prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ዕጣ ፈንታችን የተሳሰረ ስለሆነ የጋራ ጥቅሞቻችንን መሠረት ያደረገ ትብብርና መተጋገዝ ያስፈልገናል። በማንግባባባቸው ጉዳዮች ላይ ከምናጠፋው ጊዜ ይልቅ በምንግባባባቸው ጉዳዮች ላይ ብዙ ጊዜ ማጥፋት የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡"

#መደመር

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባር እንጂ በስብሰባ አይተገበርም!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለፕሪቶሪያው ስምምነት የመንግስት ጥረት Vs የህወሓት ልግጫ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከስብሰባ ውጭ ለትግራይ ህዝብ በተግባር የሚታይ ምን ሰራችሁ?

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የትግራይ ህዝብ በችግር ውስጥ እንዲኖር እና የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዳይሳካ እንቅፋት እነ ደብረ ፅዮን ናቸው

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፌደራል መንግሥት የፕሪቶሪያው ስምምነት ተግባራዊ እንዲደረግ እጅግ በጣም ሰፊ ስራዎችን ሰርቷል። ነገር ግን እንደ እነ ደብረፅዮን እና መሠሎቹ የህዝብ ቫይረሶች አሁንም በስልጣን ላይ ይገኛሉ።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አንደኛ ልዩ ስብሰባው በአማራ ክልል የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት አራዝሞታል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በርካታ ለውጦችን ማምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ተጨማሪ ስራዎች በመኖራቸው ምክንያት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘም አስፈልጓል ተብሏል።

የምክር ቤቱ አባላት ውይይት ካደረጉበት በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ ከዋጁ በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ለአራት ወራት ተራዝሟል

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Sirni Gadaa sirna bulchiinsaa dhugaa Oromoon Ijaaredha!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፊታችን እሁድ ጥር 26/2016 ዓ.ም 6ኪሎ በሚገኘው አንበሳ ግቢ በተሰናዳው የቤተሰብ ፌስቲቫል ላይ በፍፁም አይቀርም።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ቱርካዊቷ በሳምንት አንዴ እንኳን ሰውነቱን አይታጠብም ያለችውን ባሏን ፍቺ ጠይቃለች። ተከሳሹ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ልብሱን አይቀይርም የሚል ክስም ከሚስቱ ቀርቦበታል። ፍርድ ቤቱም የፍቺ ጥያቄውን ተቀብሎ፥ ተከሳሹ 16 ሺህ 500 ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል።

የስሟ የመጀመሪያ ፊደሎች “ኤ ዋይ” መሆናቸው የተነገረላት ሚስት ያቀረበችው ክስ በአንካራ በሚገኘው 19ኛ የቤተሰብ ችሎት እየታየ መሆኑን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

“ባሌ በሰባት ወይም አስር ቀናት ውስጥ አንዴ ብቻ ነው ሰውነቱን የሚታጠበው፤ ላብ ላብ ይሸታል፤ አንድ ልብስን ከአምስት ቀናት በላይ ሳይቀይር ይለብሳል፤ ጥርሱንም በሳምንት አንዴ ወይ ሁለቴ ነው የሚቦርሸው” ብላለች ከሳሽ ሚስት።

በዚህም ጤናዋም ሆነ ትዳራቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመጥቀስ ፍቺ መጠየቋ ተሰምቷል።


ምስክር ሆነው የቀረቡት የጋራ ወዳጆቻቸውና የስራ ባልደረቦቹም ግለሰቡ ንጽህናውን እንደማይጠብቅ በአንድ ቃል መመስከራቸው ነው የተነገረው።

ግለሰቡ ንጽህናውን አለመጠበቁ በስራ ቦታም ቅሬታ መፍጠሩን ባልደረቦቹ ለፍርድቤት አስረድተዋል። 

ክሱን የተመለከተው ችሎትም የፍቺ ጥያቄ ተቀብሎ የግል ንጽህናውን ባለመጠበቅ ትዳሩ የፈረሰበት ባል 500 ሺህ የቱርክ ሊራ ወይም 16 ሺህ 500 ዶላር ካሳ እንዲከፍል ወስኗል።

የከሳሿ ጠበቃ ሰነም ዪልማዘል “የትዳር አጋሮች በጋራ ለሚመሩት ህይወት ሃላፊነት አለባቸው፤ የግል ንጽህናን አለመጠበቅ ለፍቺ ሊዳርግ እንደሚችል

ማወቅ ተገቢ ነው” ሲሉ ለቱርኩ ጋዜጣ ሳባህ ተናግረዋል።

ሰውነትን ያለመታጠብና ንጽህናን ያለመጠበቅ ጉዳይ በተደጋጋሚ ለትዳር መፍረስ ምክንያት ሲሆን ይታያል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ልዩ_ስብሰባ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በዕለተ አርብ ጥር 24/2016 ዓ.ም #ልዩ_ስብሰባውን እንደሚያካሄድ ታውቋል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ውጤታችንን የምንለካው ከህዝባችን ተጠቃሚነት እና ከፓርቲያችን ራዕይ መሳካት አንፃር ነው" - አቶ ሞገስ ባልቻ - በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አመራሮች የ2016 ዓ/ም የ6 ወራት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎችን በመገምገም ቀጣይ ስራዎችን በፓርቲ አቅም መምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በግምገማዊ ውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የፓርቲ ተቋማዊ ግንባታን በማጠናከር በከተማ አስተዳደሩ የታቀዱ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ስራዎችን በፓርቲ ግንባር ቀደም መሪነት ለማስፈፀምና ለመፈጸም ተግባቦት በመፍጠር ወደ ተግባር በመገባቱ አበረታች ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት የምናደርጋት በሁሉም ዘርፍ መሆኑን ያስገነዘቡት አቶ ሞገስ የሴቶችን አመራር ሰጪነት አቅም በአግባቡ ለመጠቀምም በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች ተሳትፏቸውን ማሳደግ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በቀጣይ ወገብን ጠበቅ ማድረግ የሚጠይቁ ፣ የተጀመረውን ሌት እና ቀን የመትጋት ስራ ማጠናከር የሚፈልጉ ስራዎች እንዳሉን በመረዳት መንቀሳቀስ እንደሚገባ ያስረዱት ኃላፊው በዓመቱ መጨረሻ ከህዝባችን ተጠቃሚነት እና ከፓርቲ ያችን ራዕይ አንፃር ጠንካራ የምዘና ስርዓት እንደሚኖር አመላክተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ም/ሀላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ የአመራሩ ተልዕኮዎችን በወንድማማችነት እና በአብሮነት የመፈጸም ባህል እየዳበረ መሆኑን ጠቁመው በእንቅስቃሴዎቹ ሁሉ አርአያ መሆን ሲገባቸው በብልሹ አሰራሮች የሚሰማሩትን ተጠያቂ የማድረግ ትግሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

የተጀማመሩ የአመለካከት ቀረፃ እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማጠናከር የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይመር ከበደ የፓርቲን ስራዎች በብቃት በመፈጸም የመንግስት ስራዎችን ማሳለጥ ላይ መሻሻል መምጣቱን ጠቁመው አሰራርና መመሪያን በማስከበር፣ ዘመናዊ የመረጃ ስርዓትን በማጠናከር፣ ለጥራት ለውጤታማነትና ለተጠያቂነት ትኩረት በመስጠት ተቀራራቢ ስኬታማ አፈፃፀምን ማስመዝገብ እንደሚገባ አስረድተዋል።

በተከናወነው የመልሶ ማደራጀት ተግባር እና አመራሩና አባላት በግምገማ እና በምዘና እንዲያልፉ በመደረጉ ቀን እና ሌት የመስራት ባህል እየዳበረ መምጣቱ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።

ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር በተሰጠው ትኩረት የህዋስ ውይይቶችን የመተጋገያ መድረክ በማድረግ እና የመሰረታዊ ድርጅት ኮንፈረንሶችን በማከናወን እንዲሁም ሌሎች የውስጠ ፓርቲ ስራዎች ላይ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸው ለቀጣይ ወራትም መንደርደሪያ ሆነው እንደሚያገለግሉ በውይይቱ ተንፀባርቋል።

የፓርቲያችንን አሻጋሪ ሀሳቦች እንዲሰርፁ እና አሰባሳቢ የወል ትርክቶች እንዲጐሉ የተጀማመሩ ቅንጅታዊ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተመላክቷል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የክልሉን የጤና ዘርፍ ዐቅም ለመገንባት እንዲቻል 164 ልዩ ልዩ ባለሞያዎች ተመድበው ድጋፍ እንዲሰጡ ተደርገዋል፡፡ ሁሉንም በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት በመደገፍ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የተቻለ ሲሆን፣ ሁሉም ሆስፒታሎች ተኝቶ የማከም አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡ ከ830ሺ በላይ ሕጻናት የኩፍኝ ክትባት ከማግኘታቸውም ሌላ ከ65ሺ በላይ ሕዝብ የኮቪድ ክትባት አግኝቷል፡፡ ከአምቡላንሶች በተጨማሪ ወደ 2 ቢልዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፎችም ተከናውነዋል፡፡ በ2015/16፣ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ከ600.2 ሚልዮን ብር በላይ ለትግራይ ክልል የጤና ዘርፍ የገንዘብና የግብአት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ትግራይ በቱሪዝም ሀብት የታወቀ ክልል ነው፡፡ ይሄንን ሀብት መልሶ ወደ ጥቅም ለማዋል እንዲቻል ቱሪስቶችን የማበረታታት ሥራ ተጀምሯል፡፡ አልነጃሺ መስጊድንና የገርዓልታ ገዳምን ለቱሪስቶች የማስከፈት እንቅስቃሴም ተከናውኗል፡፡ የውኃ ሀብትን ለመጠቀምና ውኃን ለሕዝቡ ለማዳረስ እንዲቻል ለዘርፉ ተቋም ልዩ ልዩ ድጋፎች የተደረጉ ሲሆን፣ የክልሉን ቢሮ የማደራጀትና በቁሳቁስ የማሟላት ሥራ ተሠርቷል፡፡ ለተበላሹ የአገልግሎት ሰጪ ሀብቶችም ጥገና ተከናውኗል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት በተደረገው ሁለገብ እንቅስቃሴ 217 ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት ተችሏል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የገበያ ትሥሥር እንዲፈጠር በተለያዩ ባዛሮችና ኤክስፖዎች ላይ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪዎች እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ የመሠረታዊ ሸቀጦችን ተደራሽነት ለማስፋት መንግሥት በወሰደው ርምጃ የተለያዩ የምግብና የመጠቀሚያ ሸቀጦች ለትግራይ ክልል ቀርበዋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎችን እንዲጠገኑ በማድረግ፣ በክልሉ በቂ ነዳጅ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ የትግራይ ክልል ንግድ ፈቃድ ላላቸው 7240 ነጋዴዎች፣ ከተለመደው አሠራር ወጣ ብሎ ከሐምሌ 1/ 2014 ጀምሮ በአዲስ አበባ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

51.3 ሚልዮን ብር ለዘር ግዥ ወጪ ተደርጓል፡፡ በ2015/16 13.4 ሚልዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለክልሉ የቀረበ ሲሆን፣ ለ1427 አርሶ አደሮች መጠቀሚያ የሚሆን 1720 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዚሁ የምርት ዘመን ፕሮጀክቶች በኩል ለክልሉ ተገዝቶ ሥራ ላይ ውሏል፡፡

በ2015/16 የምርት ዘመን ክልሉ 80ሺ የተለያዩ ማዳበሪያዎች ጠይቆ ሁሉም ቀርቦለታል፡፡ ለ2016/17 ምርት ዘመን ደግሞ ክልሉ ከጠየቀው መካከል የ70ሺ ቶን ማዳበሪያ ተገዝቷል፡፡ ለግብርና መገልገያ የሚሆኑ የትራክተሮች፣ የውኃ ፓምፖች ድጋፍ ለአርሶ አደሮች ተለግሷል፡፡ በልማታዊ ሴፍቲኔት በኩል 6.2 ሚልዮን ብር የተላለፈ ሲሆን፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የግብርና ሚኒስቴር ባደረጉት ስምነት መሠረት ደግሞ 7መቶ ሺ ኩንታል እህል ተገዝቶ ለክልሉ ቀርቧል፡፡ ለ55 ወረዳዎች በየወረዳው አንዳንድ መኪናና ሞተር ሳይክል፤ እንዲሁም ኮምፒውተሮችና ፕሪንተሮች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በዘላቂ የመሬት አስተዳደር ፕሮግራም አማካኝነትም 89.2 ሚልዮን ብር ለክልሉ በቁሳቁስ መልክ ተሰጥቷል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ብቻ 11ሺ ኩንታል ምርጥ ዘርና 30 ትራክተሮች ለትግራይ ገበሬዎች ተለግሷል። ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ አድርገዋል።

የዊዝሆልዲንግ ታክሶችን ጨምሮ ብር 3.9 ቢልዮን ብር ወደ ክልሉ ትልልፍ ተደርጓል፡፡ ከክልሉ ግብር ከፋዮች የተሰበሰበ ብር 138.06 ሚልዮን ብር ወደ ክልሉ ሂሳብ ተላልፏል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ ለተጠቀሱትና ለሌሎችም ወጪዎች ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ከ37 ቢልዮን ብር በላይ የፌዴራል መንግሥት ለትግራይ ክልል ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተመደበው በጀትና ድጋፍ የክልሉ ዕቅድ ተግባራዊ ተደርጎ ለሕዝብ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣም ይጠብቃል፡፡

ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ መኖሪያቸው ለመመለስ እንዲቻል የፌዴራሉ መንግሥት የሚመለከታቸውን አካላት አቀናጅቶ ሥራ ጀምሯል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎችም ትክክለኛ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡ የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናንት ከሚመለከታቸው ከአማራና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ ነበር።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት በሕወሐት በኩል ታጥቀው ሲዋጉ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ አለባቸው፡፡ ለዚህም የሚረዳ የተሐድሶ ኮሚሽን የፌዴራሉ መንግሥት አቋቁሟል፡፡ በፌዴራሉ መንግሥት በኩል የሚጠበቅበትን የሰው ኃይልና በጀትም መድቧል፡፡ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥቱ ተገቢውን ርምጃ በእርሱ በኩል ወስዷል፡፡ ተጠያቂ መሆን ያለባቸውንም ተጠያቂ አድርጓል፡፡

ሌሎች ሥራዎችንም ለማከናወን እንዲቻል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዐዋጅ ረቂቅ ዝግጅት አጠናቋል፡፡ ይህ ሂደት እንዲሳካም እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ የትግራይ ክልልም ተገቢው ሚና እንዲጫወት ይጠበቃል፡፡ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል የፌዴራሉ መንግሥት እነዚህን ተግባራት ከሚገባው ባሻገር ተጉዞ አከናውኗል፡፡ ለክልሉ ሕዝብ መደረግ ያለባቸው ድጋፎችንም በራሱ ዐቅምም ሆነ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለማከናወን የፌዴራሉ መንግሥት ምንጊዜም ዝግጁ ነው፡፡

አሁንም ቢሆን ለትግራይና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚያደርጉ፤ የክልሉን ዕቅዶች ወደ መሬት በሚያወርዱ፤ የክልሉን ሕዝብ ችግሮች በተጨባጭ ለመፍታት በሚያስችሉ ገቢራዊ ነገሮች ላይ ማተኮር አማራጭ የሌለው ነው ብሎ የፌዴራሉ መንግሥት ያምናል፡፡ እነዚህ ነገሮች ተግባራዊ ተደርገው የትግራይ፣ በአጠቃላይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት እንዲረጋገጥ የፌዴራል መንግሥቱ ያለውን ቆራጥ አቋም በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡

የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ለፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት መፈጸም ሙሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ የፌደራል መንግሥቱ ጥሪውን ያቀርባል።

ጥር 23 ቀን 2016 ዓ ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል ያሰለጠናቸውን የክብር ዘብ አባላት አስመረቀ

የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል በኢፌዴሪ አየር ኃይል ያሰለጠናቸውን የክብር ዘብ አባላት በዛሬው ዕለት አስመርቋል። በምርቃቱ ተገኝተው ሽልማት በመስጠት ንግግር ያደረጉት የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ የዛሬ ተመራቂ የክብር ዘብ አባላት የሰራዊቱ ቁመና እና ስነ-ስርዓት ነፀብራቅ መሆናችሁን አውቃችሁ የሚሰጣችሁን ኃላፊነት በትጋት ልትወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይሉ የክብር ዘብ አባላት ለምረቃ እንዲበቁ ላደረጉ የአየር ኃይል ፣ የመከላከያ ስነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት አመራሮችና ባለድርሻ አካላትም ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አብድሮ ከድር የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይሉ በሀገራችን የሚካሄዱ ስብሰባዎች ፣ሀገራዊ ክብረ በዓላት በሰላም እንዲከናወኑ የተሰጠውን ኃላፊነት በትጋት እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው የዛሬ ተመራቂ የክብር ዘብ አባላት በአካል ብቃትና ፣በወታደራዊ ሥልጠና የሚሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል በቂ አቅም መጨበጣቸውን ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ ለስልጠናው መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ተመራቂ የክብር ዘብ አባላትም በስልጠና ያገኙትን አቅም በመጠቀም የሚሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአዲሱ የውጭ ዲፕሎማሲያችን አቅጣጫ ውጤት የሆነውና ሃገራችን #ኢትዮጵያ ከቀናቶች በፊት ከጎረቤት #ሱማሌ_ላንድ ጋር የተስማማችው የባህር በር የማግኘትና የመስጠት #ታሪካዊ ስምምነት ከትልልቆቹ የሁለንተናዊ ብልፅግናችን ዋልታ እና ምሰሶዎች መካከል ትልቁና ዋነኛው ሆኗል ብሎ መውሰድ ይቻላል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እነዚህ 👆 ድብን ያሉ የትግራይ እና የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው። ቆሞ ቀሮች።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስምምዕ ፕሪቶሪያ ንምትግባት እንታይ ጌርኹም??

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

መንግሥት ለትግራይ ሰላም ምንም ጊዜ ቁርጠኛ ነው።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የትግራይ እና የህዝቦቿ ብሎም የኢትዮጵያ ጠላት

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

መንግሥት ለፕሪቶሪያው ስምምነት ከምንጊዜውም በላይ ከአቋም ባሻገር ተግባራዊ እንቅስቃሴ አድርጓል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ወሬ_እና_ተግባር_የተሳናቸው አካላት የትግራይ እና የትግራይ ህዝብ እንዲሁም የኢትዮጵያም ጠላቶች ናቸው።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልእልና" በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የጋራ ጉባኤ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የጉባኤው አላማ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት የተፈጸሙ ተግባራትን በጋራ በመገምገም ውጤታማ ስራዎችን ማስቀጠል እንዲሁም ድክመቶችን ለማረም የታሰበ መሆኑን ገልጸዋል።

የአገልግሎቱ ተልእኮ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ መረጃን ለህብረተሰቡ ማድረስ የሚያስችል ስራ ማከናወን፣ እንዲሁም የህዝቡን ህብረብሄራዊ አንድነት ማስጠበቅና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማረጋግጥ እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ለዚህም የፌዴራልና ክልል የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አካላት ውጤታማ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ በተለያዩ መስኮች ለተፈጸሙ ውጤታማ ስራዎች የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ስራ አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ገልጸዋል።

ጉባኤው ጠንካራ ስራዎችን ጠብቆ ለማቆየትና ያጋጠሙ እንቅፋቶችን ለይቶ እርምት ለመውሰድ ያስችላልም ነው ያሉት።

"ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልእልና" በሚል መሪ ሀሳብ ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የተዘጋጀው ጉባኤ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎትና የተለያዩ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተጠቅሷል።

በጉባኤው የፌዴራልና የክልል የኮሙኒኬሽን የቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም የሚዲያ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እኛ ስንተጋ ተከታዮቻችን ሲተጉ ፣ ህዝባችን ሲተጋ በዛ ድምር ውጤት ነው ኢትዮጵያ ከረሀብ ወጥታ ወደ ብልፅግና የምትሄደው።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ( ዶ/ር )
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የዚህ ትውልድ ዓድዋ የኢትዮጵያን ሰላምና ብልፅግናን እውን ማድረግ ነው!

የዚህ ትዉልድ ትልቁ ዓድዋ የስራ ባህላችንን በመሰረታዊነት በማሻሻል ድህነት የሚባል አዋራጅ ጠላታችንን ድል በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እዉን ማድረግ መቻል ነዉ!

በዓድዋ ላይ በክብር ያልወደቀ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ የዓድዋ ድል የህብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ድል የሆነው በአፈጻጸም ብቃት የጠነከረ፣ በተሳትፎ ስፋት የተዋቀረ፣ በዓላማ ጽናት የተቀመረ ትልቅ ድል ነው፡፡

ከዓድዋ ጀግኖች አሸናፊነታቸውን ብቻም ሳይሆን ለማሸነፍ ያበቋቸውን ጉዳዮች ከመረመርናቸው ለዛሬ ማንነታችን የተሰነቁ እኛም አጉልተን ልንጠቀምባቸው የሚገቡ ትምህርቶችን እናገኝባቸዋለን፡፡

ያሁኑ ትውልድም ታዲያ በዓድዋ መንፈስ ሆነን፤ በድሉ ብስራት ጠንክረን፣ ኢትዮጵያ የምትጠብቅብንን ደማቅ ታሪክ ዳግም መስራት መቻል አለብን፡፡ ብዙ ያልሰራነው ፣ ገና ያልፈጸምነው ሥራ አለብን፡፡ አየሩን በሚሞሉት አሉታዊ እሳቤዎች ወደ ኋላ እየተጓተትን የዓድዋን ፍሬ መብላት አንችልም፡፡ ልክ የዓድዋ ጀግኖች እንዳደረጉት ትልቁን መዳረሻችንን አልመን ለማስተካካል አብረን መቆም ይኖርብናል፡፡

የዚህ ትዉልድ ትልቁ ዓድዋ የስራ ባህላችንን በመሰረታዊነት በማሻሻል ድህነት ከሚባል ታሪካዊና አዋራጅ ጠላታችንን ድል በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እዉን ማድረግ መቻል ነዉ፡፡

የዚህ ትዉልድ ዓብይ ዓድዋ ኢትዮጵያን ከትርክት ተቃርኖ በማላቀቅ ብሄራዊ አሰባሳቢ ትርክትን በመትከልና በማጽናት የኢትዮጵያን ሰላም በዘላቂነት እዉን ማድረግ ነዉ፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጨቅጫቃው ባል!

ለአርባ አመታት በሰላም ይኖሩ የነበሩት ባልና ሚስት ካለልክ መጨቃጨቅ ከጀመሩ ወደ አንድ አመት ሆኗቸዋል፡፡ አለመስማማቱ የጀመረው ባል ሚስትን፣ “ለምጠይቅሽ ጥያቄዎች መልስ አትሰጪኝም፣ እኔን የማናገር ፍላጎት ስለሌለሽ መዝጋት ጀምረሻል” በማለት መበሳጨት ጀምሮ ነው፡፡

ለብዙ አመታት በፍቅርና በመስማማት ይኖሩ የነበሩ እነዚህ ባልና ሚስቶች በድንገት እንደዚህ አይነት አለመግባባት ሲፈጠርባቸው ጉዳዩ ለወዳጆቻቸው ሁሉ ግራ አጋብቷል፡፡ ባልም እንዲሁ ምን እንደሚያደርግ እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የሚስቱን ሁኔታ ሲያጤነው ምንም አልተለወጠችም፡፡ ያየው ለውጥ ለሚጠይቀው ጥያቄ መልስ አለመስጠቷ ላይ ብቻ ነው፡፡ በተለያየ መልኩ ካስተዋላት በኋላ ግን፣ “በቃ ጆሮዋ እየደከመ መጥቶ ነው” ብሎ ደምድሟል፡፡ እርግጠኛ መሆን ግን ፈልጓል፡፡

አንድ ቀን ባልየው የስነ-ልቦና አዋቂ ለሆነው ለአማካሪው ስለችግሩ ሊያማክረው ወደ ቢሮው ሄደ፡፡ ትውውቃቸው የረጅም ዘመን ስለነበር የሞቀ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ፡፡ ተቀምጠው ማውጋት ጀመሩ፡፡

ባልየው፣ “ስራ የሚበዛብህ ሰው እንደሆንክ አውቃለሁ፡፡ ሌሎችም ሰዎች ሊያማክሩህ ይጠብቁሃል፡፡ ወደ ሃሳቤ ልግባ፤ በአጭሩ ሚስቴ ማድመጥ አቁማለች፡፡ እየናቀችኝ ይመስለኝ ነበር፣ አሁን ግን ሳስበው ጆሮዋ መስማት ሳያቆም አይቀርም” ብሎ ከሚስቱ ጋር ስላለው ችግርና እንዴት ለሚጠይቀው ጥያቄ መልስ መስጠት እንዳቆመች፣ በሁኔታውም ስሜቱ እየተጎዳ እንደሆነ ተረከለት፡፡

ይህ የብዙ አመታት ልምድ ያለው አማካሪ ገና ታሪኩን በመስማት ላይ እያለ ችግሩ በአንድ ጊዜ ገባው፡፡ ምክሩ አጭርና ግልጽ ነበር፡፡ “ዛሬ ወደቤት ስትገባ ከ20 ሜትር ርቀት ላይ ሆነህ አንድ ጥያቄ ጠይቃት፣ ካልሰማችህ ከ15፣ ከዚያም ከ10፣ ከዚያም ከ5 ሜትር እያልክ በምን ያህል ርቀት ላይ ስትሆን መልስ እንደምትሰጥህ አጣራ” አለው፡፡
ሰውየው ወደቤቱ ሄዶ የተባለውን አደረገ፡፡

ከ20 ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ፣ “ዛሬ ራት ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፣ መልስ አላገኘም፡፡ ይህንኑ ጥያቄ ከ15 እና ከ10 ሜትር ርቀቶች ላይ ሆኖ ሲጠይቅ አሁንም መልስ አላገኘም፡፡ ከ5 ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ ለአራተኛ ጊዜ፣ “ዛሬ ራት ምንድን ነው?” ብሎ ገና ከመጠየቁ መልስን በፍጥነት አገኘ፡፡ “ሶስት ጊዜ ነገርኩህ፣ አሁን ለአራተኛ ጊዜ ነው የምነግርህ፣ ለራት የተዘጋጀው መኮሮኒ ነው” ብላ መለሰችለት፡፡ ለካስ አልሰማ ያለው ጆሮ የባል እንጂ የሚስት አልነበረም፡፡ ባልየው ይህን እውነታ ከገባው በኋላ ወደ አማካሪው ለመመለስ ሙከራም አላደረገ፡፡

ችግሩ ያለው እኔው ጋር ይሆን?

“እይታ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከ1ሚሊዮን ብር በላይና በርካታ ዶላርና የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ በመኖሪያ ቤቱ በህገ ወጥ መንገድ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነዋሪነቱ በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 ልዩ ቦታው በተለምዶ ሻንቅላ ወንዝ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ያከማቸ መሆኑን ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጡን ተከትሎ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትእዛዝ በማውጣት በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ዛሬ ጥር 23 ቀን 2016 ዓ/ም ባደረገው ብርበራ 1ሚሊዮን 199ሺህ 290 ብር ፣ 26ሺህ 405 የአሜሪካ ዶላር ፣ 5ሺህ 100 የካናዳ ዶላር ፣ 34 ሺህ 150 ዮሮ እና 1ሺህ 635 የሳውዲ ሪያል እና 27 ጥይት በኤግዚቢትነት መያዙን አስታወቀ።

መምሪያው በብርበራ ወቅት ፈቃድ አለው የተባለ ሽጉጥ መያዙን ገልፆ የሽጉጡን ህጋዊነት እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#አንወድም_ጥቃት

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ ይፈልጋል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሕወሐት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን የፌዴራል መንግሥት በአንክሮ ተመልክቶታል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሔ የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን የኢፌድሪ መንግሥት በጽኑ ያምናል። ይሄንንም በተመለከተ የፌዴራሉ መንግሥት ከመነሻው እስካሁን ያለው አቋም ወጥ እና የማይናወጥ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የፕሪቶርያው ከአቋም ባሻገር ተግባራዊ እንቅስቃሴም አድርጓል፤ እያደረገም ይገኛል፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ ለሰላም፣ ለፖለቲካዊ መፍትሔና ለትብብር ያለውን አቋም የገለጠው ከፕሪቶርያው ስምምነት በፊት ጀምሮ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ መቀሌ ከተማ እንዳይገባ የተደረገው ለሰላም ዕድል ለመስጠት ነው፡፡ ከስምምነቱ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተመራ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ያሉበትን ቡድን ወደ ትግራይ የላከው የፌዴራል መንግሥት ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥት ተቋማትና ክልሎች ለትግራይ ሕዝብ ድጋፋቸውን ያሳዩት ወዲያው ነው፡፡ የክልል ፕሬዚዳንቶች በመቀሌ ተገኝተው ለሕዝቡ ያላቸውን አጋርነት በማሳየት የሚቻላቸውን ድጋፍ በዓይነትና በገንዘብ አድርገዋል፡፡

በፕሪቶርያው ስምምነት መሠረት የገዢው ፓርቲ ሊኖረው የሚችለውን ድርሻ በመተው ሕወሐትና የታጣቂ አመራሮች ጊዜያዊ መንግሥቱን እንዲያቋቁሙ አድርጓል፡፡ ምክንያቱም ከልዩ ልዩ አካላት ተውጣጥተው በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ የሚካተቱ አመራሮች እስኪተዋወቁና እስኪግባቡ ድረስ የትግራይ ሕዝብ የችግር ወቅት እንዳይራዘም በማሰብ ነው፡፡ በዚህም ለትግራይ ሕዝብ ሰላም ያለውን ቁርጠኝት ከፕሪቶርያው ስምምነት በላይ በመሄድ አረጋግጧል፡፡

ለትግራይ ሕዝብ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንዲቻል የባንክ፣ የቴሌኮም፣ የመንገድ፣ የጤና፣ የትምህርትና የርዳታ ሥራዎችን የሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች በትግራይ ተገኝተው ከክልሉ ቢሮዎች ጋር እንዲወያዩ የተደረገው የፕሪቶርያ ስምምነት በተፈረመ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ የሥራ ኃላፊዎች በጀትና ባለሞያዎችን በመመደብ በክልሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ አስችለዋል፡፡

በክልሉ ተቋርጦ የነበረውን የትምህርት ሂደት ለማስቀጠል ልዩ ልዩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ የሰው ኃይልና የተቋም ዐቅም ግንባታ፣ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ሥልጠና፤ የዩኒቨርሲቲዎችን የአመራር ቦርድ የማደራጀት ሥራ ተሠርቷል፡፡ በትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም በኩል 165.8 ሚልዮን ብር በዕቅድ ተካትቶ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ለአንደኛና ለሁለተኛ ሩብ ዓመታት ማስፈጸሚያ 517.9 ሚልዮን ብር በገንዘብ ሚር በኩል ለክልሉ ተልኳል፡፡

በትምህርት ላይ ከሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት 1.46 ቢልዮን ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ በ2016/17 በትምህር ቤቶች ላይ ለሚሠሩ ሥራዎች የ111.08 ሚልዮን ብር ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ የትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ 441.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል የ5 ሚልዮን፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ደግሞ የ109 ሚልዮን ብር የትምህርት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የክልሉን የማዕድናት ልማት ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ ለዘርፉ መሥሪያ ቤት የመገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል፤ የክልሉን የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በሚልኒየም አዳራሽ በፌዴራል ወጪ ተከናውኗል፡፡ የሞሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ሥራ ተመልሷል፡፡ በፋብሪካና በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚያመርቱ አካላትን በመደገፍ ሥራ ጀምረዋል፡፡ ለወርቅ ሥራ የሚያገለግሉ ሁለት ከባድ ተሸከርካሪዎች በርዳታ ተለግሰዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የክልሉን የዘርፍ መሥሪያ ቤት ለማጠናከር ከተወሰዱ ርምጃዎች ባሻገር ለካፒታል በጀት 4.9 ቢልዮን ብር፤ ለመደበኛ በጀት 11.4 ቢልዮን ብር፣ እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ 400 ሚልዮን ብር፤ በድምሩ 16.7 ቢልዮን ብር በ2015/16 ለክልሉ ተሰጥቷል፡፡ በክልሉ ለሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በድምሩ 5.1 ቢልዮን ብር ተላልፎላቸዋል፡፡ በልማት አጋሮች በኩል ደግሞ የ1.7 ቢልዮን ብር ድጋፍ ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

ከእነዚህም በተጨማሪ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በቻናል አንድ 1.7 ቢሊዬን እንዲሁም በገንዘብ ሚኒስቴር በክልሉ ባቋቋመው ጽ/ቤት በኩል፣ በትግራይ ለሚከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች እና ለአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክቶች በድምሩ ከ565 ሚልዮን ዶላር በላይ ፈሰስ ተደርጓል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክትም 65 ሚሊዮን ብር ለክልሉ ተላልፏል። የሥራና ክሂሎት ሚኒስቴር እና የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በክልሉ የሚገኙ የዘርፍ መሥሪያ ቤቶችንና ተቋማትን ለማብቃት ሥልጠና ሰጥተዋል፤ ቁሳቁስ አሟልተዋል፤ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጾታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች የምላሽ አገልግሎት የሚውል ከ7 ሚልዮን ዶላር በላይ ለክልሉ ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡ የክልሉን ማረሚያ ቤቶች ለመደገፍም የ28 ሚልዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ለማጠናከር ሲባል የቢሮ ዕቃዎችና የተሸርካሪዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ክልሉ መሠረተ ልማቶችን ለመሥራትና ለመጠገን እንዲችል ከፍተኛ ወጪ የሚያወጡ የግንባታና የጥገና ማሽነሪዎች ተሰጥተውታል፡፡ በጦርነቱ የተጎዱ ድልድዮችን በጊዜያዊነት ለመጠገን እንዲቻል ሁለት ተገጣጣሚ ድልድዮች የተለገሱ ሲሆን አራት ድልድዮችን ለመገንባት ጨረታ ወጥቷል፡፡ በጦርነቱ ወቅት የተቋረጡ የዐቅም ግንባታ ሥልጠናዎችንም በልዩ ፕሮግራም የክልሉ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ለዘጠኝ ከተሞች የፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚውል ከ409 ሚልዮን ብር በላይ እና ከ7 ሚልዮን ዶላር በላይ ለክልሉ ተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርም ለደመወዝና ለሥራ ማስኬጃ እና ለመንገድ ፕሮጀክት ጥገና ከ418.6 ሚልዮን ብር በላይ ወደ ክልሉ ልኳል፡፡ ለትግራይ ገጠር መንገድ ጥገና ከመንገድ ፈንድ ከብር 107 ሚልዮን ብር በላይ፤ የ2026 በጀት ቅድመ ክፍያ ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ተልኳል፡፡ በፕላንና ልማት ኮሚሽን በኩል ደግሞ በጠቅላላው የ4.2 ሚልዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የትግራይ ክልልን የባህልና ስፖርት እንቅስቃሴ ከተቋረጠበት ለማስጀመር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና የሚመለከታቸው የስፖርት ፌዴሬሽኖች ተገቢውን ድጋፍ ከማድረጋቸውም በላይ የተለያዩ የስፖርት እንቅስቃሴዎች በክልሉ እንዲከናወኑ አድርገዋል፡፡ ለክልሉ የስፖርት ክለቦችም የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ‹‹ብሩህ እናት›› በሚል ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያካሄደውንና ሴቶች ብቻ ተሳታፊ የሚሆኑበት የፈጠራ ሃሳብ ውድድርን ከእናት ባንክ ጋር በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችል የሥምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሄደ፡፡

የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ የሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ብሩህ የፈጠራ ሃሳብ ውድድር አዳዲስና ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የማወዳደር፣ የማብቃትና የመሸለም ሥራ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ውድድር በየዓመቱ በተለያየ ሥያሜና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በማተኮር ሲካሄድ መቆየቱን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው በ2016 በጀት ዓመት ደግሞ ‹‹ብሩህ እናት›› በሚል ሥያሜ ሴቶች ብቻ በማሳተፍ እንደሚያካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በተለያየ ደረጃ በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ሴቶችን በሚጠበቀው ልክ ከማካተት አንፃር በአገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ክፍተት እንደሚስተዋል አቶ ንጉሡ ጥላሁን ጠቁመው፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ክፍተቱን ለማጥበብ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እናት ባንክን ከመሳሰሉ የፋይናንስ ተቋማትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከእናት ባንክ ጋር የተፈራረመው የጋራ መግባቢያ ስምምነት ‹‹ብሩህ እናት›› የፈጠራ ሃሳብ ውድድርን በጋራ ከማዘጋጀት ባለፈ በአገር ውስጥ ምቹ የሥራ ዕድልን ለሴቶች ለማመቻቸት የሚያስችሉና እና ወደ ውጭ አገራት ለሥራ የሚጓዙ ሴቶች ወደ አገራቸው ሲመለሡ በተለያየ የሥራ መስክ ላይ ተሰማርተው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዙ ፓኬጆችንም አካቶ መያዙን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel