ortodoxtewahedoo | Unsorted

Telegram-канал ortodoxtewahedoo - ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

3540

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ። ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 https://youtu.be/csxxAMGtC4I ለመቀላቀል http://t.me/ortodoxtewahedo

Subscribe to a channel

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

"ልበ ንፁሐ ፍጥር ሊተ እግዚኦ
‎መንፈሰ ርቱዕ ሐድስ ውስተ ከርሥዬ
‎ኢትግድፈኒ እምቅድመ ገፅከ"

‎አቤቱ ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ
‎የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ
‎ከፊትህ አትጣለኝ
🙏❤️‍🩹

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ከስንክሳር_ገጾች አንድ ቅዱስ - ሰኔ 18

አባ ድምያኖስ


አባ ድምያኖስ ተወልደው ያደጉት ግብጽ ውስጥ ነው:: ቤተሰቦቻቸው ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነት ዕድሜአቸው ቅዱሳት መጻሕፍትንና በጐ ምግባራትን ተምረዋል:: ዕድሜአቸው ወደ ወጣትነቱ ሲጠጋ ሥርዓተ መነኮሳትን ለማጥናት ወደ ገዳመ አባ ዮሐንስ ሔዱ።

ለአሥራ ሰባት ዓመታት በአጭር ታጥቀው ገዳሙን አገለገሉ። ገዳሙም ይገባሃል በሚል ዲቁና እንዲሾሙ አድርጓል። ከዚህ በኋላ ከአባቶች ተባርከው፥ ገዳሙንም ተሰናብተው ወጡ። ነገር ግን የወጡት ወደ ዓለም ሳይሆን ራቅ ወዳለ ገዳም ነው። የረድዕነት ዘመናቸውን ጨርሰዋልና አዲስ በሔዱበት ገዳም ወደ መደበኛው ገድል ተሸጋገሩ። ያም ማለት በጾም፥ በጸሎት፥ በስግደት፥ በትሕርምት፥ በትሕትናና በፍቅር ሙሉ ጊዜአቸውን ማሳለፍ ጀመሩ። በእንዲህ ያለ ግብርም ዘመናት አለፉ።

የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ አባ ጴጥሮስ በእረኝነት ሥራ የሚያግዛቸው ሰው እንዲፈለግላቸው በጠየቁት መሠረት ትምህርትም፥ ጽሕፈትም፥ በጐ ምግባራትም የተሟላለት ሰው እንደ አባ ድምያኖስ አልተገኘምና ያለፈቃዳቸው ወደ እስክንድርያ ተወስደው የፓትርያርኩ ረዳት ሆነው ተሾሙ። በረዳትነት በቆዩበት ጊዜ በወንጌል አገልግሎትና በመንኖ ጥሪት ሕዝቡንና ሊቀ ጳጳሳቱን አስደስተዋል። ልክ አባ ጴጥሮስ ሲያርፉ ሕዝቡና ሊቃውንቱ በአንድ ድምጽ አባ ድምያኖስን ለፓትርያርክነት መርጧቸዋል።

ጻድቁ ሊቀ ጳጳስ በዘመነ ፕትርክናቸው ከግል የቅድስና ሕይወታቸው ባለፈ እነዚህን ፈተናዎች በመወጣታቸው ይመሰገናሉ። ሕዝቡ ከሃይማኖታቸው እንዳይወጡና በምግባር እንዳይዝሉ ተግተው አስተምረዋል። በአካል ያልደረሱባቸውን በጦማር (በመልዕክት) አስተምረዋል። በዘመናቸው የተነሱትን መናፍቃን ተከራክረው፥ የተመለሰውን ተቀብለው፥ እንቢ ያሉትን አውግዘዋል። ከአንጾኪያ ፓትርያርክ የመጣውን የኑፋቄ ጦማር (መልዕክት) በይፋ ተቃውመው አውግዘዋል።

ለአርባ ሦስት ዓመታት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው ያገለገሉት አባ ድምያኖስ ከብዙ ትጋት በኋላ በመልካም ሽምግልና በዚህች ቀን ዐርፈዋል። ከግብጽ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ዝርዝር ውስጥም አርባ አምስተኛ ሆነው ተመዝግበዋል። ልመናቸው፥ ክብራቸው፥ ጸጋ ረድኤታቸው አይለየን።

ሰኔ 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. አባ ድምያኖስ ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
2. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
ወርኃዊ በዓላት

1. ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
2. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3. አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4. ማር ያዕቆብ ግብጻዊ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሰበበኛ አትሁን። ለጥፋትህ ማንንም ተጠያቂ አታድርግ። ለምታደርገውና ለምትናገረው ነገር ኃላፊነት ውሰድ።


cheek my bio

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እግዚአብሔር ከእኛ ከደካሞች ጋር እንደሆነ ዲያብሎስ ያውቃል እኛ ግን አናውቅም ።

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው...❤️‍🩹

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ቅዳሴ መማር የምትፈልጉ ተቀላቀሉ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ሰላም ውድ ኦርቶዶክሳዊያን እህትና ወንድሞቼ በድምፅ ብቻ መንፈሳዊ ትምህርት የሚያስተምር ላኩልኝ እባካቹ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

1ኛ/ ባይብል አንድ ጌታ እያለ እናንተ ሦስት ጌታ ለምን ትሰብካላችሁ?

ክርስቲያኖች የሚያምኑት በአንድ አምላክ ነው፣ በሦስት አማልክት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ "አንድ ጌታ" ሲል፣ ይህ ጌትነት በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠ መሆኑን እናምናለን። ይህ ማለት ሦስት የተለያዩ አማልክት አሉ ማለት ሳይሆን፣ አንድ አምላክ በሦስት አካላት ይገለጣል ማለት ነው።

ዘዳግም 6:4 "እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።" ይህንን መሠረታዊ እምነት እንቀበላለን።

ኤፌሶን 4:5 "አንድ ጌታ፥ አንድ ሃይማኖት፥ አንዲት ጥምቀት።"
ክርስቲያኖች "ጌታ" የሚለውን ቃል ለአብ፣ ለወልድ (ለኢየሱስ ክርስቶስ) እና ለመንፈስ ቅዱስ ሲጠቀሙ፣ ሦስት የተለያዩ አማልክትን ማለታቸው ሳይሆን፣ የዚህ አንድ አምላክ የተለያዩ አካላትን ማንነት ለመግለጽ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ጌታ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል (ዮሐ. 20:28፣ ፊልጵ. 2:11)። መንፈስ ቅዱስም እንደዚሁ ጌታ ተብሏል (2ኛ ቆሮ. 3:17-18)። ነገር ግን ይህ አንድነታቸውን አይከፋፍልም።

2ኛ/ ሥላሴ የሚል ቃል ባይብል ላይ ከሌለ ከየት መጣ? ለምንስ ትሰብኩናላችሁ?

"ሥላሴ" (Trinity) የሚለው ቃል በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም። ይህ እውነት ነው። ነገር ግን፣ ቃሉ ባይኖርም፣ አስተምህሮው (ዶክትሪኑ) ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ነው። "ሥላሴ" የሚለው ቃል ይህንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ በአንድ ቃል ለመግለጽ በቤተክርስቲያን አባቶች የተሰጠ ስያሜ ነው።
ለምሳሌ "መጽሐፍ ቅዱስ" (Bible) የሚለው ቃል ራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም፤ ነገር ግን መጻሕፍቱን በአንድነት ለመጥራት የምንጠቀምበት ቃል ነው። በተመሳሳይ "ሥላሴ" የሚለው ቃል አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የተባሉት ሦስቱ መለኮታዊ አካላት አንድ አምላክ መሆናቸውን ለመግለጽ የተፈጠረ ሥነ-መለኮታዊ ቃል ነው።
የምንሰብከው ቃሉን ሳይሆን ቃሉ የሚወክለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ነው።

3ኛ/ አብ ወልድ መንፈስ ቅድስ አንድ አምላክ የሚል ባይብል ላይ መረጃ አለ? ከሌለ ከየት መጣ?

አዎን፣ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ መሆናቸውን የሚያሳዩ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፤ ምንም እንኳን "አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው" የሚል አንድ ዓረፍተ ነገር ባይኖርም። አስተምህሮው ከተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተሰበሰበ ነው።

ማቴዎስ 28:19 "ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።" እዚህ ላይ "ስም" (ነጠላ) እንጂ "ስማቸው" (ብዙ) አለማለቱ አንድነታቸውን ያሳያል። ሦስቱም አካላት ተጠቅሰዋል ነገር ግን አንድ ስም ነው ያላቸው።

የአብ መለኮትነት፦ መጽሐፍ ቅዱስ በሙሉ አብ እግዚአብሔር መሆኑን ያስተምራል (ዮሐንስ 6:27፣ 1ኛ ጴጥሮስ 1:2)።

የወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ) መለኮትነት፦

ዮሐንስ 1:1, 14 "በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ... ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ።"

ዮሐንስ 20:28 ቶማስ ለኢየሱስ "ጌታዬና አምላኬ!" ብሎ መለሰለት።

ቲቶ 2:13 "የታላቁን አምላካችንንና መድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን..."

ዕብራውያን 1:8 "ስለ ልጁ ግን። አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘለዓለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።"

የመንፈስ ቅዱስ መለኮትነት፦

የሐዋርያት ሥራ 5:3-4 ጴጥሮስ ለሐናንያ "መንፈስ ቅዱስን ታታልል ዘንድ ሰይጣን በልብህ እንዴት ሞላ? ... ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አልዋሸህም።" እዚህ ላይ መንፈስ ቅዱስን ማታለል እግዚአብሔርን ማታለል እንደሆነ ተገልጿል።

1ኛ ቆሮንቶስ 3:16 "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?"

በአንድነት የሚገለጹባቸው ቦታዎች፦

2ኛ ቆሮንቶስ 13:14 "የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የእግዚአብሔርም ፍቅር፥ የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።"
እነዚህ ጥቅሶችና ሌሎችም የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነትና አንድነት ያሳያሉ። ስለዚህ ክርስቲያኖች ይህንን "አንድ አምላክ በሦስት አካላት" በማለት ያምናሉ።

4ኛ/ ነቢያት የሰበኩት አንድ አምላክ ትታችሁ ለምን (ሰው) ግለሰቦች ያስተማሩትን አስተምህሮ ትከተላላችሁ?

ክርስቲያኖች ነቢያት የሰበኩትን የአንድ አምላክ አስተምህሮ አልተዉም። እንዲያውም ያንን መሠረት አድርገው ነው እምነታቸውን የገነቡት።

ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ነቢያት የተነበዩለት መሲሕ ነው፣ እርሱም "ከዓለም አስቀድሞ ከአብ የነበረ" ቃልና የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አስተምሯል (ዮሐንስ 1:1, 17:5)። ኢየሱስ "እኔና አብ አንድ ነን" (ዮሐንስ 10:30) ብሏል። ይህ ማለት ግን ሁለት አማልክት አሉ ማለት አይደለም።

ሐዋርያትም (የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት) ያስተማሩት ከኢየሱስ የተቀበሉትንና በመንፈስ ቅዱስ የተመሩትን ነው። ስለዚህ የምንከተለው የግለሰቦች የግል አስተሳሰብ ሳይሆን፣ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠውንና በኢየሱስ ክርስቶስ የተረጋገጠውን የእግዚአብሔርን ቃል ነው። ሐዋርያት "ሰዎች" ቢሆኑም፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመጻፍና ለማስተማር በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ መሣሪያዎች ነበሩ (2ኛ ጢሞቴዎስ 3:16)።

የብሉይ ኪዳን ነቢያት ስለ እግዚአብሔር አንድነት ሲያስተምሩ፣ አዲስ ኪዳን ደግሞ የዚህ አንድ አምላክ ውስጣዊ ተፈጥሮ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሆነ የበለጠ ይገልጥልናል። ይህ ማለት የብሉይ ኪዳንን ትምህርት መተው ሳይሆን፣ በእሱ ላይ የተገነባ ተጨማሪ መገለጥን መቀበል ነው። ለምሳሌ፣ ብሉይ ኪዳን ስለ መሲሑ መምጣት ትንቢት ይናገራል፤ አዲስ ኪዳን ደግሞ ያ መሲሕ ኢየሱስ መሆኑንና ማንነቱን በዝርዝር ያሳያል።

ይህ አስተምህሮ (የሥላሴ) የሰው አእምሮ ሙሉ በሙሉ ሊመረምረው የማይችለው ጥልቅ መለኮታዊ ምሥጢር መሆኑን እንገነዘባለን። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የሚመሰክርለትን እውነት በእምነት እንቀበላለን።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Open mind ሆነህ ለመረዳት ከመጣህ ኦርቶዶክስ መልስ አላት ለሁሉም ጥያቄ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ከንግግርም ከተግባርም በፊት እዉቀትን እናስቀድም ዝም ብለን እስፖንጅ አንሁን!!!
የማንንም ንግግር አንምጠጥ የዘላለም ሂወት ነዉ የምናበላሸዉ ወገን እንቃ!?!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ጴጥሮስ እኮ በግልፅ እየሱስ አምላክ ነው ብሏል

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Ok ስላሴ የሚል ቃል መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የለም እያልክ ነው 😁

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በአጠቃላይ ስለ ማርቆስ 13:32 የኢየሱስን መለኮትነት የሚክድ ሳይሆን፣ በስጋ የመገለጡን እውነታና በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ራሱን በፈቃዱ ዝቅ አድርጎ የሰብዓዊ ባህርዩን ገደቦች እንደተቀበለ የሚያሳይ ነው። እርሱ እንደ ሰው ሲናገር፣ ያችን ሰዓትና ቀን የማወቁን ልዩ መብት ለአብ እንደሰጠ ገልጿል። ይህ ግን ከትንሳኤውና ከዕርገቱ በኋላ፣ ወደ ቀድሞ ክብሩ ሲመለስ፣ ሁሉን ነገር የማወቅ መለኮታዊ ባህሪው ሙሉ በሙሉ እንደሚገለጥ መረዳት ይቻላል።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ግን አስረዳኝ ካልክ ደግሞ ቀለል ባለ መልኩ ላስረዳህ ።

ይህንን ጥቅስ ለመረዳት ቁልፉ የኢየሱስ ክርስቶስን ሁለት ባህርያት ማስታወስ ነው፦


ሙሉ አምላክ (መለኮታዊ ባህርይ)፦ ኢየሱስ እግዚአብሔር ወልድ ነው፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት እኩልና አንድ ነው። በዚህ ባህርዩ ሁሉን አዋቂ ነው።


ሙሉ ሰው (ሰብዓዊ ባህርይ)፦ ኢየሱስ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ ፍጹም ሰው ሆነ። እንደ ሰው፣ በፈቃዱ ራሱን ዝቅ አድርጎ የሰውን ውስንነቶች ተቀብሏል (ፊልጵስዩስ 2፡5-8)።


ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ማርቆስ 13:32ን ስንመለከት፦



ኢየሱስ የተናገረው ከሰብዓዊ ባህርዩ አንጻር ነው፦ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ፣ እንደ ሰው፣ በፈቃዱ የመለኮታዊ መብቶቹን ሙሉ በሙሉ ከመጠቀም ተቆጥቧል። ይህ ማለት ደግሞ፣ በሰብዓዊ አእምሮውና እውቀቱ፣ የአባቱን እቅድ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ራሱን ለአብ አስገዝቷል። ያችን ሰዓትና ቀን የማወቁን መብት በፈቃዱ ለአብ ብቻ ትቶ ነበር።


የአላማው አካል ነበር፦ ይህ ራስን ዝቅ ማድረግና ለአብ መታዘዝ የድነት ስራው አካል ነበር። ኢየሱስ ፍጹም ታዛዥ ሰው ሆኖ መኖርን አሳይቶናል።


መለኮታዊ ማንነቱን አይቃረንም፦ ይህ ማለት ግን መለኮታዊ ባህርዩ ሁሉን አዋቂ አይደለም ማለት አይደለም። እንደ እግዚአብሔር ወልድ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በመሆኑ፣ በመለኮታዊ ማንነቱ ሁሉን ያውቃል። ነገር ግን በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት፣ ይህንን ሁሉን አዋቂነት በሰብዓዊው ማንነቱ ሁልጊዜ አልተጠቀመበትም።



በአጠቃላይ ስለ ማርቆስ 13:32 የኢየሱስን መለኮትነት የሚክድ ሳይሆን፣ በስጋ የመገለጡን እውነታና በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ራሱን በፈቃዱ ዝቅ አድርጎ የሰብዓዊ ባህርዩን ገደቦች እንደተቀበለ የሚያሳይ ነው። እርሱ እንደ ሰው ሲናገር፣ ያችን ሰዓትና ቀን የማወቁን ልዩ መብት ለአብ እንደሰጠ ገልጿል። ይህ ግን ከትንሳኤውና ከዕርገቱ በኋላ፣ ወደ ቀድሞ ክብሩ ሲመለስ፣ ሁሉን ነገር የማወቅ መለኮታዊ ባህሪው ሙሉ በሙሉ እንደሚገለጥ መረዳት ይቻላል።

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

Asredugn new yemibalew

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ኪዳነ ምሕረት የ እረፍቴ እናት

ኪዳነ ምህረት የእረፍቴ እናት
ሰላም ሆነ ባንች አማላጅነት
ንፅህት ድንኳን በእምነት ያጌጥኩብሽ
ሰላም ሆነ በአማኑኤል ልጅሽ

የብርሀን ዝናር ባይኖረኝም
በንጉስ ፊት ተሸልሜ ብቆም
በልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በምልጃሽ ነው ስሜ መቀየሩ
በልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
አሁን ስሜ ተጠርቷል በልጅሽ
ከታች በምድር እስከሰማይ ድረስ
ድርሻየ ነው ስምሽን ማወደስ(2)

ኪዳነ ምህረት የእረፍቴ እናት

የከበረ ሁነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለክብርሽ ዘማሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብየ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በሰማይ ፀሀይ
ስለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሰሰ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሰ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በልጅሽ ነው የነፍሴ ፅናቱ

ኪዳነምህረት የእረፍቴ እናት

ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያላንች እናቴ
ተዋብኩብሽ ገፄ በአንች አበራ
አንደበቴ ስምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫየ ከፈርዖን ቀንበር
ከእንግዲማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጀ አንችን ይዠዤሻለሁ

ኪዳነምህረት የእረፍቴ እናት

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
      @mary21God
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

አትፀፀት ይልቅ ተማርበት። ከስሕተቱ የተማረ ብልህ ነው። በስሕተቱ ተጸጸቶ ራሱን የሚጎዳ ሞኝ ነው።

cheek my bio🙏🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🔻ሰላም Old Group ማለትም የቆየ የቴሌግራም ግሩፕ ያላችሁ በከፍተኝ ዋጋ እየገዛን ነው በነዚ አመተምህረት የተከፈተ ካላችሁ  አናግሩን⬇️
✅2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣1️⃣8️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣1️⃣9️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣0️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣1️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣2️⃣💵💵💵


📥📥ማሳሰቢያ ❌‼️
⏬ የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ሆነ ''1000'' ሆነ '10,000'' ዋጋው እኩል ነው
እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ😘😍
😑 clear history ያልተደረገ ግሩፕ ነው የምንፈልገው


⏺ Dm

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

💸🇲 🇦 🇰 🇪  🇾 🇴 🇺 🇷  🇲 🇴 🇳 🇪 🇾  🇼 🇮 🇹 🇭  🇾 🇴 🇺 🇷  🇬 🇷 🇴 🇺 🇵 🇸 🇸 !!

🪼2023 🪼2022
🪼2021 🪼2020
🪼2019 🪼2018

🌔Ownership always prior and first!!

ያላችሁ መሸጥ ከፈለጉ "DM" ያዋሩኝ👉 ሁል ጊዜ online 🟢 ነኝ

History Clear ያሎነ ትክክለኛ Old ብቻ ነው ምፈልገው ልታደክሙኝ አትምጡ

👉🏻 🇨 🇧 🇪 
👉🏻🇹 🇪 🇱 🇪 🇧 🇮 🇷 🇷 
👉🏻🇦 🇧 🇾 🇸 🇮 🇳 🇳 🇮 🇦 
👉🏻 🇦 🇼 🇦 🇸 🇭 
👉🏻 🇨 🇴 🇴 🇵 

⚙ 2 step verification🔒 ማብራታችሁን አረጋግጡ

⚡️Fast payment
✨we send receipt screenshot after payment

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ


"ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልእኮ ፀሎት ናት።"

\<<አረጋዊ መንፈሳዊ>>\

#መልዕክት✍

    🇯 🇴 🇮 🇳 &🇸 🇭 🇦 🇷 🇪   
        ✥┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✥
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
      ❍ㅤ           ⎙ㅤ         ⌲ 
   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ         ˢᵃᵛᵉ          ˢʰᵃʳᵉ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

#ከስንክሳር_ገጾች አንድ ቅዱስ - ሰኔ 17

አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ


አቡነ ገሪማ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሮም ውስጥ ነው። ወላጆቻቸው መስፍንያኖስና ሰፍንግያ እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ። ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑ። እመ ብርሃንም ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው። ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት። ገና በልጅነቱ አባቱ ድንገት በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ። ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ፥ መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል።

አንድ ቀን ግን ከግብፅ በርሃ የተላከ ደብዳቤ ደረሰው። ላኪው አባ ጰንጠሌዎን ሲሆኑ መልዕክቱ "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሐ ና" የሚል ነበር። ንጉሥ ይስሐቅ አላመነታም ሌሊት ተነስቶ ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ። ድንገት ግን ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ጰንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው። እርሳቸውም ተቀብለው ፍኖተ አበውን አስተምረው አመነኮሱትና ዘጠኝ ሁነው ወደ ኢትዮዽያ መጡ። ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ብዙ ሲሰሩ አንዱና ታላቁ አባ ይስሐቅ (ገሪማ) ናቸው። ሰውነታቸውን በገድል ቀጥቅጠውት ቆዳና አጥንታቸው ተጣብቆ ነበር።

አንድ ቀን አባ ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ብለው ነግረዋቸው አባ ጰንጠሌዎን አዘኑ። ልምከር ብለው "ልጄ ይስሐቅ የሰማሁብህ ነገር አለና ሰዎችን አርቅልኝ" አሉ። አባ ይስሐቅ ግን "ሰዎች ብቻ አይደሉም፥ ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ (800 ሜትር) ተጠራርጎ ሸሸ። ይህንን የተመለከቱት አባ ጰንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም አቡነ ገሪማ ተብለው ቀሩ። አቡነ ገሪማ ወደ መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች "ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ" እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል።

ጻድቁ ወንጌልን፥ ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፦ ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር።ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ያፈራ ነበር።አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ። ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች። አንድ ቀን ድርሳን እየደረሱ ሊመሽ በመሆኑ ፀሐይን አቁመዋታል። ከእነዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ ጌታችን ተገልጦ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። "ስምህን የጠራ፥ መታሰቢያህን ያደረገ፥ እስከ 12 ትውልድ እምርልሃለሁ። አንተ ግን ሞትን አትቀምስም" ብሏቸው ተሰወረ። ያን ጊዜ መላእክቱ በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አድርሰዋቸዋል።

ሰኔ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ብጹዕ አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ
2. አባ ለትጹን ዐቢይ ወየዋሕ
3. አባ ዸላሞን ፈላሲ
4. ቅድስት አርሴማ ጻድቅት
5. ሰማዕታት እለ አኮራን
6. ፯፼ ፹፻ ሰማዕታት ማኅበረ ቅዱስ ተክለሃ ይማኖት
ወርኃዊ በዓላት

1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት
2. ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ
3. ቅዱሳን መክሲሞስ ወደማቴዎስ
4. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

"የቱንም ያህል በእውቀት የመንቃት ደረጃችን የላቀ ይሁን የሰው ልጅ ከራሱ አስበልጦ ስለ ሌላው ማሰብ የሚችል ብቃት የለውም።"

Cheek my bio🙏🙏

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

እሺ ፥ መግባት ያለብኝ ይመስለኛል።

ጥያቄዎችህ ላይ አንድ በአንድ እንሂድባቸው?

ጥያቄ ለክርስቲያኖች:-
1ኛ/ባይብል አንድ ጌታ እያለ እናንተ ሦስት ጌታ ለምን ትሰብካላችሁ?
2ኛ/ሥላሴ የሚል ቃል ባይብል ላይ ከሌለ ከየት መጣ? ለምንስ ትሰብኩናላችሁ?
3ኛ/አብ ወልድ መንፈስ ቅድስ አንድ አምላክ የሚል ባይብል ላይ መረጃ አለ? ከሌለ ከየት መጣ?
4ኛ/ነቢያት የሰበኩት አንድ አምላክ ትታችሁ ለምን (ሰው) ግለሰቦች ያስተማሩትን አስተምህሮ ትከተላላችሁ?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ብሮ አንተ ነህ የዘላለም ሕይወት እያጣህ ያለኸው
ጥያቄ ካለህ በግልፅ ጠይቅ
እራስህ ጠይቀህ እራስህ መልሰህ ትንሽ ይከብዳል

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

መጀመሪያ አንተ open mind ብትሆን አይሻልም

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

ለእዉነት ፈላጊወች እዉነትን ለማገኘት ለሚጥሩ open minded ሰወች ይድረስ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

መጀመርያ አይለያዩም ብለህ ነበር!

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

በደንብ አንብበዉ ተረዳዉ ወዳጄ አብ ማለት አይደል እና ታዲያ ከአባት በቀር የሚያቅ የለም ነዉ እያለህ ያለዉ መፅሀፍ ቅዱስ መለአክትም ወልድም(ልጅ) አያዉቁም ሰለዛ ቀን...

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

መፅሀፍ ቅዱስ እንደዚህ አይልም
የታል ወልድም ቢሆን አያውቅም የሚለው?

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

የስራ እድል ለምትፈልጉ ብቻ

👉 በየትኛውም የት/ት ደርጃ ላይ ያላችሁ
👉 በየትኛውም ቦታ
👉 ሌላ ሥራ እየስራችሁ ተጨማሪ ሥራ ለምትፈልጉ
👉 ኑ   አብርን ሰርተን አብረን እንደግ
ለመለወጥ አላማ እና ቁርጠኝነት ያለው ብቻ
👌 እድሉን መጠቀም እምትፈልጉ ለበለጠ መረጃ

0942525010
@widase
@widase
@widase
ለነፍስ ለስጋ የሚጠቅም በፍቅር ሰርተው በህብረት የሚያድጉበት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ምቹ የሆነ ሥራ

"ዘእንበለ ሥጋ ኢትቀውም ነፍስ"
ከልቡ መለወጥ የሚፈልግ ሰው ያናግረኝ

Читать полностью…

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ የመወያያ ግሩፕ

🔻ሰላም Old Group ማለትም የቆየ የቴሌግራም ግሩፕ ያላችሁ በከፍተኝ ዋጋ እየገዛን ነው በነዚ አመተምህረት የተከፈተ ካላችሁ  አናግሩን⬇️
✅2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣1️⃣8️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣1️⃣9️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣0️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣1️⃣💵💵💵

✅2️⃣0️⃣2️⃣2️⃣💵💵💵


📥📥ማሳሰቢያ ❌‼️
⏬ የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ሆነ ''1000'' ሆነ '10,000'' ዋጋው እኩል ነው
እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ😘😍
😑 clear history ያልተደረገ ግሩፕ ነው የምንፈልገው


⏺ Dm

Читать полностью…
Subscribe to a channel