“ስብራትን መጠገን፤ ለትውልድ መታመን” በሚል ርዕሰ ለብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የቀረበ ገለጻ (ክፍል ሁለት)
https://twitter.com/ProsperityKera
ዛሬ ምሽት ከዜና በኋላ ይጠብቁን!
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ 👇
https://twitter.com/ProsperityKera
መምህር ዘመድኩን በቀለ ከሁሉም ጋር የሚጋጨው ወድጄ አይደለም ፤ እኔ የማላውቀው መንፈስ ነው የሚገፋፋኝ እያለ የአእምሮ እክል እንዳጋጠመው በለቅሶ መልክ እየገለጸ ነው። በአንተ ላይ አድሮ ኢትዮጵያን ሰላም ለመንሳት ተማምሎ የወጣውን መንፈስ እግዚአብሔር ያርቅልህ ከማለት ውጭ ምን እንላለን?
https://twitter.com/ProsperityKera
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የመንግስት የስራ አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል
በዚህ ግምገማ ባለፉት 6 ወራት በመንግሥት ተቋማት የተከናወኑ ስራዎች ተገምግመው ከፍተኛ አፈጻጸም ያሳዩት ተግባራት ተጠናክሮ እንዲቀጥሉና መስተካከል ያለባቸውም እንዲስተካከሉ የቀጣይ ተልዕኮ አቅጣጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል‼️
https://twitter.com/ProsperityKera
"ባለፉት አምስት አመታት ኢትዮጵያ ..."
https://twitter.com/ProsperityKera
ኢትዮጵያን ማበልጸግ የምንችለው የሀሳብ ልዕልና ካለን ብቻ ነው። የኢትዮጵያ የድህነት ታሪክ ሊቀየር የሚችለው ሁሉም ዜጋ ጥሩ ሀገራዊ ምልከታና ስብራትን ሊጠግን የሚያስችል የሀሳብ ልዕልና ሲኖረው ብቻ ነው።
@AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
"ያደገ ሀሳብና ምልከታ ሲኖረን ትናንሹ ጉዳይ ይፈታል" - ጠ/ሚ @AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
"አሻጋሪ ሀሳብን የጠረ ሀሳብን በሚሻገር ምናብ የምንይዝ ከሆነ የኢትዮጵያን ስብራት እንጠግናለን" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
https://twitter.com/ProsperityKera
#ዓድዋ፦ የጥቁር ህዝቦች ድል!
የዓድዋ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ተጋድሎና መስዋትነት ሀገራችንን ያስከበሩበት ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ አንፀባራቂ የሆነ ድል ነው፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን በጋራ መታገል እና በጋራ ድል መቀዳጀት የካበተ ልምድ ያለን ህዝቦች መሆናችን የአድዋ ድል ትልቅ ታሪካዊ ማሳያ ነው። ጀግኖች አባቶች በከፈሉት መሰዋእትነት ድልን አጎናጽፈውናል፤ ለዚህ ክብር ላበቁን አርበኞች ክብር ይገባቸዋል፡፡
ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን የአብሮነት፣ የአሸናፊነትና ፅናት ተምሳሌት ነው። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መግስታችን ደግሞ መስዋትነት ለከፈሉ ጀግኖች አባቶቻችን ክብራቸውን የሚመጥን ትልቅ እና ማስተማሪያ የሆነ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በማቆም ሌላ ደማቅ የታሪክ አሻራ ማኖር ተችሏል።
እኛም የዛሬ ትውልዶች ለአርበኞቻችን ክብር እየሰጠን ዘመኑን በመዋጀት ከአባቶቻችን ልቀን እንጂ አንሰን እንዳንገኝ የዛሬውን የጋራ ጠላት የሆነዉን ድህንትን በማሸነፍ ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ኢትዮጵያን የማስረከብ ሃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል።
https://twitter.com/ProsperityKera
"ማሳካት የምንፈልጋቸውን ነገሮች ሰላማዊ በሆነ መንገድ እናሳካለን" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
https://twitter.com/ProsperityKera
#ለሚ_እንጀራ ማእከል ዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ስራ አመራር መመዘኛ መስፈርቶችን በማሟላት የአይ ኤስ ኦ የምስክር ወረቀት (ISO 22000 - Certificate) ለማግኘት እየሰራ መሆኑን ገልፇል።
ለሚ እንጀራ ማዕከል የእናቶችን ድካም ከማቅለል እና እንጀራን ከፍ ባለ ደረጃ ከማምረት ባሻገር በኢትዮጵያ የጥራት ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የተዘጋጁ የጥራት መለኪያዎችን በማሟላት "ISO 22000" የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ስራ አመራር የምስክር ወረቀት ለማግኘት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ማዕከሉ መመዘኛዎችን ለማሟላት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንሰቲትዩት ጋር የክትትልና ድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል።
የስምምነት ፊርማውን የለሚ እንጀራ ህብረት ስራ ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ ኩሪ አየለ እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ ተፈራርመዋል።
በም/ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበርን ጨምሮ የተለያዩ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ ሲሆን እንጀራ ማዕከሉ የምግብ ደህንነት ስራ አመራር መመዘኛ መስፈርቱን አሟልቶ የምስክር ወረቀቱን ሲያገኘ እንጀራን ወደ ውጭ ለመላክና በዓለም አቀፍ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ በስፋት ለመሳተፍ ያግዘዋል ተብሏል።
እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ዓለም አቀፍ ሆቴሎች ጥራት ያለው እንጀራ ለማግኘት የምስክር ወረቀቱን እንደሚጠይቁ የተገለፀ ሲሆን በሸማቾች ዘንድም አመኔታ እንደሚያስገኝለት ተጠቅሷል።
ለሚ እንጀራ ማእከል 2015 ዓ.ም በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ስራ መጀመሩ ይታወሳል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በመግራት ለአገር ሰላምና ልማት ማዋል እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ማህበራዊ ሚዲያን ለአገር ግንባታ መጠቀም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ለወጣቶች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ወጣት መለሰ አባተ ማህበራዊ ሚዲያን ለአገር ግንባታ የተጠቀሙ አገሮች ለዕድገታቸው አጋዢ እንደሆነላቸው ጠቁመው በተቃራኒው ማህበራዊ ሚዲያውን አለአግባብ የተጠቀሙ ግለሰቦችና ቡድኖች የተበራከቱባቸው አገራት እስከ መፈራረስ ስለደረሱ ትምህርት ወስዶ አጠቃቀምን መግራት እንደሚገባ አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ ሁሴን ዝናቡ እንደተናገሩት ወጣቶች ሰላምን ዘርቶ ሰላምን ለማጨድ እና ሰላምን ለመመገብ በማህበራዊ ሚዲያው ከእኔነት ይልቅ እኛነትን በማጉላት አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።
ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ለከተማችንና ለአገራችን ሰላም እና እድገት እሴት በሚጨምሩ ጉዳዮች ላይ ማዋል እንደሚገባቸው የጠቆሙት አቶ ሁሴን በከተማችን በፍጥነትና በጥራት እየተገነቡ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ተሞክሮ በአገር ደረጃ እንዲስፋፋም ወጣቶች የበኩላቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የሚዲያ አማካሪ አቶ ዓብይ ሰለሞን የዘመኑ ቴክኖሎጂ ሁሉም ሰው በፅሁፍም ሆነ በተንቀሳቃሽ ምስል መረጃዎችን የሚያስተላልፍበትን ዕድል ስለፈጠረ ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እና የተሳሳቱትን ለማረም የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞችን እንደየዝንባሌአቸው በአግባቡ ሊጠቀሙባቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ስልጠናው ማህበራዊ ሚዲያን በተመለከተ ያላቸውን እውቀት እና ክህሎት እንዳጎለበተላቸው የገለፁት የስልጠናው ተሳታፊ ወጣቶች የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የጀማመራቸው ውጥኖች በሁሉም መስክ ፍሬአማ እንዲሆኑ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
‘’ተሻጋሪ ምናብ ያላቸው ሰዎች፤ በውስን ሰፈር አይታጠሩም‘’ - ጠ/ሚ @AbiyAhmedAli
https://twitter.com/ProsperityKera
የብቃቱ ሚስጢር ደይሊ ከመፅሀፍ ጋር ነዉ❤🙏 ዮመች ጀግናዉ ቀብራራዉ @AbiyAhmedAli ❤🙏
https://twitter.com/ProsperityKera
አዲስ ዋልታ (ዋልታ ቲቪ) ከ ፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ሊዋሀድ መሆኑ ተሰማ። በሁለቱ ወር ውስጥ የውህደቱ ስራም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ሰውዬውን ማነው የሚያቆመው!!
ባንዳዎች ከዚህ በፊትም አልቻለውም? የእንጅራ ባለቤታቸው ግብፅና ኤርትራም አልቻሉትም። እንኳን እነሱ ጌቶቻቸው እነ አሜሪካና ምዕራባዊያንም አልቻሉት? ማንም ከፊትለፊቱ ይቁም። እሱ እንደሚያልፍ ጥርጥር የለውም።
https://twitter.com/ProsperityKera
"ያደገ ሀሳብና ምልከታ ሲኖረን ትናንሹ ጉዳይ ይፈታል" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
https://twitter.com/ProsperityKera
#የበለፀገ_ትውልድ_ለበለፀገች_ኢትዮጵያ
https://twitter.com/ProsperityKera