በሚቀጥሉት11 ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከዕለት ወደ ዕለት እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡
አብዛኛዎቹ የበልግ አብቃይና ተጠቃሚ ቦታዎች በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ ዝናብ እንደሚስተዋልባቸውም ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረትም በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
በመሆኑም በበልግ አብቃይ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ በትንበያው ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡
በአጠቃላይ በሚቀጥሉት ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ሁሉም የወለጋ ዞኖች፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉአባቦር፣ ጅማ፣ ሁሉም የሸዋ ዞኖች፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ እንዲሁም ሐረሪ እና ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባ፣ ከአማራ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ የደቡብ፣ የመካከለኛው እና የሰሜን ጎንደር ዞኖች፣ የባህርዳር ዙሪያ፣ የዋግህምራ ዞኖች፣ የሰሜንና የደቡብ ወሎ ዞኖች፣ እንዲሁም የሰሜን ሸዋና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ብዙ ቦታዎቻቸውን የሚያዳርስ የተስፋፋ ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆን÷ በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ የአፋር ክልል ዞኖች፣ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ የደቡብ ምስራቅ፣ የምስራቅ፣ የመካከለኛው እና የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ዞኖች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሱማሌ ክልል የሲቲ፣ የፋፈን፤ ብዙ ቦታዎቻቸውን የሚያዳርስ የተስፋፋ ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆን፤ በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብ ትግራይ ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ የሊበን፣ የአፍዴር፣ የኤረር እና የነጎብ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ ቋራ፣ መተማ፣ መተራ፣ ዱብቲ፣ ሎጊያ፣ አብዓላ፣ አፍዴራ፣ ጎዴ፣ ቀብሪ ደሃር እና ደጋሀቡር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ተቁመዋል፡፡
ሁኔታው ለበልግ እርሻ ሥራ፣ ለአፈር እርጥበት መሻሻል ለቋሚ ተክሎች የውሃ ፍላጎት መሟላት፣ የረጅም ጊዜ ሰብሎችን አስቀድመው ለሚዘሩ አካባቢዎች የማሳ ዝግጅት ለማከናውን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የግጦሽ ሳርና የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ከማሻሻል አንፃር ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተጠቅሷል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በተኢፌዴሪ አጭር የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ጀነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖችን አስመረቀ።
በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የክብር እንግዶቹ መከላከያ ዋር ኮሌጅ፣ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና መሰረተ ልማቶች ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ ፍልሰተኞች የአፍጥር መርሃግብር አካሄዱ።
https://twitter.com/ProsperityKera
"ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና"
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ስር የተደራጁ የልዩ ወረዳዎች አባላት ኮንፈረስ እየተካሄደ ይገኛል።
ኮንፈረንሱ "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን ልዩ ወረዳዎች መሰረታዊ ድርጅት አመራሮች እና አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በኮንፍረንሱ በግማሽ ምርጫ ዘመን የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት ፣ በአፈፃፀም የታዩ ጉድለቶች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣዎች ዙሪያ ውይይት የተደረገባቸው አኳር ሀሳቦች ናቸው።
https://twitter.com/ProsperityKera
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች የሚቋቋሙበት ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 18ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት አካሂዷል።
በመደበኛ ስብሰባውም የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች የሚቋቋሙበትን በተመለከተ በወጣው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል።
የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት በተመለከተ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም አዋጁ ለልማት ተነሺዎች ተገቢ የሆነ የካሳ ክፍያ ለማከናወን እንዲሁም የልማት መጓተት ችግርን ለመፍታት መሆኑን አስረድተዋል።
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን አሰራር የሚያሳልጥ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
የመሰረተ ልማት ስራዎች ሲከናወኑ የንብረት መገመት፣ የመክፈልና የማስነሳት ስራ ለክልሎችና ለከተማ አሥተዳደሮች የሚሰጥ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በአሰራር ሂደቱ የባለቤትነት ስሜት ለመፍጠርና ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት መሆኑም ተገልጿል።
ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ለዝርዝር ዕይታ ለከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች እና ለሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ዞን በግብርናና ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች የመስክ ምልከታ አስመልክቶ ለዞኑ አመራር ግብረ መልስ ሰጠ።
በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር በዶክተር አለሙ ስሜ የተመራው የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ዞን በግብርናና ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎች የመስክ ምልከታ አድርጓል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን በሶስት ወረዳዎችና ቁሊቶ ከተማ ለ3 ተከታታይ ቀናት የተደረገውን የመስክ ምልከታን አስመልክቶ ቡድኑ በየደረጃው የሚገኘው የዞኑ አመራሮ በተገኙበት ግብረ መልስ ሰጥቷል።
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ግብረ መልሱን በጥንካሬ፣ ለሌሎች ምርጥ ተሞክሮ የሚሆኑና እና ትኩረት የሚሹ በሚል አቅርበዋል።
በዚህ መሠረትም:- በጥንካሬ የታዩ- የውስጥ ሰላምንና የአካባቢውን ሠላም ለማስጠበቅ ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ፣ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ የአረንጓዴ አሻራ እንክብካቤ፣ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር በክላስተር ማሳ ጥሩ ጅማሮ ታይቷል ብለዋል።
በሌማት ትሩፋት በዶሮ እርባታ የታየው ለየት ያለ መሆኑ፣ የግብርና ስራ በትምህርትቤት ጭምር መታየቱ፣ በኢንዱስትሪ ልማት ወጣቶችን አደራጅቶ ከማሰራት አንፃር ጥሩ ጅማሮ መታየቱ፣ በከተማ የቤት ችግር ፈቺ ተግባራት መኖራቸው፣ ከኮትሮባንድና ህገወጥነትን ከመቆጣጠር አንፃር ያለው እንቅስቃሴ፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር ጥሩ እንቅስቃሴ መኖሩ፣ የጤና መድህን ሽንፋን፣ የአመራሩ የመንፈስ አንድነት በጥንካሬ የታዩ መሆናቸውን ዶክተር አለሙ አብራርተዋል።
ለሌሎች ምርጥ ተሞክሮ የሚሆን በሚል የቀረቡ- ከሌማት ትሩፋት የዶሮ እርባታ ልማት እንደ ሀገርም ምርጥ ተሞክሮ መሆን የሚችል መሆኑ፣ በዞኑ ዌራ ዲጆ ከተረጂነት የወጣች የሲምቢጣ ቀበሌ፣ በንብ ማነብ ስራ ያለው እንቅስቃሴ፣ የአካባቢውን ሠላም ከተማስጠበቅና የአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በምርጥ ተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
በቀጣይ ትኩረት የሚሹ የከተማ ፅዳትና ውበት አኳያ ቀሪ ስራዎች መኖራቸው፣ ከጤና አንፃር የታካሚዎች ቦታ ችግር፣ በትምህርት ዘርፉ እንደ ሀገር ያሉ ችግሮች እንደዞንም መኖራቸው፣ ብድር ማስመለስ፣ በጥንካሬ የታዩትን አጠናክሮ ማስቀጠል ትኩረት የሚሻ መሆኑን ዶክተር አለሙ ገልጸዋል።
የዞኑ አመራርም ከቡድኑ በጥንካሬ የተሰጠውን ግብረ መልስ አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ትኩረት የሚሹ በሚል የተሰጠውን ደግሞ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ የህብረተሰቡን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ መዘጋጀቱን ቁርጠኝነቱን ገልጿል።
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
በዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ የተመራ የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በልደታ ክ/ከተማ የመስክ ምልከታ አደረገ፤
በሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስተር ዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ የተመራ በፊዴራል ደረጃ የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን የመስክ ምልከታ አድርጓል።
የሱፐር ቪዥን ቡድኑ በሲቪል ምዝገባና በነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት እና በንግድ ጽ/ቤት በቴክኖሎጅ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን፣ የህንፃ ግንባታ እንዲሁም በበጎ ፍቃድና በህ/ሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ ስራዎችንም ምልከታ አድርጓል።
#Prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
በአዲስ አበባ ከፍተኛ የጸኃይ ጨረር በሰው ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል በሚል ማኅበራዊ ሚዲያው የሚሰራጨው መረጃ ኃሰተኛ መሆኑን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለጸ።
ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር ገፆች በአዲስ አበባ በጤና ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ከፍተኛ የፀኃይ ጨረር እንደሚኖር ተደጋጋሚ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።
ይህን ተከትሎም አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ጉዳት ያደርስባቸዋል በሚል ከመማሪያ ክፍላቸው እንዳይወጡ ክልከላ ማድረጋቸውን ኢዜአ ከተለያዩ ምንጮች ማረጋገጥ ችሏል።
አንዳንድ ወላጆችና የከተማዋ ነዋሪዎችም በዚሁ መረጃ ምክንያት መደናገር እንደተፈጠረባቸውም እንዲሁ።
ጉዳዩን አስመልክቶ ኢዜአ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የስፔስና ፕላኔተሪ ሳይንስ ሥራ ክፍል መሪና ተመራማሪ ንጉሴ መዝገበ(ዶ/ር) አነጋግሯል።
ባለሙያው፤ ከፍተኛ የጸኃይ ጨረር በሰው ጤና ላይ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ኃሰተኛና ከሳይንሱ ውጪ ነው ብለዋል።
የጸኃይ ጨረር በሰዎች ጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለው የጤና ጉዳት አለመኖሩንም አረጋግጠዋል።
ያም ብቻ ሳይሆን ከጸኃይ የሚነሱ ሞገዶች ወይም ቅንጣቶች ወደ መሬት ወርደው ሰዎች ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም የላቸውም ነው ያሉት።
ይልቁንም ከጸኃይ የሚነሱ ጨረሮች በብዛት የሚያጠቁት ስፔስ ላይ ያሉ ሳተላይቶችን የመገናኛና የኮሙኑኬሽን መሣሪያዎችን መሆኑንም አብራርተዋል።
አለም ዓቀፍ የስፔስ ትንበያዎች እንዲህ አይነት ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ምንም አይነት ፍንጭ አለመስጠታቸውንና የተናፈሰው ሐሰተኛ መረጃ ምንጩ የማይታወቅ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ኅብረተሰቡ የሚሰራጩ መረጃዎችን ትክክለኛነት ከሚመለከታቸው አካላት ማጣራት እንዳለበት ገልጸው፣ የእለት ተእለት እንቅስቃሴውን ያለምንም ሥጋት ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በተለያዩ ክልሎችና ከተማ አሥተዳደሮች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመለከተ።
መንግስት በሁሉም ክልሎች ያሉ ሃብትና ጸጋዎችን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል፣ የሚነሱ ቅሬታዎችንም ከኀብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ ለመፍታት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ አመራሮችም በተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እያደረጉት ያለው የመስክ ምልከታና ድጋፋዊ ክትትል መርሐ-ግብር የዚህ ተግባር አካል መሆኑ ተጠቁሟል።
አመራሮቹ በጉብኝታቸው÷ የበጋ መስኖ ሥንዴ ልማት፣ የተፈጥሮ ሐብት ልማትና ጥበቃ ሥራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
በዘንድሮ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ የተማሪዎች ምዝገባ መካሄዱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተሳካ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎች የሚፈተኗቸውን የትምህርት ዓይነቶች አውቀው ዝግጅት እንዲያደርጉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መከናወኑን አንስተዋል።
ተማሪዎች በሥነ-ልቦና እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውንም ጠቅሰዋል።
ለሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚቀመጡ የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 3 እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚያከናውን ተቋሙ መግለጹ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ ተቋሙ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አንዳንድ አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን ጠቁመዋል።
በዚህም እስካሁን ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
የተቀሩት የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በዚህ ሣምንት እንደሚከናወን ነው ያረጋገጡት።
የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለና ተማሪዎቹን በአግባቡ መመዘን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።
የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አንስተው በቀጣይ የፈተናው ሕትመት እንደሚጀመርም ገልፀዋል።
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በየአካባቢው ያለውን የወርቅ ማዕድን ሀብት በአግባቡ በማልማት ለሀገራዊ የብልጽግና ኢኮኖሚ ስኬት ማዋል ይኖርብናል። ዶክተር ፍጹም አሰፋ
የፈዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦቸ ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ እየተሰሩ ያሉትን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡
ቡድኑ በቤሮ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰሩ ያሉ የሌማት ትሩፋት፣ በጀባ ከተማ ተጨማሪ የትምህርትና የጤና ጣቢያ ግንባታ፣ የወርቅ አምራች ማህበራት የስራ እንቅስቃሴና ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝ በቤሮ ወረዳ ጀባ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የተሰሩ የድሮንና የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ተጎብኝቷል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሱፐርቪዥን ቡድኑ በቤሮ ወረዳው ከጀባ ከተማ ማህበረሰብና ከማዕድን አምራች ማህበራት ጋር በሠላም ፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያም ተወያይተዋል ፡፡
የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ እንደሀገር የማዕድን ዘርፍ 5 ትኩረት ከሚሰጥባቸው የትኩረት መስኮች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ሀብቱ በተለያዩ መንገድ በጥቂቶች እጅ በመውደቁ ህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ሳይጠቀም ቆይቷል ብለዋል፡፡
በተለይም ቤሮ ወረዳ የወርቅ ማዕድን በጣም በስፋት ያለበት ቢሆንም በዘርፉ ከሚታዩ ጫናዎች ምክንያት ህብረተሰቡ ያልተጠቀመበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
በየአካባቢው ያለው የወርቅ ማዕድን ሀብት ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ መሰራት ጥቅም ላይ እንዲውል እያንዳንዱ ማህበረሰብ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ዶክተር ፍጹም አሰፋ አስታውቀዋል፡፡
ማዕድን ልማት የህብረተሰቡ መሸጋገሪያ እንጂ ዘላቂ ልማት አይደለም ያሉት ሚኒስትሯ ህብረተሰቡ ከወርቅ ማዕድን የሚገኘውን ሀብት ሌለ ልማት ላይ ማዋል አለበት ብለዋል ።
በወረዳው ህብረተሰብን በማስተባበር ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ እየተሰሩ ያሉ የትምህርት እና ጤና ጣቢያ ግንባታ ስራ በጠም የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው ይህ መልካም ተግባር ህብረተሰቡ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ጌታቸው ኬኒ የህዝብ ሀብት የሆነውን የወርቅ ማዕድን በተደራጀ መንገድ ቁጥጥር ለማድረግ ከህገወጥ መንገድ ለማስቀረት ህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተን የሚስተዋለውን ችግር የሚፈተ ሁኔታ እንደሚመቻች ገልጸዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በወረዳ የፀጥታ፣ የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማት፣ የነዳጅ ዋጋ መናር እና ህገወጥ የወርቅ ግብይት እንዲሁም የወርቅ ዋጋ ማናስ አጠቃላይ ተግባራቸው ላይ ጫና እያስከተለ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በየጊዜው የምመረተው የወርቅ ምርት በሚፈለገው መጠን ጥቅም ላይ እንዲውልና ውጤት እንዲያመጣ የፀጥታ ሃይልን ማጠንከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
#Prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
Imala badhaadhinaa jalqabneen Itoophiyaa sabdaneettii ni ijaarra!
Paartiin Badhaadhinaa imala hunda galeessa akka biyyaatti eegaleen Itoophiyaa sabdaneettii tokkummaa fi obbolummaan lammiilee itti mirkanaa'e ijaaruuf hojjataa jira.
https://twitter.com/ProsperityKera
ጢስ አባይ ከተማንና አካባቢውን ለመቆጣጠር የመጣው የፅንፈኛው ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ተገለፀ።
ከሶስት ወራት በላይ ዝግጅት አድርጎ ከየአቅጣጫው ኃይል አሰባስቦ ጢስ አባይ ከተማንና አካባቢውን ለመቆጣጠር የመጣው የፅንፈኛው ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን በጎንደር ኮማንድ ፖስት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የክፍለጦር አዛዥ ተናግረዋል።
በባህርዳር -ጎንደር ኮማንድ ፖስት በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የአንድ ክፍለጦር ሬጅመንት የረጅም ጊዜ ዝግጅት አድርጎ ለማጥቃት የመጣውን የፅንፈኛው ኃይል ታጣቂን መደምሰሱን የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ዘሪሁን ተረፈ ተናግረዋል።
ፅንፈኛው ከዚህ በፊት በማሰልጠኛነት እንዲሁም የትጥቅና ስንቅ ማከማቻና የኢኮኖሚ ምንጩ አድርጎት በሠራዊታችን ጠንካራ ምት ተቀጥቅጦ በውርደት ከተባረረ በኋላ ቁጭትና እልሁን ለመወጣት ለበርካታ ወራት ሲዘጋጅና ኃይል ከመሸንቲ፣ ከፈረሰ ቤት፣ ከሞጣ፣ ከደቡብ ጎንደር፣ ከስማዳ፣ ከደጋዳሞት፣ ከእስቴ፣ ከዋጅራ፣ ከጋሸና፣ ከአዴት፣ ከሃንዳሳ፣ ያለ የሌለ ኃይሉንና ትጥቁን አሰባስቦ ጢስ አባይን ለመቆጣጠርና በሠራዊታችን ላይ ጥቃት ለማድረስ የወጠነው ሴራ ሳይሳካ የሚገባው ቅጣት ተሰጥቶታል ብለዋል።
በፅንፈኛው ኃይል ላይ የተወሰደው ይህ የማያዳግም እርምጃ በተጨባጭ በአንድ አካባቢ ከአንድመቶ ሃምሳ በላይ የሚሆነው የዘራፊው ቡድን ስብስብ የተገደለ ሲሆን በርካታ መሣሪያና ተተኳሽ ተማርኳል አስክሬኑንም በየቦታው ጥሎ ለመፈርጠጥ ተገዷል።
ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ኃይሉ የተደመሰሰበት ፅንፈኛው ቁስለኛውን እንኳን ማሸሽ ሳይችል የሃፍረት ካባውን ተከናንቧል ብለዋል።
ፅንፈኛው ኃይል ከተቀጠቀጠበት ጢስ አባይ ሃንዳሳ በመባል እስከሚታወቀው ስፍራ በሸሽት ላይ የነበሩ የዘራፊው ቡድን ቁስለኞች ህይወታቸውን ማትረፍ ሳይችሉ በየሜዳው ተንጠባጥበው መቅረታቸውን መመልከት ተችሏል ነው ያሉት የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ዘሪሁን ተረፈ።
የሬጅመንቷ አዛዥ መቶ አለቃ አዲሱ መድፉ በበኩላቸው የጠላትን ሴራ ቀድመን በመረዳት የመጣው ኃይል እንዳይመለስ አድርገን የሚገባውን ሰጥተንዋል ካሉ በኋላ በቀጣይ ትንኮሳ የሚያስብ የፅንፈኛው ኃይል ካለ ከዚህ ቅጣት ሊማር ይገባዋልም ብለዋል።
የሠራዊቱ የማድረግ አቅም፣ ሞራልና የስነልቦና ጥንካሬ ለተገኘው ድል የላቀ ሚና ነበረው ያሉት አዛዡ በቀጣይም ፅንፈኛው የሠላም አማራጭን እስካልተከተለ ድረስ የዚህ አይነቱ ዕጣ ፈንታ አይቀርለትም በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት በሁሉም የመሰረታዊ ድርጅት የፓርቲያችን መዋቅሮች የአባላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
በፓርቲያችን ህገ -ደንብ መሰረት የሚደረገው የአባላት ኮንፈረንስ ትልቁ የአባላት መድረክ ሲሆን ከመሰረታዊ ድርጅት ጀምሮ እስከ ከተማ " ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ ያለው!
ፓርቲያችን ብልፅግና ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ቃሉን ወደ ተግባር በመለወጥ የተግባር ፓርቲነቱን እያስመሰከረ ያለ ፓርቲ ነው!
በመድረኩ ሁሉንም አባላት በኮንፈረንስ በማሳተፍ በፓርቲያችን ስኬቶችና በጉድለቶቻችን ሚናቸው ምን እንደሚመስል በመምከር ለቀጣይ የጋራ ተልዕኮዎች ተጨማሪ አቅም የሚሰነቅበት መድረክ ይሆናል።
https://twitter.com/ProsperityKera
አዲስ አበባ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ምቹ እና ተወዳዳሪ እንድትሆን እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አዲስ የተሾሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ሁለት ሀገራት በአዲስ አበባ ኤምባሲያቸውን መክፈታቸውን ተናግረዋል።
ይህም በዓለማችን ካሉ የዲፕሎማሲ መቀመጫ ከተሞች መካከል አዲስ አበባ አንዷ ሆና የመቀጠሏን ጉዞ ያጠናክረ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት።
ቃል ቀባዩ በመግለጫቸው እንዳነሱት፤ ኬፕቨርድ እና አርሜኒያ በአዲስ አበባ ኤምባሲያቸውን መክፈታቸውን ተከትሎ በመዲናይቱ ኤምባሲያቸውን የከፈቱ ሀገራትን ቁጥር 134 ደርሷል።
ከእነዚህ ውስጥ ሀምሳ ሁለቱ የአፍሪካ ሀገራት መሆናቸው ተገልጿል።
በሳምንቱ የሲዊዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢግናሲዮ ካሲስ በኢትዮጵያ ስኬታማ ቆይታ አድርገው እንደነበርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ተናግረዋል።
ጉብኝቱ የሁለቱ ሀገራትን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያደርስ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።
ቃል አቀባዩ እንዳሉት፤ አሁን ላይ 14 የሚሆኑ የስዊዘርላንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መስኮች ተሰማርተው ይገኛል።
ሀገሪቱ አምስተኛዋ የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ መዳረሻ መሆኗን አንስተው፤ የሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጥ በ 2002 እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 94 ሚሊዮን ዶላር መድረሱንም አስታውሰዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከዳውሮ ዞን እና ኮንታ ዞን አመራሮች ጋር ተወያየ
ሱፐርቪዥን ቡድኑ በተመረጡ 17 የትኩረት መስኮች ላይ መሠረት በማድረግ በዳውሮ እና ኮንታ ዞን በ2016 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የተግባር አፈፃፀም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ታይተዋል።
በሪፖርቱ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ አፈፃፀም በመገምገም ጠንካራ አፈፃፀሙ ተጠናክረው እንዲህ ቀጥሉ እንዲሁም በጉድለት የተገመገሙ ነጥቦችን ተለይቶ በቀጣይ መስተካከል እንዳለበትም በውይይቱ ተጠቁሟል።
በውይይቱም በዳውሮ እና በኮንታ ላይም እንዲሁም አዋሳኝ ክልሎች፣ ዞኖች ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ ሥራን በማጠናከር የተለያዩ የንቅናቄ መድረኮችን በመፍጠር የተሰራው ሥራና በሁለቱም ዞኖች ሠላማዊ ግንኝነቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡
ከዚህ በመቀጠል የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድኑ በተለይም በነገው ዕለት በሚኖረው ቆይታ በዳውሮ ዞን ካሉት ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ ሁለት ወረዳዎች እና አንድ ከተማ አስተዳደር የመስክ ሱፐርቪዥን በማድረግ፣ ድጋፋዊ ክትትልና ግምገማ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
#Prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ ፍልሰተኞች የአፍጥር መርሃግብር አካሄዱ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ምሽት ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ ፍልሰተኞች የአፍጥር መርሃግብር ማካሄዳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል ።
https://twitter.com/ProsperityKera
ኢትዮጵያ በስደተኞች አያያዝ እና ጥበቃ በአርዓያነት የምትጠቀስ ሀገር ናት ሲሉ የአሜሪካ የስደተኞች እና የፍልሰት ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ድኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አምባሳደር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በትምህርት፣በስደተኞች፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በዓለም አቀፍ መድረክ በትብብር እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።
ስደተኞችን አስመልክቶም መንግስት በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች፤ ከ1 ሚሊዮን በላይ የውጭ ስደተኞችን በማስተናገድ የቤት፣የምግብ እና የመጠለያ አቅርቦት በሟሟላት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
የአሜሪካ የስደተኞች እና የፍልሰት ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞችን ተቀብላ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት የምታከናውነው ተግባር በአርአያነት የሚጠቀስ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ረዳት ሚኒስትሯ የአሜሪካ መንግስትም ይህን ስራ በመደገፍ በትብብር አብሮ እንደሚሰራ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
Imala badhaadhinaa jalqabneen Itoophiyaa sabdaneettii ni ijaarra.
**
Paartiin Badhaadhinaa imala hunda galeessa akka biyyaatti eegaleen Itoophiyaa sabdaneettii tokkummaa fi obbolummaan lammiilee itti mirkanaa'e ijaaruuf hojjataa jira.
https://twitter.com/ProsperityKera
አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ ለመጠቀም ሙከራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል።
እነዚህ አጭበርባሪዎች በአብዛኛው ከባንክ የደወሉ በማስመሰል “የተዘጋ ሒሳብችሁን እንክፈትላችሁ”፤ “ሒሳባችሁ እንዳይዘጋ የምንልክላቹሁን ኮድ አስገቡ” የሚል የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም የዘረፋ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸው ብሏል ባንኩ።
ነገር ግን ባንኩ ስልክ ደውሎ ስለ ሒሳብ መረጃ የሚጠይቅበት፣ ሒሳብ የሚከፍትበትም ሆነ የሚዘጋበት አሠራር እንዲሁም ደንበኞች እንዲጠቀሙበት የሚልከው ምንም ዓይነት ኮድ አለመኖሩን ደንበኞች እንዲረዱ አስገንዝቧል።
በመሆኑም ማንኛውም የባንኩ ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሔድ አሊያም በ951 የባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል ስለሁኔታው መረጃ መጠየቅ እንዳለበት አሳስቧል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የፖለቲካና ርዕዮተ-ዓለም ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመልክቷል።
መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ በመላ ሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የመስክ ምልከታና ድጋፋዊ ክትትል በፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እየተደረገ ይገኛል።
መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች ያሉ ሐብቶችና ጸጋዎችን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል፣ የሚነሱ ቅሬታዎችንም ከኀብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ ለመፍታት በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ሲሆን÷ የመስክ ምልከታና ድጋፋዊ ክትትል መርሐ-ግብሩም የዚህ ተግባር አንድ አካል ነው።
በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን የተመለከተው ቡድንም÷ በከተማው የተከናወኑ የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር፣ የመስኖና ሌሎች የልማት ሥራዎችን እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።
#Prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
የፌዴራል መንግሥት የሱፐርቪዥን ቡድን በሲዳማ ክልል እያካሄደ የሚገኘውን የክትትል እና ግምገማ ስራ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ኢንዲስትሪዎችን እና የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝቷል ።
በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የፌዴራል መንግሥት የልኡካን ቡድን በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች በመገኘት ድጋፋዊ ፣ ክትትል እና ግምገማ እያካሄዱ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የሀዋሳ ኢንዲስትሪ ፓርክ የሥራ እንቅስቃሴዎችን፣የሱፐር ኦቫ እንቁላል ፋብሪካ፣የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንቅስቃሴን ፣ በከተማው በመናኻሪያ ክፍለ ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው በኢንዱስትሪ ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው መመልከት መቻሉን እና ኢንዱስትሪውን የሚደግፍ የተማረ የሰው ሐይል ከማምረት አንፃር የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እያደረገ የሚገኘውን የስራ እንቅስቃሴ በመመልከት የድጋፍ ቡድኑ አባላት ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
#Prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
በባንኩ የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት አለመኖሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
ባንኩ ሰሞኑን አጋጥሞት የነበረውን የአገልግሎት መቋረጥ ችግር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በዚህም በባንኩ የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የለም ሲሉ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ይፋ አድርገዋል።
ባንኩ የውስጥ አሰራሩን ለማዘመን ሲያደርግ በነበረው እንቅስቃሴ አርብ መጋቢት 6 ለሊቱን በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ጤናማ ያልሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንደነበረ መጠቆማቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው እንደገለጹት የተፈጠረው ክስተት ከሳይበር ጥቃት ጋር የተያያዘ አይደለም።
አርብ ለሊት ብቻ ከ490 ሺህ በላይ የገንዘብ ልውውጥ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ይህ የገንዘብ ልውውጥ ጤናማ የሆነውንም እንደሚጨምር ተጠቁሟል።
ገንዘብ በተለያየ መንገድ ጤናማ ባልሆነ መልኩ ከባንኩ በማውጣት ላይ በዋናነት የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው ያሉት ፕሬዝዳንቱ አብዛኛው ተማሪዎች በባንኩ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ መሆኑ ገልፀዋል።
የባንኩን ጥሪ ተቀብለው ገንዘቡን ተመላሽ ላደረጉ ተማሪዎች ባንኩ ምንም አይነት ክስ እንደማይመሰርትም ማስታወቃቸውን በዘገባው ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተደጋጋሚ በሀገራት በሚደገፉ ትልልቅ ተቋማት ጭምር የሳይበር ጥቃቶች ሙከራዎች ቢያጋጥሙትም አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ያለው ተቋም በመሆኑ ሁሉንም ሲያከሽፍ እንደቆየ ነው ፕሬዝዳንቱ የገለፁት።
የደረሰው ጉዳት ከባንኩ አጠቃላይ ሀብት አንፃር በጣም አነስተኛ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ የደንበኞች የግል አካውንት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት ባለመኖሩ ደንበኞች ምንም አይነት ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ የባንኩ ፕሬዝዳንት መግለጻቸውም ተጠቁሟል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስና እና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች መሆናቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ፡፡
ድርጊቱን የፈፀሙት የኮሚሽኑ ሸራተኞችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው÷ በሰሞነኛና በአየር መንገዱ እንቅስቃሴ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም÷በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአየር መንገዱ በተጨማሪ፣ ኢሚግሬሽን፣ጉምሩክ፣ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ፌዴራል ፖሊስ የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው አስረድተዋል።
በቅርቡ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት መንገደኛ ላይ ተፈፅሟል የተባለውን ሙስናና እንግልት የፈፀሙት የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች እንጅ የአየር መንገዱ ሰራተኞች አይደሉም ነው ያሉት፡፡
በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ መሰል ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የደህንነት ካሜራዎች እንዳሉም ነው የገለፁት።
አሁን ላይ 145 አውሮፕላኖች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተው÷በቅርቡ የአዳዲስ አውሮፕላኖች ግዥ ትዕዛዝ መሰጠቱንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያሳየች ያለው የላቀ ውጤትና እመርታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥም ነው ያረጋገጡት፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ብልፅግና ፓርቲ ያልተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ተጠናቅቆ በሀገራችን የወል እውነቶች እንዲጸኑ አበክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
የተናጠቀቀ ሀገረ-መንግስት የወል እዉነት የጸናበት ነው፡፡ አብዛኛው የፖለቲካ ሊሂቃንና ህዝቡ ሀገረ-መንግሥቱን በሚመለከት ጠንካራ፣ ወጥ እና ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ መግባባትን መጎናጸፍ ከቻሉ የአንድ ሀገረ-መንግስት ግንባታ በጽኑ መሰረት ላይ ተጥሏል ማለት ነው፡፡ የዚህ ማረጋገጫም ዘላቂ አዎንታዊ ሰላም (Positive Peace) የተገነባበት፣ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ መግባባት (National Consensus) የተረጋገጠበት፣ ህግና ስርዓት (Law and Order) የሰፈነበት፣ የህዝብ ወሳኝነት የተረጋገጠበት (ህዝባዊ ጥያቄዎችና የስልጣን ሽግግር በህዝቡ ይሁንታ የሚወሰንበት)፣ የፖለቲካ ባህሉ ከጉልበት ወደ ሀሳብ ፉክክርና ሀሳብ ልዕልና (Hegemony of ideas) የተሸጋገረበት፣ መሰረታዊ የሆኑ የዴሞክራሲ ተቋማት (democratic institutions) ወጥነትና ቀጣይነት ባለዉ መልኩ የተገነቡበት ሲሆን ነው፡፡
ፓርቲያችን ብልፅግና በእንጥልጥል ያለው የሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ተጠናቅቆ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲረጋገጥ ሀገር በቀል እሳቤዎችን በመቀመር ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተለይም የሀገራችን የፖለቲካ ተቃርኖዎችን ከመሰረታቸው መፍታት የሚያስችል አካታች ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን ከዚህ አንጻር ጉልህ ሚና ስላለው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለውጤታማነቱ የየራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ፓርቲያችን ጥሪ ያቀርባል፡፡
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!
© Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና
https://twitter.com/ProsperityKera
አፍረካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን፣ የአፍሪካ ምርጥ ሴት መሪ ተሸላሚ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪