prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1352

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የተከፈተው የሠላም በር 👆👆👆

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

🤔 የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ቢትኮይን ወደ 1 ሚሊዮን ዶላር ያድጋል ሲል ተደምጧል 🤔

አባቱ አሜሪካን የአለም ክሪፕቶ ዋና ከተማ እንደሚያደርጋት ያምናል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Nageenya keenya, aadaa fi duudhaa keenyaan!

Aadaa fi duudhaaleen bu’uura sirna gadaa ta’an lammiilee gidduutti tokkummaa fi jaalala cimsuudhaan gamatti nageenya waaraa mirkaneessuuf shoora guddaa ta’e qabu.

Rakkoolee jiran marii fi marabbaadhaan furuu, nageeya labsuu fi waliin jirrenya jabeessuudhaan qormaatilee imala keenyaa ta’an hundaaf furmaata kaa’uuf aadaa fi duudhaalee gaarii qabnutti qixaan gargaaramuun murteessaadha.

Misooma biyyaa dhugoomsuu fi galmoota imala badhaadhinaa fiixaan baasuudhaaf bu’uura kan ta’e nageenyi, qabeenya waloo tumsaa fi hirmaannaa lammii hundaa gaafatudha.

Rakkoolee nageenyaa kallattii garaa garaatiin mul’atan bu’uuraan furuudhaan nagaa waaraa bu’uuressuudhaaf qaama biraa eeggachuu caalaa, duudhaalee gaggaarii furtuu rakkoolee maraa ta’an waan qabnuuf isaanitti qixaan dhimma bahuu fi hojiirra oolchuun barbaachisaadha.

Aadaa fi duudhaalee keenyaan nageenya keenya waaressuuf jalqabbiiwwan gaarii eegalaman caalmaatti itti fufsiisuudhaan mul’ata qabanne galmaan gahuuf gahee nurraa eegamu haa bahannu.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የፌደራል እና የክልሉ የአመራሮች ቡድን በምስራቅ ባሌ የልማት ሥራዎችን እየጎበኘ ነው፡፡

ቡድኑ ጉብኝቱን የጀመረው በዳዌ ቃቸን ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን የዌብ ግድብ ፕሮጀክት በመመልከት ነው፡፡

የአመራሮቹ ቡድን በምስራቅ ባሌ እየተከናወኑ የሚገኙ የግብርና እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በከተማችን የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንስ እና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊና የተሟላ ዲጂታል የሲቪል ምዝገባ ስርዓት የሚተካ ፣ ለነዋሪዎች ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ለሀገራችን ሞዴል የሆነ ስራ እየሰራን እንገኛለን።

የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ ምዝገባን፤ የነዋሪነት መታወቂያ አሰጣጥን፤ ሰነድ ማመሳከር እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ ዲጂታል አገልግሎት በመተካትና ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ 132 የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በካሜራ ቁጥጥር ስርዓት የተሸፈኑ በማድረግ የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የመታወቂያ፣ ሰነድ ማመሳከር እና ተያያዥ የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች በየእለቱ በየወረዳው በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት፣ ከማዕከል አገልግሎት አሰጣጡን መከታተል እና በየሰአቱ እና በየዕለቱ ምን ያህል አገልግሎት እንደተሰጠ ወዲያዉ ያለምንም ሪፓርት ማወቅ የተቻለበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።

የተቋሙን ሰራተኞች የተቋሙ ሰራተኛ በመምሰል ከሚያጭበረብሩ እና ከደላላዎች መለየት እንዲቻል ሁሉም የደንብ ልብስ እና መለያ ባጅ እንዲኖራቸው በማድረግ ከአሰራር በተጨማሪ ሰራተኛዉን መለየት እንዲቻል ግልፅነትን ጨምረናል።

ለነዋሪዎቻችን በማዕከሉ ከሚሰጡ አገልግሎቶች በተጨማሪ የሰርግና የልደት ፕሮግራሞቻቸውን በጊቢው ውስጥ እንዲያከናውኑ የቀድሞው ሸገር መናፈሻ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ተደርጓል። በትላልቅ ፓርኮች እና የመዝናኛ ቦታዎች ከፍለው ይህን አገልግሎት ማግኘት የማይችሉ ነዋሪዎቻችን በዚህ ጊቢ እና በቅርንጫፎቹ በተዘጋጁ የሰርግና የልደት ማክበሪያ ቦታዎች ፣ የቁሳቁሶች እና የፎቶግራፍ ግልጋሎት ጭምር እንዲያገኙ በማድረግ ፍትሃዊነትን እያረጋገጥን እንገኛለን።

በተጨማሪም በአሁኑ ሰዓት የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎትን በዋና መስሪያ ቤትም ሆነ በየቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ እና ሰፋፊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ተቋማት ነዋሪዎችን በመመዝገብ ላይ እንገኛለን። በዚህ አጋጣሚ የብሄራዊ መታወቂያ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ሁላችሁም ምዝገባችሁን እንድታጠናክሩ ጥሪ አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

Via - አዴ አዳነች አቤቤ
የከተማችን አዲስ አበባ ከንቲባ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳዳር ሆነው መሾማቸውን መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Nageenya, Bu’uura Jiruu fi Jireenyaa!
Imalli jiruu fi jireenyaa ilmi namaa guyyaa guyyaatti taasisu, sochiin siyaasaa, diinagdee fi hawaasummaa sadarkaa hundatti gaggeeffamu nageenya bu’uureffateeti.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከጃል ሰኚ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ  ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በምሕጻረ ቃል IYF ከዓለም አቀፉ ወጣቶች ፊሎሺፕ እና ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር የተቀየረ የወጣቶች የስራ ባህል ለብልጽግና በሚል መሪ ቃል የማይንድ ሴት ስልጠና ሰጠ

ወጣቶችን በምግባር ለማነጽና የስራ ባህልን ለማዳበር ተሞክሮን መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሃና የነገ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጠብቀው አመሸ በበኩላቸው ወጣቶች ባገኙት ስልጠና ራሳቸውን እና አገር ለመለወጥ እንዲሰሩ አሳስበው እንዲህ አይነት ስልጠናዎች የአመለካከት ለዉጥ ለማምጣት አዎንታዊ ተፅእኖ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ስልጠናውን የሰጠው የIYM ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ናም ድርጅቱ በመላው ኢትዮጵያ በመንቀሳቀስ ወጣቶች በስራ እንዲጠነክሩ በስፓርት አካላቸው እንዲዳብር ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ማከናወናቸውን አስታውሰው የማይንድ ሴት ስልጠና ጥቅም፣ የስራ ባህል ራስህን መገንባት፣ የህይወታ መርህ ትምህርትና ጥበብ ላይ ስራና ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል

መቀመጫውን ኮርያ ካደረገው ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተሰጠው የማይንድ ሴት ስልጠና ላይ ከ1500 በላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች መሳተፋቸው ተመልክቷል

ቢሮው በቅርቡ ከአይ.ዋይ.ኤፍ ጋር
የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁለትዮሽ የስምምነት ፊርማ ማድረጉ ይታወሳል።

ቢሮው በንቃተ ህሊና ላይ ለወጣቶች የሚሰጠው ስልጠናው በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚካሄድ የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በመዲናችን አዲስ አበባ ህገ ወጥነትን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የተቋቋመዉ የገበያ ማረጋጋት እና ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ-ሀይል ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ ሴክተር ተቋማትና አመራሮች ጋር እቅድ አፈፃፀሙን ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ ።

ግብረ ኃይሉም በመሠረታዊነት በምርት አቅርቦትና ስርጭት ፣ የገቢ ምንጭ ማስፋትና ገቢ መሰብሰብ፣ የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና የህግ ማስከበር ስርዓት እንዲሁም የመረጃ ተደራሽነት ላይ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል ።

በግምገማዊ ዉይይቱም ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ዋና ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት ከቀረበዉ ሪፖርትና ከቀረበዉ አስተያየት በመነሳት እንደተናገሩት ግብረሁይሉ የተደራጀዉ ችግሮችን እንዲፈተና አቅጣጫ እያስቀመጠ እንዲመራ መሆኑን ጠቁመዉ በዚህ ረገድ ተስፋ ሰጪ ዉጤቶች ማስመዝገብ ቢቻልም ስራዉ የአመራሩን ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ይበልጥ በየደረጃዉ ስራዉ እየተገመገመ ፖለቲካዊ ዉሳኔ አየተሠጠ መመራት አለበት ብለዋል ።

በከተማዋ ከማዕከል እስከ ወረዳ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በገበያ ማእከላት፣በእሁድና በቅዳሜ ገበያ፣በመጋዘን ክምችት፣ከክልሎች እና ከአጎራባች ከተሞች ያለዉ የግብይት ስርዓት እንዲሁም በአምራች በአቅራቢና በሸማቹ መካከል ያለዉ የግብይት ሠንሠለት አፈፃፀሙ የተሻለ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ የገበያ ማዐከላትን በመደገፍና በመቆጣጠር እንዲሁም እድሳት በማድረግ ያልገቡትን ወደ ስራ ማስገባት ፣የእሁድና የቅዳሜ ገበያ ቦታዎችን በማስፋፋትና፣በልማት የተያዙ የገበያ ቦታዎች ምትክ በመስጠት ፣አምራች አቅራቢና ሸማችን በማስተሳሰር ፣ተኪ ምርቶችን በማሳደግ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር መሥራትና በዘይትና በስኳር ላይ ችግሩን ለይቶ አስተማሪ እርምጃ መዉሰድ ይገባል ብለዋል።

የገቢ ምንጭ ከማስፋትና ገቢ ከመሠብሠብ ረገድ በበጀት ዓመቱ የንቅናቄ መድረክ ፈጥሮ በማወያየት የጋራ መግባባት ከመፍጠር፣ፀጋዎቻችንን ከመለየትና ምንጮቻችን ከማስፋት፣እስከ ብሎክ ወርዶ ነጋዴውን ወደ ህግ ስርዓት ከማስገባት ፣በህጋዊ ደረሰኝ ግብይት እንዲፈፀም ከማድረግ እንዲሁም ክትትልና ቁጥጥር ስርዓትን ከማጠናከር የተሰራዉ ስራና በዚህም የእቅዳችንን 84.72 በመቶ በመፈፀም ገቢ መሠብሰብ መቻሉ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አክለዉም ከዚህ በተሻለ ገቢያችንን አሳድገን ትላልቅ የልማት ስራዎቻችንን ለማሳካት በየደረጃዉ ተቋማት አሰራራቸዉን መፈተሽ ችግራቸዉን ማረም ፣መሠረታዊ ንቅናቄ አሰከ ወረዳ ፈጥሮ ግንዛቤ መፍጠር፣ህጋዊ ስርዕት ማስያዝና የተቀራረበ አፈፃፀም እንዲኖር ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ሲሉ ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ እንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ዋና ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።

ግብረ ኃይሉና አመራሩ ከነጋዴዉ ማህበረሰብና ከሌሎች አካላት ጋር በመቀናጀት ያለደረሰኝ የሚነግዱ፣ንግድ ፍቃድ የሌላቸዉ፣ ምርት በመጋዘን የሚደብቁ ፣ዋጋ የሚጨምሩ፣አሳቻ ሠዓት ጠብቀዉ ህገወጥ ግብይት በሚፈፅሙት ላይ የወሰዳቸዉ ህጋዊ እርምጃዎች ህግን ከማስከበር አኳያ የተሻለ ለዉጥ መምጣቱን ገልፀዉ አሁንም ማስተማርን ቀዳሚ ተግባር አድርገን ከዚህ ባለፈ ህግና ስርዓትን የተከተለ ጤናማ የግብይት ስርዓት በዘላቂነት እንዲኖር ህጋዊ እርምጃዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ግብረሀይሉ ስምሪቱን በሽፍት በመጠቀም ቀን ከሌት በትጋትና በቁርጠኝነት ደንብና አሠራርን ጠብቀን መስራት ይጠበቅብናልም ብለዋል።

ለንግዱ ማህበረሰብ እና ለሸማቹ ወቅታዊ የግብይት ስርዓቱን አስመልክቶ በመደበኛና በማህበራዊ ሚዲያ እንዲሁም ህትመት ዉጤቶችን በመጠቀም መረጃን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ የንግድ እንቅስቃሴ ወጥ በሆነ መንገድ ለህብረተሰቡ መረጃ የመስጠት እና በዘርፉ ምሁራኖች የሚሳተፉበትና ህብረተሰቡ ሀሳቡን የሚገልፅበት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት የመማማሪያ የዉይይት ፕሮግራም እንዲኖር ማድረግ ለስራችን ስኬት ቁልፍ መሳሪያ ነዉ ብለዊል ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ እንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ኃይሉ ዋና ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊና የግብረ ኃይሉ ምክትል ሰብሳቢ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር) በበኩላቸው ግብረሀይሉ ከስራ አስፈጻሚ ጋር በቅንጅት መስራቱ ፣ የግንዛቤ መፍጠር ስራ በንቅናቄ መታጀቡ፣ህግ በተቀናጀ አግባብ የማስፈነና አማራጭ የገቢ ምንጮችን በመጠቀምና የገቢ ስርዓትን በማዘመን ገቢን እለት እለት ማሳደግ መቻሉ እና መርካቶ ላይ ወደ ህጋዊ ስርዓት የመግባት ጅምር ዉጤት ያመጣንባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል ።

አክለዉም እነዚህን ተስፋ ሰጪ ጅምር ስራዎች በአደረጃጀትና በአሰራር በማጠናከር ህገ ወጥ ንግድን በሕጋዊ የንግድ ስርዓት መተካትን ጨምሮ በዘላቂነት ገበያ የማረጋጋት ዝርዝር ተግባራትን ግብር -ኃይሉ በዕቅድ እየተከታተለ እንዲፈፅም በማለት ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች በመድረኩ ማብራሪያና ምላሽ መስጠቱና የጋራ ዉሳኔ በሚያስፈልጋቸዉ የበላይ አመራሩ ተወያይቶ አስቸኳይ መፍትሔ እንደሚሰጥባቸዉ በመግባባት በቀጣይም በተቀመጠዉ የጋራ አቅጣጫ መሠረት ግምገማዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በማጠቃለያ ጥሩ አፈፃፀም ያመጡትን ተቋማት እዉቅና መስጠት እንደሚገባና የአፈፃፀም ዉስንነት ያለባቸዉ ችግራቸዉን ገወምግመዉ በማረም ለቀጣይ የተሻለና የተቀራረበ አፈፃፀም እንዲኖር ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሩድ ቫን ኔስትሮይ በሀላፊነት ተሾመ !

በቅርቡ አሰልጣኝ ሴቲቭ ኩፐርን ያሰናበተው ሌስተር ሲቲ አዲስ አሰልጣኝ በሃላፊነት መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ሌስተር ሲቲ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ሌስተር ሲቲን በአሰልጣኝነት በመረከቡ መደሰቱን እና መኩራቱን ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይ ሌስተር ሲቲ ማክሰኞ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ቡድኑን በመምራት ስራውን የሚጀምር ይሆናል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ ጠዋት የአውሮፓ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጂያን-ኖኤል ባሮትን በሁለቱ ሀገሮቻችን ባሉ ትስስሮች ላይ ለመነጋገር በጽህፈት ቤታችን ተቀብያለሁ።

Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በብርቱው መሪ የኢትዮጵያ ዕዳ ወደ ምንዳ የተቀየረበት አምስት አመታት
#ዐብይ_አህመድ
#አምስት_የስኬት_አመታት
#አሻጋሪ_ፓርቲ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ

@AbiyAhmedAli 🙏🙏🙏

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ወርቁ ሰው ሀገራችንን ወርቅ አድርጎልናል!
#ዐብይ_አህመድ
#አምስት_የስኬት_አመታት
#አሻጋሪ_ፓርቲ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ

@AbiyAhmedAli 🙏🙏🙏

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ Abiy Ahmed Ali (phd) መልዕክት #ቢሾፍቱ ከሚገኘው አየር ኃይል ግቢ ... 👆

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የቀድሞዋ ካዛንችስ ወደ አዲስ ገፅታ ጉዞ …

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

9 የመንግስት ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እና የደህንነት ስራን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ። የትብብር ስምምነቱ ብሄራዊ ደህንነትን ብሎም ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ እንደሆነ ተመላክቷል።

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች ጊዜ ቆጣቢና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ትራንዚት የሚያደርጉ ተጓዦች እግረ መንገዳቸውን በኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ እና ሰዉ ሰራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ዕድል ይፈጠራልም ተብሏል።

ኢትዮጵያ ያላትን ድንበር በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ በመጠበቅ ህገወጦች በአንድ የትራንስፖርት አማራጭ ገብተው በሌላ አማራጭ እንዳሻቸው መውጣት እንዳይችሉ በማድረግ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ቅንጅታዊ አሰራርን እንደሚፈጠርም ተጠቁሟል።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር፣ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ኢንፎርሜሽን እና መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬይሽን ባለስልጣን፣ አርቲሻል ኢንተለንጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናቸው ስምምነቱን የፈረሙት።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ክፍት የሆኑ የማንሆል ክዳኖች እየተጠገኑ ነው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአስፋልት መንገድ ጥገና ስራ ጎን ለጎን በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሆል ክዳኖች በመለየት የጥገና ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ አስኮ፣ አዲስ ሰፈር፣ ብርጭቆ ኮንደሚኒየም እና ከኮልፌ 18 መዝናኛ በኢትዮ ጠቢብ እስከ ኪዊንስ ሱፐር ማርኬትአካባቢ የሚገኙ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተጎዱና ክፍት የሆኑ የውሃ መፋሰሻ መስመር ክዳኖች ተጠግነዋል፡፡

የጥገና ሰራው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑትን ሙሉ በሙሉ በአዲስ የመተካት እና እድሳት የሚያስፈልጋቸውን ደግሞ መልሶ በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡

በቀጣይም ክፍት የሆኑ እና በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሆል ክዳኖች የመጠገንና የመቀየር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የማንሆል ክዳን የድሬኔጅ መስመሮች የዝናብ ውሃን በአግባቡ እንዲያስተናግዱ እና የመዲናዋ ጎዳናዎች ውብና ጽዱ ሆነው ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል በመሆኑ ሕብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆነውን መንገድ እና የመንገድ አካላትን በባለቤትነት ስሜት ከጉዳት እንዲጠብቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

''ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን ከፍተኛ ቡና አምራች ሀገር ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ስራዎች ዓመታዊ የቡና ምርት መጠንን ከነበረበት 500 ሺህ ቶን በእጥፍ ማሳደግ ተችሏል።

ከገቢ አንጻርም በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፤ በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ ይህን አሃዝ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው።

እስካሁን ባለው ሂደትም እቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ አበረታች ውጤቶች ከወዲሁ እየተመዘገቡ ነው።

ዘመናዊ የቡና መስኖ ልማትና በማሽን የታገዘ የቡና ለቀማ በማካሄድ በሄክታር እስከ 60 ኩንታል ማግኘት መቻሉ ደግሞ ለዚሁ ስኬት ጥሩ ማሳያ ነው።'' - ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከዩኔስኮ መቀበሏ ተገለጸ።

በኒው ደልሂ በተካሄደው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በባህል ቅርስነት ያስመዘገበችውን የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሐምሌ 24 ቀን 2016 መመዝገቡ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ  ኢትዮጵያ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዳይሬክተር ከሆኑት ሚስተር ላዛሬ ኤሎውዶ አሶሞ ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት መረከቧን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ካወጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Araarri Bu’uura Nageenya Waaraati!

Biyya kamuu keessatti, haala kamuu keessatti, bal’ina keessattis ta’ee dhiphina keessatti wal dhibdeen yadaa yeroo kamuu uumamuu danda'a garuu, wal dhibdee uumamu kamuu karaa nagaan ilaafi ilaameen, mariifi marabbaan hiikuun  dandeettii ogummaa addaa kan barbaadu ta'us, ulfoo guddaa waaqaafi nama biratti jaalatamudha. Biyya keenyattis ta’ee akka waliigalaatti malaafi falli guddaan wal dhibdee ittiin furamu inni guddaafi hangafaa  wal mufannaa jiru karaa nagaa araaraan furuudha.

Nagaafi araara uumaafi uumamatu jaalata waan ta'eef araarri bu’uun immoo nageenya waaressa, tasgabbii gabbisa, amantummaa jabeessuun hariiroo waloo cimsee irree tokkummaatti humna guddaa kan horuufi misooma biyyaa saffisiisuun guddina diinagdee biyyaa mirkaneessa. Kanaaf ammoo wal hubannaan uumamee ulaa nagaa banaa taasisuun fedhii nageenyaaf qabnu gabbisuun barbaachisaadha.

Haaluma kanaan biyya keenya keessattis walitti bu’insi kallattii garagaraan mudachaa turuun Kan yaadatamu ta'us, Mootummaan naannoo Oromiyaa rakkoo wal dhibdee yaadaan mudatu karaa aadaafi duudhaa oromummaan fala akka argatuuf daandii deemuun barbaachisu hunda deemuun rakkoo jiru mariifi marabbaan hiikuuf yeroo yeroon waamicha karaa nagaa taasisaa tureeraa.

Harki nagaaf direere yeroo kamuu kan hin dachaaneefi balballi nagaa simachuuf baname kan hin cufamne ta’uu irra deddeebiin ibsaa kan ture yoo ta'u, uummanni keenyas hawwiifi dheebuu nageenyaf qaburraa ka’uun gamtaan alatti ba'ee, sangaa camadee, Farda lugaamee, daa’ima baatee, deessuu qabatee waamicha nagaa qaama hundaaf taasiseera.

Kanumaan wal qabatee waliigalteen  araaraa guyyaa kaleessaa mootummaa Naannoo Oromiyaafi Qondaaltota WBO gidduutti taasiifame guddummaa uummata Oromoo kan mul’isee, aadaaf dhuudhaa sirna Gadaa kan calaqqisiiseefi uummanni Oromoo rakkoo kamuu mariifi marabbaan hiikkachuu akka danda’u kan mirkaneessedha.

Waliigalteen taasifame Mootummaan  garaagarummaa siyaasaa madda rakkoo nageenyaafi gaagga’amaa ture ilaafi ilaameen marii karaa nagaan hiikuuf kutannoofi ejjennoo hin raafmne qabaachuu kan agarsiisuufi ammas balballi nagaaf baname kan hin cufamneefi harki nagaaf diriire waan hin dachaaneef owwaannaan nagaaf tasgabbii buusuuf taasifamaa jiru itti fufuun qe’ee Oromootti nagaaf tasgabbii  horee, uummanni keenya kan facaafate nagaan akka haammatu, daldalaan hojjetee bu’aa akka buufatu, barataan karaa tasgabbii qabuun barnootasaa akka hordofuuf tumsi qaamolee hundaa murteessadha.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ትችቱን ረገብ አድርጉት!

በሰማችሁት፣ ባያችሁት እና ባነበባችሁት ነገር ሁሉ ላይ ግምታዊ ሃሳብ ሰጭነት፣ ትችት-ተኮር አስተያየትና አክራሪ አቋም ያዥነት ማንንም ከሚጎዳው በበለጠ ሁኔታ እናንተንው እንደሚጎዳችሁ ታውቃላችሁ?

ከእንደዚህ አይነቱ ልምምድ ጋር ተያይዞ የሚመጣው መዘዝ ብዙ ነው፡፡

በሰው ነገር ጥልቅ እያሉ ከመኖር የሚመጣ ዓላማ-ቢስ ኑሮ መኖር፣ ሌሎችን በማጣጣል ያደግን የመምሰል የውሸት ስሜት እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የአንድን ነገር የጀርባ ታሪክና አመጣጥ ሙሉ ለሙሉ በማታውቁት ሁኔታ ውስጥ እየገባችሁ ሃሳብ ሰጪነቱን ረገብ አድርጉትና እስቲ ዝም ብላችሁ ራሳችሁን ማሳደግ ላይና ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከጃል ሰኚ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ  ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ መርኃ ግብር በዛሬው እለት በዓደዋ መታሰቢያ ተካሄደ።

በመርኃ ግብሩ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዲሁም የፓርቲውና የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ አመት የምስረታ በዓል "የሀሳብ ልእልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱ ይታወሳል።

በዓሉ እስከዛሬዋ እለት ድረስ በፓናል ውይይት፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በደም ልገሳ፣ በማስ ስፖርት፣ በፎቶ አውደርእይ፣ በከተማ ጽዳት በመሳሰሉ ተግባራት ሲከበር ቆይቷል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩን ጋር ተወያዩ።

“ዛሬ ጠዋት ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ጂን ሊኩን ጋር በኢትዮጵያ እና ባንኩ መካከል ሊኖር ስለሚችለው የአረንጓዴ ኢነርጂ፣ አቪዬሽን እና መሠረተ ልማት ትብብር ዙርያ ተወያይተናል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚከተለውን ሹመት ሰጥተዋል፡፡

1. አቶ መሐመድ እድሪስ፦ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ ጠዋት የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዩ ልዑክ የሆኑትን ዶክተር ቲሞቲ ዊልያምስን በምግብ እና ግብርና አቅርቦት ጥምረት አፈፃፀም ጥረቶች ላይ ለመወያየት ተቀብያለሁ።

Abiy Ahmed Ali (phd)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የብልፅግናው መሀንዲስ ኢትዮጵያ የሚገባትን ልክ እያሳየን ነው!
#ዐብይ_አህመድ
#አምስት_የስኬት_አመታት
#አሻጋሪ_ፓርቲ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ

@AbiyAhmedAli 🙏🙏🙏

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#መርጣቸሁ_ንገሩ

1. የወደፊት እቅዳችሁንና ዓላማችሁን
ጤናማዎቹ በማበረታታት ይደግፏችኋል፣ ቀናተኞቹ ግን ይቀኑባችሁና ያሰናክሉባችኋል፡፡

2. ስጋቶችና ፍርሃቶቻችሁን
ጤናማዎቹ በርቱ ብለው ያደፍፍሯችኋል፣ ጤናቢሶቹ ግን ይንቋችኋል፡፡

3. የሰራችኋቸውን ስህተቶችና ደካማ ጎናችሁን
ጤናማዎቹ በፍጹም ሳይለወጡባችሁ ከነስህተታችሁ ይቀበሏችኋል፣ ጤና ቢሶቹ ግን ከጀርባችሁ ሆነው ያወሩባችኋል፣ አንድ ቀን ጠብቀው ደግሞ ደካማ ጎናችሁን እናንተን ለመጉዳት ይጠቀሙበታል፡፡

የሚነገረውንና የማይነገረውን ለዩ፡፡ ለማን እንደሚነገርና ለማን እንደማይነገር ለዩ፡፡ ብልህ ሁኑ፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ያከናወነው የሪፎርም ስራ ኢትዮጵያን የሚመጥንና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመገንባት ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ነው። አየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ''ጸሐይ 2 '' የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ አድርጓል። አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ናት። ይህም አየር ኃይሉ በ2030 በአፍሪካ ስመጥር አየር ኃይል ለመሆን  የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው" - የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…
Subscribe to a channel