የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት አመታት በፕሬዝዳንትነትና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት የሚመሩ እጩዎችን ስምዝርዝር ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት አመታት በፕሬዝዳንትነትና በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት የሚመሩ እጩዎች ስምዝርዝር ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታህሳስ 12-13/2017 በአዲስ አበባ ከተማ በሚያካሂደው 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት አመታት የሚመሩ ፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን እንደሚመረጡ ይታወቃል።
በመሆኑ የእጩዎች ማቅረቢያ ቀነ ገደብ ህዳር 16/2017 ከቀኑ 11:30 ድረስ ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች እጩዎቻቸውን አሳውቀዋል። ስለሆነም በእጩዎች ተገቢነት ላይ አስፈላጊው ማጣራት እየተካሄደ መሆኑን ከግንዛቤ ገብቶ ከክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተላኩት እጩዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች መለየትና ማስከበር፡ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለመለየትና ለማስከበር የምትከተለው የዓይን አፋርነት አካሄድ ነበር፡፡ ይሄም በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስከበር የሚያስችል ገቢራዊ አካሄድ እንዳንጓዝ አድርጎን ኖሯል፡፡ ለውጡ ይሄን አካሄድ ቀይሯል፡፡ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስከበር ግልጽና ጉልሕ የሆነ መንገድን ትከተላለች፡፡ ባለፉት ዘመናት የተከሠተውን የባሕር በር የማጣት ስብራት ለመጠገንም ይሄንኑ መንገድ መከተል አስፈላጊ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን ዓለም በብዛት እንዲቀበለው ለማድረግ ተችሏል፡፡ በዓለም አቀፍ መድረኮችም ብሔራዊ ጥቅሞቿን ሊያስከብሩ በሚችሉ የሁለትዮሽና ባለ ብዙ ዘር ትብብሮች ላይ በጉልሕ ትሳተፋለች፡፡ አባል ትሆናለች፡፡ እንደ ብሪክስ ባሉ ማሕቀፎች ላይ ያደረገቸው የአባላነት ተሳትፎም የዚህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ የለውጡ መሪም ውጤትም የሆነውን የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት ስናከብር፣ ያለፉትን ስኬቶች ቆጥረንና አዳብረን በማስቀጠል፤ ፈተናዎቻችንን በመወጣትና ስሕተቶችን በማረም ይሆናል፡፡ የለውጡ ትግል፣ የለውጡ ሥራና ውጤት ከአንድ ፓርቲ በላይ ነው፡፡ ጥቅሙም ሀገራዊና ለሁሉም ዓይነት ማኅበረሰብ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ማሳያዎች የጅምራችንን ትክክለኛነት አመላካች ናቸው፡፡
ነገር ግን መጀመራችንን እንጂ ማጠናቀቃችንን አያሳዩም፡፡ ስለሆነም የፖርቲያችን አመራርና አባላት፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራርና አባላት፣ እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለውጡ ሰክኖና ሥር መሠረት ይዞ፣ ይህ ዘመን የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን እንዲሆን በጋራ እንድንነሣና እንድንታገል በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!
ህዳር 17፤ 2017
Abiy Ahmed Ali (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#ለውጡና_የለውጡ_ፍሬዎች
በሕዝብ ግፊትና በፓርቲ ሳቢነት የመጣው ሀገራዊ ለውጥ፣ የመጀመሪያውን ምእራፍ እየተሻገረ ነው፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ምእራፍ የለውጡን ሐሳቦች በቃልና በተግባር ተገልጠዋል፡፡ የለውጡ ፈተናዎችም አካል ገዝተው በሚገባ በመገለጣቸው ሕዝብ ዐውቆ እንዲታገላቸው ተደርጓል፡፡ ይሄም የለውጡን ፍሬዎች ለማጎምራት፣ የለውጡን ፈተናዎችንም ለመርታት ዕድል ሰጥቷል፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ሲጠየቁ የነበሩ ጥያቄዎች ከቃል አልፈው ተግባራዊ ምላሽ አግኝተዋል፡፡ የፖሊሲ፣ የሕግ እና የአሠራር ብቻ ሳይሆን የባህል ለውጥ አምጥተዋል፡፡ ለውጡ ያለፉት የሀገሪቱን ስብራቶች የሚጠግን፣ ዛሬን የሚዋጅና የነገውን የኢትዮጵያ ጉዞ የሚያቀና ነው፡፡ የለውጡ ዘመን መሪ ፓርቲ የሆነው ብልጽግና አምስተኛ ዓመቱን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት የሚከተሉትን አንኳር የለውጥ ውጤቶች ማንሣቱ ተገቢ ነው፡፡
የብልጽግና መመሥረት፡ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ ነው፡፡ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ንቃት በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ የፖለቲካ አደረጃቶችን አምጥተዋል፡፡ የሕዝብ ጥያቄዎችን ቅርጽና መልክ ሰጥተዋል፡፡ የፖለቲካ ትግል ስልቶችንም አስተዋውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የትጥቅ ትግልና የፖለቲካ ትግል እንዲቀላቀል፤ የጥላቻ ፖለቲካ እንዲነግሥ፣ በብሔር፣ በርዕዮተ ዓለምና በትግል ስልት መፈራረጅ እንዲበረታ በማድረግ ለዘመናዊ የፖለቲካ ጉዟችን ሳንካዎችን አኑረዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ነባሮቹን ፖለቲካዊ ዕሤቶች በሚያጎለብትና የፖለቲካ ስብራቶቻችንን በሚጠግን መልኩ ተመሥርቷል፡፡ ይሄም የለውጡ አንዱ ፍሬ ነው፡፡ የብልጽግና መመሥረት የዳርና የመሐል፤ ዋና እና አጋር፣ አርብቶ አደርና አርሶ አደር፤ ተራማጅና አድኃሪ፤ ጠላትና ወዳጅ፣ ወዘተ. የሚባሉትን ግንቦች በማፍረስ በሐሳብ ላይ ብቻ የተመሠረተ የፖለቲካ አደረጃጀትን ፈጥሯል፡፡ የሐሳብ ልዩነቶችን እንደ ጌጥና ዕሴት በመውሰድ ተፎካካሪዎቹን በጠላትነት አይፈርጅም፡፡ በኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ላይ በመመሥረት፣ ከሌሎች ሐሳቦች በመማር፣ በገቢር ነበብ መንገድ ይጓዛል እንጂ የርዕዮተ ዓለም እሥረኛ አይደለም፡፡ ለአንድ አካባቢ ወይም ብሔር የቆመ ሳይሆን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለው የሐሳብ ፓርቲ ነው፡፡ ይሄም የኢትዮጵያን የፖለቲካ መልክአ ምድር የለወጠ የለውጥ ፍሬ ነው፡፡
የእምነት ተቋማት ልዕልና፡ የእምነት ተቋማት የመንግሥት ጥገኛነትና የህልውና ፈተና ነበረባቸው፡፡ የህልውና ፈተናውም በመንግሥት ጣልቃ ገብነት የተነሣ የሚፈጠር ፈተና ነው፡፡ ከለውጡ በኋላ የእምነት ተቋማት ልዕልና ተከብሯል፡፡ ይሄንን ልዕልና ለማስከበርም መንግሥት በተቋማቱ ላይ ሲያደርግ የኖረው ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት እንዲቆም ተደርጓል፡፡ ተቋማቱ ምንም እንኳን ነጻነትን የማስተዳደር ችግር ቢያጋጥማቸውም፣ ነገር ግን ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው ጉዳዮቻቸውን በሃይማኖታቸው ሕግ ብቻ እንዲያከናውኑ ዕድል ተሰጥቷቸዋል፡፡
ልዕልናቸውን ይፈታተናቸው የነበረውን መለያየት ለማስቀረት ተለያይተው የነበሩ የሃይማኖት አመራሮችን ለማቀራረብ፣ ለማግባባትና ወደ አንድነት እንዲመጡ ለማድረግ መንግሥት የሚጠበቅበትን ሚና ተጫውቷል፡፡
በዚህ ሚና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች መካከል የነበረው መለያየት ተወግዶ አንድነት ተፈጥሯል፡፡ የሃይማኖት ተቋማቱ አንድነታቸውን በማጽናት ተልዕኳቸውን በሚፈልጉት ልክ ለመወጣት እንዲችሉ በሕግ በኩል የነበረባቸው ክፍተት ተሟልቷል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የሕጋዊነት ጥያቄ ሲያነሡ ነበር፡፡ ይሄንን የግማሽ ምዕተ ዓመት ጥያቄ ለመመለስ ሁለቱም በዐዋጅ እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡ ይሄም የለውጡ አንዱ ፍሬ ነው፡፡
የሲቪክ ተቋማት፡ የአንድ ሀገር ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሕይወት እንዲሣለጥ የሲቪክ ማኅበረሰብ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ሲቪክ ተቋማት ማኅበረሰቡ በራሱ ፈቃድ በመደራጀት መብቱን የሚያስከብርባቸውና ሐሳቡን በተደራጀ መልኩ የሚቀርብባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ በእነዚህ ተቋማት ላይ የነበረውን የተንሸዋረረ አመለካከት በማስተካከል፣ የታሠሩበት ቀፍዳጅ ሕግ በለውጡ ተሻሽሏል፡፡ ለውጡ የሲቪክ ተቋማትን እንቅስቃሴ ለተቋማቱም ሆነ ለሀገር በሚበጅ መልኩ በአዲስ ሕግና አደረጃጀት እንዲዋቀሩ አድርጓል፡፡ ከለውጡ በፊት 1900 የሲቪክ ማኅበራት ብቻ ነበሩ፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ግን 3300 አዳዲስ ሲቪክ ማኀበራት ተመዝግበዋል፡፡
የዴሞክራሲ ተቋማት፡ የዴሞክራሲ ሥርዓት የሚሣለጠው በዴሞክራሲ ተቋማት አማካኝነት ነው፡፡ የዴሞክራሲ ተቋማት ደግሞ ነጻ፣ ገለልተኛና ተአማኒ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከለውጡ በፊት የነበረው የተቋማቱ ስብራትም ይሄንን ባሕሪይ ለመላበስ አለመቻል ነበር፡፡ ከለውጡ በኋላ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የዕንባ ጠባቂ ተቋም እና የመገናኛ ብዙኃን ባለ ሥልጣን እንደገና እንዲደራጁ ተደርገዋል፡፡ ነጻ፣ ገለልተኛና ተአማኒ እንዲሆኑ የሚያስችል የሕግና የአደረጃጀት ለውጦች ተደርጎባቸዋል፡፡ ከመንግሥት ጫና እና ጣልቃ ገብነት ውጭ በሕግና በኅሊናቸው ብቻ እንዲሠሩ የሚያስችል አካሄድን ይከተላሉ፡፡ እነዚህ ተቋማት ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ መንግሥትንም ሆነ ገዥውን ፓርቲ በሕጋቸው መሠረት የሚከታተሉ፣ አስፈላጊ ነው ባሉበት ጊዜ የሚቀጡ ተቋማት ሆነዋል፡፡
የሚዲያ ነጻነትና ዕድገት፡ ሚዲያ የብዝኃ እና የዓይነተ ሐሳብ መድረክ ነው፡፡ የሐሳብ ነጻነት አንዱ መገለጫና የሥልጣኔ መንድ መተለሚያ ነው፡፡
ለውጡ የሚዲያ ነጻነት እንዲከበር፤ ሚዲያዎች በሕግ ብቻ እንዲሠሩና እንዲተዳደሩ፣ የሁሉም ዓይነት ማኅበረሰብ የሐሳብ ገበታዎች እንዲሆኑ ለማድረግ አስችሏል፡፡ የመገናኛ ብዙኃ ባለ ሥልጣንን ሕግ ማሻሻል፣ የሚዲያን አሣሪ ሕጎች ማሻሻል፤ የሚዲያ ተደራሽነትን ማበረታታት፣ ሚዲያዎች እርስ በርስ ራሳቸውን የሚቆጣጠሩበትን ሥርዓት የመዘርጋት ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ከለውጡ በፊት 122 የነበሩት መገናኛ ብዙኃን በአሁኑ ጊዜ 123 ዕድገት በማሳየት፣ 272 ደርሰዋል፡፡ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ከ25 ወደ 78፤ የሬዲዮ ጣቢያዎች ደግሞ ከ52 ወደ 73 አድገዋል፡፡ የእነዚህ መገናኛ ብዙኃን የቋንቋ ተደራሽነትም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 39 ቋንቋ በመላቅ አሁን በ60 ቋንቋዎች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
ኢትዮጵያን ማዘመን፡- የኢትዮጵያ አንዱ ስብራት የኋላ ቀርነት ፈተና ነው፡፡ በሁሉም ዓይነት ዘርፎች ኋላ ቀርነት በመንሠራፋቱ የተነሣ ኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት እድሜዋን ያህል አላደገችም፡፡ ለውጡ ከመጣባቸው ገፊ ምክንያቶች አንዱም ይሄው የኋላ ቀርነት ስብራት ነው፡፡ በለውጡ ዘመን ኋላ ቀርነትን ቀርፎ ኢትዮጵያን ለማዘመን አያሌ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ ለውጥም አምጥተዋል፡፡
"የኢፌዴሪ አየር ኃይል በበርካታ ጀግኖች መስዋዕትነት የፀና ታላቅ ተቋም ነው" -ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ
"የተከበረች ሀገር የማይደፈር አየር ኃይል" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 89ኛውን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ቀንን በማስመልከት ከመከላከያ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይል ተመስርቶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በርካታ ጀግኖች ላባቸውን እና ደማቸውን ከማፍሰስም በላይ ውድ ህይወታቸውን ሰውተው ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር ማድረግ ችለዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አዛዡ በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰውን አየር ኃይል ይበልጥ በማዘመንና ለታላቅ ሀገር የሚመጥን አየር ኃይል ገንብተን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማሸጋገር በሁሉም ዘርፉ ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ነው ያሉት።
በቀጣይም ሰራዊታችን አሁን ተቋሙ እየሰራ ያለውን እና ያስመዘገበውን ውጤት እንደመነሻ በመያዝ በቀጣይ የበለጠ ተግቶ በመስራት የላቀ ውጤት ሊያስመዘግብ ይገባል ሲሉም ሌተናል ጄኔራል ይልማ ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከመፍጠር ጀምሮ የአባላቱን አቅም በስልጠና ለማዳበር ብሎም በራስ አቅም ታላላቅ ስራዎችን እየሠራ የሚገኝ መሆኑን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ በተለይም ምቹ የሥራ አካባቢን በመፍጠርና በሁሉም መስክ ዝግጁ እና ቀልጣፋ የሆነ ሠራዊት በመገንባት ለታላቅ ሀገር የሚመጥን ታላቅ አየር ኃይል እየተገነባ እንደሚገኝም አመላክተዋል።
አየር ኃይል ወቅቱ የሚጠይቀውን የውጊያ መሠረተ ልማት በማሟላት እና የትጥቆቻችንን አቅም በማዘመን የኢትዮጵያን የአየር ክልል ከየትኛውም ጥቃት በንቃት እየጠበቀ የሚገኝ መሆኑን የተናገሩት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ሃይል በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት በሚያስችል ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን ተናግረዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"መሠል የብልፅግና ፓርቲ ዕሴቶች የሆኑ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ስራዎችን በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ" - ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ህብረተስብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት #በጎነት_በሆስፒታል በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ተበርክቷል፡፡
በድጋፍ ስጦታው ፕሮግራም የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተገኝተው ህሙማኑን በማጽናናት የቁሳቁስ ድጋፍ አበርክተዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ህብረተስብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሐብታሟ ቡልቻ በበኩላቸው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በመገኘት ከበጎ ፈቃድ ለጋሾች ያሰባሰቡት፤ ፍራሽ፣ ብርድልብስ፣ አንሶላ እና የንጽህና መጠበቂያ ለተኝቶ ታካሚዎች ህሙማን እንዲውል ታስቦ ለሆስፒታሉ አስተባባሪ አብርክተዋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዴንማርክ አየር ይበክላል በማለት በላም ፈስ ላይ ቀረጥ ልትጥል ነው።
የላም ፈስ አየር ሚቴን የተባለ በካይ ጋዝ ያለው ሲሆን ሚኒስትሮች ከተስማሙ ከሰባት አመት በኋላ ላሞቻቸው በሚያመርቱት ሚቴን ለአንድ ቶን 43 ዶላር ገደማ እንዲከፍሉ መታቀዱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአፍሪካ የሰላም ኮንፈረንስ "የበለጸገና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ፣ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴዎዬ፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የአፍሪካ የሰላም ስብሰባ ሰላም የሰፈነባት፣ የበለጸገችና የለማች አፍሪካን እውን ለማድረግ በጋራ የሚመክሩበት መድረክ ነው።
በመድረኩ ኢትዮጵያ ለዓለምና ለቀጣናው ሰላም ከኮሪያ ዘመቻ እስከ ሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ይቀርባል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ ለመላው የክፍለ ከተማችን የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የከበረ ምስጋናቸውን አቀረበ።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ "ባለፉት ሳምንታት የፓርቲያች 5ተኛ አመት ክብረ በዓልን በክፍለ ከተማችን ደረጃ እና በከተማ ደረጃም በመገኘት በተለያዩ ኩነቶችና የፓርቲያችን እሴቶች ላይ ተመርኩዘን በስኬት አክብረነዋል። ለዚህ ደግሞ መላው የክፍለ ከተማችን የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና የፓርቲያችን ደጋፊዎች አስተዋጽኦ እጅግ የሚደነቅና የሚያስመሰግንም ጭምር ነው" ብለዋል
ኃላፊው አክለውም "በእነዚህ ውጤታማ ስራዎች ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ መላው የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎችን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ከልብ እናመሠግናለን ለማለት እፈልጋለሁ" ብለው ሃሳባቸውን ቋጭተዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ከመላው ነዋሪያችን፣ አመራራችን፣ ሰራተኞቻችን፣ መዋቅራችን እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሁሉም መስክ የክፍለ ከተማችንን ብልፅግና ማስቀጠሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል" - የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እየተሰሩ ያሉ #ብልፅግና ተኮር ስራዎች ተጠናክረው በመቀጠል ላይ እንደሚገኙ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ገለፁ።
የኮሚቴ አባላቱ "ከመላው ነዋሪያችን፣ አመራራችን፣ ከመላው ሰራተኞቻችን፣ እንዲሁም የበርካታ ስኬቶቻችን ቁልፍ ከሆነው መላው መዋቅራችን ጋር ሲልቅም ከሚመለከታቸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ክፍለ ከተማችን #አዲስከተማ ን የአዲስ አበባ #ብልጽግና እምብርት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" ብለዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።
ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።
Before officially inaugurating ‘Quality Village ‘today, I had the opportunity yesterday to visit and review the National Quality Infrastructure we have developed.
This critical institution is designed to catalyze the competitiveness of our local products in global markets and enhance our participation in global value chains.
As one of our leading national institutions, it will play a vital role in strengthening our export capabilities and ensuring we remain competitive in the international arena.
Via - Dr. Abiy Ahmed Ali - FDRE PM
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ሁሉ አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪህ ቃል የተዘጋጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ካውንስል ጉባዔ አካሂደናል::
ሌተቀን የከተማቸውን ሰላም በመጠበቅ፣ የጎደሉ በየአካባቢው ያሉ መሰረተ ልማቶችን በህብረተሰቡ ተሳትፎ በመስራት እና በማሰራት በልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ፣ ማህበራዊ ጫናዎችን በመቀነስ እና በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው እንዲሁም በእውቀታቸው ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ የከተማችንን ነዋሪዎችን እና የብሎክ አደረጃጀቶችን እስከ አሁን ለሰሩት ስራ እውቅና ሰጥተን የ2017 እቅድ ላይም ተወያይተናል።
ቀና ልብ ያላቸው በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የበርካቶችን የመኖር ተስፋ ያለመለሙ ስራዎችን ለሰራችሁና ላስተባበራችሁ ሁሉ በነዋሪዎቻችን ስም እያመሰገንኩ የከተማችንን ፈጣን ለውጥ ቀጣይነት ባለው መንገድ ለማስቀጠል ከህብረተሰባችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Yaa'ii kaawunsilii hirmaannaa hawaasaa mata duree "Hirmaannaa hawaasa hunda hammataa misooma itti fufaaf" jedhuun qophaa'e geeggeessineerra.
Halkanii fi guyyaan nageenya magaalaasaanii eeguun,bu'uuraalee misooma bakka garagaraatti hir'atan hirmaannaa hawaasaatiin hojjechuun fi hojjechiisuun, hojiiwwan misoomaa irratti dammaqinaan hirmaachuun,dhiibbaalee hawaasummaa hir'isuun fi hojiilee tola ooltummaa hedduurratti qarshii isaaniitiin, humna isaaniitiin akkasuma beekumsa isaaniitiin hirmaannaa taasisaa kan jiran jiraattota magaalaa keenyaa fi gurmaa'insa bilookiilee hojiiwwan hamma ammaatti hojjetaniif beekamtii laannee karoora bara 2017 irrattis mari'anneerra.
Tola ooltota onnee gaarii qaban qindeessuun hojiiwwan jireenyaa hedduuwwaniitti abdii horan kan hojjettan fi kanneen qindeessitan hunduu maqaa jiraattota keenyaatiin isin galateeffataa jijjiirama saffisaa magaalaa keenyaa karaa itti fufiinsa qabuun itti fufsiisuuf hawaasa keenya waliin tumsaan hojjechuu itti fufna.
Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!
Via ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
የዘንድሮውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሻለ ሁኔታ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን።
በዚሁ መሰረት ዛሬ ከሆቴል ባለቤቶች እና ከዘርፉ አካላት ጋር ተወያይተናል።
በውይይቱ እንደተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትንና እንግዳ ተቀባይነታችንን አጉልተን በማሳየት በላቀ አገልግሎት ሰጪነት እንድናስተናግድ እንዲሁም ከተማችንን የቱሪዝምና የኮንፍራንስ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስራ ይበልጥ በሚያጠናክር አግባብ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ትላልቅ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉባኤዎች ወደ ከተማችን እንዲመጡ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ተግባብተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ክብርት አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የግብርና ኋላ ቀርነትን ቀርፎ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማስከበር በተሠራው ሥራ የባህልም የውጤትም ለውጥ መጥቷል፡፡ ከዚህ በፊት የዝናም ወቅት ብቻ ይጠብቅ የነበረው የግብርና ባህል መስኖን በመጠቀም፣ በኩታ ገጠም እርሻና መሬት ጦም እንዳያድር በተሠራው ሥራ፣ ዓመቱን ሙሉ የሚመረትበት ባህል እያመጣ ነው፡፡ ስንዴን፣ ሩዝን፣ ገብስን፣ በቆሎንና የፍራፍሬ ምርቶችን ትኩረት አድርጎ በተሠራው ሥራ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚዋ የስንዴ አምራች ሀገር ሆናለች፡፡ ስንዴን ከውጭ ማስመጣትም አቁማለች፡፡ በአትክልትና በፍራፍሬ ዘርፍም የወጪ ምርት መጠናችን ጨምሯል፡፡
በሌማት ትሩፋት በተሠራው ሥራ የወተት፣ የዶሮና የማር ምርቶች በየቤተሰቡ ሌማት ላይ እንዲገኙ ጥረት ተጀምሯል፡፡ በዚህም የዶሮ ሥጋን ምርት ከነበረበት 70 ሺህ ቶን ወደ 208 ሺ ቶን፤ የወተት ምርት ከነበረበት 7.2 ቢሊዮን ሊትር ወደ 10. ቢሊዮን ሊትር ደርሷል፡፡ የማር ምርት ደግሞ ከ129 ሺህ ቶን ምርት ወደ 272 ሺህ ቶን ለማሳደግ ተችሏል፡፡
ሌላው ኢትዮጵያን የማዘመን ተግባር ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማድረግ ተግባር ነው፡፡ ከመመናመን አልፎ እየጠፋ የነበረው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ልብስ፣ እየተመለሰ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከመራቆት ወደ አረንጓዴ ጋቢ እየተሻገረች ናት፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት 40 ቢሊዮን የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል በቅተናል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 50.4 በመቶ የደን ዛፍ ችግኞች ሲሆኑ፣ 48.6 በመቶ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ፣ የፍራፍሬ፣ የመኖና የማገዶ የእንጨት ዛፎች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያን ለማዘመን በተሠራው የኢንዱስትሪ ምርታማነት ሥራ አያሌ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት እየተቻለ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ከውጪ የሚገቡትን የቢራ ብቅል፣ የምግብ ዘይት፣ ፓስታና አልሚ ምግቦች፣ የተማሪዎች ዩኒፎርም፣ የጸጥታ አባላት የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች (ፖል፣ገመድና ትራንስፎርመር) በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ሥራ ውጤት እያሳየ ይገኛል፡፡
በዚህ ዘመን የሚደረግ ሀገርን የማዘመን ተግባር ያለ ዲጂታላይዜሽን ሊሳካ የሚችል አይደለም፡፡ በዚህም የተነሣ መንግሥት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚያደርገው ምርምር እና የሚያፈሰው ሙዓለ ንዋይ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ለማሳያም ያህል የዲጂታል አካውንት ብዛት ከነበረበት 52.1 ሚሊዮን ዛሬ ወደ 205.4 ሚሊዮን ሆኗል፡፡ በዘመናዊ የክፍያ ዘዴ የተላለፈው የገንዘብ መጠን ደግሞ 9.6 ትሪሊዮን ብር በመሆን ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል፡፡
ሌላው የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ በዘርፉ የተሠራው የዲጂታል ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ነው። በአጠቃላይ 7.7 ቢሊዮን ብር በዲጂታል ቁጠባ ሂሳብ ተሰብስቧል፡፡ 8.4 ቢሊዮን ብር የሚያህሉ ጥቃቅን ብድሮች ደግሞ በተለመደው የባንክ ሥርዓት ብድር ሊያገኙ ለማይችሉ ዜጎች ተሰጥቷል።
ኢትዮጵያን ለማዘመን በአንድ በኩል ነባር ዐቅሞቿን አውጥቶ የመጠቀም፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለዘመናዊነት በር የሚከፍቱ ተግባራትን የማከናወን ሥራ ተሠርቷል፡፡ በገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነቡት የቱሪስት መዳረሻዎች በተጨማሪ፣ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት በጎርጎራ፣ በወንጪ፣ በሐላላ ኬላና በኮይሻ የቱሪስት መዳረሻዎች ተገንብተው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ በገበታ ለትውልድ ደግሞ በሌሎች ሰባት የሀገሪቱ ክፍሎች እየተገነቡ ናቸው፡፡ ይሄም ነባር ዐቅማችን በማውጣት ተጨማሪ ገቢዎችንና የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር አስችሏል፡፡
የኢትዮጵያን ከተሞች ለዜጎች ምቹ፣ ጤናማና አካታች ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከአዲስ አበባ ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ደርሷል፡፡ በዚህ የዝመና ፕሮጀክት አማካኝነት መሠረተ ልማቶችን የማሟላት፣ ከተሞችን ጽዱና አረንጓዴ የማድረግ፣ በድህነት አኗኗር ውስጥ ላሉ ዜጎች ኢትዮጵያን የሚመጥን የመኖሪያ አካባቢዎችን የመስጠት፣ ሕጻናትና ወጣቶች ከሱስና ከአጉል ሕይወት እንዲርቁ የሚያስችሉ መዋያዎችን የማዘጋጀት፣ ማኅበረሰባዊ ትሥሥርን የሚፈጥሩ ዐደባባዮችንና መስኮችን የመፍጠር ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡
ለውጡ ካዘመናቸው ነገሮች አንዱ የፕሮጀክቶችን የሥራ ባህል ነው፡፡ በቀናት እና በወራት የሚጠናቀቁ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሀገሪቱ እየተፈጠሩ ናቸው፡፡ ከለውጡ በፊት ቆመው እና ተበላሽተው የነበሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችም በልዩ ክትትል እየተጠናቀቁ ይገኛሉ፡፡ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለዚህ ዋነኛው ማሳያ ነው፡፡ የሕዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ በተደረገው ርብርብ የግድቡ ሥራ ከ97.6 ፐርሰንት በላይ ደርሷል፡፡ ግድቡ ትልቅ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ፈጥሯል፡፡ አሁን ላይ አራት ተርባይኖች በድምሩ 1443 ሜ.ዋ ኃይል እንዲያመነጩ ተደርጓል፡፡ ይሄም የብልጽግና ጉዟችንን ማንምና ምንም እንደማያስቀረው ምሳሌ ነው፡፡
የጸጥታና የደኅንነት ተቋማትን ለማዘመን በተሠራው ሥራ ሰብአዊ፣ መዋቅራዊና ቴክኖሎጂያዊ ብቃት ያላቸው የጸጥታና የደኅንነት ተቋማት ተፈጥረዋል፡፡ እነዚህ ተቋማት ሕገ መንግሥቱን ብቻ መሠረት አድርገው ተልዕኳቸውን እንዲያከናውኑ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነጻ ሆነዋል፡፡ የሕግ፣ የአሠራርና የአደረጃጀት ሪፎርም በማድረግ ኢትዮጵያን የሚመጥኑ ተቋማት እንዲሆኑ እየተደረገ ነው፡፡
የመከላከያ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና በመፍጠር የሀገርን ዐቅም እየገነቡ ናቸው፡፡ ለሠራዊታችን የሚያስፈልጓቸውን ትጥቆችና ስንቆች ለማሟላት ዳር ደርሰዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያን ከባንዳና ከባዳ ጠላቶች በአስተማማኝ ሁኔታ መከላከል የሚችሉበት ቁመና ላይ ይገኛሉ፡፡
የኢኮኖሚ ሪፎርም፡ለውጡ እንዲመጣ ከገፉት ሀገራዊ ስብራቶች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት ነው፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱ ሀገሪቱን ከዐቅሟ በላይ ለሆነ ዕዳ የዳረገ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛነፍን ያስከተለ፣ የዋጋ ውድነትንና ግሽበትን ያመጣ ስብራት ነው፡፡ ይሄንን ስብራት ለመጠገን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በመዘርጋት ሁሉን አቀፍ ሥራ ተሠርቷል፡፡ በዚህ ማሻሻያ አማካኝነትም የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም፣ ሀገራዊ ገቢን በሀገራዊ ምርት ልክ የማድረግ ሪፎርም፣ ምርትና ምርታማነትን የመጨመር ሪፎርም፣ የባንኮች የውጭ ምንዛሬን ከሌሎች ገበያዎች ጋር የማጣጣም ሪፎርም፣ የዕዳ ቅነሳና ሽግሽግ የማድረግ ሪፎርም፣ የመንግሥትን የመበደር ሁኔታና መጠን የማስተካከል ሪፎርም፣ ተከናውነዋል፡፡
በዚህም ከዓለም አቀፍ ተቋማት የምናገኘው ብድርና ድጋፍ ጨምሯል፡፡ የዕዳ ሽግሽግና ቅነሳ ውይይቶች ወደ ውጤት ቀርበዋል፡፡ የሀገራችን የውጭ ምንዛሬ ክምችት አድጓል፡፡ የሀገር ውስጥ ገቢን የማሰባሰብ ዐቅማችን ከፍ ብሏል፡፡
የፖለቲካ ተሳትፎ፡ በለውጡ ዘመን ከተለወጡት ባህሎች አንዱ የፖለቲካ ተሳትፎ ባህል ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሕጋዊና ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ማንኛውንም ዓይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ለማድረግ አይከለከልም፡፡ ከገዥው ፓርቲ የተለየ የፖለቲካ አደረጃጀትም በተፎካካሪነት እንጂ በጠላትነት አይታይም፡፡ በዚህም የተነሣ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮች በፌዴራልና በክልል የአመራርነት ቦታ ላይ ተመድበዋል፡፡ ይሄ ለኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ባህል ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የክልል ፕሬዚዳንቶች ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በየጊዜው ይመካከራሉ፡፡ በሀገር ዕቅዶች፣ በአፈጻጸሞችና በዋና ዋና የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ይደረጋል፡፡ ይሄም የሠለጠነ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት መንገድ እየጠረገ ነው፡፡
#ባሌ #አርሲ የግብርና ስራችን በውጤታማነት ቀጥሏል
Gareen miidiyaa daawwannaa hojii qonnaaf godina Baaleefi Arsiitti bobba'an Oomishni yeroo ammaa jiru imalli birmadummaa nyaataa mirkanaa’aa jiraachuu agarsiiftuu ta'uu ibsan.
Oomishni Qonna Gannaan Godina Arsii fi Baaleetti oomishamaa jiru imalli birmadummaa nyaataa Itiyoophiyaa mirkanaa’aa jiraachuu agarsiiftuu ta'uu Tajaajilli Kominikeeshinii Mootummaa beeksise.
Deeggarsi mootummaan qonnaan bultootaaf taasise Badhaadhina gamhedduu Itiyoophiyaan eegalte mirkanaa’aa jiraachuu mul’iftuu ta’uu Ministir Deetaan Ministira Tajaajila Kominikeeshinii Mootummaa Obbo Kabbadaa Deessisaan ibsaniiru.
Garbuu fi Qamadiin Godina Baalee fi Arsiitti oomishamaa jiran fakkeenya ta’uu himaniiru.
Birmadummaa nyaataa mirkaneessuuf hojiilee bu’aa qabeessa ta’anirratti xiyyeeffachuun hojjetamaa jiraachuu kaasaniiru.
Miidiyaaleen Muuxannoo gaarii kana babal’isuurratti hojjechuu akka qaban hubachiisaniiru.
#Oromia
#Ethiopia
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት የተከበሩ ሳልቫኪር ማያርዲት ለክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል አበረከቱ፡፡
የተበረከተላቸው የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል የሁለቱን ሀገራት የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት በማጠናከር፣ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በመከላከል እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ሪፎርም ሂደትን በመደገፍ የአገልግሎቱን ከፍተኛ መኮንኖች አቅም ለመገንባት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰጡት የትምህርትና ስልጠና እድሎች አስተዋፆ መሆኑን ተገልጿል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱም ላይ የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አምባሳደር ቾል ማውትን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ነቢል መሀዲ እና የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል ክቡር አተም ማሮል ተገኝተዋል ፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አሁን ያለው የኢትዮጵያ እውነት ፈጣን እድገት እንጂ ሚሊዮኖች የሚያልቁበት የረሀብ ታሪክ አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ህዳር 17/2017(ኢዜአ)፦ አሁን ያለው የኢትዮጵያ እውነት በአርአያነት የሚጠቀስ ፈጣን እድገት እንጂ ሚሊዮኖች የሚያልቁበት የረሀብ ታሪክ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
በኢትዮጵያ በ1977ቱ ድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ተቀንቅኖ ድጋፍ የተሰበሰበበት Do they know its Christmas? መዚቃ አሁን ላይ ዳግም መለቀቁ የኢትዮጵያን አሁናዊ የልማት ጉዞ ያላገናዘበ ገጽታን የሚያበላሽ ተረክ መሆኑንም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በ1977 የተከሰተው ድርቅ ያስከተለውን ሰፊ ጉዳት ተከትሎ አይርላንዳዊው ሙዚቀኛ ቦብ ጊልዶፍና መሰል እውቅ ሙዚቀኞች ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል Do they know its Christmas? የሚል ሙዚቃ አቀንቅነው ከፍተኛ ድጋፍ አሰባስበዋል።
የዚህ የሙዚቃ 40ኛ ዓመት ዘንድሮ የተከበረ ሲሆን በወቅቱ የተሰራው ሙዚቃ ዳግም ተለቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሙዚቃው 40ኛ ዓመት ሲዘከር ሙዚቃው ዳግም እንዲለቀቅ መደረጉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መናገራቸውን "ዘ ታይምስ" የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ሙዚቃው ላይ እንደተገለጸችው ሳይሆን በፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ መሆኗን ገልጸዋል።
ሙዚቀኞቹ በወቅቱ የሰሩት ሥራ የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም ሙዚቃው ዛሬ ላይ ከጊዜው ጋር አብሮ አለመሄዱ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሙዚቃው የኢትዮጵያን አሁናዊ ሁኔታ ያቃለለና ሰዋዊነትን ዝቅ የሚያደርግ ተረክ የያዘ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ያለ የኢኮኖሚ ባለቤት፣ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎቿ ከሚጎበኙ ሥፍራዎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን እንዲሁም በአፍሪካ ትልቁን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እየገነባች ያለች ሀገር ሆና ብትታወቅ ይጠቅም ነበር ብለዋል።
ሙዚቃው አሁን እኛ ለምንፈልገው ኢንቨስትመንት የሚጠቅም አይደለም፤ ድርቅ አሁን ላይ እኛን አንደ አህጉርም እንደ ሀገርም አይገልጸንም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ በረሃብ ልትታወቅ አትችልም ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንፆት ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እና በሌሎች መስኮች እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ዳግም ረሃብ እንዳይፈጠር የሚያደርጉ መሆናቸውንም ጠቅሰል።
ኢትዮጵያ በስንዴ ራሷን ችላለች፤ ሌሎች ምርቶችንም በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት አቅም ፈጥራለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ በአፍሪካ ሊጠቀስ የሚችል የግብርና ዘርፍ አብዮት እያካሄደች መሆኑንም ነው ጠቀላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተናገሩት።
ይህ ሙዚቃ የተለያዩ ወቀሳዎች እየደረሰበት መሆኑንም "ዘ ታይምስ" ጋዜጣ በዘገባው አስነብቧል።
ሙዚቃው አንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 እንደ አዲስ ሲሰራ እውቁ እንግሊዛዊ ኢድ ሺራን በሙዚቃው ከተሳተፉ አርቲስቶች መካከል አንዱ ነበር።
ይሁንና አሁን ላይ ሙዚቃው የአፍሪካን ወቅታዊ ሁኔታ እንደማይገልጽ በሚሰነዘርበት ወቀሳ በወቅቱ በሙዚቃው ተሳትፎ ባላደርኩ እስከማለት መደርሱም በዘገባው ተጠቅሷል።
በመድረክ ስሙ ፉስ ኦ ዲ ጂ የተሰኘው የጋና ሙዚቀኛ፤ ሙዚቃው የተጠቀማቸው የግጥም ስንኞች አፍሪካን በተመለከተ አሉታዊ መልዕክት እንዳላቸው ገልጿል።
ይህም የአፍሪካን ልማት፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት አድገት ያቀጭጨዋል ነው ያለው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለትግራይ ክልል 200 አምቡላንሶች ድጋፍ መደረጉን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ
ለትግራይ ክልል 200 አምቡላንሶች ግዢ ተፈፅሞ ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ላይ እንደሚገኙና የተወሰኑትም አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ገልጿል።
ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ፣ ዲፕሎማሲና የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ መስፍን ደረጄ፤ "የተገዙት አምቡላንሶች ከዚህ በፊት በጦርነቱ ምክንያት የወደሙትን 200 የሚደርሱ አምቡላንሶች የሚተኩ ናቸው" ብለዋል።
በግጭቱ ምክንያት እንደ ቀይ መስቀል ማኅበር ብቻም ሳይሆን አጠቃላይ የአምቡላንስ አገልግሎት ያቆመበት ጊዜ እንደነበር ጠቅሰው፤ "በርካታ የሕብረተሰብ ክፍል በችግር ውስጥ ነበር፤ አሁን ላይ ያንን ችግር ለመቅረፍ አምቡላንሶች ገብተዋል" ብለዋል።
የአምቡላንሶች ግዢ የተፈፀመውም በአንድ የአሜሪካ ባለሀብት በኩል መሆኑን አክለዋል። "ባሳለፍነው ዓመት ከ500 በላይ አምቡላንሶች በመላው ሀገሪቱ ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር" ብለዋል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበርና እህት ማኅበራት አማካኝነትም በሁሉም ክልሎች አምቡላንሶች እንደተከፋፈሉ ያስታወሱት ኃላፊው፤ በቅርብ ጊዜም ሀያ አምቡላንሶች ግዢ ተፈፅሞ ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሚኒኬሽን ኃፊው "የያዝነውን ዓመት ጨምሮ ባሳለፍነው ዓመት በግጭትና በድርቅ የተጎዱና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና ከአደጋ ስጋት ለማላቀቅ ሰፊ ሥራና ርብርብ ተደርጎ አመርቂ ውጤት አስገኝቷል" ብለዋል።
ማሕበሩ በእንግሊዝና በአሜሪካ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለግጭት፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ የተጋለጡ አካባቢዎች ተለይተው በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤንሻንጉል ክልሎች የጤና ምርመራ ድጋፍ እያከፋፈለ እንደሚገኝ አክለዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ብልፅግና ከፍተኛ የለውጥ መሻት ያለው ፓርቲ በመሆኑ የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓሉ አከባበርም ከሰራው በላይ ለመስራት አጋዥ ነው" - አቶ ሞገስ ባልቻ
ብልፅግና ከፍተኛ የለውጥ መሻት ያለው ፓርቲ በመሆኑ የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓሉ አከባበርም ከሰራው በላይ ለመስራት አጋዥ ነው ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡
"በሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች በድምቀት የተከበረው የብልፅግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል የታለመለትን ተልዕኮ ማሳካቱ ተመላክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር የበዓሉን አከባበር በገመገሙበት ወቅት እንደተናገሩት በታላላቅ ስኬቶችና በአጓጊ ተስፋዎች ታጅቦ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው ፓርቲያችን የበዓሉ አከባበርም ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅና የታለመለትን ግብ ያሳካ መሆኑን ገልፀዋል።
የአሻጋሪ እሳቤዎች ባለቤት የሆነው ብልፅግና ከፍተኛ የለውጥ መሻት ያለው ፓርቲ ነው ያሉት አቶ ሞገስ የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓሉ አከባበርም ከሰራው በላይ ለመስራት አጋዥ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አመራሩ፣ አባላት፣ ደጋፊዎች እና መዋቅሮች በተቀናጀ መልኩ ለበዓሉ ስኬት የድርሻቸውን መወጣታቸውን ያመሰገኑት ሀላፊው የተፈጠረውን መነሳሳት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለበዓሉ ስኬታማነት የተደራጁ ዓብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ዕቅዶቻቸውን በማውጣት እና የጋራ በማድረግ በተቀናጀ መልኩ መከወናቸው በቀረበው ሪፖርት የተገለፀ ሲሆን ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሀይምኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙባቸው የውይይት መድረኮች በየደረጃው መደረጋቸው ተጠቅሷል።
የፓናል ውይይቶች፣ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች፣ የጥያቄና መልስ ውድድር፣ የእግር ኳስ ውድድሮች፣ የፎቶ ኢግዚቪሺኖች እንዲሁም ቤት እድሳት፣ ደም ልገሳ፣ ማዕድ ማጋራት፣ የትራፊክ አገልግሎት እና የመሳሰሉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችም በዓሉንም በማስመልከት መከናወናቸውም ተገልጿል።
በመልዕክቶች፣ በዘገባዎች እንዲሁም በዶክሜንተሪዎች አሰባሳቢውን የብሔራዊነት ገዥ ትርክት ለማስረፅ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የበዓሉ አከባበር የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በአግባቡ ለመጠቀም ሊጎለብት የሚገባው አበረታች ጥረት መደረጉም ተወስቷል።
የበዓል ዝግጅቱ የታለመለትን ዓላማ በማሳካቱ ትምህርት የተወሰደበት መሆኑ የተመላከተ ሲሆን በተለያየ አግባብ የድርሻቸውን ለተወጡት ሁሉ ምስጋና መቅረቡን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ 15 ሺህ የአሜሪካ ጦር አባል ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ተገለጸ‼️
ከአንድ ወር በፊት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ጥር አጋማሽ ላይ ስልጣን የሚይዙ ሲሆን ካቢኔያቸውን ከወዲሁ እያዋቀሩ ነው።
የፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጁ ፔቴ ሄግሴትን የመከላከያ ሚንስትር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።
ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው የሚያምኑት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ታይምስን ዋቢ አል አይን አስነብቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።
ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውት ነበር።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና
5ኛ አመት የብልፅግና ፖርቲ የምስረታ በዓል የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዳዋ መታሰቢያ ሙዚየም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ነገ ጠዋት በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ክፍለ ከተማችን እንደ ተለመደው የነቃ እና የደመቀ ተሳትፎ ያደርጋል" - አቶ ዮናስ ስዩም - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
ነገ ጠዋት ከ 12:00 ጀምሮ በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ይከናወናል።
ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቡ በሚሳተፍበት በዚህ ፕሮግራም ላይ ክፍለ ከተማችን አዲስ ከተማ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ የነገዋን ወጋገን እየጠበቀ እንደሚገኝ የክፍለ ከተማችን ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ዮናስ ስዩም ገለፁ።
የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮናስ ስዩም "ነገ ጠዋት በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ክፍለ ከተማችን እንደ ተለመደው የነቃ እና የደመቀ ተሳትፎ ያደርጋል። ለዚህም አስፈላጊ ዝግጅት ሁሉ ከወዲሁ ተጠናቋል" በማለት ክፍለ ከተማችን የነገ የከተማ አቀፍ ፕሮግራም ድምቀትና ውበት እንደሚሆን ሃሳባቸውን አካፍለውናል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ መቐለ ከተማ ገቡ
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ የተመራ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ መቐለ ከተማ መግባቱ ተሰምቷል።
ልኡኩ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ በትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት ትናንት ትግበራውን የተጀመረው የዲሞቢላይዜሽን ሂደት ይታዘባል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪ ልኡኩ ግንባታው 40 በመቶ የደረሰውንና የገበታ ለሀገር አካል የሆነውን የገርዓልታ ፕሮጄክትንም ተመልክቷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።
ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።
Before officially inaugurating ‘Quality Village ‘today, I had the opportunity yesterday to visit and review the National Quality Infrastructure we have developed.
This critical institution is designed to catalyze the competitiveness of our local products in global markets and enhance our participation in global value chains.
As one of our leading national institutions, it will play a vital role in strengthening our export capabilities and ensuring we remain competitive in the international arena.
Via - Dr. Abiy Ahmed Ali - FDRE PM
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ ትውልድ ግንባታ አስፈላጊ ነው። በባህር ዳር ቆይታችን በግዙፉ ስቴዲየም ቅጥር ግቢ ውስጥ ኳስ ተጫውተናል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የገበያ ማረጋጋት የጋራ ግብረ-ሃይል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ በመወያየት የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የጋራ ግብረሃይሉ ሰብሳቢ ወ/ሮ አይዳ አወል የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተከፈቱ እሁድ ገበያዎች በማቅረብ ሸማቹ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም የእህድ ገበያን በማጠናከር እንዲሁም ምርቶችን በስፋት በማስገባት የተረጋጋ ገበያ እንዲፈጠር መስራት እንደሚገባ የጋራ ግብረሃይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉትን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ ይመዝገቡ፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹