እስኪመስልብን ሱስ እስኪመስል አባዜ
ልባችን ተሰብሯል ብዙ….ብዙ ግዜ ፤
የወደድነው ሲሄድ ያመንነው ሲከዳን
ያተርፈናል ያልነው ሲጥልብን ዕዳን
ይቻለናል መዳን ?
ውሸት!
ሁሉም ልብ ውስጥ አለ የሀዘን ጥላሸት!
ከ ዕለታት አንድ ቀን…
ይሄ ምስኪን ልቤ አንዲት ሴት አፍቅሮ
እየሳቀ ገባና …ወጣ አቀርቅሮ ፤
ቢያልፍም እንኳ ግዜ …ቢየልፍም እንኳ ዘመን
እስካሁን አልወጣም ከ ሀዘን ሰመመን፤
የረሳ ቢመስልም …
አሁንም ይፈራል አሁንም ይባባል
ደንብሮ ይሸሻል ገና ፍቅር ሲባል፤
ከሚስቅ ሰው ጀርባ ፤
አንገት አቀርቅሮ አንብቶ ቁጭ ያለ
አንድ ታሪክ አለ !
እናም…
አታውቀውምና ፤
ሰው አልፎ እንደ መጣ በየት መንገድ በኩል
ለመፍረድ አትቸኩል ።
[ እዮብ ዘ ማርያም ]
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
ልክ እንደ በደሌ እንደ ሀጢአቴ ብዛት
ሳይሰጠኝ ለክፉ ሳይሰጠኝ ለ እርዛት ፤
እኔ ልጁን ምሮ
አመትን ጨምሮ
ለዚህች ደቂቃ ላደረሰኝ አምላክ
ከምስጋና በቀር ምን አለ የሚላክ?
ተመስገን!
መልካም ልደት ለ እኔ🎂
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@eyob567
ሰኞ ሰኔ 12 በዓለም ሲኒማ ሠኔ 16 17 እና 18 እንዲሁም ሠኔ 23 24 እና 25 በተመረጡ የግልና የመንግስት ሲኒማ ቤቶች በድምቀት ይመረቃል። #ሚያዚያ!
ምንተስኖት ለገሰ! GOOD LUCK BRO 🤞
<<አይደለም ምኞቴ>>
አይደለም ምኞቴ…
ጡቶሽን ማለብ
ቀሚስሽን መግለብ
እጭንሽ ስር መግባት ባገኘሁት ሰበብ፤
አይደለም ምኞቴ….
እንደ ኮርማ በሬ እላይሽላይ መውጣት
ፍትወቴን ማስታገስ ስሜቴን መወጣት
እነዚህን ሁሉ ፤
አላስብም ጭራሽ አላስብም ቅንጣት
ልንገርሽ አይደለ?
የመንፈሴን መሻት የልቤን መመኘት
ከነፍስሽ ዜማ ጋ ዜማየን መቃኘት፤
የደማ ስሜቴን …
በሀሳቦችሽ ማከም በቃሎችሽ መግራት
ከጎንሸ ቁጭ ብዬ አይንሽን እያየሁ…
ምትዪኝን መስማት ሚሰማኝን ማውራት፤
አየሽ …
ካካላችን በፊት ነፍሳችን ከጋለ
ከልባችን ግድም ፍቅር ከበቀለ
አልሰገበገብም …
ገላሽ ላይ ደርሳለሁ ገላሽ ሁሌም አለ!
አዎ …
አስገድጄሽ ሳይሆን: ፍቅሬ አሸንፎሽ ገላሽን ስትሰጪኝ
ያኔ ነው እንደ ማር የምትጣፍጪኝ!
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
ሰላም ወዳጆቼ እንዴት ናችሁ, ብዙዎቻችሁ “የደከሙ ገጾች” መፅሀፍን የት እንደምታገኙ ስትጠይቁኝ ነበር ! የተወሰነ ኮፒ (40 ) እጄ ላይ ስላለ ከዛሬ ጀምሮ መውሰድ ትችላላችሁ!
የ 1 መፅሀፍ ዋጋ 100 ብር (1000213882728 cbe) ማስገባት ትችላላችሁ! @eyob567 👈🏾 በዚህ ደረሰኝ ላኩልኝ! አመሰግናለሁ🙏🏾
@poeteyobzmariam
ሄለን በጣም የምትገርመኝ ሴት ናት! ፕሮግራሟ (ሄለን ሾው) EBS ቴቪ ላይ መተላለፍ ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል! በዚህ ሁሉ አመታት በስህተት አንድ ቀን በፕሮግራሟ መሀል ማስታወቂያ ሲመጣ አይቼ አላውቅም( በእርግጥ ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች ሆይ ሆይታ እንጂ ሀሳብ ያለው ነገር ስፖንሰር አያደርጉም🙂) በረጅሙ የግዜ ሂደት ውስጥ በመሰላቸት ከመስመር ሳትወጪ ከቢዝነስ ይልቅ ሀሳብን! …ከተራ አሉዋልታ ይልቅ ጥልቅ ውይይትን ስላስቀደምሽ በጣም አከብርሻለሁ! Hats off🎩🙏🏾
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@Poeteyobzmariam