ሰላም facebook የምትጠቀሙ ወዳጆቼ! ከስር የማስቀምጥላችሁ link የስነፅሁፍ ውድድር እየተካሄደበት ያለበት page ነው!...comment ላይ እየገባችሁ eyob z mariam በሚል pofile የተፃፈውን "ናተይ" የሚል አጭር ልቦለድ like እንድታደርጉ ጠይቃለሁ...አመሰግናለሁ🙏
link
👇
https://www.facebook.com/share/p/VX6SuiXZcyYYBnmY/?mibextid=oFDknk
link አልሰራ ካላችሁ @ሙስተጃብ ነኝ በሚል የፌስቡክ ስም ታገኙታላችሁ!
ለ እናቴ!
ይመስለኝ ነበረ፣
የልብ ሀሳብ ሁሉ በቃል የሚወጣ
አንቺ ጋር ስደርስ፣
ቃል ወዴት ገደመ ቃል ከወዴት ላምጣ?
ትሰቂያለሽ እኮ ልብሽ እያነባ
ህመምሽን አይቶ፣
ልጅሽ እንዳያዝን ሆዱ እንዳይባባ
ትስቂያለሽ እኮ፣
ሆድሽ እየራበው ጉሮሮሽ ተጠምቶ
ልጅሽ እንዲጠግብ፣
ልጅሽ እንዲረካ ያንቺ አካል ሳስቶ
ሰው ወረተኛ ነው ግብሩ ያስታውቃል
ቀን ሲጥል ይሸሻል ከሌላ ይጠጋል
በመዓልት አብርቶ ሌት ይጠወልጋል
ሰላም ላካላትሽ፣
ቀንን ተከትለው ወረት ለማያውቁ
ሰላም ለጥርሶችሽ፣
ስሜትን ሸሽገው ዘወትር ለሚስቁ
እማ ያንቺ ፍቅር፣
ከሀሳብ የሰፋ~ከጠፈር እርቀት እጅጉን የራቀ
ማይገቡት ጥልቅ ነው
ማይፈቱት ቅኔ ነው እጅግ የረቀቀ
አንቺ የገነት ቁልፍ፣
የእውነት መወጣጫ የህይወት መሰላል
ምድር ተዘቅዝቃ፣
ጉያዋ ቢፈተሽ አንቺን ማን ይመስላል?
የመኖር ፍቺ ነሽ፣
የህይወቴ ዝማሬ የነፍሴ በገና
እማ ክፉሽ ይራቅ፣
ግዜሽ ሁሌም ይኑር ሞት ባንቺ ይቅርና!
(እዮብ ዘ ማርያም)
Join
@Poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
ቲክቶክ ላይ ከ ግጥም ባሻገር ታሪኮችንና…ወጎችን በፅሁፍ ማጋራት ስጀምር ሰዉ ምን ያህል ያነባል ሚለዉን ቼክ ለማድረግ ነበር! እስካሁን ከ 30 በላይ ታሪኮችንና ወጎችን ፅፊያለሁ!…ከምጠብቀው በላይ የሚገርም ምላሽ ነው ያገኘሁት!…የሰዉ የንባብ ባህል ማደግ ላይ የራሴን ትንሽዬ አስተዋፅኦ ማድረግ በመቻሌም በጣም ደስተኛ ነኝ😊
ካጋራኋቸው ታሪኮች መሀከልም! “ናተይ…” የሚለውን story ወደ ፊልም የመቀየር ሀሳብ አለኝ!…እንቅስቃሴም ጀምሪያለሁ! እና ይህን ሀሳብ ማገዝ የምትፈልጉ (የምትችሉ) ወዳጆች በውስጥ አውሩኝ! አመሰግናለሁ🙏
[tiktok acc,]
👇🏾
eyobzmariam" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@eyobzmariam
የተሰረቁ ግጥሞቼን ብዛት ቤቱ ይቁጠረው🙂 ለሰው ግጥም ስም ጠቅሰው ተገቢውን credit የሚሰጡ ጨዋ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ብዙ አይን አውጣ ሌቦችም አሉ!…4 years ago in 2018, I wrote this poem based on Bob Marley's quote!
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
አንዳንዴ አለ አይደል
ፅኑ ያልከው ልብህ፣
ጥንካሬው ጠፍቶ ሲገባብህ ገደል
አንዳንዴ አለ አይደል
ቀጫጫ ህይወትህ፣
ድራሹ እንዲጠፋ ሲመታ በጠብደል
አንዳንዴ አለ አይደል፣
የምታፈቅራት ሴት፣
ስትሆንብህ ህመም ስትሆንብህ ዕዳ
አንዳንዴ አለ አይደል
በምታፍቅሪው ወንድ፣
ልብሽ ሲንኮታኮት ደጋግሞ ሲጎዳ
ብቻ...
ሁሉም በልቦናው ሸሽጎ የያዘው
ልክ እንደ መጋዝ ጥርስ፣
ሲሄድም ሲመጣም የሚገዘግዘው
ልክ እንደ ጠባሳ፣
ላይጠፋ ተስሎ ልቡን ሚያቆስለው
ለሰው ማያወራው ድብቅ ህመም አለው!
(እዮብ ዘ ማርያም)
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
100k ቤተሰቦች🥂 አመሰግናለሁ🙏
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
Instagrams
http://www.Instagram.com/eyob_z_mariam
Tiktok
eyobzmariam" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@eyobzmariam
[በስቅለት ቀን ያጋጠመኝ አስገራሚ ክስተት]
:
መስገጃ ቦታ እንዳላጣ ብዬ በግዜ ብሄድም አልተሳካልኝም ነበር! የቤተክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ በሰው ተሞልቶ ጠበቀኝ! ምንጣፌን ይዤ በአይኔ ክፍት ቦታ ስቃኝ ያየኝ አንድ አስተባባሪ "ና ቦታ ልስጥህ" ብሎ ወደ አንድ ቦታ መራኝና "እዚህ ጋ ተቀመጥ" ብሎ በእጁ ጠቆመኝ! ልጁን አመስግኜ ምንጣፌን አንጠፍሁና የአቅሜን ከሰገድሁ በኋላ ትንሽ ረፍት ለመውሰድ ተቀመጥሁ!
ድንገት አንዲት ሴት አጠገቤ መጥታ ቆመች!ዕድሜዋ በሀያዎቹ አጋማሽ ላይ ነው!...በእጇ መስገጃ የሚሆናት ምንጣፍም ሆነ ምንም ነገር አልያዘችም!..ያደረገችውን ክፍት ጫማ አወለቀችና ጠጠሩ ላይ መስገድ ጀመረች!...የያዝኩት ምንጣፍ ሰፊ በመሆኑ ምንጣፉ ላይ ሆና እንድትሰግድ ነገርኳት!.."እሺ" ብላ አመስግናኝ ወደ ምንጣፉ ተጠጋች!...ፊቷን አየሁት!...ጉንጮቿ ደም መስለዋል..ሁለቱም አይኖቿ በዕንባ ብዛት በሚመስል መልኩ ቀልተዋል!...ደነገጥኩ!..."ምን ሆነሽ ነው?" ብዬ ልጠይቃት አልኩና "እኔ ማነኝ?" ብዬ መልሼ ተውኩት!...ተነሳሁና መስገድ ጀመርኩ!...ጎን ለጎን ሆነን መስገድ ጀመርን!...ብዙ ከሰገድኩ በኋላ ደከመኝና ተቀመጥሁ!...ልጅቷ ከገባች ጀምሮ አላረፈችም!...እየሰገደች ነው!...ድንገት ጎንበስ ስትል ዕንባዋ ምንጣፉ ላይ ጠብ ሲል ተመለከትሁ!...ድጋሚ ዝም ማለት አልቻልኩም!...እጇን ያዝ አደረኳትና "እህቴ እስቲ ትንሽ አረፍ በይ" አልኳት ዕንባዋን በነጠላዋ ጫፍ ጠራረገችና ተቀመጠች!..."ምን ሆነሽ ነው የኔ እህት...ምን ሆነሽ ነው ምታለቅሺው?" አልኳት!...ስጠይቃት ይበልጥ አለቀሰች!..."ማንም ምን ሆነሽ ነው ብሎ ጠይቆኝ አያውቅም እኮ" አለችኝ!..."እንዴት"? አልኳት...ረጅም አመት የምታውቀኝ ያህል አወራችልኝ!...ከእናቷ በቀር ምድር ላይ ማንም ዘመድ እንደ ሌላት አወራችልኝ!...እናቷ በጣም ሀብታም እንደ ነበረች አወራችልኝ!...እናቷ ከ 5 ወር በፊት እንደ ሞተች አወራችልኝ!...እናቷ ስትሞት የመኖር ትርጉም እንደ ጠፋትና ሱስ ውስጥ እንደ ተዘፈቀች አወራችልኝ!...በዕንባ ብዙ ብዙ ነገር አወራችልኝ!...ላቋርጣት አልፈለግሁም!...ዝም ብዬ ሰማኋት!...መጨረሻ ላይ ዕንባዋን ጠራረገችና ፈገግ ብላ..."ታውቃለህ" አለችኝ..."ታውቃለህ እናቴ ከሞተች በኋላ መጀመሪያ ግዜዬ ነው ቤተክርስቲያን ስመጣ!...በእርግጥ የመጨረሻዬም ነው!...የመጨረሻዬ ስግደትም ስለሆነ ነው ያለማቋረጥ ስሰግድ የነበረው ምን አልባት ቢምረኝ ብዬ!"...ብላ ትንሽ ዝም አለችና!..."ይቅርታ በማያገባህ ብዙ ጨቀጨኩህ!...አመሰግናለሁ ቻው በቃ" ብላኝ ተነስታ ሄደች!...ከሄደች በኋላ ስታወራቸው የነበረችው ነገሮች አይምሮዬ ላይ ማቃጨል ጀመሩ...
"ታውቃለህ እናቴ ከሞተች በኋላ መጀመሪያ ግዜዬ ነው ቤተክርስቲያን ስመጣ!...በእርግጥ የመጨረሻዬም ነው"
"የመጨረሻዬ ስግደትም ስለሆነ ነው ያለማቋረጥ ስሰግድ የነበረው.... ምን አልባት ቢምረኝ ብዬ!"
በድንጋጤ ከተቀመጥሁበት ተነሳሁ!...ከህዝብ መሀል በአይኔ ፈለኳት...በሩ አከባቢ ስትወጣ ተመለከትኩ...ጫማዬን እንኳ ሳላደርግ በፍጥነት ሄድኩ!
:
:
የመኪናዋን በር ከፍታ ልትገባ ስትል ደረስኩባት!...እጇን ይዤ አስቆምኳት...ወደ ኋላ ዞራ አየችኝ...
"እራስሽን ልታጠፊ ነው አይደል?" አልኳት!
ምንም ሳትናገር እጇን አስለቀቀችና መኪናዋ ውስጥ ገባች...ምንም ብናገር...ምንም ባወራ በዚህ ስሜት ሆና ማድረግ ከፈለገችው ነገር እንደማትመለስ አውቃለሁ...ብቻ ግን እግዚአብሔር አንደበቴ ላይ ቃላቶችን አስቀመጠ..
"እግዚአብሔር ከ እናትም ከ አባትም በላይ እንደ ሆነ አታውቂም?...ተስፋን የሰጠን የታመነ እንደሆነ አታውቂም?....ክርስቶስ ተሰቅሎ አለምን ባዳነበት ዕለት አንቺ ትሞቻለሽ?"...አልኳት!....ተንሰቅስቃ አለቀሰች!
:
:
መርሀ ግብሩ ካለቀ በኋላ ከማውቃቸው ደግ እማሆይ ጋ አገናኘኋት!...ፀለዩላት!...አረጋጓት!...እንደ እናት አቀፏት!...አባበሏት!..አይዞሽ አሏት!...
ዲያቢሎስ አስቦባት የነበረውን የሞትን ደብዳቤ ክርስቶስ ኢየሱስ በስቅለቱ ዕለት ሰቀለው!....ስሟን ጠየኳት!...ሩት አለችኝ....
:
ሩት!....በእግዚአብሔር ምህረት ከሞት እና ከዘላለማዊ እሳት ያመለጠች ነፍስ!
[እዮብ ዘ ማርያም]
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
አይመስለኝም ነበር የምንረሳሳ
አይመስለኝም ነበር...
ልብሽና ልቤ በወረት ሚበሳ
ሁሉም ከንቱ ቀረ ተረሳሳን በቃ
የዘመናት ፍቅር ጠፋ በደቂቃ
እኔም ዘነጋሁሽ አንቺም ዘነጋሺኝ
በሌላ ተካሁሽ በሌላ ተካሺኝ
ያ ሁሉ መገዘት ያ ሁሉ መሀላ
ያ ሁሉ ቃል ማብዛት ሁሉ ሽንገላ
በቃ ለዚሁ ነበር?
ልብሽ ሊኮበልል እኔም ላቅፍ ሌላ?
የሚያስቀናው ፍቅር...
ሲታይ የሚመስለው ማይገኝለት አቻ
እዚህ ጋ ተቋጨ ሳይደርስ ዳርቻ
የኔና አንቺ ነገር ያሳዝናል ብቻ!
[Eyob Z Mariam]
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
(እንዲህ ናት የኔ ሴት)
ጾሜን አስገድፋ፣
አንጀቴን ስትበላ እሮብ አርብ የማትል
ሆዴን ምታላውስ ገብታ ልክ እንደ ትል
ቀጥ የምታደርገኝ...
ጉንጩን ዳበስ አርጋ "ወድሀለሁ" ስትል!
እንዲህ ናት የኔ ሴት...
ሀዘን ቅስሜን ሰብሮ ለፀፀት ሲሰጠኝ
መሰንበት ጠልቼ ትካዜ ሲንጠኝ
ፀጉሬን ደባብሳ...
የመኖርን ተስፋ ዳግም ምትሰጠኝ!
እንዲህ ናት የኔ ሴት...
በጠመመ ግዜ ጨርቄን ጥዬ ባብድም
የማደርገው ጠፍቶኝ በራሴ ላይ ባድም
መሰልቸት ደባብሷት፣
ትታኝ የማትሄድ አብራኝ ምትወድም!
እንዲህ ናት የኔ ሴት...
በማላቀው ጥፋት በስሜ ቢነገድ
ሊያጠፋኝ ቢነሳ አንድ ሙሉ ነገድ
ፈፅሞ ማትከዳኝ...
በሄድኩበት ሁሉ አብራኝ ምትሰደድ!
እንዲህ ናት የኔ ሴት..!!
እቴ የኔ አበባ፣
ዘመድ አዝማዶቼ መኖሬን ሳይሰሙት
ጠላቶቼ ሁሉ...
የኔን ደስታ ማግኘት ጭራሽ ሳይተልሙት
ፍቀጂልኝና፣
ካንቺ ጋራ ኖሬ ካንቺ ጋራ ልሙት!
(እዮብ ዘ ማርያም)
join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
(መነሻ ሀሳብ …)
“You left and I cried tears of blood. My sorrow grows. Its not just that You left. But when You left my eyes went with You. Now, how will I cry? “
-Rumi -
(መልሽልኝ አይኔን)
ዛሬ ስትለዪኝ...
ልብሽ ከኔ ርቆ፥ ወደ ሌላ ሲበር
ማድረግ የፈለኩት...
አብሮ መብረር ሳይሆን፥ ማልቀስ ብቻ ነበር::
የልቤን አውጥቼ...
ግን እንደምን ላልቅስ፥ ዕንባ እንደምን ልዝራ
ማለቅስበት አይኔ...
ከኔ ተለይቶ ሄዶ ካንቺ ጋራ::
አላሳዝንሽም ?
ይዤ አልታይሽም ? ብሶት ሰቀቀኔን
እንዳለቅስ እንኳን መልሺልኝ አይኔን !
( እዮብ ዘ ማርያም )
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
[የወረወርኩት ሎሚ ማን ላይ አረፈ…🍋]
እንደው ግራ ጎኔን ባገኝ ብዬ ነበር ፀሎት ካደረስኩ በኋላ የገዛሁትን ሎሚ በአራቱም ኪሴ ጠቅጥቄ ከቤት የወጣሁት!
የመጀመሪያ ኢላማዬ አይኔ ውስጥ ገባች!…ፀጉሯ ረጅም!…አቋሟ የሚያምር ደስ የምትል ቀይ ልጅ ናት!…አንድ አይኔን ጨፍኜ ካነጣጠርኩ በኋላ ኢላማዬን ጠብቄ ሎሚውን ወገቧ ላይ ወረወርኩት! …ከቅፅበት ከ ጎኗ የነበረችው ከ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ (ነፍሳቸውን ይማረውና) ትንሽ መለስ የምትል ዝሆን የመሰለች ጓደኛዋ በቅፅበት ሎሚውን አነሳችውና ወደ እኔ መጣች…ወደ ኋላ ትንሽ አፈገፈግሁና…
“ሴትዮ ሎሚውን እኮ እሷ ላይ እንጂ አንቺ ላይ አይደለም የወረወርኩት”…አልኳት!
አንድ ግዜ በግልምጫ ከታች ወደላይ አነሳችኝና ማስቲካዋን እያንቀጫጨች…
“እኔ ምን አንሶኝ ነው እሷ ላይ የወረወርከው እ?” ብላ አፈጠጠችብኝ!
“ቅጥነት ያንስሻል!…አንቺ ላይ እኮ ሎሚ ሳይሆን ሀብሀብ ወይም ዱባ ነው የሚወረወረው!…ሎሚ ቢወረወር ጠጠርም የተወረወረ ስለማይመስልሽ sense አታደርገውም” አልኳት!
ፊቷ እያየሁት በንዴት በርበሬ ሆነ!…”ለማንኛውም ሴት ልጅ ላይ ሎሚም ሆነ ሌላ ነገር መወርወር harassment ነው እሺ “ ብላ እንደ አሜሪካ ላይ ከወረደ ጡቷቿ መሀል ፊሽካ አውጥታ ጆሮ ግንዴ ላይ ነፍታብኝ ሄደች!
በልቤ “አንቺ ላይማ ቦንብ ነበር መወርወር” ብዬ ድጋሚ ዕድሌን ለመሞከር ዞርዞር ማለት ጀመርኩ!
ሌላ አበባ የመሰለች ልጅ አይኔ ውስጥ ገባች!…”ይህቺማ አታመልጠኝም”…ብዬ ሁለተኛ ሎሚዬን ከኪሴ ውስጥ አወጣሁና አመቺ ሰዓትመጠባበቅ ጀመርኩ!…ከ ጎኗ የነበሩ ሰዎች ራቅ ራቅ ማለት ሲጀምሩ “just do it” አልኩና የያዝኩተን ሎሚ ወደ ልጅቷ ሰደድሁት!…ወይኔ! ልጅቷ ጫማዋን ለማሰር ዝቅ ስትል ሎሚው እሷን አልፎ ፊት ለፊቷ የነበረ ከማይክ ታይሰን መለስ ያለ ግለሰብ መቀመጫ ላይ አረፈ! በድንጋጤ በቆምሁበት ደርቄ ቀረሁ! ሰውየው በslow motion ወደኋላ ዞረና ወደ እኔ ተንደረደረ!…ወደ ኋላ አፈገፈግሁ! በቅፅበት አጠገቤ ደረሰና ቁልቁል እያየኝ!…”ጭራሽ የወንድ ልጅ መቀመጫ ላይ ሎሚ መወርወር ጀመራችሁ” ብሎ ጎኔን በቡጢ አለኝ!…መሬት ላይ ወደቅሁ!
ግራ ጎኔን አገኛለሁ ብዬ የወጣሀት ልጅ ግራ ጎኔ ተሰብሮ እንደ እባብ መሬት ለመሬት እየተሳብኩ ወደ ቤት ገባሁ!
ምን አለ የቅድሟን ወፍራም ሴትዮ አርፌ ባበስል ኖሮ🥲
[Eyob Z Mariam]
join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
(ጽፌ ያልሰጠሁሽ ግጥም...🙂)
ያኔ ስንለያይ፣
እስትንፋስ አውጥቼ የልቤን ሳነግርሽ
ዛሬ ባጋጣሚ...
መንገድ ላይ አግኝቼ ቆሜ ሳናግርሽ
ናፍቆት የበላውን...
የልቤን ትኩሳት ምን ብዬ ልንገርሽ?
ሊታረም የማይችል፣
የፀፀት ፊደላት ልቤ ላይ ደቅድቄ
መንፈሴን ፈንቅሎ፣
ሊወርድ ሚታገል ዕንባዬን አምቄ
ምንም አንዳልሆንኩኝ
ልጆችሽን ስሜ ተለየሁሽ ስቄ፣
ካንቺ ትለይቼ...
በደመነብስ ሀሳብ ቤቴ እንደገባሁ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ...
አንገቴን ቀብሬ ቁጭ ብዬ አነባሁ፣
ያኔ ዕድሉ ሳለኝ
ግዜ የሰው አድርጎ አንቺን ሳይከልለኝ
ግዜ ምትሀተኛ ከኔ ሳይሰውርሽ
ምን ነበር!?...ምን ነበር!?
አፈቀርኩሽ ብዬ የልቤን ብነግርሽ!
ብሶት ተንተርሼ ስቃይ ተደግፌ
ናፍቆት ደራርቤ ፀፀቴን ታቅፌ
ሰው ለሊት ሲተኛ
ቁጭ ብዬ አድራለሁ አይመጣም እንቅልፌ፣
ይኸው በቀድም'ለት...
ልረሳሽ ፈልጌ
ልተውሽ ፈልጌ
ፎቶሽን ሰብስቤ ዶግ አመድ አድርጌ
ለራሴ እንዲህ ስል...
ጥርግርግ ብሎ አሁን ጠፋ ደብዛሽ
አስታወስኩሽ ደግም
በንፋሱ በኩል ደረሰኝ መዓዛሽ፣
እባክህን አምላክ
እሷን የሚያስረሳ ምህረት ወደ'ኔ ላክ
ብዬ ፀልያለሁ
መች ይሆን ፀሎቴ?
ካርያም ሚደርሰው እኔ ምን አውቃለሁ፣
ያኔ ስንለያይ፣
እስትንፋስ አውጥቼ የልቤን ሳነግርሽ
ዛሬ ባጋጣሚ...
መንገድ ላይ አግኝቼ ቆሜ ሳናግርሽ
ፀፀት የበላውን...
የልቤን ትኩሳት ምን ብዬ ልንገርሽ?
ከ እንግዲህ በኋላ፣
ልብሽ ከልቤ ጋ ዳግመኛ ላይገጥም
ይሄ ነው አለሜ፣
በዕንባ ላባ ፅፌ ያልሰጠሁሽ ግጥም::
(እዮብ ዘ ማርያም)
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
እስኪመስልብን ሱስ እስኪመስል አባዜ
ልባችን ተሰብሯል ብዙ….ብዙ ግዜ ፤
የወደድነው ሲሄድ ያመንነው ሲከዳን
ያተርፈናል ያልነው ሲጥልብን ዕዳን
ይቻለናል መዳን ?
ውሸት!
ሁሉም ልብ ውስጥ አለ የሀዘን ጥላሸት!
ከ ዕለታት አንድ ቀን…
ይሄ ምስኪን ልቤ አንዲት ሴት አፍቅሮ
እየሳቀ ገባና …ወጣ አቀርቅሮ ፤
ቢያልፍም እንኳ ግዜ …ቢያልፍም እንኳ ዘመን
እስካሁን አልወጣም ከ ሀዘን ሰመመን፤
የረሳ ቢመስልም …
አሁንም ይፈራል አሁንም ይባባል
ደንብሮ ይሸሻል ገና ፍቅር ሲባል፤
ከሚስቅ ሰው ጀርባ ፤
አንገት አቀርቅሮ አንብቶ ቁጭ ያለ
አንድ ታሪክ አለ !
እናም…
አታውቀውምና ፤
ሰው አልፎ እንደ መጣ በየት መንገድ በኩል
ለመፍረድ አትቸኩል ።
[ እዮብ ዘ ማርያም ]
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam