢየሱስ
🙏
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ቤዛነት ላይ የተጨመሩና ጐላ ብለው የሚታዩት ቤዛዎች ማርያም እና ዕፀ መስቀል ናቸው። ሌሎች፥ “ቤዛ” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙዎች ቤዛዎችም አሉ።
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፥ “ማርያም ቤዛዊተ ኵሉ ዓለም አትባልም” ብለው ብቻ አላበቁም። ቤዛ ሳይኾን በተሳሳተ መንገድ “ቤዛ” እየተባለ የሚጠራው ዕፀ መስቀልም “ቤዛ”` እንደማይባል በግልጽ አስተምረዋል፤ እንዲህ ሲሉ፥
“…መስቀል ቤዛችን ነው ስንል፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መከራው ሥቃዩ መስቀል ተብሎ ነው የሚተረጐመው። መስቀል ቤዛ ነው ስንል ይኼ (የዕንጨቱ መስቀል) ቤዛ ኾነልን ማለት አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የከፈለውን ዋጋ ያሳየውን ደግነት መልካምነት ማለታችን ነው።” ይህ እውነተኛና መጽሐፍ ቅዱሰዊ መሠረት ያለው ትምህርት ነው።
ዛሬ የዕንጨት መስቀል ቤዛ ይባላል የሚሉ ሰዎችን፥ ቤዛ ለማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊው ማስረጃችኹ ምንድነው? ብለን ብንጠይቃቸው፥ ልክ ስለ ማርያም ቤዛዊተ ዓለምነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ማቅረብ እንዳልቻሉ ኹሉ፥ የዕንጨት መስቀልንም ቤዛነት የሚያስረዳ ንባብ ማቅረብ ከቶ አይችሉም፤ የለማ!!
ክርስቶስ እኛን ስለ ማዳን የተቀበለው መከራም፥ ስለ እኛ መከራን ለመቀበልና ለመሞት የተሰቀለበት ዕንጨትም በተመሳሳይ ስም “መስቀል” ተብለው ስለሚጠሩ፥ የመከራውን ቤዛነት፥ ቤዛ ላልኾነውና አንዳችም የቤዛነት ሥራ ላልሠራው ለዕንጨቱም መስጠት ተለምዷል። ክርስቶስ በመስቀል የተቀበለውን መከራማ ማን ልብ ብሎት አያ!
አብዛኛው ሰው፥ “መስቀል ቤዛነ” እያለ የሚያምነውና የሚመሰክረው ስለ ዕፀ መስቀል ነው እንጂ ስለ መከራ መስቀሉ አይደለም። ስለዚህ ዕፀ መስቀል የክርስቶስን የመከራ መስቀሉን ቤዛነት ቀምቷል። ብፁዕ አቡነ ገብርኤልም በእጃቸው የያዙትን የዕንጨት መስቀል እያገላበጡ፥ “መስቀል ቤዛ ነው ስንል ይኼ (ቍስ የኾነው የዕንጨቱ መስቀል) ቤዛ ኾነልን ማለት አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የከፈለውን ዋጋ ያሳየውን ደግነት መልካምነት ማለታችን ነው።” ብለዋል።
በዘወትር ጸሎት ውስጥ፦
“መስቀል ኀይልነ፣ መስቀል ጽንዕነ፣ መስቀል ቤዛነ፣ መስቀል መድኀኒተ ነፍስነ፣ አይሁድ ክሕዱ ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኀይለ መስቀሉ ድኅነ”
ትርጕም፦ “መስቀል ኀይላችን፣ መስቀል ጽንዓችን፣ መስቀል ቤዛችን፣ መስቀል የነፍሳችን መድኀኒት ነው፤ አይሁድ ካዱት፤ እኛ ግን አመንነው፤ ያመንነው እኛም በመስቀሉ ድነናል።”
የሚለው ዕንጨቱን አይመለከትም። እነዚህ ኹሉ ለመከራ መስቀሉ እንጂ ለዕንጨቱ አይስማሙትም። ብዙው ሰው ግን ይህን ጸሎት ሲጸልይ የሚያስበው ዕፀ መስቀሉን ብቻ ነው። መከራ መስቀሉንም ነው የምናስበው ከተባለ ግን፥ በመጀመሪያ ቤዛ የኾነውን መለየት እንጂ ኹለቱንም ቤዛ ብሎ መጥራት ከስሕተት አያድንም። ስለዚህ ዕፀ መስቀሉ ቤዛ አይባልም ያሉት ብፁዕነታቸው ያስተማሩት ትምህርት ትክክለኛ ትምህርት ነው።
ጌታችን በዕንጨት መስቀል ላይ የተቀበለው መከራና ሞት፥ ስለ እኛ ኀጢአት የተከፈለ ቤዛ ነው። የዳንንበት፣ የምንመካበት መስቀልም ርሱ ብቻ ነው። ዕፀ መስቀሉ ደግሞ ይህ የተከናወነበት ቍስ እንጂ ራሱ ቤዛ አይደለም። ዕፀ መስቀል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠራው በዚህ መንገድ ነው፦
• “የኢየሱስ መስቀል” (ማቴ. 27፥32፡40፡42፤ ማር. 15፥21፡30፡32፤ ሉቃ. 23፥26፤ ዮሐ. 19፥25፡31፤ ፊል. 2፥8፤ ቈላ. 2፥14፤ ዕብ. 12፥1-2)፣
• “መስቀል” (ማቴ. 27፥40፡42፤ ማር. 15፥30፡32፤ ዮሐ. 19፥31፤ ፊል. 2፥8፤ ቈላ. 2፥14፤ ዕብ. 12፥1-2) እና
• “ዕንጨት” (ሐ.ሥ. 5፥30፤ 10፥39፤ 13፥29፤ ገላ. 3፥13፤ 1ጴጥ. 2፥24) ተብሎ ተጠርቷል።
ይኹን እንጂ በእነዚህ ጥቅሶችም ኾነ በሌሎች ክፍሎች “ቤዛ” ተብሎ ፈጽሞ አልተጠራም። ይህ መስቀል በክርስትና ውስጥ ኢየሱስ የተሰቀለበት ቍስ ከመኾን ያለፈ አገልግሎትም የለውም። ሐዋርያትም በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ፥ ጌታ ስለ ተሰቀለበት መስቀል የተለየ የጻፉት ነገር የለም።
ስለ ተሰቀለው ክርስቶስ በጻፉባቸው አንዳንድ ክፍሎች ግን፥ ጌታችን የተሰቀለው በዕንጨት ላይ መኾኑን ጠቅሰዋል፤ ከዚህ በቀር ስለ ዕንጨቱ ቤዛነት የጻፉት የተለየ አንዳች ነገር የለም (ሐ.ሥ. 5፥30፤ 10፥39፤ 1ጴጥ. 2፥24)። ይህም የሚያመለክተው ስለ ዕፀ መስቀል በዘመናችን የሚሰጠው ትምህርትና ሰዎች የሚያደርጉት ነገር በሐዋርያት ዘመን ያልነበረና ዘመን አመጣሽ ትምህርትና ልምምድ መኾኑን ነው።
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተጻፈውን ልብ ብለን ስንመለከት፥ ስለ ተሰቀለበት ዕንጨት የተገለጠው በአዎንታዊ ሳይኾን በአሉታዊ መልክ የቀረበ ነው። ለምሳሌ ሐዋርያው ጴጥሮስ፦
• “እናንተ በዕንጨት ላይ ሰቅላችኹ የገደላችኹትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው” (ሐ.ሥ. 5፥30)።
• “ርሱንም በዕንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት” (10፥39)።
በማለት ስለ ተሰቀለበት ዕንጨት ሲናገር፥ ጌታን ለማዋረድ ብለው በዕንጨት ላይ የሰቀሉት አይሁድ መኾናቸውን ከማውሣት በቀር፥ ጌታ የተሰቀለበት ዕንጨት ቅድስና የተላለፈለት ወይም ክብር ያገኘ መኾኑን የሚናገር አንድም ነጥብ የለም። ይልቁንም ሐዋርያው ጳውሎስ በኦሪት ዘዳግም 21፥23 ውስጥ የተጻፈውን ጠቅሶ፥
“በዕንጨት የሚሰቀል ኹሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና፥ ክርስቶስ ስለ እኛ ርግማን ኾኖ ከሕግ ርግማን ዋጀን” በማለት የገለጠው (ገላ. 3፥13)፥ የዕንጨት መስቀል የርግማን ምልክት መኾኑንና ክርስቶስም ስለ እኛ ርግማን በመኾን በዕንጨት ላይ መሰቀሉን ብቻ የሚያስረዳ ነው።
ክርስቶስ በተሰቀለበት መስቀል አምሳል በተለያየ መጠንና ቅርጽ ከተለያዩ ነገሮች ማለትም፦ ከዕንጨት፣ ከድንጋይና ከልዩ ልዩ ማዕድናት የተሠሩትንና በዐንገት ላይ የሚታሰሩትን፣ ቀሳውስት የሚያሳልሙበትን፣ በሥርዐተ ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ የሚይዘውን ባለመጾር (ባለመሸከሚያ) መስቀል … ኹሉ የክርስቶስ መስቀል ናቸው ማለት አይደለም። ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ነው ተብሎ፥ ሊታይ ወይም ሊቀርብ የሚችል ቍስ የኾነ መስቀል ዛሬ ላይ የለም። ኹሉም ያን ምሳሌ አድርገው ሰዎች በልዩ ልዩ ቅርጽና መጠን ጌጠኛ አድርገው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሠሯቸው ሌሎች መስቀሎች ናቸው።
በክርስትና ውስጥ የመስቀል ምልክት፥ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንዲያመለክት የቆመ ትእምርት (Symbol) ነው። የተሰቀለውን ከማመልከትም በቀር ሌላ ምንም ሚና የለውም። “ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ” እንዲሉ፣ ቍስ የኾነው መስቀል፥ የተሰቀለውን ክርስቶስን ማመልከት ትቶ እኔኑ እዩኝ ካለ፣ ራሱን ዋና መስቀል ካደረገ፣ የተሰቀለውን ክርስቶስን ተክቶ ርሱው ከተሰበከ፣ ክርስቶስ በርሱ ላይ የተቀበለው መከራና ሞት ቤዛ መኾኑን ወደ ጐን ገለል አድርጎ ርሱው ቤዛ ከተባለ፣ ለርሱው ከተዘመረለትና ርሱው ከተመለከ፣ ትእምርትነቱን ትቶ ዋናው ኾኗልና ሚናውን ስቷል፤ ስሙ “መስቀል” ቢኾንም እንኳ ጣዖት ወደ መኾን ተሸጋግሯል።
" ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ልማትና ዕድገት እናሻግራለን ብላችሁ እየደከማችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን እባካችሁ መለስ ብላችሁ እናታችሁ የተንገላታችበትን እዩና በቃ በሉ፤ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ፤ በዚህ ኣማራጭ እናት ሀገር እፎይታ እንድታገኝ ኣድርጉ፤ ይህንም ለውድ እናት የሚደረግ ካሣ ኣድርጋችሁ ውሰዱት።"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ኣሜን!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጰጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጰሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!!
እንደዚሁም በዚህ ቀኖናዊና ዓመታዊ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ የተገኛችሁ በሙሉ፤ ጸጋንና ሓዋርያነትን ያጐናጸፈን ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ትንሣኤውን በሰላም ኣክብረን ይህንን ዓመታዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለማካሄድ ስለ ሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ የጉባኤው ኣባላት የሆናችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም እንኳን ለረክበ ካህናት ጉባኤ ኣደረሳችሁ! እንኳንም በሰላም መጣችሁ!
“ረከብነ ጸጋ ወተሰየምነ ሓዋርያተ ከመ ናስምዖሙ ለኣሕዛብ ወይእመኑ በስሙ፡- ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሓዋርያነትን ተቀበልን” (ሮሜ.፩÷፭)፤
ይህ ሐዋርያዊ ኣስተምህሮ የኛን ተእልኮና ተልእኮው ያስፈለገበትን ምክንያት ኣጉልቶ ያሳያል፤ የተቀበልነው ስጦታም ምን ያህል ታላቅ እንደ ሆነ ምንባቡ ያስረዳል፤ ሓዋርያው በዚህ መልእክት የቅዱስ ወንጌል ኣስተምህሮ ዋና ግብ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ማድረግ ነው በማለት ያስተምረናል፤ እውነት ነው ድሮውኑም ቢሆን ለእግዚኣብሔር መታዘዝ ኣቅቶን ነው የወደቅነው፤ ዛሬም የምንነሣው ከእምነት የተነሣ መታዘዝን ገንዘብ ስናደርግ ነው፤ ከሁሉ በፊት እምነት ይቀድማል፤ ከሱ በኋላ ደግሞ ለእምነቱ በሙሉ ልብ መታዘዝ ይከተላል፤ ይህ ሲሆን መዳንና ትንሣኤ ይገኛል፤ ዓለም በእግዚአብሔር እየተደረገላት ያለ ጥሪ ይኸው የመታዘዝ ጥሪ ነው፤
ይህንን መለኮታዊ ጥሪ ለዓለም የማድረስ ኃላፊነትም ለኛ ለቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት የተሰጠ እንደሆነ ሐዋርያው አስገንዝቦኣል፤ ኃላፊነቱ ሲሰጠን ከነመሳርያው ነው፤ እሱም ጸጋና ሓዋርያነት ነው፤ እኛም እሱን ተቀብለናል፤ እንግዲያውስ የተቀበልነውን ጸጋና ሓዋርያነት በዓለም ውስጥ ላለው ሕዝበ እግዚአብሔር ኣገልግሎት ማዋል ከኛ ይጠበቃል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣበላት!!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአሁኑ ጊዜ የሌለበት ክፍለ ዓለም የለም፤ ምክንያቱም የዚህ ሲኖዶስ ወኪሎች ሊቃነ ጳጳሳት በኣፍሪካ፣ በኣውሮፓ፣ በሰሜን ኣሜሪካ፣ በላቲን ኣሜሪካ፣ በካናዳና በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በእስያና በኣውስትራሊያ ወዘተ የሚገኙ ሕዝበ እግዚአብሔር ምእመናንን በማገልገል ላይ ይገኛሉና ነው፤ ይህ ዕድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መለኮታዊ ተልኮውን በአጽናፈ ዓለም ሁሉ ለማድረስ ምቹ መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ከዚህም በመነሣት በየክፍለ ዓለሙ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃነ ጳጳሳት ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ባሻገር የየአካባቢውን ሕዝብ በማስተማርና በማቀፍ የተጣለባችሁን ሓዋርያዊ ተልእኮ በትጋትና በንቃት መወጣት ይኖርባችኋል፡፡
በማእከል ሆኖ እየመራ የሚገኝ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚህ ተልእኮ ምቹ መደላድል የመፍጠር ኃላፊነቱን በኣግባቡ መወጣት ይገባዋል፡፡ በተለይም ትምህርተ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የተማሩና በጥልቀት የተገነዘቡ፣ ብስለትም ያላቸው፤ እንዲሁም በቋንቋና በሥነ ልቦና ዕውቀት የላቀ ሀብተ ጸጋ ያላቸውን በሐዋርያነት እያሠለጠነ በአጽናፈ ዓለም ሁሉ ሊያሰማራ ይገባል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣበላት!
በብሂለ አበው (ፀሐይ ለመስኮቷ ሳታበራ…) እንደሚባለው ለሌላው በብቃት መድረስ እንችል ዘንድ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሲኖዶሱ መንበር በሚገኝባት ምድረ ኢትዮጵያ ከመቸውም የተሻለ ስራ በመስራት ለእግዚአብሔር መታዘዝ ሕዝቡንም ማገልገል ይገባናል፤ ሁላችንም እንደ ምንገነዘበው በሲኖዶሳችን ያልታቀፉ ብዙ ወገኖች በሀገር ውስጥ ኣሉን፤ እነዚህ ወገኖች አንዳንዶቹ በተለያየ ምክንያት ከኛ የወጡ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሄዱት ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ፣ ሌሎችም ወደ መንጋው እንዲቀላቀሉ በርትቶ መስራት የዚህ ጉባኤ ተቀዳሚ ተልእኮ ነው፤ ምክንያቱም ጸጋንና ሐዋርያነትን የተቀበልንበት ዋናው ምክንያት ይህንን ለማድረግ ነውና፡፡ ከዚህ አኳያ የቤተ ክርስቲያናችን ተደራሽነት በሳሳበት ኣካባቢ ሁሉ የተለየ ትኵረት ሰጥተን መስራትና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል፤
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነትና ምእመናን የሆን ሁላችን፣ ከሁሉ በፊት ያለንን ዓቅምና ብቃት በኣግባቡ መገንዘብ ይኖርብናል፤ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁንና ለፈጣሪው በቈራጥነት የሚታዘዝ ምእመን፣ ወጣት፣ ካህን ኣለን፤ ይህ ትልቅ ጸጋ ነው፤ ይህንን ጸጋ እግዚአብሔር፡ ለእግዚአብሔር መንግሥት በሚመች ሁናቴ ዝቅ ብሎ ማገልገል የክብር ክብር ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሓቅ፣ በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ቆመን ካገለገልነውና ኣባትነታችንንና መሪነታችንን በመልካም አሰራር በትክክል በኅሊናው እንዲቀረጽ ካደረግን፣ ይህ ኃይል ከጐናችን እንደማይለይ እርግጠኞች መሆን እንችላለን፤ ይህንን ካሳካን ለኛ የተሰጠ ኃይልና ብቃት በየትም ኣይገኝም፡፡
በዚህም በዚያም ሃይማኖቱ የሚጠይቀውን ሰብእና እና ቁመና ይዘን ከተገኘን፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ ያለውን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን ሳይቀር ለመስጠት ወደ ኋላ የማይል የእግዚአብሔር ሕዝብ ኣለን፤ ስለዚህ ይህንን ማሳካት እንችል ዘንድ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንድናስገኝ የተቀበልነውን ጸጋና ሐዋርያነት በክብር እንያዝ፤
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!!
ለሕዝበ እግዚአብሔር የምናበረክተው ኣገልግሎት በመንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚውና በማኅበራዊው ኣገልግሎትም ጭምር ነው፤ ከዚህ ኣንጻር ሕዝባችን የተሻለ ማኅበራዊ ኣገልግሎት እንዲያገኝ፣ በኢኮኖሚውም ከድህነት የተላቀቀ እንዲሆን፤ እንደዚሁም ሰላሙና ኣንድነቱ የተጠበቀ እንዲሆን፣ በማስተማርም በተግባር በመሳተፍም የሕዝቡ መሪዎችና ኣርኣያ ሆነን መስራት ይገባናል፤በተለይም ከሰላም እጦት የተነሣ በእጅጉ እየተጎዳ ያለውን ሕዝባችን ሰላምና ፍትሕ እንዲያገኝ በጸሎትም በትምህርትም፣ በምክርም ተግተን መስራት ኣለብን፤
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
"፻፴፪ኛው መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል።
ግንቦት ፭/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
፻፴፪ ኛው መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል።
በየዓመቱ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን የሚካሔደው ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ መሪነት የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሔዳል።
በየዓመቱ የሚካሔዱት ሁለቱ ጉባኤያት አንደኛ ቋሚ በሆነ ቀን በጥቅምት 12 ሲጀምር ሁለተኛው ግን የአጽዋማቱን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣው የባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት በዓለ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን የርክበ ካህናት ጉባኤ ይከናወናል።
በዚህ በ2017 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነገ ግንቦት 6/2017 ዓ/ም የሚጀምር ሲሆን በዋዜማው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የፕትርክና መንበሩ ከግብፁ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ከሰኔ 21/1951 ዓ/ም ወዲህ አስቸኳይ ጉባኤያትን ሳይጨምር ከ131 መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት መካሔዳቸውን ታሪክ ያስረዳል።
ከነዚህ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቅዱሳን ፓትርያርኮች ጥረት ርእሰ መንበርነት የተመሩ ሲሆን በሁለት የተለያዩ ዓመታት ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፓትርያርክ ባለመኖሩ ምክንያት በአቃብያነ መንበር በብፁዓን አባቶች ተመርተዋል።
ከእነዚህ አንደኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ በወቅቱ በነበረው አገዛዝ ምክንያት በግፍ ለግዞት ስለተዳረጉ ግንቦት 11 ቀን 1968 ዓ/ም የዋለውን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቃቤ መንበር በነበሩት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የመላ ትግራይ ሊቀ ጳጳስ ርእሰ መንበርነት ተመርቷል።
ሁለተኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ነሐሴ 10/2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በማረፋቸው ምክንያት የጥቅምቱ 12/2005 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖደስ ምልዓተ ጉባኤን የወቅቱ አቃቤ መንበር የነበሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በርእሰ መንበርነት መርተዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጥበት ሲሆን እምነት የማጽናት ሥርዓትን ማስጠበቅ አስፈላጊ ከሆነም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች የማሻሻል ሥልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ነው።
“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
ሐዋርያት ፳፥፳፰
🔵የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ስለ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን
✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
"የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።"
#ኤፌ 6፥11
"እርሱስ በአርምሞአችን ካልተጠቀመ በመናገራችን አይጠቀምም"
#አሞ 5፥13
"ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።"
#ያዕ.1፥19
"ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን"
#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo.