prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Bright future for 🇪🇹!!
Positive indicators point to a promising future for Ethiopia's economy, as the nation embraces economic diversification, infrastructure development, and improved business climate. #HandsOffEthiopia #NoMore_Landlocked #Fast_Growing_Ethiopia
#Abiy_Ahmed

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ስብራትን መጠገን፤ ለትውልድ መታመን" - ክፍል 1

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ያቀረቡት ገለጻ - ክፍል 1

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያ ብቻ አይደለም፤ ለኢትዮጵያውያን ብቻም አይደለም፤ ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ ኩራት ነው" ክብርት ከንቲባ አዴ @AdanechAbiebie 🙏🙏🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ሀገርን ለማዳን የምንሠራቸው ሥራዎች ብርሃናቸው ቦግ ብሎ ዛሬ ላይበራ ይችላል፡፡ ለሁሉም እኩል ላይታዩ ይችላሉ፡፡ ካለፈው የችግር ጊዜ እየወጣን መሆኑ፣ ወደ አዲስ ሀገራዊ ሁኔታ እየተሻገርን መሆኑ ለጊዜው ላይታወቅ ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ትንሣኤና ሕዳሴ ለሁሉም ግልጽ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡"
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አንድ ነገር ላስታውሳችሁ

በማንኛውም ማሕበራዊ ግንኙነት በየእለቱ ለምታገኟቸው ሰዎች ደስተኛነት እናነት ሃላፊነት ሊሰማችሁ አይገባም፡፡

ጠቋሚ ሃሳቦች . . .

•  ሁል ጊዜ ደስተኛ የመሆናቸውንና ያለመሆናቸውን ሁኔታ የማየትና የመከታተል ዝንባሌ ካላችሁ …

•  የሰዎቹ ፊትና ሁኔታ በተለወጠ ቁጥር የሚጨንቃችሁ ከሆነ …

•  ደስ ያላቸው ሲመስላችሁ ደስ የሚላችሁ፣ ደስ ያላላቸው ከመሰላችሁ ደግሞ ውጥረት ውስጥ የምትገቡ ከሆነ ...

እና መሰል ሁኔታዎች የሚንጸባረቅባችሁ ከሆነ ለሌሎች ሰዎች ደስታ እናንተ ሃላፊነትን የመውሰድ ችግር እንዳለባችሁ ጠቋሚ ናቸው፡፡

የመፍትሄ ሃሳቦች . . .

•  ከእነሱ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሚዛናዊ እና ጤናማ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

•  ያጠፋችሁት ጥፋት ካለ በግለጽ በመንገር ይቅርታን በመጠየቅ እርማት ስጡት፡፡

•  ለሚያሳይዋችሁ ደስተኛ የመሆንና ያለመሆን ተለዋዋጭ ስሜት ምላሽ ባለመስጠት ያንን ተቀያያሪ ባህሪያቸውን ባለመመገብ አስርቡት፡፡

•  ለእነሱ ደስተኛነት ሃላፊነት ያለመውሰዳችሁን ያህን የእናንተንም ደስተኛነት በእነሱ ሁኔታ ላይ በማስደገፍ እነሱ በተለዋወጡ ቁጥር አትደናበሩ፡፡

ነጻ ሰዎች ናችሁ!

የሰላምና የደስታ ቀን ይሁንላችሁ!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አዲስ አበባ ኮልፌ የሚገኘው እፎይታ ገበያ ከመሸ የእሳት አደጋ አጋጥሞታል ... 😭😭😭

ዛሬ ምሽት 3:00 ሰአት የተነሳው እሳት አደጋ ከማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየተራባረቡ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያሳያል።

ቦታው በቅርብ ጊዜ ተመሳሳይ የእሳት አደጋ አጋጥሞት ነበር።

የእሳቱ መነሻ ምን እንደሆነ እስከ አሁን አልታወቀም።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ሰላም_አሸንፏል 🙏 የጥምቀት በዓላችንን በትልቅ ድል ተወጥተነዋል። ከባድ የ 24 ሰዓት እና ያለ እረፍት ስራችንን ጨርሰን ዛሬ ከአምስት ቀናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ አረፍ ለማለት ችለናል።

ተመስገን ብለናል። ጠላቶቻችን ካሴሩብን ወጥመድ በፈጣሪ እርዳታ፣ በህዝባችን ጥንካሬ፣ በፀጥታ መዋቅራችን አስተማማኝ ቁመና፣ በከተማ አስተዳደራችን ጥረት፣ ... ወጥተናል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ከሰዓት ስብሰባ ጀምረናል።

Koreen Hoji-raawwachiiftuu Paartii Badhaadhinaa dhimmoota ijoo biyyaafi ajandaawwan paartii garaagaraa irratti marii'achuuf har'a waaree booda walgahii jalqabneerra.

This afternoon we have began Prosperity Party’s Executive Committee meeting to discuss key national as well as party agenda items.
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ 2,274 የመንግሥት ሰራተኞች ፈተና ይቀመጣሉ።

ዛሬ ለባህሪና ብቃት ምዘና ፈተና የሚቀመጡት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የማዕከልና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞች ናቸው

ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቪርስቲ በ6 ኪሎ ካምፓስ ውስጥ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ የመሬት ልማት አስተዳደር አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም 15,151 የአስተዳደሩ አመራሮች፣ ሠራተኞች / ባለሞያዎች የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና መውሰዳቸውና ውጤቱም ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስምንተኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል ከፊታችን ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የባህል ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አስፋው ኩማ÷ ፌስቲቫሉ ከጥር 16 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በአዲስ አበባ ሙዚዬም እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በተዘጋጀው የንባብ ባህል ፌስቲቫል በከተማው ለንባብ ባህል ዕድገት የሚያግዙ መልዕክቶች በማዘጋጀት ተደራሽ እንደተደረገ ገልጸዋል።

በዚህም አዲሱ ትውልድ ጊዜውን አልባሌ ቦታ እና በማይጠቅሙ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ተጠምዶ ከማሳለፍ እንዲቆጠብና ንባብን ባህል እንዲያደረግ ለማነቃቃት አበርክቶ ማድረጉን ተናግረዋል።

ዘንድሮም ስምንተኛው ዙር ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል ''አንባቢ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና'' በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በፌስቲቫሉ በህትመት ዘርፍ ዕድሜ ጠገብ የሆኑ ማተሚያ ቤቶች፣ ደራሲያን፣ በመጻሕፍት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ አካላት እንዲሁም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ቤተ-መጻሕፍቶች ይሳተፋሉ ተብሏል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#የውሻዬና_የመኪናው_ነገር
የምትፈልገው (Ur wants) እና የሚያስፈልግህ (Ur needs)

አንድ ሰው ለወዳጁ እንዲህ ብሎ አጫወተው፡፡ “የውሻዬና የመኪናው ነገር በጣም ነው ያደከመኝ፡፡ በሰፈራችን ያለፈው መኪና ሁሉ አንድም አይቀረውም፣ በብርቱ እየተከታተለ ይጮሃል፡፡ ያየውን መኪና ሁሉ ለተወሰነ ርቀት ካሳደደው በኋላ ተመልሶ ይመጣል፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ሌላ መኪና ሲመጣ ጠብቆ ያንኑ ነገር ይደግማል፡፡ ስለእርሱ እኔ ደከመኝ”፡፡

ወዳጁ ይህንን ከሰማ በኋላ አንድ ጥያቄ ጠየቀው፣ “ለመሆኑ፣ ውሻህ መኪናን አባርሮ የሚደርስበት ይመስልሃል?” ሰውዬውም መልሱ እንዲህ የሚል ነበር፣ “እኔን የጨነቀኝ የመድረስ ብቃቱ አይደለም፣ ከዚህ በፊት በቀስታ የሚሄዱ መኪናዎች ላይ ሲደርስ አይቻለሁ፡፡ ልክ ሲደርስባቸው ፊቱን አዙሮ ይመለስና ሌላ የሚያልፍን መኪና እንደገና ለማሳደድ ይጠብቃል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ይህንን ሲያደርግ ነው የሚውለው፡፡ ውሻዬ የሰው ቋንቋ ቢችል፣ ጊዜህን በአግባብ ተጠቀምበት ብዬ እመክረው ነበር”፡፡

“የስኬት የመጀመሪያው መመሪያ ፍላጎት ይባላል - የምትፈልገውን ማወቅ፡፡ ፍላጎት አለህ ማለት ዘርህን ዘራህ ማለት ነው” - Robert Collier

አሁን በጽኑ የምትፈልገውን ነገር ቆም ብለህ አስበው፣ ብትደርስበትና በእጅህ ቢገባ ምን ታደርጋለህ? ለዚህ ጥያቄ ብዙም ሳታስብና ሳትጨናነቅ ቁልጭ ያለ መልስን መስጠት ካልቻልክ ምናልባት የምትከታተለው ነገር ለምንም ጥቅም የማይውል ጊዜ ማባከኛ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የሚፈልጉት ነገር ምን እንደሆነ አያውቁትም፡፡ በአንድ ነገር ላይ ገንዘባቸውን ያፈስሳሉ፣ ጊዜአቸውን ይሰዋሉ፣ ብዙ ኪሎ ሜትር ይጓዛሉ፣ ከዚያም ያንን ነገር ልክ እጃቸው እንዳስገቡት ሲያውቁ ቀድሞውንም የሚፈልጉት ነገር እንዳልሆነ ይገነዘባሉ፡፡ ከዚያም እንደገና ሌላ ነገር መከተል ይጀምራሉ፤ አዙሪቱ ይቀጥላል፡፡

አሁን በብርቱ የምትከታተለውን፣ ብዙ ጊዜህን የምታጠፋበትን፣ ገንዘብህን ያባከንክበትን ነገር በእጅህ ብታስገባው፣ በህይወትህ ካለህ ዋነኛ ዓላማ ጋር አብሮ ካልሄደና ወደትምሄድበት የሕይወት አቅጣጫ አንድ እርምጃ ካላራመደህ ጊዜህን በከንቱ እያባከንክ ነው፡፡ የማያዛልቅን ነገር ማባረር! የምትከተለው ነገር በምትሄድበት የሕይወት ዓላማ አቅጣጫ መሆኑን ማወቅ የአዋቂነት ሁሉ አዋቂነት ነው፡፡ መመለስ ያለበት ጥያቄ፣ “የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው?” የሚለው ነው፡፡

ፍላጎትህን በማወቅ ስትደላደል ሌላው ሰው ላይ አይተኸው ያማረህ ነገር ሁሉ የግድ እንደማያስፈለግህ ማስተዋል ትጀምራለህ፡፡ በሕይወትህ በምትፈልገው (Your wants) እና በሚያስፈልግህ ነገሮች (Your needs) መካከል ለይተህ ማወቅ በብዙ ይጠቅምሃል፡፡ የምትፈልገው ነገር ሁሉ የሚያስፈልግህ ላይሆን ይችላል፤ በተቃራኒው ደግሞ አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልግህን ሁሉ ለጊዜው ላትፈልገውና ልታስተላልፈው ትችላለህ፡፡ የእነዚህን ሁለት ነገሮች ልዩነት ጥርት ባለ መልኩ መለየት አለብህ፡፡ የምትመኛቸውንና የምትፈልጋቸውን ሁሉ ከመከተል ይልቅ በሚያስፈልጉህ ነገሮች ላይ ማተኮር ስትጀምር፣ ሁኔታው ለሌሎች ግር ቢልም ለአንተ ግን እውነታው ኩልል ብሎ ይታይሃል፡፡

በሚያስፈልገንና በእርግጥም ብንደርስበትና በእጃችን ብናስገባው ለመልካም አላማ ልንጠቀምበት በምንችል ነገር ላይ ትኩረትን መጣል ራስን የመግዛት ዲሲፕሊን ይጠይቃል፡፡ ራስን የመግዛት ዲሲፕሊን የንግስና ሁሉ ንግስና ነው፡፡

“እኔ በእርግጥ ንጉስ ነኝ፣ ምክንያቱም ራሴን መግዛት አውቅበታለሁና” - Pietro Aretino

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያ ወደብ ከቻይና እስከ ብሪክስ!

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ አለም ካሳካቻቸው ትላልቅ ድሎች መሃል አንዱ የብሪክስ አባልነት ማግኘቷ ነው። #BRICS አባል ሃገራቶቹን በንግድና በኢንዱስትሪ እያያዘ ይገኛል።

@AbiyAhmedAli

@EngGiduma

@Qarreeoromia

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከተማችን ሰሟን እየኖረች ነው

አሻራ ማኖር የሚችሉ እጆች እስካሉ ድረስ የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ ውበት መገለጡ አይቀሬ ነው።

በደማቅ ውበት እንደ ስሟ አዲስ አበባ እየሆነች ያለችው የሁሉም መናሀሪያ የአለማችን የዲፕሎማቶች መገናኛና የአፍሪካውያን ወንድሞቻችን ከተማ ጭምር የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ! በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአቃቂ እስከ ጫካ ፕሮጀክት ባስጎበኙን ወቅት የተሰራው የሸራተን መንገድ አይተን ነበር።

ይሄው ፈክቶና አብቦ በምሽት በደመቀ መልኩ ውበቴን እንካቹ እያለን ይገኛል! ደማቅ አሻራ ማኖር የቻሉ እጆች የተባረኩ ይሁኑልን! ከተማችን ሰሟን ኖረች! አበባ ስትባል ኖራ በአበባ እጦት ውስጥ ኖረች!

ዛሬ ግን እውነትም አበበች! እንደሰሟ አበባ እናደርጋታለን ብላ ነበር ከንቲባችን! ከአበባ በላይ ሌላ የአድናቆቷ ቃል ቢኖር በጨመርንበት ነበር።

ከቃሏ በላይ የሆነ ስራ ሰርታልናለች! ክብረት ይስጥልን!

/channel/ProsperityFirst

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ቀናተኛው_ንስር

የጥንት አፈ-ታሪክ ሁለት በአንድ አካባቢ ያደጉ ንስሮች እንደነበሩ ይነግረናል፡፡ እነዚህ ንስሮች ፈጣንና ወደ ከፍታ በመብረር አደናቸውን ከሩቅ በማየት የታወቁ ነበሩ፡፡ በመካከላቸው ግን ከባድ የሆነ ውጥረት አለ፡፡ አንደኛው ንስር ከሌላኛው ንስር የበለጠ ከፍታ የመብረር ብቃት ስለነበረው ከእርሱ እኩል መብረር ያቃተው ንስር እጅግ ይቀናበት ነበር፡፡ ቅንአቱ እየበረታ ሲሄድበት ይህንን በከፍታ የበለጠውን ጓደኛውን ለማጥፋት ወሰነ፡፡ በምን መልክ ሊያጠፋው እንደሚችል ሲያሰላስል ሳለ አንድ ቀስትን በእጁ የያዘ አዳኝ ሰው አገኘ፡፡

ወደ እርሱም ቀረብ በማለት ችግሩን አጫወተው፡፡ “ያ ንስር ይታይሃል?” አለው ቀና ብሎ በሚያስገርም ከፍታ ላይ በመብረር ላይ ያለውን ንስር እያሳየው፡፡ የማየት ብቃቱ ከንስር አይን ጋር ሊወዳደር ያልቻለው አዳኝ ሰው በመዳፉ የጸሃዩን ጨረር እየተከላከለ ለማየት ቢሞክርም ንስሩን ሊመለከተው አልቻለም፡፡ ይህ ሰው፣ “ንስሩ አይታየኝም፣ እጅግ ሩቅ ነው” ብሎ ለቀናተኛው ንስር መለሰለት፡፡ ይህ መልስ የቀናተኛውን ንስር ልብ ይበልጥ በምቀኝነት አቃጠለው - የጓደኛውን ወደከፍታ የመብረር ብቃት አስታውሶታልና፡፡

ጥቂት ጊዜ ከጠበቁ በኋላ ንስሩ አዳኙ ሊያየው ወደሚችልበት ቅርበት ስለወረደ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡ ቀናተኛው ንስር ለአዳኙ፣ “እባክህ ይህንን ንስር በቀስትህ ግደልልኝ” አለው፡፡ አዳኙም፣ “ለምን?” አለው፡፡ ቀናተኛው ንስር “ከእኔ በላይ ከፍ ብሎ መብረር ስለሚችል ቀንቼ ነው”፡፡ አዳኙም፣ “በእኔ እምነት ከእርሱ ለመሻል ከመታገል ለመሻሻል ብትጥር ይሻልሃል፡፡ ያም ሆነ ይህ፣ ቀስት ጨርሻለሁ እንጂ የጠየከኝን ነገር አደርግልህ ነበር” ብሎ መለሰለት፡፡ ቀናተኛው ንስር ጥቂት ካሰበ በኋላ፣ አንደኛውን ክንፉን ጠጋ በማድረግ “አንዲትን ላባ ከክንፌ ላይ ንቀልና እንደ ቀስት ተጠቀምበት” አለው፡፡ በዚህ ተስማሙና አንድን ላባ ከንስሩ ክንፍ ላይ በመንቀል ቀስቱን ለጥጦ ተኮሰ፡፡ ኢላማውን ግን አላገኘውም፡፡ ይቅርታ ይህንን ንስር ቀስቴ አላገኘውም ብሎት ጉዞውን ሊቀጥል ሲል፣ ቀናተኛው ንስር አንዴ በድጋሚ እንዲሞክር ለመነው፡፡ ከሌላኛው ክንፉ ሌላን ላባ ነቅሎ ከተኮሰ በኋላ አሁንም ኢላማውን ስለሳተው ለመሄድ ተነሳ፡፡ ቀናተኛው ንስር ግን በቀላሉ ሊለቀው አልቻለም፡፡ በዚህ ሁኔታ ክንፉን እያፈራረቀ ለአዳኙ እየሰጠው ብዙ ላባ ካስነቀለ በኋላ ሰውየው ስለደከመው ጥሎት ሄደ፡፡

በሁኔታው የተበሳጨው ቀናተኛ ንስር ጉዞውን ለመቀጠል ሲሞክር ለካ ላባው ሁሉ ከክንፉ ላይ ተነቅሎ አልቆ ነበር፡፡ መብረር አልቻለም፡፡ ይህ ሕይወቱን ሙሉ በከፍታ ላይ በመብረር የታወቀው ንስር “ዶሮ” ሆኖ ቀረ፡፡

ቅንአት ትኩረታችንንና ጊዜያችን ሁሉ በማፍረስ ላይ እንድናውል ስለሚያሳውረን የገነባነው አንዳች ነገር እንደሌለ የሚገባን፣ በኋላ ስንባንን ነው ፡፡ ቅንአት ያለ የሌለንን ኃይል ለተቃውሞ እንድናውል ስሚያደነዝዘን ደግፈን ወደፊት ያራመድነው አንድም ቁም ነገር እንደሌለን የምንገነዘበው በኋላ ስንነቃ ነው፡፡ ቅንአት ከመንቀል ሌላ ተልእኮ ስለማይሰጠን አንድም ነገር ተክለን እንዳላለመለምን ወደማወቅ የምንመጣው ከድንዛዜው ስንወጣ ነው፡፡

በቅንአት እሳት ስንነድና ስንግለበለብ አይኖቻችን የተከፈቱትና ትኩረታችንን የሳበው ማን ምን ደረጃ እንደደረሰና በእንዴት አይነት ሁኔታ ያንን ሰው መግታት እንደሚቻል እንጂ እኛ ራሳችን በምን አይነት ሁኔታ አሁን ካለንበት ደረጃ ወጥተን ወደ ተሻለው ደረጃ እንደምንደርስ አይደለም፡፡

• ቅንአት የአናሳነት ምልክት ነው፡- የቅንአት መንስኤው አናሳነት ስለሆነ አቅምህንና በራስህ ላይ ያለህን አመለካከት ገንባ፡፡

• ቅንአት አክሳሪ ነው፡- ቅንአት ያለበት ሰው ሌላውን በማጥፋት ሂደት ውስጥ በራሱ ላይ የሚመጣውን ክስረት ስለማያስተውለው ከሳሪው እሱ ነው፡፡

• ቅንአት ጨካኝ ነው፡- ቅንአት ያለበት ሰው የበለጠውን በመሰለው ሰው ላይ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለስም፡፡ የአለማችን የጭካኔ ጥጎች አብዛኛዎቹ መነሻቸው ቅንአት ነው፡፡

• ቅንአት የስራ ፈትነት ምልክት ነው፡- ሰዎች በራሳቸው ስራና እድገት ላይ ሲያተኩሩ የሌላውን ሰው እድገት እንደመነሳሻ እንጂ እንደ መበለጥ አያዩትም፡፡ የራሳቸው አላማና ስራ የሌላቸው ሰዎች የሌላውን እድገት እያዩ ከመቃጠል ውጪ ሌላ ስራ የላቸውም፡፡

ንስር ሆነህ ተወልደህ ዶሮ ሆን እንዳታልፍ ቅንአትን ጣልና አብሮ መስራትን አንሳ!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ለሠራዊታችን ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ሃይል ሆኖ ቀጣይ የሚሠጠውን ተልዕኮ በቁርጠኝነት ሊወጣ ይገባል" - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዘመናዊነትን በተከተለ አግባብ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለአምስት አመታት የሌሎችን አገሮች አደረጃጀት ከሀገራችን አከባቢያዊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም መዋቅራዊ ሥራ ሠርቷል ፡፡

አሁን የተገነባው ባህር ሃይል ጠንካራና ብቃት ያለው በየትኛውም የውሃ አካል ላይ ግዳጅ መወጣት የሚችልና በመከላከያ ሃይላችን ላይ ተጨማሪ የማድረግ አቅም የሚፈጠር እንዲሆን ተደርጎ መገንባቱንም ተናግረዋል።

ባህረኞቹ ከሙያቸው ጋር በቀጥታ ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ የአለም አቀፍ ሳይንሳዊ መርሆዎችን ፣ የደህንነት ጉዳዮችን፣ የአለም አቀፍ የባህር ላይ ህጎችን በመከተል ሀገር ወዳድ አገልጋይ ዜጋ ሆነው እንዲበቁ ማድረግ ከአመራሮች ይጠበቃል ብለዋል።

የባህር ሃይል አመራሮች አለም አቀፋዊና ቀጠናዊ ብሎም ሀገራዊ ሁኔታን ከግምት ያስገባ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ ወትሮ ዝግጁነት አቅም በማረጋገጥ ባህረኞቹ በቀጣይ ለሚሰጣቸው ሀገራዊና ተቋማዊ ግዳጅ በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ እንዲሆኑም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አሳስበዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ ባህር ሃይሉ እስከአሁን የሠራቸውን ሥራዎች በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ባህረኞቹ በናቪጌሽን ፣ በኢንጂነሪግ ፣ በኤሌክትርክሲቲ ፣ በኮሚኑኬሽንና በአርማመንት ሙያ በሀገር ውስጥና በውጭ የሰለጠኑ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አንድ ነገር ላስታውሳችሁ

በማንኛውም ማሕበራዊ ግንኙነት በየእለቱ ለምታገኟቸው ሰዎች ደስተኛነት እናነት ሃላፊነት ሊሰማችሁ አይገባም፡፡

ጠቋሚ ሃሳቦች . . .

• ሁል ጊዜ ደስተኛ የመሆናቸውንና ያለመሆናቸውን ሁኔታ የማየትና የመከታተል ዝንባሌ ካላችሁ …

• የሰዎቹ ፊትና ሁኔታ በተለወጠ ቁጥር የሚጨንቃችሁ ከሆነ …

• ደስ ያላቸው ሲመስላችሁ ደስ የሚላችሁ፣ ደስ ያላላቸው ከመሰላችሁ ደግሞ ውጥረት ውስጥ የምትገቡ ከሆነ ...

እና መሰል ሁኔታዎች የሚንጸባረቅባችሁ ከሆነ ለሌሎች ሰዎች ደስታ እናንተ ሃላፊነትን የመውሰድ ችግር እንዳለባችሁ ጠቋሚ ናቸው፡፡

የመፍትሄ ሃሳቦች . . .

• ከእነሱ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሚዛናዊ እና ጤናማ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

• ያጠፋችሁት ጥፋት ካለ በግለጽ በመንገር ይቅርታን በመጠየቅ እርማት ስጡት፡፡

• ለሚያሳይዋችሁ ደስተኛ የመሆንና ያለመሆን ተለዋዋጭ ስሜት ምላሽ ባለመስጠት ያንን ተቀያያሪ ባህሪያቸውን ባለመመገብ አስርቡት፡፡

• ለእነሱ ደስተኛነት ሃላፊነት ያለመውሰዳችሁን ያህን የእናንተንም ደስተኛነት በእነሱ ሁኔታ ላይ በማስደገፍ እነሱ በተለዋወጡ ቁጥር አትደናበሩ፡፡

ነጻ ሰዎች ናችሁ!

የሰላምና የደስታ ቀን ይሁንላችሁ!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ነው!!

የመደመር ትውልድ ጥላቻን በፍቅር፣ ቂምን በይቅርታ፣ ግጭትን በውይይት የሚተካ ትውልድ ነው።

የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ፤ ጽንፈኝነትን የሚጸየፍ ትውልድ ነው።

የመተማመን ክበቡ በብሄርና በመንደር ሳይታጠር ኢትዮጵያዊነትን በአርበኝነት መንፈስ የሚያፀና ነው።

በመሆኑም ከራስ ወዳድነት የፀዳ፣ ለሌሎች የሚራራ፣ ሀላፊነት የሚሸከም ፣ እውነተኛና የሌላው ህመም የሚያመው ትውልድ መቅረጽ የጋራ ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።

በመደመር ትውልድ ተሠናስለን፣ ተከባብረንና ተባብረን ለጋራ ግብ ቋሚ ተሰላፊ በመሆን ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለበርካታ ዓመታት የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ኘሮግራሞች በማቅረብ የሚታወቀዉ የአስፋዉ መሸሻ ስርዓተ ቀብር ተፈጽሟል።

ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በ ኢ. ቢ. ኤስ ቴሌቪዥን በፕሮግራም አቅራቢነት ያገለገለዉ አስፋው መሸሻ ዛሬ የቀብር ስርአቱ ቤተሰቦቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ እና .አድናቂዎቹ በተገኙበት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

አስፋው 25 ዓመታትን በሚዲያ ዘርፍ ያገለገ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 12 ዓመታትን በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን አገልግሏል።

ኑሮ በአሜሪካ በተሰኘዉ ኘሮግራሙ ተወዳጅነት ያተረፈዉ አስፋዉ ለህክምና በሄደበት አሜሪካ ጥር 4/2016 ዓ.ም ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

አስፋው መሸሻ የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን እና ጋምቢያ ነገ ምሽት 2 ሰዓት የሚያደርጉትን የምድብ 3 የመጨረሻ ተጠባቂ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ ተመድበዋል።

ዳኛ ባምላክ ተሰማ በኮትዲቫር እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከዚህ ቀደም ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ዛምቢያ ያደረጉትን የምድብ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት የመሩ ሲሆን የአሁኑ ሁለተኛ ጨዋታቸው ይሆናል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ እስካሁን ያላትን የሻይ ተክል ልማት ወደ እጥፍ ለማሳደግ ዘንድሮ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ነው ያለው። እስካሁን የተተከለው እንዳለ፣ ምርቱን ለማሳደግ ከፍተኛ የችግኝ ዝግጅትም እየተከናወነ ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ( ዶ/ር )

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel