"... አንዳንዶች መስቀል ጨብጠው ጦርነት ያውጃሉ፤ እኛ መስቀል ጨብጠን ሰላምን እናውጃለን ..."
https://twitter.com/ProsperityKera
ኢትዮጵያ የ28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ውሳኔዎችን ለመተግበር ከሁሉም አጋር አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አዘጋጅነት በዱባይ ከተማ በፈረንጆቹ ካሳለፍነው ሕዳር 30 እስከ ታህሳስ 12 ቀን ድረስ የተካሄደውን 28ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በማብራሪያውም÷ኢትዮጵያ በተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (COP28) በዝርዝር በተካሄዱ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮች እንዲሁም ኢትዮጵያ እያከናወነቻቸው ባሉ የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ፕሮጀክቶች ተያያዥ ጉዳዮች ስኬታማ ተሳትፎ አድርጋ መመለሷን አስታውሷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተሳተፉበት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር÷በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ ሀገሪቷን እየገጠሙ ለሚገኙ ችግሮች ምላሽ ለመስጠት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ32 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን እንዳሳወቁም ጠቅሷል፡፡
በስንዴ ምርት፣በታዳሽ ኃይል አቅርቦት፣ በምግብ ራስን ለመቻል የተወጠነው የሌማት ትሩፋት እንዲሁም የትራንስፖርት ዘርፍ ለአየር ንብረት ለውጥ ተስማሚ አማራጭ የትራንስፖርት ዘርፎች ማበረታቻ የተወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር እንዳስረዱም ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡
ኢትዮጵያ የምትወስዳቸው የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎች በእዳ መቆለል የተነሳ ከፍተኛ ተግዳሮት እየገጠማቸው መሆኑን ጠቅሰው÷የሚመለከታቸው ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተገቢ ማሻሻያ እንዲያርጉ መጠየቃቸውንም መግለጫው አስታውሷል፡፡
እንዲሁም የአየር ንብረት ተጽዕኖ ተጋጭነትን በትብብር ስለመፍታት፣ ፍትሃዊ፣ ተመጣጣኝ፣ ተደራሽ እና ስርዓት ያለው የኢነርጂ ሽግግር እና የቡድን 77 እና ቻይና ጉባኤ በሚመለከታቸው የዘርፉ ሚኒስትሮች ጋር ኢትዮጵያ ተሳትፎ ማድረጓ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም ሁሉን ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያን አቋምና ሀሳብ ማጋራት እንደተቻለ ነው የተገለጸው፡፡
በጉባዔው ወቅት ኢትዮጵያ “ዩ ኤ ኢ ዔ ኤም ኢ ዔ ፖወር” ከተሰኘ ድርጅት ጋር የ600 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የ300 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ማንጫ ፕሮጀክትእንዲሁም ከጣሊያን የ8 ሚሊየን ዩሮ የአካባቢ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎችን በትብብር ለመስራት ስምምነት መፈራረሟ ተመላክቷል፡፡
በ28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ኢትዮጵያ በመሪነት እንደተሳተፈች የገለጸው ሚኒስቴሩ÷አባል በሆነችባቸው የአፍሪካ ቡድን፣ በዝቅተኛ የእድገት ደረጃ የሚገኙ ሀገራት ቡድን በመምራትም መሳተፏን አስታውቋል፡፡
በተለይ የወቅቱ የአፍሪካ የአካባቢ ሚኒስትሮች ጉባዔ ፕሬዚዳንት እንደመሆኗ በጉባዔውአፍሪካውያን በአንድ ድምጽ እንዲደራደሩና ጥቅማቸውን እንዲያስጠብቁ አስተባብራለች ተብሏል፡፡
በጉባዔው ወቅት የበለጸጉ ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የሚውል የ792 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጥፋትና ውድመት ፈንድን ጨምሮ የ85 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመስጠትም ቃል እንደገቡ ተጠቁሟል፡፡
የዓለም ባንክ በበኩሉ ከአየር ንብረት ለውጥ ተያያዥ ለሆኑ ፕሮጀክቶች በ2024 እና 2025 የ9 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ጭማሪ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የባለብዙ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ድጋፎች ከ22 ነጥብ 6 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ በጀት ለመመደብ ቃል ገብተዋል ነው የተባለው፡፡
በኢትዮጵያ በተለያየ ዘርፍ ያሉትን ራዕዮችና አሁን እየተከናወኑ ያሉ ተግባሮችን በኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ፓቪሎን በኤግዝቢሽን መልኩ እንደቀረቡ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በተመድ ማዕቀፍ በባለብዙ የትብብር ማዕቀፎች ያላትን እምነት መሰረት በማድረግ የ28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ውሳኔዎችን ለመተግበር እና በትግበራ ሂደት ከሁሉም አጋር አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ስህተትን የማመን ነጻነት
አንደኛው ምርጫህ ራስህን ስህተት-የለሽ አስመስሎ በማቅረብ ከስህተት የመማርንና የይቅርታን ጣእም ሳታጣጥም ማለፍ ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ስህተትን በማመንና ይቅርታን በመጠየቅ ውስጥ የሚገኘውን ነጻነት መጎናጸፍ ነው፡፡
አምባ-ገነን መሪዎች ከሚታወቁበት ዋነኛ ባህሪያቸው ያው እንደ ስማቸው የፈለጉትን ነገር በፈለጉበት ጊዜ፣ ሁኔታ መጠን የማድረግ መብት እንዳላቸው የሚያምኑና ያንንም ከማድረግ ወደኋላ የማይሉ ሰዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ከ1740 እስከ 1786 የፕሩዢያ ገዢ የነበረ ፍሬደሪክ ግን ምንም እንኳን የአምባ-ገነንነት ባህሪይ እንደነበረው ቢታመንና ይህም ስም ቢሰጠው፣ ለየት ያለ ባህሪይ እንደነበረው ይነገራል፡፡ ሆኖም፣ ፍሬደሪክ ከሚታወቅበት ባህሪይ እንዱ አምባ-ገነንነት የአመራር ስልቱን ለሕዝቡ ጥቅም የማዋል ሁኔታ አንዱ ነበር፡፡
አንድ ቀን በአንድ በግዛቱ ውስጥ በሚገኝ ማረሚያ ቤት ከአጃቢዎቹ ጋር ሲዘዋወር ሳለ አንድ አስገራሚ ነገርን ተመለከተ፡፡ ገና ታላቁ ፍሬደሪክ ለጉብኝት ወደማረሚያ ቤቱ ይመጣል ተብሎ እንደተነገረ ታራሚዎች በሙሉ ተዘጋጅተው ይጠብቁ ነበር፡፡ ይህ ሰው ካለው አምባ-ገነንነት ባህሪይ የተነሳ እንዲሆንና እንዲደረግ የፈለገውን ነገር ሊያስደርግ እንደሚችል ታራሚዎቹ በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ምናባትም ወደ እነሱ ተመልክቶ ወይም ጩኸታቸውን ሰምቶ ትንሽ ከራራላቸው፣ ወዲያው እንዲፈቱ የማዘዝ አቅም እንዳለው ያውቃሉ፡፡ ለዚህ ነው በጉጉት የሚጠብቁት፡፡
ፍሬደሪክ ልክ ወደ ማረሚያ ቤቱ ግቢ እንደገባ ታራሚዎች በሙሉ መጮህ ጀምረዋል፡፡ አንዱ በዚህ በኩል፣ “ንጉስ ሆይ፣ እኔ አንድ ነገር ሳልበድል ነው የታሰርኩት፣ እባከህ አስፈታኝ” ይላል፡፡ ሌላኛው በዚያ በኩል፣ “ንጉስ ሆይ፣ እኔ ንጹህ ሰው ነኝ፣ ፍጹም ወንጀል የሌለብኝ ሰው ነኝ” ይላል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ በግራና በቀኝ ምን ያህል ስህተት-የለሽ እንደሆኑና ፍትህ በጎደለው መልኩ ማረሚያ ቤት እንደገቡ እንዲሰማላቸው ይጮሃሉ፡፡
ንጉሱም ይህን ያህል ሰው ፍትህ የለሽ በሆነ መልኩ ወደማረሚያ ቤት እንዴት ሊገባ ይችላል በማለት እያሰበ ወደ አንድ አቅጣጫ ዘወር ሲል በአንድ ጥግ ዝም ብሎና አቀርቅሮ የተቀመጠ ታራሚ ተመለከተ፡፡ ይህ ታራሚ እንደሌሎቹ አይጮህም፡፡
ንጉሱ ወደዚህ ታራሚ ቀረብ በማለት፣ “ይህ ሁሉ ታራሚ ንጹህ እንደሆነ ይናገራል፣ አንተ ምነው ዝም አልክ? የአንተስ ሁኔታ ምንድን ነው?” በማለት ጠየቀው፡፡ ታራሚውም ቀና በማለት፣ “እኔ የሰራሁትን አውቃለሁ፣ ጥፋተኛ ነኝ፣ የሚገባኝን ነው ያገኘሁት” ብሎ ከተናገረ በኋላ መልሶ አቀረቀረ፡፡
ታላቁ ፍሬደሪክ ይንን ከሰማ በኋላ፣ ወደ አጃቢዎቹና ወደ ማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎቸ ዘወር በማለት አንድ ትእዛዝ አስተላለፈ፣ “እነዚህ ሁሉ ታራሚዎች ንጹህ ነን ብለዋል፡፡ ይህ ሰው ደግሞ ስህተተኛ እንደሆነ አምኗል፡፡ በሉ፣ ይህ ስህተተኛ ሰው በብዙ ንጹሆች መካከል ሆኖ የእነሱን ባህሪ እንዳያበላሽ አሁኑኑ ይፈታ፡፡” ንጉሱ ይህንን በተናገረ በጥቂት ደቂዋዎች ውስጥ ይህ “ስህተተኛ” ታራሚ ነጻ በመውጣት ወደቤቱ እንዲሄድ ተፈቀደለት፡፡
ምንም ስህተት እንደሌለበት የሚያስብ ሰው እንደዚያ በማሰቡ ሌላ ተጨማሪ ስህተት እየሰራ ነው፡፡ ከዚህ የከፋው ደግሞ በስህተቱ መዘዝ ውስጥ ራሱን ሲያገኘው የሰራውን ስህተት ላለማመን የሚታገል ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህኛው ስህተትን ካለማመን ምርጫ የተሻለው መንገድ ለሰራነው ስህተት ሃላፊነት በመውሰድና ይቅርታን በመጠየቅ ወደፊት መገስገስ ነው፡፡
ሁል ጊዜ ስህተትህን ከማመን ይልቅ የክህደትን ምርጫ የምትከተል ከሆንክ ለብዙ ጠንቆች ራስህን ታጋልጣለህ፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ሃላፊነት ያለመውሰድ ሌላ ስህተት የመስራትህ ሁኔታ አንዱ ነው፡፡ በተጨማሪም ከስህተት ያለመማርና ስህተትን የመደጋገም እንቅፋት ይገጥምሃል፡፡ ይህ ደግሞ ራሱን የቻለ የስሜት እስረኛ ያደርግሃል፡፡ ዛሬ አንድን ያጠፋኸውን ሰው ሰው ይቅርታ ጠይቅና ነጻ ውጣ፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ቱሪስቶች ጭምር በትህትና ያገለገሉበት ጥምቀት‼
https://twitter.com/ProsperityKera
ኢትዮጵያ በዑጋንዳ ካምፓላ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 77 እና የቻይና ሦስተኛው የደቡብ- ደቡብ ትብብር የመሪዎች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
ጉባዔው በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓየር ንብረት ለውጥ፣ ድኅነት ቅነሳ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች የደቡብ-ደቡብ ትብብርን ለማሣደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
#ሁሌም_ከምስጋና_የሚልቀው_የከተማችን_ነዋሪ ዛሬም 🙏
ለውጡን ተከትሎ የራሳቸውን የግል አጀንዳ ለማሳካት እና ዛሬ እየተገነባች ያለችውን የነገዋን ኢትዮጵያ ጉዞ ለማሰናከል ብዙዎች ብዙ አቅደዋል፣ ብዙም አድርገዋል። ከግባቸው ከጥቂት ያነሰ የኢምንቶች ኢምንት ነገር ለማሳካትም ሞክረዋል።
እነሆ ዘንድሮም ከተማችን #አዲስአበባ ን ብሎም ሃገራችን #ኢትዮጵያ ን የአጀንዳቸው ማራማጃ በማድረግ ለሁከትና ብጥብጥ የሚችሉትን ሁሉ ያህል ወዲህ ወዲያ ቢሉም በከተማችን ሰላም ወዳድ ነዋሪ፣ በፀጥታ መዋቅራችን ያላሰለሰ ጥረት፣ በከተማ አስተዳደራችን ልፋት፣ በሰላም ሰራዊታችን ትጋት እና በሌሎችም ባለ ድርሻ አካላት ትብብር የቆሞ ቀሮች ሃሳብ ገደል ገብቶ #ከተራ ንም #ጥምቀት ንም #ቃናዘገሊላ ንም ያለምንም ኮሽታ አልፈነዋል።
ለዚህ ስኬት ከቆሞ ቀሮቹ በስተቀር የማይመሰገን አካል አይኖርምና ሁላችንም #እናመሠግናለን ለማለት እፈልጋለሁ።
ሃገራችን #ኢትዮጵያ የያዘችው ጉዞ ከዛሬ የዘለለ ነገርን የተሻገረ ለቀጣይ ትውልድ ተስፋን ብቻን ሳይሆን ተጨባጭ ለውጦችን ለማስረከብ የሚተጋ ጉዞ ነው።
የዛሬው ልፋታችን የነገዋን የበለፀገች #ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ ነው። የልጆቻችን፣ ልጅ ልጆቻችን እና የትውልዳችን ተስፋ ዕውን ይሆናል። የበለፀገች ሃገር ባለቤትም ይሆናሉ።
ከዚህ ጉዞ ወደኃላ ሊጎትተን የሚያስብም፣ የሚያቅድም፣ የሚችለውን ያህል የሚንደፋደፍም ሁሉ ከቅዠቱ ጋር አብሮ ይከስማል፣ ይቀበራል።
#የበለፀገ_ትውልድ_ለበለፀገች_ኢትዮጵያ
#የበለፀገች_ኢትዮጵያ_ለበለፀገ_ትውልድ
https://twitter.com/ProsperityKera
አቶ ተፈራ ከተማ አበበ የተባለ የፅንፈኛው ከፍተኛ አመራር በአየር ወለድ ክፍለ ጦር ተማረከ 💪💪💪💪💪💪💪💪
ይህ ግለሠብ ከዚህ በፊት መምህር የነበረ ሲሆን ፅንፈኛ ቡድኑን ከተቀላቀለ አምስት ወራት ሆኖታል፡፡ በፅንፈኛው ሀይል ውስጥ በህዝብ ግንኙነት በፕሮፖጋንዳና ቅስቀሳ ሀላፊነት ተመድቦ የብዙ ደሀ ልጆችን ወደ እሳት የማገደ ነው፡፡
አሁን ግን ሁኔታው ሁሉ ገብቶኛል በአማራ ህዝብ ላይ በደል ፈፅሜያለሁ ብሏል። ፅንፈኛው ቡድን በህዝብ ላይ ከፍተኛ መዋጮን ጥሎ በግድ እያስከፈለ መሆኑንም ተናግሯል። ለአርሶ አደሩ የመጣን መዳበሪያና የምግብ ዘይት ዘርፎ መልሶ በዉድ ዋጋ አንዱን ከረጢት መዳበሪያ ማለትም 50 ኪሎ ግራም የሚመዝን መዳበርያ እስከ አራት ሺህ ብር ለገበሬው በመሸጥ ህዝብን አራቁቷል፡፡ በድሏል ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ እኔም ነበርኩበት ተሳትፌያለሁ ሲል በሠራዊቱ የተያዘው አቶ ተፈራ ተናግሯል፡፡
ፅንፈኛው ቡድን በግንባር ቀደምትነት የአማራ ህዝብ ጠላት ነው ፣የምስራቅ አፍሪካን ለማመስም እቅድ ያለው ስለመሆኑም አጋልጧል።
የኤርትራን ሉአላዊነት የማይቀበል ሆኖለት እንኳ ስልጣን ቢይዝ ኢትዮጵያን የማልማት ሳይሆን ቀጣይ የጦርነት አውድማ ለማድረግ ሴራ ጠንስሶ የሚንቀሳቀስ ሃይል መሆኑንም ተናግሯል።
በመሆኑም ይህ ፅንፈኛ ቡድን ጋላቢው ሌላ የሆነ የኢትዮጵያ አጥፊ ፈረስ በመሆኑ መጥፋት እንዳለበት ተረድቶ የአማራ ህዝብ ከሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ጎን ሆኖ መዋጋት አለበት ብሏል አቶ ተፈራ ፡፡
አቶ ተፈራ ከተማ አበበ ተሳስታችሁ ከዚህ ቡድን ጎን የተሰለፋችሁ ወንድሞቼ ሁሉ ከእኔ ልትማሩ የገባል እኔ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ተይዠ በፍቅር ቤቴ ገብቻለሁ ሀገሬንም ማድማት ትቻለሁ ሁሉም ነገር እንደሚወራው አይደለምና ከቡድኑ መሠሪ ሴራ ራሳችሁን አግልላችሁ ለሠራዊቱ አጃችሁን ሰጥታችሁ ወደ ሠላማዊ ኑሯአችሁ ተመለሡ ሲሉ ለቡድኑ አባላት ጥሪ አቅርቧል።
ግብ ለሌለው አላማ ለግለሠቦች ፍላጎት ብላችሁ ህይወታችሁን አትጡ ያለው አቶ ተፈራ ሀገሩን የሚወድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አለና ከመሞት ውጭ ምንም አታመጡም ህዝባችሁን ከማሠቃየት ይቅርታ ጠይቁና በሠላም ለመከላከያ እጅ ስጡ ሲል ለቡድኑ አባላት መልዕክት አስተላልፏል።
ከአቶ ተፈራ ከተማ ጋር ተሽከርካሪዎችና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
"ዓድዋ አለምን የለወጠ ክስተት ነው" - ዶ/ር ህያው ተረፈ - በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአይ ቢ ሲ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር
https://twitter.com/ProsperityKera
"አፍሪካን ያገለለ የፀጥታው ምክር ቤት ተቀባይነት የለውም" - አንቶኒዮ ጉታሬዝ - የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ
አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አንድም ቋሚ ተወካይ አለማግኘቷ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉታሬዝ ተናገሩ፡፡
የተመድ ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉታሬዝ ይህን ያሉት በኡጋንዳ ካምፓላ የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባኤ ላይ ነው፡፡
ተመድን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ከ80 ዓመታት በፊት የነበረውን ሳይሆን አሁናዊና ወቅታዊ ዓለም አቀፍ ሁኔታን ታሳቢ ያደረጉ መሆን እንዳለባቸው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
የዓለም ሀገራት በጋራ አመራር የሚሰጡባቸው ተመድን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ ዳግም መተማመን ለመፍጠር የፊታችን መስከረም የሚካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆንም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ክርስቶስ ከልደቱ እስከ ጥምቀቱ በተጓዘ ጊዜ የኦሪቱ መሥዋዕት አልቀረም፤ የኦሪቱ የበላይነት አልተወገደም፤ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ አልተቀደደም፤ ምኩራብ አልተሻረችም፤ በሰማይና በምድር፣ በሰውና በመላእክት፣ በነፍስና በሥጋ መካከል የነበረው ጠላትነት ገና ሙሉ በሙሉ አልተሻረም፤ የሞት መውጊያ አልተሰበረም፡፡ በዚህም የተነሣ አብዛኛው ሰው ከጨለማው ዘመን እየወጣ፣ ከመከራው ዘመን እየተሻገረ፣ ከሞት ቀንበር እያመለጠ መሆኑን ገና አልተገነዘበም፡፡ ነገር ግን ቀንበሩ እየተሰበረ፣ ሞትም እየተሻረ፣ አዲስ ሕይወት እየተበሠረ፣ አዲስ መንገድም እየተጀመረ ነበር፡፡
ሀገርን ለማዳን የምንሠራቸው ሥራዎች ብርሃናቸው ቦግ ብሎ ዛሬ ላይበራ ይችላል፡፡ ለሁሉም እኩል ላይታዩ ይችላሉ፡፡ ካለፈው የችግር ጊዜ እየወጣን መሆኑ፣ ወደ አዲስ ሀገራዊ ሁኔታ እየተሻገርን መሆኑ ለጊዜው ላይታወቅ ይችላል፡፡ ከጥምቀት በኋላ ለሁሉ እንደተገለጠው፣ የኢትዮጵያ ትንሣኤና ሕዳሴ ለሁሉም ግልጽ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡
© Abiy Ahmed Ali (phd) - የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
https://twitter.com/ProsperityKera
"ሰው ቤት ይሰራል፤ እኛ መንገድ እንሰራለን፤ ወጣቱ ዛፍ ይተክላል፤ ይህ እየተገናኘ እየሄደ ሲሄድ የተሰራ ሀገር ይኖረናል!!"
@AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
ጫካን የሚያቆም መንግስት አልፈልግም የሚል ህዝብ እንደሚፈጥር እርግጠኛ ነኝ።
@AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
ለአብቹ ፈተናዎች ወደ ከፍታ መንበር መወጣጫ እርካብ እንጂ ካቀደው የሚመልሱት መሰናክሎች ሆነው አያውቁም!
@AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
ነገን አሻግሮ በማየት የዛሬው ችግር ሳይበግረው መቆም መፅናት የሚችል ብርቱ መሪ!! @AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
የወል ትርክታችንን እየገነባን የነገ ታሪካችንን በላባችን እውን እናደርጋለን!
የብሔር፣ የሀይማኖት፣ የባህል ወዘተ ብዝሀነቶች ፀጋዎቻችን ናቸው። የራሳችንን ማንነት አክብረን የሌሎችንም ማክበር ብቻ ሳይሆን ማስከበር ሰብአዊ ግዴታችን መሆኑኑ በተግባር እያጎለበትን ስንሄድ ለሰው ልጆች ክብር ሲሉ ራሳቸውን መስዋዕት እንዳደረጉት አባት እናቶቻችን የአርበኝነትን ክብር እንጎናፀፋለን።
የአገራችንን ሉዓላዊነት ያስጠበቁና የሚያስጠብቁ፣ በሩጫውና በሌሎችም መስኮች ኢትዮጵያን ያስጠሩ ጀግኖቻችን ብሔራዊ ጀግኖቻችን ናቸው።
ኢትዮጵያውያን ከውጭ የተቃጡብንን ጦርነቶች በጋራ የመመከት ባህል ቢኖረንም የውስጥ ችግሮቻችንን በውይይት የመፍታት ውስጣዊ መስተጋብር አላዳበርንም።
በታሪካችን ካለፍንባቸው በላይ ችግሮችን የተጋፈጡ አገሮች ትርክታቸውን በአወንታ በመቃኘታቸው ሀገረ-መንግስት ግንባታቸውን አጠናቀዋል። ትርክትን በአሉታዊነት የቃኙት ደግሞ ተበታትነዋል፣ ተገዳድለዋል፣ ከነበሩበት ገናና ታሪክ ቁልቁል ተፈጥፍጠዋል።
የኢትዮጵያ ትርክት በአንድ በኩል ፍፁማዊ አንድነትን የሚሰብክ በሌላ በኩል ደግሞ ፍፁማዊ ልዩነትን የሚያቀነቅን ዋልታረገጥነት ተጫጭኖት ለዘመናት ዘልቋል። በሚዛናዊነት ላይ ያልቆመው፣ በተንሸዋረረ የታሪክ እይታ የሚባዝነው የአገራችን የተዛባ ትርክት በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮቻችን ምንጭ ነው።
ፓርቲያችን ብልፅግና ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትን እና ህብረብሔራዊነትን የሚያጎለብት የብሔራዊነትና የአርበኝነት ክብርን የሚያጎናፅፍ አሰባሳቢውንና ታላቁን አገራዊ ትርክት ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ትርክትን የምንገራው ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የመከባበር እሴቶቻችንን በማጎልበት ነው።
ከመጠላለፍ ይልቅ አብሮ መልማትን፣ ከመነቃቀፍ መተባበርን፣ ከመራራቅ መቀራረብን ምርጫችን ስናደርግ የወል ትርክታችን የተነሰነሰበትን አቧራ አራግፎ ይነሳል።
ከስሜታዊነት ይልቅ አስተዋይነትንና ሚዛናዊነትን፣ ከቂም በቀል ይልቅ ይቅር መባባልን፣ ባለፈ ትርክት ከመበላላት ይልቅ የነገን ታሪክ በጋራ መስራትን፣ ጠብመንጃ ከመማዘዝ ይልቅ ለሰላም መንበርከክን ባህል ስናዳብር የህብረ-ብሔራዊነታችንን በረከት እንቋደሳለን።
ታላቁ አገራዊ ትርክት በቤተሰብ የምንነጋገረው፣ በትምህርት ቤት የምናስተምረው፣ በየሀይማኖት ተቋሞቻችን የምንሰብከው፣ በየሚዲያው የምናሰራጨው ሀሳብ ውጤት በመሆኑ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁላችንም እርብርብ የሚጠይቅ ነው።
አሰባሳቢውን ታላቁን አገራዊ ትርክት ከማስረፅ ባለፈ ይህ ትውልድ በላቡ መስዋዕትነት ታሪክ እየሰራ መሆኑን ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገአችንን አስተሳስሮ የያዘው የታላቁ ትርክት ውጤት የሆነው አድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዜምን እና ታላቁ የህዳሴ ግድባችንን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera
የአደጋ ተጎጂዎች የካሣ ክፍያ ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ነው
የመንገድ ደህንነት መድህን ፈንድ አገልግሎት በሶስተኛ ወገን መድህን ሽፋን ማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ የሚታየውን ክፍተት ለማስተካከል ማሻሻያ እንደሚደረግ አስታወቀ።
የአገልግሎቱ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፈቲያ ደድገባ÷ የመንግስትና የግል ህክምና ተቋማት በትራፊክ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች እስከ 2 ሺህ ብር በነፃ አስቸኳይ የህክምና እና በትራፊክ አደጋ ለደረሰ የሞት አደጋ መንግስት ካሳ ይከፍላል የሚሉት ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው ተናግረዋል።
ማሻሻያው የወቅቱን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ መሆኑን ነው ምክትል ስራ አስፈጻሚዋ የጠቀሱት።
ማሻሻያው እንዲጸድቅ ለሚመለከተው አካል መላኩን ጠቅሰው፤ በቅርቡ ጸድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
Ethiopia’s commitment for peace and security in Somalia has been demonstrated through the blood and sweat of its precious sons and daughters. Ethiopia & Somalia are not just neighbors who share a border but they are fraternal nations sharing a common language, culture & people.
https://twitter.com/ProsperityKera
በወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር የተጀመረውን የፈረስ ግልቢያና ትርኢት በማስፋትና ሌሎች ውድድሮችን በማካተት አካባቢውን የስፖርትና የባህል ትርኢት ማዕከል ማድረግ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በገበታ ለሀገር የተገነባውና በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት በአካባቢው መሠረተ-ልማት እንዲስፋፋና በርካቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለ ነው።
የጥምቀት በዓል በወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት በወንጪ ሀይቅ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሯል።
በሌላ በኩል በደንዲ ሀይቅ ዳርቻ የፈረስ ጉግስ ውድድርና ትርኢት ለመጀመሪያ ጊዜ በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል።
በመርኃ ግበሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር እና የወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ውድድሩን ያስጀመሩት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፥ የኦሮሚያ ክልል ለቱሪዝምና ባህል ልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
በክልሉ 5 መቶ ሺህ ሄክታር መሬት በመከለል 24 ፓርኮችና 18 የኢኮ ቱሪዝም ማዕከላትን የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህም መካከል በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የተገነበው የወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር እና ሎጅ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለአከባቢው ማህበረሰብ የገቢ ምንጭ መሆን መጀመሩን ገልጸዋል።
በደንዲ ሀይቅ ዳርቻ ዓመታዊ የፈረስ ጉግስ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ መጀመሩን አያሌ ፋይዳዎች እንደሚኖረው ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ለፈረስ ያለውን ክብርና ታሪክ ከግምት በማስገባት የነበረውን ባህል በጠበቀ መልኩ በማልማት የምጣኔ ሃብት ምንጭ ለማድረግ እየሰራ ነው ብለዋል።
ፈረስ የኦሮሞ ህዝብ በደስታና በሀዘኑ፣ በባህልና በበዓል ወቅት ደምቆ የሚታይበትና የእርስ በርስ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት መሆኑን ገልጸዋል።
እንደዚሁም ጠላት ሀገርን በወረረ ጊዜ አባቶች ከፈረሶቻቸው ጋር በመሆን የተቃጣባቸውን ጥቃት መመከት እንደቻሉ አስታውሰዋል።
በውንጪ-ደንዲ የኢኮ ቱሪዝም መንደር የተጀመረውን የፈረስ ግልቢያና ትርኢት ውድድር በማስፋት በሀገር አቀፍና በቀጣናው ትልቁ የፈረስ ወድድር ስፍራ ማድረግ የሚያስችል ዕድል መኖሩን ጠቁመዋል።
ከዚህም ባለፈ ስፍራውን የብስክሌትና የሌሎች ውድድሮች ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቁመው በቀጣይ ሳምንት በወንጭ ሃይቅ የአትሌትክስ ውድድር ይካሄዳል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል የቱሪስት የመህስብ ስፍራዎችን በልዩ ትኩረት ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሮን በጠበቀ መልኩ በስፋት እያለማ መሆኑን ጠቅሰው ህብረተሰቡ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር እና የወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በበኩላቸው ይህን መሰል ሁነቶች ቱሪስቶችን የመሳብ አቅማቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በመሆኑም የህዝቡን ባህልና ክብር በሚመጥን መልኩ በየዓመቱ በተጠናከረ ሁኔታ ውድድሮችንና ሁነቶችን ማካሄድ ይገባል ብለዋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የውድድሩ ተሳታፊ ፈረሰኞች እንደገለጹት ውድድሩ ለቱሪስት መስህብ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ባህላቸውን ለማስተዋወቅ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው።
ከተወዳዳሪዎቹ መካከል አቶ ቤኩማ ዋቁማ በውድድሩ መሳተፋቸው ትልቅ ደስታ እንደፈጠረባቸው ገልጸው የአባቶቻቸውን ታሪክና ባህል ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በውድድሩ ያገኙትን ልምድ ተጠቅመው በቀጣይ ጠንካራ ተወዳዳሪ ለመሆን ዝግጅት እንደሚያደርጉ የገለጹት ደግሞ አቶ ሞቲ ኢቲቻ ናቸው።
በውድደሩ በፈረስ ጉግስ 1ኛ በመውጣት የዋንጫና የ50 ሺህ ብር ተሸላሚ የሆኑት መስቀሉ ረጋሳ በበኩላቸው በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይም አሸናፊ ለመሆን ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በፈረስ ጉግስ ውድድሩ ላይ ከደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች የተውጣጡ ፈረሰኞች የታደሙ ሲሆን፤ ከአንድ እስከ ሶስት የወጡ አሸናፊዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው 50 ሺህ፣ 20 ሺህ እና 10 ሺህ ብርና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ውድድሩ የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው በስነስረዓቱ ላይ ተገልፅዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ኬንያ በአጼ ሀይለስላሴ ስም የሰየመችውን ፈጣን መንገድ አስመረቀች።
ዋና መንገዱ በናይሮቢ ይደርሱ የነበረ የትራፊክ መጨናነቅን ያስቀራል ተብሏል።
አዲሱ የመውጫ መንገድ በአምስት ወራት ውስጥ በቻይና እና ኬንያዊያን ተቋራጮች ተገንብቷል።
ኬንያ በአጼ ሀይለስላሴ ስም የሰየመችውን ፈጣን መንገድ አስመረቀች።
ጎረቤት ሀገር ኬንያ የፈጣን መንገዷን መውጫ ኢትዮጵያን ከ40 ዓመት በላይ ለመሩት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በመሰረቱት አጼ ሀይለስላሴ ስም ሰይማለች።
ካሳለፍነው ሀምሌ ጀምሮ የተገነባው ይህ የፈጣን መንገድ መውጫ በናይሮቢ ዋና የትራፊክ ፍሰትን ለማቀላጠፍ በሚል በቻይና እና የኬንያ ተቋራጮች ተገንብቷል።
መንገዱ ከዛሬ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ሁለት ሰዓት ይፈጅ የነበረውን መንገድ ወደ 20 ደቂቃ ዝቅ እንዲል እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ባለ አምስት መስመር ያለው ይህ የመውጫ መንገድ ከናይሮቢ በፍጥነት ለመውጣት እንደሚያስችል የኬንያ ትራንስፖርት ሚንስትር ኪፕቾምባ ሙርኮመን ተናግረዋል።
ሚንስትሩ አክለውም አዲሱ መንገድ ወደ ማዕከላዊ የቢዝነስ ቦታዎች እና መንግስታዊ ተቋማት አካባቢ ያሉ መጨናነቆችን ያስቀራልም ብለዋል።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በክፍያ ይጠቀማሉ የተባለ ሲሆን በቀን 65 ሺህ አሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ተገልጿል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ስንብት እና የቀብር ስነስርዓት በነገው ዕለት ይከናወናል።
አስከሬኑ ዛሬ እሁድ ጠዋት በዋሽንግተን አቆጣጠር ከጠዋቱ 10 AM ተነስቶ ሰኞ ጥር13 ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ቦሌ አየር ማረፊያ በጉምሩክ በር በኩል አቀባበል ይደረጋል።
በነገው ዕለት ከጠዋቱ 4 እስከ 4፡30 ሰዓት ሚሊኒየም አዳራሽ ይደርሳል።
ከጠዋቱ 5:00 እስከ ቀኑ 6፡30 በሚሊኒየም አዳራሽ የስንብት መርሐግብር ይካሄዳል።
ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ፍትሃት እና የቀብር ስነ ስርዓት ይፈጸማል።
https://twitter.com/ProsperityKera
አዲሱ የቲክቶክ ገፄ 👇 Pls Follow ያድርጉ?
አመሠግናለሁ 👇👇👇
estifopp?_t=8jDTFBZ7AX7&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp?_t=8jDTFBZ7AX7&_r=1
"ጥቁር ድመት በጨለማ መፈለግ አስቸጋሪ ነው በተለይ ድመቷ ከሌለች" - ረዳት ፕ/ር አበባው አያሌው - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እና የታሪክ መምህር
https://twitter.com/ProsperityKera
የዘንድሮው የውጭ ጉዳይ ኤግዚቢሽን ካተረፈልን ነገሮች አንዱ መጻሕፍት ናቸው። ሁለት መጻሕፍት ታትመዋል። አንደኛው መጽሐፍ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ታሪክ ከ1900 - 2015 የቃኘ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ የዘመናዊቷን ኢትዮጵያ ታሪካዊ መረጃዎች አጠናቅሯል። በሞያው ያጠኑ ምሁራንን ከተቋሙ በሳል ዲፕሎማቶች ጋር አቀናጅቶ የተሠራ በመሆኑ ደርዘ ሰፊ ነው። አለማንበብ ይቆጫል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የፅንፈኛ ሃይሉ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሠደ ነው።
የኮማንዶ ክፍለጦር በሰሜን ሸዋ ዞን ሰላ ድንጋይ እና በአከባቢው መሽጎ የነበረው ፅንፈኛ ቡድን በመደምሠሥ በፌሮ ብረት ለበስ አድርጎ የሰራቸውን ሁለት ተሽከርካሪዎች መማረኩን የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አደራጀው ሠረበው ገልፀዋል፡፡
ክፍለጦሩ ዘመቻ ሚኒሊክ እና መብረቅ ብርጌድ በሚል ስያሜ በፌሮ ብረት ታጥሮ ለሽብር ስራ ያዘጋጃቸውን ተሽከርካሪዎች ከመማረኩም በላይ ፍቃዱ የተባለውን የብርጌዱን መሪ መግደሉንና ፅንፈኛው መብረቅ ብሎ የሚጠራውን ብርጌድ በመደምሰስ ድል አስመዝግቧል ብለዋል፡፡
ፅንፈኛው ቡድን በዚህ ባዘጋጀው ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ተከልዬ ሠራዊቱን እበትንበታለሁ ብሎም አጠቃበታለሁ ብሎ ያዘጋጀው ቢሆንም ያሰበው ሳይሳካ ከነህልሙ ተቀብሯል ያሉት አዛዡ ብረት በብረት በይዶ የሠራው በፓትሮል መኪና ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ሰውን ከተፈጥሮ ያዋሀደ ታላቅ መሪ አብቹ አባመላ!!
@AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
Tangible growth of Ethiopia
👉In terms of food sustainability
👉In terms of Eco-Tourism
👉In terms smart city
@AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
ከጫፍ ጫፍ የደመቀው ጥምቀት በሰላም ተጠናቋል
https://twitter.com/ProsperityKera
እነ ጭር ሲል አልወድም አመለኞቹ እዚህም እዛም ይሯሯጣሉ፤
#አመለኛው_እሱም ፀጥ ብሎ የነገዋን #ኢትዮጵያ ዛሬ ይሰራል
https://twitter.com/ProsperityKera
ሁለቱም አመለኞች ናቸው። 👇👇👇
የአጥፊነት አመል፤ እኔ ያልኩት ካልሆነ አመል፤ ያላማሰልኩት ወጥ አይጥምም የሚል አመል፤ ቆሞቀር አመል ...
Vs
በጋራ ቆመን፣ በፍቅርና በይቅርታ ተደምረን፣ የነገዋን #ኢትዮጵያ ዛሬ እንስራ፤ ... የሚል አመል
https://twitter.com/ProsperityKera