ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo
የእስር ዜና!!!
ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታሰረ‼️
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስብከት አገልግሎቱ፣በተለያዩ ስልጠናዎች ላይ ስልጠና በመስጠት፣በተለይም ተሃድሶውያንን በመዋጋት የምናውቀው ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች መወሰዱ ተሰማ።
እንደሚታወቀው የቅዱስ ሶኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሚካሄድበት ወቅት በተለይም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በሚመረጥበት ግዜ ሁሉ ለቤተክርስቲያን ይታገላሉ የሚባሉ ወንድሞች እና እህቶች ይታሰራሉ። ዛሬም ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ታስሯል።
የቅዱስ ሲኖዶስን ጸሐፊ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅን መምረጥ የመንፈስ ቅዱስ እና የብፁዓን አባቶች ድርሻ ነው። በዚህ ወቅት የሚታሰር አንዳችም ሰው መኖር የለበትም ።ወንድማችንን እንድትፈቱት እንጠይቃለን ።
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
DOOBA – From 100 USDT to Big Rewards
Many users have already seen results—are you next?
💸 100 USDT can grow up to 800% on DOOBA
💸 Daily passive income with zero effort
💸 Free trading bot, stable platform, real growth
Big returns favor early movers—join today!
መዝሙር 78
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ይበሉም ዘንድ መናን አዘነበላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ ሰጣቸው።
²⁵ የመላእክትንም እንጀራ ሰው በላ፤ ስንቅንም እስኪተርፋቸው ላከላቸው።
...
በሰማይ መላእክት አንጻር "እስመ አኮቴቶሙ እረፍቶሙ፥ ወእረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ የመላእክት እረፍታቸው ምስጋናቸው ፤ ምስጋናቸው እረፍታቸው ነው፤ የመላእክት ምግብና መጠጣቸውም ምስጋናቸው ነው፤
ስለዚህ የመላእክት እንጀራን የሰው ልጅ በላ ማለት ፤ አመሰገነ ማለት ነው፤
ይህንን አጥንትን የሚያለመልም የመላእክት እንጀራ ምግብ የሆነ ምስጋና ወደኛ ላመጣልን በመላእክት ምስጋናም ምስጉን እግዚአብሔርን እንድናመሰግን ላደረገን ለቅዱስ ያሬድ ለተሰወረበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤
የቅዱሱ በረከት ይደርብን😊
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ዜኖኩ ጽድቅከ ወነገርኩ አድህኖትከ ከሰትኩ ቃላቲከ ለህዝበ ኢትዮጲያ(፪)
# ግንቦት_11
በምድር ሁኖ በሰማያዊ ቋንቋ የሚናገረው አልቦ እምቅድሜከ ወአልቦ እምድህሬከ ከአንተም በፊት ከአንተ በኋላ አንተን የሚመስል የለም የተባለለት ብቸኛው የኪሩብም ደቀ መዝሙር ቅዱስ ያሬድ የመሰወር በዓሉ ነው በረከቱ ይደርብን
ዜኖኩ ጽድቅከ ወነገርኩ አድህኖትከ ከሰትኩ ቃላቲከ ለህዝብከ ኢትዮጲያ(፪)
በጸጋሑ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሀርክዎሙ አነ ይቤ ያሬድ ካህን(፪)
+++ጽድቅህን ነገርኩ አዳኝነትህን አስተማርኩ ቃላትህን ለኢትዮጲያ ሕዝብ ነገርኩ(፪)
እኔም በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አስተማርኳቸው አለ ያሬድ ካህን(፪)
በመጨረሻም እግዚአብሔር ለቅዱስ ያሬድ ቃልኪዳን ገብቶለታል
ዝክረ ቅዱስ ያሬድ
'ብፁዕ ውእቱ ዘገብረ ተዝካረከ...አነ እሁቦ ሕይወተ ዘለዓለም ወአወርሶ መንበረ ክብር' ይቤሎ እግዚአብሔር ለያሬድ ካህን
እግዚአብሔር ለካህን ያሬድ እንዲህ ብሎታል 'ተዝካርህን ያደረገ ንዑድ ነው ክቡር ነው... የዘለዓለም ሕይወትን እሰጠዋለሁ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ' በምልጃው ያስበን
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#11 የቅዱስ ያሬድ በዓል]
#በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡
“ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ” ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡
ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፡- “ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” (ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው) ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት፣ በማለት አርያም በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡
ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡
ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም
፩ኛ) ድጓ ፪ኛ) ጾመ ድጓ
፫ኛ) ምዕራፍ ፬ኛ) ዝማሬ ፭ኛ)መዋሥዕት ናቸው፡፡
እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ፣ በዕዝል፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ “ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ” ይላል፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡
ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን “የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡
“ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን” ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ፤ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ” (በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር) ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡
በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡
ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት “ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር... ” (ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል” ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡
ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ፦
“ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ*መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ”
(የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል) በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ፡-
“ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤
ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት
ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት
ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ
ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ
ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ”፡፡
(የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡
[የጽሑፉ ምንጭ፡- አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የደረሰው ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተጻፈ፤ ከገጽ 232-235]፡፡
የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን፤ እናንተም ይኽነን ሊቅ አወድሱት።
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ዜኖኩ ጽድቀከ ወነገርኩ አድኅኖተከ
ከሠትኩ ቃላቲከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ(፪)
በጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሀርክዎሙ
አነ ይቤ ያሬድ ካህን(፪)
ጽድቅህን ነገርኩ አዳኝነትህን አስተማርኩ(፪)
ቃላትህን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገለጥኩ
እኔም በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አስተማርኩአቸው አለ ያሬድ ካህን(፪)
#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ግሩኙን ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedoo
#ለሃሳብ አስተያየት
@Orthodox_tewahedo_Bot
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
የታላቁ ሙስሊም ቃሪእ (ኢብን መስዑድ) ቁርአን ወደጎን መወርወር {ክፍል አንድ}
በዓለም ውስጥ እጅግ የተጠበቀው መጽሐፍ ቢኖር ቁርአን ነው ፥ ቁርአን ካልተጠበቀ የተጠበቀ መጽሐፍ የለም። በጣም ከመጠበቁ የተነሣ አሁን ያለን ቁርአን በኢብን መስዑድ (መሐመድ "ቁርአንን መማር ከፈለጋችሁ ከእነዚህ ተማሩ" ካለላቸው መካከል አንዱ) የተጠላና የተነቀፈ ቁርአን ነው። ኢብን መስዑድን ወደ ጎን ወርውረውት እርሱ እንደሌለ ቆጥረውት የጻፉት ቁርአን ነው አህን በእጃችን ላይ ያለው። ስለዚህ ሙስሊሞች የሚገቡበትን dilemma አስቡበት ፥ "ኢብን መስዑድ ልክ ነበር የኡስማንን ቁርአን ሲቃወም? አዎ ፥ ከኾነ እናመሰግናለን አሁን ያላችሁ ቁርአን እንደተበረዘ ስለነገራችሁን። አይ ፥ ከኾነ ደግሞ መሐመድ ለቁርአን የመረጠው ሰውዬ ስለቁርአን አያውቅም ማለት ነው። መሐመድ ተሳስቷል ማለት ነው ይህንን ሰውዬ ለቁርአን ሲመርጠው"። በኹለቱም በኩል የሚገድል ሰይፍ ማለት ነው።
ኢብን መስዑድ ማለት መሐመድ እጅግ ይወደው የነበረ ፤ ይልቁንም ደግሞ መሐመድ "ቁርአንን ጥርት እንዳለ መማር ከፈለጋችሁ ከእነዚህ ከአራቱ ተማሩ" ብሎ ከተናገረላቸው ከአራቱ መካከል አንዱ ነው። ኡስማንም ኾነ ዘይድ ቢን ሣቢት ከዚያ ቁጥር ውስጥ የሉም።
Narrated Masruq:
Abdullah bin Masud was mentioned before Abdullah bin Amr who said, "That is a man I still love, as I heard the Prophet (ﷺ) saying 'Learn the recitation of Qur'an from four from Abdullah bin Masud -- he started with him--Salim, the freed slave of Abu Hudaifa, Muadh bin Jabal and Ubai bin Kab."
Sahih al-Bukhari 3808
Narrated Masriq: Abdullah bin Amr mentioned Abdullah bin Masud and said, "I shall ever love that man, for I heard the Prophet (ﷺ) saying, 'Take (learn) the Qur'an from four: Abdullah bin Masud, Salim, Muadh and Ubai bin Kab.' "
Sahih al-Bukhari 4999
It was narrated from Qais bin Marwan that he came to 'Umar and said: I have come from Koofah, O Ameer al-Mu'mineen, and I left behind in it a man who dictates the Mushaf From memory. ‘Umar got exceedingly angry and said: Who is he, woe to you? He said: 'Abdullah bin Mas'ood. ‘Umar began to calm down, and went back to normal, then he said: Woe to you, I do not know of anyone who is more qualified to do that than him, and I will tell you about that. The Messenger of Allah ﷺ used to stay up at night talking with Abu Bakr رضي الله عنه discussing some affairs of the Muslims. He stayed up talking with him one night, and I was with him. The Messenger of Allah ﷺ went out, and we went out with him, and we saw a man standing and praying in the mosque. The Messenger of Allah ﷺ listened to his recitation, and as soon as we recognised him the Messenger of Allah ﷺ said: Whoever would like to recite the Qur'an fresh as it was revealed, let him recite it according to the recitation of Ibn Umm 'Abd. Then the same man sat and offered supplication (du'a') and the Messenger of Allah ﷺ started saying to him: Ask, you will be given;ask, you will be given.” ‘Umar said: By Allah, I shall go to him tomorrow and tell hirm the glad tidings. I went to him the next morning to tell him the glad tidings, and I found that Abu Bakr had beaten me to it and given him the glad tidings. By Allah, I never competed with him to do good but he beat me to it.
Musnad Ahmad 175
Grade: Two Sahih isnads (Darussalam)
'Abdullah (b. Mas'ud) reported that he (said to his companions to conceal their copies of the Qur'an) and further said: He who conceals anything he shall have to bring that which he had concealed on the Day of judgment, and then said: After whose mode of recitation you command me to recite? I in fact recited before AIlah's Messenger (ﷺ) more than seventy chapters of the Qur'an and the Companions of Allah's Messenger (ﷺ) know it that I have better understanding of the Book of Allah (than they do), and if I were to know that someone had better understanding than I, I would have gone to him. Shaqiq said: I sat in the company of the Companions of Mubkmmad (ﷺ) but I did not hear anyone having rejected that (that is, his recitation) or finding fault with it.
Sahih Muslim 2462
ሀብታም ነች በዛላይ መልክ የደፋባት እመቤት፡ ከሚያምረው ሰረገላዋ ልትወርድ ስትል መሬቱ ጭቃ ነው መርገጥ አልፈለገችም፡
በዛው ቅፅበት አንድ ወጣት እና አንድ ጎልማሳ መነኩሴ በዚያ ሲያልፉ አዯት፡
ወጣቱ ውበቷ፡ አለባበሷ፡ መልኳ፡ ማርኮት ፈዞ ያያታል
ጎልማሳው መነኩሴ ግን ወደሷ ጠጋ ብሎ፡ "ጀርባዬ ላይ ወጪ እኔ አሻግርሻለሁ" አላት፡ ያንን የሚያዳልጥ ጭቃ ተሸክሞ ካሻገራት በኋላ፡ አመሰግናለሁ እንኳን ሳትለው ገፍትራው ሄደች።
ሁለቱ ጉዟቸውን ቀጠሉ ወጣቱ ግን በስጨት ብሎ "ምን አይነት ሴት ነች አመሰግናለሁ እንኳን ሳትል እዴት ገፍትራህ ትሄዳለች" አለው።
መነኩሴው ተረጋግቶ "ልጄ እኔ ከትከሻዬ ካወረድኳት እኮ ቆየው አንተ ግን እስካሁን ተሸክመሃታል፡ እኔ የኔን ስሜት እንጂ የሷ መቆጣጠር አልችል" አለው።
ይቅር የምንለው ለነሱ ብለን አይደለም የራሳችንን ሸክም ለማቅለል ነው።
ሁላችንም የይቅርታ ልብ ያድለን🙏
#መልዕክት
🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪
✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
💸MAKE YOUR MONEY WITH YOUR GROUP
#Old Group አላችሁ ?
ለምሳሌ በፊት ት/ቤት እያላችሁ የከፈታችሁት ግሩፕ ካለ ወደኛ ጋር ይምጡ።
2023 -(January, February and March)
🪼2022 ---- 500
🪼2021-----650
🪼2020 -----800
🪼2019 -----950
🪼2018 -----1100
ያላችሁ መሸጥ ከፈለጉ "DM" ያዋሩኝ👉 ሁል ጊዜ online 🟢 ነኝ
History Clear ያሎነ ትክክለኛ Old ብቻ ነው ምፈልገው ልታደክሙኝ አትምጡ
CBE
TELEBIRR
Abyssinia
Awash
ለየት የሚያረገን በባዶ ሜዳ owner
አስተላልፉ አንልም!
💧 full proof አለን
በታማኝነት እንገዛለን ከ scammers
እራሳችሁን ጠብቁ::
⚙ 2 step verification🔒 ማብራታችሁን አረጋግጡ
✨No scam
⚡️Fast payment
✨we send receipt screenshot after payment
ማህሌት ተከታታይ መንፈሳዊ ልብ ወለድ ክፍል አስራ አራት
ይቅርታ አድርግልኝ የሰንበት ተማሪ ጓደኛ እንዲኖረኝ አልፈልግም ብዬ ጥዬው ልሄድ ተነሳው ። ልክ ነሽ ያልሽውን ነገር በሙሉ ይደረጋል ግን ሁለት ነገሮችን ተሳሳትሽ ።
የመጀመሪያው ሁሉንም ዘፋኝ ሁሉንም ሀሜተኛ ሁሉንም ቀልደኛ አድርገሽ ማሰብሽ ወይም መጠቅለልሽ ነው ። ለምሳሌ አበበ የሰንበት ተማሪ ነው ይሰርቃል ። ስለዚህ የሰንበት ተማሪ ሁሉ ይሰርቃል እንደማለት ነው ።
በነገራችን ላይ የማልዋሽሽ ነገር እስከመጨረሻው ድረ ስ ክፉ ሥነ ምግባር ያላቸው ሰዎች እንኳን ሰንበት ትምህርት ቤት ይቅርና ቤተ መቅደስም ይኖራሉ ። ልክ ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር ይሁዳ እንደነበረው ከኤልሳም ጋር ግያዝ እንደነበረው ።
ምን አልባት አንቺ የምታያቸው ዐውደ ምሕረት ላይ የሚዘምሩ አ ስራ አምስት ወይም ሀያ ሰዎችን ነው ከእነሱም ቢሆን ደህና ሰዎች የሉም ማለት አይደለም ።
ነገር ግን ሰንበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ብትሄጂ ብዙ ልታይ ልታይ የማይሉ እግዚአብሔርን ብቻ እያሰቡ የሚያገለግሉ ብዙ ልጆች አሉ ። ፍቃድሽ ከሆነም በኋላ ወስጄ አሳይሻለው ።
ሰንበት ትምህርት ቤት ከመግባቴ በፊት አ ስተሳሰቤ ልክ እንዳ አንቺ ነበር ። ኧረ እንደውም ካንቺም ይከፋ ነበር ። ወንዶቹ ቁማርተኞች ሴቶች የሚኳኳሉ ሱሪ የሚለብሱ እያልኩ አማርር ነበር ።
እኔ እንደውም የሰንበት ተማሪ ሳይ እዩት ይሄን አስመሳይ እዩዋት ይቺን አስመሳይ እያልኩ እቀልዳለው ። እንደውም ሁለት ልጆችን አስታውሳለው አንዱ የጓደኛዬ ጓደኛ ሲሆን ሁለተኛዋ ደግሞ በስልክ የማዋራት ጓደኛዬ ነበረች ሁለቱም ላይ እቀልድ ነበር ።
የጓደኛዬ ጓደኛ ስለ ዝሙት ስናወራ ኧረ እንድዚህ አይነት ወሬ አታውሩ ሲል እሺ አባ እሺ ቄሱ ሌላስ የሎትም በማለት ባለ ማወቅ በእርሱ ላይ የቀለድኩ መስሎኝ በራሴ ነፍስ ላይ እቀልድ ነበር ።
በስልክ የማዋራትን ጓደኛዬን ደግሞ በአካል ተገናኝተን ግንኙነት እናድርግ ብያት እንቢ ስትለኝ እሺ አንቺ መነኩሲት እሺ እማ ሆይ ደህና ይሰንብቱ ብያት ነበር ።
የሚገርምሽ ብዙ ልጆች ሰንበት ተማሪነታቸውን እንደማስበው በሁለት መንገድ መናገር አይፈልጉም ። አንድ የሚሰሩት ስራ ከሰንበት ተማሪ ስለማይጠበቅ ሁለት ደግሞ ሕግን ሲያከብሩ አለማውያን የሆኑ ሰዎች ስለሚያሸማቅቋቸው ።
አንድ በጣም ከምወደው የሰንበት አስተማሪዬ ሲናገር የሰማሁትን ልንገርሽ አደራ በልብሽ ውስጥም ትከዪው ።
├───────────────
├ተከታታይ መንፈሳዊ ልብ ወለድ
├───────────────
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ክፍል አስራ አራት (14)
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
𝗝𝗢𝗜𝗡
🔰@EOTC21_media🔰
🔰@EOTC21_media🔰
ክፍል አስራ አምስት 20 Like ስሞላ ይቀጥላል
10 10 ብርም ትሁን ወንድሞቸ በማርያም ልለምናቹ ያላችሁን ተባበሩኝ ያቅማችሁን ተባበሩኝ ለኔ እርዳታ ናታ እሷም በማርያም ረሃብ ላይ ነው ያለሁት ማርያምን ያቅማችሁን አግዙኝ ወንድሞቸ ልለምናቹ 🙏🙏🙏
Читать полностью…10 10 ብርም ትሁን ወንድሞቸ በማርያም ልለምናቹ ያላችሁን ተባበሩኝ ያቅማችሁን ተባበሩኝ ለኔ እርዳታ ናታ እሷም በማርያም ረሃብ ላይ ነው ያለሁት ማርያምን ያቅማችሁን አግዙኝ ወንድሞቸ ልለምናቹ 🙏🙏🙏
Читать полностью…አንች ያልታደልሽ ቤተክርስቲያን መከራሽ መቸ ቆሞ እንደምናይ። እግዚአብሄር እሱ እራሱ ይሁንሽ በእውነት። እኛ ከስልጣነ ክህነቱ ይሻርልን ይሆናል አልን እንጅ መች ጭራሽ የመንጋው ጠባቂ ይሆንልሻል አልን። ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የበላ አውሬ እንኳንስ አባቴ ልለው መቸስ እስካሁን ልቤ ተቀበለው። እጃቸው ላይ ያለው የጌታዬ መስቀል እሱ ብቻ ነው የሚታየኝ እሳቸውን ለማየት ህሊናዬ አቅቶታል። ሰው ቅድስናውም ትህትናውም አገልግሎቱም ይፋ ሲሆንበት ከንቱ ውዳሴን ሸሽቶ በረሃ ይገባል። በኛ ዘመን ግን በግድ እኔ ልሾም በግድ እኔን አመስኑኝ ሆነብን ነገሩ። አባቶቻችን ሆይ እባካችሁ እረፍት ስጡን!!! በስጋት አለቅን፤ በሰቀቅን ተጨነቅን፤ አፈርን፤ አንገታችንን እየደፋን ነው። መንግስት ገድሎ ጨረሰን፤ በረሃብ አሰቃዬን፤ በጎን ደግሞ እናንተ ሰላማችንን አትንሱን። እኛ በናንተ በኩል " ሰማዕተ ጽድቅ ብጹ አቡነ ጴጥሮስን እንናፍቃለን" ካልቻላችሁ ግን ተጨማሪ ህመም አትሁኑብን። የሰው ደም ያፈሰሰና የሰው ደም የበላ አባት አንሻም። ነውስ የቤተክርስቲያን ህግ ለመእመናን ብቻ ነው የተሰራው። እባካችሁን ተስፋ አታስቆርጡን!!! ተስፋ የምናደርጋችሁ 3 እና 4 አባቶች አላችሁ። ተስፋችንን እንዳታተፉብን እንለምናችኋለን። እኔ የራሴ ሃጢያት ለራሴ ጭንቀት መች አንሰኝና እናንተ ጭንቀት የምትሆንብን። እንለምናችኋለን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!11111
Читать полностью…🌟ቅዱስ ቁርባንን ከመቀበል በፊት የሚጸለይ ጸሎት☀️
✨✨✨አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኩሰት ከሆነች ከቤቴ (ከሰውነቱ) ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደስም፧ እኔ አሳዝኜሃለሁና፡ በፊትሀም ክፋ ሥራ ሠርችሃለሁና፡ በአርአያህና በአምሳልህ የፈጠርከው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና፤ ሥራም ምንም ምን የለኝምና፡ ነገር ግን እኔን ስለመፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፧ ስለ ክቡርመስቀልህም ማሕየዊት ስለምትሆን ስለ ሞትህ፡ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ ከኃጢአትና
ከርኩሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡ እማልድሃለሁም። የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልኩት ጊዜ ለወቀሳና ለመፈራረጃ አይሁንብኝ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ። የዓለም ሕይወት ሆይ፡ በርሱ የኀጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ። በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም፡ በመጥምቁ በዮሐንስም አማላጅነት፡ ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም፡ በሰማዕታትና ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን ✨✨
@mary21God
✨ቅዱስ ቁርባንን ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት✨
🌟🌟 ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፡ ንጹህ ሥጋህንና ክቡርደምሀን ተቀበልሁ፥ ስለኃጢአቴና በደሌ ሁሉ ማሥተሥረያ ይሁነኝ። ሰውን የምትወድ ወልድ ዋሕድ ሆይ፡ ምስጋናህን በአንደበቴ ሙላ፡ (ክብርሀን) አመሰግን ዘንድ። ቀድሞ አንተ ሰው የሆንህ፡ በርሱም የተገለጽህ እስከ ዘለዓለሙ ታድነኝ ዘንድ ነውና፧ ስለ ቅዱስ ስምህም ለዘለዓለሙ አዳንከኝ። ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፡ በአገልጋይህ በካህኑ እጅ ሥጋህንና ደምህን አንድ አድርገህ ስለሰጠሕኝ ለአንተ ምስጋና ይገበል። አመሰግንሃለሁ፡ እለምንህማለሁ ፡ ከምእመናን ጋር አንድ እሆን ዘንድ ከበጎችህም ትቆጥረኝ ዘንድ ተቀበለኝ። አሁንም ኃጢአቴን አትቁጠርብኝ፡ ለእኔ የተሰጠኝን ጸጋህንና በእኔ ያለች ረድኤትሀን አመሰግናለሁ። ዳግመኛም ጌታዬ ሆይ፡ ይህ የተቀበልኩት ሥጋሀና ደምህ ሥጋዬንና ነፍሴን እንዳያስነቅፍና እንዳያሳድፍ እለምንሃለሁ፡ እማልድሀማለሁ ፈጽሞ የሚያድነኝ አንተን መፍራትንም የሚያስረዳኝ ይሁን እንጂ፣ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለአንተ አደላ ዘንድ ያለማቋረጥሞ አመሰግንህ ዞንድ። አቤቱ ነፍሲን አንጻት፡ ስለአንተ መሥዋዕት ትሆን ዘንድ ዳግመኛም አጥራት፧ ልቤ እንዲድን መንፈስ ቅዱስ እንዲያድርበትና እንዲመላበት አድርገው:: ሥጋህንና ደምህን አምኜ ከካህናቱ እጅ ተቀብዬአለሁና ለአንተ ሞስጋና ይገባል፡ለዘላዓለሙ አሜን።🌟🌟
መጽሐፈ ቅዳሴ፡ ቅዳሴ ሐዋርያት፣ ቁ. 121-124 146-14
@mary21God
DOOBA – From 100 USDT to Big Rewards
Many users have already seen results—are you next?
💸 100 USDT can grow up to 800% on DOOBA
💸 Daily passive income with zero effort
💸 Free trading bot, stable platform, real growth
Big returns favor early movers—join today!
ሥርዓተ ቅዳሴ
ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡
፩. የቁርባን መስዋዕት፡- በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ
ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡
፪. የከንፈር መስዋዕት፡- ካህኑ፣ ዲያቆኑና
ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡
፫. የመብራት መስዋዕት፡- በቅዳሴ ጊዜ
የሚበራው ጧፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨለማ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡
፬. የዕጣን መስዋዕት፡- የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበርእንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያለውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡
፭. የሰውነት መስዋዕትነት፡- በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዙሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡
ይህ የፀሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል
፩. የዝግጅት ክፍል
፪. የንባብና የትምህርት ክፍል
፫. ፍሬ ቅዳሴ እነዚህ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ ናቸው ። እነዚህም፡-
፫.፩. ሥርዓተ ቅዳሴ
፫.፪. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
፫.፫. ቅዳሴ እግዚእ
፫.፬. ቅዳሴ ማርያም
፫.፭. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
፫.፮. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
፫.፯. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
፫.፰. ቅዳሴ ባስልዮስ
፫.፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፫.፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
፫.፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
፫.፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
፫.፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
፫.፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
የጌታችን በዓል ከሆነ (ቅዳሴ እግዚእ)
የጌታችን ምጽአት፣ ጷጉሜ እሁድ ቀን ከዋለች ሰንበት (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)
ቅዳሴን ለመቀደስ ብዙ ጊዜ ፭ ሆነው ይቀድሳሉ ይህውም የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሣሌ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከዚያም በሚያንስም ሆነ በሚበዛ ሰው ቅዳሴን መቀደስ ይቻላል ለምሳሌ ፯ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ይመስላሉ። ፲፫ በ12ቱ ሐዋርያት እና በጌታችን ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ፤ ፳፬ በሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይህ የሚሆነው እንደ ካህናቱ ብዛት ነው ጭራሽ ካህን ከጠፋ ደግሞ ፩ ቄስና ፩ ዲያቆን ሆነው መቀደስ ይችላሉ ሁለትነታቸው የመለኮትና የትስብዕት (የሥጋ) ምሳሌ ሆነው ይቀድሳሉ በሦስት ከሆነ በሦስቱ ሥላሴዎች አራት ከሆኑ በ4ቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ ከሁለት ባነሰ ግን 1 ሆኖ ግን ቅዳሴ አይቀደስም ቀኖናው የቤተክርስቲያኒቱ ሥርዓት ይከለክላል፡፡
“ጸልዩ” ይህ የቅዳሴው የፀሎት ዓይነት ሲሆን ለ13 ጊዜያት ይባላል፡፡ በሦስተኛው ክፍለ ቅዳሴ ፬ ጊዜ ይባላል ፀልዩን ዲያቆኑ ሲያውጅ ፊቱን ወደ ህዝቡ ይመልስና እንዲጸልዩ ያውጃል፡፡ በዚህ ጊዜ ተሰጥዖ ካለ ተሰጥዖ ይመለሳል ከሌለ ግን “አቡነ ዘበሰማያት” ሕዝቡ እንዲደግሙ ያውጃል፡፡
ለምሳሌ፡-
ንፍቁ ዲያቆን “ፀልዩ በእንተ እለያበዕኡ መባዕ መባን ስለሚያገቡ ሰዎች ፀልዩ” ሲል በዚህ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት አይደገምም ምክንያቱም የራሱ ተሰጥዖ ስላለው “ተወከፍ መባዖሙ ለአሃው ወተወከፍ መባዖን…” ይህ አቡነ ዘበሰማያት የሚተካ ፀሎት ነው፡፡
ድርገት ሲወርዱ “ፀልዩ በእንቲአነ” በሚባልበት ጊዜ እንድንጸልየው የሚያዘው የዳዊትን መዝሙር 150ኛውን መዝሙርነው፡፡ ፀልዩ ብሎ ያዘዘው በዚህ ክፍል ያል የዳዊትን 150ኛውን የመዝሙር ክፍል ነው ማለት ነው፡፡
እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር
1ኛ የኃጢአት ሥርየት ይገኛል ምክንያቱም በአንቃዕዶ ሕሊና ይቅርታን ስለሚጠይቅ፣
2ኛ በነፍስም በስጋም በረከትን ያገኛል፣
3ኛ ጸሎቱም ይደመጣል፣
4ኛ የመላእክትን በረከት በቀጥታ እንሳተፋልን ቅዳሴን አስቀድሶ ሥጋ ወደሙ መቀበል የዘለዓለምን በረከት ያስገኛል፡፡
በተጨማሪም ቅዳሴ በማስቀደስ 4 ነገሮች ይገኛሉ እነዚህም፡-
፩. ትምህርት
የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ እና የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ትምህርት በቅዳሴ ጊዜ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የማርያምን ቅዳሴ አባ ሕርያቆስ የደረሰውን ይህን ቅዳሴ ሲቀደስ በውስጡ ምሥጢረ ሥላሴ፣ እና ምሥጢረ ሥጋዊ እና ነገረ ማርያምን አምልቶ ይነግራል፡፡
፪. ታሪክ
14ቱንም ቅዳሴ የሚያስቀድስ ሰው የቤተክርስቲያንን ታሪክ በቅዳሴ ውስጥ እንማራለን፡፡
፫. ምክር
በቅዳሴ ውስጥ ተፋቀሩ፣ መጽውቱ፣ ተስማሙ፣ ጹሙ፣ ጸልዩ እየተባለ በቅዳሴ ውስጥ ሰፋ ባለ መልኩ ምክር ይሰጣል ስለዚህ ቅዳሴን በማስቀደስ ምክርን ማግኝት ይቻላል ማለት ነው፡፡
፬. ተግሣጽ
ቅዳሴ ውስጡ ተግሣጽን ይዞ እናገኝዋለን ለምሳሌ በቅዳሴ እግዚእ ላይ ከወንድሙ ጋር የተጣለ ቢኖር ይተውለት ይላል በዚህ የቅዳሴ ክፍል ውስጥ ራሳችንን ምን ላይ እንደቆምን ከሰዎች ጋር ያለንን ኅብረት ስምምነት ለፈጣሪ ራሳችንን ማስገዛታችንን እየገሠፀ ይነግረናል፡፡ እነዚህን መሠረታዊ የሆኑትን ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ቅዳሴ በማስቀደስ እናገኛቸዋለን፡፡
#የቅዱስ_ያሬድ_ሌሎች_መጠሪያ_ስሞች
፠ ጥዑመ ልሳን፤
፠ የሱራፌል አምሳያ፤
፠ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤
፠ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤
፠ መዓርዒረ ዜማ፤
፠ ካህን (ካህነ ስብሐት)
፠ ማኅሌታይ፤
፠ መዘምር ዘበድርሳን፤
፠ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት)
፠ ዓርከ ሊቃውንት፤
፠ ደራሲ፤
፠ የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ)
፠ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤
፠ የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ
፠ ልዑለ ስብከት፤
፠ ሰማዕት፤
፠ ባሕታዊ፤
፠ መናኝ
፠ የዜማ አባት፤
፠ የኢትዮጵያ ብርሃን፡፡
፠ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ::
፠ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ
፠ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ::
፠ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ::
፠ አእምሮው የመጠቀ፤
፠ ድርሰቱ የተራቀቀ፤
፠ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ ማን እንደርሱ:: …...
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
መላእክት ምስጋናቸው እረፍታቸው ፣እረፍታቸው ምስጋናቸው ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግናሉ፡፡
ቤተክርስቲያንም አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናትና ይህን አብነት በማድረግ ልዑል እግዚአብሔር ሃያ አራት ሰዓት የሚመሰገንበትን የምስጋና ሥርዓት ዘርግታለች፡፡
ሕያው እግዚአብሔር የአዳም ልጆች በመላእክት ምስጋና
እንዲያመሰግኑት በመውደዱ ሰማያዊውን ምስጋና ይማር
ዘንድ ቅዱስ ያሬድን መረጠ፡፡
ማህሌታዊው ቅዱስ ያሬድ የመላእክት የምስጋናውን እንጀራ
ያበላን የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ እንቁ ነው።
በረከቱ ይደርብን!
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
#መልካም ቀን
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ዋው በጣም ደስ ይላል ኦርቶዶክስ ለዘለአለም ትኑር ወንድሜ ወደ ኦርቶዶክስ በመምጣት በጣም ደስ ብሎኛል በርታ እኛም እናግዝ አለን
Читать полностью…ተመሰጌን
የበፊቱ ፓስተር የአሁኑ ባለማዕተብ ተሙ!
ለ34 ዓመት በፕሮቴስታንት ውስጥ ቆይቷል
ለአንድ አመት በጥሞና ቆይቷል። ለ interview ሲጠየቅ እራሱ መጀመሪያ ክርስትናን ልኑረው ነው መልሱ።
ተሙ ሁለት ቸርች ከነምዕመኑ ያስጠመቀ ጀግና ነው።
ክርስቶስ ስለበራልኝ ነው ወደ ኦርቶዶክስ የመጣሁት በማለት መስክሯል። እንዲህ በማለት.......
"ፕሮቴስታንት ጋር አብዛኛው ጊዜ ቸርች የግለሰብ ነው ነገር ግን እውነተኛ ቸርች የግለሰብ ሳይሆን የክርስቶስ ነው ።
እሮብ እኮ ፓስተር እከሌ ይመጣል ተብሎ ይኬዳል ስለዚህ ህዝቡ የሚሄደው ነቢይ ደመቀን ወይም ኢዩ ጩፋን ለመቀበል እንጂ ኢየሱስን ለመቀበል አይደለም።
አሁንም መምጣት የሚፈልጉ አሉ ነገር ግን እንደሚታወቁ ደሞዝ ይከፈላቸዋልና ስንወጣ ምን እንሆናለን ነው የሚይአሳስባቸው።
በዚህ አጋጣሚ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጀት መድባ ትልቅ ሥራ ብትሰራ ደስ ይለኛል። ምክንያቱም ከመጡ ቸርቻቸውን ዘግተው ነው የሚመጡት ሌላ ስራ የላቸውም።
የፕሮቴስታንት ቸርች ጭስ አልባ ኢንዱስትሪ ነው።
ብዙኦች ገና ይመጣሉ ትዝታው እራሱ ይመጣል አይታችሁት እንደሆነ የእሱ ትችት የክርስቶስ ትምህረት ላይ ሳይሆን በግለሰብ ነው። ኦርቶዶክስ ደግሞ በግለሰብ አትለካም እኛ ሰዎች ደካማ ነን አንድ ጳጳስ ፣ አንድ ቄስ ሳተ አንድ ዲያቆን ተሳሳተ ማለት ኦርቶዶክስ ተሳሳተች ማለት አይደለም።
በዚህ አጋጣሚ የኦርቶዶክስ ወጣቶች ጀግና ናቸው፣ ዘመዴ፣ ወገኔ የምላቸው የበፊት ጓደኞቼ ሁሉ የእግዚአብሔር ሰላምታ እራሱ ሲነፍጉኝ ኦርቶዶክሳዊያን ግን በፍቅር ወደ እውነተኛው የክርስቶስ ህብረት እንድጨመር ምክንያት ሆኖዉኛል"
በማለት ገልጿል። በርታ! 💪
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo
ከቅዳሴ ጋር በተያያዘ፣ የልጅነት ትዝታዬ ከሆኑት መካከል፣ ከጓደኞቼ ጋር ተሰብስበን ወደ ደብራችን ለቅዳሴ ስንሄድ ደወል ከሰማን “አሐዱ” ሳይባል ቤተ መቅደስ ውስጥ ለመግባት የምንሮጠው ሩጫ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስላድግን ነው መሰለኝ፣ ለቅዳሴ የተለየ ፍቅር አለኝ፡፡ ሠራዒው ካህን መጽሐፈ ቅዳሴው በሚያዝዘው መሠረት ሁለቱን “እጆቹን ዘርግቶ፣ ቀጥ ብሎ በመቆምና ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ”:-
አሐዱ አብ ቅዱስ (አንዱ አብ ቅዱስ ነው)፤
አሐዱ ወልድ ቅዱስ (አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው)፤
አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ (አንዱ [መንፈስም] ቅዱስ ነው)፤
እያለ ሲያዜም (በተለይ ድምጻዊ ከሆነ) እጅግ የሚመስጥና ሕሊናዬን ሰማይ አድርሶ የሚመልስ ስሜት ይሰማኛል፡፡ “አሐዱ” ሳይባል ቤተ መቅደስ ውስጥ ለመግባት ከጓደኞቼ ጋር እንሮጥ የነበረውን የልጅነት ሩጫ ሳስታውስ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ እኛ እየሮጥን ካህኑ በድምጽ ማጉያ “አሐዱ” ሲል ከሰማን፣ ዜማውን እስኪጨርስ ድረስ ባለንበት ቦታ ቀጥ ብለን እንቆማለን፡፡ ለምን እንደምንቆም የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራኖቻችንን ስንጠይቅ "ካህኑ አሐዱ በሚልበት ሰዓት ኅብስቱና ወይኑ ወደ ጌታ ሥጋና ደም ስለሚለወጥ ነው” የሚል መልስ እንደሰጡን አስታውሳለሁ፡፡ ቀሲስ ፍቅረ መለኮት ስለ ቅዳሴ ሲያስተምሩን፣ ይህ ጥያቄ ተነስቶ የሰማሁትን መልስ ስነግራቸው የሚከተለውን አስደናቂ ማብራሪያ ሰጡኝ፡-
"አይ ፍቅርተ ኢየሱስ! ምክንያቱ ይህ አይደለም፤ ኅብስቱና ወይኑ የጌታ ሥጋና ደም ወደ መሆን የሚለወጡት በቅዳሴው ሦስተኛ ከፍል (የአማንያን ቅዳሴ/አኰቴተ ቊርባን) ካህኑ ወደ እግዚአብሔር አብ መንፈስ ቅዱስን በኅብስቱና በወይኑ ላይ (እንዲሁም በሁላችን ላይ) እንዲልክ በሚጸልይበት ሰዓት ነው እንጂ አሐዱ ሲባል አይደለም፡፡ እንዲያውም ግሪኮች ይህን ጸሎት Epiklësis (ጽዋዔ መንፈስ ቅዱስ) በማለት ይጠሩታል፡፡ ካህኑ አሐዱ ሲል ቆመን የምንሰማው፣ የእምነት ምስክርነት እየሰጠ ስለሆነ ያን ለማዳመጥ ነው፡፡ ሲጨርስም የእርሱ እምነት እምነታቸው ነውና ምእመናን (ሕዝቡ) ‘በአማን አብ ቅዱስ (አብ በእውነት ቅዱስ ነው)፣ በአማን ወልድ ቅዱስ፣ በአማን ውእቱ መንፈስ ቅዱስ' በማለት ይመልሱለታል፡፡"
ቅዳሴ
በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ
ገፅ 26-27
ሠላም ቤተሰብ አንድ አብረን የምንሰራ ስራ ነበር
በመንፈሳዊ ታሪክ ዙርያ ችሎታ/ተሰጥኦ ያላችሁ
የኦርቶዶክስ ልጆች ብቻ በውስጥ አናግሩኝ መንፈሳዊ ስራ አብረን እንስራ።
ለስራው በፈተና በቂ መሆናችሁን አረጋግጠን አብረን እንሰራለን
ለፈተና ለመመዝገብ Comment ላይ አሳውቁኝ
እረ ወንድሞቸ ያላችሁን ያቅማችሁን እርዱኝ ሰው ነው ለሰው ደራሽ ተባበሩኝ ወንድሞቸ ረሀብ ላይ ነው ያለሁት አግዙኝ🙏🙏
Читать полностью…እረ ወንድሞቸ ያላችሁን ያቅማችሁን እርዱኝ ሰው ነው ለሰው ደራሽ ተባበሩኝ ወንድሞቸ ረሀብ ላይ ነው ያለሁት አግዙኝ🙏🙏
Читать полностью…የጌታችን ፍጹም አምላክነት፡ ዮሐ 5፥30 {ክፍል አንድ}
ሙስሊሞችና ምሥጢረ ሥላሴን የማይቀበሉ መናፍቃን (የይሖዋ ምስክሮች፣ ወዘተ…) ከሚያነሧቸው ጥቅሶች መካከል በጣም ከተለመዱት መካከል ይህ ጥቅስ አንዱ ነው። የዮሐ 5 ፥ 30ን ምሥጢረ ሥላሴን ለማጥቃት የሚያነሡ ሰዎች በርግጠኝነት የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ዐውዱን አላነበቡትም ወይምድ ደግሞ እንደአባታቸው እንደሰይጣን ውሸታሞች ናቸው። አንድ ሰው የጌታችንን አምላክነት ለመካድ ሊሄድባቸው የሚችላቸው የመጨረሻዎቹ ጥቅሶች ማለት ይህ ጥቅስ ነው። ምክንያቱም ዐውዱን ስታነቡ መናፍቁ ላይ መልሶ ፈንድቶ የጌታችንን ፍጹም አምላክነት ስለሚያሳይ። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ደግሞ በደንብ ጥልቅ ለመግባት እሞክራለሁኝ። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን።
እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።
ወንጌለ ዮሐንስ 5 ፥ 30
🔻ሰላም Old Group ማለትም የቆየ የቴሌግራም ግሩፕ ያላችሁ በከፍተኝ ዋጋ እየገዛን ነው በነዚ አመተምህረት የተከፈተ ካላችሁ አናግሩን⬇️
✅2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣💵💵💵
✅2️⃣0️⃣1️⃣8️⃣💵💵💵
✅2️⃣0️⃣1️⃣9️⃣💵💵💵
✅2️⃣0️⃣2️⃣0️⃣💵💵💵
✅2️⃣0️⃣2️⃣1️⃣💵💵💵
✅2️⃣0️⃣2️⃣2️⃣💵💵💵
📥📥ማሳሰቢያ ❌‼️
⏬ የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ሆነ ''1000'' ሆነ '10,000'' ዋጋው እኩል ነው
እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ😘😍
😑 clear history ያልተደረገ ግሩፕ ነው የምንፈልገው
⏺ Dm
10 10 ብርም ትሁን ወንድሞቸ በማርያም ልለምናቹ ያላችሁን ተባበሩኝ ያቅማችሁን ተባበሩኝ ለኔ እርዳታ ናታ እሷም በማርያም ረሃብ ላይ ነው ያለሁት ማርያምን ያቅማችሁን አግዙኝ ወንድሞቸ ልለምናቹ 🙏🙏🙏
Читать полностью…10 10 ብርም ትሁን ወንድሞቸ በማርያም ልለምናቹ ያላችሁን ተባበሩኝ ያቅማችሁን ተባበሩኝ ለኔ እርዳታ ናታ እሷም በማርያም ረሃብ ላይ ነው ያለሁት ማርያምን ያቅማችሁን አግዙኝ ወንድሞቸ ልለምናቹ 🙏🙏🙏
Читать полностью…