ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ያደረጉት ውይይት::
https://twitter.com/ProsperityKera
አፍረካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን የአፍሪካ ምርጥ ሴት መሪ በሚል ሽልማት አበረከተላቸዉ።
መቀመጫዉን በእንግሊዝ ያደረገዉ እና በየአመቱ በአፍሪካ ምርጥ ብቃት ያሳዩ አፍሪካዉያን መሪዎችን የሚሸልመዉ የአፍሪካን ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን የፈረንጆቹን 2024 የሽልማት ስነስርቱን በአዲስ አበባ አከናዉኗል።
በስካይ ላይት ሆቴል የተከናወነዉ የሽልማት ስነስርአት በኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ ሰዉ በሚል ሲካሄድ የመጀመሪያዉ ነዉ ።
የአፍረካን ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን አካል የሆነዉ አፍሪካን ሊደርሺፕ መጋዚን የአመቱን ምርጥ ሰዉና መሪ በላቀ የአመራር ብቃት የሚሸልም ሲሆን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ሽልማቱን የአፍሪካ ምርጥ ሴት አመራር በሚል ተሸልመዋል።
ሽልማቱን የተቀበሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሽልማቱ ስለተበረከተላቸዉ አመስግነዋል።
“የማይበገር የአፍረካን ኢኮኖሚ መገን ባት” በሚል መሪቃል የተካሄደዉ የሽልማት ስነስርአቱ ከ25 በላይ የሚሆኑ እና በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ አፍረካዉያን መሪዎች የተገኙበት ነዉ።
የማይበገር ኢኮኖሚን መገንባት ችለዋል የተባሉት እና በአመራራቸዉ ዘላቂ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስመዘገብ የላቀ ሚና ያላቸዉ አመራሮች የተሸለሙበትም ስነስርአት ነዉ።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኡጋንዳ ሪፐብሊክ የፍትሕ እና የሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ኖርበርት ማኦ ከፕሬዚዳንት ካጉታ ሙሴቬኒ መልእክት ለማድረስ በመጡበት ወቅት ተቀብዬ አናግሪያለሁ። በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርገናል።
This afternoon, I received Hon. Norbert Mao, Minister for Justice and Constitutional Affairs of the Republic of Uganda, who came to deliver a message from President Kaguta Museveni. We also engaged in discussions on matters of bilateral and regional importance.
© Abiy Ahmed Ali
FDRE 🇪🇹 PM
የዛሬው ውይይት ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ነበር። በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ያለን ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ፅኑ ነው። የዛሬው ውይይታችንም ይህንኑ የጋራ አላማ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ነው::
Today's discussions have been held with community representatives from Tigray who traveled from the region to the capital to address important issues. Our commitment to the stability and development of the Tigray region remains unwavering, and our engagement today further supports our shared objective.
© Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM
የኢትዮጵያ ውበት ተመልካች አጥቶ ገረጣ እንጂ አልሞተም፡፡ አቧራ ተጭኖት ደበዘዘ እንጂ ከነጭራሹ አልጠፋም፡፡
ኢትዮጵያ አሁንም ሊወጡ የሚችሉ ብዙ አስደማሚ የውበት ፀጋዎችን ታድላለች፡፡ ሀገራችን ጥበበኞች በአድናቆት የሰላ ብዕራቸውን ቀለም የሚያንቆረቁሩባት፣ ተአምራትን መፍጠር የሚያስችል እምቅ ውበት ባለቤት ናት፡፡
የዚህ እምቅ ውበት ምስጢር የተለያዩ ህብረ ቀለማት በአንድ ላይ የተሰባጠሩባት አሻራ መሆኗ ነው፡፡ ከደብረ ብርሃን የጠባሴ ብርድ እስከ የአፋር ኤርታሌ ሙቀት የሚስተናገድባት፣ ከራስ ዳሽን ከፍታ እስከ ዳሎል ዝቅተኛ ቦታዎች ከታላቁ አባይ ወንዝ እስከ አርባ ምንጮች፣ ከሰላሴ ሜዳዎች እስከ ገርዓልታ ተራራዎች፣ ከከፋ ጥቅጥቅ ደኖች እስከ ኦጋዴን በረሃማ ሥፍራዎች ድረስ፣ ተፈጥሮ ልዩነቶችን በአንድ ላይ አስተሳስሮ ያስቀመጠባት የውበት መሥፈሪያ ናት፡፡
ብዙ ሀገራት በተፈጥሮ የታደሉ ከሆኑ፣ ለዓለም የሚያሳዩት እጅግም ሰፊ ታሪክ አይኖራቸውም፡፡ አንዳንድ የድንቅ ታሪክ ባለቤት የሆኑ ሀገራት ደግሞ፣እዚህ ግባ የሚባል የተፈጥሮ ሀብትና ውበት ባለቤቶች ሆነው አይገኙም፡፡
ኢትዮጵያችን ግን በዓለማችን ድንቅ ታሪክን፣ ተፈጥሯዊ ውበትንና ባህላዊ ፀጋዎችን በገፍ ታድለው ከተጎናፀፉ ውሱን ሀገራት መካከል የምትመደብ ናት፡፡ የክርስቲያንና የሙስሊም ሥልጣኔ ነፀብራቆች ሙዚየም ናት፡፡ በበርካታ ባህሎች ሀብታም የሆነች፣ ብዝኃነትና አንድነት በአንድ ላይ የገጠሙባት ሥፍራ ናት፡፡
የመደመር ትውልድ ገጽ 122
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
ሶስት የሜዳይ እና ሁለት የኒሻን ሽልማት አይነቶችን የሚያቋቁም የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ ።
በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ በተለያዩ መስኮች “የላቀ ስራ የሰሩ” ግለሰቦችን እና ሌሎች አካላትን እውቅና እና ሽልማት ለመስጠት የሚያስችል የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ። አዋጁ ለላቀ የስራ ፈጠራ፣ አርአያነት ላለው የሲቪል አገልግሎት እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ስራ ለሰሩ ሰዎች እና አካላት የሚበረከቱ ሶስት የተለያዩ ሜዳዮችን እንዲሁም ሁለት የክብር ኒሻን አይነቶችን የሚያቋቁም ነው።
ሜዳይ እና ኒሻን “በአብዛኛው ሳንቲም በሚመስል ብረት ላይ ጌጥ በመቅረጽ ወይም በማተም፤ የማዕረግ አርማ በማድረግ አሊያም ቃላትን፣ ድርጊትን፣ ኩነትን በሚገልጽ መልኩ በመቅረጽ” የሚሰጡ የክብር ሽልማቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ከአጼ ዮሐንስ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ሜዳዮችን የመስጠት ልማድ የነበረ ቢሆንም፤ ሽልማቶቹ በህግ ደረጃ ተቋቋመው ሲሰጡ የነበረው በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት እንደነበር ለፓርላማ በቀረበ የአዋጅ ማብራሪያ ላይ ተጠቅሷል።
አሁን በስራ ላይ ባለው የኢፌዲሪ ህገ መንግስት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት “በህግ መሰረት” ኒሻኖችን እና ሽልማቶችን እንደሚሰጥ ቢደነገግም፤ ይህንኑ የሚመራ ህግ እስካሁን ሳይወጣለት ቆይቷል። እስካሁን ድረስ “በተበታተነ ሁኔታ” ሲከናወን የቆየውን የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት አሰጣጥ “ህጋዊ ስርዓት የሚያበጅለት” እንደሆነ የተነገረለት የአዋጅ ረቂቅ፤ በአምስት ክፍሎች እና በ29 አንቀጾች ተከፋፍሎ ተዘጋጅቷል።
ከወታደራዊ እና ፖሊስ አገልግሎት ውጪ ያሉ አካላት ላይ ብቻ ተፈጻሚ እንዲሆን የተዘጋጀው ይህ አዋጅ፤ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 3፤ 2016 ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ለዝርዝር ዕይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴዎች ተመርቷል። የአዋጅ ረቂቁ በውስጡ ከያዛቸው ድንጋጌዎች ውስጥ ስለ ሜዳይ፣ ኒሻን አይነቶች እንዲሁም ስለሚሰጡበት ሁኔታ የሚያትቱት ይገኙበታል። በአዋጁ መሰረት ከሚቋቋሙ የሜዳይ አይነቶች በመጀመሪያ ረድፍ የተቀመጠው፤ “የላቀ የፈጠራ ስራ” ላከናወኑ ግለሰቦች፣ ቡድኖች ወይም ድርጅቶች የሚበረከተው ነው።
“ብሔራዊ የላቀ የፈጠራ ስራ ሜዳይ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሽልማት፤ በኢትዮጵያ ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ “በተለያዩ ዘርፎች የህብረተሰብን ችግር የፈታ ወይም የሚፈታ እጅግ የላቀ ስራ ለሰሩ” ሰዎች የሚበረከት መሆኑ በአዋጅ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል። አንድ የፈጠራ ስራ የሰራ ሰው ይህን ሽልማት ሊሸለም የሚችለው፤ “በሀገሪቱ አግባብነት ባላቸው የፓተንት ወይም የቅጂና ተዛማጅ ህጎች መሰረት ፓተንት ወይም የቅጂ መብት የተሰጠው” እንደሆነ ብቻ መሆኑን በአዋጁ ማብራሪያ ላይ ተቀምጧል።
በአዲሱ አዋጅ የሚቋቋመው ሁለተኛ የሜዳይ አይነት፤ “ብሔራዊ የህዳሴ ሜዳይ” የሚል ስያሜ ያለው ነው። ይህ ሜዳይ የሚሰጠው፤ በሳይንስና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ፣ በስነ ጥበብ፣ በስፖርት ወይም በተለያዩ ዘርፎች “ለሀገር፣ ለህዝብ ወይም በአጠቃላይ ለሰው ልጆች እጅግ የላቀ ስራ ለሰሩ” ግለሰቦች፣ ቡድኖች ወይም ድርጅቶች መሆኑ ተገልጿል።
“ብሔራዊ የላቀ ሲቪል አገልግሎት ሜዳይ” የተባለው ቀሪው የሜዳይ አይነት፤ “የስራ ዲሲፕሊን ጠብቀው፣ በታታሪነት እና በታማኝነት በማገልገል የላቀ ስራ የሰሩ” የመንግስት ሰራተኞች የሚሸለሙት እንደሆነ በአዋጅ ረቂቁ ተመልክቷል። ይህ የሜዳይ ሽልማት “ለረጅም ጊዜ አርአያነት ያለው አገልግሎት ሰጥተው” በጡረታ ወይም በሌላ ምክንያት የመንግስት መስሪያ ቤትን ለለቀቁ ወይም በስራ ላይ እያሉ ለፈጸሙት ሀገርን የማገልገል ተግባር “እውቅና እና ክብር የሚሰጥበት ነው” ተብሏል።
እነዚህን የሜዳይ አይነቶች የተሸለሙ ግለሰቦች፤ “ልዩ መብቶች” እንደሚያገኙ በአዋጅ ረቂቁ ላይ ተደንግጓል። አንድ ተሸላሚ ደመወዝ ካለው የደመወዙ 25 በመቶ፤ ጡረተኛ ከሆነ ደግሞ የጡረታ አበሉ 40 በመቶ እንደሚጨመርለት በአዋጅ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል። ተሸላሚው ደመወዝ ከሌለው፤ አዋጁን ለማስፈጸም በሚወጣ መመሪያ የሚወሰን የገንዘብ መጠን “በስጦታነት” እንደሚሰጠው ተጠቅሷል።
የሜዳይ ተሸላሚዎች ከሚያገኟቸው ልዩ መብቶች ውስጥ “በመንግስት የጤና ተቋማት ነጻ የህክምና አገልግሎት ማግኘት” የሚለው ተካትቷል። የሜዳይ ተሸላሚዎች በመንግስት የትምህርት ተቋሞች “ቅድሚያ የትምህርት ዕድል ይሰጣቸዋል” የሚለውም “በልዩ መብትነት” ተዘርዝሯል። ተሸላሚዎች በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የተፈረመ “መታወቂያ እና ሰርተፊኬት” የሚሰጣቸው መሆኑ፤ ሌላው “በልዩ መብትነት” የተካተተ ድንጋጌ ነው።
የአዋጅ ረቂቁ ከሜዳዮች በተጨማሪ “የኢትዮጵያ ታላቅ ክብር ኒሻን” እና “የአፍሪካ ታላቅ ክብር ኒሻን” የሚል ስያሜ የተሰጣቸውን የክብር ሽልማቶችን የሚያቋቁሙ ድንጋጌዎችን በውስጡ ይዟል። የኒሻን ሽልማቶች በአብዛኛው “ሀገራት ለሀገር መሪዎች እና በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ግለሰቦች የሚበረከቱ” መሆናቸውን አዋጁን ለማብራራት የቀረበው ሰነድ አትቷል።
በዚሁ ማብራሪያ ላይ “የኢትዮጵያ ታላቅ ክብር ኒሻን” በሀገር ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ “በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊ ዘርፎች እንዲሁም በዲፕሎማሲ መስክ እጅግ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ” ግለሰቦች፣ ቡድኖች ወይም ድርጅቶች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። “የአፍሪካ ታላቅ ክብር ኒሻን” ደግሞ “በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያ፣ ማህበራዊ ዘርፎች” አህጉራዊ ችግር ፈቺ ስራ ላበረከተ ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ድርጅት የሚሰጥ መሆኑ ተጠቅሷል። ይህ የኒሻን ሽልማት በአፍሪካ ሀገራት መካከል “መልካም ወዳጅነት እና ዘላቂ ትስስር እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ” ግለሰቦች እና አካላትም የሚሰጥ መሆኑን የአዋጅ ረቂቁ አክሏል።
እነዚህን የኒሻን ሽልማቶች ያገኙ ግለሰቦች፤ በስማቸው “መንገድ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤት፣ ህንጻ ወይም ተመሳሳይ ተቋም እንደሚሰየምላቸው” በአዋጅ ረቂቁ ተደንግጓል። የኒሻን ተሸላሚዎቹ፤ በብሔራዊ በዓላት የአከባበር ስነ ስርዓት ላይ በሚዘጋጅላቸው ቦታዎች ላይ ይቀመጣሉ። የኒሻን ተሸላሚዎች ሜዳይ የሚሰጣቸው ሰዎች የሚያገኟቸው የደመወዝ፣ የገንዘብ ስጦታ፣ የትምህርት ዕድል እና የህክምና አገልግሎት በተመሳሳይ መልኩ ተጠብቆላቸዋል።
ሜዳይ፣ ኒሻን ወይም ሽልማት ለማግኘት የሚያበቃ ተግባር ፈጽሞ ለሞተ ሰው፤ በአዲሱ አዋጅ መሰረት አግባብነት ያለው ሽልማት እንደሚዘጋጅለት በህግ ረቂቁ ላይ ተመልክቷል። በአዋጁ መሰረት የሚዘጋጀው ሜዳይ፣ ኒሻን ወይም ሽልማት “ለሟቹ ተሸላሚ ታላቅ ልጅ ወይም በልጆቹ ዕድሜ ቅደም ተከተል የሚሰጥ” ይሆናል።
ሁለት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ሜዳይ ወይም ኒሻን የተሸለመ ግለሰብ ከእነዚህ ዕውቅናዎች በተጨማሪ በማንኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ “አግባብነት ባለው ስፍራ ሀውልት ሊቆምለት እንደሚችል” በአዋጅ ረቂቁ ላይ ተቀምጧል። የሀውልቱ አይነት፣ መጠን፣ ይዘት እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች የሚወሰኑት፤ ወደፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚወጣ መመሪያ መሆኑም ተጠቁሟል።
በአሜሪካ ኮሎራዶ የአድዋ በዓል በየአመቱ ህዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ተወሰነ::
WOW 💪💪💪
https://twitter.com/ProsperityKera
ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል::
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ታሪኩን፣ ጀግንነቱን እና ጽናቱን በሚመጥን መልኩ ታሪክን ያሸጋገረ ፣ ትውልድ የሚማርበት እና በወቅቱ የነበረውን አንድነት በሚገልጽ መልኩ መገንባቱ እንዳስደሰታቸው አባቶቹ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል::
https://twitter.com/ProsperityKera
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ16 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት አፅድቋል፡፡
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን÷ በስብሰባውም በፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስርዓትን ለማሻሻል እና ለማዘመን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመትን መርምሮ አጽድቋል፡፡
የምክር ቤት አባላትም የዳኞችን ሹመት አስመልክቶ በሰጡት ሃሳብ የዳኝነት ስርዓቱ ሀገርን መምሰል እንዳለበት በመግለጽ ዳኝነት ነጻነት እንዲኖረው አሳስበዋል፡፡
ዳኞች ለሹመት ሲመለመሉ ፈተናዎችን እንደወሰዱ የተገለጸ ሲሆን÷ አመራረጡም ኢትዮጵያን እንዲመስል ተደርጓል ተብሏል፡፡
ሹመቱ የጸደቀላቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችም ሀገርን እና ህዝቡን ለማገልገል ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን በሚመለከት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የፓፓያ ምርጥ ዘር ችግኝ የማስፋፋት ንቅናቄ በየዓመቱ እየጨመረ መጥቶ ባለፈው ዓመት 10 ሺህ 400 ሄክታር መሬት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ለውጭ ገበያ የሚውሉ የፍራፍሬ ምርቶችን በብዛትና በጥራት የማምረት ስራው በፍጥነት በመተግበር ላይ ይገኛል ብለዋል።
የዛሬ ሶስት ዓመት የተጀመረው የፓፓያ ምርጥ ዘር ችግኝ የማስፋፋት ንቅናቄ በየዓመቱ እየጨመረ መጥቶ ባለፈው ዓመት 10 ሺህ 400 ሄክታር መሬት መድረሱን አመልክተዋል።
በዚህ ዓመት 50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ ዘር የፓፓያ ችግኝ ለማልማት "የቁጭት ዕቅድ" መያዙን ጠቅሰው፤ ለዚህም 135 ሚሊዮን ችግኞችን ለማዘጋጀት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
እስከ አሁን 127 ሚሊዮን ችግኝ በማዘጋጀት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ባለው ቀሪ ጊዜ ዕቅዱ በሙሉ እንደሚሳካ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
መደመር የማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን ጨምሮ ሁሉንም ግላዊና ማህበረሰባዊ የህይወት ዘይቤን የሚነካ እሳቤ ነው፡፡ አላማዎቹም አገራችን ኢትዮጵያ ልትሄድበትና ልትደርስበት የሚገቡ መንገዶችና መዳረሻዎች ናቸው፡፡
አለም አቀፍ ዕውቀቶች የመደመርን ሐሳብ ለማዳበር አጋዥ ሚና አበርክተዋል፡፡ሆኖም ግን የእነዚህ ዓለም አቀፍ ዕውቀቶች ፋይዳ መለኪያውና ማንጠሪያው ተጨባጭ ውስጣዊ አገራዊ ሁኔታ ነው፡፡
ዓላማውም አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበቻቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ድሎች ጠብቆ ማስፋት፣የተሰሩ ስህተቶችን ማረም፣እንዲሁም የመጻኢውን ትውልድ ጥቅም እና ፍላጎት ማሳካት ነው፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገው እለት ከጠዋቱ ሶስት ስዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ፣ በስብሰባው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞች ሹመትን፣የፌዴራል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እና የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን እና የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች እንደሚመራም ከኢፌዴሪ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
በያዝነው በጀት ዓመት ግንባታቸው ከተጀመሩ 56 ትምህርት ቤቶች 39ኙ ግንባታቸው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የሸገር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡
የአሥተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ፍራኪያ ካሣሁን እንደገለጹት÷ በያዝነው የበጀት ዓመት ግንባታቸው ከተጀመሩ 56 ትምህርት ቤቶች 39 ቅድመ መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡
በግንባታ ላይ የሚገኙ ቀሪ ትምህርት ቤቶችንም በዚሁ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ከግንባታው ጎን ለጎንም የግብዓት እጥረት ላለባቸው ትምህርት ቤቶች ግብዓት የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢትዮጵያ ውበት ተመልካች አጥቶ ገረጣ እንጂ አልሞተም፡፡ አቧራ ተጭኖት ደበዘዘ እንጂ ከነጭራሹ አልጠፋም፡፡
ኢትዮጵያ አሁንም ሊወጡ የሚችሉ ብዙ አስደማሚ የውበት ፀጋዎችን ታድላለች፡፡ ሀገራችን ጥበበኞች በአድናቆት የሰላ ብዕራቸውን ቀለም የሚያንቆረቁሩባት፣ ተአምራትን መፍጠር የሚያስችል እምቅ ውበት ባለቤት ናት፡፡
የዚህ እምቅ ውበት ምስጢር የተለያዩ ህብረ ቀለማት በአንድ ላይ የተሰባጠሩባት አሻራ መሆኗ ነው፡፡ ከደብረ ብርሃን የጠባሴ ብርድ እስከ የአፋር ኤርታሌ ሙቀት የሚስተናገድባት፣ ከራስ ዳሽን ከፍታ እስከ ዳሎል ዝቅተኛ ቦታዎች ከታላቁ አባይ ወንዝ እስከ አርባ ምንጮች፣ ከሰላሴ ሜዳዎች እስከ ገርዓልታ ተራራዎች፣ ከከፋ ጥቅጥቅ ደኖች እስከ ኦጋዴን በረሃማ ሥፍራዎች ድረስ፣ ተፈጥሮ ልዩነቶችን በአንድ ላይ አስተሳስሮ ያስቀመጠባት የውበት መሥፈሪያ ናት፡፡
ብዙ ሀገራት በተፈጥሮ የታደሉ ከሆኑ፣ ለዓለም የሚያሳዩት እጅግም ሰፊ ታሪክ አይኖራቸውም፡፡ አንዳንድ የድንቅ ታሪክ ባለቤት የሆኑ ሀገራት ደግሞ፣እዚህ ግባ የሚባል የተፈጥሮ ሀብትና ውበት ባለቤቶች ሆነው አይገኙም፡፡
ኢትዮጵያችን ግን በዓለማችን ድንቅ ታሪክን፣ ተፈጥሯዊ ውበትንና ባህላዊ ፀጋዎችን በገፍ ታድለው ከተጎናፀፉ ውሱን ሀገራት መካከል የምትመደብ ናት፡፡ የክርስቲያንና የሙስሊም ሥልጣኔ ነፀብራቆች ሙዚየም ናት፡፡ በበርካታ ባህሎች ሀብታም የሆነች፣ ብዝኃነትና አንድነት በአንድ ላይ የገጠሙባት ሥፍራ ናት፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
አፍረካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዴ አዳነች አቤቤን የአፍሪካ ምርጥ ሴት መሪ በሚል ሽልማት አበረከተላቸዉ።
https://twitter.com/ProsperityKera
Magaalonni keenya bakka oomishaas bakka gurgurtaadhas
Bulchiinsa Magaalaa Bishooftuu Kutaa Magaalaa Duukamitti sassaabbii qamadii jallisii bonaa
https://twitter.com/ProsperityKera
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆነ።
በሩብ ፍጻሜው አርሰናል ከ ባየር ሙኒክ፣ አትሌትኮ ማድሪድ ከ ቦርሲያ ዶርትሙንድ፣ ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ፣ ፒ.ኤስ.ጂ ከ ባርሴሎና እንደሚጫወቱ የወጣው ዕጣ ያሳያል፡፡
በግማሽ ፍጻሜው ደግሞ አትሌትኮ ማድሪድ ከ ቦርሲያ ዶርትሙንድ አሸናፊ ከ ፓሪሰንት ጀረሜን ከ ባርሴሎና አሸናፊ የሚጫወቱ ሲሆን፣ የአርሰናል ከ ባየር ሙኒክ አሸናፊ ከ ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ አሸናፊ ይጫወታሉ፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የዛሬው ውይይት ከትግራይ ክልል ተጉዘው ከመጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ነበር። በትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማስገኘት ያለን ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ፅኑ ነው። የዛሬው ውይይታችንም ይህንኑ የጋራ አላማ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ ነው::
Today's discussions have been held with community representatives from Tigray who traveled from the region to the capital to address important issues. Our commitment to the stability and development of the Tigray region remains unwavering, and our engagement today further supports our shared objective.
© Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሴቶች ተሀድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጉብኝት እና ምረቃ መርሀ-ግብር (በፎቶ)
📸 - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች እና አመራሮች ለቀድሞ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በነበራቸው የአመራርነት ዘመናቸው ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የክብር ሽኝት አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር የአቶ ደመቀ የካበተ የአመራርነት ልምድ ከተቋም ባለፈ በአገርም ደረጃ ወደፊትም ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ብለዋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ጊዜያቸው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የጀመሯቸውን መልካም ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቶ ደመቀ መኮንን በነበራቸው ቆይታ በተለይም አገራችን በገጥመዋት የነበሩ ፈተናዎችን እንድትሻገር ችግር ፈቺ ሐሳቦችን በማፍለቅ እና ቆራጥ አመራር በመስጠት ቁልፍ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ስኬት እንድታስመዘግብ አበርክቷቸው የጎላ እንደነበር ጠቅሰዋል።
በተለይም በተረጋጋ እና በሰከነ አመራር ሰጭነታቸው ከሁሉም ሠራተኞች ጋር በቅርብ በመሥራት እና ሥራዎችን በመከታተል ወደ ተግባር እንዲቀየር ላደረጉት ጥረት ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።
አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው፣ ለተደረገላቸው እውቅና ሠራተኛውን እና አመራሩን አመስግነው ቀሪ ጊዜያቸውን ተቋሙን፣ አገራቸውን እና ሕዝባቸውን በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ እንደሚያግዙ ገልጸዋል።
በሽኝት እና እውቅና ሥነ-ሥርዓቱ የዋናው መሥሪያ ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ዘመኑን የዋጀ አየር ሀይል
https://twitter.com/ProsperityKera
Waadaa Galame Gochaan Raawwachuun Badhaadhina Biyya Keenyaa Dhugoomsina
See more
facebook.com/10005743729135…
የመሬት ልማትና አስተዳደር ስርዐት!
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
https://twitter.com/ProsperityKera
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን በሆሳዕና ከተማ እያካሔደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ የተጣራ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን አቅርቦ መወሰን፣ በክልሉ የሰባት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ የስራ መመሪያ ማድረግ፣ የሰው ኃይል የመዋቅር ጥናት የደረሰበትን ደረጃ ለይቶ ማወቅ እና ግብዓት መስጠት ልዩ ልዩ አዋጆች እና ደንቦች ላይ ውይይት ማካሔድ በእለቱ የተመረጡ አጀንዳዎች ናቸው።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀረቡለት አጀንዳዎች ላይም እየመከረ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የፍትህ ሚኒስቴር ከተ.መ.ድ. የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል መከላከል ጽ/ቤት (UNODC) ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ሁለተኛው ዙር የኢትዮ-ኬንያ የሁለትዮሽ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
መደበኛ ባልሆነ መንገድ ኢትዮጵያውያን በኬንያ በኩል አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት በሚያደርጉት ፍልሰት በርካታ ዜጎች ለሞት እና ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተዳረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
በሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በሕገወጥ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመዋጋት በሕግ ነክ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም ደግሞ በጋራ የወንጀል ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ተጠያቂ ስለማድረግም ነው መድረኩ የሚመክረው ፡፡
ስብሰባውን የከፈቱት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር የመንግስት ሕግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ ባለፉት አራት እና አምስት ዓመታት መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመቀነስ እና መደበኛ የሆነ የሰዎች እንቅስቃሴን ለማበረታታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
በተከናወኑት ተግባራትም አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን የጠቆሙት ሚንስትር ዴኤታው በአንድ ሀገር እንቅስቃሴ ብቻ የተፈለገውን ውጤት ለማግኘት ስለማይቻል ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል
በተጀመረው የኢትዮ-ኬንያ የሁለትዮሽ ውይይት መድረክ ላይ የሚደረስባቸውን ድምዳሜዎችና ስምምነቶች በኢትዮጵያ በኩል ለመተግባር ቁርጠኝነት ስለመኖሩ ገልፀዋል፡፡
ውይይቱ እስከ መጋቢት 04 ቀን 2016 ድረስ እንደሚቆይም ከሚኒስቴሩ ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ከተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የተውጣጡ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
አዲስ አበባ ፕሮጀክት ጀምሮ በማጠናቀቅ፣ በአመራር ቁርጠኝነት እና ከሕዝብ ጋር ተቀራርቦ እየተመካከሩ ስራዎችን በመስራት ትልቅ ልምድ የሚቀሰምባት መሆኗን በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ከንቲባዎች ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ የከተማዋን ገፅታ የሚቀይሩ እና የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ትላልቅ ሥራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን በጉብኝቱ ወቅት መታዘባቸውንም ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ ላይ ለውጥ ለማምጣት የቻልነው ዋናው የአስተሳሰብ ለውጥ በማድረጋችን ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከተሞች ከፕላን ውጪ ሲገነቡ ችላ በመባሉ ዛሬ በከተማ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት የልማት ስራዎችን ለመተግበር መሰናክል ስለሆነብን እኛም ዛሬ ተመሳሳይ ስህተት እንዳይፈጠር ከተማችንን እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ ለማድረግ በከተማዋ ስታንዳርድ ልክ በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ በበኩላቸው፣ ስራው እንደ ሀገር መስፋት ስላለበት እይታችንን በማስፋት ከተሞችን ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ማድረግ አለብን ያሉ ሲሆን አንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ከተማ ልክ የሆኑ ተጨማሪ ከተሞችን መገንባት ይጠበቅብናልም ብለዋል።
የከተማ አመራሮችና ከንቲባዎች መሰጠትን፣ ቆራጥነትን እና የምንናገረውን በተግባር መለወጥን ከአዲስ አበባ ተሞክሮ በመውሰድ ለሕዝብ የገባነውን ቃል በመተግበር የሕዝቡን ችግር የሚቀርፉ ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚጠበቅባቸው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ መናገራቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ከጫጫታው ባሻገር የመጽናት አቋምና የእድገት ጥሪ!
ከመሠረተ ቢስ ሃሰተኛ ወሬዎች የተነሳ ለኢትዮጵያ ዕድገት ያለኝ ቁርጠኝነት ፈጽሞ አይናወጥም። በሚዲያና በህዝብ ፊት ባደረኩት የ12 ዓመታት ጉዞዬ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ላሳዩኝ ያላሰለሰ ድጋፍና አክብሮት ከልብ አመሰግናለሁ። በዚሁ አጋጣሚ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመቃወም ጸንቻለሁ! በህዝብ አደባባይ አንዳለ ግለሰብ ተግዳሮቶች ሊመጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን እነዚህ ፈተናዎች ወጣቶቻችንን በማንቃት እና በዕውቀት በማስታጥቅ ብሩህ የወደፊት ተስፋን እንዲሰንቁ ለማድረግ ያለኝን ቁርጠኝነት ያቀጣጥላሉ። #ኢትዮጵያ 💚💛❤️
ሰሞኑን ለተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ ላይ ይፋዊ ምላሼን ከስር አያይዣለሁ።
Beyond the Noise: A Clarion Call for Integrity and Progress!
Amidst the whispers of unfounded rumors, my dedication to Ethiopia's progress remains unshaken. Grateful for 12-years of unwavering support and respect by fellow Ethiopians in my journey as a media person and public figure, I stand firm against misinformation! Challenges may come as a public figure, but they only fuel my commitment to empower and educate, aiming for a brighter future for our youth. #Ethiopia 💚💛❤️
Below is my official statement on the recent misinformation.
https://twitter.com/ProsperityKera
ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ የሚያሰራቸውን የ5ሺህ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረናል።
እንዲሁም ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማሕበር፣ መንግስት ከስድስት ዓመታት በፊት በነጻ ባስረከበው 3.8 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባቸውን 5ሺህ ቤቶች መርቀናል።
የህዝባችን ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል አንዱ አማራጭ የግል አልሚዎችን ማበረታታትና በአጋርነት የምንሰራበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሰራን እንገኛለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ የተደረገ ማስተካከያ👆👆👆
https://twitter.com/ProsperityKera