prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አዲሱ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር በመሆን በጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂዮርጂያ ሜሎኒ አስተናጋጅነት በተሰናዳው የጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ ታድመዋል። ጉባኤው "ኤ ብሪጅ ፎር ቀን ግሮውዝ"/የጋራ እድገት ድልድይ/ በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤው 'ማቲዬ ፕላን ፎር አፍሪካ' የተሰፕው የጣልያን ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኢትዮጵያ ወረርሽኝን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ፥ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና የዓለም የጤና ድርጅት የቀጣናው ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በቀጣይ ሶስት ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ የአለም ክፍሎች በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በትላንትናው ዕለት በኦሳካ እና በሲቪያ የተካሄዱትን የሴቶች ማራቶን አትሌት ወርቅነሽ እዴሳ እና አለምፀሀይ ዘርይሁን አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል።

በስፔን ሲቪያ ከተማ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን አትሌት አለምፀሀይ ዘርይሁን እና አበራሽ ሸለማ አንደኛና ሁለተኛ ወጥተዋል።

በጃፓን ኦሳካ በተካሄደው የማራቶን ውድድርም እንዲሁ አትሌት ወርቅነሽ እዴሳ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሆናለች።

በሌላኛው የኦሳካ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር ደስታ ቡርቃ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር የሴቶች ውድድር ላይ የተሳተፈችው ሊኪና አምባው ሁለተኛ ወጥታለች።

በታይላንድ ቡሪራም በተካሄደ የወንዶች እና የሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድርም አትሌት ደሬሳ ፍቃዱና አለምፀሀይ አድባሩ አንደኛ በመውጣት ማሸነፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚሁ በቡሪራም የሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ጸጋ ደስታ እና ጸጋነሽ የዳው አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት ሲያሸንፉ በወንዶች ደግሞ ቢልልኝ ይመር ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያ የፓተንት ሕግን ለማሻሻል የሚያስችል ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በላይ በፓተንት ሕጓ ላይ ማሻሻያ ሳታደርግ መቆየቷን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል በውይይቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

የፓተንት ሕጉ አሁን ካለው ዓለም አቀፍ የፓተንት ሕግ ጋር ሲወዳደር ብዙ ክፍተት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

ይህን ለማሻሻል ባለስልጣኑ ለሁለት ዓመታት የተለያዩ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰው÷ የውይይት መድረኩም ሕጉን ለማሻሻል የሚያግዙ ግብዓቶችን ለመሰብሰብ እንደሚያስችል ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

እያደገ ያለው የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ዘርፍ በፈጠራ ሥራዎች እንዲታገዝ÷ የፈጠራ ሥራዎችን መጠበቅ የሚያስችልና ከዓለም አቀፉ ሕግ ጋር የተዛመደ ሕግ እንደሚያስፈልገውም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

መድረኩን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና የአውሮፓ የፓተንት ቢሮ በትብብር እንዳዘጋጁትም ተመላክቷል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የሃገር ባለቤት መሆናችሁን ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ በእየተሠማራችሁበት መስክ የመጨረሻ አቅማችሁን ተጠቅማችሁ ለሃገራችሁ #ብልፅግና የሚጠቅመውን ነገር ማበርከታችሁን፣ መስራታችሁን እርግጠኛ መሆን ይጠበቅባችኋል" - ዶ/ር ሚኤሳ ኤሌማ - ለወረዳ እና ለክፍለ ከተማ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ለመልካም ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ስልጠና በሰጡበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ማስነጠስ ደከመኝ

እንግሊዝ ውስጥ ባለች ሃምፕሻየር (Hampshire, England) የምትባል ከተማ ነዋሪ ፓትሪክ ዌብስተር (Patrick Webster) የተሰኘ ሰው በሕይወት ዘመኑ ለረጅም ጊዜ ካለማቋረጥ የማስነጠስን “ክብረ-ወሰን” በመያዝ በዝነኛው “ጊነስ” በተሰኘው የክብረ-ወሰን መጽሐፍ (The Guinness Book of World Records) ላይ የተመዘገበ ሰው ነው፡፡ ፓትሪክ ዌብስተር ለ35 ዓመታት ሙሉ ካለማቋረጥ በየሁለት ደቂቃው አስነጥሶታል፡፡ በቀን ውስጥ ቢያንስ 700 ጊዜ እንደ ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ በ35 ዓመታት ውስጥ ከ7 ሚልየን ጊዜ በላይ አስነጥሶታል፡፡

ፓትሪክ ዌብስተር በእነዚህ በማስነጠስ ችግር ውስጥ በነበረባቸው አመታት ውስጥ ከ60 በላይ ዶክተሮች ጋር በመሄድ፣ “ማስነጠስ ደከመኝ” በማለት ችግሩን ገልጦላቸው ምንም መፍትሄ አላገኘም፡፡ ከተለያዩ ሃኪሞች ምክርን በማግኘት በሃገር ውስጥ አለ የተባለ የአለርጂ ምርመራና ህክምና ወስዷል፡፡ ፓትሪክ ዌብስተር ሲናገር እንዲህ ይላል፣ “በቀን በመቶ የሚቆጠር ጊዜ ስለሚያስነጥሰኝ ደክሞኝ ነበር፡፡ ስድስት ወር ከስራ እረፍት ወስጄ ሶስት የተለያዩ ሆስፒታሎች ተኝቻለሁ፡፡ አንዱ ዶክተር ቢቸግረው “የአንተ አለርጂ ራስህ ነህ” ብሎኛል፡፡”

ፓትሪክ ዌብስተር ከእለታት አንድ ቀን ወደ አንድ የምግብ አጠቃቀም አዋቂ ሃኪም (Nutritionist) ጋር ሄደ፡፡ ስፍራው ትልቅ ሆስፒታል አይደለም፣ በአካባቢ የሚገኝ የግል ክሊኒክ ነው፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ይህኛው የህክምና ሙከራ ተቃናለት፡፡ በዚህች አነስተኛ ክሊኒክ የሚገኝ ሃኪም በአንድ ጊዜ ችግሩን አገኘለት፡፡ የፓትሪክ ዌብስተር አለርጂ የእንቁላል አስኳልና አጃ ነበር፡፡ ፓትሪክ ዌብስተር ከ17 አመቱ ጀምሮ በየቀኑ የእንቁላል አስኳልና አጃ ሳይበላ አይውልም ነበር፡፡ መፍትሄው ከተገኘለት በኋላ፣ ፓትሪክ ዌብስተር ሲናገር እንዲህ አለ፣ “ሃኪሞች ይህንን ችግር ነግረውኝ የእንቁላል አስኳልና አጃ መጠቀም እንዳቆምኩኝ ማስነጠሱ ተወኝ፡፡”

ፓትሪክ ለአለርጂ ችግሩ መንስኤ ይሆናሉ ብሎ ያሰባቸው የተለያዩ ነገሮችን ከችግሩ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ገባው፡፡ ችግሩ ያለው ሩቅ አልነበረም፣ ራሱው ጋር ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ግር ያለንን የሕይወታችን ሁኔታ ምንጭ ለማግኘት የማንሮጥበት ቦታ የለንም፡፡ ሩቅ ስናይ አጠገባችን ያለውን እናጣዋለን፡፡ ከሁሉ በፊት ግን የችግሩ ምንጭ ምናልባት አጠገባችንና ከእኛ ጋር የተያያዘ ሆኖ እንደሆነ ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ምናልባት ከእኛው ከራሳችን አካባቢ ብዙም ሳንርቅ አንዳንድ አጉል የሆኑ አመለካከቶቻችንን የቀረጹትን ሁኔታዎች እናገኛቸው ይሆናል፡፡ ስለዚህም፣ “አሁን ያለኝን አመለካከት የቀረጸው ነገር ምንድን ነው?” ብለን ራሳችንን ስንጠይቅ ችግሩ አጠገባችን ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

በሕይወትህ አልሄድ ያለ ችግር ካለብህ፣ አልለወጥ ያለ በህሪይ ካጠቃህና ምክንያቱን የማታውቀው አለመሳካት ከተደጋገመብህ፣ መፍትሄ ፍለጋ ብዙ ከመሮጥህና ሌሎች ነገሮችን ከመሞከርህ በፊት በቅድሚያ የሚከተሉትን ነገሮች ተመልከታቸው፡፡ ምናልባት የችግርህ ምንጭ አጠገብህ ሆኖ ታገኘው ይሆናል፡፡

• የየቀን ልማዶችህንና ልምምዶችህን በሚገባ አጢናቸው፣

• በየእለቱ የምታገኛቸውን የቅርብ ወዳጆችህን ተጽእኖ በሚገባ አጥናው፣

• በየጊዜው የምትውልባቸውን ስፍራዎች በሚገባ ተመልከታቸው፣

• በተደጋጋሚ ሁኔታ የምታየውን፣ የምትሰማውን፣ የምታነበውንና የምታሰላስለውን ነገር ምን እንደሆነ በሚገባ መርምረው፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#የዐብቹ_ጉዳይ_ሁሌም_ለሚያዞራችሁ እኔን 💪

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት፣ በሮም ጣልያን በተሰናዳ ክብረ በዓል የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸልመዋል።

ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ርዕይ፣ አመራር እና ቁርጠኝነት፣ ብሎም ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ዕውቅና ለመስጠት የተበረከተ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤  የተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ ልዑካን ቡድኖች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች፣ በጣልያን የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ተልዕኮዎች አባላት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በተገኙበት ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት ዓመታት በግብርናው መስክ ቁልፍ ኢንቨስትመንቶችን ያደረገች ሲሆን በስንዴ ምርት ራስን የመቻል ሥራዎችን በማከናወን በዐበይት ምርቶችም ላይ ከፍተኛ ዕድገት አስመዝግባለች።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

️⚠️ ራስ ወዳደ እና ምኞት ወለድ ፖለቲካ️ ⚠️

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

2024 Corporate Sustainability Achievement Award owner!!
#Fast_Growing_Ethiopia
#NoMore_Landlocked
#Abiy_Ahmed

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

The current situation of #Egypt and #Somalia.

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ተደምረን የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እናሳካለን‼

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኢትዮጵያ የሚዲያ ኢንዱስትሪ በሁሉም ዘርፍ ቀዳሚ እና ተመራጭ ለመሆን እየሰራ ያለውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ) ከሰሞኑ በድንገት ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡

ወደ ኃላፊነት ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በየተቋማቱ ባልተጠበቀ ሰዓት እየተገኙ ሥራዎችን የሚገመግሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና መሥሪያ ቤት የተቋሙን አዳዲስ የማስፋፊያ ሥራዎች በመመልከት ነው ጉብኝታቸውን የጀመሩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቀድመው የተመለከቱት ሕንፃ ፋና ቴሌቪዥን በቅርቡ ወደ ሥራ የሚያስገባውን አዲስ ስቱዲዮ ነው፡፡

በዋናነት የመዝናኛ ፕሮግራሞችን እና አሳታፊ መድረኮችን እንዲያስተናግድ ታስቦ የተገነባው ይኸው ስቱዲዮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተጨማሪ ጥንካሬን የሚያላብስ ነው፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሁሌም በእድገት ውስጥ እንዳለ የሚያመላክትም ነው፡፡

ፋና እስካሁን ድረስ ተወዳጁን ፕሮግራም ፋና ላምሮት ጨምሮ በርካታ ሰዎች የሚገኙበት የውይይት መድረኮችን ከዋናው መሥሪያ ቤት ውጭ በተከራየው ሕንፃ ነው ወደ ተመልካቾች እያደረሰ የቆየው፡፡

ሕንፃው ለሚዲያ ታስቦ የተሰራ ባለመሆኑ ግን ለሥራው በሚፈለገው ልክ ምቹ አልነበረም፡፡

ተቋሙ ለሕንፃ ኪራይ በየወሩ ከፍተኛ ገንዘብ ለማውጣትም ይገደድ ነበር፡፡

አዲሱ ስቱዲዮ ታዲያ ይህን ወጪ የሚያስቀርና ፋና በተሻለ አቀራረብ ወደ ተመልካቾቹ እንዲደርስ የሚያስችለው ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ነባሩን የፋና ስቱዲዮ እና የሥራ ቦታም ተመልክተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሐሰተኛ መረጃዎች ሥርጭት የሚዲያው ዘርፍ አልፎም የሀገራት ዋነኛ ፈተና ነው፡፡

የሐሰተኛ መረጃው ፍጥነት እና አድማጭ ተመልካቹ ጋር የሚደርስበት መንገድ መብዛት ደግሞ ወቅቱን ይበልጥ ፈታኝ አድርጎታል፡፡

በተለይ እንደ ኢትዮጵያ የትርክት ችግር ባለበት ሀገር ጉዳቱ ከፍ ያለ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ ችግሩ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማስቀረት መንግሥታቸው ቅድሚያ ሰጥቶ ሪፎርም ካደረገባቸው ዘርፎች መካከል ሚዲያ አንዱ ነው።

በመገናኛ ብዙኃን ላይ በተሰራው የሪፎርም ሥራ የወል ትርክቶችን ማጽናት የሚያስችል ተግባር መጀመሩን አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ እየታየ እንዳለው ተቋማት እየተጠናከሩ ሲሄዱ አፍራሽ ሃሳቦች ቦታ እያጡ ይሄዳሉም ብለዋል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ከአዲሱ ስቱዲዮ እስከ ነባር የሥራ ክፍሎቹ ተዘዋውረው የተመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ባዩት ነገር እጅግ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

በቀጣይነትም ተቋሙ በፈጠራዎች ውስጥ ሆኖ እድገቱን በማፋጠን ሀገራዊ ተልዕኮውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሁላችን እናቶች እና አባቶች ድል የሆነውን የአድዋ ድል የመሩትን አፄ ምኒሊክ በድጋሚ ያከበረ አስተዳደር 👏 🇪🇹 የ #አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ትልቅ ምስጋና ይገባዋል። 👏 🇪🇹

ከተማ አስተዳደራችን ለአፄ ሚኒሊክ ተጨማሪ ሐውልት አቁሟል። #Fact መጥታችሁ አድዋ 00 ኪ.ሜ ፕሮጀክት ላይ ተመልከቱ።

ይኼ አጭር፣ ግልፅ በተግባር የተገለጠ ጉዳይ ያልገባው አካል ካለ #በቁሙ_የተኛ ነውና ምንም ተጨማሪ ማብራሪያ ልሰጠው፣ ልፅፍለት አልችልም። ይኼው ነው #KANUMA

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ቂርቆስን_የአዲስአበባ_የብልፅግና_ተምሳሌት የሚያደርጉ የንቅናቄ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ቂርቆስ ክፍለ ከተማን ስማርት ክፍለ ከተማ የማድረግ፣ የስራ ዕድል የማስፋት፣ ምርታማነትን የማሳደግ፣ ልማት ትሩፋትን አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት፣ ቂርቆስን  ፅዱ፣ ውብ እና ለመዝናኛ እና ለኑሮ ምቹ ማድረግ የሚያስችሉ የቀጣይ ንቅናቄ እቅድ ለአመራሩ ይፋ ተደርጓል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በተለምዶ"ሿሿ" የተባለውን ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩ ሦስት ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ ሲያዙ አንደኛዋ ወንጀል ፈፃሚ በክትትል መያዟን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን የፈጸሙት ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ ወሎ ሰፈር ሸዋ ሱፐር ማርኬት አካባቢ ከቀኑ 5 ሰዓት ላይነው።

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ኮድ 1- 09609 ትግ በሆነ ሚኒባስ ሁለቱ ሴቶች ተሳፋሪ አንደኛው ረዳት በመምሰል የግል ተበዳይ የሆነቸውን ወ/ት ሌሊሴ ያደታን ካሳፈሩ በኋላ አንደኛዋ ወንጀል ፈፃሚ ያመማት በመስመሰል የግል ተበዳይ ላይ ምራቅ በመትፋት ሌሎቹ ደግሞ የሚጠርጉ መስለው ግምቱ 40ሺ ብር የመያወጣ የእጅ ስልኳን ከሰረቁ በኋላ ከመኪናው ላይ ገፍትረው በማስወረድ ያመልጣሉ፡፡

የግል ተበዳይ ያሰማችውን የድረሱልኝ ጥሪ የሰሙ በወንጀል መከላካል ስራ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና በአካባቢው በነበሩ ግለሰቦች ትብብር ሦስቱ ወንጀል ፈፃሚዎች ከግል ተበዳይ ከሰረቁት ሞባይል ስልክ እንዲሁም አንድ ሌላ ተጨማሪ ስልክ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ፓሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ክትትል እንደኛዋን ወንጀል ፈፃሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ደጋጋሚ መሆናቸውን መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ፖሊስ አስታውቆ መሰል የወንጀል ድርጊት የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ላንቻ ፖሊስ ጣቢያ በመቅረብ ወንጀል ፈፃሚዎቹን መለየት እንደሚችሉ ፖሊስ ጣቢያው አስታውቋል።

የህብረተሰቡ ድጋፍ ከታከለበት ወንጀለኞችን በቀላሉ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቆ የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርበዋል።

ተመሳሳይ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሠቡ ትራንስፖርት ሲጠቀም አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለፀጥታ አካላት ማሳወቅ እንዳለበት ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እኛ የምናልም ያልምነውን የምንናገር የተናገርነውን ተግተን የምንተገብርና ዓለም እንዲያይ የምናደርግ ነን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ በመሸለማቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሽልማቱ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ከፍ የሚያደርግ እና የላቀ ገፅታዋን የሚያሳድግ በመሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽዖም እናመሠግናለን ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሠሯቸው መልካም ሥራዎች ጎልተው የሚታዩ መሆናቸን ያመላከተ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

ይህ ሁኔታ ዓለም ላይ የምንታወቅበትን የድህነት ታሪክ እየቀየረ ያለ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ማሳያ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት÷ እረፍት የለሹ፣ ለኢትዮጵያ ጊዜያዊ ችግር ፍቱን መፍትሄ ሃሳብ አፍላቅ መሪያችን ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሳል አመራር ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም የጋምቤላ ክልል÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ባደረጉት ዘርፈ ብዙ ስራ ውጤት በመመዝገቡና ተሸላሚ በመሆናቸው የክልሉ መንግስትና ሕዝብ ኩራት ይሰማዋል ብሏል።

በቀጣይም ዘርፉን ለማሳደግና የሕዝቦችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የክልሉ መንግስትና ሕዝብ ከጠቅላይ ሚኒስትር አሕመድ (ዶ/ር) በሳል አመራር ጋር በጋራ እንደሚሰራ ገልጿል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ፓርቲው በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መስክ ተገቢውን ስራ እየሰራ ነው - ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)

የብልፅግና ፓርቲ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መስክ ተገቢውን ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ፓርቲው ለቀናት ባደረገው የማዕከላዊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የዘመነ መረብ ምንነት፣ መልካም እድል እና ፈተናዎቹን በተመለከተ ሰፊ ግምገማ ማደረጉን የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ወቅቱ ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀምና ባለመጠቀም መካከል በሚደረግ ውድድር ላይ የሚመሰረት እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ይህንን በመገንዘብ ፓርቲው በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መስክ ተገቢውን ስራ እየሰራ ነው ብለዋል።

መረጃ በፍጥነት በሚዘዋወርበት ወቅት መረጃን የማዛባት እድል እየሰፋ የመጣበት ወቅት በመሆኑ ይህንን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በእውነት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን በፍጥነት በመስጠት ረገድ ተጨማሪ ስራዎች ይሰራሉ ነው ያሉት።

ፓርቲው ጊዜውን ባማከለ መልኩ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ተቋማት በማደራጀት እና በዘርፉ ብዙ የሰው ሃይል በማፍራት እየሰራ ባለው ስራ ከወዲሁ ውጤት መታየት መጀመሩንም ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የተደራረቡ እና የቆዩ ችግሮች ያሉ በመሆናቸው መግባባት ባልተፈጠረባቸው ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ላይ እንዲደረስ ፓርቲው በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"Hundi keenya biyya teenya kan jaallannu yoo ta'e, dirree itti bobbaanerratti hamma dandeettii qabnutti fayyadamnee ga'ee akka lammiitti qabnu ba'annee, badhaadhina Itoopphiyaa dhugoomsuu danda'uu qabna!" - Dr. Mieessa Elemaa - waan dubbate irraa fudhatame

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"እኛ ስንተጋ ተከታዮቻችን ሲተጉ ፣ ህዝባችን ሲተጋ በዛ ድምር ውጤት ነው፤ ኢትዮጵያ ከረሀብ ወጥታ ወደ ብልፅግና የምትሄደው" - ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ( ዶ/ር )
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ከቃላቶቻችን_ከፍ_ያለብን #ዐብቹ 💪💪💪

ለተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምናደርገው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ ስላጎናፀፈን ምስጋናዬን ለመግለፅ እወዳለሁ። ከፍ ያለ ጠቀሜታ ባላቸው እና የኢንደስትሪ ግብዓት  በሆኑ የግብርና ምርቶች ላይ ማተኮራችን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያስገኘልን ይገኛል። የምግብ ሉዓላዊነት ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን።

I express my gratitude to the United Nations Food and Agriculture Organization (FAO) for bestowing the prestigious Agricola Medal for our efforts towards the attainment of food security. Our focus on high value and industrial crops is yielding promising results and we are committed to our food sovereignty path.

© ዐብይ አህመድ አሊ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በገዘፈ ሀሳብ የምትመራ ሀገር!!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#አድዋ ከንግግርም፣ ከፅሁፍም ከፍ ያለ የእኔም፣ የአንቺም፣ የአንተም ... የሁላችንም የጋራ ማንነታችን አኩሪ አሻራ ነው።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዐብቹይ በጣሊያን ሮም 👌👌👌
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ 23 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በሚሳተፉበት የጣሊያን - አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ቅዳሜ ሮም ገብተዋል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የተጀመረውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባራዊ ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል" - ብልፅግና ፓርቲ

#ከእዳ_ወደ_ምንዳ  
#ቀይባህር_ህልውናችን

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በመንግሥትና በሸኔ መካከል ተጀምሮ ያለ ስምምነት የተቋጨውን የሰላም ንግግር ለመቀጠል መንግሥት ዝግጁ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣በታንዛኒያ በመንግሥት እና በሸኔ ቡድን መካከል ተጀምሮ ያለ ስምምነት የተጠናቀቀውን የሰላም ንግግር ለመቀጠል እና ከመግባባት ለመድረስ መንግሥት አሁንም ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያን ሰላም ለማጽናት ባለፉት ዓመታት በልዩ ሁኔታ እና በብዙ መልኩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ ችግሮች ሲፈጠሩ መቆየታቸውን ያነሱት አቶ ሽመልስ፤ የክልል የጸጥታ ኃይል በሕግ ከተፈቀደለት ውጭ አደረጃጀት ፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።

በኋላም ችግሩን የማስተካከል እና የማረም ስራ መሰራቱን ጠቅሰው፤ ከዚህ ባለፈ በክልል ደረጃ ፖሊስ በብቁ ሁኔታ እንዲደራጅ የማድረግ እና የማጠናከር ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የጸጥታ አካላት አስደናቂ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ያወሱት አቶ ሽመልስ፤ በጸጥታ ዘርፉ እየተከናወነ ያለውን ይህን ተግባር በፖለቲካ የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ መተላለፉን ገልጸዋል።

በየደረጃው ህዝባዊ የሰላም ኮንፈረንሶችን በማካሄድ፣ የሰላም ግንባታ ስራዎችን በአግባቡ በማከናወን እና የሰላም በሮችን ለእርቅ ክፍት በማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች አሁንም ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አቅጣጫ መቀመጡን ተናግረዋል።

ለመንግሥት ሰላም የማስፈን ስራ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፤ የሰላም እጦት መንግሥት ለመልካም አስተዳደር እና ለልማት መረጋገጥ ሊያውለው የሚገባውን ጊዜ፣ ሀብት እና የሰው ኃይል የሚሻማ ክስተት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ባለፉት ጊዜያት የተደረጉ የሰላም ጥሪዎች የማይናቅ ውጤት አስገኝተዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ለአብነትም ከሸኔ ጋር የተደረገውን የሰላም ንግግር ጠቅሰዋል።

በንግግሩ ወቅት ምንም እንኳ መንግሥት ከፍተኛ የሆነ የሰላም ፍላጎት የነበረው ቢሆንም፤ በሸኔ በኩል በነበሩ ኢ-ሕገመንግስታዊ ፍላጎቶች ምክንያት የሰላም ሂደቱ ተደናቅፎ ቆሟል ብለዋል።

ነገር ግን መንግሥት ለሰላም የዘረጋው እጅ አሁንም እንዳልታጠፈና የሰላም ንግግሩን ለመቀጠልም ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አክለውም ታጣቂ ቡድኑ ኢ-ሕገመንግስታዊ ፍላጎቶቹን ገትቶ እና ሕገመንግሥቱን ተቀብሎ ወደ ሰላማዊው መንገድ እንዲመጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችም በተመሳሳይ መልኩ በሰላማዊ መንገድ እየተፈቱ መሆናቸውን አንስተዋል።

በሌላ በኩል፥ በአንዳንድ ቦታዎች ሰዎችን የማገት ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ያነሱት አቶ ሽመልስ፤ እነዚህን ተግባራት በሚፈጽሙ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሌላ ሀገር ሲሆን ዝም ተብሎ አትዮጵያ ስትጠይቅ ግን ለምን ጫጫታ ይበዛል??? #ለምን ???
/channel/ProsperityFirst
#ቀይባህር_ህልውናችን
#No_More_Landlocked
#Fast_Growing_Ethiopia

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የጋምቤላ እና የሲዳማ ክልል መንግሥታት ተወካዮች በእጃቸው የሚገኙ ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከቡ።

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንዲቀመጡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበል የጋምቤላ እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ተወካዮች ዛሬ በእጃቸው የሚገኙ ቅርሶችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል።

ቅርሶቹን የተረከቡት የከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ፣ ቅርሶቹ ትውልድ የሚማርባቸው ጎብኚዎች እና ተመርማሪዎች የሚመራመሩባቸው በመሆናቸው በመታሰቢያ ሙዝየሙ እንዲቀመጡ ሁለቱ ክልሎች ስላበረከቱ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ቂርቆስን_የአዲስአበባ_የብልፅግና_ተምሳሌት የሚያደርጉ የንቅናቄ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ቂርቆስ ክፍለ ከተማን ስማርት ክፍለ ከተማ የማድረግ፣ የስራ ዕድል የማስፋት፣ ምርታማነትን የማሳደግ፣ ልማት ትሩፋትን አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት፣ ቂርቆስን  ፅዱ፣ ውብ እና ለመዝናኛ እና ለኑሮ ምቹ ማድረግ የሚያስችሉ የቀጣይ ንቅናቄ እቅድ ለአመራሩ ይፋ ተደርጓል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel