Irreecha Keenya, Haaromsa Aadaa Keenyaaf!
እሬቻ: ለባህላችን ህዳሴ!
Irreechaa for Our Cultural Renaissance!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች እስከ ጥምቅት 30/2017 ድረስ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ ቤቱን ለሌላ እድለኛ አስተላልፈዋለሁ" የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየገነባ ለቤት ተጠቃሚዎች በዕጣና በጨረታ የሚያስተላልፈው የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን " በሽያጭ ከተላለፉና ውል ከተፈጸመባቸው ቤቶች መካከል የቤት ባለቤቶች ወደ ቤታቸው ገብተው እየኖሩ አለመሆኑን አረጋግጫለሁ " ብሏል።
" በህጋዊ መንገድ ውል የተያዘባቸው ቤቶች ለህገወጥ ተግባር እየዋሉ ነው " ያለው ኮርፖሬሽኑ ፥ የቤት ባለቤቶች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በያዙት የሽያጭ ውል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ አስጠንቅቋል።
" በተያዘው ጊዜ ውስጥ ወደ ቤቱ የማይገባ የቤት ባለቤት የሽያጭ ውሉ በህግ አግባብ እንዲቋረጥ ተደርጎ ቤቱን ለሌላ ዕድለኛ እናስተላልፋለን " ሲልም አስጠንቅቋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሚኒ-ግሪድ ታሪፍ መቀመሪያና፣ የኦንላይን የፍቃድ ምዝገባ እና አጠቃቀም መተግበሪያ (ፖርታል) ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ።
መስከረም 20/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ (ISA) እና ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የሚኒ-ግሪድ ታሪፍ መቀመሪያ፣ የኦንላይን የፍቃድ ምዝገባና አጠቃቀም መተግበሪያ (ፖርታል) የማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሄደ።
መርሀግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ አማካሪ አቶ ጎሳዬ መንግስቴ ኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ (ISA) ለኢትዮጵያ መንግስት ከሌሎች የፕሮግራም ድጋፎች መካከል የሀይል አፕሊኬሽን ሲስተምን ዘላቂ፣ ተደራሽነትና አዋጭ የሆነ የፀሀይ ሀይል ስርዓቶችን ለመፍጠር የሚያስችል ፖሊሲዎችንና ደንቦችን ለማዘጋጀት ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።
አቶ ጎሳዬ አክለውም የሚኒ-ግሪድ ታሪፍ መቀመሪያና የኦንላይን ፖርታል ለሚኒ-ግሪድ ፍቃድ ማመልከቻ መግቢያው ዝግጁ ስለሆነ ከፍተኛ ባለሙያዎችን በማሳተፍና በውይይት በማዳበር የተዘጋጀውን የታሪፍ መቀመሪያና የመስመር ላይ አፕሊኬሽን ፖርታልን በማቅረብ የሚኒ-ግሪዶችን የፍቃድ አሰጣጥ ሂደትን ድጅታል ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።
ውጤታማና ፍትሃዊ የታሪፍ አወቃቀርን በመዘርጋት የታሪፍ አወጣጡ ደረጃውን የጠበቀ ማዕቀፍ ለማቅረብ እድል ይፈጥራል ያሉት አቶ ጎሳዬ መተግበሪያው በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ የኢስት አፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ በበኩላቸው የክፍያው ስርአት ተግባራዊ ሲሆን ህብረተሰቡን የተመጣጠነ የኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ፣ የግሉ ዘርፍ ሀይልን አምርቶ ለተጠቃሚው ለመሸጥ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር እና ተጠቃሚው የሚከፍለው ክፍያ የተጋነነ እንዳይሆን ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።
በመድረኩ የሚመለከታቸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተወካዮች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች የተሳተፉ ሲሆን በባለሙያዎች በቀረቡት ፅሁፎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ የተደረገው በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የመንግስታቱ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ከደቂቃዎች በፊት ከባድ ፍንዳታ ተከስቷል።
ፍንዳታው የተከሰተው በብሄራዊ ቲያትር አቅራቢያ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ ነው። ይህ ፍንዳታ የተፈፀመበት ቦታ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መቀመጫ በቅርብ እርቀት ላይ ነው።
እስካሁን የሟቾችን እና የቆሰሉ ሰዎችን ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።
🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴
የኮሪደር ልማት ግንባታ ያካተታቸው የመሰረተ ልማቶች፦
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ያቀፋቸዉ መሰረተ ልማቶች
- በዚህ ኘሮጀክት ላይ ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ የመንገድ ልማት
-4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ መንገዶች፣
-96 ኪ.ሜ ሰፋፊ የእግረኛና 100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገዶች፣
-5 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ
-48 የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጡ የአውቶቡስ እና የታክሲ ተርሚናሎችንና መጫኛ ማውረጃ ስፍራዎች፣ በጥቅሉ ከ 240 ኪ.ሜ በላይ የሚሆን የመንገድ እና ተያያዥ መሰረተ ልማት፤
-70 የከተማን ውበት የሚጨምሩ የህዝብ መናፈሻ ስፍራዎች፣ ፋውንቴኖችና የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ የመዝናኛና የመናፈሻ ስፍራዎች፣ የልጆች መጫዎቻና የህዝብ ፕላዛዎች፣
-120 የሚሆኑ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የፍሳሽ ማስተላለፊያዎች፣ ከተማችንን የሚመጥኑ የደህንነት ካሜራዎች፣ የብልህ ትራንስፖርት ስርዓት ( intelligent transport system) በመሬት ውስጥ የመዘርጋት ስራ ፣
-ከ400 በላይ ህንጻዎች እንዲታደሱ የማድረግ እንዲሁም የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑ የቀለምና የመብራት ስራዎች እና ሌሎች በርካታ ግንባታዎችን በመከናወን ላይ ይገኛሉ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢቢሲ በጅማ ከተማ አዲስ ያስገነባውን ስቱዲዮ አስመረቀ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን "ኢቢሲ ወደ ይዘት" በሚል እያካሄደው ያለው ሪፎርም አካል የሆነው ተጨማሪ የይዘት ምንጭ የኢቢሲ አዲሱ የጅማ ስቱዲዮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢቢሲ ቦርድ እና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ የመስቀል ደመራ በዓል አስመልከተው ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
********
"ለመላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች፤ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
የመስቀል በዓል አገራችን ኢትዮጵያ በብዝሃ-ብህል እና ልዩ ልዩ በዓላት እጅግ የከበረች እና የበለፀገች መሆኗን የምናሳይበት ሕያው ምስክር የሆነ እና በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገበ፤ የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ የምናሳይበት የሁላችንም የጋራ በዓላችን ነው።
የመስቀል ደመራ በዓልን ስናከብር በዓሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን እና ባሕላዊ ትውፊቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም እንዲከበር ሁላችንም የድርሻችን እንድንወጣ እያሳሰብኩ በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እንዲሁም ወንድማማችነትና እህትማማችነት መተባበራችን የምናሳይበት የአንድነት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ!!"
አቶ ሙስጥፋ ትኩ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!
ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ደሙን አፍስሶ፣ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ፍቅሩን ገልጿል። ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለበት መስቀል ምሳሌነት በዚህች ምድር ስንኖር እርሰበርሳችን ያለ ምንም ልዩነት በፍቅር፣ በምህረት እና በመተሳሰብ እንድንኖር ነው።
መላው የከተማችን ነዋሪዎች የከተማችን ሌላኛው ድምቀት የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል እንደ ምሳሌነቱ የሰው ልጆችን ሁሉ በመዉድ፣ እርሰበርስ በመተባበር፣ በመከባበርና በፍቅር የዓሉን እሴቶች በመጠበቅ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በዓሉ ፍቅር፣ የደስታ እና አብሮነት የሚጎላበት የተዋበ በዓል ይሁንልን።
በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን፤ አደራሰችሁ!
መልካም በዓል!
ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለጂ ፓወር ኮንሰርት አስቴር አወቀ እና ጎሳዬ ተስፋዬ ዱባይ ገቡ
ጂፓወር በዱባይ ያዘጋጀው የመስቀል በዓል ኮንሰርት ለመታደም አንጋፋ ሙዚቀኞች በቦታው መድረሳቸው ተነገሯል ።
ጂ ፓወር በባንድ ደረጃ ከመሃሪ ብራዘርስ ጋር እየሰራ ያለ ሲሆን ጎሳዬ ተስፋዬ ከባለቤቱ ጋር ዱባይ ላይ ሲደርስ ለየት ያለ አቀባበል የተደረገለት መሆኑን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
በኮንሰርቱ ላይ ለበዓል ወደ ሀገራቸው መግባት ላልቻሉ ኢትዮጵያውያን ታሳቢ ያደረገ ኮንሰር መሆኑን እና በርካታ ሰዎች እንደሚታደሙም ተጠቁሟል።
አስቴር አወቀ ተሸፋፍና ዱባይ የገባች ሲሆን የተለየ አቀባበል ባይደረግላትም ከሙዚቀኞቹ ጋር ልምምድ እያደረገች እንደሆነ ተነግሯል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በተመድ የመሪዎች ጉባኤል ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የቀረቡትን ሰዎች ፎቶ ተመልከቱ፤ ፎቶው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ የደረሰበትን ደረጃ አጉልቶ ያሳያል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ክቡር ጄነራሉን ምን እንጠይቅልዎ?
ትዊተር ስፔስ (X ስፔስ) ላይ ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ጋር ቆይታ እናደርጋለን። ጥያቄ እና አስተያየት ካልዎት Inbox ይላኩ 👇 👇 👇
@KiyaEthiopia
👆👆👆👆👆👆
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሁሌም ሀገርን የሚያሥጠራው ፈርጣችን የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ሆኖ ለ 3ተኛ ጊዜ ተመረጠ! ይህ የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅር ግንባት ስኬት ማሳያ ነው!
#ዐብይ_አህመድ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢትዮቴሌኮም ከነገ ጀምሮ የታሪፍ ማሻሻያውን (ጭማሪ) ተግባራዊ አደርጋለሁ አለ
መንግስታዊው የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት ኢትዮቴሌኮም ከነገ መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የዋጋ ማሻሻያ አደርጋለሁ ብሏል።
ተቋሙ የሚደረገው የዋጋ ማሻሻያ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል እንደማይነካ የገለፀ ሲሆን ተመጣጣኝ እና የዲጅታል አካታችነትን መርህን በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ሲል ገልጿል።
ተቋሙ የሚደረገዉ ማሻሻያዉ 22 ፓኬጆችን የማይነካ እንደሆነ ቢገልፅም በምን ያህል ፐርሰንት የሚለዉን እና በየትኞቹ አገልግሎቶቹ ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ አላሳወቀም።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
እስራኤል በሊባኖስ ባደረሰችው ጥቃት 33 ሰዎች ሲሞቱ 1መቶ95 የሚሆኑ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል‼️
ቅዳሜ ዕለት እስራኤል በሊባኖስ ባደረሰችው የአየር ጥቃት 33 ሰዎች መሞታቸውን እና 1መቶ95 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በደቡባዊ ቤሩት እና አከባቢው ላይ ጥቃታቸውን መቀጠላቸው ነው የተገለጸው።
በእስራኤል እና በሊባኖሱ ሄዝቦላህ መካከል ከጥቅምት 7 የጀመረው እና አሁን ላይ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ 1ሺህ6መቶ40 ሰዎች ሲገደሉ፤ ከ8ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እስራኤል ከሰሞኑ ባደረሰችው ከባድ የአየር ጥቃት የሄዝቦላውን መሪ ሀሰን ናስረላህን መግደሏ የሚታወቅ ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ነው!!
የመደመር ትውልድ ጥላቻን በፍቅር፣ ቂምን በይቅርታ፣ ግጭትን በውይይት የሚተካ ትውልድ ነው።
የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ፤ ጽንፈኝነትን የሚጸየፍ ትውልድ ነው።
የመተማመን ክበቡ በብሄርና በመንደር ሳይታጠር ኢትዮጵያዊነትን በአርበኝነት መንፈስ የሚያፀና ነው።
በመሆኑም ከራስ ወዳድነት የፀዳ፣ ለሌሎች የሚራራ፣ ሀላፊነት የሚሸከም ፣ እውነተኛና የሌላው ህመም የሚያመው ትውልድ መቅረጽ የጋራ ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።
በመደመር ትውልድ ተሰናስለን ተከባብረንና ተባብረን ለጋራ ግብ በማበር ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ ቤት
#aa_prosperity
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አብሮነት፣ አዲስ ሃሳብ አዲስ ተስፋ ፣ መከባበር ፣ በጋራ መቆም በወርሃ መስከረም!
የመስከረም ወር አዲስ ብስራት ፣ የአዲስ ተስፋ፣ የእንደገና መጀመር እና ለመኖር፣ ለማደግ፣ ለመበልፀግ ማሳያ የሆነ የእድል ወር ነው። በዚህ ወርም በሃገራችን የአብሮነታችን ማሳያ፣ የህብረ- ብሔራዊነታችን መሰናሰል ምሳሌ ፣ የመተሳሰሪያችን ገመድ፣ በጋራ የመቆማችን ጥንካሬ የሆኑ በዓላት እናገኛለን።
እነዚህ በዓላት ኢትዮጵያዊነታችን የሚያጐሉ እሴቶች በሰፊዉ የምናይበት በሁሉም ዘንድ አብሮነት፣ መተሳሰብ እና መከባበር በግልፅ የሚታዩበት ወቅት ነው። በሃገራችን የተነፋፈቁ ቤተሰቦች እንደገና የሚገናኙበት፣ የቆዩ አለመግባባቶች እና ቁርሾዎች ይቅር በማለት ወደ ጎን የሚቀሩበት እና አዲስ ተስፋ ፣ መከባበር ፣ በጋራ መኖር በልባችን ውስጥ የሚወለድበት ጊዜ ማሳያ ናቸው።
በዓላት ብዝሃነታችንን እና የሚያስተሳስረንን ማሳሪያ ፀጋ ነው፣ በተለያዩ እምነቶችም አንዱን ለአንዱ በአብሮነት በማሳለፍ ወንድማማችነት እና በእህትማማችነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን የሚያሳየ እያሳየን የሚቀጥል ነው።
እንደ ፓርቲም አብሮነትን እና አንድነትን ለማጠናከር እየተሰሩ የሚገኙ ተግባሮቻችን ለእሴቶቻችን ማጠናከሪያ ናቸው።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ ቤት
#aa_prosperity
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👉 የአደባባይ በዓላት በደመቀ ሁኔታ መከበራቸው ለጋራ የገዥ ትርክት ግንባታችን መሠረት ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 🌻🙏🌻
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"እንኳን ለብርሃነ-መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!!"
ወ/ሮ አይዳ አወል:- የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
****
ከሁሉ አስቀድሜ ለመላው የክፍለ ከተማችንና ከተማችን ነዋሪዎች እነዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረስን ማለት እወዳለሁ!!!!
የመስቀል ደመራ በዓል በየዓመቱ በደመቀ ሁኔታ የሚከበር፤ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እውቅና ተሰጥቶት ዓለም አቀፋዊ ቅርስ ተብሎ የተመዘገበ ነው፡፡
በዓሉ በአገራችን ብሎም በመዲናችን ነዋሪዎች ዘንድ በታላቅ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ-ስርዓት የሚከበር ትልቅ ማህበራዊ እሴት ያለው ባህል ነው።
ለከተማችን ልዩ ድምቀት የሚሰጠውን እና በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የመስቀል ደመራ በዓል ኢትዮጵየዊ ጨዋነት እና በመተሳሰብ ስናከብር ቆይተናል፤ ይህንንም የአብሮነት እሴቶቻችንን በማጠናከር ማስቀጠል ይኖርብናል፡፡
ወቅቱ እኛ ኢትዮጵያዊያን የበለጠ መተባበርና አንድነታችን በማጠናከር እና አካባቢያችንን በንቃት በመጠበቅ ሰላማችንን ማስጠበቅ ይኖርብናል።
ውድ የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች፤ ከሰላም ሰራዊታችን እና ከፀጥታ ሃይሎች ጎን ሆነን ሰላማችንን ከመጠበቅ ባሻገር የሃገራችንን አንድነት የሚያጠናክሩ እሴቶቻችንን በማጉላት ወንድማማችነትን እህትማማችነትን ማጠናከር ይገባል። በዓሉን ስናከብር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውን ወገኖቻችን ካለን በማካፈን እብሮነታችንን ማሳየት ይኖርብናል።
በድጋሚ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!
ወ/ሮ አይዳ አወል
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
መስከረም 16-2017 ዓ.ም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለ2017 ዓመት የመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ
የመስቀል በዓል የሕልም ጉልበት የታየበት በዓል ነው፡፡
ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ለማውጣት ያለመችው ምንም አመቺ ነገር ባልነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ዙሪያዋ ጨለማ ነበር፡፡ መንገዶች ሁሉ ዝግ ነበሩ፡፡ ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ማንም በማያስበው ጊዜ፤ አይቻልም አይሞከርም በሚባልበት ወቅት፤ አንድ ቀን፤ ፈጣሪዋ ሲፈቅድ፤ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት ሕልም ነበራት፡፡
ሕልሟ እንዲሳካ ሠራች፤ ታገለች፡፡ ጨለማውን እየገፈፈች፤ አስቸጋሪውን ጎዳና እየጠረገች፤ ከውስብስብ ችግሮች ጋር እየተጋፈጠች ወደ ፊት ተጓዘች፡፡ በመጨረሻም ኢየሩሳሌም ተሻግራ፣ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት በቃች፡፡ ሕልሟ እውን ሆነ፡፡ ታሪክን ቀየረች፡፡ ልዕልናን ዐወጀች፡፡ ደመራ ለሚታገል፤ ተስፋ ለማይቆርጥና እስከ መጨረሻው ለሚጸና ሰው ሕልሙ አንድ ቀን እውን እንደሚሆን የሚያሳይ ትእምርት ነው፡፡
እዮሃ፤ ማለት “ይሄዋ” ማለት ነው ይባላል፡፡
ይሄው ተገኘ፤ ይሄው ተሳካ፤ ይሄው እውን ሆነ ማለት ነው፡፡ ከበረቱ፤ ከታገሉና ከጸኑ የማይሳካ ምን ነገር አለ? ሕልሙን ለሚያውቅ፤ ሕልሙ እንዲሳካ በነገሮች ተስፋ ሳይቆርጥ ለሚለፋ፤ እንደ ንግሥት እሌኒ ሕልሙ እውን ሆኖ አንድ ቀን ማየቱ አይቀርም፡፡ የሕልሙን ደመራ መደመሩ አይቀርም፡፡ “እዮሃ”፤ “ይሄዋ!” ማለቱ አይቀርም፡፡
መስቀል ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በሁለት መንገድ የሚያሳይ በዓል ነው፡፡ ደመራው ከእንጨት ወደ ችቦ፤ ከችቦ ወደ ደመራ የሚያድግበት መንገድ መደመር ምን ያህል ኃይልና ጉልበት እንዳለው ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መስቀል በተለያየ መንገድ፣ በተለያየ ባህልና አከባበር በብዙ ብሔረሰቦች ይከበራል፡፡ ይሄ ደግሞ በኅብረ ብሔራዊነታችን ውስጥ ያለውን ነባር ትሥሥር፣ የወል ትርክትና አንድነት የሚሳይ ነው፡፡
እንዲህ ዓይነት በዓላት ሃይማኖታውያን ብቻ አይደሉም፡፡ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫዎች ጭምር ናቸው፡፡ በመደመር ውስጥ ያለውን ጥንካሬና ጉልበት የሚሳዩ ትውልድ ለእኛ ትምህርት ያቆማቸው ምልክቶች ናቸው፡፡
ደመራውን በደመርን ጊዜ፤ ደመራውን በለኮስን ጊዜ፤ እንደየባህላችን የመስቀልን በዓል ለማክበር በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ በተሰባሰብን ጊዜ ኢትዮጵያን እናስባት፡፡
የሁላችንም ዕሴቶች፣ ባህሎች፣ ወጎች፣ ዐቅሞች፣ ጸጋዎች፣ ሀብቶች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች፣ ወዘተ. ተደምረው ኢትዮጵያን ታላቅ፣ የበለጸገችና የተከበረች ሊያደርጓት እንደሚችሉ እናስብ፡፡ ኢትዮጵያ የእነዚህ ሁሉ ድምር መሆኗን እናስብ፡፡ ከድምሩም በላይ መሆኗንም እናስብ፡፡ ደመራውን እያሳየን ለልጆቻችን ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ትርጉሙ በተጨማሪ “እኛ ኢትዮጵያውያን ከተደመርን እንደ ደመራው ብርቱ እንሆናለን፤ እንደደመራው ከፍ ብለን እናበራለን” በሏቸው፡፡
መልካም የመስቀል በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2017 ዓ.ም
ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የመስቀል ደመራ በዓል ከሐይማኖታዊ ክብረ በዓልነቱ ባሻገር የኢትዮጵያውያን የፍቅር፣ የወንድማማችነትና እህተማማችነት እሴት መገለጫና የጋራ ሀብታችን ነው።
የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ለበርካታ ዘመናት ሲከበር የቆየና በማይዳሰሱ የዓለም ቅርስነት ዘርፍ የተመዘገበ ድንቅ በዓላችን ነው።
ከዚህ አንፃር የመስቀል ደመራ በዓል ኃይማኖታዊ ስርዓት መሰረት በማድረግ ከሚያከብሩት ወገኖች በዘለለ ከመላው የሀገራችን ሕዝብ ጀምሮ የአለም ሕዝቦች ቅርስና ንብረት ሆኗል። ይህ ደማቅ በዓላችን በዓለም ቅርስነት ሲመዘገብልን ኃይማኖታዊ የበዓል አከባበሩ እንዳለ ሆኖ በአደባባይ የሚከበር እጅግ ድንቅ፤ ሰላማዊ፣ ወንድማማችነትና እህተማማችነትን የሚያጠናክርና የአለምን ቀልብ መሳብ በመቻሉ ነው።
እኛ ኢትዮጵያውያን የመስቀል ደመራ በዓልን በታላቅ ወንድማማችነትንና እህትማማችነት ፍቅር ስናከብረው ኖረናል። ይህንን በዓል አብሮ በጋራ የማክበር እሴታችን ደግሞ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህተማማችነት ወደ ጋራ ብልፅግና ያመራናል ብሎ በሚያምነው የለውጡ መንግስት ደግሞ ይበልጥ እንዲጠናከርና እንዲጎመራ ተደርጓል።
እኛ ኢትዮጵያውያን አንድነታችን የጥንካሬያችን መሰረት፣ መተሳሰባችን ያቆራኘን ኢትዮጵያዊ ማሰሪያችን፣ መከባበራችን የአብሮ መኖራችን ሚስጥርና መለያችን ሆኖ ዘመናትን ተሻግረናል ፤ ትውልዱም ይህንን ድንቅ ጥበብና ሚስጥር ይዞ እንዲቀጥልም ፓርቲያችን እየሰራ ይገኛል።
የጋራችን የሆነውን በዓል በሰላም ሲከበር ኢትዮጵያውያውያንን በዓለም አደባባይ በማንገስ አንድነታችንን ያጠናክራልና በልዩ ትኩረት ልናከብረው ይገባል ምክንያቱም አንዳችን ያለአንዳችን ድምቀት የለንም።
የመስቀል ደመራ በዓል ከሀይማኖትነቱ ባሻገር የኢትዮጵያውያን መገለጫና የዓለም ህዝቦችን ያስደመመ የጋራ ሀብታችን በመሆኑ ይህንን ድንቅ በዓል በጋራ ማክበር ደግሞ ትልቅ እንድምታ ይኖረዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ ቤት
#aa_prosperity
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ብልጽግና የአደባባይ በዓላት ለሀገር ገፅታ ያላቸውን ጉልህ ሚና በመረዳት ባማረና በደመቀ ድባብ በሰላም ይከበሩ ዘንድ በትብብር ይሰራል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሁሌም ሀገርን የሚያሥጠራው ፈርጣችን የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮን ሆኖ ለ 3ተኛ ጊዜ ተመረጠ! ይህ የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅር ግንባት ስኬት ማሳያ ነው!
#ዐብይ_አህመድ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Irreechi Ibsituu Aadaafi Hawwii Gaariiti!
Uummanni Oromoo saba guddaa Gaanfa Afrikaa seenaa boonsaa qabu, uummata safuufi duudhaa mataa isaa kan Addunyaa hawwatuufi simboo miidhaginaa ta'een bulaa turedha. Oromoon saba falaasama gabbataa qabuufi qaroomina gurguddoo heddu Addunyaaf gumaachaa har'a ga'eefi har'aas itti jirudha.
Uummatichi hacuuccaafi dhiibbaa sirnoota dhufaa darbaan hundaa danda'ew jiruufi jireenya isaa gaggeessuuf, hariiroo uumaafi uumamaa murteessuuf, madaallii uumamaa eeguuf, hariiroo ilmaan namaa gidduu jiru qajeelchuufi madaallii uumamaa eeguuf sirnootaafi jaarmayoota garagaraa tolchee ittiin wal qajeelchuun safuu, aadaafi duudhaa isaa gabbisuun Addunyaaf fakkeenya guddaa ta'eera.
Sirnoota Oromoon kalaqee ittiin jiraachuufi wal gaggeessaa ture keessaa inni tokkoofi beekamaan Sirna Gadaa Oromoo yoo ta'u, Sirni Gadaa Oromoo sirna guddaa dhimmoonni bulchiinsaa, siyaasaa, hawaasummaa, diinagdeefi hariiroon Waaqaafi namaa ittiin qajeelfaman sirna baay'ee ulfoofi kabajamaadha.
Oromoon sirna ajaa’ibsiisaa kana kalaqee ittiin wal bulchuu kan eegale waggoota kumaatamaan dura yoo ta’u, yeroo Oromoon sirna kana kalaqee ittiin wal bulchaa turetti Addunyaan dukkana waraanaafi wal balleessuu kan jibbaan guute keessa turte. Oromoon garuu hariiroo bulchiinsa sirna Gadaa tolchuun nageenya, obbolummaa, birmadummaa, walqixxummaafi kabaja ilma namaa mirkaneessee wal jiraachisaa, waliinis jiraachaa tureera.
Uummatichi sirna miidhagaa kana bocee dhimmoota hawaasummaa, siyaasaa, diinagdeefi uumaafi uumamaa qajeelchuuf aadaaf wal jaalachuu, wal kabajuu, waliin jiraachuu, walooma jabeessuu, ofirra darbee saboota biraa haammachuu dagaagsuun dimokiraasii har'a Addanyaan ittiin wal bulchu kanaaf bu'uura jabaa ta'eera.
Safuufi duudhaaleen Oromoon ittiin jiraataafi wal jiraachisaa ture, akkasumas hariiroo namaafi uumaa gidduu ittiin hubachaa ture Sirna Gadaa keessaa kan madde yoo ta'u, Jaarmayaaleen Oromoon hariiroo ollaa isaa, namaafi uumamaa, dacheefi samii, ittiin qajeelchaa ture heddu keessaa tokko Irreecha.
Irreechi jaarmayaalee Sirna Gadaa keessaa tokkoofi isa guddaa ta’ee Ayyaana Oromoon waggoota dheeraadhaaf kabajaa tureedha. Irreechi Oromoo sirna Oromoon Waaqa itti galateeffatu, ayyaana araaraafi obbolummaa akkasumas falaasama galateeffannaa Oromoon addunyaa kana keessatti ittiin humna Waaqaa ibsu, jireenya lafa kanaa raajuufi dhoksa jiruufi jireenyaa dhaloota itti aanuuf ittiin ibsudha.
Kanaafuu, Irreecha ibsituu aadaafi hawwii gaarii keenya ta'e kana guyyaa yaaddoo nageenyaa osoo hin taane guyyaa araaraa, nagaa, tokkummaan Oromoofi sabaafi sablammootaa itti calaqqisu, akkasumas malkaan Irreechaa iddoo wal dorgommiifi ajandaan siyaasaa itti gaggeeffamu osoo hin taane dachee safuufi nagayaafi guyyaa guddinniifi miidhaginni Oromoo addunyaatti ittiin mul’atu waan ta’eef qaamni kamuu kabaja guyyaa ayyaanaa kana ofiifis miidhagee ayyaanicha miidhaksuun barbaachisaadha.
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹