ዘመን የማይሽረው አርቲስት፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ እና አፍሮ-ጃዝ ላይ ድንቅ አስተዋዕዖ ያበረከተውን #ጋሽ_ማህሙድ_አህመድ የኢትዮጵያ የመጨረሻውን የመድረክ ስራ በሚሊኒየም አዳራሽ ጥር 3፣ 2017ዓም ያቀርባል!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Gachanni Sirnaafi Milishaan wabii nageenyaa uummata keenyati!
Bulchinsa Magaalaa Bishooftuu Kutaa Magaalaa Dhibaayyuutti miseensonni Gaachana Sirnaafi Milishaa leenjii gahuumsa qaamaafi tooftaalee diina qolachuu leenji'aa taran eebbifaman.
Sirna Eebba Gaachana Sirnaa kanarratti Bulchaan Kutaa Magaalaa Dhibaayyuu Obbo Lammaa Kafanii humni kun humna nageenya hawaasaa murteessaa ta'e sirna jijjiiramaa ittiin tikfannu, nageenya waloo keenyaa ittiin eegannuudha jedhan.
Waan kana ta'e kaayyoo keessan beektanii ergama isinirra jiru imaanaa nageenyaa guuttanii fakkeenya gaarii hawaasa keessatti qabaachuun naamusaan dursitanii akka waardiyaa nageenya ta'uu qabdu jedhan.
Dabalataan, milishoonni keenyaa akkuma kaleessaa nageenya waaraa mirkaneeasuuf gaachana hawaasa taatanii olaantummaa heera biyyatti akka kabajamuuf aarsaa kaffalamuu qabu kaffaluu akkuma kanaan duraa diina nageenyaafi misoomaa hawaasaaf gufuu tahuuf yaaluu kamiyyuu dura dhaabachuun nageenya aanaa keessaniifi ummata keessaniif wabii ta'uu keessan akka mirkaneessitan abdiin qaba jedhan.
Kantiibaa Magaalaa Bishoftuu Obbo Alamaayyoo Asaffaa gamasaaniin Milishaan har’a eebbifnu kunneen mallattoo humnaafi kutannoo waloo keenyaati.
Dhiironni fi dubartoonni jajjaboon kun magaalaa keenya tajaajiluufi eeguuf gara fuulduraatti tarkaanfataniiru, Magaalaan Bishooftuutti kutaan Magaalaa Dhibaayyuu jiraattota ishee hundaaf bakka nageenya qabuufi dagaagaa tatee akka itti fuftu mirkaneessaaa jirtis jedhan.
Kominikeeshinii Bulchinsa Magaalaa Bishooftuu
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ለልማት ተነሺ አርሶአደሮች የሚሆኑ 770 ደረጃቸውን የጠበቁ ምትክ ቤቶችን ቅድሚያ ሰጥተን ግንባታቸውን በማፋጠን ላይ እንገኛለን" - ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በከተማችን ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት ከምናካሂዳቸው የቤት ግንባታ መርሃ ግብር ትልቁ የሆነው የኦቪድ ገላን ጉራ ሳይት 60 ሺሕ ቤቶች ግንባታ፣ በለገሀር ጊፍት ሪልስቴት የሚገነባቸው 4,370 ቤቶች የግንባታ ሂደትን እንዲሁም በቦሌ ሩዋንዳ በግሉ ዘርፍ እየለሙ የሚገኙ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን መጎብኘታቸውን አመልክተዋል።
በምናካሂዳቸው የልማት ስራዎች ቅድሚያ ለልማት ተነሺዎች በማለት በጀመርነው አሰራር መሰረት የኦቪድ ገላን ጉራ ሳይት ለልማት ተነሺ አርሶአደሮች የሚሆኑ 770 ደረጃቸውን የጠበቁ ምትክ ቤቶችን ቅድሚያ ሰጥተን ግንባታቸውን በማፋጠን ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል::
በዚህ የገላን ጉራ ፕሮጀክት ከሚገነቡ ቤቶች ውስጥ ኮንዶሚኒየም በመቆጠብ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ የምንገኝ ሲሆን በከተማችን ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር የጀመርናቸው ስራዎችን ከመሰረተልማትና ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው::
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የፕላንና ልማት ሚንስትሯ ዶ/ር ፍፁም አሰፋ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በገላን ጉራ የተቀናጀ የመኖርያ መንደርን ጨምሮ በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎበኙ።
አዲስ አበባ ባለፉት ጊዜያት የነበራት ገፅታ ፕላንን መሰረት ያላደረገና መዲናዋን የማይመጥን መሆኑን ያነሱት የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፍ (ዶ/ር) ባለፉት ጥቂት አመታት ግን በተከናወኑ ስራዎች አዲስ አበባን በሚመጥናት ደረጃ ተወዳዳሪ ከማድረግ ባሻገር የዘመናት ጥያቄ የነበረውን የነዋሪውን የመሰረተ ልማት ጥያቄ መመለስ ስለመቻሉ ተናግረዋል።
እንደ ሚንስትሯ ገለፃም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነባውና ለካሳንቺስ የልማት ተነሺዎች የተላለፈው የገላን ጉራ የተቀናጀ መንደር የዜጎችን በተሟላ መሰረተ ልማት ውስጥ የመኖር መብትን ያጎናፀፈና የተሰራውም መሰረተ ልማት ነዋሪውን ያማከለ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በገላን ጉራ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደር ያሉ የልማት ስራዎችን የጎበኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በበኩላቸው የመኖሪያ መንደሩ ይህንና መጪውን ትውልድ የሚያስተሳስር መሰረታዊ የሚባሉ ልማቶችን የሟላና ለሰው ልጆች ምቾትን የሚያጎናፅፍ ስለመሆኑ አንስተዋል።
የከተማን እድገትና ዘመናዊነትን የሚረጋገጠው ዜጎችን መሰረት ባደረገ ልማት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ማሳያው በአዲስ አበባ ባለፉት ጥቂት ጊዜያት የተከናወኑት ሰው ተኮር የልማት ስራዎች መሆናቸውን ገልፀዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ገላን ጉራ የመኖሪያና የተቀናጀ የልማት መንደር‼️
✍️ በ1200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘ መኖሪያ መንደር ነው፣
✍️ ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል አለው፣
✍️ ከቅድም አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነምገባ ማዕከሉ ይዟል፣
✍️ለ270 እናቶች የስራ እድል የፈጠረ የእንጀራ መጋገርያ ፋብሪካይዟል፣
✍️ 500 አረጋዉያን እና አቅመ ደካሞችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል የምገባ ማዕከል፣
✍️ ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፤ የህጻናት መጫወቻ እና የህጻናት ማቆያ ይዟል፣
✍️ በቋሚ እና በጊዜያዊነት ለ1646 ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፣
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Daandiin Nagaa Injifataadha!
Godina Horroo Guduruu Wallaggaatti waliigaltee nageenya waareessuu MNO fi WBO gidduutti taasifame hordofuun miseensotni garichaa karaa nagaan galanii jiru.
Miseensota WBO waamicha nagaa owwaatanii galan kanneeniif Abbootii Gadaa, Haadholii Siinqee fi qaamolee hawaasaa garaa garaatiin simannaan taasifameefii jira.
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"በክብርት የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራ ልዑክ ቡድን በወረዳችን ያደረገው የመስክ ምልከታ እየሰራናቸው ያሉ የተለያዩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አንድ ማሳያ ነው" - አቶ ታደለ አስማማው - የቂርቆስ ወረዳ 04 ዋና ስራ አስፈጻሚ
በኢፌዴሪ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ የተመራ የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 እየተከናወነ ያለውን የልማት ስራ ምልከታ አካሄዱ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተው የሱፐርቪዥን ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የሚገኙ ሴክተር ተቋማትን የሥራ እንቅስቃሴና የተቋም ማዘመን ሥራ እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ተመልክቷል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በወረዳው የተገነቡ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችና የአገልግሎት አሰጣጥን እንዲሁም የከተማ ግብርና ፣ በበጎ ፍቃድ የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ የመደመር ሜዳ፣ የህፃናት የመጫወቻ ስፍራዎችን ጉብኝት አካሄደዋል።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አዲሱ ሻንቆ፣ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ አደፍርስ ኮራ እንዲሁም ሌሎች የወረዳ እና የክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በሱፐርቪዥኑ ላይ ተገኝተዋል።
ይህንን አስመልክቶ የቂርቆስ ወረዳ 04 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ Tadele Asmamaw "በክብርት የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራ ልዑክ ቡድን በወረዳችን ያደረገው የመስክ ምልከታ በወረዳችን እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ስራዎች ውጤታማ ሆነው እየቀጠሉ እንደሚገኙ አንድ ማሳያ ነው" ብለዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ጠንካራ የስፖርት ምክር ቤት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና!" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ 15ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደናል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የከተማችንን የስፖርት እድገት ለማረጋገጥ እንዲሁም በአካል እና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለመገንባት በርካታ ስራዎች የሰራን ሲሆን፣ በከተማችን 1,314 የህፃናት እና ወጣቶች የመጫዎቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አብቅተናል።
ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በ11ዱም ክፍለ ከተሞቻችን 128 የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና መርሃ-ግብሮችን ከፍተን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ ማህበረሰባችን የስፖርትን ጥቅም ተረድቶ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Via ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ጊዝያዊ ምክር ቤት ማቋቋሙን አስታወቀ
ታህሳስ 4 ምሽት ይፋ የተደረገው መግለጫ እንደሚያሳየው ከሆነ የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላማዊ ትግልና ውይይት እንጂ በጦርነት አይደለም ብሎ የሚያምነው በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ፓርቲው መደበኛ 14 ጉባኤውን እስኪያካሂድ ድረስ ፓርቲውን የሚመራ ጊዝያዊ ምክር ቤት ማቋቋሙን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል።
የምክር ቤቱ አባላት ደግሞ ከኃላ ቀሩና ከወንጀል ቡድኑ ጋር አንሰለፍም ያሉ ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን መግለጫው ይገልፃል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በመቄዶኒያ የተጀመረውን 2B+G+12 በአጠቃላይ 15 ወለሎች ያሉት የአረጋውያን መኖሪያ እና ዘመናዊ ሆስፒታል ለመጨረስ የሚያስፈልገውን 4.3 ቢሊዮን ብር ለማሳካት የፊታችን የካቲት 1 ጀምሮ ታላቃ ሀገራዊ የገቢ ማሰባሰቢያ በSeifu on ebs tube ይደረጋል።
ኢትዮጵያውያን ከወዲሁ ቀና ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ጥሪውን ያቀርባል!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ፤ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ እየገቡ ነው‼️
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ተመን ይፋ አድርጓል፡፡
ግብር ስወራን ለመከላከል በሚል ለንግድ ዘርፎቹ ስራ ላይ የዋለው #የሰራተኛ_ደመወዝ እና የሰራተኛ ቁጥር ተመን የህጋዊነት ጥያቄ አስነስቷል፡፡
አነስተኛ የደመወዝ ወለል በህግ ባልፀደቀበት ሁኔታ ‘’ዝቅተኛ መክፈል የምትችሉት ደመወዝ 5,000 ብር ነው ብሎ በመወሰን ግብር መሰብሰብ ህገ-ወጥ አሰራር ነው’’ ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/38s7cx2p
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሰነደ መዋእለ ንዋዮች ገበያ በጥር ወር የመጀመሪያው ሳምንት በይፋ ይጀመራል ተባለ።
የኢትዮጵያ የሰነደ መዋእለ ንዋዮች ገበያ አ.ማ የሰነደ መዋእለ ንዋዮች ገበያን በይፋ የሚያስጀምርበትን መርሀግብር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ የሰነደ መዋእለ ንዋዮች ገበያ አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል ካሳሁን: በአንድ አመት ውስጥ ተቋሙ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ከማደራጀት አንስቶ በገበያው ተሳታፊ ለሚሆኑ አካላት ስልጠና እስከመስጠት ድረስ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሙሉ በሙሉ የተሟላ የኤሌክትሮኒክስ የገበያ ስርአት የላቸውም ያሉት ስራ አስፈፃሚው ኢትዮጵያ ይህን ማሳካት ከቻለች ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደጊዜ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ማደግም ለካፒታል ገበያው ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተነግሯል።
ማንኛውም በካፒታል ገበያ ውስጥ ተሳታፊ መሆን የሚፈልግ አካል ወደ ሰነደ መዋእለ ንዋዮች ገበያ ሲያቀና ሟሟላት የሚጠበቅበት መስፈርቶች እንዳሉም ተገልጿል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በኢትዮጵያ የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደህንነቱንና ጠራቱን የጠበቀ ዘመናዊ፣ ተደራሽ የውጭ ዜጎች አገልግሎት በመዘርጋት የሀገራችን የውጭ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍስት በመጨመር የተጀመሩትን የልማትና የለውጥ ጉዞ በማፋጠን የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ የበኩሉን ሚና ለመወጣት የሚያስችለውን የሪፎርምና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏት ተፈጥራዊና ታሪካዊ የቱሪዝም እምቅ ሀብቶች እና ኢንቨስትመንት ተጠቃሚ ለማድረግና የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ በሀገር ደረጃ በሚደረግ ጥረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቱሪስት ቪዛ፣ ኮንፈረን ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው የቪዛ ክፍያ ተመን ከ23 በመቶ በላይ እንዲቀንስ መደረጉን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የክፍያ አገልግሎት ደንብ ቁጥር 550/2016 መገንዘብ ይቻላል።
መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው መልካም ጉርብትናና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ካለው ቁርጠኛ አቋም በድንበር አካባቢ ከሚደረጉ ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ መፍቀድ በተጨማሪ መግቢያ ቪዛ ሳይጠየቁ በቀን ማህተም (ያለ ቪዛ ከፍያ) ገብተው ለ90 ቀናት እንዲቆዩ መፍቀዱ ይታወቃል።
በተለይ ከኤርትራ (አስመራ ወደ አዲስ ኣበባ ኢትዮጵያ) የሚመጡ ኤርትራዊያን ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ ማድረጉ በሁለቱም ህዝቦች ያለው ግንኙነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ምን ያህል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ስደተኞች በጥገኝነት እንደሚኖሩ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ፣ ሚዛኑን ባልጠበቀ እና ኃላፊነት በጎደለው አግባብ ተቋማችን ኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውን ሰዎች የተለየ በደል እና አድልዎ እየፈጸመባቸው እንደሆነ፣ ለመውጪያ ቪዛ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ፣ በስደተኝነት የተመዘገቡ ኤርትራዊያን ዲፖርት እየተደረጉ እንደሆነ አድርገው ሲዘግቡ ተስተውሏል።
በርካታ የውጭ ሀገር ሰዎች በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ በመግባትና ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ሀገር ውስጥ ሲቆዩ የሚስተዋሉ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ ሀገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ከመሰማራት ጀምሮ በህገወጥ የማዕድን ዝውውር፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በአደገኛ እፅ ዝውውር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በኮንትሮባንድ፣ በሀሰተኛ ሰንዶች ዝግጅት ወዘተ የመሳሰሉ የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራት ከባድ እና የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ሲፈፅሙ መገኘታቸውን ማርጋገጥ ችለናል።
በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር በመግባትና በህጋዊ መንገድ ገብተው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እነዚህን አካላት ወደ ህጋዊ መንገድ ለማስገባትና ለመመዝገብ በተደጋጋሚ ጥሪ ማድርጉ የሚታወቅ ቢሆንም ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ስርዓቱ የገቡ ግን በጣም ጥቂት ናቸው።
ስለሆነም የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጉላት አስፈላጊ ነው።
ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሐሰተኛ ወይም የተጭበረበረ ማንነት በመያዝ ለውጭ ሀገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ተገኝተዋል።
በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች በሻንጣ በማስገባትና በማስወጣት የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ ተገኝቷል።
በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር በርካታ ፍልሰተኞችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩና በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲያከናውኑ ተገኝቷል።
ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።
የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነድና ማንነት በመጠቀም ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሲያከናውኑ እና ከህግ ውጭ ሰነዶችን ሲጠቀሙ መገኘታቸው።
ስለዚህ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የሀገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ይታወቃል።
በመሆኑም ህጉ ተፈጻሚ የሚሆነው በሁሉም የሚመለከታቸው የውጭ ሀገር ሰዎች እንጂ በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው። ስለሆነም ለኤርትራዊያን ዜጎች እንደማንኛውም የጎረቤት ሀገር ዜጎች በቀን ማህተም ገብቶ በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ (90) ቀናት ቆይቶ ለሚሔድ ሰው ምንም ዓይነት የቪዛ ክፍያ እንደማይጠየቅ ለመግለጽ እንወዳለን።
ከተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ቆይተው የሚጣልባቸው ቅጣት ቢሆንም የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎችን ጨምሮ ለጎረቤት ሀገራት እንዲከፍሉት የሚጠየቀው ክፍያ በእጅጉ (በ200 በመቶ) የቀነሰ ሆኖ እያለ ለኤርትራዊያን የተለየና የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ተደርጎ መዘገቡ ከእውነታ የራቀ ነው።
በተመሳሳይ መልኩ ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተም ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ ጥላ ከለላ መሆን የቆየ ታሪኳና ባህሏ እንደሆነና የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ስደተኞችን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች በጥገኝነት እንድሚገኙ ይታወቃል።
በመሆኑም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከሀገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲከፍል የተረገ ሰው የሌለ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
እውነታው ይህን ሆኖ እያለ በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ያለ አግባብ ክፍያና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ መዘገቡ ከእውነት የራቀ ነው።
የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በመጠበቅ ህጋዊ የውጭ ሀገር ሰዎች እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ ለሚሰራው ስራ ላይ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችን እያቀረብን በተለይ ሚደያዎች ሚዛናዊ በመሆን የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በጠበቀ መልኩ አወንታዊ ሚና እንዲወጡ እናሳስባለን።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኤርዶጋን አዲስ አበባ ሊመጡ ነው
የኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ውዝግብ በሽምግልና የፈቱት የቱርክ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያንና ሶማሊያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ፥የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ማምሻውን እንደዘገቡት የቱርክ ፕሬዚዳንት ጤይብ ኤርዶጋን በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 2025 አዲስ አበባ እና ሞቃዲሾን ለመጎብኘት መርሃ ግብር ይዘዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአሜሪካ ኮንግረስ አባሉ ስኮት ፔሪ #ሶማሊላንድ የሉአላዊ ሀገርነት እውቅና ከዋሽንግተን ይሰጣት ዘንድ በአሜሪካው ኮንግረስ በይፋ አስተዋወቀዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#ካሳንችስ 🇪🇹 #ገላን_ጉዳ
#ቂርቆስ ወረዳ 08 🇪🇹
#አቃቂ_ቃሊቲ ወረዳ 10
የአደባባይ እውነታዎች፤ በአደባባይ ሲገለጡ 👏👏👏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
'መኒ አባ ገዳ' በሚለው ተወዳጅ ዘፈኑ የሚታወቀው ድምጻዊ መሃዲ ሼካ፥ 'ቶኩማ' የተሰኘ 14ተኛ የሙዚቃ አልበሙን ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ በተገኙበት በድሬዳዋ አስመርቋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የልማት ስራዎቻችን ሙሉ የሚሆኑት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን ታሳቢ ያደረጉ ሲሆኑ ነው።
Abiy Ahmed Ali
PM of the FDRE 🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹 Hallmarks of Diplomatic Success under Prime Minister Abiy Ahmed Ali (Ph. D)
The recent agreement between Ethiopia and Somalia, coupled with Ethiopia’s port access deal, represents a watershed moment in the Horn of Africa’s geopolitical landscape.
These achievements highlight Ethiopia's adept diplomacy and the visionary leadership of Prime Minister Abiy Ahmed (Ph.D). Here in my opinion I explores the multifaceted benefits of these agreements and underscores their roots in Ethiopia’s strategic diplomatic approach and Abiy Ahmed's transformative leadership.
👉 Strengthening Regional Peace and Stability
The Ethiopia-Somalia peace agreement signals a profound shift toward stability in a region historically marred by conflict and instability. By resolving longstanding tensions, the agreement fosters mutual trust, enabling Ethiopia and Somalia to prioritize common challenges such as terrorism, border disputes, and regional integration.
The peace accord strengthens regional security, as it reduces opportunities for extremist groups like Al-Shabaab to exploit inter-state rivalries. This stability benefits not only Ethiopia and Somalia but also the broader Horn of Africa, a region pivotal for international trade and security.
👉 Economic Benefits of Cooperation
Economic integration is another crucial outcome of this rapprochement. The peace agreement lays the groundwork for enhanced cross-border trade, investment, and infrastructure development. Improved relations with Somalia facilitate trade routes, reduce transaction costs, and create new markets for Ethiopian goods.
Somalia, with its vast coastline and access to the Indian Ocean, presents Ethiopia with opportunities to diversify its economic partnerships. Conversely, Somalia benefits from Ethiopia’s robust infrastructure network and growing economy, creating a mutually reinforcing cycle of economic growth ( ጠንካራ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን አጎልብተን በጋራ መስፈንጠርን የለመ/ wal malee maal qabna).
👉 Diplomatic Mastery of Ethiopia, and quality of Abiy Ahmed’s Leadership
These achievements are a testament to Ethiopia’s diplomatic acumen, led by Prime Minister Abiy Ahmed. Since assuming office in 2018, Abiy has redefined Ethiopia’s foreign policy, prioritizing dialogue, regional integration, and multilateralism.
His Nobel Peace Prize-winning efforts to end the Ethiopia-Eritrea conflict also set the stage for Ethiopia’s enhanced diplomatic credibility, enabling progress in resolving other regional challenges.
Abiy’s pragmatic approach combines visionary leadership with an emphasis on results. His ability to mediate complex conflicts and foster win-win agreements underscores his diplomatic finesse.
By prioritizing partnerships and leveraging Ethiopia’s strategic importance, Abiy has positioned the country as a stabilizing force in the region.
His focus on economic diplomacy, as seen in the port access deal, reflects a long-term strategy of economic integration and self-reliance, ensuring Ethiopia’s growth aligns with regional prosperity.
👉 Conclusion
The agreement between Ethiopia and Somalia and the port access deal epitomize Ethiopia’s successful diplomacy under Prime Minister Abiy Ahmed. These agreements not only enhance regional stability and economic growth but also reflect Ethiopia’s growing influence in shaping the Horn of Africa’s future.
As a cornerstone of Ethiopia’s foreign policy, these achievements exemplify the power of visionary leadership and strategic engagement in fostering sustainable development and peace.
🇪🇹 what a move! What a success! What a journey🙏
Proud your PM Dr. Abiy Ahimed Ali!
Dear readers:- Expect The strategic Value of Port Access 👈
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል። በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባውን የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀን ከፍተናል። ማዕከሉ ወላጅ የሌላቸውንና በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናትን ከማሳደግ ባሻገር የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ትብብር ማሳያ ነው።
በ ክቡር ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (phd)
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እጩዎች የምርጫ ክርክር አካሄዱ።
የአፍሪካ አንድነት፣ ሰላምና ደህንነት፣ አህጉራዊ የንግድ ትስስርን ማጎልበት፣ ኢኮኖሚ፣ የአፍሪካን ተሰሚነት በዓለም መድረክ መጨመር፣ ተቋማዊ ሪፎርም እና የዜጎች በተለይም የወጣቶች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በክርክሩ ትኩረት የተደረገባቸው ዋንኛ አጀንዳዎች ናቸው።
ክርክሩን ያደረጉት የጅቡቲ የውጭ ጉዳዮች እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሐሙድ አሊ የሱፍ፣ የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ ናቸው።
እጩዎቹ ለሁለት ሰዓታት በዘለቀው ክርክራቸው ቢመረጡ ሊፈጽሟቸው ያቀዷቸውን እቅዶች በዝርዝር አስረድተዋል።
የጅቡቲ የውጭ ጉዳዮች እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሐሙድ አሊ የሱፍ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሆነው ቢመረጡ በሰላም እና ደህንነት በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የአፍሪካ ሕዝብ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘውን ወጣት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችንም እንደሚተገብሩ ተናግረዋል።
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሆኜ ብመረጥ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ለማሳደግ እሰራለሁ ብለዋል።
ሌላኛው እጩ የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽነር ሆነው ቢመረጡ የሕብረቱ መስራች አባቶች ሕልም የሆነውን አፍሪካን አንድ የማድረግ ውጥን ማሳካት ዋነኛ ትኩረታቸው እንደሚሆን ገልጸዋል።
በትምህርት፣ በጤና፣ በምርቶች እሴት መጨመር እና በተለያዩ ቁልፍ መስኮች እድገት ላይ በትኩረት እሰራለሁ ብለዋል።
የአፍሪካን የእርስ በእርስ የንግድ ምጣኔና የመሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶችን የማስፋፋት እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።
የማዳጋስካር የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሆነው ቢመረጡ አካታች የፋይናንስ ተደራሽነት እንዲፈጠርና የዜጎች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የአፍሪካንና የሀገራትን ጥቅል ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት የሚያሳድጉ የአሰራር ማዕቀፎችን እንደሚዘረጉም አመልክተዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ተቋማዊ አቅም በማጎልበት የውሳኔ ሰጪነት እና ተወዳዳሪነት አቅሙን ለማሳደግ እሰራለሁ ብለዋል።
የሊቀመንበርነት ምርጫው የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ይከናወናል። የዘንድሮው የሕብረቱ ኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ከምስራቅ አፍሪካ ቀጣና እንደሚመረጥ ይታወቃል።
ከእ.አ.አ 2017 አንስቶ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የ64 ዓመቱ የቻድ ፖለቲከኛና ዲፕሎማት ሙሳ ፋቂ ማህማት የስልጣን ጊዜያቸው በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ኢዜአ ዘግቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ 4ተኛ ዓመት፤ 4ተኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ልማት ጉልህ ፍይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች ተወያይቶ አፅድቋል፡፡
የፀደቁ አጀንዳዎች 👇
1ኛ. የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎቻ ጤና እና ፅዳትና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
2ኛ. በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፤ አፈፃፀም ቁጥጥር፤ ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በመወያየት፤ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
3ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ ላይ መርምሮ በጥልቅ በመወያየት በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) እንተዳደሩ፣ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ እና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ::
4ተኛ- በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ
5ተኛ - ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት ህንፃዎች፣ የግልና የመንግስት ቢሮዎች የምሽት ፣ ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ብሔራዊ ክብርን ያረጋገጠ የውጭ ግንኙነት ለኢትዮጵያ ልዕልና"
ሀገራዊ ክብር ማለት ሀገራችን ታፍራ እና ተከብራ ሉዓላዊነቷን አረጋግጣ እንዲሁም የዜጎቿን ደህንነት እና ክብር አስጠብቃ እንድትኖር የሚያስችላትን አለም አቀፍ ይዞታ መፍጠር ማለት ነው። ህዝቦቿ በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ዘንድ ዋጋ የማግኘት እና የመከበር እሴት ነው።
የብልጽግና ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ፍልስፍና የማዕዘን ድንጋይ ለጎረቤት ሀገራት ትኩረት የሚሰጥ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ በውጭ ግንኙነታችን ውስጥ የብልጽግና የመጀመሪያው ትኩረት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመተባበርና በመነጋገር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ማጠናከር ነው፡፡ የኛ እና የጎረቤት ሀገሮቻችን እጣ ፈንታ የተሳሰረ ስለሆነ የጋራ ጥቅማችንን መሰረት ያደረገ መተጋገዝና ትብብር ያስፈልጋል ብሎ ስለሚያምን ብልጽግና ከጎረቤት ሀገራት የጋር ጥቅም ላይ ተመስረቶ ሊበይን እንደሚገባው ያስረዳል፡፡ ስለሆነም በቀጠናው ካሉ ሀገሮች ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሰረት ያደረገ አከባቢያዊ የልማት፤ የኢኮኖሚ እና የሰላም ዲፕሎማሲ ትሥሥር እንዲፈጠር ቀስ በቀስ እያደገ የሚሄድ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ጥምረት እንዲሆን አስፈላጊውን ሁሉ የዲፕሎማሲ ስራ እየሰራ ይገኛል።
ሀገራችን ኢትዬጵያ ከጎረቤት ሀገራት እስከ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በምትከተለው የውጭ ግንኙነት ፓሊሲ ከተሳታፊነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት በመሸጋገር ላይ ትገኛለች።
ለዚሁ ማሳያ በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ በፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር በሰላም መጠናቀቁ አንዱ ማሳያ ነው።
ከዚህ ቀደም የተበሩት መንግስታት የሰሩት ታሪካዊ ስህተትን የለውጡ መንግስት በጥበብና በእውቀት፣ እውነተኛ መርህ ላይ ቆሞ በሀሳብ የበላይነት ኢትዬጵያ ያጣችውን የባህር በር አጀንዳ በማድረግ ሀሳቡም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ቅቡልነት እንዲያገኝ አድርጋል። ይህም የባህር በር ባለቤትም ያደርጋታል።
ስምምነቱም የሀገራችንን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ያደረገ ፣ ኢትዬጵያ አሸናፊ ሁና የወጣችበት ታሪካዊ መድረክ ነው። ብሔራዊ ክብርን ያረጋገጠ የውጭ ግንኙነት በመከተል የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን እናደርጋለን።
#aa_prosperity
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢትዮጵያን ጨምሮ 9 የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የአለም አቀፍ ጎብኝዎች መዳረሻ መሆናቸው ተገለጸ። በ2024 9 ወራት ብቻ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ1ቢሊየን በላይ ሰዎች የጉብኝት ጉዞዎችን አድርገዋል።
የአፍሪካ ቱሪዝም ሴክተር በከፍተኛ መነቃቃት ውስጥ እንደሚገኝ ትራቭል ኤንድ ቱር ወርልድ የተባለው ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡
አለም አቀፋዊ የቱሪዝም መዳረሻቸዎችን እና ደረጃዎችን የሚያወጣው ድረገጹ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ሞሪሽየስ፣ ሲሽየልስ እና ስዋቲኒ በአህጉሪቷ ቀዳሚ የቱሪስ መዳረሻ መሆናቸውን አመላክቷል፡፡
እነዚህ መዳረሻዎች በጋራ ከ50 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎችን የተቀበሉ ሲሆን ይህም ለአፍሪካ የጉዞ ኢንዱስትሪ መሻሻል ትልቅ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
እያንዳንዳቸው ሀገራት ልዩ የተፈጥሮ መስህቦችን ፣ ባህል ፣ ቅርሶችን እና ዘመናዊ መስህቦች መገኛ መሆናቸው ከመላው ዓለም ተጓዦችን እንዲስቡ አስችሏቸዋል፡፡
በ2024 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 1.1 ቢሊዮን ቱሪስቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ለጉብኝት ተጉዘዋል፤ በአመቱ የአፍሪካ የቱሪዝም ዘርፍ ከ2019 ጋር ሲነፃፀር የ6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተችው ኢትዮጵያ 1.08 ሚሊየን አለም አቀፍ ጎብኝዎችን እንዳስተናገደች ተገልጿል፡፡
የበለጸገ ባህል ፣ ታሪክ እና ቅርጽ ባለቤት መሆኗ በሚነገርላት ኢትዮጵያ ጎብኚዎች የላሊበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ ጥንታዊቷ የአክሱም ከተማ እና አስደናቂውን የስሜን ተራሮች ለማየት ያቀናሉ፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚገኙ የቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን ፣ የመርካቶ ገበያ እና በመዲናዋ የሚገኙ ሙዝየሞች እንዲሁም የጎንደር ቤተ መንግስቶች ወደ ኢትዮጵያ ለሚሄዱ ጎብኝዎች ተጨማሪ አይን ማረፍያ ናቸው ተብሏል፡፡
አዲስ አበባ የአፍሪካ ፣ የመካከለኛው ምስራቅ ፣ የደቡብ አሜሪካ የእስያ እና የሰሜን አሜሪካ ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ ለ90 ሀገራት ከቪዛ ነጻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ፈቅዳለች።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢሳያስ አፈወርቂ‼️
ከብዙ ጊዜ በኋላ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አሰብ አቅንተው ለካቢኒያቸው አመራር ሰጡ ‼️
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከረጅም ጊዜ ቦኃላ አሰብ ተገኝቶ የደቡባዊ ቀይ ባህር ዞን አመራሮችን ሰብስቦ ጥብቅ መመርያ ሰጥቷል።
ኢሳይያስ አፈወርቂ ይሄን ያደረጉት በትናትናው ዕለት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ አፍሪካ ጉዳይ ረዳት ፀሀፊ
የሆኑት ቲቦር ናጊ "በሶሪያው መሪ በሽር አላሳድ ላይ የተደገመው በኤርትራ መንግሥት ላይ ይደገማል" የሚል ፅሁፍ በቲዊተር ገፃቸው ካስተላለፉ በኋላ ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹