🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🟢$ USDT በ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ⬇️
$1 USDT ~ 50 ብር
$2 USDT ~ 100 ብር
$3 USDT ~ 150 ብር
$4 USDT ~ 200 ብር
$5 USDT ~ 250 ብር
$6 USDT ~ 300 ብር
$7 USDT ~ 350 ብር
$8 USDT ~ 400 ብር
$9 USDT ~ 450 ብር
$10 USDT ~ 500 ብር
$20 USDT ~ 1,000 ብር
$30 USDT ~ 1,500 ብር
$40 USDT ~ 2,000 ብር
$50 USDT ~ 2,500 ብር
$60 USDT ~ 3,000 ብር
$70 USDT ~ 3,500 ብር
$80 USDT ~ 4,000 ብር
$90 USDT ~ 4,500 ብር
$100 USDT ~ 5,000 ብር
You need to send a message, too! For example:/welcome Hello $username, welcome to $title!
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
"ሰው ሀጥያትን ከሰው ያየዋል፤ ያይና ያደንቀዋል፤ ያደንቅና ይመኘዋል፤ ይመኝና ይሰራዋል፤ ይሰራና ይደጋግመዋል፤ ይደጋግምና ይለምደዋል፤ ይለምድና ጠባዩ ያደርገዋል፤ ጠባዩ ሲያደርገው አልለቀው ይላል ፤ አልለቀው ሲል ልቡ ይደነድናል፤ ልቡ ሲደነድን ቀኝና ግራውን የማይለይ ይሆናል ፦ ማለት ሀጥያትን ፅድቅ ይላል ፅድቅን ሀጥያት ይላል ማለት ነው።
ያ ማለት ወተት ይጠቁርበታል፤ ማር ይመርበታል፤ ሬትይጣፍጥለታል ማለት ነው። ሀጥያትን የሚያደንቅ ፅድቅን የሚተች ትውልድ የሚፈጠረው ከልብ መደንደን የተነሳ ነው። ከዚህ በኋላ ሰው... መቃወም ብቻ ይጀምራል። ጸሎት መቃወም፤ ስግደት መቃወም፤ ቅዳሴ መቃወም፤ ካህናትን መቃወም፤ ጳጳሳትን መቃወም፤ መጸሐፍትን መቃወም፤ ታዕምረ ማርያምን መቃወም፤ ገድላትን መቃወም፤ ስርአተ ቤተክርስቲያንን መቃወም፤ ምንኩስናን መቃወም። ለምን? ። ቀኝ እና ግራውን አይለይም። ልቡ ሲደነድን ሀጥያትን ያደንቃል ፅድቅን ይጠላል። የሚገርመው ደግሞ እሱ ብቻ አይደለም የሚሰራው በደል ራሱ ትክክል እንደሆነ ይሰማዋል። አስባችሁታል አይደል? ገድለው የሚፎክሩ፤ በሰው ደም ታጥበው እየበሉ እንኳን ልባቸው የማይደነግጥ ሰዎች እነዚህ ናቸው። ከዚህ ሲደርስ ነው። እግዚአብሔር እንዲህ ካለ ደረጃ አያድርሰን! "
#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ ገብር ኪዳን ካስተማሩት ትምህርት
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
አዳር ለምታድሩ መልካም ቁመት ይኹንላችኹ
በተለያዩ ምክንያቶች ማደር ላልቻላችኹ ይኽችን የማኅሌተ ጽጌ ክፍል ጋበዝኳችኹ🥰 ደኅና እደሩልኝ!😘
“እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፥🌹
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፥
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፥
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፥
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።”
ትርጉም፦
“በመንጻት ወራት በተዓምርም ቀን ወደቤተ መቅደስ ስትገቢ፥
ነጭና ቀይ አበባ የሚመስል ልጅሽን ታቅፈሽ፥
ከኀዘኔ ታረጋጊኝ/ታጽናኚኝ ዘንድ ርግቤ ኾይ ነይ፥
መልካም እናቴ ኾይ ደስ የሚል ዜና ከያዘ ከገብርኤልና፥
እንደ አንቺ ርኅሩኅ ከኾነ ከሚካኤል ጋር ነይ።”
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
በኒውዮርክና አካባቢው ግዛቶች የሚገኙ ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ዓመታዊ የአንድነት የቅዳሴ ጸሎት አከናወኑ !
ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በኒውዮርክና አካባቢው ግዛቶች የሚገኙ ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ዓመታዊ የአንድነት የቅዳሴ ጸሎት አገልግሎት በቅዱስ ኤፍሬም የማላንካራ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አከናውነዋል::
ይህ መርሐ ግብር በየዓመቱ በተሳካ መልኩ እንዲከናወን የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቋሚ ኮሚቴ የሚያስተባብር ሲሆን ዛሬ በተካሄደው የቅዳሴ ጸሎት የኢትዮጵያ፣ የሕንድ፣ የግብጽ፣ የአርመን፣ የሶርያ እና የኤርትራ አብያተ ክርስቲያናት ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት እንዲሁም ምእመናን ተሳትፈዋል::
ይህ አይነቱ የአንድነት አገልግሎት “ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” የሚለውን አስተምህሮ በተግባር የሚገልጥ ሲሆን በማጠቃለያ ላይ በተደረገው ንግግር ጉባኤው በአብያተ ክርስቲያናቱ መካከል የሚኖረውን ግንኙነት የሚያጎለብት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ተገልጿል::
ጉባኤው በየዓመቱ በጥቅምት ወር የሚካሄድ ሲሆን ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በኒውጀርሲ ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን መከናወኑ ይታወሳል።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🗣Referral Program
ለ አንድ ሰው ሲያጋሩ 1 USDT ያገኛሉ.
Earn up to 10 levels from your referrals:
Level 1: 1 USDT per invite
Level 2: 2 USDT per invite
Level 3: 3 USDT per invite
Level 4: 4 USDT per invite
Level 5: 5 USDT per invite
Level 6: 6 USDT per invite
Level 7: 7 USDT per invite
Level 8: 8 USDT per invite
Level 9: 9 USDT per invite
Level 10: 10 USDT per invite
ተጨማሪ ለመስራት ለሰዎች ያጋሩ.
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete The text contains the robot command ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete site link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
ማርያም ማለት ምን ማለት ነው❓
ማርያም ማለት፦
✅ #እግዝእት:- እመቤት ማለት ነው የዓለሙን ንጉስ በመውለዷ ከፈጣሪ በታች የፍጥረት ንግስት ሆናለችና ፤
✅ ጸጋ ዘተውኅበት ለኩሉ ዓለም :- ለዓለሙ ሁሉ የተሰጠች ጸጋ ማለት ነው። ለአበው በተስፋ የሰጣቸው ሲሆን ለእኛ ደግሞ ከመስቀሉ ሥር እናት ትሁናችሁ ብሎ ሰጥቶናልና።(ዮሐ ፲፱፤፳፮)
ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ንግሲቲቱ በቀኝህ ትቆማለች የሚለውን የዳዊት መዝሙር ሲተረጉም In becoming the mother of creator she become the Mistress of all creation (የፈጣሪ እናት በሆነች ጊዜ የፍጥረታት ሁሉ ንግስት እመቤት ሆናለችና በማለት ተርጉሞታል።(መዝ 44፤9)
✅ ተስፋ ማለት ነው:- ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ካለው ጀምሮ መድኃኒቴን የምትወልጅልኝ ልጄ እያለ ተስፋ አድርጓት በልቦናው መዝገብነት ይዟት የኖረ ስንቁ ናት።አበውም ድንግል ማርያምን መቼ ፀሐይ ክርስቶስን ወልዳልን ከቁረ መርገም ድነን አይተነው እያሉ ተስፋ አድርገዋት ነበር። ተስፋቸው ክርስቶስም ከእርስዋ ተወልዶ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ገብተዋል ። ለዚህ ምስክር የሚሆነን አረጋዊ ስምዖን - ጌታ ሆይ አገልጋይህን ዛሬ ታሰናብተዋለህ ፥አቤቱ በሰላም እንዳዘዝክ አይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና በህዝብ ፊት ሁሉ ያዘጋጀኸውን ለአህዛብ ብርሃንን ትገልጽ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ክብርን በማለት ተስፋውን አይቶ አርፏል። (ሉቃ 2፥29)
✅ የባህር ከርቤ (Myrrh of the sea) ማለት ነው። ይህ ከርቤ እጅግ ውድ ዋጋ ያለው ከዘይት ጋር ተጨምሮ ቀጠበብተ ኦሪት ተቀምሞ ለንዋያተ ቅድሳት ማክበሪያ የታዘዘ ሽቱ ነው።ሙሴ ደብተራ ኦሪቱን-በኦሪት መቅደሱ ያሉትን ሁሉበዚህ ሽቱ እንዲቀባ ታዟል።ሽቱ ያረፈባቸውን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮታል። ባህር የተባለ ይህ ዓለም ሲሆን እመቤታችንም ከእርስዋ ስጋን ነስቶ #ክርስቶስ ተብሎ ስሙ እነሰደ ዘይት ተዋህዶን ክርስቲያን ተብለን እንድንጣፍጥ የድህነት መሳሪያ የመዓዛ መንፈሳዊ ምንጭ ናትና የባህር ሽቱ ትባላለች ።
ሽቱ ያረፈበትን የነካ ሁሉ እንደሚቀደስ በልጇ ስም አምነው ተጠምቀው በእምነት የሚቀርብ ሁሉ ይጣፍጣልና ይላሉ አበው !
✅ የባህር ኮከብ (Star of the seas )ማለት ነው።ባህር የተባለ ይህ ዓለም ነው፥በባህር የሚበላም የማይበላም ደግሞ ክፉም ፍጥረት እንዳለ በዚህ ዓለምም አማኒም ከሓዲም መናFKም ጻድቅም ኃጥእም ይኖራልና፥ ዳግመኛም ባህር ከሁከት አይርቅም ይች ዓለምም ከሁከት አትርቅምና፥
በባህር ላይ ሲጓዙ በመርከብ ላይ ሆነው የንጋት ኮከብን አብነት አድርገው ከተጓዙ ካሰቡት ይደረሳል። ሰብአ ሰገልን ኮከብ እየመራ ቤተለሄም እንዳደረሳቸው ማለት ነው።እንዲሁም ሁሉ እመቤታችን በዚህ ዓለም የክህደት የኃጢአት ምገድ እንዳያጠፋን የተረፍንባት መርከባችን ናት።
✅ #ብርህት(Illuminated ) ማለት ነው። ብርሃኗ ከፀሐይ ይበልጣል ፤ መለወጥ የሌለባት የድህነት በር ናት ውበቷም በፍፁም ክብርና ሞገስ የተሸለመ ነው፤እውነት በእውነት የመና ሞሰብ ነች። ጽድልት መባሏ ነውርና ነቀፈሠ የሌለበት የእግዚአብሔር እናት በመሆኗ ነው።
✅ አሐቲ ፍቅርት :- ብቻውን የምትወደድ (Beloved One ) ማለት ነው። ንጉስ ውበትሽን ወዷልና ተብሎ የተዘመረላት እግዚአብሔር መዓዛ ድንግልናዋን ወዶ ከእርሷ ሰው እስኪሆን ድረስ ፥ ፍጥረትን ሁሉ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብቅሎ የሚመግብ ጌታ ጡቶቿን ጠብቶ እስከማደግ ድረስ ደርሶ ብቻዋን በእግዚአብሔር የተወደደች ናትና ።
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🔺Warning:\nThe robot failed to operate [ Delete link ]
.
🔸reason :
robot is not a manager
🗝️
✅72ቱ ቅዱሳን አርድዕት ስምና መታሰቢያ ቀን
1➡️ማርቆስ ዮሐንስ ወንጌላዊው===ሚያዝያ 30
2➡️እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት=====ጥር 1 እና ጥቅምት 17
3➡️ጳውሎስ ሐዋርያ==========ሐምሌ 5
4➡️ጢሞቴዎስ ወልዱ ለጳውሎስ====ህዳር 27 ና ጥቅምት 26
5➡️ሲላስ ወልዱ ለጳውሎስ=====ጥቅምት 15
6➡️በርናባስ ወልዱ ለጳውሎስ
7➡️ቲቶ ወልዱ ለጳውሎስ======ታህሳስ 18ና ጳጉሜ 2
8➡️ፊልሞና ወልዱ ለጳውሎስ====መጋቢት 7ና ሕዳር 7
9➡️ቀሌምንጦስ ወልዱ ለጳውሎስ====መጋቢት 12
10➡️ዘኪዎስ ወልዱ ለማቴዎስ====ጥር 28
11➡️ቆርነሌዎስ ወልዱ ለጳውሎስ====መስከረም 11
12➡️ቴዎፍሎስ ወልዱ ለሉቃስ====መስከረም 1
13➡️ኤውዴዎስ=========ሰኔ 21
14➡️አግናቴዎስ=========ነሐሴ 23
15➡️አናንያኖስ ዘይሰመይ ይሁዳ====ነሐሴ 3
16➡️ማልኮስ (አግሊጦስ)====መስከረም 24
17➡️ኤሌናስ (ኢተኮስ)======ሚያዝያ 16
18➡️አርሳጢስ (አርጣቦሉ)====ሚያዝያ 29
19➡️አስተራቲዎስ ሀናንያ======መጋቢት 7 እና ሰኔ 26
20➡️አርሰጦበልስ ወልዱ ለጳውሎስ=====መጋቢት 19
21➡️ጋይዮስ=======ሚያዝያ 23
22➡️እድማጥስ=======መስከረም 16
23➡️ሉኪዮስ==========ታህሳስ 29
24➡️ድዮናስዮስ========ጥር 21
25➡️መርአንዮስ (ዊይዳ)=====ነሐሴ 6
26➡️አርክቦንዮስ==========ህዳር 24
27➡️አናሲሞስ============ጳጉሜ 3
28➡️ከርላዲስ ወልዱ ለፊልጶስ=======ሐምሌ 10
29➡️አኪላስ==========መጋቢት 15
30➡️ንኪትስ (ኢያሶን)======ግንቦት 3
31➡️ቀርጾስ (ጢባርዮስ)=====መስከረም 21
32➡️ክርስቶፎሮስ (የአውሬ መልክእ ነበረው)========ሚያዝያ 2
33➡️ፊልጶስ ካልዕ=========ጥቅምት 14
34➡️ጰርኮሮስ==========ሰኔ 8
35➡️ኒቃሮና (3 ጊዜ ሞቶ የተነሳ)
36➡️ጢሞና ኡቲቦስ ረድዑ ለዮሐንስ ወንጌላዊ========ሚያዝያ 16 እና ሰኔ 8
37➡️ጰርሚና==========መስከረም 21
38➡️ኒቆላዎስ ወልዱ ለሉቃስ==========ሚያዝያ 15
39➡️ሉቃስ ወንጌላዊ ወልዱ ለዮሐንስ====ጥቅምት 22
40➡️ዮሴፍ========ነሐሴ 25
41➡️ኒቆዲሞስ=======ሚያዝያ 6
42➡️ያዕቆብ እሁሁ ለእግዚእነ====ጥቅምት 26 እና የካቲት 18
43➡️አብሮኮሮስ==========መጋቢት 1 እና ጥር 20
44➡️ሮፎስ ወይም አንሲፎሮስ======መጋቢት 25
45➡️እስክንድሮስ========መጋቢት 1
46➡️ስልዋኖስ==========የካቲት 11
47➡️ሳንቲኖስ (እንደ በቅሎ ተጎትቶ የሞተው)========= መጋቢት 5
48➡️ኢዩስጦስ========ሚያዝያ 16
49➡️አክዩቁ (አጋቦስ)=======የካቲት 4 እና ሚያዝያ 15
50➡️አፍሮዲጡ (አፍሮዲጦስ)======ግንቦት 23
51➡️አንሞስ (በጉድጋድ ጥለው ያሰቃዩት)=======ታህሳስ 9
52➡️ገማልኤል========ሐምሌ 5
53➡️አንዲራኒቆስ========ጥር 8 እና ግንቦት 22
54➡️አናንያ=============ጥቅምት 4 እና ሰኔ 27
55➡️ድርሶቅላ=============ሰኔ 7
56➡️አቄላ===============ሚያዝያ 5
57➡️ኤጴንጢስ===========ሕዳር 15
58➡️አንድራኒቆስ (ጴጥሮስ)====ሕዳር 3
59➡️ዮልያል (ዮልዮስ)=======ግንቦት 23
60➡️ጰልያጦስ============ሐምሌ 19
61➡️መርማርያን (በመጋዝ ሰንጥቀው የገደሉት)=====መጋቢት 5
62➡️ኬፋ ወልዱ ለሉቃስ=======ሰኔ 25
63➡️ኡርባኖስ ወልዱ ለቶማስ=====ሰኔ 9
64➡️ስጠክን ወልዱ ለማትያስ====ሕዳር 13
65➡️አጤሌን ወልዱ ለፊልጶስ====ጥር 12
66➡️አክሌምንጦስ ወልዱ ለያዕቆብ========ጥር 21
67➡️ሔሮድያኖስ ወልዱ ለቶማስ======ሰኔ 21
68➡️ጥርፌና ወልዱ ለታዴዎስ======ህዳር 3
69➡️ጠርፌስ ወልዱ ለበርተለሜዎስ=====መጋቢት 16
70➡️አስከሪጦስ ወልዱ ለጴጥሮስ========ሰኔ 25
71➡️ሉቅዮስ ወልዱ ለያዕቆብ ወልደዘብዴዎስ=========ህዳር 3
72➡️ሱሲ ወልዱ ለማቴዎስ======መጋቢት 9
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
" ዘመናችን ሳይፈጸም እጁን ወደኛ ዘርግቶ የሚጠራንን እንስማው ፊታችንን በፊቱ እናዋርድ፤ አቤቱ ጌታችን ሆይ እነሆ አንተን በደልን እኛን በዓይነ ምሕረት ተመልከት ፍጥረቶችህን አትጣል ፍጥረቶች ነንና ከሞት በኋላ የሚያስብህ በመቃብር ተስፋ የሚያደርግህ ማነው? እያልን ፈጥነን ንስሐ እንግባ ፤
እንኪያስ ፈጥነን ንስሐ እንግባ እሪያዎች ከሚበሉት አሰር መጥገብ አይቻለንም ፈጣሪያችንን የሰማዩን የምድሩን ያህል አንተን በደልን ላንተ ልጆች መባል አይገባንምና
ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ አድርገን እንጂ እንበለው "
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo