Join
@poeteyobzmariam
“እውነት ልብስ የላትም” የግጥም መፅሀፍን ቀድማችሁ ለመግዛት 1000213882728 CBE (Eyob Gezahegn) ላይ 250.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) በማስገባት ደረሰኝ ላኩልኝ🙏🏽
ትብብራችሁን ፈልጌ መጥቻለሁ ዛሬ🙏🏽
ይህን “እውነት ልብስ የላትም” የተሰኘ ሁለተኛ የግጥም መፅሀፌን ለማውጣት ካሰብሁ ትንሽ ሰንብቼ ነበር! የውስጥም የሆነ የገፅ ስራው ተጠናቆ ማተሚያ ቤት ብቻ ነበር መግባት የቀረው! በመሀል ግን ብዙ ያላሰብኳቸውነገሮች መጡ! ሀዘንም ህመምም ገጠመኝ! ሁሉም ነገር ሀዲዱን ሳተብኝ!
እና ዛሬ አንድ ሃሳብ ይዤ ወደ እናንተ መጥቻልሁ! መፅሀፉን አብረን እናሳትመው ሀሳቡ ከ ሀሳቡ ዘልሎ እውን እንደ ሚሆንም አምናለው!…የአንዱ መፅሀፍ የመሸጫ ዋጋ 250.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ነው ሚሆነው!
በ 1000213882728 CBE (Eyob Gezahegn) ብላችሁ 250.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) ላኩና መፅሀፉን ቀድማችሁ ግዙት! የላካችሁበትን ደረሰኝም ላኩልኝ!…መፅሀፉ እንደ ወጣ ቀድሞ እጃችሁ ላይ ይገባል!…ስፖንሰር መሆን የምትፈልጉ ከላችሁም አውሩኝ!….አመሰግናለሁ🙏🏽
ፅሁፉን ለሌሎች ሰዎች share በማድረግ አጋሩልኝ!

My Solo Art exhibition titled "Scribbes of the Soul" will be held at Atmospehere, Addis Ababa, Ethiopia starting from Friday 6pm, Nov. 22
You're invited🙏
ጥሩ አመት አልነበረም ለኔ…
ድሮ “በጣም የምትፈራው?” ነገር ተብዬ ስጠየቅ “እናቴን ማጣት” የሚል ነበር መልሴ! የፈራሁት ነገር ደረሰብኝ!…እናቴን አጣሁ!
“አቢዬ በቅርብ እመጣለሁ አብረን እንኖረለን” ብላኝ ነበር እናቴ! እንደ እሷ ሀሳብ ቢሆን ኖሮ 2017ትን አብረን ነበርን! ግን አልሆነም!…2016 ላይ ቀረች! እግዚአብሔር የፈቀደው ሆነ!
ህይወትን ያለ እናቴ ተጋፍጫት አላውቅም!…አሁን ግን ልጋፈጣት ነው!…እንደማትመለስ ቁርጤን አውቅያለሁ!…ለበዓል “እንኳን አደረሰህ አቢዬ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ!…”ፀጉርህን ስትስተካከል በጣም አስገብቶ ቅርፅ እንዳያወጣብህ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ!…ለልደቴ “እንኳን ተወለድክ የኔ ልጅ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ!”አንተ ብቻ ጠንክረህ ተማር እንጂ እኔ እናትህ እያለሁ ስለምንም ነገር እንዳትጨነቅ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ ”ወድሀለሁ” እንደማትለኝ አውቅያለሁ! ካሁን በኋላ ምንም እንደማትለኝ አውቅያለሁ!
“ Nothing in life is promised except death” ይላል ካንዬ ዌስት! ትክክል ነው! እዚህ ምድር ላይ ከሞት በስተቀር ቃል የተገባልን ነገር የለም! ሞት ደግሞ መች እንደሚመጣ አይታወቅም!…በህይወት ሳላችሁ ተዋደዱ! በህይወት ሳላችሁ ተፋቀሩ! እናታችሁን እንደ ምትወዷት በየደቂቃው ንገሯት! ምንም ከምታደርጉላቸው በላይ ደስታቸው ለነሱ ይሄ ነው!
ሰማይ ቤት ባለሽበት መልካም አዲስ አመት እናቴ! ለራሴ ነው እንጂ ማዝነው ከዚህ ክፉ አለም ላንቺ የእመብርሀን እቅፍ እንደሚሻልሽ ጠፍቶኝ አይደለም!
ልቤ ውስጥ አይደል የቀበርኩሽ? መቸም አትበሰብሽም!!!
ወድሻለሁ!
ላማርር ፈልጌ አይደለም! እንዲሁ ልቤ ውስጥ ያለውን ላውጣው ብዬ ነው!
ነገር ሁሉ ለበጎ ነው!…ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!!
መልካም አዲስ አመት🌼
©[Eyob Z Mariam]
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam