"Baga guyyaa dhaloota Yesuus Kiristoos Nagaan Geessan" Shimallis Abdiisaa PMNO
Ilmi namaa akka bifaafi fakkeenya Waaqaatti uumame; ulfinaafi simbo qabeessas ture.
Show more facebook.com/10005743729135…
👆 በገና በአል ዋዜማ በክፍለ ከተማችን #አቃቂ_ቃሊቲ የተተገበረ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጥቂቱና በአጭሩ 👆
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከ1923-2017
አንጋፋው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ዛሬ ተሰምቷል።
"አገር ከፖለቲካ ፓርቲዎች በላይ ናት" በሚል አባባላቸው የሚታወቁት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ነበራቸው።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የገንዘብ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል።
የአቶ ቡልቻ ደመቅሳ የህይወት ጉዞ ምን ይመስላል? ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3W8NwJf
ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ክልል አዲስ ጥቃት ፈጸመች
ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ግዛት የመልሶ ማጥቃት መጀመሯን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። የዩክሬን ባለስልጣናት የጦር ዘመቻው እየተካሄደ መሆኑን ሲጠቁሙ ሞስኮ ጥቃቱን በመድፍ እና በአየር ሃይል እንደተፈፀመባት ተናግራለች። የዩክሬን ሃይሎች በነሀሴ ወር ወደ ኩርስክ ክልል ገብተው የተወሰነውን ግዛት ይዘዋል። የሩስያ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ የዩክሬን ወታደሮችን ማስወጣት ባይችሉም አንዳንድ አካባቢዎችን መለሰው ተቆጣጥረዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ጦርነቱን የሚያቆመው የጸጥታ ዋስትና ውጤታማ የሚሆነው በዶናልድ ትራምፕ የሚመራው አዲሱ የአሜሪካ መንግስት በሚሰጠው መመሪያ ብቻ ነው ብለዋል። ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ጦርነቱን በፍጥነት ለማቆም ቃል ገብተዋል ፣እንዴት እንደሚያስቆሙት ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። ዘሌንስኪ እንዳሉት "እኔ እና ትራምፕ ወደ ስምምነት እንመጣለን። ጠንካራ የደህንነት ዋስትናዎችን ከአውሮፓ ጋር እንሰጣለን፤ ከዚያም ከሩሲያውያን ጋር መነጋገር እንችላለን " ሲሉ አክለዋል።
እንደ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ፣ ሁለት ታንኮች፣ አንድ ወታደራዊ ተሽከርካሪ እና 12 የታጠቁ ተዋጊ ተሽከርካሪዎችን ያካተተ የዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ቡድን እሁድ እለት በበርዲን መንደር አቅራቢያ ጥቃት መሰንዘሩን ያሳያል።የሩስያ ሃይሎች በወሰዱት የመከላከል እርምጃ ሁለቱንም ታንኮች፣ የወታደራዊ ተሸከርካሪ እና ሰባት የታጠቁ ተዋጊ ተሽከርካሪዎችን ማውደማቸውን ገልጿል። ትግሉ እንደቀጠለ ነው ሲል የሩሲያ ጦር ኃይሎች አስታውቋል። በበረዶ በተሸፈነው ገጠራማ አካባቢ ያለውን ውጊያ የሩሲያ መንግስታዊ የዜና ወኪል ሪያ በቪዲዮ በማስደገፍ ዘግቧል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ከ400 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ እና የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል።
እንዲህ ያሉ የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቀሉ ስራዎችን እንድንሰራ፣ “መስጠት አያጎድልም” ብለው ከጎናችን በመቆም ጉልበት የሆኑንን የከተማችን ባለሀብቶች በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
መልካም በዓል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
via ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች በከባድ በረዷማ ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
በኬንታኪ፣ ቨርጂኒያ፣ ካንሳስ፣ አርካንሳስ፣ ምዕራብ ቨርጂኒያ እና ሚዙሪ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ሚሲሲፒ እና ፍሎሪዳ ጨምሮ ከባድ እና ያልተለመደ ቅዝቃዜ በአሜሪካ ግዛቶች አጋጥሟል። አውሎ ነፋሱ ወደ ምሥራቃዊው የሀገሪቱ ክፍል ይጓዛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በአጠቃላይ 30 ግዛቶች የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። ዋሽንግተን ዲሲ፣ ባልቲሞር እና ፊላደልፊያን ጨምሮ ከተሞች ከእሁድ አንስቶ ለከባድ በረዷማ ሁኔታዎች ተጋልጠዋል።
60 ሚሊዮን አሜሪካውያን በክረምት የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ይገኛሉ።
እንደ ዋሽንግተን ዲሲ እና ፊላደልፊያ ያሉ ዋና ዋና ከተሞችን ጨምሮ ከመሃል አገር እስከ ምስራቅ ጠረፍ ያሉ 30 የአሜሪካ ግዛቶች ከባድ የክረምት ሁኔታዎች እንደሚታዩ ይጠበቃል። የአየር ሁኔታው የከፋው በፖላር አዙሪት በአርክቲክ አካባቢ ከሚዘዋወረው ቀዝቃዛ አየር ንብረት እንደሆነ የትንበያ ሰጪዎች መረጃ ያሳያል። የአሜሪካ አየር መንገድ መሀል አሜሪካን እና ምስራቃዊ የባህር ዳርቻን ይጎዳል ተብሎ በሚጠበቀው የክረምት አውሎ ንፋስ ምክንያት ለ46 አየር ማረፊያዎች የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ማስጠንቀቂያው ከካንሳስ ሚዙሪ እንዲሁም ፔንሲልቬንያ እና ኒው ጀርሲ ድረስ በበርካታ ግዛቶች አየር ማረፊያዎችን ይመለከታል።
አየር መንገዶች ለትኬት ለውጦች ሙሉ ዝርዝር ሁኔታዎችን ይፋ አድርገዋል። ዴልታ፣ ሳውዝ ዌስት እና ዩናይትድ አየር መንገዶችም ለደንበኞቻቸው ተመሳሳይ የበረራ ስረዛ መረጃን ሰጥተዋል።ከ2,000 በላይ በረራዎች አስቀድሞ ከተያዘላቸው ሰዓት እንዲዘገዩ የተደረገ ሲሆን 1,500 የሚሆኑት ደግሞ ወደ አሜሪካ መግባት እና መውጣት መሰረዛቸውን የበረራ የክትትል ድረ-ገጽ ፍላይት አዌር ዘግቧል። የካንሳስ ሲቲ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ውጭ ለሚደረጉ በረራዎች በጣም የተጎዳው ሲሆን 86 በመቶው ተሰርዟል። ወደ ሀገር ውስጥ ለሚደረጉ በረራዎች፣በሚዙሪ የሚገኘው ሴንት ሉዊስ ላምበርት አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 53 በመቶ በረራዎቹ ዘግይተዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⚡️ በቻይና የሜታፕኒሞቫይረስ በፍጥነት እየተሰራጨ ነው - ሚዲያ።
የሜታፕኒሞቫይረስ (hMPV) ምልክቶች ከኮቪድ-19 ጋር ተመሳሳይ የተባለ ሲሆን ብርድ ብርድ ማለት፣ ሳል፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ ድክመት እና መፍዘዝ ምልክቶች የሚታይበት ሲሆን የተጨናነቁ ሆስፒታሎች በተለይም የህጻናት ሆስፒታሎች በበሽታው የተያዘን ሰው የህክምና እርዳታ ሲያደርጉ ታይተዋል።
በመገናኛ ብዙኃን እንደተዘገበው በአንዳንድ ክልሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል የተባለ ሲሆን ነገር ግን እስካሁን ድረስ በይፋ ስለ አዋጁ የተረጋገጠ መረጃ የለም።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
መቄዶንያ ለቡግና የድርቅ ተጎጂዎች ድጋፍ አደረገ
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የተለያዩ የምግብ፣ የአልባሳት እና አልሚ ምግቦችን በአይነት የያዘ ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#የገና_ማዕድ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማችን ነዋሪዎች የገና ማዕድ ያጋራል።
"በጎ ፈቃደኝነት፤ ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ማስታወቂያ!
1 :- የ 1 2ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 /2017 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ስለሆነም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ ከቀነ ገደቡ አስቀድማችሁ እንዲታጠናቅቁ እናሳስባለን።
2:- የ2017 የትምህርት ዘመን ፈተናዎች ይዘት የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ሁኔታ ከ 9 - 12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ 8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7- 8ኛ ክፍሎች የሚሸፍን ይሆናል።
3:- እያንዳንዱ ተማሪ በተማረበት የክፍል ደረጀ የተማረውን የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርጐ ሊዘጋጅ ይገባል። ፈተናዎቹ ተማሪዎቹ የተማሩትን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ይሆናል።
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።
በተለይ ቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ረዘም ላለ ሰከንድ ንዝረቱ ተሰምቷቸዋል።
የአሁኑ ንዝረት ከትላንት ምሽቱ አንፃር ጠንክሮ የተሰማ ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአእላፋት ዝማሬ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለ ሥልጣን የቅጂና ተዛማጅ መብቶች ተመዘገበ
በአዲስ አበባ ለሁለተኛ ግዜ በድሬደዋ ለመጀመሪያ ግዜ የሚደረገው የአእላፋት ዝማሬ ወይም "The Melody of Myriads" የተሰኘውን የዝማሬ መረሀግብር በገና ዋዜማ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚካሔደውን ዓመታዊ የዝማሬ ሁነት የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የመጀመሪያውን የአእላፋት ዝማሬ በ2016 ዓ.ም ካደረገበት ማግሥት ጀምሮ የአእላፋት ዝማሬን በቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በብፁዓን አበውና በምእመናን በተሠጠው ‘የአእላፋት ዝማሬ መቀጠል አለበት’ የሚል አደራ ምክንያት የአእላፋት ዝማሬን የተመለከቱ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተገልፆል፡፡
በዚህም መሠረት ‘የአእላፋት ዝማሬ’ "The Melody of Myriads" የተሰኘውን በገና ዋዜማ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚካሔደውን ዓመታዊ የዝማሬ ሁነት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የቅጂና ተዛማጅ መብቶች በማስመዝገብ የአእላፋት ዝማሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሊካሔድ የሚችልና የባለቤትነት መብቱም የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ሆኖ መመዝገቡን አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የ2017 ዓ.ም የአእላፋት ዝማሬ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ የሚካሔድ ሲሆን ላለፉት ስምንት ወራት ለዚህ ታላቅ የዝማሬ ጉባኤ ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶአልም ተብላል፡፡ በ2017 ዓ.ም የአእላፋት ዝማሬ መረሀግብስ የሚካሔደውም በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና በድሬዳዋ ለገሀር አደባባይ ብቻ ነውም ተብላል።
የአእላፋት ዝማሬ ዋነኛ ዓላማ ምእመናን ልደቱን በባለ ልደቱ ቤት’ በዝማሬ እንዲያከብሩ ለማድረግ በመሆኑ በዚህ ዕለት የአእላፋት ዝማሬ’ ስሙ እንደሚያሳየው አእላፋትን የሚያሳትፍ ዝግጅት በመሆኑ በከተማ ደረጃ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ተባርኮ እንዲደረግና የአንድን ከተማ ሕዝብ በነቂስ ማሳተፍ በሚችል ደረጃ እንዲከናወን የታሰበ ዝግጅት መሆኑም ተጠልፆል።
የአእላፋት ዝማሬ በEOTC ቴሌቪዥን አንዲሁም፣ በሀገሬና በአርትስ ቴሌቪዥን ጣብያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን ከአምስት በላይ ዓለም አቀፍ ሚድያዎችና ወደ ሰባት የሚጠጉ ሀገር አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሥፍራው ተገኝተው ለመዘገብ ፍቃድ ወስደዋልም ተብላል።
የዘንድሮውን የአእላፋት ዝማሬ ከአምናው በተለየ ጥራት ለማካሔድ ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን ያስታወቁት አስተናጋጆቹ በሥፍራው እስከተገኘ ድረስ የትኛውም ቦታ ላይ የቆመ ሰው የሚሰማው ድምፅም ሆነ የሚያየው ምስል እኩል እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ተደርጓልም ብለዋል፡፡
በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባው የአእላፋት ዝማሬ 60 ላይናሬ ስፒከር እና 10 ሞንታርቮዎች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሲሆን በድምፅ መሐንዲሶች ከፍተኛ ጥረት መድረክ ላይ የሚሰማው ድምፅና ከሩቅ የሚሰማው ድምፅ እኩል እንዲሆን ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁም አክለዋል፡፡
ከድምፅ በተጨማሪ 250 ካሬ ስክሪን ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን 18 ትላልቅ ስክሪኖች በየትኛውም ቦታ ላይ ያለ ሰው የመዝሙሩን ግጥም እያየ በዐውደ ምሕረቱ ላይ የሚዘመረውን ዝማሬ ለመዘመር እንዲችል ሆኖ ተዘጋጅቶልም ተብላል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ተረጂነት ቀጣይነት እንዳይኖረው ተግተን እንሠራለን" - ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"የቅዳሜና የእሁድ ገበያዎች በአሉን በማስመልከት ሳምንቱን ሙሉ በመቆማቸው / በመገኘታቸው ዋጋን ከማረጋጋት በተጨማሪ ማህበረሰባችንን በብዙ መስክ እየደገፉት፣ እየጠቀሙት ይገኛሉ" - አቶ በላይ ደምሴ - የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዛሬ ታህሳስ 28 ዝናብ ብርቅ በሆነባት ሳውዲ ጅዳ ዝናብ ዘንቧል። እዛ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደስ ብሎናል ሲሉ ከላይ የሚታየውን ምስል አጋርተዉናል።
ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ምንም አይነት ወንዝም ሆነ አንድም ሃይቅ የለም። ጥቂት ዝናብ ከሚያገኙ የአለም ሃገራት መሃከልም አንዷ ሳውዲ ናት። ዝናብ ከዘነበም አመታዊ የዝናብ መጠኗ ከ4 ኢንች አይበልጥም።ዛሬ ዝናብ ያገኙበት ቀን ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአእላፋት ዝማሬ የምስጋና መርሐ ግብር በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሃኒዓለም ካቴድራል ተካሄደ፡፡
የምስጋና መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ነው የተካሄደው፡፡
በምስጋና መርሐ ግብሩ ላይ በሺህዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ።
በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ።
እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#የመደራጀት_ወሳኝነት
“አንድ ነገር ለማደራጀት (Organize ለማድረግ) የምታጠፏት አንዲት ደቂቃ ወደ ስራው ስትሰማሩ አንድ ሰዓት ታተርፍላችኋለች” – Benjamin Franklin
በሕይወታችን ስኬታማ መሆን ከፈለግን ማዳበር ከሚገቡን ስልቶች አንዱ የማደራጀት ስልት ነው፡፡
ሁኔታውን ሰፋ አድርገን ከተመለከትነው ግን ከስልት ክልል ያለፈና ወደ ልማድ ቀጠና የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
ምንም እንኳን ስልቱን ብናውቀውም ልማዱን የማዳበር ደረጃ ካልደረስን ስለማይጠቅመን ማለት ነው፡፡
በአጭሩ ሲቀመጥ አንድን ነገር ማደራጀት ማለት ቀድሞ ፊታችን የቀረበልንን ከማድረግ ልማድ በመውጣ አንድን ነገር ሆን ብለን በማሰብና በማቀድ (intentional በመሆን) ማድረግ ማለት ነው፡፡
ምንድን ነው የማደርገው? እንዴት ነው የማደርገው? መቼ ነው ማድረግ ያለብኝ? እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች መሰራዊ የመነሻ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ጥያቄዎች በመጠየቅና ትክክለኛ መልስ ለመስጠት ግን በግር-ግር ተነስተን፣ በግር-ግር ውለንና በግር-ግር አምሽተን አንችለውም፡፡ በቀን ውስጥ ለብቻችን በጸጥታ የምናስብበትና የምናቅድበት ጊዜ ያስፈልገናል፡፡
ለብቻችሁ መሆንን ልመዱ፡፡ ማሰብን ተለማመዱ፡፡ ነገ ለሚሰራው ስራ ዛሬ ማቀድና ማደራጀትን ተለማመዱ፡፡ ከየት ጀምራችሁ ወደ የት እንደምትሄዱ በሚገባ አስቡ፡፡ በደመ-ነፍስ አትኑሩ፡፡
ይህንን ጠቃሚ ልምምድ እንዳትለማመዱ የሚያደርጓችሁን የግል ሁኔታዎች ቅረፉ፡፡
• አንዳንዶቻችን ያደግንበት ቤትና ሕብረተሰብ ያንን ስላላሳየንና ስላላስተማረን ያንን አንለማመደውም፡፡
• አንዳንዶቻችን የግንዛቤ ጉድለት አለብን፡፡ ሕይወትንና ስራን ማደራጀት ያለው ጥቅም አልገባንም፡፡
• አንዳንዶቻችን በአማካኙ መስከን ለምደናል፡፡ አንድ ነገር በሚገባ ቢደራጅ የሚመጣውን ውጤት ከመፈለግ ይልቅ በለመድነው በመቀጠል በውጤቱ መርካት እንመርጣለን፡፡
• አንዳንዶቻችን ፍላጎቱና አቅሙ እያለን የምኖርት ቤትና የምንሰራበት መስሪያ ቤት አይመቸንም፡፡
እነዚህ ምክንያቶች የየራሳቸው መዘዝ ቢኖራቸውም፣ ሁኔታውን ለይተን ብልሃት መፈለጉ ግን የእኛው ሃላፊነት ነው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጎልደን ግሎብ አዋርድ 2025
በአውሮፓውያኑ አዲስ አመት ማግስት የፊልሙ አለም ተጠባቂው መድረክ ጎልደን ግሎብ አዋርድ ተካሄደ።
ትላንት አመሻሹ ላይ በነበረ ደማቅ ዝግጅት የጎልደን ግሎብ አዋርድ ለ82ኛው ተካሂዷል።
መድረኩ ከ1944 አንስቶ የፊልምና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ የሚሰሩ ባለሞያዎችን ሲሸልም ቆይቷል።
ትላንትናም በተመሳሳይ በካሊፎርኒያ ቢቨርሊ ሂልተን ሆቴል በነበረው ደማቅ ዝግጅት በ27 ዘርፎች ባለሞያዎችን አወዳድሮ ሸልሟል።
ዞይ ሳልዳና ፣ኮሊን ፋሬል ፣ጄሚ ፎክስ፣ ሄሮዩ ኪሳናዳ በታጩበት የተለያዩ ዘርፎች ማሸነፍ የቻሉ ባለሞያዎች ናቸው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት፤ ከዛሬ እሁድ ታሕሳስ 27 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ ጥር 2 ቀን 2017 ድረስ የሚቆይ "ልዩ የሆነ ወደ አላህ የመመለስና መልካም ሥራ እየሰሩ ለሀገር ሰላምና ደህንነት ዱዓ የማድረግ ቀን ተግባራዊ እንዲደረግ" ጥሪ አቀረበ።
የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤቱ ለጠቅላላው ሕዝበ ሙስሊም ባስተላለፈው መልዕክት፤ "ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰው ሰራሽን በተፈጥሮ ችግሮች ምክንቶች እየታመሰች ትገኛለች።" ብሏል።
"ለዚህም ዋና ምክንያቱ የሰው ልጆች የርስ በስርስ ፍቅር መጥፋት፤ ጥላቻ መስፋፋት የእርስ በርስ መገዳደል መበራከትና የሰው ልጅ ነብስ ከምን ጊዜውም በላይ ርካሽ የሆነበትና በቀላሉ ሕይወት የተቀጠፈ የሚገኝበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡" ሲልም ገልጿል።
"ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጥፋቶቻችንና ከስህተቶቻችን ለመመለስ ባለመቻላችን ምክንያት ተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመከሰት ላይ ይገኛሉ፡፡" ያለው ጽ/ቤቱ፤ ለአብነት ያህልም ባለፈው ክረምት በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ፤ እንዲሁም በአማራ ክልሎች በተከስተው የመሬት መንሸራተት በርካታ ሰዎች መሞታቸውና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን አንስቷል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ በሀገሪቱ እየተከሰተ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ "ይህ ሁሉ ክስተት እኛ የሰው ልጆች በምንሰራቸው ወንጀሎች ሳቢያ የሚመጡ ክስተቶች በመሆናችው ነው" ብሏል።
በዚህም ምክንያት ከላይ በተጠቀሱት ቀናቶ ለሀገር ሰላምና ደህንነት ዱዓ የማድረግ ቀን ተግባራዊ እንዲደረግ የኡለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ለመላው ሕዝበ-ሙስሊም የሚከተሉትን መልእክቶች አስተላልፏል፡፡
በዚህ መሰረት 👇
1. ሕዝበ-ሙስሊሙ በአጠቃላይ ተውበት በማድገረግ ወደ አላህ እንዲመለስ
2. ሁላችንም እርስ በርስ ይቅርታ እንድንባባል፤
3. ለተቸገሩትና ረዳት ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሶደቃ ( ምጽዋት) መስጠት
4. በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ አጠቃላይ መስጂዶች በየአምስት አውቃት ሶላቶች ላይ ቁነት እንዲደረግ፤
5. የቀጣዩ ጁሙአ ቀን በሁሉም መስጂዶች የሚደረጉ ኹጥባዎች በዚህ ዙሪያ እንዲሆኑና አጠቃላይ ዱዓ እንዲደረግ ጽ/ቤቱ አሳስቧል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአፋር ክልል ንግድ ቢሮ እና የክልሉ ጸጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ነዳጅ ጭነው በየቦታው ተደብቀው የነበሩ ቦቴዎች ከተደበቁበት እንዲወጡ መደረጉ ተገለጸ፡፡
አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ሰርዶ አድማስ በሚባል ቦታ በየጥሻው የተደበቁ ቦቴዎች በፀጥታ አካላት አሰሳ መያዛቸውን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ሠዓትም የክልሉ ንግድ ቢሮ ለተሽከርካሪዎቹ እጀባ እንዲሰጥ በማድረግ ወደ የመዳረሻቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል መባሉን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በአፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎችን እያደረገ ነው።
በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የመሠረታዊ አገልግሎቶች እና መልሶ መቋቋም መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታዬ ጌታቸው፥ ኮሚሽኑ ለተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።
የአፋር ክልል ከፍተኛ አመራር እና በክልሉ የአደጋ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ አቶ አህመድ ኢብራሂም በበኩላቸው፥ ከ6 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለትም ከሁለት ወረዳዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የዱቄት፣ ማካሮኒና አልሚ ምግብ እንዲሁም የምግብ ማብሰያና የመጠጥ ውሃ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትም ለተፈናቃዮች የመጠጥ ውሃ እያቀረበ መሆኑን ጠቅሰው፤ የክልሉ መንግሥት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚያከናውነው ሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የአደጋ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች በማዛወር የጤና እና ሌሎች ድጋፎች የማድረስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዛሬ በይፋ የተመረቀው የዋቆ ጉቱ ኤርፖርት ተርሚናል ጎብኚዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም የአካባቢው ተወላጆች ከመላው ዓለም ወደ ባሌ ዞን ሲመጡ ምቾት ያለው አገልግሎት በመስጠት ቁልፍ መተላለፊያ (Gateway) ሆኖ ያገለግላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
“ማኅበራዊ ፍትሕን በማረጋገጥ ለብዙ ዘመን አንገት ያስደፋንን እና ለተረጂነት የዳረገንን ድህነትን በማሸነፍ በልተን ማደር ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋጥ በትጋት እንሠራለን” - ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤአዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በኢትዮጵያ የቢትኮይን ማይኒንግ 10 አበይት ምእራፎች
ኢትዮጵያ በምታቀርበው ርካሽና ንፁህ የኤሌክትሪክ ኃይል ምክንያት የቢትኮይን ማይኒንግ ኢንቨስትመንት ዋነኛ መዳረሻ እየሆነኝ መታለች::
ኢትዮጵያ በ2024 ለጠቅላላ የ #ቢትኮይን ሃሽ መጠን 2.25 በመቶ አበርክቶ እንዳለው ተገልጿል።
ዋና ዋና ምዕራፎቹም:
1. የቢትክላስተር መምጣት (ታኅሣሥ 2016)፡ የሩሲያ ኩባንያ ቢትክሉስተር በአዲስ አበባ 120MW የማዕድን ፋሲሊቲ ሙሉ በሙሉ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ( #GERD) መገንባት ጀምሯል።
2. QRB ቤተመከራ መስፋፋት (ታኅሣሥ 2016)፡ የአገር ውስጥ ስራ ፈጣሮች QRB ቤተ ሙከራ በአዲስ አበባ አካባቢ የሞዱላር ማዕድን ሥራዎችን ያስጀመሩ ሲሆን ይህም ትርፍ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ 150MW እንዲደርስ አድርጓል።
3. የ250ሚ ዶላር የመንግስት ስምምነት (የካቲት 2016)፡ ኢትዮጵያ ከሆንግ ኮንግ ዌስት ዳታ ግሩፕ ጋር የቢትኮይን ማምረቻ ፋብሪካዎችን በቴክኖሎጂ ለማቋቋም የ250ሚ ዶላር ስምምነት ተፈራርማለች።
4. የቻይና ኩባንያዎች ገብተዋል (የካቲት 2016)፡ 21 ቻይናውያን የቢትኮይን ማዕድን አውጪዎች የህዳሴ ግድብ 5.3GW የውሃ ሃይል አቅምን ተጠቅመው ስራቸውን ኢትዮጵያ አድርገዋል።
5. ከፍተኛ ገቢ አስገኝቷል (ከየካቲት 2016 - ህዳር 2017)፡ የኢትዮጵያ #ኤሌክትሪክ ኃይል ለማዕድን ኩባንያዎች 55ሚሊየን ዶላር የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ በማግኘቱ የዘርፉን ትርፋማነት ያሳያል።
6. ቢት ክለስተር መስፋፋት(መስከረም 2017)፡- ቢትክላስተር 12,000 የማዕድን ማሽኖችን ወደ ስራ በማስገባት ኢትዮጵያን በቢትኮይን ማዕድን ስነ-ምህዳር ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲኖራት አድርጓል።
7. የአፍሪካ ቢትኮይን #ማዕድን ሰሚት (ጥቅምት 2017)፡ የአረንጓዴው አፍሪካ ማዕድን ህብረት አዲስ አበባ ላይ ትልቅ ጉባኤ በማዘጋጀት ኢትዮጵያ በዘላቂ የማዕድን ቁፋሮ ላይ ያላትን ተጽእኖ አረጋግጧል።
8. ቢትፉፉ መምጣት (ጥቅምት 2017)፡- ቀዳሚው ዓለም አቀፍ የማዕድን አገልግሎት ቢትፉፉ በኢትዮጵያ የ80MW ፋሲሊቲ አስጀምሯል።
9. የዌስት ዳታ አዲስ ሳይት ( ህዳር 2017)፡- ዌስት ዳታ ግሩፕ በወላይታ ሶዶ በ15 ሚሊየን ዶላር 20MW የማዕድን ማምረቻ መሰረተ ልማት ላይ መስርቷል።
10. ቢት ማዕድን #ኢንቨስትመንት (ታህሳስ 2017)፡ ቢቲ ማይኒንግ ሊሚትድ 51MW የመረጃ ማዕከላትን እና 17,869 የማዕድን ማሽኖችን በ14.3ሚ ዶላር በማግኘት የኢትዮጵያን አለም አቀፋዊ አቋም የበለጠ አጠናክሯል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹