papael_smu_legzihabher | Unsorted

Telegram-канал papael_smu_legzihabher - ፓፓኤል

235

👳ይህ ፓፓኤል ነው :: ጥንታዊቷ ኩላዊቷ ርትዕይቷ ከመጋረጃ በስተጀርባ ገና እና ገዝፋ ያለችውን እንደ ባህር የጠለቀ እነደ ወቅያኖስ የሰፋ ሀብቷን እየጨላለፍን የምንጠጣበት ገጽ ነው። ከእኛው ጋ በጭልፋ መጠጣት የሚሻ ሰው ካለ ወደ ዚህ ገጽ ጋብዟቸው!

Subscribe to a channel

ፓፓኤል

በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በአበው ጥበብ የተሰወሩት ጥንታዊ ጥበቦች አሁን ያለውን የአለም የቴክኖሎጂ አቅምና ሀይል መቀልበስ የሚችሉ ናቸው። ይህን ስል ከስሜታዊነት ተነስቸ አይደለም ብዙ ማስረጃወች ስላሉ እንጅ። አለም አሁንም ድረስ የሀገራችን ሉአላዊነት ለመንካት እንዴት እንደሚፈራ የአደባባይ ሚስጥር ነው ይህም ምክንያቱ የህዝቦቿ ጀግንነት፤ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ የበላይነት ፤የተደራጀ አስፈሪ ጦርም ሆኖ አይደለም ፡፡
ሃገሪቱ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ ደሃ ፤ በፖለቲካ ርዕዮቷም የከሰረች ፤በየ ጊዜው በአሳደገቻቸው ልጆቿ ጡቷን የምትነከስ ምስኪን ሃገር ነች.. ጠላቶቿ ብዙ እያሉ በእየ ደጇፎቿ እያገሱ ታዲያ ግን ለማንም ወራሪ ራሷን አታስደፍርም፤ ለጠላቶቿ ግርማዋ ያስፈራል፤ በሃይል ለመጣ ወራሪ ከሃይሉ በላይ ትሆናለች፤ የነካት ሁሉ ሲፈረስ ሲቃጠል እነ የመን ና ሶርያ እነ ሊቢያ ምስክሮች ናቸው .. ይህ በተላይ ለታሪክ አጥኝወች ሆነ ለብዙወቻችን ሚስጥር ነው....ታዲያ ምንድነው የሃይል ምንጯ? ወዴትስ ነው የጥበቧ መገኛ? ደካማ ሲሏት ጠንክራ የምትገኝ፤ የወደቀች ሲሏት ሃያል ሁና የምትነሳ፤ ጠላቶቿ ብዙ ሳሉ የማትፈረስ ፤መሪወቿ ደካማ ሳሉ የማትጠፋ፤ ጠባቂወቿ ሲሸሹ የማትወርር.. እች እንቁ፣ ክቡር፣ ጽሩይ ፣ሃገር ብሔሯ ወዴት ነው? ዘመን የማይሽረው አልደፈር ባይነቷስ ከየት ነው? በለን/ብላችሁ አበውን ብትጠይቁ ? ልዩ የሆነ የመላእክት ጥበቃ ስላላት ነዉ የሚል መልስ ታገኛላችሁ... ፡፡
አበው ሲያስረዱ እንዲህ ይላሉ እግዚአብሔር ቃሉን ሲሰጥ አይወስድም፤ የተናገረውን ለዘመናት ያጸናል፤ የዘረጋውንም እጂ እስከ ልጂ ልጂ አይጥፍም.. ፤ መሬቷ በውጭ ወራሪ እንዳትመዘበር፤ የኖህ ልጂ ነገደ ካም በምርኮ እንዳይወድቅ፤ ለባርነት እንዳይገዛ፤ የእግዚአብሔር ቃል በዘሮቹ ላይ ጸንቷልና ምስኪኗን ሃገር አይነኬ አስፈሪ አደረጓታል ።
ወደ ቀደመዉ ነገራችን እንግባና
ይህም ከከርሰ ምድር ማእድናት፣
ከስነህዋ ጥበባት፣ ከህክምና ጥበብ፣ ከአስተዳደር ጥበብና ከመከላከያ ጥበብ ጋር የተዛመዱ ናቸው። እነዚህ ጥበባት የተሰወሩት በነስማዝያ ጭፍራ
ከሚመሩት ምእራባውያን ዘረፈና ሴራ ለመታደግ እንደሆነ እናምናለን።
ምእራባውያኑ እነዚህን ጥበባት
ለማግኘት ብሎም ተተኪው ትውልድ እነዚህ የአያቶቹን ጥበባት እንዳይረዳ በርካታ መረጃዎችን በርዘዋል፣ በርካታ ሺህ መፃህፍቶቻችንን ሰርቀዋል አሰርቀዋል፣ በርካታ ቅርሶቻችንንም አቃጥለዋል፣ በተሰራው ዘመን ተሻጋሪ ሴራም ኢትዮጵያዊ ስብእናችንንም ለውጠውት አሁን ላይ እነርሱን ለመሆን እየታተርን እንገኛለን።

ይህ ዘመን አብቅቶ የተሰወሩት የሚገለጡበት ዘመን እንዲመጣ የነስማዝያ ስልጣኔ ተንኮታኩቶ
የአያቶቻችን ጥበብ እንዲያንሰራራ እያንዳንዳችን እራሳችንን በኢትዮጵያዊ ስብእና በማብቃት ቅርሶቹን የሚጠብቅና ለአገር ጥቅም የሚያውላቸው መንገድ
ጠራጊ ትውልድ መገንባት አለብን። ለውጥ የሚጀምረው ከግለሰብ ነውና እራሳችንን በማብቃት ቤተሰባችን እናብቃ። በኢትዮጵያ ስብእና የበቃ
ቤተሰቦችን ማፍራት ከቻልን መንፈሳዊና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የተረዳ ንቁ ማህበረሰብ መገንባት ይቻለናል። በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ጠንካራና
ንቁ ማህበረሰብ መፍጠር ከቻልን የጥንቷን ኢትዮጵያ መገንባት እንችላለን። ስለዚህ የትንሳኤውን መንገድ እራሳችንን በጥበብና በምግባር በማብቃት እንጀምር። ያኔ በመላዉ አለም እንዲህ ይባላል "ኢትዮጽያ ተነሳች"....
አሜን ጌታ ሆይ የኢትዮጵያን ትንሳኤዋን አሳየን ፡፡

Читать полностью…

ፓፓኤል

"ሳሚ ነኝ " አስኪ ባይጠቅማችሁም ሊጠቅማችሁ ስለሚችል አስተዛዝበው ያሥተምራሉ ያልኳቸውን ከዘንድሮ የታዘብኩትን ጥቂት ነጥቦች ላጋራችሁ !


በቅድሚያ ስለ ፍቅር🚫

❓የሰው ልጅ ፍቅርን በምን ያህል ዋጋ እየተመነው እንደሆነ አልገባኝም ፥ ሰጪውም ተቀባዩም ለጆሮ በሚጣፍጥ መልኩ ተሽሞንሙነው በሚወጡ ቅንዝራም አማረኛዎች እና ዘፈኖች ታጅቦ በማሥመሠል ብቻ መኖርን የመረጥንበት ጊዜ..



ስለትዳርማ📛

❓ወንዱም ሴቷም በገንዘብ የተተመነ ቅዠታም የሆነ የትዳር ምኞት የበዛበት ጊዜ........
ልብ ማለት ያልብን ግን ጊዜው የገንዘብ እንጂ ትዳር የገንዘብ እንዳልሆነ ነበር፦

> በፊት በፊት ትዳር በጣም ይፈራና ይከበር ነበር፤ አሁን አሁን ግን እንደ አንድ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ይቆጠር ጀምሯል)


ስለ ማህበራዊ ኑሯችን🚷

❓ ዘንድሮ የማህበራዊ ኑሮ መላላት ብሶበታል... አብዛኛዎቻችን በኮረና ሰብብ በር በመዝጋት ስግብግብነትን እያጣጣምንው ነው።

> እውነት እራሳችንን ካልዋሸነው በስተቀር በፊት ተቀራርበን ከመጡብን በሽታዎች ይልቅ አሁን ተራርቀን የመጡብን ውጋት ውጋት የሆኑ #በሽታዎች የትየ ለሌ ናቸው።


ስለ ወጣቱ🔞

❓ወጣቶች ያራዳነት ጥጉ እስከምን እንደሆነ አልገባንም። አንድ ሰካራም ሰካራም እንደሆነ የሚገባን ወይ በንግግሩ ነው ወይ በአረማመዱ ነው ።

? የጊዜው ወጣትንም በድርጊቱ መገመት ይቻላል

> ወንድ ወጣቶች ዝንጥል አለሌ እነደሆንን የሚገባን በተልካሻ ምክንያት በተነሳ ፀብ ለ10 ተቧድነን ጊዜ የጣለውን አንዱን ሰው መሬት ስናስግጠው ነው፣ አሁንም እንዲሁ ተቧድነን አማረኛን እንደቅርጫት ኳስ አያንቀረቀብን ስንቅም ስናጨስ ነው።

❓ሴት ወጣቶችም ሞኛ ሞኝ እንደሆናችሁ የሚያሳብቀው ወንድ ያበደበትን እኛም እንበድበት ስትሉ ነው። ብቻ ምን አለፋን ይህ ነው የኛ የአራዳነት ጥግ..... ይህኔ እኮ 2013 እና 2014 የመከራ ዘመን ነው የሚለውን የአባቶችን ትንቢት ሰምቶ ላወራልህ ሰው ንግግሩን እንደጫት ገራባ ትቆጥሩት ይሆናል። ወገኔ እውነት እንዳሰብከው መሥሎህ ከሆነ የሞት ሞትን የሞትከው አሁን ነወ።




> እኔ አሁን ትዝብቴን ላበቃ ነው ልብ እንድትሉ የምፈልገው ግን ልታፈቅር የምትመኘውም ፣ አፍቃሪውም ፣ልታገባ የምትመኘውም ፣ባለትዳሩም ፣ እናት ጎረቤታሞችም፣ ወጣቱም... #እኔ_ከእናንተ_ባላውቅም
ታናሽ ታላቁን ቢመክር አይከፋም እና... ልላችሁ የምችለው

የመጣችሁበት መንገድ መልካም ከሆነ አጣፍጣችሁ ቀጥሉበት መጥፎም ከሆነ ባለፈ ማንነት መጥፎውን ወደኋላ ትታችሁ በአዲስ ጅማሮ በመልካም ቀጥሉት........ አያችሁ ይህን ጊዜ የምናልፈውና የኢትዮጵያንም ትንሳኤ የምናየው በዚህና በዚህ በቻ ነው።


🇪🇹 ፈጣሪ በፀጋው የኢትዮጲያን ትንሳኤ ከሚያዩት ጋር ይደምረን🙏







ማድነቅም ማጣጣልም ይቻላል

Читать полностью…

ፓፓኤል

የኮከቡ ሚስጢር.... የቀጠለ

ባለስድስት ቀንድ ኮከብ የሰለሞን ማኅተም፥ የዳዊት ኮከብ [የዳዊት ጋሻ]፥ የቴዎድሮስ ኒሻን፥ የላሊበላ ጌጥ፥ የአክሱም ጌጥ፥ የፋሲል ጌጥ፥ የይምርኀነ ክርስቶስ ጌጥ (ማኅተም) በመባል ሲጠራ አብዛኛውን ጊዜ ግን የሰለሞን ማኅተም አለያም የዳዊት ኮከብ በመባል ይታወቃል።

የዚህ ኮከብ አመጣጥ እንዲህ ነው፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚደጋገሙት ክስተቶች ውስጥ የኮከብ መታየት አንዱ ነው። ለምሳሌ ሙሴ ሲወለድ ፥ ሰለሞን ቤተመቅደስ ሲሰራና ክርስቶስ ኢየሱስ ሲወለድ የታየው ኮከብ ለአብነት ተጠቃሽ ነው። ይህ ሰለሞን አርማው አድርጎ በምኩራባት እንዲሰቀል ያዘዘው የኮከብ ቅርፅና በአገራችን ለብዙ ዘመናት የቆየው የሰሎሞናው ሥርወ-መንግስት እንደአርማ ይጠቀምት የነበረው ኮከብ ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ በፈለገ ጊዜ ከላይ በሠማይ እያበራ የቤተመቅደሱን መሥሪያ ሥፍራ የጠቆመው ኮከብ ነው።
ነብየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ የሚጠቁመውን በራዕይ ያየውን የኮከብ ቅርፅ ስሎ ቤተ መቅደሱን እንደሚሰራ አስቀድሞ ለተነገረለት ልጁ አስቀምጦታል። ልጁም ስዕሉን ተጠቅሞ ኮከቡን ከከዋክብት ለይቶ ባየው ጊዜ ኮከቡ ባበራለት ሥፍራ ላይ ቤተመቅደሱን ሰርቷል።

ወደአገራችን ስንመጣ ደግሞ የካም ዘሮች የደሸት ልጆች በታላቁ ወንዝ በግዮን (አባይ)ዳርቻ በሚዋኙበት ጊዜ ምስለ ፍቁር ወልዳንና ይሄንን ባለስድስት ጫፍ ኮከብ በግዮን ውኃ ላይ ተስሎ እንዳዩትና ከዛን ጊዜ ጀምረው የኮከቡን መውጣት በልጅ ልጆቻቸው እየተቀባበሉ በተስፋ ይጠብቁት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ላይ እናገኘዋለን። የካም ልጆች (ኢትዮጵያዊያን) የዚህን ኮከብ በሰማይ መገለጥ ሲጠባበቁ ከኖሩ በኋላ መድኅን ዓለም ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ኮከቡ በሰማይ ላይ ሲያበራ በመመ ልከታቸው ከአባቶቻቸው ጀምረው ይጠብቁት የነበረው ትንቢት እንደደረሰ በማወቅ ኮከቡን ተከትለው ቤተልሔም ድረስ በመሄድ በከብቶች በረት ለተ ወለደው ለወልደ እጓለ እመሕያው እጅ መንሻ እንደሰጡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ተጽፎልናል።

የዚህ ኮከብና የኢትዮጵያዊያን ግንኙነት የሚጀምረው ከ ሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት አስቀድሞ የኖኅ ልጅ ካም ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበትና ኮከቡን በግዮን ውኃ ላይ ከተመለከቱበት ጊዜ ነው።

እንግዲህ ከላይ ለመዳሰስ እንደሞከርኩት የእሴይ ልጅ ዳዊት የቤተመቅደሱን መሥሪያ ሥፍራ የሚያመለክተውን ኮከብ በትንቢት ካየ በኋላ በዙፋኑ፣ በጋሻውና በምኩራቦቹ ሁሉ እያስቀረፀ አስቀምጦታል። የእርሱ ልጅ ሰሎሞንም በተመሳሳይ ኮከቡን በንግስና ዙፋኑና በሌሎች ቦታወች ሁሉ ላይ ማስቀረጽ ጀመረ። ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ማክዳ (ንግስተ ሳባ ወይም ንግስተ አዜብ) የሰሎሞንን ጥበብ በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ልትፈትነው ከብዙ እጅ መንሻ ጋር ወደ ሀገረ ኢየሩሳሌም ተጓዘች።
በእንግድነቷም ጊዜም ከንጉስ ሰለሞን ጸነሰች። የእስራኤል ቆይታዋን አጠናቅቃ ስትመለስም ንጉስ እብነመለክ/አቤሜሌክ ወይም ቀዳማዊ ምንሊክን ወለደች። ንጉሥ ምኒልክ እድሜው በሃያዎቹ መጀመሪያ በሆነ ጊዜ አባቱን የእስራኤልን ንጉሥ ሰለሞንን ጎብኝቶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ብዙ ሌዋውያን ካህናትንና ታቦተ ጽዮንን ከብዙ አጃቢ አይሁዶች ጋር ይዞ መጣ። ከዚህም በኋላ ምንሊክ በኢትዮጵያ በነገሰ ጊዜ ቀድሞ በእናቱ ዙፋን ላይ ተቀርጾ የነበረውን የዘንዶ ምስል በማጥፋት ከአባቱ ያገኘውን የኮከብ ምስል በዙፋኑና በእቃዎቹ እንዲሁም በጋሻውና በቤተመቅደሶች ሁሉ ላይ ቀረጸ።

ከዚህም በኋላ ዘራቸው ከሰለሞን የሚመዘዝ የሰሎሞናዊ ሥርወ ንግስት ነገስታት ሁሉ ይህን ኮከብ እንደአርማ ይጠቀሙበት ነበር።
ይህን ይመስላል የኮከቡ አመጣጥ።

የኮከቡ ትርጉም የሰፋ ቢሆንም Element encyclopedia of secret signs and symbols ከተሰኘው የAlede Nozedar መጽሐፍ ያገኘሁትንና ሌሎችንም ተጨማሪ
ምንጮችን ተጠቅሜ ያገኘሁትን መረጃ እንዲህ በአጭሩ ፃፍኩላችሁ፦
ምስሉ ላይ እንደሚታየው እያንዳንዳቸው የኮከቡ ጉጦች (ጫፎች) የተወከሉበት ቁጥር አላቸው። ቁጥሮቹም በሁለንታ ውስጥ የሚገኙትን ፈለኮችን ይወክላሉ። ይኸውም፦
1=ጨረቃ
2=ቤነስ
3=ሜርኩሪ
4=ሳተርን
5=ማርስ
6=ጁፒተር
7=ፀሐይ ተብለው ይሰየማሉ። ይህም የሚያሳየው ምልክቱ ስለጠፈር የያዘው
ሚስጢር እንዳለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ መሀል ላይ መስቀሉ ሲጨመር የመስቀሉን ብርሃናማነት [ፀሐይነት] ያሳያል።ላመኑበት መስቀል ብርሃን ነው።ላመኑበት መስቀል የሀይል ምንጭ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ምልክቱ ለኢትዮጵያ የትንሳኤዋ አርማ ነው። በትንቢት እንደሚነገረው ይህ ኮከብ በመጨረሻው ዘመን ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው ሳልሳዊው ቴዎድሮስ ሲወለድ (ከሳምንት በፊት እንደፃፍኩት ) በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እያበራ በመታየት የትንሳኤዋን ብስራት ያውጃል ተብሎም ይነገራል...። ይሄን የሰማው ካሣ ኃይሉ የንግስና ስሙን ዳግማዊ ቴዎድሮስ በማለት ኮከቡን የአንገቱ ማዕተብ ላይ አድርጎት ነበረ ታሪክ ያወሳል ። የጀግኖቹ የሽልማት ኒሻን ሁኖም ነበር።

ኮከቡን በሚገባ ተጠቅመውበታል ተብለው በታሪክ መዛግብት የሚጠቀሱት ዳዊትና ልጁ ሰሎሞን ናቸው። በተለይ ሰሎሞን
1-የአእዋፋትን ቋንቋ ለመስማት
2- የእንሰሳትን ቋንቋ ለመስማት
3-ሰይጣንን ለማሰርና
4-መናፍስትን ለማዘዝ ይጠቀምበት ነበር።
.
በአጠቃላይ ግን ይህ ኮከብ
1-የጥንቱን የአሁኑን እና የወደፊቱን ክስተት ሚስጢር ገላጭ
2-የደኅንነት አርማ። የእግዚአብሔርንና የሰውን በመስቀሉ መታረቅ የሚገልፅ የፍቅርና የነፃነት አርማ ነው።
ወደ ላይ የሚያመለክተው ሶስት መዓዘን ሰማይን ሲወክል ወደታች የሚያመለክተው ደግሞ ምድርን ይወክላል።መስቀሉ ሰማያዊዉንና ምድራዊውን ሶስት
መዓዘን ማገናኘቱ በመስቀሉ ሰማያዊያንና ምድራዊያን መታረቃቸውን ያሳያል።
3-አእምሮን ያጎለብታል።[መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው ።መረጃውን ያገኘሁት
Element encyclopedia of secret signs and symbols ከተሰኘው
የAlede Nozedar መጽሐፍ ነው።]
4-ሁሉም አጽናፈ ዓለማት በመስቀሉ ስር እንደሆኑ ያሳያል። እነሱም፦ ሰሜን፥ ደቡብ፥ ምስራቅ፥ ምዕራብ፥ አዜብ፥ መስእ፥ ባሕርና ሊባ ናቸው።
ለተጨማሪ የተክለ ጻድቅ መኩሪያን መፅሀፍ ማንበብ ቻላል፡፡

Читать полностью…

ፓፓኤል

​​VALENTINE'S DAY
ሼር በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ❗

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም።

የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ???

ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው።

የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው።

ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት።

ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡

ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም።

እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው።

ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።

ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር።

በዚህ የሃጥያት ቀን በትንቹ ይህ ይሆናል

1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗

2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗

3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው።

Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው።

እንግዲህ ምርጫው ያንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን???

" ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። "
(ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 6)

እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel