ተጓዡ ልቤ
✍በየሱስራ ተፅፎ
🎙በሀና አዲስ የቀረበ
ሴት ልጅ እናትህ ህይወትህ ናት መናገርን ባሥተማረችህ አንደበትህ ክፉ ቃል አትናገራት።!!!!!!!!
#ከእንጃ_ባሻገር
ተራራ የሚያህል ፥ ግዙፍ እምነት አለኝ
ለምንድነው ታዲያ
የሰናፍኝን ቅንጣት ፥ በመግፋት ያልተቻለኝ?
እንጃ!
ክሀሳብ የሰነፉ
ሰፊ መንገድ ኖሮኝ ፊቴ የተሰጣ
ከቶ ለመንድን ነው
ለመሔድ መጋፋው ፥ መርገጫ እስከማጣ ?
እንጃ!
በብርሐን ፍጥነት ፥ መፍጠን የምችል ሰው
ለወንድነው ታዲያ
ቀድሜ ወጥቼ ፥ አርፍጄ ምደርሰው ?
ከቶ ለምንድ ነው
ለጥያቄዬ መልስ ፣ እንጃ የማበዛው?
እንጃ !
ከቶ ለምንድን ነው
ለጥያቄዬ መልስ እንጃ የማበዛው?
እንጃ!
እሺ ለምንድነው ?
ነፃ ያደልኩትን ፣ በውድ የምገዛው ?
እንጃ!
ታድያ ለምን ይሆን
መልስ አልባ ጥያቄ የምፈለፍለው?
እንጃ !
እንጃ!
እንጃ!
ብቻ አንድ እውነት አለኝ እንጃ የማልለው
ከሙሉ ነገር ላይ መጉደል ነው ሚጎድለው።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ከአረፍተ ነገር ወደ አረፍተ ሀገር
።።።
ምንሊክ ተወልዶ ፣ ባያነሳ ጋሻ
ይናፍቀው ነበር ፣ ሀጎስን አንባሻ ።
።።።
ምንሊክ ተወልዶ ፣ ባያሸንፍ ነግሶ
ይናፍቀው ነበር ፣ ለ አበበ በሶ ።
።።
ምንሊክ ተወልዶ ፣ ጠላትን ባይቀላ
በጨበጠው ጩቤ ፣ ይሞት ነበር ጫላ ።
።።
እምዬም አብዬም አፄ ምንሊክ እንኳን ተወለዱልን።
/channel/belaybekeleweyaa
ምን አገባኝ ለሷ፤
ለመጣው ለሄደው ለምትገልብ ቀሚሷ፤
ድንግል ነች ይላሉ ተደፍራ በልጇ፤
ምን አገባኝ ለሷ፤
ወንበር ለማይገባው፤አድላ አድላ፤
ዞራ ታለቅሳለች ልጆቿን ሲበላ፤ (የአዞ እምባ)
ምን አገባኝ ለሷ፤
ጀግና ለምትበላ፣በይዋን አክርማ፤
ምን አገባኝ ለሷ፤
ምን አገባኝ ብዬ ላይሆንልኝ ነገር፤
ልሸልል አልኩና "እኔ ቀልድ አላቅም በእናትና ባገር፤
ስሸልል ስሸልል ጀግናዋ መስያት፤
ደሞ እንዳትበላኝ የለመደች መብላት፤
አይደለሁም ጀግና፤
እኔ እንደው ፈሪ ነኝ ለሷው የምፈራ!!፤
#ኢልያስ #ሀበሻ
@poemers @poemers
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
""""""""""""""""""""''''''''''''''''''''
አያታለሁ ሁሌ
አምራ ተንቆጥቁጣ
ከመንገዱ ቆሜ፤
ለሰው ቀልብ በማይስብ
ቆሻሻ ....አዳፋ
ልብሴን አገልድሜ፤
ባረጀ ወዘና
በገጠጠ አጥንቴ
በከሲታ አቋሜ፤
ለአለም የከበደ
ፍቅር ተሸክሜ፤
አልሃምዱሊላሂ አያታለሁ ሁሌ!
(አለሁ)
አለች
ከተንቆጠቆጠው
ከዚያ ማዶ ህንፃ፤
በህይወቴ ማህደር
የውበት ማህተብ
እንዳይጠፋ ቀርፃ፤
የልጅነት ፍቅር
የማይዘም የማይፈርስ
ልቤ ላይ አንፃ፤
አለች እንደዋዛ
በደመቀ ውበት
ህይወቴን አፍዝዛ!
.
.
አልሃምዱሊላሂ እኔም አያታለሁ
.
.
ሄጄ ለሰላምታ
እጆቼን ደፍሬ
ሰጥቻት ባላቅም፤
እሷን እሷን ብዬ
የፍቅር ስካር ይዞኝ
አቅፌያት አውርቻት
ደስ ብሎኝ ባልስቅም፤
በወዝአደርነት
እቃ ተሸክሜ
ካለችበት ህንፃ
ሳልፍና ሳገድም፤
ሰርቄ አያታለሁ
ሰርቄ ሳላያት
ጀንበር አዘቅዝቃ ፀሀይ አትጠልቅም!
.
.
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
.
.
እሷ የጠፋች ለታ
ዕውቀት ብርሃኔ
በከንቱ ቢቀርም፤
ከንዋይ ጎድዬ
ከኑሮ መቀመቅ
ዘቅጬ ብቀርም፤
አይቻት ውላለሁ
አይቻት አድራለሁ
አልሃምዱሊላሂ ከቶ አላማርርም!
.
.
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
.
.
አፍቅሪያት መውደቄን
አይታና ተረድታ
ገምታኝ ባታውቅም፤
ለፍቅር ባከነ
የሚል ስም አልብሶኝ
በዱንያ ዓለም ሰዉ ቢሳለቅም፥
እውነተኛ ፍቅር
መስጠት ብቻ እንጂ
መቀበል አያውቅም፤
ውለታ አይጠይቅም!
(አለሁ ....አለሁ እኔ)
በኑሮ እስርስር
በህይወት ውትፍትፍ
ችግር ተጣልፌ፤
እስከምሞት ድረስ
የፍቅሯን ዘምዘም
ለልቤ አጠንፍፌ!
ሲርበኝ ሲጠማኝ
ከህንፃዋ ማዶ
ሄጄ ተመልሼ፤
የችምችሙ ጥርሷን
የሂጃቧን ጥምጣም
የዓይኖቿን ንጣት
የጉንጮቿን ቅላት
በሩቁ አይቼ አካሌን አርሼ፤
አልሃምዱሊላሂ
እኔ እንዳለሁ አለሁ
ፍቅሯን ተንተርሼ!
.
.
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት
.
.
ደስ ብሎኝ ውላለሁ
ደስ ብሎኝ አድራሁ
ከሩቅ ስመለከት ስትስቅ አይቼ፤
ኑሮ ድባቅ መትቶኝ
ከህይወት ጎድዬ
ከፍቅር ሞልቼ፤
የህይወት መጥፎ እጣ
የዓለም ክፉ ፅዋ
አላግባብ ተግቼ፤
እየተገላበጥኩ
በውበቷ ዱላ
ልምጭ ተመትቼ!
(አለሁ ....እናማ)
ንገሩልኝ ስሞት
ጅናዜ ወደ አፈር
እንደተቀበረ፤
በሉልኝ ሄዳችሁ
በጣም የሚያፈቅርሽ
አንድ ሰው ነበረ፤
ከውበትሽ ቀምሶ
በአይን ፍቅር ፈዞ
ቀልቡ እንደሰከረ፤
ስምሽን ሲያነሱለት
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት እያለ፤
በሳቅሽ የሳቀ
በሀዘንሽ ያዘነ
ዱኒያን ካንቺ ላይ
ገንብቶ የኖረ፤
አንድ ሰው ነበረ....!
(ብላችሁ ንገሯት)
አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት!
.
.
.
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Run_Viva_Run
ከአሌክስ አብርሃም ዙቤይዳ መፅሀፍ ከ"አልሃምዱሊላሂ ደህና ናት"በሚለው አጭር ልብ ወለድ ፅሁፍ የተመሰረተ
።።።።።👇👇👇👇።።።።።
።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/joyefk🦋🦋
@poemers
ሀጫሉ ሁንዴሳ ስለ ኢትዮጵያ ካዘመው ...
።።
ልጆችሽ ዓለሜ ፣ ያውም በዚህ ዘመን
በርስት ይጣላሉ ፣ ሲሉኝ እንዴት ልመን?
።።።
ያልፋል ይህም ቀን ያልፋል
ልጅሽ ወንድሙን ያቅፋል ።
#ሼርርርርርርርርር
@belaybekeleweyaa
@poemers @poemers
#ቀጥረሽኝ_ፈላስፋ_አደረግሽኝ
“ላገኝህ” ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፥ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፥ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬ'ት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፡ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በ'ላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፥ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
ሰዓቱ እስኪደርስ ፥ ሰዓት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፥ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን
እንዴት እንደምሔድ ፥ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፥ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዱ እግሬን ስጎትት ፥ አንዱ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፥ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፥ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፥ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው!
ሊስትሮ ጋር ሔድኩኝ ፥ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው ...
በወስፌ መንጠቆው ፥ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፥ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ !
“የህይወት ትንሽ ሽንቁር
ጊዜና ግመልን ፥ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፥ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
እየተጣደፍኩኝ….
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፥ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፥ “ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፥ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ…
“መፈለግ ነው” ብዬ ፥ የፍልስፍና አቅም፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፥ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፥ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፥ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፥ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፥ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ
ትቼው መጥቻለሁ ፥ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር
ላይጠግን ይሰፋል ፥ በወስፌ ተቀዶ።
እፈላሰፋለሁ !
ቀድሜ መጥቼ ፥ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ
እጅጉን ይሻላል ፥ አርፍዶ የመጣ፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ሰው የሚሉት ፍጡር..
ነፍስ ከስጋ ጋር ፥ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፥ ፍፁም የሚስተው፡፡
እፈላሰፋለሁ !
ቀድሜሽ መጥቼ ፥ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፥ ማይጠነቀቀው!!
@poemers @poemers
@poemers
* ፀሎቴ *
፡
ምነው ባደረገኝ ያንገትሽ ላይ መስቀል፣
ከጡቶችሽ መሀል ሁሌ እንድንጠለጠል፣
፡
ምነው ባደረገኝ የእግርሽን አልቦ፣
ሲናፍቅ ከሚኖር ልቤ አንቺን ተርቦ፣
፡
እዘዪኝ በጀርባሽ ልረፍም ከዳሌሽ፣
ውሃ ተሸክሜ ገንቦውን ሆኜልሽ፣
፡
መደብሽስ ብሆን እንደው ምን አለበት፣
የዛለው አካልሽን ምታሳርፊበት፣
፡
ልሁንም ትራስሽ ለአንገትሽ ድጋፍ፣
ዘንዶ መሳይ ጠጉርሽ ቆሌዬንም ይግፈፍ፣
፡
ተጫሚኝ ግዴለም ጫማ ልሁንና፣
አብሬሽ ልኳትን በዱር በጎዳና፣
፡
ልበሺኝ ልብስ ሆኜ እርቃንሽን ልጋርድ፣
ከገዳዩ ገላሽ አጥብቄ ልዋደድ፣
፡
ልሁን ሽፋሽፍትሽ ከአይንሽ ስር ልኑር፣
ነቅቼ ልጠብቅ ልክ እንደ ወታደር፣
፡
ሸብ አርገሽ እሰሪኝ ውዴ ከወገብሽ፣
አጥብቄ ልቀፍሽ ሆኜ መቀነትሽ፣
፡
ካሻሽም አለሜ፣
፡
ንግስቴ ሆኚና ሎሌ ሆንሻለሁ፣
ያልሽኝን በፍቅር እታዘዝሻለሁ፣
፡
ምንጣፍም ያድርገኝ ለእግርሽ መረገጫ፣
ምቾት እንዲሰማሽ እንዳይነካሽ ጭንጫ፣
፡
ምነው በሆንኩና አዝማሪ የቤትሽ፣
ማስቆዬን ይዤ እልፍ ባዜምልሽ፣
፡
ልክ እንደ በውቀቱ ዕውቀትን ቢያድለኝ፣
ምን ነበር ስላንቺ ገድል ቢያስከትበኝ፣
፡
ውሃመም ያርገኝና ልፍሰስ ከበላይሽ፣
በጉንጭሽ ወርጂ ልሙት ከደረትሽ፣
፡
አንዴ ብሆን ምነው የመሶብ እንጀራ፣
ተዋድጄ በኖርኩ ከአንጀትሽ ጋራ፣
፡
ፀሎቴ
፡
አንቺን የኔ ብቻ የግሌ እንዳረግሽ፣
ፀሎቴ ይሄ ነው አያርገኝ ዘመድሽ፣
#share_join
@manbabemulusewyaderegal
@poemers
የላኩልሽን ግጥም እያነበብሽው ነው?
ግን እኮ ዓለሜ
ይህ ሁሉ መወድስ ይኼ ሁሉ ግጥም
እንኳንስ ልብሽን ስምሽን አይበልጥም፡፡
ከገነት ቢፈልቅ የነፍስ ማይ
አይንሽ አይደለም ወይ የገነትም ሰማይ፡፡
በቀኝ በግራ ቢደረደር
የሰው ዘር
ነፍስ ሁሉ ሚዛን ላይ ቢወጣ
የፀደቀ ፀድቆ ያጠፋ ቢቀጣ
ኤልያስ ምን ተዳው?
ባይፀድቅ ቢቃጠል መንደደን ቢቀምሳት
አይንሽ ማጣት ነው የዘላለም እሳት፡፡
:
ይህ ሁሉ መወድስ ይኼ ሁሉ ግጥም
እንኳንስ ልብሽን አይንሽን አይበልጥም፡፡
💪መበርታት መጀገን ከፈለክ በዙሪያህ ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ በተለይማ ራስህን ለመለወጥ ስትፈልግ አይን የሚገልጡ ሁኔታዎች ሞልተዋል ካንተ የሚጠበቀው ለመማር መዘጋጀት ነው። አትርሳ ወዳጄ ተማሪ ካለ አስተማሪ የትም ቦታ አለ!
ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@poemers
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
"""ነበርን ብንኖር"""
እንደ ሰዶም ሀገር ፡ የፈጣሪ ቁጣ፣
የሴቶችን ዳሌ ፡ ሊያጠፋ ቢመጣ፣
"ወደ ኋላ ዞረህ" እንዳታይ ተብሎ ፡ ለወንዶች ቢነገር፣
ልክ እንደ ሎጡ ሚስት፣
የጨው ሐውልት ሆነን ፡ በደረቅን ነበር።
✍ በላይ በቀለ ወያ
@poemers @poemers
ሀሞት
ፀሐይዋ ካልገባች
ጨረቃም ካልጠፋች
ጥላህ አይለቅህም
ክፉም እንደዛው ነው
ገዝግዞ ካልጣለህ
አንተን አይርቅህም።
ገጣሚ፦ሰለሞን ሳህለ ትዕዛዙ
#ያፍቃሪሰውትንፋሽ
@poemers
መተሽብኝ ነበር :
ለሊት ላይ በህልሜ፣
አቤት ብዬም ነበር :
ስምሽ መስሎኝ ስሜ፣
ግና ሳልጨርሰው :
ፍቅርን አጣጥሜ፣
ፍጥን እንደ ንፋስ :
እጥር እንደ #ጳጉሜ፣
..............አልሽብኝ አለሜ ።
✍ Yibest Belay
@kidapoim
ጥቂት ነው ምኞቴ
(በእውቀቱ ስዩም)
እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ከድፍና ከግፍ
የጠዳ
በረንዳ
እዚያ ላይ መቆየት ፥
ከሚደምን ዛፍ ላይ ፥ ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤
አኔ በህይወቴ
ጢኖ ነው ምኞቴ
ለከርስ ጤፍ እንጀራ
ለነፍስ ባለንጀራ
ድክመቴን ስናዘዝ ፥ተግቶ ሚያዳምጠኝ
በደሌን መዝኖ ፥ ቀኖና እማይሰጠኝ፤
እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ሊሞላ የቃጣው፥ ደርበብ ያለ ኑሮ
በስዊዝ ቤተ-ንዋይ፥ ሶስት መቶ ሺህ ዩሮ
ደሞ ከተቻለ፥ ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ
እግዜርና ሰይጣን ፥ተጋግዘው የሳሏት
ቢቻል ትንሽ ቪላ ፥አስር ክፍሎች ያሏት
ግና ምኞቴ ሆይ ፥ እንዲያው ለመሆኑ
ጥቂት ብሎ ነገር ፥ስንት ነው መጠኑ?
@getem
@getem
@beckyalexander
(ከማለዳ ድባብ)
ነጠብጣብ ሐሳቦች
ሰማይ ከሚመክን ፤ይጸንስ መከራ
ያርግፍ ! ያርግፍ! ያርግፍ ! መኣት እያፈራ
የ’ሣት ዛፍ ባለበት ፤ ሰደድ አያስፈራ
ከሐምሌት ጋር ሞቷል፤ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፤ አለመሆን የለም
ሸክም ጸጋ ሆኗል፤ ጸጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ፤ ትከሻህን አስፋ!
አንድ ሕልም እንደ ጠጅ፤ እየደጋገሙ
ንግር ፤ትንቢት ሳይሆን፤ ታሪክ እያልለሙ
ተኝቶ መነሣት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሣት
ነፍሴን እንቆቅልሽ
@poemers
#ግጥም
🎧 ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ
እንባኪ ከያ (keya)
ፀሀፊ በዕውቀቱ ስዩም
#share_join
@manbabemulusewyaderegal
@poemers
ርዕስ: ማነው ሚፋረድሽ?
አንቺ
ፀሀይና ዝናብ ቢፈራረቅበት : ፊትሽ ጠወለገ
ደም ተተፋ ካይንሽ : እንባሽም ደረቀ
እግሮችሽ ደቀቁ : ደከሙ አቃታቸው
ከአቋቋምሽ መብዛት : መራመድ ጠፋቸው
በዘመን ቋጠሮ : ፀጉሮችሽ ነጭ ሆኑ
በፈዘዙ ጥርሶች : ሳቆችሽ ደመኑ
እኔን በመጠበቅ : ቀኖችሽ አርጅተው :
: ጥለውሽ ሄደዋል
ከመዘርጋት ብዛት : መታጠፍ የረሱ
: እጆችሽ ደክመዋል
እኔ
ፊቴን ብቻ አውቃለሁ : ጀርባዬን እኔእንጃ
ናፍቆትሽ ነው እንጂ : አካልሽ መች መጣ
ምን እንደሚጠብቅ : ልቤ ተረስቶታል
ብዙ ከመቆሙ : መቀመጥ ጠፍቶታል
ሁሌ እጠብቃለሁ...
ሲበርደኝ እትት : ሲሞቀኝ እየየ
በመጠበቅ ብዛት : ላረጀው እኔየ
አቅም ላጣ አካሌ : መጠበቅ ላስረጀው
ለደከመች ነፍሴ : ናፍቆት ላደረጀው
እየየ ነው እንጂ : ምን ይባላል ሌላ
ውል በጠፋው ፍቅር : ለደከመ ገላ
እኚህ ሁለት ልቦች : ማይተዋወቁ
በማይደርስ ሰው ናፍቆት : ከሰሙ ደረቁ
ከማይሆነው ቦታ : ጠብቄሽ ብትቀሪ
ማነው የሚጠየቅ : አንቺ ነሽ? ፈጣሪ?
ከጠበቅሽኝ ቦታ : ባልገኝ ባልላክ
ማነው ሚቀጣልሽ : እኔ ወይስ አምላክ?
አየሽ
አቋቋሙ ያላማረ : መዳረሻው ይጠፋዋል
ማያውቀውን ሲጠብቅ ሰው : የሚያውቀውም ያመልጠዋል
በአቤኒ
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@poemers @poemers
@poemers
አገሬ
አገርን ለፈሪ ፤ አይሰጡም አደራ
ዳር አድርጎት ያድራል ፤ የማሀሉን ስፍራ፤
አገርን ለፈራ፣ አደራ ብሰጠው የዘላለም ቤቴን፣ባንድ አዳር ለወጠው፣
አባ ነጋ ሞቶ
አባ ጽልመት መጥቶ
አገሬ አንደ ዛጎለ፣ እያብረቀረቀች
ከባሕር ተገፍታ ፣የብስ ላይ ወደቀች።
[ በእውቀቱ ስዩም ]
ከ አድማስ ማዶ ከዚያ ወዳ
ውብ ተፈጥሮ መልክዓ ሜዳ
ጀምበር ሳትጠልቅ አፈንጥቃ፣
ነይ እንሂድ አንዳበባ አንፈንድቃ።
✍የሱፍ
@poemers
. የገሀነም መዝገብ
አንድ ጦማር አንድ መዝገብ
አምልጦ ወድቆ ከሠማይ
ወደገሀነም የሚገቡ
ሰዎች ዝርዝር የሚያሣይ
አነሣሁትና ሥበር
ከራሤ ሥም አሥቀድሜ
የፈለኩት ያንቻን ነበር
ይስማከ ወርቁ
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poemers
ሳይሽ ደስ ዪለኛል
ተርቦ እንደመብላት ሰው ናፍቆ እንደማግኘት ሳይሽ ደስ ዪለኛል
አምናና ታች አምና ያፈቀረሽ ልቤ እንዲህ በል ዪለኛል
ሂድና ጥራልኝ ፍቅሬን ግለጽልኝ፣ ባታወራት እንኳን አይን አይኗን እይልኝ፣
ብሎ ቢያስጨንቀኝ...
አንችኑ ወዳጁን ፍለጋ ደጅ ደጁን ማተርኩኝ፤
በለስ ቀንቶኝ ሀባሲያው ዘልቄ ቋጥኝ ተሸሽጌ ፣
ስመለከት ኖሮ ሀተራራው ግርጌ፣
ባባትሽ አሽከሮች ዙሪያሽን ትጅበሽ ስትዘልቂ አየሁሽ።
በኔ አይን ስትታዪ፤ የዉበትሽ ፍካት ጨረቃን ያስንቃል
የ ፈገግታሽ ብርሃን ከጸሃይ ዪሞቃል፣ እዉር ያስቦርቃል፣
የተከዝሽ ጊዜ ጋሞራ ዪበርዳል፣ ጸሃይ ትጠፋለች፣
ጨረቃም ከማጀት ገብታ ትቀራለች።
አዎ ዉዴ ያላየሁሽ ጊዜ ዪጠናወተኛል
ልቤ አላፊ አግዳሚውን ፍጥረቱን በሞላ ባንቺነት ዪመኛል
እያንዳንዷን ኮቴ የሷ ነው ዪለኛል
አንቺን በመማተር ሺህ ዜማ ዪቀኛል።
ባንጻሩ ስትመጪ፣ አፌ ምን ቢለግም
የልቤን ፈንጠዝያ የሚገዳደረው አንዳች ስሜት የለም
እናልሽ አለሜ ሃዘንሽ ሃዘኔ፤ ሳቅሽ ሳቄ ሁኖ ዪተናነቀኛል
ሁልጊዜ ሳቂልኝ ደስ ብሎሽ ሳይሽ ዪበልጥ ደስ ዪለኛል።
ገጣሚ : የሱፍ
@poemers @poemers
ክፉም ንጉስ መጣ
ደግም ንጉስ መጣ
ብቻ ግን ያልፋሉ ፣ ሁሉም እንደመልኩ
ይብላኝ ከህዝብ ጋር
ለሚጣሉ ህዝቦች ፣ መሪ እያመለኩ !!!
✍በላይ በቀለ ወያ
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poemers