ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
በታላቅ ኃይልና ሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
ዲያብሎስን አሰረው
አግኣዞ ለአዳም
አዳምን ነጻ አወጣው
ሰላም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ከዛሬ ጀምሮ
ኮነ
ሆነ
🕊 ፍስሃ ወሰላም
ደስታና ሰላም 🕊
"እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤"
ማቴ፳፰፥፭-፮
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ
እንኳን አደረሰህ ምትሉኝ ካላቹ😍/channel/pilupader_yeab_wedaj
◈ወዮ! እንደ ምን ያለ ስንፍና ነው?! እንደምንስ ያለ ድንቁርና ነው?! እናንተ ሰወች ስትሆኑ እግዚአብሔር " ሰውን በአርአያችን በአምሳላችን እንፍጠር ያለው ለመላእክት ነው" ስትሉ ምክንያታችሁ ምንድነው ?መላእክትስ እግዚአብሔርን አያማክሩትም ፤ የሚላቸውን ለማድመጥ ይፋጠናሉ እንጂ ።ይህን መረዳት ብትወዱ ከነብያት ኹሉ ይልቅ ስለ መላእክት ተልእኮ ግልፅ አድርጎ የተናገረው ልዑለ ቃል ኢሳይያስን አድምጡ ፤ እንዲህ ያለውን፦"ሱራፌልም በዙርያው ቆመው ነበር ፤ ለእያንዳንዱም ስድሰት ክንፍ ነበረው፤ በኹለቱ ክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በኹለቱም ክንፎቻቸው እግሮቻቸውን ይሸፍኑ ነበር"..[፩]..።
➲ከዚህ መረዳት እንደምንችለው ቅዱሳን መላእክት እግዚአብሔርን ማማከርስ ይቅርና በፊቱ ብርሃን እንኳን መቆም እንደማይቻላቸው ይልቁንም በረዓድና በመንቀጥቀጥ ኾነው በፊቱ እንደሚቆሙ ነው። ትዕዛዙን ለመፈፀም በእግዚአብሔር ፊት መቆምም የፍጡር ባህርይ ነው ።እነዚህ በዚህ ኃይለ ቃል ያለውን ምሥጢር ያልተረዱ ሰዎች ግን እንዲሁ በስንፍና ወደ ልቡናቸው የመጣውን ይናገራሉ ።እኛም ስንፍናቸውን እንጸየፈው ዘንድ ለቤተ ክርስያን ልጆችም የቃሉን አማናዊ ትርጓሜ እንናገር ዘንድ ይገባናል።
➲ስለዚህ "ሰውን በአርአያችን በአምሳላችን እንፍጠር " ብሎ የተናገረው ለማን ነው? የታላቅ ምክር መልአክ..[፪]..፣ዕፁብ ድንቅ መካሪ ፣ንግሥና የባህርይ ገንዘቡ ፣የሰላም አለቃ፣ የዘለዓለም አባት ..[፫]..፣የእግዚአብሔር አብ አንድያ ልጅ ፣ከአብ ጋር አንድ የኾነ ፣ፍጥረት ኹሉ በእርሱ ለተፈጠረው ለወልድ ካልኾነ ለማን ሊኾን ይችላል? "ሰውን በአርአያችን በአምሳላችን እንፍጠር " ያለው ለእርሱ ነው። ዳግመኛም ይህ አንቀጽ የአርዮሳውያንን [Arians] ትምህርት ከንቱ የሚያደርግ ነው። ምክንያቱም አብ ሲናገር ወልድን እንደ ተወራጅ ወይም ከእርሱ እንደሚያንስ አድርጎ "ፍጠር" አላለውምና። አንድ ባሕርይ መኾናቸውን በሚያስረዳ ንግግር " እንፍጠር " አለው እንጂ። ከዚህም በተጨማሪ ፦ "ሰውን በአርአያችን በአምሳላችን" ማለቱም ይበልጥ አንድ ባሕርይ መኾናቸውን የሚያስረዳ ኃይለ ቃል ነው። አንዳንድ መናፍቃን ደግሞ "በአርአያችን" የሚለውን ንግግር ይዘው ነገረ እግዚአብሔርን በሰውኛ አገላለጽ ሊናገሩ ይወዳሉ ።..[፬]..ነገርግን መጠኑ የማይታወቀውን ፣ምሳሌ የሌለውን፣ በባሕርዩ የማይለውጠውን፣ ግዘፍ የሌለው ረቂቁን ልክ እንደ ሰው እጅና እግር መስጠት ፍፁም ስህተት ነው።በመንፈስ ቅዱስ መሪነት..[፭]..
የተጻፈው ቃለ እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ካለመቀበልም በላይ ከዚያው ቃል ብዙ ፍርድን በራስ ላይ መጨመርን የሚተካከል ምን ስንፍና አለ? እነዚህ ሰዎች እንዲሁም ዓይናቸውን የታመሙ ሰዎች ይመስላሉ። ደዌ ዘሥጋ ያገኛቸው ሰዎች ደኅነኛውን ምግብ እንኳን ከመብላት ፊታቸውን ያዞራሉ ።ዓይናቸውን የታመሙ ሰዎችም እንደዚሁ ፀሐይን ማየት አይሹም። ከፀሐይ ብርሃን ሊያገኙት የነበረውን ጥቅምም ሳያገኙ ይቀራሉ ። ዓይነ ልቡናቸውን የታመሙ ሰዎችም ልክ እንደዚሁ የእውነት ብርሀንን የማየት ዓቅም የላቸውም ።
-------------------------------------------------
[፩]- ኢሳ.6:2
[፪]- ጌታችንንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንዳንድ ቦታ ላይ በተለይ የአበው ጽሑፍ ላይ (ለምሳሌ፦ የሰማዕቱ ዮስጢኖስ) "መልአክ" ተብሎ ልናገኘው እንችላለን ።
[፫]- ኢሳ.9:6
[፬]- በአሁኑ ሰአት ይህን የሚሉት የሞርሞኒዝም እምነት ተከታዮች ናቸው።
[፭]- "theopneustos - inspired"
➲source :
➺[ኦሪት ዘፍጥረት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ድርሳን 1-18, ድርሳን ስምንት ,ገፅ 145 እና 146]
©/channel/pilupader_yeab_wedaj
#የአውሮፓ_አህጉር_የሥያሜ_ምንጭ #ጥቁሯ_ንግሥት ፣
አፍሪ-ኢትዮጵያውያን የመሰረቷት ኃያሏ #ጢሮስ
{ክፍል-፩}
(ቱካ ማቲዎስ)
ከሠባቱ የዓለማችን ክፍል አንዷ አህጉረ አውሮፓ በውስጧም ያሉ ነዋሪዎች እራሳቸውን "አውሮፓውያን" ብለው ቢጠሩም የስያሜው ምንጭ ግን አፍሪካ ነች።
Europe የተባለችው አህጉር የጥቁሮች ቀደምት መኖሪያ ስትሆን ስፔንን ማስተዳደራቸው የሚነገርላቸው Moorish ዝርያ በሆነችው ጥቁር ንግሥት EUROPA ወይም (TYRE MACULA ) በስሟ ተሰይሟል።
በቀደመ ጊዜ Kana ' Anu ወይም Poent-ia (Phoenicians) "ፑንታዊያን" የተባሉ ጥቁር ኢትዮጵያዊ ዝርያዎች ቀደምት የአውሮፓ ሰፋሪዎች እንደሆኑና አውሮፓን ለሺኽ አመታት እንዳስተዳደሩና ሮማውያን ከመነሳታቸው በፊት ለነ Greeks, Etruscans, Carthaginians ለሥልጣኔ መነሻና አስተማሪ እንደነበሩ በታሪክ ፀሐፍት እየተደረሰበት የመጣ ሃቅ ነው።
ይኽ ′′ Europa ′′ or Oroba (P እና B የሚለዋወጥ ነው) የሚለው ቃል የመጣው Kana ' Anu Oroba ወይም "where the sun sets" (ፀሐይ ምትጠልቅበት ሥፍራ) ማለት ነው።
Oroba ወይም Europa የኢትዮጵያዊው Agenor የጥንታዊቷ Tyre ጢሮስ (Syria) ንጉሥ ሴት ልጅ ናት።
ንጉሥ አግኖር እንደሚነገረው ዝነኛና ገናና የሆነው ከባሊሎን መስራቾች አንዱ የሆነው የ Belus መንትያ ወንድም ነው።
ከጥታዊቷ Kemet የወጡና በባሕል በዝምድና የሚገናኝ ታላቅ ጥምረት ያላቸው Aetiops / Afrikains ቤተሰቦች ናቸው።
መፅሐፍ ቅዱስ ስለ "ጢሮስ" ምስረታ እንዲህ ይላል
ትንቢተ ኢሳይያስ 23÷7
"በቀድሞ፡ዘመን፡ተመሥርታ፡የነበረችው፥በዚያም፡እንደ፡እንግዳ፡ኾና፡ትኖር፡ዘንድ፡እግሮቿ፡ወደ፡ሩቅ፡ያፈለሷት፡የደስታችኹ፡ከተማ፡ይህች፡ናትን፧
8፤አክሊል፡ባስጫነች፡ከተማ፡በጢሮስ፡ላይ፡ይህን፡የወሰነ፡ማን፡ነው፧ነጋዴዎቿ፡አለቃዎች፡
ናቸው፥በርሷም፡የሚሸጡና፡የሚለውጡ፡ #የምድር_ክቡራን፡ናቸው።"
Oroba ወይም ' Eur-opa ' በግሪክ ትርጉሙ ' Large-Face ' ማለት ሲሆን እንደ አፈ-ታሪኩ ከሆነ Kena ' ani በኃላ አውሮፓ የተባለችው ንግሥት Kananu ወደብን ባጠቁት የግሪክ (Crete) መርከበኞች ታፍና በመወሰዷ የተበሳጨው King Agenor የባሕር ኃይል ቡድኑን "ጥፋቱን የፈፀሙትን የግሪክ መርከበኞች ተከታትለው ሳይዙ ወደ ሃገራቸው እንዳይመለሱ" ያዛቸዋል።
አሳዳጁ የባሕር ኃይል ቡድን የሚመራው በ Europa ወንድም Cadmus (Kadmos) ቢሆንም Oroba'ን አግኝቶ ወደ ሃገራቸው መመለስ አልቻሉም።
Cadmus የአግኖር ልጅ Thebes የተባለችውን ጥንታዊት ከተማ እንደቆረቆረና Ilir, Gal, Kelt የተባሉ ሦስት ልጆች እንደወለደ ከልጆቹ አንዱ Ilir አልባኒያዎችን (Illyrians) አስገኚ መሆኑ ይነገራል።
ባዶ እጃቸውን እንዳይመለሱ ንጉሡ አዟልና፣ በደረሱበት ቦታ ግዛቶችን እየተቆጣጠሩ ስለነበር ለጥንታዊቷና በአፈታሪክ ላይ የገነነችውን የግሪክ መካከለኛ ከተማ Thebes ምስረታ ፈር ቀደዋል።
ይኽውም የንጉሥ ልጅ የሆነችው ጥቁሯ ንግሥት Oroba መታፈን ምዕራብ፣ምስራቅና ሜዲትራንያን የአለማችን ክፍል ′′ Oroba " ከዛ በኃላ Europe ለሚለው ሥያሜ መነሻ ሆነ ማለት ነው።
#ይቀጥላል.......
(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)
#ከሠማይ_የወረደው_ምስጢራዊው_ምግብ
{{መና}} ምንድነው? አሁንስ የት ይገኛል? ሳይንሱ ምን ይላል?
[ክፍል ፩]
የገነት/የሰማይ እንጀራ፣የመላእክት ምግብ፣አምስተኛው(ከውሃ፣ከአየር፣እሳት፣አፈር) ውጪ ያለ ምስጢራዊው ንጥረ ነገር ይባላል።
#ከሰማይ_የወረደበት_ምክንያት?
በዘፀሐት ጊዜ እስራኤላውያን በሲን በረሃ ሳሉ "ራበን አሉ" ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ
ዘፀ ፲፮÷፫ "....በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚኽች ምድረበዳ አውጥታችኻል፣ በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እንጀራ ስንበላ ስንጠግብ ሳለን በግብጽ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን አሏቸው።"
ዘፀ ፲፮÷፬ "እግዚአብሔርም...እንሆ እንጀራን ከሰማይ አዘንብላችኃለሁ...የሚበቃቸውን ይልቀሙ"
#የስሙ_ስያሜ
ዘፀ 31 "...ስሙን መና ብለው ጠሩት።
ምናልባት በኛ ቋንቋ #መና ሲጠብቅ በረከት፣ስጦታ ድንገት የሚገኝ አዱኛ ይሆናል። ሲላላ "መና" ባዶ መቅረት፣ኃብት አጠራቅሞ ድንገት ማጣትን ለመግለጽ " መና ቀረሁ" መባሉ ከዚህ ምስጢራዊ ምግብ ጋር ተያይዞ የመጣ ሳይሆን አይቅርም።
እንግሊዝኛው Manna ይለዋል ይኽውም marriam-Websrmter መዝገበ ቃላት ሲፈታው "usually sudden & unexpected source of gratification,plasure or gain" ይለዋል ከኛ ጋር ተዛምዶ አለው።
ዘፀ ፲፮÷፲፭ "...ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና ርስ በርሳቸው #ይኽ_ምንድር_ነው? ተባባሉ " በዚህም "what's it?" "ምንድርነው?" "Manna" አሉት የሚሉ አሉ።
መና አማርኛ
መና (ህብስተ-መና) ግእዝ፣
ማና (መና) ትግርኛ
Ma'n Hu እብራይስጥ
በብዙ ቋንቋዎች ኦሮምኛን ጨምሮ "ማል? ማሊ? ምንድር ነው ማለት እንደሆነ የታወቀ ነው።
ምግብ ፣ mile ፣ manna የሚባሉ ቃላትም መብልን የተመለከተ ትርጉም አላቸው።
#መና_ንጥረ_ነገሩ_ምንድነው?
ዘፀ ፲፮÷፲፩ "...ማንጎራጎር ሰማሁ...ወደ ማታ ሥጋን...ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ።"
እዚህ ላይ #ሥጋ እና #እንጀራ ተብሎ የተገለፀ ቢመስልም ወረድ ብሎ ግን...
፲፫ "እንዲህም ሆነ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ ፣ ሰፈሩንም ከደኑት ፣ ማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር።
{ወደ ማታ ሥጋን ያለው ድርጭቶችን መግቧቸው ነው።(ስለ #ድርጭት በሚቀጥለው ክፍል ትንሽ እናወራለን) ፣ ማለዳም እንጀራን ያላቸው ሲነጋና ጠሉ ሲያልፍ #መና አግኝተዋል።}
፲፬ " የወደቀውም ጠል ባለፈ ጊዜ እነሆ በመሬት ላይ እንደ ደቃቅ ውርጭ ኾኖ ቅርፊት የሚመስል ደቃቅ ነገር በምድረ በዳ ታየ"
#የመና_መልክና_ዓይነቱ?
ዝፀ 31 "ርሱም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ ነው።
ዘኍ ፲፩÷፯ " ...እንደ ድንብላል ዘር ነበረ።መልኩም ሙጫ ይመስል ነበር።
#ጣዕሙ
ዘፀ 31 "....ጣዕሙም እንደ ማር ቂጣ ነው።
ዘኍ ፲፩÷፰ "...ጣዕሙም በዘይት እንደተለወሰ እንጎቻ ነበረ።"
ይለናል ይኽም ለሰው ልጆች ከሚያውቁት የተለየና እንግዳ ነገር መሆኑንና እጅግ ደቃቅ ምናልባትም ድንብላል ያኽል መጠን ያለው እንደሆነ መረዳት ይቻላል።
፲፭ "...ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና...ይኽ ምንድር ነው? ተባባሉ
#አንባቢ_በርትተህ_እንድትከተለኝ_ይሁን!
#እባክህ??
--------- #ይቀጥላል --------------
(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)
እኛ ከምናያት ከምናውቃት አለም ጀረባ የማናየውና ያልተረዳነው እጂግ ብዙ ነገሮች አሉ። ከሺ አመታት በፊት አለማችን ላይ የነበሩ እጂግ አስደማሚ ነገሮችን በመ መዝገብ ለበርካታ መቶ አመታት በብራናው ለትውልድ ያስተላለፈ የጊዮርጊስ ወለደ አሚድ ን ድርሰት በጥቂቱ።
''ወሀሎ ዖፍ ዘይሰመይ ርኩ በሀገረ ሲን ውሳጣይ ተብህለ ከ መሶበ ይሠርር ይከይዳ ለሀገር በዕላሎተ ክንፊሁ.... ''
ሲን በምትባል አገር ውስጥ ርኩ በመባል የሚታወቅ ወፍ ነበር ይህም ወፍ በበረረ ጊዜ አገሪቱን በጥላው ይርግጣጣል።
ታድያ የህ ወፍ የነገስታትን ልጆች እየነጠቀ በመውሰድ ለልጆቹ ምግብ ያስበላቸው ነበር ይላል ይህ ድንቅ መጻህፍ።
አንድ ነጋዴም ከሲን ደሴቶች ባንዱ ደሴት ሁለት የርኩ እንቁላሎች ማየቱን ገልጾ እነሱም ትላልቅ ድንኮኖች እንደሚያክሉ ተናግሯል።
ዘይቶን የምትባል በሕንድ ሀገር የምትገኝ ዚአን የምትባል ከተማ ነበረች ይላል ታድያ በዝች ሀገር አንድ እንግዳ የሆነ ልዩ ፍጥረት ነበር። ይህ ሰው ሀገሪቱን የሚያስተዳድራት ንጉስ ነበር ይላል ታድያ ይህ ሰው ሶስት አይን ያለው ሲሆን አንዱ አይን ከ ግንባሩ ላይ ነበር ይላል።
''አይድእ አሐዱ ብእሲ ዘይሰመይ ታዝብሉክ እስመ ሶበቦአ ሀበ ሀገሪነ ዳር ውሳጣይ በመልእልተ ተናሦር ሥልጣነ ኀለብ ኀበ አልቃን ዓቢይ ንጉሰ ሀገረ ዳር ርእየ በሀቤሁ ዘአልቦቱ ርእስ ብእሴ ''
ታዝልኩ የሚባል አንድ ሰው በሐለብ ሥልጣን ስር ወድቅ ሆነ በናሶር ላይ ከምችገኝ ነደር ወደምትባል አገር በገባ ጊዜ በታላቁ የዳር ንጉስ አልቃን ዘንድ ራስ የሌለው ሰው እንደነበር ይገልጻል።
ታድያ የዚህ ሰው አይኖች በሁለቱ ትክሻው ላይ ሲሆን አፉና ምላሱ ደግሞ በደረቱ ላይ ይገኝ ነበር። ታዲያ በዚህ ለገር ውስጥ የዝሆን ጀሮ ያለው ሰው እንደነበርም ይናገራል።
አዛም በምትባል ሀገረም በውስጠኛዋ ምድረ ነዳር መካከል ከ አውሬዎች መካከል እንደ ሌሎች አውሬወች አድኖ የሚበላ ፊቱ የሰው ፊት የሆነ አውሬ ነበር።
ታድያ ይህ አውሬ አዳኞች በጦር ከወጉት የነዳር ሕዝቦች በሚናገሩበት ቋንቋ ይረግማቸዋል።
ታድያ ይህ ድንቅ መጻህፍ እንዳሰፈረው... ''ሀሎ አሀደ ላሕም ዘይወፅእ እም አሀዱ ጽዮዕ በሀገረ ከዕብ በበ ዓመት '' ይላል..
መጥፎ ጠርን ካለው አንድ ባህር የሚወጣ አንድ በሬ ነበር ከባህሩ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ይወጣል ታድያ ይህ የባህር ሐይቅ ሲከፈል ይህ በሬ ፒሳ ወደተባለው የዕጽ እንጨት ዘይትነት ይለወጣል የአፍራጊያ ሰወች ይህን የዕጽ እንጨት ዘይት መርከቦቻቸውን እንዲቀቡበት ለባለ መርከቦች ይሸጡላቸው እንደነበር በምዕራፍ 23 ላይ ይገልጻል።
;'ተብህለ ከመ በምድረ ሐይቅ ሀለወት ዕጽ ለእመ ነበሩ ሰብእ ይላሕው ወያስቆቅው በታሕቴሃ ይትናገፍ ቁጽል ኢይትርፍ ወኢምንተኒ ወኢ አሀዱ ቁጽል''።
በሐይቅ ምድር አንድት ታሪካዊት ዕንጨት እንደ ነበረች ይነገራል ሰወች ከዚች ዛፍ ስር ተቀምጠው ካለቀሱ ቅጠሏ ሙልጭ ብሎ ይረግፍና ግንድዋ ብቻ ይቀራለ።
ደንደራ በተባለው አገር ጋስ የሚባል ዕንጨት ነበር ይላል እንጨቱ የሚገኝበት ቦታ ልዩ ስሙ ጽአዲ ይባላል እንጨቱ ረጂምና ሰፋፊ የለመለሙ ቀጠሎች አሉት ሰው መጥቶ አንተ ጋስ የተባልክ ዛፍ ሆይ ብሎ ከጠራው ነፋስ ይነሳና ይረግፋል የተበታተኑትን ቅጠሎች ተሰብስበው ሰውየውን ይጣሉታል።
''ወፈድፋደሰ መንክራት ዘውስተ ባህር ዘኤርትራ ሀለው''
ይህ ታላቅ ጥንታዊ መጻህፍ በኤርትራ ባህር የተፈጸሙ ነገሮች እጂግ አስገራሚና በርካቶች ናቸው ይላል......
በባህረ ኤርትራ ውስጥ ባሉት ደሴቶች ነብሮች አሉ የአውሬና የሰውን መልከ የያዙ አሳ(በቅርቡ ሜርሜድ የሚል የሆሊውድ ፊልም በዚህ ዘወገ ተሰረቷል) በነዚሁ እንደሚገኝም ይናግራል..... እያለ ይቀጥላል።
ታድያ እኒህን የመሳሱ ድንቃድንቅ ታሪኮች ብዙወቻችን ከፊልም የዘለለ በእውነታን የተመሰረተ አይመስለንም። ለዚህም ነው የ Hollywood የፊልም ኢንዱስትሪ አብዛኛው የታሪክ ጭብጥ ከእኛ ብራና ከ ዘረፏቸው መጻህፍት ነው የምንለው።
ባለ አምስት ጫፉ ኮከብ...(የደም ኮከብ)
የእኛይቱን ሃገረን ጨምሮ ከ60 ሀገራት በላይ ባለ አመስት ጫፍ ያለውን ኮከብ በሰንደቅ አላማቸው ላይ አስፍረው ይጠቀሙበታል።
ይህ የኮከብ ውክል ቅቡልነቱ እንደየ ማህበረሰቡ ቢለያይም አለምን የሚያስተሳስርበት አንድ የሆነ ድብቅ ሚስጥር አለ።
ይህ ምልክት ከ ክርስቶስ ለደት በፊት በርካት አመታትን ቀደም ብሎ በውክልና ሲውል ቆይቷል። በተለያየ አዝማናት የተለያየ ትርጉምና ውክልና ቢሰጠውም በሆሊውድ ፊልም ኢንዱስትሪው ላይ በተደጋጋሚ በሚያስብል ሁኔታ ድብቅ ሴራው በቀላሉ በማህበረሰቡ ዘንድ እንዲላመድ ማድረግ ተችላሉ።
ይህ የደም ኮከብ በመባል የሚጠራው ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ የጣኦት አምላኪወች መለያ ወይም የሰይጣን (የጥልቁ አርማ) እንደሆን በተደጋጋሚ እንሰማለን።
በጥንት የምልክት እና የአርማወች አጥኝ የሆኑ ምሁራን የራሳቸውን የጥናት ምልከታ ሲያስረዱ ይህ ኮከብ የጥንት መሰረቱ የቀደምት የተፈጥሮ አምልኮ ምሳሌ እንደሆነ ይታመናል ይላሉ።
በዚህ የኮከብ ምልክት የምትመለከው አንስት አማልክት ቅድሰቷ ወይም መለኮታዊ አምላክ በመባል ትጠራለች። ይህ ማለት ይህ ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ የሴቶች የጾታዊ ፍቅርና የውበት አምላክ ምልክት ናት ተብላ በምትታመነው ለ ቬንስ የተሰጠ ነው። በቀድሞ የእምነት ስርአት አምላኳ ቬኑስ የምትባለው ፕላኔት ልዩ ክብርና ሞገስ ያላት አማልእክት ነበረች። ቬኑስ የምስራቋ ኮከብ አሽታር እና አስታርቲ የሚባሉት ስሞቿ ከተፈጥሮ ከጸሃይና ጨረቃ ከምድር ኡደት ጋ የተዛመደ ስም ነው።
እች ቬኑስ የምትባለው ፕላኔት በየ ስምንት አመታት ባለ አምስት ጫፍ ያለው ኮከብ ሁኗ በሰፊው ሰማይ ስር ትወጣለች። ቬኑስና ኮከብ የሚመሰለው ቅርጿ የፍጹምነት የዕምነትና የጾታ ውህደት ምልክት የሆነች አማልእት በመባል ትመለክ ነበር ።
የሚደንቀው ለቬኑስ ለተባለች አማልእክት ታምራዊ ተግባር መታሰቢያ እንዲሆን ግሪካውያን የኦሎምፒክን ጨዋታ ለማዘጋጀት የስምንት አመት ዙርን ተጠቅመዋል። በአሁ ወቅት በእየ አራት አመቱ የሚከናወነው ዘመናዊ የኦሎምፒክ ውድድር በ ቬኑስ የግማሽ ዙር ታሳቢ በማድረግ እንደሚካሄዱ በ ብዙሀኑ ዘንድ አይታወቅም።
ይህ የአማልእክቷ የቬንስ ወክል ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ የ የኦሎምፒክ ይፋዊ ምልክት ሊሆንም ተቃርቦ እንደነበርና በመጨረሻው ቅጽበት አምስቱ ጫፎች የውድድሩን አንድነትና ጥምረት ለማመልከት በአምስት ክቦች መቀየሩ በብዙሀኑ ዘንድ ያልተገለጠ ሚስጥር ነው።
እኒህ የባዕድ አምልኮ ስርአት ለሺ ዘመናት ዘልቆ ዛሬም ድረስ የፖሲዶን ሶስት ጉጥ መሳሪያ የቬኑስ የሚወከለው ባለ አምስቱ ጫፍ ኮከብ የአሮጊቷ ሾጣጣ ባርኔጣ ጨምሮ በጦር ጀቶችና በወታደራዊ አርማወች ላይ ግንባር ቀደም ሆነ።
አሁን እኛ ባለንበት ዘመንም የጥልቁ ሉሲፈር አርማ እንደሆን በየ ጊዜው በተከታዮቹ በሚወጡ በ ሶስት መአዘን አርማወች ታጂቦ በግልጽ ታውጇል።
ለዚህም ነው ከ 60 በላይ የሆኑ የአለም ሀገራት በተጽኖው ውስጥ ሁነው በሰንደቁ ላይ ባለ አምስት ጫፍ ኮከብን የሚያውለበልቡት..
#መለኮታዊው_የቁጥር_ቀመር PHI=1.628
Gold Section (ወርቃማው ክፍልፋይ),Golden Mean (ወርቃማው አማካይ)፣መለኮታዊ አማካይ፣መለኮታዊው ምጣኔ በማለት ይጠሩታል።
በአርክቴክቸር፣ታሪክ፣ሥዕል፣ሙዚቃ፣ሳይኮሎጂ፣ባዮሎጂ፣Spirals፣በእፅዋት፣በዘር፣በዘረ-መል፣በእፅዋት፣በቆዳ በተለያዩ ቁሶች ላይ በአስገራሚ ሁኔታ እናገኘዋለን።
ክንዳችንን እስከ ጣታችን ጫፍ ለክተን ከክንዳችን መጋጠሚያ እስከ ትከሻችን ላለው ውጤት ብናካፍለው PHI ይሰጠናል
ሆሊውድ የወጣት ሴቶችን ማራኪነት የፊቶቻቸውን ልኬቶች ከዚህ ቁጥር ጋር ያለውን ቅርበት በመለካት እንደሚያሰሉ የታወቀ ነው።ሰውነትን ከራሳቸን እስከ እግራችን በመለካት ከእምብርታችን እስከ እግራችን ላለው ብናካፍለው ይህው...PHI ይሰጠናል።
የጭንቅላታችን ርዝመትና ስፋት መካከል ያለው Ratio...ይህው PHI ቁጥር ነው።የህብለ በራኄ (DNA) minor grove እና major ጥምዝምዝ Ratio --PHI ቁጥር ይሰጠናል።የአፍሪካ ካርታ በ Fibonacci Sequence ሲሰላ ይህን ተሃምራዊ ቁጥር ይሰጠናል።የግብፅ ፒራሚዶች፣የህንዱ ታጅ መሃል ቤተ-መቅደስ፣Parthenon,The norte-Dame of laon cathedral ከሰው ሰራሽ እንፃዎች በዚህ ቀመር ከተሰሩት ውስጥ ይገኙበታል::
የልብ ምት ምጣኔ፣በአለም ላይ ያለ የትኛውም የንብ ቀፎ የወንዶቹን ቁጥር ለሴቶቹ ብናካፍለው ይህን ቁጥር ይሰጠናል።Natutal Balance & Fit proportion ለማምጣት ሊዎናርዶ ዳቬንቺ ስዕሎቹ ላይ በተለይ ሞናሊዛን ሲስል ተጠቅሞበታል::
አንድ ብዙ ሚሆንበት ብቸኛው ክፍልፋይ ነው
የ PHI- 1.618 እና lower case 0.618 ሲሆን ግሪኮች Ophidial ይሉታል "Uniter" ወይም እራሱን የሚያድስ እውቀት።።።በጥንት ሰዎች ክብ ቅርፁ የመንፈሳዊነት ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል....Square ደሞ የአካላዊ ምልክት ቅርፅ ተደርጎ ይወሰዳል PHI ደሞ የነዚህ ሁለቱ አንድ አድራጊ ነው።
ብዙዎች Pi=3.14 እና PHI=1.618 ልዩነቱን ሳይረዱ በግብፅ ፒራሚዶች Royal Cubit (mahe) ላይ ሁለቱም ስለተጠቀሙ እንደ አንድ ይቆጥሩአቸዋል...ሰፊ ልዩነት ግን አላቸው።
PHI ቁጥር Square ብናደርገው ስኩዌሩ በአንድ ቁጥር ብቻ የሚበልጥ ብቸኛ ቁጥር ነው
√5 + 1/2=1.618
√5-1/2 = 0.618 lower case
ምሳሌ:-
A____________________B
ይህ መስመር C ላይ ቢከፈል
A_________C________B
AB=1.618 *AC
AC=1.618*CB
CB=0.618 ] of AC
AC=0.618 ] of AB
√√በተደጋጋሚ ትልቁን ለትንሹ እያካፈልን እስከቻልነው ብንቀጥል እስከመጨረሻው ይሄን ተሃምራዊ ቁጥር እየሰጠን ይቀጥላል።
0 1 1 2358 13 21 34 55 89 144 233 377 610 987....ይህ ቁጥር የመለኮት ክፍልፋይ (Fibonacci Sequence) ይሉታል ሁሉም ቁጥር የቀደሙት ሁለት ቁጥሮች ጋር ቢደመር ከቀጣዩን ይሰጠናል።
# Fibonacci_Sequence
ጂኦሜትሪካል ጥምዝ ሲሆን ድምሩን እየቀጠልን ስንመጣ ጂኦሜትሪካል ጥምዝ ቅርፅ ይሰጠናል።
987/610=0.610 ወይም 610/987=1.618 ይሰጠናል የትኞቹንም ብናሰላ ከዚህ ውጭ አይሆንም ሞክሩት::
የተፈጥሮ ቀመር ህግ የመስመሮችን መጠን ሂደትና ግንኙነት (Geometry) ማወቅ እራስን እንደማወቅ ነው።
ይሄ ቁጥር ሂሳብ ላይ ብቻ ሳይሆን በቀጥታ መስመር የተወሰነ ሳይሆን በትለያዩ አስገራሚና ውብ ቅርፆች ይገለጣል...
(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)
"የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ገፅ 60"
ከታች ያለውን ፅሑፍ ከማየትዎ በፊት photo ላይ ያለውን ያንብቡ !!
"የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ ቁጥር ሶስት ገፅ 60"
ማብራሪያ :-
በመጀመሪያ ይህ ፅሑፍ ሀይማኖትና ሳይንስን እንዴት ማየትና መለየት እንዳለበት የማያውቅ ሰው ለትንተና ሀሳብ ባይሰጠኝ ደስ ይለኛል ።
ቀጠልኩ..የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለስልጣኔ ፣ለአዳዲስ ግኝት እንዲሁም ለቴክኖሎጂ በሯ ሁልግዜ ክፍት ነው አይደለም ለዘመን አመጣሽ አስተሳሰብ ለሀይማኖት ብዝሀነት እንኳ የሚወዳደራት የለም ለሁሉም ቦታ አላት በተግባርም ከርሷ ውጪ ለሆነ ሀይማኖት በሯን ከፍታ አቀባበል አድርጋ አሳይታለች ይህን የምላችሁ ይህን እየከለከለች ለስልጣኔ በሯ ዝግ ነው የሚሉ መሠረተ ቢስ አስተያየቶች እንዳሉ ከመገንዘብ ነው ።
ቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ሁሌም አዲስ ቴክኖሎጂያዊ ግኝት ሲያመጡባት ከቴክኖሎጂው ጀረባ ስላለው ነገር ትመረምራለች ፣ ትጠይቃለች መመዘኛ አላት የማትግባባው ከቴክኖሎጂው ጋር ሳይሆን ከጀርባው ምን ይዞ ሊመጣ ነው? ምን ታስቦ ነው? ለምን ዓላማ ነው የሚውለው? የሚለውን በመመርመሯ ነው ።
እንግዲህ የፈጠራው ባለቤቶች ይህን ነገር ለምን ዓለም ላይ ማስፋፋት እንደፈለጉ ካየንና ኢትዮጵያ ሐገራችን ላይ ምን ፈልገው እንደሆነ ለማወቅ የምናደርገው አቀባበል እንዴት ነው ? እነሱ ባሰቡን ልክ ወይስ እኛ ራሳችን ይጠቅመናል ብለን አስበን ነው ?
ኢትዮጵያ በስልጣኔ ቀደምት ነበረች ከተባለ ማንም ሊክደው የመይችለው ትልቅ ሐቅ አለ ይሄውም ሁሉ ነገሯ በዚቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን የተዋጀ የተመረመረ ስለነበር ነው በ4ተኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃና በአጽብሐ ዘመነ መንግሥት ከ298-336 ዓ.ም ብሔራዊ ሀይማኖቷ ኦርተዶክስ ተዋህዶ እንደሆነ አውጃለች እንግዲህ በነዚህ ዘመናት ኢትዮጵያ በጣም ሰልጥና ነበር በ1966 የ ቀ.ኃ.ሥ መንግስትን አንኮታኩቶ ስልጣን የያዘው ደርግ ሲመጣ ነው ሁሉ ነገር ብልሽትሽት ያለው ይሄ ደግሞ ማንም የሚያውቀው የታሪክ ምስክር ነው ።
የዚህ ፈጠራ ባለቤቶች ደግሞ ኢትዮጵያን ለመምታትና በቁጥጥራቸው ስር ለማዋል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ማዳከም እና ማጥፋት እንዳለባቸው አምነው ፍኖት ከትበው እና ቀርፀው እየተንቀሳቀሱ ነው አሁን እኛ የቱ ላይ ነው የቆምነው?
እደግመዋለሁ እኛ ከስልጣኔ አይደለም ችግራችን ያን ተከትሎ ከጀርባው ስላለው ድብቅ አላማ እንጂ ለስልጣኔማ ያኔ ዓለም በሙሉ ሲያንቀላፋ ሳይንሳዊነቱ ተወዳዳሪ የሌለው የምድሪቱ ቀዳማይ ፊደልን በመቅረፅ ፣ ለመጀመሪያ ግዜ ፈረስና አህያን አዳቅሎ (hybridization) በቅሎ የፈጠሩባት ሳይንሳዊ ጠበብቶች ሀገር በመሆን ፣ ለሌላው ዓለም ከተክሎች ዝግባ ፣ ዋንዛ ከአራዊቶች ዋልያ ፣ የሜዳ አህያ ከምግብ ጤፍ እና ቡና ያሉ ድንቅ የተፈጥሮ ምርቶችን በማስተዋወቅ ፣ የዲሞክራሲ ስርዓትን ለግሪኮች ያስተማረች ቤተ-ህዝብ ፣ ቤተ-ምልክና ፣ ቤተ-ክህነት ሶስቱን የስልጣን ክፍፍል ለዓለም ያበረከተች ፣ በህክምና በተፈጥሮ ፀረ-ቫይረስ የሆኑትን ቁንዶ በርበሬ ፣ ሚጥሚጣ ፀረ-ትላትል ኮሶ ፣ መተሬ ፣ እንቆቆ እና እልፍ ዕፆችን በምድሯ አፍርታ በመድሃኒትነት በመጠቀምና ለሌላው ዓለም በማበርከት ቀደምት በመሆን የምትገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የታነፀች ሐገርን ለስላጣኔ ቦታ የላትም ማለት ስህተት ነው ።
እና የኔ ሐሳብ ኢትዮጵያ ላይ አሁን ያለው መንግስት ስለዚህ ነገር ምን ያስባል ? ቴክኖሎጂውን ከምን አንፃር ነው እንድንጠቀመው የተፈለገው ?
የተሰነዘረው ሀሳብ እንጂ ተምዘግዛጊና አውዳሚ የጦር ሚሳኤል አይደለም ሀሳብ ነው በሀሳብ መልስ ካላችሁ መምጣት ነው ።
"የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችኹ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ዅሉ ልበሱ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋራ አይደለምና፥ከአለቃዎችና ከሥልጣናት ጋራ ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዢዎች ጋራ በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋራ ነው እንጂ"
(ኤፌ ፮:፲፪)
ተፃፈ በሐብተስላሤ አባተ
ከ"ኢዛና ወ ሳይዛና" ነገስታት ከንጉስ "አርማህ" እንዲሁም ከጃንደረባ "ባኮስ" ቅድስት ሐገር ሰማይ ስር ።
Superhuman abilities,
Powerful herbs : ሰላቢላ
እርሷ ሀይል ነው የምትሰጥ : grants enhanced physical attributes , speed , endurance, strength , master all forms of unarmed combat, genius intellect , master strategies:: እነዚህን ክህሎት ትሰጣለች በእኛ ዘንድ ሰላቢላ ተብላ ትታወቃለች:: በተመሳሳይ
. ለመካን ሴት
. ለመፍትሔ
• ከዚህ በተጨማሪ እፀ አበው ፣ እፀ ዳዊት እና እፀ ሐረገወይን ዋንኛ እፅዋት ናቸው::እፀ ሐረገወይን ሊቃውንቶቻችን በተለይም የዜማ ሰዎች ድምፅ ለማሳመር ጉሮሮ ለመክፈት ይጠቀሙበታል::
• Bullet proof - ዐቃቢ ርዕስ
ጥይት የማያስመቱ መሳሪያዎችን በተለያዩ የሆሊውድ ፊልሞች ላይ ተመልክተናል:: በገሀድም አለ:: ከበርካታ ሺህ ዘመናት አንስቶ ግን አያቶቻችን ጥይት የማያስመታ መሳሪያ በሚከተሉት እፅዋት ያዘጋጁ ነበር : እፀ መፍርህ ፣ ጠምበለል፣ ዝግባ፣ ዋጊኖስ፣ ታለህ፣ የሰው ለንቋጣ ፣ ፈረስ ዘንግ ፣ ቀረፅ፣ ክትክታ ፣ እፀ ሕይወት፣ ምስሮች፣ በትረ ሙሴ ፣ ዋርካ ፣ ዶቅማ ፣ ሴት ቀስት ፣ ጥንጁት ፣ ስር ኩሉ የመሳሰሉት ናቸው::
• Anti-metal - እፀ ሳቤቅ
በተለያዩ ፊልሞች ላይ አሁንም ብረት የሚጨመድዱ ብረት የሚያቀልጡ ብረት የማይበሳው ልብሶችን ወዘተ ተመልክተናል:: ጥንት አበው ብረትን የሚፃረሩ እፅዋትን በመጠቀም ብረት ነክ መሳሪያዎችን Manipulate ያደርጉ ነበር:: ከነኝህ እፅዋት መካከል ዋነኛዋ እፀ ሳቤቅ ዋንኛዋ ናት::
ምንጮ
- ራፋቱኤል
- wikipedia
- Google
አለም ላይ ካሉ ሚስጥራዊ ቦታወች አንዱ እና ዋናው ኤረር(የረር)።
ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል እንደሚገኝ የሚነገረው እጅግ ሚስጥራዊው ኤረር ተራራ በጥቅሉ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ቦታ እንደሆነ ድርሳናት ይናገራሉ። በእርግጥ ከዚህ ከፍ ብሎም ኤረር ተራራ የአዳም ርስት ሀገር ማዕከላዊ ቦታም እንደሆነ ይነገርለታል። ኢትዮጵያ የአዳም ርስት ሀገር በምንለው ምድር ወስጥ የምትገኝ እንደመሆኗ በአዳም ርስት ሀገር አሉ ተብለው ከሚነሱ ሰባት ታላላቅ ስፍራዎች መካካል ሶስቱ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። እነዚህ ስፍራዎች የጥንታዊ ኢትዮጵያ ስልጣኔ መውጫ ለሆነው መንፈሳዊ ክፍል እንደ ማዕከል የሚያገለግሉ ነበሩ። ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች መካካል የመጀመሪያው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሲገኝ ሁለተኛው ምስራቁ የሀገራችን ክፍል ላይ የሚገኝ ሆኖ ሶስተኛው በመካከለኛው ኢትዮጵያ ላይ የሚገኝ መለኮታው ሃይል ያላቸው ቦታቸወች ናቸው ።
እንግዲህ ኤረር ከእነዚህ ሶስት ስፍራዎች አንዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የሁሉም ማዕከላዊ ቦታ ነው። ስለ ኤረር ተራራ በርካታ ንግርቶች (Myths) ይነገራሉ። ሆኖም ከእነዚህ ንግርቶች መካካል ትልቁን ስፍራ የሚይዘው አዳም ከገነት ሲመለስ ስድስቱን የክብር ዕቃዎች ከኤረር ማዕከላዊ ስፍራ አስቀምጦታል የሚለው ነው። ይህ በኤረር ተራራ ላይ የምናገኘው ማእከላዊ ስፍራ በተራራው መካካል ላይ የጉልላት ቅርጽ ይዞ ይታያል። ከዚህም ስፍራ አሁንም በርካታ መንፋሳዊ ሰዎች በስውር ይኖራሉ ። በዚህ ስፍራ እንዚህን በርካታ የሆኑ መንፈሳዊ ሰዎችን ያሰባሰባቸው ይህ ማዕከላዊ የሆነው ስፍራ ነው። በዚህ ስፍራ ላይ በግልጽ እንዲሁም በስውር ኢትዮጵያኖች እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን ያልሆኑ መንፋሳዊ ሰዎች ከአለም ዳርቻ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተሰባስበው ይገኛሉ። ንግርቱ(Myth) እንደሚለው እውነት አዳም ይዟቸው የመጣው ስድስቱ የክብር ዕቃዎች እዚህ ይሆን የሚገኙት? ይህንን ጥያቄ ይህ ትውልድ ሊጠይቀው እና እውነቱን አነፍንፎ ሊያገኝ የሚጋባ ነው።
የዚህ ሚስጥራዊ ኤረር ተራሮችን ለማወቅ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ህንጻ አሰራር ማወቅ የግድ ይላል፤ በዚህም መሰረት የህንጻ ቤተክርስቲያናችንን ተምሳሌታዊ አወቃቀር ይዘን ኤረር ተራሮች ላይ ስንሄድ ተራራው ሁለት ክፍሎችን ይዞ እናገኘዋለን፤ የመጀመሪያው ክፍል ከተራራው በላይ የሚገኘውና በአይን ሊታይ የሚችለው በሥጋ ባህሪ የሚመሰለው ክፍል ነው፤ ሁለተኛው የተራራው ክፍል የውስጠኛው ስውር ከተማ ሲሆን ይሄውም በነፍስ ባህሪ የሚወከልው ነው፤ ወደዚህ ወደ ሁለተኛው ወይንም ወደ ውስጠኛው የተራራው ክፍል ለመግባትም ልክ እንደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን በአጠቃላይ ሦስት በሮችን ይዟል፤ የመጀመሪያው በር በምስራቁ አቅጣጫ የሚገኘውና ከተራራው በላይም የቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን የሚገኝበት በር ነው፤ ሁለተኛው በሰሜናዊው የተራራው አቅጣጫ የሚገኘውና ከበላዩም በደን የተሸፈነው እንዲሁም የባህታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሚገኝበት ሲሆን ሦስተኛውና የመጨረሻው በር በደቡባዊው አቅጣጫ በኮራ ማርያም ቤተክርስቲያን በኩል ይገኛል። ወደዚህ ስውር ከተማ በምስራቁ በር ከብሔረ ህያዋን ብሎም በምድር የበቁ ታላላቅ አባቶቻችን የሚጠቀሙበት በር ሲሆን የሰሜናዊውን በር ወንድ ነገስታት እስከ አሥራ ሦስተኛው ክ/ዘመን ድረስ ሲጠቀሙበት ኖረዋል፤ ይህንን በር ለዘመናት ሲናፈቅ የኖረውና የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀውና የገዢነት ክብሩን ይዞ የተወለደው ካህኑ ንጉሥ ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ዳግም ይጠቀምበታል ተብሎም ይነገራል ፤ ሦስተኛውን በር እና በደቡባዊው አቅጣጫ በኩል የሚገኘውን በር ሴት ነገስታት ሲጠቀሙበት እንደኖሩ ።
ይሄንን አቀማመጥ ወደ ህንጻ ቤተክርስቲያናችን ስናመጣውም በምስራቁ በር ካህናት በሰሜኑ በር ወንድ ምዕመናን እንዲሁም በደቡቡ በር ሴት እና እናት ምዕመናን እንደሚጠቀሙበት ያሳያል። በዚህ ታምረኛ ኤረር ተራራ ውስጥ ከ 300 በላይ የሚሆኑ ዋሻወች እንዳሉና ከመላው አለም የመጡ ቅዱሳን መነኮሳት እግዚአብሄርን እያመሰገኑ እንደሚኖሩበት ይታመናል፡፡ በአለም ካሉት 7 ቱ ሚስጥራዊ ቦታወች 3 ቱ ኢትዮጵያ ውስጥ እነደሚገኙ ከሶስቱ አነዱም ኤረር ተራራ እንደሆን አየን፡፡ በሰሜን እና በምስራቅ የኢትዮጵያ ክፋል የሚገኙት የፈጣሪ ሚስጥራዊ ከተሞች እነማን ይሆኑ ?? በውስጣቸውስ ምን ምን የረቀቁ ሚስጥራትን ተሸክመው ይሆን? ...
ተጽኖ ፈጣሪዋ ሞናሊዛ ማን ናት?
ከ 1099 ዓም ጀምሮ የጽዮናዊዝም ህቡዕ እንቅስቃሴወችን በሚስጥር በመምራት ለ 900 አመታት እንደ ሰረ አይዛክ ኒውተን፣ ሳንድሮ ቦቲቼሊ፣ ቪክቶር ሂዩጎ፣ እና ገናናው ሊኦናርዶ ዳ ቬንች፣ ያሉ በርካታ እውቅ ተጽኖ ፈጣሪ መሪወችና አባላት አሉት።
ባለ ብዙ ዘርፉ፣ ደራሲ፣ የፊዝክስ ሊቅ፣ የሒሳብ እና የፍልስፍና ምሁር፣ ፖለቲከኛ እንዲሁም የሚስጥር ኮዶች አዘጋጂ....በረቀቀና ሚስጥራዊ በሆኑ ስእሎች የሚታወቅም ስአሊ ሊኦናርዶ ዳቪች ተጠቃሽ ነው።
አለም ላይ ካሉ ዘመን አይሽሬ ክፈለ ዘመናትን ተሻጋሪ ከሆኑ ጥቂት ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች አንዱ ሊኦናርዶ ነው። በተለይ ''ሞናሊዛ'' በተባለች የስእል ስራው አለም ያውቀዋል...
የሞናሊዛ በአለም ዙርያ መግነን ከሚስጥራዊ ፈገግታዋ ጋር የሚያያዝ እንዳልሆነ ይታወቃል። ወይም ደግሞ በብዙ የጥበብ ታሪክ ሊቃውንት ወይም በአወዛጋቢ አድናቂወቿ ምስጢራዊ ትርጓሜ ስለ ተሰጣት አይደለም።
በቀላሉ ሞናሊዛ ዝነኛ የሆነችው ሊኦናርዶ ዳ ቬንች ምርጥ ስራየ እሷ ናት ስላለ ነው።
በተጓዘበት ይዟት ይሄድ ነበር ሲተኛም ከአጠገቡ አትለየውም።
ይሁን እንጂ ብዙ የጥበብ ታሪክ ተመራማሪወች ዳ ቬንች ከሞናሊዛ ጋር የነበረው ቁርኝነት ጥበባዊ ዋጋዋ ከፍ ያለ ስለሆነ ላይሆን እንደሚችል ይጠረጥራሉ።
እንደ እውነቱ ከሆነ ስእሉ ተራ የፋሜታ የሰው ምስል ነው። ዳቬንች ለዚች ስዕል ልዩ ፍቅር የመነጨው በስእሉ ውስጥ ድብቅ መልዕክት ስላለ እንደሆነ ብዙወቹ ይናገራሉ።
ሞናሊዛ በአለም ላይ እጂግ የተጻፈላት የገነነች የከበረች ዘመን ተሻጋሪ ስዕል ነች።
ይሁን እንጂ የስዕሏ አስገራሚ ሚሰጥሮች በብዙሀኑ ዘንድ አይታወቅም። ነገር ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ አብዛኛው የአለማችን ህዝብ የስዕሏ ታላቅ ሚስጥር ፈገግታዋ እንደሆነ ነው የሚያምነው ።
ሞናሊዛን ድንቅ ካደረገበት አንዱ ምክኒያት በ ስዕላዊ ኮዲንግ ለጽዮናዊዝም ወይም ወንድማማቾች ማህበር ለዘመናት ለተከታዮቹ ሚስጥራቱን በስርአት ማስተላለፋ መቻሉ ነው።
ከ ስዕሏ ላይ እንደሚታየው በግራ በኩል የሚገኘው ገጠራማ መልከዓ ምድር ዝቅ በማድረግ ሞናሊዛ ከቀኝ ጎኗ ይልቅ በግራ ጎኗ ጎላ ብላ እንድትታይ አድርጓታል።
በታሪክ እንደምናወቀው ሰወች በግራ በቀኝ ይመሰላሉ ሴት ግራ ወንድ ደግሞ ቀኝ የሚባል ቢሂል አለ።
ዳ ቬንች የእንስት(ሴት) መርሆች ሃይለኛ ተከታይ ነበር። ለዚህም ነው ሞናሊዛ ከቀኟ ይልቅ በግራዋ ጎልታ እንድትታይ በሚስጥር የገለጠው።
ብዙ የአለም ህዝብ ሞናሊዛ ሴት ስእል እንደሆነች ነው የሚረዳ። ነገር ግን ለሚያስተውል የስእላዊ ኮደ ቀማርያን ሁለት የወንድና የሴት ምስሎችን የምትሰጥ ስእል ነች።
የስእሉ ሞናሊዛ በተናጠል ወንድም ሴትም አይደለችም ሞናሊዛ የሁለቱም ውህድ ነች። ለዚህም ማመሳከሪያነት ዳቬንች ሚስጥራዊ መልዕክትን ለተከታዩች ትቶ በስሟ በኩል ትቶ አልፏል።
ስለ ሞናሊዛ ደራሲያ ን ደርሰውላት ፣ሙዚቀኞችም ዘፍነውላታል፣ አልፎም ለልጆቻቸው በስሞ ሰይመውላታል ።
ሞናሊዛ ከሁለት ታላላቅ ስሞች የተገኘች መጠሪያ ነች።
አሞን የሚባል በጥንት የግብጽ ምድር የሚመለክ ከፊቱ ባለ ቀንድ የወጠጤ በግ ጭንቅላት ሲኖረው ከጎኑ የግብጽ የፍሬያማነት ጣኦት እንዳለው የሚታመን ጦኦት ነው ።
የዚህ አሞን የተባለው ጣኦት ተዛማጁም የግብጸ የፍሬአማነት አንስት ጣኦት ናት። ስሟም ሊዛ በመባል ትታወቃለች።
AMON LISA በሚባሉ ቃል ውስጥ ሆህያቶች በሌላ አደራደር በህቡዕ መረጃን የማድረስ ዘዴን ታሳቢ በማድረግ ሲደረደሩ MONA LISA የሚል ትርጉም ይሰጠናል።
የወነድና የሴት መለኮታዊ ጥምረት ወጤት እንደሆነች ለተከታዮቹ ለ500 አመታት በህቡዕ በሚስጥር ሲያስተላልፍ ዳ ቬንች ለተራው አለም ጎብኝወች ግን ሰሳ ባለው ፈገግታው ስታፌዝ አመታትን እንድታሳለሰፍ አድርጎ ተጠቦባታል ።
እና ጓደኞቸ አለም ላይ እንዲሁ እንደ ቀልድ ያለፈ ዘመን እና ስራ የለም የዳቬንች ቅንጣት ሚስጥር የሞናሊዛ ሆን ተብሎ የተቀመጠው ፈገግታዋ ፍቹ
የጥንቶቹ የአሞን እና የ ሌሳ ጣኦቶች በዘመናዊነት የመ መለክ ውጤት ነው፠
እፀ አብኖስ ......
እፀ አብኖስ... ይህ እፅ በገነት ምድር ከታላቅ ክብር ጋር ተዳምሮ የተፈጠረ ሲሆን የራሱ ሃይልና መክስት እንዳለው ይታመናል።
ይህንን እጸ አብኖስ ሃይሉን የተረዱ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ አካላት በህቡዕ እያሰሱት ይገኛል እንዲሁም በፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥም ሃሉን ይገልጡታል ።
አባታችን አዳም ከገነት ወደ ምድር በተመለሰ ወቅትም በንስር መሪነት አዕዋፋት ለአዳም ከገነት ካመጡለት የእጸዋት አይነት አንዱ ይሄው እፀ አብኖስ እንደሆነ አባቶቻችን ያስተምራሉ፤ በተጨማሪ አባታችን ኖኅም ይህንን እፅ ለደውል ይጠቀምበት እንደ ነበር የተለያዩ ድርሳናት ያስረዳሉ። " መጥቅዕሰ ተወጥነ በኖኅ፤ ወገብረ መጥቅዓ እምዕፀወ አብኖስ " እንዲል።
ስለዚህ የዚህ እፅ ተክል አሁን ላይ የት አካባቢ ይገኛል ? አባቶችስ ለምን አይንተ ጥበብ ይጠቀሙበታል?ይህ እፅ ከእፀ መሰውር (ሰው እንዳይታይ እራሱን ለመሰወር ) ከሚያገለገለው ክታብ ጋር ምን ግኑኝነት ይኖርው? መስጥመ አጋነት አጋንትን ወደ ጥልቁ ለመወርወርስ ይህ እፅ ፍቱን መዳሀኒት ይሆን? ለዚህ ሁሉ ጥያቄወች መልስ እንዳለው ይታመናል፡፡ የዚህን እፅ ተክል አገልግሎት አበውን በመጠየቅ ከመልስ ጋር እንመጣለን፡፡
ግን አንድ ነገር አምናለሁ አዳም የፈጣሪን ትዛዝ ተላልፎ ከ ገነት ሲወጣ ከገነት አንድ ክንድ ዝቅ ወዳለችው ማእከላዊ ምድር ነበር ከእጸ አብኖስ ጋ መኖሪያው የነበረች ሰለዚህ ይህ እፀ አብኖስ እኛው ሀገር ነው ያለው (የት በምን ሁኔታ የሚለው ሌላ ጥያቄ ሁኖ) ማለት ያስችላል..::
‹‹በአፍህ ተጠንቀቅ ከሁሉም በላይ ግን በአእምሮህ ተጠንቀቅ ! ክፉ ሃሳቦች ከአንተ ላይ እንዲመላለሱ አትፍቀድ። ወንድምህን የሚጎዳ ቃል አፍህ አይናገር! #ከንፈሮችህ መዓዛ የሚያሰራጩ ቃላትን፣ #የመጽናኛ ቃላትን፣ #ማበረታቻዎችን እና ተስፋን ይናገሩ! በአፍ ከሚነገረው ውስጥ የውስጣዊው ሰው ማንነት እንዲሁ ይታያል።››
+ ◉የአሪዞናው #ኤፍሬም_አረጋዊ
/channel/papael_smu_legzihabher
ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ....
.
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››
እንኳን ለአምላካችን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
#ጎግ_ማጎግ ማናቸው?#ውጊያቸውስ_መቼና_ከማንጋ_ነው? ኢትዮጵያስ?
{ክፍል-፩}
(ቱካ ማቲዎስ)
የሥማቸው መጠሪያ?
አማርኛው:- ጎግ ማጎግ ፣ አረብኛው:- Ya'juj Ma'juj (እጁጅ እና ማእጁጅ)፣ እንግሊዝኛው:- Gog and Magog ይላቸዋል።
አንድም:- ጎግ- "ሠራዊት፤በዝቶ የሚሄድ፤የሚንጋጋ ማለት ነው:-ጎግ'ማጎግ የ"ብዙ ብዙ" ማለት ነው ይባላል።
አንድም:- ጎግ ግለሰብ ፣ማጎግ ደግሞ የሚመጣበት ሃገር ነውም የሚሉ አሉ።
ወይም ማጎግ ያስገኛቸው ጎጎች የሚለው ምናልባት ፅዑፉን ጠልቀን እያነበብን ስንመጣ ስለ ስያሜያቸው የምንረዳው ይሆናል።
የሆኖው ሆኖ ሥያሜያቸው ለጦርነት፣ለጥፋትና ለአመፃ ስለሚተባበሩ በዓላማና በተግባር በአንድነት የፀኑ ሕዝቦች እንደሆኑ ስማቸው ራሱ ይናገራል።
ከየት መጡ?
በኃለኛው ዘመን ስለሚነሱና ጥምረት ፈጥረው ውጊያ አድርገው ምድርን እንዳልነበረች ስለሚያደርጓት ጎግ ማጎግ ለእዝቅኤል ማንነታቸው ተነግሮታል:-
ት. ሕዝ 38÷2 - "...ፊትኽን፡#በጎግ፡ላይና፡#በማጎግ፡ምድር፡ላይ፥#በሞሳሕና፡#በቶቤል፡ዋነኛ፡አለቃ፡ላይ፡
አቅናበት፥ትንቢትም፡ተናገርበት..."
እዚኽ ላይ ማጎግ የተባሉትና ከሱምጋ ወግነው ለውጊያ ሚሰለፉት የኖህ ልጅ #ያፌት የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
ዘፍ.10÷2 "የያፌት ልጆች ጋሜር፥ #ማጎግ፥ማዴ፥ያዋን፥ይልሳ፥ #ቶቤል፥ #ሞሳሕ፥ቴራስ፡ናቸው።" ብሎ በግልፅ አስቀምጦልናል።"
አለቃ ሆኖ ጦርነቱን የሚመራው ዋናው ጎግ እንደሆነ ደግሞ እንዲኽ ይለናል ት.ሕዝ 38÷3 "የሞሳሕና፡የቶቤል፡#ዋነኛ_አለቃ_ጎግ፡ሆይ..."
የጎግ የማይቀር አለቅነትና ወደርሱም ስለሚሰበሰቡ ወገኖች ት.ሕዝ 38÷3 ይኽን ይላል። " አንተና፡ወዳንተ፡የተሰበሰቡ፡ወገኖችኽ፡ዅሉ፡ተዘጋጁ፥አንተም፡ራስኽን፡አዘጋጅተኽ፡አለቃ፡ኹናቸው።"
ከቅዱስ መጽሐፍ በተጨማሪ በታላቁ እስክንድር ጀብዱ "ዜና እስክንድር" ላይ #የእስክንድር_በር ተብሎ የሚታወቀውና በራሱ በታላቁ እስክንድር የተገነባ፣ ክፉ ጨካኝና የሰውን ሥጋ የሚበሉ የተባሉ ጎሳዎችን ወደ ሰው ልጅ መኖሪያ እንዳይቀርቡና ÷ የሰውን ዘር እንዳያጠፉ "ምድቅኤል"ና "ቅርፍትኤል" የሚባሉትን ሁለት ተራሮች እስክንድር መቄዶናዊ በፀሎት አቃርቦ አጋጥሞባቸው እንዳይወጡ የመላዕእክት ጠባቂ (ወደበሩ ሲቀርቡ የበገና ድምፅ የሚያሰማ ሮቦት፣መካኒካል ጥበብ) አቁሞባቸዋው ወደ በሩ አይጠጉም። እነዚሕም ከያፌት ማጎግ ከተባለው የዘር ግንድ የወጡና መናፍስታዊ ፍጥረታት እንደሆኑ ያስረዳል።
የታሸገባቸው ተራራም ሥፍራውም በቱርክ ሃገር በአርመኒያና አዘርባጃን አካባቢ በቱርክና ሩስያ ድንበር ካውካስ ተራራ እንደሚገኝ የሚናገሩ አሉ።
Vikings , Huns , Khazars, Mongols , Turanians እና ሌሎች ዘላን ዝርያዎች ዘሮች ናቸው የሚሉ አሉ።
የእስክንድር በርና ጎግ ማጎግ የሚገናኙባት ብዙ ታሪክ ተፅፏል። በኛም ግእዝ "ዜና እስክንድር" በሚል የተጠቀሰ አለ።
ስለነዚኽ ፍጡራን ቅዱስ ቁርዓንም Surah Kahaf
የተባለው ምዕራፍ Yajuj and Majuj ( ﻳَﺄْﺟُﻮﺝُ ﻭَﻣَﺄْﺟُﻮﺝُ ) ጎግ ማጎግን ኃላ ቀርና ግብረ ገብነት የጎደላቸው ዘሮች በማለትና በ Zu'l-Qarnayn (በባለ ሁለት ቀንዱ) የፅድቅና ትክክለኛ ነገር በሚሰራው ገዢ ) በብረት መዝጊያ እንደተነጠሉና እንደታገዱ ይገልፃል።
{{ ስለ ታላቁ እስክንድር መቄዶናዊ በርና በውስጡ ስለታገዱት አስገራሚ ፍጡራን ሌላ ቀን በሠፊው እንመለሥበታለን።}}
ቁጥራቸው ብዛታቸውስ?
ዮሐ.ራዕ 20÷8 "በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ..."
ይኽ ማለት #ከሰሜን_ከደቡብ_ከምሥራቅና_ምዕራብ የምድራችን ክፍል፣ ጎግ አለቃ ሆኗቸው ለጦርነት እንደሚያሰልፋቸውና፣
"ቍጥራቸውም፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡የሚያኽል፡ነው።" ይለናል።
#ይቀጥላል
(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)
ምስጢራዊው የአፍጋኒስታኗ #ካንዳሃር_ግዙፍ_ኔፍሊምና የአሜሪካ #ወታደሮች_ያደረጉት_ትንቅንቅ
(ቱካ ማቲዎስ)
ይኽ እጅግ አስገራሚ ታሪክ የተፈፀመው ጥንት በድሮ ዘመን ሳይሆን አሁን ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን በ2002 እ.ኤ.አ እስካሁን ባላለቀው የአፍጋን-አሜሪካ ጦርነት ወቅት ነው።
ጉዳዩ በአሜሪካ መንግሥት #classified (ለብሔራዊ ደኽንነት ሲባል የሚጠበቅ ምስጢር) ከሚባሉ እጅግ ጥብቅና ድብቅ ወታደራዊ ምስጢራቶች አንዱ ቢሆንም ምንም ነገር ተደብቆ ስለማይቆይ ማፈትለኩ አልቀረም።
በተራራማዋና በረሃማዋ እጅግ ፈታኝ መልክዓ-ምድር ያላት አፍጋኒስታን የአሜሪካ ወታደሮች አንድ ሙሉ ብድን (squad) ደብዛው ይጠፋል።
ይኽን ክስተት ተከትሎ ልዩ ኦፕሬሽን አሳሽ ቡድን የጠፉ ወታደሮችን ፍለጋ ይሠማራሉ።
በፍለጋቸው ተራራማ ቦታዎችን አልፈው ወታደሮች ጠፉበት ከተባለው ግምታዊ የተራራ አምባ ላይ ወጥተው ከአንድ ትልቅ ዋሻ አቅራቢያ ይደርሳሉ።
ወደ ተልእኮው ሲያመሩ በጠፋው ቡድን ላይ የሆነው ነገር ሳያሳስባቸው አልቀረም፣ ያው እንደተለመደው ambush (የደፈጣ ጥቃት) መስሏቸው የነበረ ቢሆንም በደፈጣ ጥቃት ወቅት ሁሌም "የድረሱልን ጥሪ" እንደሚኖር አሁን ግን ምንም አይነት መልእክት ሆነ ጥሪ አለመደረጉ ግራ አጋብቷቸዋል።
ይኽ አሳሽ ቡድን በመሬት ላይ የመኪናና የእግር ዱካ መከተል አማራጭ አድርጎ አሰሳ ፍለጋ ጀመረ። ይኽም ክትትል ነው ወደዚኽ ትልቅና ጥልቅ ዋሻ ያደረሳቸው።
ዋሻ ማግኘታቸው ሳይሆን ትኩረታቸውን የሳበው ምስክርነት የሰጡ ወታደሮች ሲናገሩ "የተሰባበሩ የአሜሪካ ወታደራዊ እቃዎችና መገልገያዎች የተሰባበሩ ምንነታቸው መለየት አዳጋች የሆኑ ቅሪተ አጥንቶች፣ድንጋዮች፣የራድዮ መገናኛዎች በዋሻው መግቢያ ተበታትነው ማየታቸውና " የደፈጣ ወይም አንድ የሆነ የዱር እንስሳ ጥቃት እንደሆነ መገመታቸውን ያስረዳሉ።
የዋሻው መግቢያ እጅግ ሠፊና ጥልቅ በመሆኑ ቡድኑን በሙሉ አፋፉ በአንድ ላይ ለማስገባት ቢቻለውም ከመግቢያው ፈንጠር ብሎ ያለ ድንጋይ ወደ ውስጥ እይታቸውን ጋርዶታል።
ከውስጥ በሚሰሙትና እየቀረባቸው በመጣው ድምፅ ምክንያት ፀረ-ደፈጣ ጥቃት ለመፈፀም ከዋሻው መግቢያ ፈቀቅ ብለው ቦታ ቦታቸውን ይዘው መጠባበቅ ጀመሩ ግርምትን በፈጠረባቸው ፍጥነት ግን ከዋቻው ውስጥ፣ ከ 13-15 ጫማ (ከ4 ሜትር በላይ) ቁመት፣ ባለ ቀይ ረዥም ትካሻዎቹን የሸፈነ ፀጉርና ፂም፣ #ሥድስት_ጣቶችና ተደራራቢ ጥርሶች ያሉት ሰው መሰል (humanoid) ፍጡር በድንገት ከዋሻው በመውጣት ጥቃት ይፈፅምባቸዋል።
ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እንሂድ:-
2ኛ ሳሙኤል 20 "ደግሞም፡በጌት፡ላይ፡ሰልፍ ኾነ፤በዚያም፡በእጁና፡በእግሩ፡ስድስት፡ስድስት፡ዅላዅሉ፡ኻያ፡አራት፡ጣቶች፡የነበሩት፡አንድ፡ረዥም፡ሰው፡ነበረ፤ርሱ፡ደግሞ፡ከራፋይም፡የተወለደ፡ነበረ።"
#ማስገንዘቢያ:- ይኽ #ራፋይ የተባለው የግዙፋኑ ኔፍሊምስ አባትና አስገኚ እንደሆነ ብዙ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰ ነው።
{ ከታች በምስሉ ላይ ያያዝኩላችሁ ወታደሮች ከበውት ያለው የግዙፉ ገላጭ ምስልም ላይ 6 ጣቶችን መቁጠር ይቻላል።}
አፍጋኒስታን እንመለሥ:-
ከወታደሮቹ አንዱ ወደ ፍጡሩ በመሮጥ ይተኩስበታል፣ "በዚኽ ጊዜ ሁላችንም ከከባዱ እውነት ጋር ተፋጠጥን
ከዚኽ ቀደም ከነበረን ወታደራዊ ሥልጠናና ልምድ ውጪ በ adrenaline: (adrenaline (n) = በንዴት ወይም በፍርሀት ጊዜ ከኩላሊት በላይ ያሉ ዕጢዎች የሚያመነጩት ኬሚካል) በመታገዝ ሁላችንም መተኮስ ጀመርን" ይላል እማኝ ወታደሩ።
#ይቀጥላል
ሚስጥሩ ያልተፈታው ራስ ደጀን!
~ ከምድራችን በታች ታላቅ የእሳት ባህር አለ፤ በታላቅ የእሳት ቀለበትም የተከበብን ነን፤ በዚህ የእሳት ፍሳሽ ተጽዕኖ ምክንያትም አለማችን በአመት እስከ 20 ኪ.ሜ ወደ ምድረ በዳነት ትቀየራለች፤ ለአብነትም ከሳሃራ በታች ያሉ ሃገራትን መጥቀስ ይቻላል። ታዲያ ይህ የእሳት ባህር ( ቀለበት ) በምድራችን ላይ ዛፎች በተተከሉ ቁጥር በዛፎቹ ሥሮች አማካኝነት ቅዝቃዜን ያገኛል፤ በዚያን ወቅት እንፋሎቱን በነፋስ መልክ የምድርን ደረት ቀዶ ወደ ላይ ይተነፍሳል፤ ይህን ተከትሎም ነፋሱ ከፍተኛ ጥፋትን ያስከትላል፤ የእዚህ እንፋሎት ( ነፋስ ) መተንፈሻ ተብለው ምድራችን ላይ የሚጠቀሱ ሁለት ታላላቅ ስፍራዎች ሲገኙ አንዱ በሃገራችን የሚገኘውና #ራስ_ደጀን ብለን የምንጠራው ተራራ ነው፤ ሌላኛው ከሜዲትራኒያን ውቅያኖስ ስር ይነሳል።
ታዲያ ብዙ ከማይነገርለት እጂግ ሚስጥራዊ ቦታ ከሆነው ራስ ደጀን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆርጂ ዳብል ቡሽን ጨምሮ የተለያዩ የአለም ነገስታት እንዲሁ አለም ላይ ያሉ ሚስጥራው የጽዋ ማህበራት The brothers(የወንድማማቾች ማህበር) and the zions chalice(የጽዮን ጽዋ) የተባሉ እንጂግ ሚስጥራዊ እና ረቂቃዊ ማህበራት ለበርካታ መቶ አመታት የቆዩ የሃያላን ግለሰቦች ስብስብ (ስለ እኒህ ሚስጥራዊ የጥንት መዛጎብትን አሳሽ አደገኛ የስለላ ተቋማት በሌላ ጊዜ አቀርብላችሁ አለሁ) በግልጥና በህቡዕ እየተመላለሱ ይህንን ቦታ ሚስጥሩን ለመፍታት ይጎበኙታል።
ታዲያ ከራስ ደጀን ከፍታማ ተራራዎች የሚነሳው ነፋስ እስከዛሬ አለማችን ላይ ቀላል የማይባል ጥፋትን አስከትሏል በተለይም በምዕራቡ አለም ሃገራት ላይ። ለዛም ይመስላል በሱናሜ በማዕበል በተደጋጋሚ ሲጠቁ ''ሳተላይታችን ማዕበሉን ያስከተለው ነፋስ ከኢትዮጵያ ሰሜናዊ ተራሮች ተነስቷል'' እያሉ የሚዘግቡት። እንዲሁም በቅርቡ ቅዱስ ያሬድ ከተሰወረበት ራስ ደጀን የተነሳው ከበድ ነፋስ የተለያዩ የአለም ከተሞችን በማቋረጥ የአሜሪካን ግዛቶች እንደመታ የአለም የዜና አዉታሮች Bbc algezira CNN የመሳሰሉት ከ አመት በፊት በዜና እወጃቸዉ ይዘዉ ወጠዉ ነበረ ። እዲሁም በግልጽ በዶላንድ ትራንፕ የዚህን ነፋስ መነሻ ቦታ በሚሳኤል እንመታዋለን ነበር ያሉት።
ለምን ይሆን ብዙ የአለማትን ከተሞች አልፎ አሜሪካን የመታው ? Gps እንደሚያሳየው ከ ራሰ ደጀን ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ገዳም ተነስቶ አሜሪካን ያናወጠበት እና ያስጨነቀበት ምክኒያቱ ምን ይሆን? ይህ ታላቅ ሚስጥር ለመግለጥ ጠቢባኑ ብዙ ረቀት ተጉዘው ተመራማሪዎችም በርካታ ምርምርን አድርገዋል።
ይህ ቦታ መለኮታዊ ሚስጥር ሚገለጥበት ዛሬም ድረስ እጂግ በርካታ ታምራት የሚታይበት ድንቅ ቦታ ነው። ራስ ደጀን እጂግ ሰፊ ቦታ ሲሆን ደጋማ የአየሩ ሁኔታ ያለው እና በርካታ ስውራን ገዳማትና መነኮሳት የሚገኙበት የበረከት ቦታ ነው ። ይህ ቦታ የራሳቸው የኑሮ ዘየ ያላቸው ዘመናዊ የሆነ አንዳችም ነገር ያልገባበት የዘር ሃረጋቸው በእግዚአብሄር የተባረከ የሆኑ ትውልዶች በስውር ይኑሩበታል።
ይህ ፈለገ ጥበባት ነው የአየነውን ልንናገር የሰማነውን ልንመሰክር የጠቢባን አባቶች አደራ አለብን።
👓 ቅዳሜ በፍጥነት ያልፋል እሁድና ሰኞ ግን ቶሎ አያልፉም የምንል ብዙዎች ነን፤ ኸረ እንደውም እሁድ ቢፈነከት ሁለት ቅዳሜ ይወጣዋል እንላለን። አልበርት አንስታይን "የጋለ ምጣድ ላይ 1 ደቂቃ የተቀመጠ ሰው 1 ዓመት የቆየ ይመስለዋል ጊዜው ይረዝምበታል በተቃራኒው ደግሞ በጣም ከሚወዳት ፍቅረኛው ጋር 3 ሰዓት ያሳለፈ ወጣት ለ 3 ደቂቃም የቆየ አይመስለውም ጊዜው ያጥርበታል" ይለናል።
የፊዚክሱ ሊቅ አልበርት
ሁሉም ነገር አንፃራዊ ነው፤ አንተ ፊልም ስታይ ብትውል ደስ ብሎህ ጊዜው ያልፋል፤ ጓደኛህ ደግሞ ለስራው እያቀደ እያነበበ ቢውል ነገ ህይወቱ ላይ የሚታይ ጉልህ ለውጥ በሚያመጣ ነገር ላይ ሌተቀን እያጠፋ ነገን በተስፋ እያየ ደስ ብሎት ቀኑ ያልፋል። ሁለታችሁም ቀናችሁ በደስታ ቢያልፍም አንተ ፊልም ታተራምሳለህ ትስቃለህ........እሱ ግን እያየኸው ህይወቱ ይቀየራል። እኔስ...ነው ጥያቄው?
ቀኑን ያረዘመብህም ያሳጠረብህም ምርጫህ ነው!
ወዳጄ ጊዜህን ምን ላይ ነው የምታሳልፈው?
የት ነው ምታሳልፈው?
ምርጫህስ ምንድነው?
#like #share
''ትቤ ምእታወ አክሱም መኑ አንተ.. .?''
(የተዘጋች የሆነች) የአክሱም በር አንተ ማነህ ትላለች....
ከ 889-869 ከክረስቶስ ልደት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል አብሪ ኮከብ የሆነች በአለም ተጽኖ ፈጣሪ ታላቅ እና ገናና የንግድ ከተማ በታላቁ ንጉስ አክሱማይ ራሚሱ እንደተመሰረተች የታሪክ ድረሳናት ይናገራሉ።
የአክሱም ከተማ ለዘመናት የሕዝብ መኖርያ ብቻ ሳትሆን ዛሬም ድረስ አለም ላይ የደመቁ የሥነ ጽሁፍ ፣የ ሥነ ሕንጻ የቅርጻ ቅርጽ ሥዕላት እንዲሁም የታላላቅ ገዳማት መገኛ አሁን ላለንበት ሰፊ የክርስትና አማኝ መገኘት ሚናዋ ከፍተኛ ነበር።
ታዲያ ከታላቋ አክሱም ስር ብዙ ያልተ ተረከ ሀብት ፣ያልተነገረ ጥበብ ፣ያልተገለጠ ማንነት ፣ዘመንን እያስረጀ ትውልድን እየገፋ የሚኖር፣ የሚታይ ግን ያላስተዋልነው፣ ፊቷን እንጂ ልቡን ያልመረመርነው ፣ተዝቆ የማያልቅ ሚስጥራዊ ዶሴን በተገለጠ ሀውልት ያልተገለጠ ሚስጥሩን እንመርምረው ዘንድ ጉዞአችን ወደ አክሱም ሐውልት ይሁን።
የታነጸበት ዘመን በተለያየ ጻህፍት የተለያዩ ሐሳብ አለ አንዳንዶች ከ 3ኛው -4ኛው መቶ ክፈለ ዘመን ሲሉ ፤በላሌ በኩል የአክሱም ስረው መንግስቷ ሲመሰረት እንደታነጸ ይናገራሉ ይህም ማለት 546-532 ዓ.ዓ የ3ሺ አመት እድሜ መሆኑ ነው።
በቂ ጥናት መደረግ ቢገባው ካለው ነባራዊ ሁነት እና ከታሪካዊነቱ አንጻር በብዙ የሚያ ስማማው የ3ሺ አመት እድሜን እንደያዘ መሆኑ ነው።
ታላቁ የአክሱም ሐውልት 33 ሜትር ከፍታ ክበደቱ ደግሞ 520,000ኪግ ነው።
ስለ ታላቁ የእክሱም ሐውልት አገነባብና አቋቋም ብዙ አወዛጋቢና አከራካረ ነገሮች በየ ዘመናቱ በተነሱ ጠቢባኑ ይካሄዳል። ይህ አወዛጋቢነቱ ዛሬም ለ አርኪኦሎጂስቶች እና ለህንጻ ባለሙያወች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።
አንዳንዷቹ ከተገነባበት ዘመን አንጻር የሰው ልጂን ንቃተ ህሊና ታሳቢ በማድረግ በሰወች እንኳን ሊሰራ ሊታሰብ አይቻለም ይላሉ። ታድያ የእዚህ ሐውልት ሰሪወች የቀደሙ ሐያላን ርአይት ወይም ግዙፍን ወይንም ከሰማይ የወረዱ ኔፍሊሞች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
በእርግጥ የሰው ልጂ ልብሱ ሰርቶ መልበስን በማያውቅበት የደንጋይ ዘመን ይህንን የመሰለ ዘመን ተሻጋሪ ሐውልት መስራት መቻሉ ጥያቄ ውስጥ ይጥላል።
ዛሬም ድረስ ይህ ሐውልት በጥንታዊየቱ ከአንድ ወጥ አለት መሰራቱ በአለም የሚመጥነው የሚተካከል አለመኖሩ በዛን ዘመን በሰወች ተገነባ ብሎ ማሰብ ይከብዳል።
ታድያ ይህ ሐውልት የተቀረጸው በምን አይነት መሳሪያ ነው...?
ይህ የእሱም ሐውልት ለመቅረጽ የተገለገሉበት መሳርያ እብነ አድማስ ይባላል ታድያ ይህ ታምራዊ መሳርያ አለትን እንደ ሰም የሚያቀልጥ ጽነ ማዕድን ነው።
''ወአምጽኡ ሎቱ እብነ አድማስ ወወሀብዎ ወይቤልዎ ሑር ምድር ወንበርታ ወሕንጽ በኀየ ቤተክርስትያን''
''አብርሐና አጽብሐ በዚያን ጊዜ እብነ አድማስ አምጥተው ሰጡትና ወንበርታ ወደ ሚባል ሀገር ሂደህ በዚያ ቤተክርስትያን ስራ አሉት'' ይላል ገድለ አብርሐ ወአጽብሐ.... ይህ ማለት እብነ አድማስን እውነትም ለህንጻ አገልግሎት ሲጠቀሙበት እንደ ነበር ያሳያል።
ታላቁ ጥበብ እንዴት 33ሜትር ቁመት 520,000 ኪሎ ክብደት የሚመዝንን ግዙፍ ሃውልት ሊቆም ቻለ የሚለው ነው?
የቆመበት ሚስጥር ምንም በውል ባይታወቅም ጥበባዊ በሆነ መንገድ በነፋስ አውታር እንዳስቆሙት አበው ይናገራሉ።
ይህ ካልሆነ ምን አይነት ጥበብ ተጠቅመው ይሆን?..
ከዚህ ሃውልት ስር የሚገኝ ህንጻ መኖሩ ደግም ለሚሰማና ለሚያየው የሚደንቅ ነው።.....
ይህ ድንቅ ሃውልት ከሃያላኑ የፒራሚድ ገነቢወች ጋ የሚያገናኘው ነገርም እንዳለ ይነገራል። በአንዳንድ መዛግብት ላይም ከሃውልቱ ራስ ታምራዊ የሚያበራ ብርሃን እንነበርን እና ብዙ የሚደነቅ ታምራት ይታይበት እንደነበር ከ ሃውልቱ የተነሳበትና የጠፋበት ሁኔታ ከተነሳ በኋላም አሁን ያለበት ቦታ በብዙሃኑ ዘንድ ጥያቄን ይፈጥራል ....
ይህ ሃውልት ከአስደናቂ ስነ ህንጻው ይበልጥ ጥብቅ እና የጠለቀ ሚስጥራዊ ኮድን ይዟል... ሐውልቶቹ የተቀረጹበት መንገድ ከ ልማዳዊ የህንጻ አሰራር ባሻገር የተለየ መልእክትን የያዙ ይመስላሉ....በእኒህ ሐውልቶች ላይ የተዘጉ በርካታ ከአለት የተቀረጹ በሮች በፎቅ መልክ ተደርድረዋል ።
ይህ የተቆለፈ የድንጋይ በር ከፋቹን እስኪያገኝ ጥበባዊ ማንነቱን ለመግልጽ ፈቃደኛ አልሆነም እንደውም ጠቢባኒ ቅኔያዊ በሆነ መንገድ ታላቅ መልእክትን በዚሁ በተቆለፈ የአለት በር እያስተላለፉ ይመስላል...
ዛሬም ቆመው ከሚታዘቡንም ሆነ ወድቀው ከሚያስለቅሱን የአክሱም ሐውልቶች ላይ በበር ቅርፅ የተሰሩ የድንጋይ በሮች እና በነሱም ላይ ተደራራቢ የሆኑ ፎቆች ሚስጥራዊ የቁጥር ውክልናን ይዘው በዝምታ ለሚያልፈው የትውልድ ጅረት የሚናገሩት ሚስጥር
እንደነበር እናያለን:: እነዚህ የድንጋይ በሮች የተቆለፉ
ይመስላሉ:: በበር ቅርፅ እስከተሰሩ ድረስ የሚከፍታቸው ሆነ በሥራቸው የሚያልፍ ትውልድን የሚጠብቁ ለመሆናቸው እርግጠኞች ልንሆን ይገባል::
ያለ ምክኒያት በር አይሰራም፤ በሩም ከፋቹን እስኪያገኝ በ ሃያል እና በ ጥበቢባኑ ዘመን የተዘጋዉ ሚስጥር ከ ሶስት ሽ አመታት በኋላም የተዘጋውን የሚከፍት ሃያል እና ጠቢባኑን ትውልድ ይፈልጋል..... የተዳፈነችው ጥበብ ራሷን ጥገለጥ ዘንድ በር ፈላጊ ናትና ትቤ ምእታው አክስው መኑ አንተ ትላለች ? ....
የበሮች ሚስጥራዊ ኮዱን ቀጣይ እንመለከታለን..!
''ትቤ ምእታወ አክሱም መኑ አንተ.. .?''
(የተዘጋች የሆነች) የአክሱም በር (ትክፍትልህ ዘንድ) አንተ ማነህ ትላለች....
#መኖቅሪጥስ (Uni-Corn) ባለ አንዱ ቀንድ እንስሣ
አንድ ቀንድ ያለው የበረሃ እንስሣ ነው...መልኩም ፍየልና ዋልያ ይመስላል አዳኞች ይፈሩታል ብርቱ ነውና...አንድ ቀንድ በጭንቅላቱ መካከል አለ...
#ለድንግል_ሴት ግን ይሸነፋል...ወደ እርሷም ይቀርባል በደረቷ ትታቀፈዋለች እርሷም ለንጉሡ እጅ መንሻ አድርጋ ትወሥደዋለች በእርሡም የተነሣ ታላቅ ሃብት ታተርፋለች…
#ፊስአልጒስ(ሥነ-ፍጥረትን የሚተነትን) መፅሐፍ ላይ ተጠቅሷል።
...ይህ እንስሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ይገኝ እንደነበረና ነገስታት በቤተመንግስት እንደ ክብር ይዘው ያቆዮት እንደነበር በአንዳንድ ድርሣናት ተጠቅሷል።
ይህን ዝናውን ብርታቱን የተለያ ባህርዩን የሰሙም መንግስታት የሃገራቸው አርማ አድርገው ይጠቀሙበታል:: (አባ ተስፋስላሴ ሞገሥ በመፅሐፋቸው ጠቅሰውታል)
#መፅሐፍ_ቅዱስ ምን ይላል?
መዝ 22፤21 <<ከአንበሳ፡አፍ፡አድነኝ፥ብቻነቴንም #አንድ_ቀንድ ካላቸው>>
መዝ 91÷10 <<ቀንዴ #አንድ_ቀንድ እንዳለው፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፤ሽምግልናዬም፡በዘይት፡ይለመልማል>>
የዳዊት መዝሙር 28(29)፤6 <<እንደ፡ጥጃ፡ሊባኖስን፥አንድ፡ቀን፡እንዳለው፡አውሬ፡ልጅ፡ስርዮንን፡ያዘልላቸዋል>>
ዘኁ 23፤22 <<እግዚአብሔር፡ከግብጽ፡አውጥቷቸዋል፤ጕልበቱ፡አንድ፡ቀንድ፡እንዳለው፡ነው>>
(ነጽሩ ወዘሠናየ አጽንዑ)
ኧረረረረረረረረ ይነበብ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🔘ቀደምት ኢትዮጵያውያንና ቴክኖሎጂ | ኤሌክትሮን እና ፕሮቶውስ የተባሉ የኢትዮጵያ ነገሥታት 🔘
በዓለማችን ላይ የተለያዩ ጥንታዊ ህዝቦች ቀደምት ሥልጣኔዎችን መስርተዋል። እነዚህ ህዝቦች የሀገረሰብአዊ ጥበቦችን፥ እሴቶችን፥ እውቀቶችንና ፍልስፍናዎችን ፈልስፈዋል። በጥንታዊው ታሪክ ላይ ተጽዕኖ ካሳደሩ ታላላቅና ገናና ህዝቦች መካከልም ቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።
👉🏾 ሰላም ለናንተ ይሁን ውድ ኢትዮጵያውያን የ ‘ወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት መርኃግብር ተከታታዮች! በዛሬው መርኃግብራችን ስለ ቀደምት ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ውጤቶች የምንመለከት ይሆናል።
ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ በርካታ የታሪክ ተመራማሪዎች ብዙ ብለዋል።
👉🏾 ለመጥቀስ ያኽልም፦
ከክርስቶስ ልደት በፊት 60 ዓመት ላይ የነበረው ዲዎዶሮስ ሴኩለስ የተባለው ሊቅ “አውሮፓውያን ኋላ ቀር እድገትና አኗኗር ላይ በነበሩበት ወቅት ኢትዮጵያ ታላቅ ሥልጣኔ ላይ ነበረች፤…. ለግብፃውያን ሥልጣኔን ያስተማሩና እስከ ሕንድም ድረስ የገዙ ናቸው።” ብሏል።
የቤዛንታይኑ እስቴፋንስም ባጠናው ጥናት መሰረት “ኢትዮጵያ መሬታችን ላይ የተመሰረተች የመጀመሪያ ሀገር ነች!” ብሏል።
አያቶቻችን ባስቀመጡልን ጥንታዊ መዛግብት መሰረትም የአዳም መኖሪያ፥ የኤልዳ መገኛ፥ የሰው ልጅ እስከ 14ኛው ትውልድ ድረስ የኖረባት የተጻፈ ታሪክ ከ7500 ዓመታት በላይ ከአዳም ጀምሮ ያላት ድንቅ ምድር ኢትዮጵያ! በዚህም ዓለም ይህችን ሀገር ይፈራታል፤ በብዛትም ታሪኳን ለሌላ መስጠት የተለመደ ነገር ነው።
ስለ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ግኝቶች ድሩሲላ ዱንጂ ሐውስተን የተባለች አሜሪካዊት የታሪክ ተመራማሪና ጸሐፊ እንዲህ ትላለች፦
“... የጥንቶቹ ድንቅ ኢትዮጵያውያን የቀለም ሥራዎች ለዘመናት ፈጽሞ የማይደበዝዙ ፣ ጠንካራ አለትን ሰርስሮ የመቆፈር ፍሎታ የነበራቸው ፣ እንደብዙ ሣይንቲስቶች አባባል ዛሬ ለጠፉት በርካታ የሥነ ጥበብ ውጤቶች ባለቤቶች የነበሩ ፣ በዘመናቸው የኤሌክትሪክ ባህርያትን በማወቃቸው ከሜታል ሮቦቶችን የሰሩ ፣ በራሪ መሳሪያዎችንና ፔጋሰስ (በራሪ ፈረስ) የፈበረኩ ቢሆንም ፤ ዛሬ ግን እነዚህ ሁሉ ድንቅ የስራ ውጤቶቻቸው እንደ አፈታሪክ ሲነገሩ ይታያል።” ፒራሚድ ገንቢዎቹ ጥንታዊ ኢትዮጵያውያን ገጽ 11ና Wonderful Ethiopians of the ancient Cushitic Empire page 5 ላይ ተመልከቱ።
🔘ስለ ኤሌክትሪክ ካነሳን አይቀር ከክ.ል.በ(B.C) ከ2515-2485 ድረስ ለ30 ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ የነገሠ “ኤሌክትሮን” የተባለ ንጉሥ መኖሩን መዘንጋት የለብንም። በተጨማሪም ኤሌክትሮን በሳይንሱ የአቶም ክፍል ከሆኑት ውስጥ አንዱ ሲሆን ሌላኛው የአቶም ክፍል ደግሞ ፕሮቶን ይባላል። በተመሳሳይ መልኩ ከክ.ል.በ(BC) ከ1514-1481 ድረስ ለ33 ዓመታት የገዛ “ፕሮቶውስ” የተባለ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ መኖሩን ስናውቅ ደግሞ የሥልጣኔና የሳይንስ ሁሉ መሰረት ኢትዮጵያ መሆኗን እንገነዘባለን። ይህ የነገሥታት ዝርዝርም በታሪክ ጻሓፊው ተክለ ጻድቅ መኩሪያ የኢትዮጵያ ታሪክ ኑቢያ ገጽ19-22 ላይና የግእዝ ጥናት በተባለው የመ/ሐ/ አማኑኤል መንግሥተ-አብ መጽሐፍ ገጽ 128-129 ላይ ታጽፏል።
በጥንታዊ ግብጽ ሥልጣኔዎች ግድግዳዎች ላይም ተመራማሪዎች አንድ ሰው መቀመሪያ ወይንም በዘመናችን አነጋገር Computer የተባለውን መሳሪያ ሲጠቀም/ስትጠቀም መመልከታቸው ጥያቄ ውስጥ ከቷቸዋል። ረቀቅ ያሉ የቴክኖሎጂና የፊዚክስ ቀመሮችና ሥራዎችንም ተመልክተዋል፤ እሱን በሌላ ጊዜ የምናየው ይሆናል።
👉🏾 በታላቁ እስክንድር ዘመንም “ከብረት የተሰሩ በራሳቸው የሚያጨበጭቡ በራሳቸው የሚጮኹ የሙዚቃ መሳሪያዎች እንደነበሩ ዜና እስክንድር የተባለው ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ ላይ ተጽፏል።
አያቶቻችን እንዴት እኒህን ሥራዎች ሊሰሩ ቻሉ? የዘመናችን ሳይንስ እውቀቱን ከማን ወስዶ ሰራው? የሚለውን ምርምር ሁሉ እኔ ፍንጭ ለአስተዋዩ ትውልድ ሰጥቻለሁ፤ ተጨማሪ ማስረጃም እንደምናገኝ ተስፋ አደርጋለሁ!
👉🏾በሌላ ጊዜ ስለ በራሪ ሠረገላ፥ ሠረገላ ኤልያስና ስለ በራሪ ፈረሶች በ ወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት የምናይ ይሆናል።
📜 ደማቁ ታሪካችን 📜
" ... የጥንቶቹ ድንቅ ኢትዮጵያውያን የቀለም ሥራዎች ለዘመናት ፈጽሞ የማይደበዝዙ ፣ ጠንካራ አለትን ሰርስሮ የመቆፈር ፍሎታ የነበራቸው ፣ እንደብዙ ሣይንቲስቶች አባባል ዛሬ ለጠፉት በርካታ የሥነ ጥበብ ውጤቶች ባለቤቶች የነበሩ ፣ በዘመናቸው የኤሌክትሪክ ባህርያትን በማወቃቸው ከሜታል ሮቦቶችን የሰሩ { የዛሬ 4500 ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ "ኤሌክትሮን" የተባለ ንጉሥ ለ30 ዓመታት ሀገሪቷን እንደገዛ ስናውቅ ደግሞ የበለጠ እንገረማለን።😱} ፣ ፔጋሰስ (በራሪ ፈረስ) የፈበረኩ ቢሆንም ፤ ዛሬ ግን እነዚህ ሁሉ ድንቅ የስራ ውጤቶቻቸው እንደ አፈታሪክ ሲነገሩ ይታያል።
የጥንታዊቷን ኩሽ ኢትዮጵያ የንግድ እንቅስቃሴ በተመለከተ ፣ በተራቀቀ ክህሎት የተሞሉት ደፋር ባህርተኞቿ መርከቦቻቸው የዓለማችንን ውቅያኖሶች ሰንጥቀው ስለማለፋቸው ፈጽሞ የማያጠራጥር መረጃዎችን እናገኛለን።{ውድ የወደ ኋላ ጥንታዊ ጥበባት ቤተሰቦች ምናልባት MOANA በሚለው ፊልም ላይ ገጸ ባሕርያቱን ለምን ጥቁር አድርገው ሰሩ ? እንጠይቅ ምን ሊነግሩን ፈልገው ነው?! } ለዚህም ማስረጃ የሆኑ የኢትዮጵያውያን የባህልና የሃይማኖታዊ ቅርሶች ዛሬም በአሜሪካን ኢንስቲውቲሽኖች ውስጥ ይገኛሉ። በደብዛዛው ከሚታወቀው የጥንት ታሪክ ውስጥ ስላለው ዘር ሥልጣኔ ምንጭ ' የጥንቱ አትላንቲስ ' ይታወቃል። እነዚህ የአትላንቲስ ሰዎች እንስሳትን በማላመድ ፣ ዕፅዋትን በማዳቀል ታላቅ አስተዋጾዖ አድርገዋል።{ ጄኔቲክ ሳይንስ በኢትዮጵያውያን ተጀመረ? } ግሪኮችና ሮማውያን እንደ አማልክቶቻቸው ይጠሯቸው የነበሩት የኩሽ ኤምፓየር ነገሥታትና ንግሥቲቶች ከአትላንቲስ የዘር ግንድ አንዱ ነበር ተብሎ ይታመናል። ስለእነዚህ ነገሥታት፣ የጥንት ዘመናት የታሪክ ጽሑፎች ፣ ትረካዎችና አፈታሪኮችን ለሚያጠናና ለሚመራመር በቀላሉ መረዳት ይቻለዋል።...... "
📜'ፒራሚድ ገንቢዎቹ ጥንታዊ ኢትዮጵያውያን ገጽ 11' ሙሉ መጽሐፉን እንድታነቡትም እመክራለሁ!
👉ከላይ ያለውን ጽሑፍ እኔ ፈጥሬ አይደለም የጻፍኩት የራሴን ምልከታ { } በማድረግ ከማስቀመጥ ውጭ ታዋቂዋና በአፍሪካ ታሪክ ላይ አሻራዋን ያኖረችው ድሩሲላ ዱንጅ ሒውስተን {Drusilla Dunjee Houston} በመጽሐፏ ላይ የጻፈችው እውነታ ነው!
በተለይ ደግሞ ያሰመርኩባቸውን ጽሑፎች በልባችሁ ያዙ!
ታሪካችንን እንመርምር ! መነሻውን ያላወቀ መድረሻውን አያውቅም።
🙏🏾መልካም ጊዜ 🙏🏾
✍🏾ከኃይለሚካኤል ዘኢትዮጵያ ✍🏾
#ሼር_የማድረግ_ኢትዮጵያዊ_ውዴታ_አለብዎት!
📌የአንድ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ፕሮፌሰር የሚከተለውን ድንቅ ጥናት እንዳገኘ በቅርቡ ይፋ አድርጓል !! ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው አስከመጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠ A b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z ። የነዚህን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል ኣስቀመጠ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 በጥናቱም ለያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ ለ"A"=1 ፣ ለ"B"=2 ......... እያለ አስከ "Z" =26ን ሰጠ ። በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ ።
1. ትጉ ስራ
(H+a+r+d+w+o+r+k)
(8+1+18+4++23+15++18+11)=98%
2. እውቀት
(K+n+o+w+l+e+d+g+e)
(11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96%
3. ፍቅር
(L+o+v+e)
(12+15+22+5)=54%
4. እድል
(L+u+c+k) = 47%
በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም መቶ ፐርሰንት (100%)
ለውጥ ሊሰጡ አንደማይችሉ አስቀመጠ ።
ታዲያ (100%) ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው? ገንዘብ ይሆን እንዴ??
5. ገንዘብ (M+o+n+e+y)
(13+15+14+5+25)=72%
አይደለም ምን አልባት አመራር ይሁን?
6. አመራር
(L+e+a+d+e+r+s+h+i+p)
(12+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97% አሁንም አይደለም! ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው። አስተሳሰብ ፣ አካሄድ አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል ። ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ
7. አስተሳሰብ
(A+t+t+i+t+u+d+e)
(1+20+20+9+20+21+4+5)=100%
እናም ወዳጄ ውጤትና የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው
✅የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አረጋገጠ
The secret of zion chalice ..የጽዮናዊዝም ጸዋ ማህበር ሚስጥር!
የ አለምን ታላላቅ ሚስጥራትን በመሰብሰብ፣ በማጥናት፣ እንዲሁም በረቀቀ መንገድ የራስ ለማድረግ በተለያየ ዘመን እጂግ ሚስጥራዊ የጸዋ ማህበራት ተመስርተዋል።
ከማህበራቱ ጥንክርና የተነሳ ለበርካታ መቶ አመታት ሰንሰለታቸው ሳይቋረጥ፣ ሚስጥራቸው ሳይገለጥ፣ ማንነታቸውም ይፋ ሳይወጣ፣ ዘመንን ያስረጁ፣ እጂግ ተጽኖ ፈጣሪ የጸዋ ማህበራት ይገኛሉ።
አንዳንዶቹ እጂግ በረቀቀ መልኩ ከመከናወናቸው የተነሳ ህልውናቸው ያለ እስከማይመስል ድረስ ህቡዕ ናቸው። ሚስጥራቸውም ከማህበራቸው የሚወጣው ከማህበሩ በድንገት አፈንግጦ የወጣ በሌሎች ማህበራት የተሰለበ ሰው ሲኖር ብቻ ነው ።
ከእኒህ ሚስጥራዊ የጽዋ ማህበራት አንዱ እና ዋናው የጽዮን የጽዋ ማህበራት ነው።
ጸዮናዊነት በሂብሪው እየሩሳሌም የሚል ትርጉም ሲኖረው ይህም ግንደ ቃሉ የተወረሰው ከመጻህፍ ቅዱስ ነው።
ይህ ሃይማኖታዊነቱ የገነነ፣ በፖለቲካውም ስር የሰደደ፣ እንቅስቃሴ በዘመናዊ መልክ በ19 ኛው ክፈለ ዘመን ቢቋቋምም ለበርካታ መቶ አመታት ከጀርባው ሚስጥራዊ እንቅስቃሴወችን ሲያከናውን የኖረ ማህበር ነው።
አሁን አሁን ይህንን ጽዮናዊነት መጠሪያ አለም እንዲረዳው የተደረገው በቋሚነት እስራኤላውያንን እንደ አሽዋ ከተበተኑበት አህጉራት ወደ አገራቸው ለመሰበሰብ የተቋቋመ ታላቅ ዝና ያለው ማህበር እንደሆነ ብቻ ነው።
ነገር ግን ይህ የጽዋ ማህበር እንደ አውሮፖ የዘመን ስሌት በ 1099 ወይም 11ኛው መቶ ክ/ዘመን በ አውሮፓ የተበተኑት ሊቃውነት በሚስጥር ተሰባስበው የመሰረተቱ የጽዮን ቤተ እምነት የተሰኘው ሃይማኖታዊ ተቋም በገሃዱ አለም የሚገኝ ሚስጥራዊ የሆነ ድርጂት ነው።
በ1975 በፖሪስ ብሄራዊ ቤተ መዛግብት (ቢብልዮቴክ ናስዮናስ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ና ሚስጥራዊው ሰነድ( ሌ ዶስዮ ስክሬ) ተብሎ የሚታወቀው የብራና ጽሁፍ እንደ ሰረ አይዛክ ኒውተን፣ ሳንድሮ ቦቲቼሊ፣ ቪክቶር ሂዩጎ፣ እና ገናናው ሊኦናርዶ ዳ ቬንች፣ ያሉ በርካታ በርካታ የጽዮን ቤተ እምነት አባላትን ስም ይፍ አድርጓል።
እኒህ አለም ላይ በዘመናቸው ገናና የነበሩ ሰወች ከተመሰረተበት ከ1099 እስከ 21ኛው ክ/ዘመን በተለያየ ዘመናት ተጽኖ ፈጣርያን ግለ ሰቦች የሆኑ የሚስጥሩ የጽዮን ማህበር መሪወችም ነበሩ።
ይህ ማህበር ለ900አመታት አካባቢ ሚስጥሩ እንደ ተጠበቀ፣ ህቡዕ እንቅስቃሴው እንደ ቀጠል ፣ አለም ላይ የነበሩ ሚስጥራዊ ኩነትና ታቦተ ጽዮንን ጨምር የቅዲስ ጽዋውን ቅርሶችን እንቅስቃሴወችን ሲመረምሩ ለመውሰድም ሲጥሩ እና ፍላጎታቸውን በስውር ሲያስፈጸሙ ኑረዋል።
ይህ ህቡዕ ድረጂት ሚስጥሩ በፖሪሱ ቢብልዮቴክ ናስዮናል ሚስጥራዊ ሰንድ እስከተጋለጠ ድረስ በርካታ እንቅስቃሴወቹን ከውኗል።
የእስራኤሉ የስለላ ድረጂት ሞሳድ ን ጨምሮ የጽዮን ፕሮቶኮሎች ከፍተኛ የመንግስት አካላት ና ፖለቲከኞች ጭምር ያሉበት አይሁዳውያኑ ስብስብ ወደ ፊት ክርስቶስ ይወለዳል በሚል አሁን በቅረብ የሰሎሞን ቤተ መቅደስን ገንበተው የሰሎምንን ታቦት የጽዮንን ጽላት ይጠባበቃሉ።
በእርግጥ የሌዋዊው ሙሴ ጽዮን፣ የሰሎሞን መጽናኛ ታቦተ ጽዮን፣ ከ እስራኤም ምድር ወደ ኢትዮጵያ ከወጣች እንሆ ሶስት ሺ አመታትን ስላስቆጠረች በረከት ከ እስራኤል ምድር ጸጋም ከእየሩሳሌም ተነስቷል...ወደ ሀገሯ ትመለስ ዘንድ የቅዱስ ሰሎሞን ምኞቱም ነበረች!
በሰሎሞን ስረወ መንግስት ከመነበሯ የተነሳችውን ጸዮን ወደ ፊት ይወለዳል በሚሉት በመሲሁ ኢየሱስ ትመለሳለች ብለው በቀቢጸ ተስፋ ቤተመቅደሱን አንጸው ጽዮንን ከመነበሯ ኢየሱስን ከዙፋኑ እስኪ መጡ ይጠበቃሉ።
ይህ ታቦተ ጽዮንን ከ ኢትዮጵያ ለመውስድ በተለያዩ አዝማናት ቢሞከርም ከመንበሯ ትነሳ ዘንድ ፈቃደ እግዚአብሔር አይደለምና ፈጽሞ ሊያገኟት አልተቻላቸውም።
በተለይ እስራኤል ከተበታተነችበት አገግማ በ1948 እንደ ሃገር ከተመሰረተች ወዲህ የጽዮን ጽዋ ማህበር ጨምሮ ሞሳድና የተለያዩ ሚስጥራዊ ተቋማት እንደ ኦፐስ ዴይ ያሉ የቫቲካን የካቶሊክ ሚስጥራዊ ማህበር እምነትን ከመመረዝ አንስቶ ታቦተ ጽዮንን ለመውሰድ ይሞክራሉ.. .. ግን አይችሉም ።
ለዚህም ነው ታቦተ ጽዮን የነበረችበት፣ ያለችበት፣ ወደ ፊትም የምትኖርበት፣ ሁኔታ እጂግ መግነጢሳዊ ሃይሏ በጊዜ የሚገለጥ ሚስጥበት
ያልተገለጠችው ኢትዮጵያ!
እንደቀደመው ነገሬ የሀገሬ የኢትዬጰያን የታሪክ እና የጥበብ ባለቤትነት የአባቶቻችን የእወቀት ጥግ የተሰወሩና የማይታወቁ ተገልጠውም ያልተተረጓሙ ቢተረጓሙም ያልተነበቡ ቢነበቡም የማናስተዉላቸው ግን እጀጉን የረቀቁ እጀጉንም ከአእምሮ በላይ የሚሆኑ የሀገሬ የኢትዮጵያ ሀብት ብራናወች ለማወቅ ለመረዳት እንዲሁም ስለፕላኔቶች ብዛት አወቃቀር ምህዋር የብራና መፃህፍቶቻችን ምን ይላሉ የሚሉ እና ሌሎችን ጥያቄወችን መልስ ሳፈላልግ መፀህፋትን ሳገላብጥ ጎግል ስጎለጉል ካገኘሁት ላካፈላችሁ ወደድኩ በኢትዮጵያ ምድር በ1900 ከክርስቶስ ልደት በፊት አሐሜኔስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሰው ነው። ይህ አሐሜኔስ የተባለው ኢትዮጵያዊ 16 ፕላኔቶች እንዳሉ የተናገረ ሲሆን፤ ፀሀይን ለመዞር ስንት ግዜ እንደሚፈጅባቸው፤ በስንት ምህዋር እንደሚዞሩና በውስጣቸው ያሉትን ፍጥረታትን ጽፍል።
፨ #NASA እንኳን አስካሁን እርገጠኛ የሆነው ዘጠኝ ፕላኔቶች እንዳሉ ነው ነገር ግን ገና 7 ፕላኔቶች ይቀራሉ።
፨ አሐሜኔስ መዝገበ ሰማያትና አውደ ከዋክብት የተባለው መፀሀፈ በታወቀው ቦታ ዋልድባ እሚገኝ ሲሆን ይህው መፀሀፍ ደግሞ ከዚህ በፊት በዚህ የቴሌግራም ፔጅ እንደፃፍኩት ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካ ውስጥ በስርቆት ተወስዶ በሚስጥር በጥብቅ እየተጠበቀ ተቀመጦ ይገኛል ፡፡
፨በነዚህ ፕላኔቶች ውስጥ ያሉ ፍጥረታትን በተለየ ቋንቋ ወደ ምድር አየሳቡ የምሥርን/የግብጽ/ ፒራሚዶችን ጨምሮ አለም ላይ ያሉ ሚስጥራዊ የጥንት ቅርሶችን የገነቡ ነበር ።
የምሥር/የግብጽ/ ፓራሚዶች የተሰሩት በሰው ልጆች ሳይሆን ከነዚህ ፕላኔቶች በመጡት ፍጥረታት እንደሆነ መፀሀፈ ምሥጢር ዘአደናይ ራፍኤል በተባለው መዝገብ ላይ እና ከዛው ፒራሚዱ ውስጥ በሚስጥር ተቀርጾ ይገኛል።
✦ እነዚህም ባለ ሥስት ማዕዘን ድንጋይ ያለስሚንቶና ያለጭቃ ሰው ሊሸከመው በማይችል በትልልቅ ድንጋይ ተነባብሮና ተደራርቦ በሚያስደነቅ ሁኔታ ታንጿል።
የጥንት ስሟም ምሥር የተባለችውም ግብጽ ኢትዮጵያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ምሥርን ስላበቀሉባት ምሥር እየተባለች ትጠራ ነበር የሚሉም አሉ ።
ኢትዮጽያ ውስጥም እንደ ምሥር/ግብጽ/ሀውልቶች/ ከብዙ ድንጋዮች ሳይሆን ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰሩ 700 ፒራሚዶች 600 የአክሱም አይነት ሀውልቶች ከነ ቤተመንግስታቸው እና በዙ የላሊበላ አይነት ሀውልቶች ይገኛሉ። ይህም አንድ ግዙፍ ከተማ ማለት ነው።
ነገር ግን እነዚህን ሀውልቶች ኢትዮጵያኖች አስቀብረዋቸዋል። እነዚህም ከተማዎች የጥንቷን ኢትዮጵያ ጥበብ ሸክፈው ይዘዋል። በኛዋ ምድር ኢትዮጰያም የጥበብን ጥግ ና የእወቀትን መጠን የሚያሳዬ እጅግ ጥበባዊ የሆኑ ፒራሚዶች አሁንም በኢትዮጰያ ምድር በተለያዩ አካባቢወች ተሰውረው ይገኛሉ። እነዚህን ሀውልቶች የት እንደሚገኙና በስንት ሜተር እርቀት ቆፍሮ ማውጣት እንደሚቻል ዋልድባ ባለው መዝገብ ላይ እሚገኝ ሲሆን፤ ነገር ግን የመገሐጫ ጊዜው እስኪደርስ በሚስጥር ተይዟል።
ለምሳሌ ያህል ደግሞ በቅርቡ በቁፍሮ የወጣውን እንዲሁም በጥበበኛው መነኩሴ የታነፀዉ የዳግማዊ ላልበላን ሀውልት ማየት ይቻላል። ዮሐንስ በራዕዩ ሲከፈት ያየው ቤተ-መቅደስ እነዚሁ የላልበላን ሀውልቶች እንደሆኑ አባ ተስፍ ስላሴ ሞገስ ያስረዳሉ።
እንደ ምንጭነት የተጠቀሰውም የምሥጢሮች ሁሉ ቁልፍ የሆነው መፀሀፈ ምሥጢር ዘአዶናይ ራፍኤል ሲሆን ይህም መፀሀፈ እጅግ በጣም ብዙ ምሥጢሮችን የያዘ ሲሆን መፀሀፍ ሙሉ በሙሉ ቢተረጎም እጅግ በጣም የሚያሥፈራና አስደንጋጭ ታይቶና ተስምቶ የማይታወቅ ከሰው ልጆች በላይ የሆነ ምሥጢር አለው፤ ሁሉም ነገር እንደ ፈጣሪ ፋቃድ በጊዜው ይሆናል።የተለየ መንፈሳዊ አይን ያለው ሰው ግን አሁንም እነዚህን የፒራሚድ ከተሞች መመልከት ይቻላል፡፡
ወደ ፊት መልካሙ ጊዜ ሲመጣ የተሰወሩት ይገለጣሉ ኢትዮጵያን የናቋት ሁሉ ከእግሯ በታች ይሆናሉ ዛሬ የሳቁባት ነገ የመከራቸው መሸሸጊያ መረከብ ትሆናቸዋለች ያኔ አለም እንዲህ ይላል ''ኢትዮጰያ ተነሳች'' ይባላል ኢትዮጰያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች ይላልና ትንቢቱን በዘመን ውስጥ ይገለጣል።
#የመረጃ_ምንጮቸ፦
፩) አባ ተስፍ ስላሴ ሞገስ መጣጥፎች
፪) ሔኖክ ዘአዶናይ