"ነገ ጠዋት በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ክፍለ ከተማችን እንደ ተለመደው የነቃ እና የደመቀ ተሳትፎ ያደርጋል" - አቶ ዮናስ ስዩም - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
ነገ ጠዋት ከ 12:00 ጀምሮ በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ይከናወናል።
ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቡ በሚሳተፍበት በዚህ ፕሮግራም ላይ ክፍለ ከተማችን አዲስ ከተማ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ የነገዋን ወጋገን እየጠበቀ እንደሚገኝ የክፍለ ከተማችን ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ዮናስ ስዩም ገለፁ።
የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮናስ ስዩም "ነገ ጠዋት በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ክፍለ ከተማችን እንደ ተለመደው የነቃ እና የደመቀ ተሳትፎ ያደርጋል። ለዚህም አስፈላጊ ዝግጅት ሁሉ ከወዲሁ ተጠናቋል" በማለት ክፍለ ከተማችን የነገ የከተማ አቀፍ ፕሮግራም ድምቀትና ውበት እንደሚሆን ሃሳባቸውን አካፍለውናል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ መቐለ ከተማ ገቡ
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ የተመራ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ መቐለ ከተማ መግባቱ ተሰምቷል።
ልኡኩ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ በትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት ትናንት ትግበራውን የተጀመረው የዲሞቢላይዜሽን ሂደት ይታዘባል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪ ልኡኩ ግንባታው 40 በመቶ የደረሰውንና የገበታ ለሀገር አካል የሆነውን የገርዓልታ ፕሮጄክትንም ተመልክቷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።
ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።
Before officially inaugurating ‘Quality Village ‘today, I had the opportunity yesterday to visit and review the National Quality Infrastructure we have developed.
This critical institution is designed to catalyze the competitiveness of our local products in global markets and enhance our participation in global value chains.
As one of our leading national institutions, it will play a vital role in strengthening our export capabilities and ensuring we remain competitive in the international arena.
Via - Dr. Abiy Ahmed Ali - FDRE PM
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ ትውልድ ግንባታ አስፈላጊ ነው። በባህር ዳር ቆይታችን በግዙፉ ስቴዲየም ቅጥር ግቢ ውስጥ ኳስ ተጫውተናል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የገበያ ማረጋጋት የጋራ ግብረ-ሃይል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ በመወያየት የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የጋራ ግብረሃይሉ ሰብሳቢ ወ/ሮ አይዳ አወል የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተከፈቱ እሁድ ገበያዎች በማቅረብ ሸማቹ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም የእህድ ገበያን በማጠናከር እንዲሁም ምርቶችን በስፋት በማስገባት የተረጋጋ ገበያ እንዲፈጠር መስራት እንደሚገባ የጋራ ግብረሃይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉትን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ ይመዝገቡ፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#የፎረንሲ_ሳይንስ_ኢንስቲትዩት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት 👌
ዛሬ የፌዴራል ፖሊስ የፎሬንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከልን መርቀናል። ከአንድ አመት ተኩል በፊት እንደ ሀገር የዲኤንኤ ምርመራ ሲያስፈልግ ወደ ውጭ ይላክ ከነበረበት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከዲኤንኤ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲገጥማት በራሷ መስራት ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም ገንብተናል። ይህ በጸጥታ እና ደህንነት ዘርፍ ባለፉት አመታት የሰራናቸው የሪፎርም ስራዎች ውጤት ነው።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር Abiy Ahmed Ali (phd)
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዛሬ ማለዳ ከቦሌ ካርጎ እስከ ቡልቡላ አቃቂ ድልድይ ድረስ ተገንብተው ለነዋሪዎቻችን አገልግሎት ክፍት የተደረጉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ጎብኝተናል።
በቦሌ ክፍለከተማ እየተገነባ ያለውን 13 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን የጎበኘን ሲሆን ይህም አራት ዘመናዊ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች፣ ሁለት የህጻናት የመጫዎቻ ሜዳዎች፣ አንድ የስፖርት ሜዳ፣ አምስት ዘመናዊ የህዝብ መገልገያ የጋራ መጸዳጃ ቤቶች፣ ደረጃውን የጠበቀ ሰፊ የእግረኞች መንገድ፣ በከተማው ስታንዳርድ መሰረት የተከናወኑ የህንጻዎች እድሳት፣ ፋውንቴኖች፣ የመዝናኛ ፓርኮች እንዲሁም የህዝብ መናፈሻ ቦታዎች የተካተቱበት ነው።
ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎች በመደገፍ ይህን ስራ ያሳካችሁ የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ ባለሀብቶችን እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎችን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የምናከናውናቸውን ስራዎችን ከነዋሪዎቻችንን ጋር በመተባበር መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Via 👇
ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የታላቅ ወንድሜን የስጋ እረፍት ተከትሎ አጠገቤ ለነበራችሁ ወዳጆቼ በሙሉ ከልብ አመሠግናለሁ። በይበልጥም ደግሞ ከመሀል ከተማ አዲስ አበባ #ሰበታ ድረስ መጥታችሁ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ 🙏🙏🙏
ታዬ፣ ካስሽ፣ ቶማስ፣ ሳራ 🙏🙏🙏
😭😭😭😭😭
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አድሲና ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በምግብ ዋስትና ፕሮጄክቶቻችን እና ጥረቶቻችን ላይ ስላለው ሰፊ ትብብር ዛሬ ጠዋት ከጓደኛዬ አኪንዉሚ አድሲና ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ከመላው ነዋሪያችን፣ አመራራችን፣ ሰራተኞቻችን፣ መዋቅራችን እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሁሉም መስክ የክፍለ ከተማችንን ብልፅግና ማስቀጠሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል" - የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እየተሰሩ ያሉ #ብልፅግና ተኮር ስራዎች ተጠናክረው በመቀጠል ላይ እንደሚገኙ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ገለፁ።
የኮሚቴ አባላቱ "ከመላው ነዋሪያችን፣ አመራራችን፣ ከመላው ሰራተኞቻችን፣ እንዲሁም የበርካታ ስኬቶቻችን ቁልፍ ከሆነው መላው መዋቅራችን ጋር ሲልቅም ከሚመለከታቸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ክፍለ ከተማችን #አዲስከተማ ን የአዲስ አበባ #ብልጽግና እምብርት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" ብለዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።
ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።
Before officially inaugurating ‘Quality Village ‘today, I had the opportunity yesterday to visit and review the National Quality Infrastructure we have developed.
This critical institution is designed to catalyze the competitiveness of our local products in global markets and enhance our participation in global value chains.
As one of our leading national institutions, it will play a vital role in strengthening our export capabilities and ensuring we remain competitive in the international arena.
Via - Dr. Abiy Ahmed Ali - FDRE PM
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ሁሉ አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪህ ቃል የተዘጋጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ካውንስል ጉባዔ አካሂደናል::
ሌተቀን የከተማቸውን ሰላም በመጠበቅ፣ የጎደሉ በየአካባቢው ያሉ መሰረተ ልማቶችን በህብረተሰቡ ተሳትፎ በመስራት እና በማሰራት በልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ፣ ማህበራዊ ጫናዎችን በመቀነስ እና በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው እንዲሁም በእውቀታቸው ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ የከተማችንን ነዋሪዎችን እና የብሎክ አደረጃጀቶችን እስከ አሁን ለሰሩት ስራ እውቅና ሰጥተን የ2017 እቅድ ላይም ተወያይተናል።
ቀና ልብ ያላቸው በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የበርካቶችን የመኖር ተስፋ ያለመለሙ ስራዎችን ለሰራችሁና ላስተባበራችሁ ሁሉ በነዋሪዎቻችን ስም እያመሰገንኩ የከተማችንን ፈጣን ለውጥ ቀጣይነት ባለው መንገድ ለማስቀጠል ከህብረተሰባችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Yaa'ii kaawunsilii hirmaannaa hawaasaa mata duree "Hirmaannaa hawaasa hunda hammataa misooma itti fufaaf" jedhuun qophaa'e geeggeessineerra.
Halkanii fi guyyaan nageenya magaalaasaanii eeguun,bu'uuraalee misooma bakka garagaraatti hir'atan hirmaannaa hawaasaatiin hojjechuun fi hojjechiisuun, hojiiwwan misoomaa irratti dammaqinaan hirmaachuun,dhiibbaalee hawaasummaa hir'isuun fi hojiilee tola ooltummaa hedduurratti qarshii isaaniitiin, humna isaaniitiin akkasuma beekumsa isaaniitiin hirmaannaa taasisaa kan jiran jiraattota magaalaa keenyaa fi gurmaa'insa bilookiilee hojiiwwan hamma ammaatti hojjetaniif beekamtii laannee karoora bara 2017 irrattis mari'anneerra.
Tola ooltota onnee gaarii qaban qindeessuun hojiiwwan jireenyaa hedduuwwaniitti abdii horan kan hojjettan fi kanneen qindeessitan hunduu maqaa jiraattota keenyaatiin isin galateeffataa jijjiirama saffisaa magaalaa keenyaa karaa itti fufiinsa qabuun itti fufsiisuuf hawaasa keenya waliin tumsaan hojjechuu itti fufna.
Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!
Via ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
"ፓርቲያችን ብልፅግና ባለፉት 5 አመታት የገጠሙትን ችግሮች ወደ ዕድል በመቀየር በተጨባጭ በርካታ ስኬቶችን ማግኘት የቻለ ኢትዮጵያን የመሠለ ህብረ ብሔራዊ ደማቅ ቀለም ያለው ፓርቲ ነው" - ወ/ሮ አይዳ አወል - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሁለተኛ ተከታታይ ግዜ በ “Arabian Cargo Awards” ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን ተቀዳጀ። የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብሩ በዱባይ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በገልፍ ሀገራት ለሚሰጡ ምርጥ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎቶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ ነው ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Good Luck سيد Mr. Muse Bihi Abdi - President of the Republic of Somaliland 🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሙዝ ጭኖ ሲመለስ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ሰምጦ ከተሳፈሩ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ መገኘታቸውን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙት እና ገጽታ ግንባታ ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደገለጹት ትላንት ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ የጀልባውን አሽከሪካሪ እና 15 የቀን ሠራተኞችን ከሙዝ ጋር ጭኖ ከአማሮ ዞን አቡሎ አልፋጮ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ጀልባው መስጠሙን ተናግረዋል ።
በጀልባው ላይ ከነበሩ 16 ሰዎች ሁለቱ በጀርካን ላይ ተንሳፈው የተረፉ ሲሆን 14ቱ ባለመገኘታቸው ፖሊስ በፍለጋ ላይ መሆኑን ኮማንደር ረታ ተናግርዋል ።
15 ተሳፋሪዎች በሙሉ ሙዝ ለመጫን ከአርባምንጭ ዙሪያ አካባቢ የሄዱ መሆናቸውን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡
1. ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ፦ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፦ የቱርዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Badhaadhinaaf Tokkummaan Murteessa dha!
Imala keenya waliinii yeroo qaaccessinuu humni keenya tokkummaa keessa akka jiru hubatama. Tokkoomnee heddumina keenya gaafa fudhannu, aadaan, afaanii fi safuun hundi eenyummaa waloo keenya ni guddisa.
Mul’ata waloo boruu keenyaa karaa dammaqina qabuun mirkaneessuf tumsi waloo barbaachisaa dha. Kallattii kanaan nageenyaafi badhaadhina hunda galeessa mirkaneessuf hundi keenya waliin haa kaanu.
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹