በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ፤
እንኳን ለ2ዐ17 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
በሰላም ያደረሰን ፈጣሪ አምላክ የተባረከና የተመሰገነ ይሁን።
መልካም አዲስ አመት !
አዲሱን አመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የስኬት ያድርግልን፡፡
ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር የተጋረጡብንን በርካታ ፈተናዎች በድል የተሻገርንበት፣ ስኬታማ ስራዎችን በመስራት ውጤቶችን ያስመዘገብንብት፤ እና የሕዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ያደርግናቸው ጥረቶች ፍሬ ማፍራት የጀመሩበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው፡ መዲናችን አዲስ አበባም በፍቅር የደመቀች እና በህብረ-ብሔራዊነት ያጌጠች ከተማ መሆኗን በተግባር እያሳየች የአብሮነት፣ የመተባበርና የመከባበር እሴትን አጠናክራ ያሳየችበት አመት ነው፡፡
ባለፈ ያሳለፍነው አመት አብሮነታችንን በማጠናከርና የበጎ ተግባር ስራዎቻችንን በማስፋት፡ የበርካታ የከተማችንን አቅመ ደካማ የሀገር ባለውለታዎች እና ለችግር የተጋለጡ ወገኖችቻንን እንባ ያበስንብት፣ የትኩረትና ክብር ተነፍጓቸው የኖሩ ወገኖቻችንን ዝቅ ብለን በማገልገል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ያጎላንበት አመትም ነው፡፡
ልማታችን ማንንም ወደኋላ የተወ አይደለም፡፡
በመሆኑም ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው የተሻሉ ውጤቶችን በመዘከር በቀጣይ ትልሞቻችን ላይ የሰላምና የልማት ሀይሎችን በማስተባበር በርካታ ሀገር አሻጋሪ ተግባራትን ለማከናወን ተዘጋጅተናል፡፡
በአዲሱ አመት እስከ አሁን በሰራነው ሳንረካ ይልቁንም የዛሬውን ትውልድ ከነገው ትውልድ ጋር በማስተሳሰር የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በብዙ ጥረት፣ በብዙ ትጋትና እና በማያቋርጥ ልፋት እጅ ለእጅ ተያይዘን በመስራት ሕዝባችንን ዝቅ ብለን እናገለግላለን፡፡
አዲሱ ዓመት በአንድነት የምንነሳበት፤ ከማይረቡን አጀንዳዎች ርቀን፡ እጆቻችንን ለስራ በማትጋት የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በማረጋገት ሰላማችንን ምናፀናበት ከውጭና ከውስጥ የሚተናኰሉንን ሀይሎች በመመከት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አስጠብቀን የምንቀጥልበት እንደዚሁም የነዋሪዎቻችንን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ተግተን የምንሰራበት ፍሬያማ ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ፡፡
አመሰግናለሁ
መልካም አዲስ ዓመት!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሶማሊያ የሳውዝ ዌስት ግዛት ፕሬዝዳንት ላፍታ ጋሪን የግብፅ ወታደራዊ ኃይል በሶማሊያ መሰማራቱን በይፋ ተቃወሙ።
ፕሬዝዳንቱ በትናንትናው ዕለት ባደረጉት ንግግር፤ “መቀመጫውን በሞቃዲሾ ያደረገው መንግስት፤ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው ቀጠናዊ ፉክክር ውስጥ ሀገሪቱን አስገብተዋል” ሲሉ ተችተዋል።
አክለውም የሚያስተዳድሩት የሶማሊያ ሳውዝ ዌስት ግዛት የግብፅ ወታደሮች መኖርን እንደማይቀበል አስረግጠዋል።
ከሳምንት በፊት፤ የሶማሊያ መንግስት የግብጽ ጦር በአገሪቱ መስፈሩን የተቃወሙ የፕሬዝዳንቱ ልዩ ልዑክ እና የምክር ቤት አባል አብዲረሺድ ሞሃመድ ኑር ጂሌይ ከሃላፊነት ማንሳቱ ይታወሳል።
በተጨማሪም ቪላ ሶማሊያ የወታደሮችን መስፈር የተቃወሙ የሳውዝ ዌስትን በፌዴራል ፓርላማ የሚወክሉ 25 የፓርላማ አባላት ላይ ያለመከሰስ መብታቸውን እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወቃል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ተስፋ ቆርጠው የነበሩ ተስፋቸው ሲለመልም፤ ኑሯቸው ሲዘምን ማየት ደስ ያሰኛል" - ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ከንቲባ አዳነች አቤቤ 837 መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታ ነዋሪዎች አስተላለፉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ 837 መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታ ነዋሪዎች አስተላለፉ።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው ለነዋሪዎች ከተላለፉ ቤቶች ውስጥ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በየካ ክፍለ ከተማ 54 ቤቶችን የገነባ ሲሆን ለዚህም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚልን አመሰግናለሁ ብለዋል።
እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ በተለያዩ ባለሀብቶች 108 ቤቶች፣ በአራዳ ክፍለከተማ በአብዱለጢፍ ዑመር ፋውንዴሽን (አሚባራ ግሩፕ) 32 ቤቶች ተገንብተዋል፤ ሁሉንም ቤቶች ለነዋሪዎች አስተላልፈናል ነው ያሉት።
ነዋሪዎች አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ እንዲጀምሩ ትልቅ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማት እና የከተማዋ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቹ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"በሰላም እና ፀጥታው ዘርፍ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የሕዝብ ደኅንነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት ሥራዎችን ከማስቀጠል አኳያ መሠረት የሚጥል ነው" - ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ዐውደ ርዕይ ድንገቴ ጉብኝት:: በሀገር ውስጥ የሚመረቱትን እና ለሽያጭ የሚቀርቡትን ዕቃዎች የሚያሳይ ተስፋ ሰጪ ሥራ።
Sudden oversight of the Ministry of Trade and Regional Integration’s exhibition. A promising curation featuring our locally produced goods for sale.
Via - AbiyAhmedAli 👏👏👏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🌴🌴🌴 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
CONGRATULATIONS 🎉🎉🎉 Bro 👌👌👌
የቀድሞ የአራዳ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዳይሬክተር የነበሩ አቶ ፋንታሁን ለማንቾ በብልጽግና ፓርቲ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በመሆን ተሹሟል።
መልካም የስራ ጊዜ ዘመን ወንድምአለም።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት የስኬት ደረጃ ከድኅነት ወደ ብልፅግና የመሻገር ተምሳሌት ነው -ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት የስኬት ደረጃ ከድኅነት ወደ ብልፅግና የመሻገር ተምሳሌት መሆኑን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።
የዘንድሮው ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ.ም የመሻገር ቀን በሚል ሥያሜ "የመሻገር ጥሪቶች የአዲስ ብርሃን ወረቶች" በሚል መሪ ኃሳብ እየተከበረ ይገኛል።
ስያሜውም የለውጡ መንግሥት የሀገር እድገትና አብሮነት መሰረት የሆኑት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ ግብርና፣ ቱሪዝምና አምራች ኢንዱስትሪዎች ከነበሩበት ማነቆ ወጥተው ኢኮኖሚውን በእጅጉ ማንቀሳቀስ በመጀመራቸው የተሰጠ ነው ተብሏል።
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ኢትዮጵያዊያን የዘመናት ቁጭት መልስ ያገኙበት እንደነበር ገልጸው በግድቡ ግንባታ ሂደት ያጋጠመው የፕሮጀክት አመራር ቀውስ ግድቡ አደጋ ተጋርጦበት እንደነበር አስታውሰዋል።
ግድቡ አሁን ላይ የመገባደጃ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያን ከድኅነት ወደ ብልፅግና፣ ከጨለማ ወደ ብርሀን የተሸጋገሩበት ሜጋ ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጸዋል።
የሕዳሴው ግድብ ከኃይል ልማት ባሻገር ለቱሪዝም ኢንቨስትመንት ምቹ ከባቢ በመፍጠር ወደ ዘርፈ ብዙ ስኬት የሚያሻግር መሆኑንም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹👌👌👌👌👌🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ይህ እውነተኛ ፈገግታ የዳማከሴን @noha_wi ጨጓራ እንዴት እንደሚያስነሳው ሳስበውና... የኢትዮጵያ ብልፅግና ከአንቺ የተላላኪነት ሂሳብና ክፍያ በብዙ መላቁን / መብለጡን ስትረጂ፣ ያኔ ነው ለአንቺ የማዝነው። ምክንያቱም በብዙ ራስሽን ትወቅሺያለሽና"
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል እና ላካሄድነው ጠቃሚ ውይይት አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያ የቻይናን ያልተቋረጠ ዘርፈብዙ ድጋፍ በእጅጉ ታደንቃለች። እንደ ሀገር የተለያዩ ተግዳሮቶችን ብናስተናግድም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንደስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ዘርፎች ትርጉም ያላቸው የለውጥ ርምጃዎች ተራምደናል።
በዚህ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። በቱሪዝም ብሎም በወረቀት እና እንደ ፐልፕ ያሉ ተያያዥ ግብዓቶች ኢንደስትሪንም ለማሳደግ እምቅ አቅም አለ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በጽናት እንሰራለን።
Thank you, President Xi Jinping, for the warm welcome and our valuable discussions today. Ethiopia greatly appreciates China's continued and multifaceted support. Despite facing various challenges, we are making significant strides in agriculture, manufacturing, industry, tourism, telecommunications, and other sectors.
Chinese investments have played a key role in this progress, and there is substantial potential for growth in areas like tourism and the paper and pulp industry. We are deeply committed to further strengthening our partnership.
ረፍት የለሿ ከተማችን አዲስ አበባ ዛሬም በእለተ እሁድ እንዲህ ስትገነባ፣ ስታብብ፣ ስሟን ስትመስል ውላለች 👏👏👏
@AbiyAhmedAli 👏👏👏
@AdanechAbiebie 👏👏👏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🌴🌴🌴 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
እንኳን ለ2017 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !
መጪው ዓመት ተባብረን ራዕያችንን እውን የምናደርግበት፣ እቅዳችንን የምንፈጽምበት ይሁንልን!
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዩጋንዳዊቷን አትሌት ያቃጠለው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ !
ዩጋንዳዊቷ አትሌት ርብቃ ቼፕቴጌ ኬንያ በሚገኘው በመኖርያ ቤቷ ውስጥ በእሳት ተቃጥላ ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው የቀድሞ ፍቅረኛዋ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።
ግለሰቡ አትሌቷን በሚያቃጥልበት ወቅት እሱም ጉዳት አጋጥሞት ሆስፒታል በፅኑ ህሙማን መታከሚያ ክፍል ህክምና ሲደረግለት እንደነበር ተነግሯል።
በቃጠሎው ከሰላሳ በመቶ በላይ የአካል ክፍሉ ተቃጥሎ እንደነበረ የተገለፀው ግለሰቡ አሁን ላይ ህይወቱ ማለፉን የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ማራቶን ውድድር ሀገሯ ዩጋንዳን ወክላ የተሳተፈችው አትሌት ርብቃ ቼፕቴጌ ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የሰውነት አኳሏ በመቃጠሉ ህይወቷ ማለፉ ይታወቃል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡን ኃላፊነት መሰረት ዛሬ በጎንደር ከተማ ተገኝተን በፍጥነት ያስጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተናል።
የኮሪደር ልማት ስራው 12 ኪ.ሜ ርዝመት አለው። በዋነኛነት ከኤርፖርት እስከ መሃል ከተማ ፒያሳ፣ ፋሲል ግንብ ዙሪያን እንዲሁም ፒያሳ አካባቢ የማደስ ስራን ያካተተ ሲሆን የህዝቡ ተባባሪነት ከፍተኛ በመሆኑ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል።
የጎንደር ከተማ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ እንደመሆኗ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንፃዎችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን በማደስ የቱሪስት መስህብነቷ ይበልጥ እንዲጨምር የምንሰራ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Via - ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከጥንት እስከዛሬ ከክብር ፣ ልቆ ከመገኘት እና ከነጻነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። ኢትዮጵያ ለዘመናት ሉዓላዊነትቷን ጠብቃ ከመቆየት ባሻገር በየትኛውንም ሀገር ወረራ ፈጽማ አታውቅም። ነገር ግን ሉዓላዊነቷን የተዳፈሩትን አሳፍራ መልሳለች፤ ትመልሳለችም። ይህም በልጆቿ የጋራ ጥረት የጸና ነው።
The name Ethiopia has long been associated with honor, excellence, and freedom. Throughout its history, Ethiopia has maintained its sovereignty and never invaded another country. However, it has always defended itself against those who threatened its sovereignty. And this will continue to be upheld by the united efforts of its people.
Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM
ቢሮው እና ኮርፖሬሽኑ ጳጉሜ 2 የሪፎርም ቀንን በማስመልከት ተገልጋዮችን ሲያስተናግዱ ውለዋል
የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 2 የሪፎርም ቀንን በማስመልከት በደመቀ መልኩ ተገልጋዮቻቸውን ተቀብለው ሲያስተናግዱ ውለዋል።
የሁለቱም ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ዛሬ ሙሉ ቀን በስራ ገበታቸው ተገኝተዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሚሰጠውን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ Online ማድረጉን ተከትሎ የምርቃትና የምስጋና ፕሮግራም እያከናወነ ይገኛል።
ቢሮው ዛሬ ጳጉሜ 2/2016 ዓ.ም እያከበርን ባለነው #የሪፎርም_ቀን "ተቋማዊ ለውጥ ለላቀ አገልግሎት" ብሎ ተቋሙን ሙሉ ለሙሉ ወደ E-Service ከማስገባቱም በተጨማሪ ቢሮውን የማዘመን፣ ዲጂታል የስልጠና ማዕከልን መክፈት፣ የሰራተኞች ዘመናዊ የካፍቴሪያ አገልግሎት፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶቹን በይፋ እያስጎበኘና እያስመረቀ ይገኛል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"የቢሯችን 47 አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ከወረቀት ንክኪ የፀዱና Online ተደርገዋል፣ ከዚህም በተጨማሪ በነገው ዕለተ ዲጂታል የስልጠና ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች አሻጋሪ አገልግሎቶችንም ወደ ስራ እናስገባለን" - የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አገልግሎቶቹን ሙሉ ለሙሉ ከወረቀት ንክኪ የፀዱና ONLINE እንዳደረጋቸው አስታወቀ።
ቢሮው ያሉትን 47 አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ Online ከማድረጉም በተጨማሪ ነገ ጳጉሜ 2/2016 ዓ.ም በ #ሪፎርም_ቀን ዲጂታል የስልጠና ማዕከልን ጨምሮ፣ የሰራተኞች ካፍቴሪያ፣ አዳዲስ የ Online አገልግሎቶችን እና ሌሎችም ስራዎችን በይፋ ወደ ስራ እንደሚያስገባ አስታውቋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሁን የደረሰበት የስኬት ደረጃ ከድኅነት ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የምናደርገው ጉዞ አንዱና ዋነኛው ተምሳሌት ነው" - ዶ/ር ሐብታሙ ኢተፋ - የኢፌዴሪ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር
🌴🌴🌴🌴🌴🌴
@HItefa 🙏🙏🙏
🌴🌴🌴🌴🌴🌴
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://x.com/ProsperityKera/status/1831395691475956022?t=D30Ms_CmUFN3oxFQjDVDaw&s=35
Читать полностью…ኢትዮጵያ የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን በነገው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ ታስተናግዳለች
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በአድዋ ድል መታሰቢያ ታካሂዳለች፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጥናት እንደሚያመላክተው በአውሮፓውያኑ ሚሊንየም በአፍሪካ በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር 47 በመቶ ሲሆን ይህ አሃዝ በአውሮፓውያኑ 2050 ወደ 60 በመቶ ከፍ ይላል ፡፡
ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በተደረገው ጥናት ደግሞ ዓመታዊ የከተሞች እድገት 3 ነጥብ 5 በመቶ እንደሆነ ነው የተጠቆመው ፡፡
ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምስራቅ አፍሪካ የከተሞች ነዋሪ ብዛት እና መስፋፋት ዝቅተኛ ሲሆን፤ ደቡባዊ እና ሰሜናዊ የአፍሪካ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆኑ ዜጎች በከተማ የሚኖሩባቸው ቀጠናዎች በመሆን ቀዳሚ ናቸው፡፡
ማእከላዊ እና ምእራብ የአፍሪካ ቀጠናዎች ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባቸው ግዙፍ ከተሞች መገኛ በመሆን ወደር የላቸውም ፡፡
ይህ የአፍሪካ እና አፍሪካዊያን የከተሞች መስፋፋትና የከተሜነት ፍላጎት ማደግ ያሳሳበው የአፍሪካ ህብርት ኮሚሽን ፤ከተማ እና ከተሜነት ግዙፍ ለውጥ እየታየበት ያለ እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ስለመሆኑ ያመለክታል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንም በአውሮፓውያኑ ነሃሴ 2022 በግብጽ ርእሰ መዲና ካይሮ በተካሄደው የኮሚሽኑ ልዩ አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ከተሞች ፎረምን አቋቁሟል፡፡
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በኮሚሽኑ ሲቋቋም ዋና አጀንዳው በአህጉሪቱ ያሉ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ ሲሆን ፤የአፍሪካ ከተሞች ለዜጎቻቸው ተስፋ የሚሰጡ፤ ለውጥ የሚያመጡ እና የብልጽግና ማእከል መሆን አለባቸው የሚሉ ዘርፈ ብዙ አጀንዳዎችን የያዘ ነው፡፡
በአውሮፓውያኑ ነሃሴ 2022 ከካይሮ የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ምስርታ በኋላ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ጉባኤን በአፍሪካ ህብርት ኮሚሽን አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ታስተናግዳለች፡፡
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉባኤው የአፍሪካ ከተሞች ሁለንተናዊ እና ዘመኑን የዋጀ እድገት እንዲኖራቸው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፤የተለያዩ ሃገራት ፤ከተሞች፤ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የልምድ ልውውጥ ፤የጎንዮሽ ውይይቶች እና ስምምነቶችን፤ ከማድረግ ባለፈ ኢግዚብሽን የሚቀርብ ይሆናል፡፡
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ማእቀፍ ዘላቂነት ያለው የአፍሪካ ከተሞች እድገት ለአፍሪካ ሁለንተናዊ ለውጥ ፤አጀንዳ 2063 አካል ሲሆን በአህጉሪቱ የሚታዩ የከተማ እና ከተሜነት ችግሮች የሚዳሰሱበት ይሆናል፡፡
🇮🇷 የኢራን ጦር ሃይል የተሻሻለውን የኤም 60 ታንክ መታጠቁ ተነገረ 🇮🇷
በዛሬው እለት ይፋ የሆነው እና ሱሌማን 1402 ተብሎ የተሰየመው አዲሱ ታንክ በ1959 የተመረተው የሁለተኛው ትውልድ አሜሪካን ኤም 60 ዋና የጦር ታንክ፤ የላቀ አቅም እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የያዘ ነው።
የተሻሻለው ታንክ የእሳት አደጋን መለየትና ማጥፋት የሚችል፣ ዲጂታል ዳሽቦርድ ያለው፣ የሌሰር ጃሚንግ እና የማስጠንቀቂያ ስርዓት ያለው ነው ተብሏል።
🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷🇮🇷
👆👆👆
“Uummata dararuun hojii idilee humna badii ABO Shaneeti” Miseensota daandii nagaa filatan.
@OromiaPParty 👆👆👆
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👆👆👆
"የኮሪደር ልማት ዕሳቤ ዜጎችን ለመጪው ዘመን የከተሜነት ኑሮ ማዘጋጀት ዘመንንም ለህዝብ ማዘጋጀት ነው" @AbiyAhmedAli 👆👆👆
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሁሉም በሰራው ልክ ሽልማት ይቀበላል ‼️
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሽልማቱ፦ የስኬት፤ የህልና እርካታ፣ የምስጋና ስጦታና የህዝባችን ደስታ ነው ። ውዷ ከንቲባችን @AdanechAbiebie ከአንቺ ገና ብዙ እንጠብቃለን እንኳን ደስ አለሽ።
@AbiyAhmedAli 🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹