ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለች። የኢትዮጵያ ብልፅግና ቅርብ ነዉ
#ፅንፈኝነት_ይውደም
#እንድነትUnity
https://twitter.com/ProsperityKera
ተረት ተራኪ ሳይሆን ታሪክ ሰሪ መሪ ያለን ህዝቦች ነን
መሪያችን፣ አብቹ @AbiyAhmedAli 🙏🙏🙏
https://twitter.com/ProsperityKera
የመንግስት አገልግሎትና የአስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም በተመረጡ ሰባት የፌዴራል ተቋማት ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለጸ።
ይህ የተገለጸው የየገንዘብ ሚኒስቴርና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም ዙሪያ ባደረጉት የምክክር መድረክ ላይ ነው።
በምክክር መድረኩ ላይ በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም ይዘት፣ በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ፣ በመንግስት ሰራተኞች ብቃት ምዘና ማዕቀፍ እና በፖሊሲው ማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ ለገንዘብ ሚኒስቴርና እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የሪፎርሙ ዓላማ የመንግስት ተቋማትን አደረጃጀትና አሰራር በማዘመን በክህሎትና በባህሪ የበቃ የሰው ኃይል አስተዳደርና ልማትን በመዘርጋት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የሀገርን የዕድገትና የልማት ግቦች አውን ለማድረግ እንደሆነ ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር ዶክተር መኩሪያ ኃይሌ ማሻሻያ ሪፎርሙ የገንዘብ ሚኒስቴርን ጨምሮ ለሙከራ በተመረጡ ሰባት የፌዴራል ተቋማት ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ ሪፎርሙ የመንግስት ተቋማት አሰራራቸውን በማዘመን ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ያስችላል ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በበኩላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርሙ ለሙከራ ትግበራ አንዱ ሆኖ በመመረጡ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርሙን ማስፈጸም የሚችል የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በማደራጀት፣ በቂ ሃብት በመመደብ እና እቅድ በማውጣት በቶሎ ወደ ትግበራ እንደሚገባ አክለዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ድኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ትልልቅ ሀገራዊ ሪፎርሞችን መሸከም የሚችል ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የፀሐይ አውሮፕላን ወደ እናት ሃገሯ #ኢትዮጵያ ልትመለስ ከስምምነት መደረሱ፤ የአዲሱ የውጭ ዲፕሎማሲያችን ታላቅ ድልና ስኬት አንድ ማሳያ ነው።
https://twitter.com/ProsperityKera
ለ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል በቂ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ገለጹ።
37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የፊታችን የካቲት ወር መጀመሪያ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ በርካታ የዝግጅት ምዕራፎች ሲካሄዱ መቆየቱን ጠቁመዋል።
በዚህም ከተማዋን የማስዋብና የማፅዳት፣ እንግዶችን የሚቀበሉ ሆቴሎች የመለየትና የማዘጋጀት፣ የትራንስፖርት አገልግሎትና የፀጥታ አካላት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።
ሕብረተሰቡ በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ለእንግዶች አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።
''የአዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት በነፃ የተገኘ አይደለም ''ያሉት አምባሳደር መለስ፤ በትውልድ ቅብብሎሽ የተሰሩ ሥራዎች ውጤት መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ ፀንቶ እንዲኖር የአሁኑ ትውልድ የቤት ሥራ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ይህ አህጉር አቀፍ ጉባዔ የኢትዮጵያን በጎ ገፅታን ለመገንባት ጭምር ሰፊ ሚና የሚጫወት ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።
የዘንድሮው 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የፊታችን የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ 44ኛው የአባል ሀገራቱ የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከመሪዎች ጉባዔ ቀደም ብሎ የካቲት 6 እና 7 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ሕብረት የ2024 መሪ ቃል "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል ይካሄዳል።
https://twitter.com/ProsperityKera
#ፀሐይ አውሮፕላንን በማስመልከት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ጋር የተደረገ ቆይታ
https://twitter.com/ProsperityKera
ከተማ አስተዳደራችን ለጋራ ድላችን #አድዋ የሰጠው ትኩረትና ያንን የጋራ ድል ፍንትው አድርጎ የሰደረውን #ህያው_ፕሮጀክት #የአድዋ_ድል_መታሰቢያ ን በመሃል ከተማችን #አዲስአበባ፣ ለዛውም ጀግኖቹ ከመሃል ሃገር ወደ አድዋ ከተመሙበት ታሪካዊ ስፍራ ላይ መገንባቱ ከትውልድ ትውልድ የሚያስመሠግነው እጅግ የሚናኮራ ስራ ነውና #አዲስአበባ ከተማ አስተዳደራችን እናመሠግናለን 🙏
https://twitter.com/ProsperityKera
"ስፖርት ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልፅግና "
በክፍለ ከተማው በተገነባው የመደመር ትውልድ የህፃናት የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያና የመጫወቻ ማዕከል ጉብኝት ተካሄደ ።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተፃፈው 'የመደመር ትውልድ' መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ በክፍለ ከተማው ወረዳ 05 አስተዳደር የተገነባው የታዳጊ ህጻናትና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ጉብኝት ተካሄደ።
በጉብኝቱም የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ሀላፊ ዶ/ር ሚኤሶ ኤለማ ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣ የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙልጌታ ጉልማና ሌሎች የክፍለ ከተማ አመራሮች እና የሁሉም ክፍለ ከተማዎች የብልፅግና ፓርቲ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በክፍለ ከተማው የመደመር ትውልድ የወጣቶች እና ህጻናት የስፖርት ማዘውተሪያው ማዕከል መገንባቱ በጤናና በአይምሮ እንዲሁም በአስተሳሰብ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ስፖርት ህዝባዊ መሰረት እንዲይዝ የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰራም አስታውቋል።
በተጨማሪም በጉብኝቱ ተሳታፊ አካላት በማዕከሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶችና ህፃናትን አበረታተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የከተማችንን ፀጋዎች በመለየት እና ሁሉንም አቅሞች በማስተባበር የህዝባችንን ህይወት ለማሻሻል መረባረብ እንደሚገባ ተገለፀ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ ሶስት ወራት በስራ ዕድል ፈጠራ እና የኑሮውድነትን በማቃላል በሚከናውኑ ስራዎች ላይ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር መክረዋል ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት አንዱ ለአንዱ ግብአት በሚሆን መልኩ የተሳሰረው የከተማችን የልማት እንቅስቃሴ በርካቶች ተሞክሮ የቀሰሙበት ውጤት መመዝገቡን አስታውሰው ግለቱን ጠብቆ መጓዝ እንደሚገባው አስገንዝበዋል ።
አቅርቦትን በማሳደግ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ዋነኛው መፍትሄ ምርትና ምርታማነትን መጨመር መሆኑን ያስረዱት ከንቲባ አዳነች ተቋማዊ አሰራርን በማዳበረ ጉራማይሌ አፈፃፀሞችን ማረም እንደሚገባ ገልፀዋል፡።
የሚፈጠሩ የስራ ዕድሎችም የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት የሚያሻሽሉ ሊሆኑ እንደሚገባ ያመላከቱት ከንቲባዋ ወደ ላይ እና ወደታች እንዲሁም ወደ ጎን ተቋማዊ ቅንጅትን በማጠናከር ለላቀ አፈፃፀም መረባረብ እንደሚገባ አስረድተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት የሚደረገው ንቅናቄ የአመለካከትና የሀሳብ አንድነት በመያዝ ተግዳሮቶችን በጋራ በመቅረፍ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ለስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል እንዲሁም የሌማት ቱሩፋት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው የጠቆሙት አቶ ሞገስ ለዚህም አሰራርን መፈተሽ ፣ ክህሎትን መሙላት ፣ ያልተሟሉ ግብአቶችን ማሟላት እንዲሁም ክትትልና ድጋፍን ማጠናከር እንደሚገባ አብራርተዋል ።
ለወጣቶች እና ለሴቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ቤተሰብ ለልጆቹ ውጤትና ስኬት የሚገኘው ላብን ጠብ አድርጐ በመስራት መሆኑን በማስገንዘብ አመለካከትን በመቅረፅ የድርሻቸውን እንዲወጡም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ክህሎት መር የስራ ዕድል ለመፍጠር በከተማችን የሚገኙ ኮሌጆች ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው የስራ እና ክህሎት ቢሮ በሰለጠነ የሰው ሀይል አቅርቦት ዙሪያ ከግሉ ኢንዱስትሪ ጋርም ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባው አስረድተዋል።
የንቅናቄው ዓላማ የሌማት ቱሩፋቱን ለማጠናከር ፣ የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል ፣ የወጣቶችንና የሴቶችን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ለመጨመር እና የህዝባችንን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሆኑን በብልፅና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ባቀረቡት ሪፖርት ተመላክቷል።
በቀጣይ ሶስት ወራት ከመደበኛ ስራዎች በተጨማሪ ለንቅናቄ ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት በስራ ዕድል ፈጠራ እና የኑሮ ውድነትን በማቃለል የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጃቻቸውን በውይይቱ የተሳተፉ አመራሮች አረጋግጠዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ዛሬ "ፀሐይ" አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባችንን የምናከብርበት ቀን በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ታላቅ የኩራት ቀን ነው። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ላለፈው አንድ አመት የአውሮፕላኑን መመለስ ስራ በማገዛቸው ለማመስገን እፈልጋለሁ።
"ፀሐይ" እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1935 ዓ.ም በጀርመናዊው ኢንጂነር እና የንጉሱ ፓይለት ሄር ሉድዊግ ዌበር ብሎም በወቅቱ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሞያዎች ትብብር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራ አውሮፕላን ነው።
Har'a guyyaa itti xiyyaara "Tsahaay" Mootummaa Xaaliyaaniirraa ifatti deebifachuu keenya kabajnu waan ta'eef, Itoophiyaanota hundaaf guyyaa guddaa itti boonanidha. Ministira Muummee Xaaliyaanii, Joorjiyaa Meeloonii waggaa guutuudhaaf haala itti xiyyarichi deebi’u mijeessuun waan deeggeraniif guddaan galateeffadha.
"Tsahaay" A.L.A. bara 1935 walta'insa injiinara lammii Jarman kan paayileetii Mootichaa ture, Herr Ludwig Weber jedhamuufi ogeessota Itoophiyaa bara sana turaniin xiyyaara yeroo jalqabaaf Itoophiyaatti hojjetamedha.
Today is a day of great pride for Ethiopians as we celebrate the official handover of “Tsehay” by the Italian Government. I extend my immense gratitude to Prime Minister Giorgia Meloni for her support over the past year in facilitating its return.
"Tsehay" is the first aircraft built in Ethiopia in 1935, under the collaborative efforts of the German engineer and pilot of the emperor, Herr Ludwig Weber, and Ethiopian individuals of that era.
https://twitter.com/ProsperityKera
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 በጀት አመት የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት፤ ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት በከተማዋ የሚከሰቱ የደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም አመርቂ የሚባል ዉጤት ማየት ተችሏል።
በተለያዩ አካባቢዎች ከ56ሺ 300 በላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ነጋዴዎችን፣ 254 ሺ 255 ህገ ወጥ ማስታወቂያዎችን የለጠፉ፣ ሶስት ሺ700 ህገወጥ ግንባታዎችን ሲከዉኑ የተገኙ ሰዎች ላይ እርምጃ መዉሰድ መቻሉን አብራርተዋል
በእነዚህና በሌሎች ደንብ ጥሰቶች በተወሰደ እርምጃም ባለስልጣኑ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረጋችን አመሰግናቸዋለሁ።
ተጠናክረው የቀጠሉት ግንኙነቶቻችን በሁለቱ ሀገሮቻችን እያደገ ለመጣው ትብብር ዋቢ ናቸው።
Gratitude to Prime Minister Giorgia Meloni for our discussion on bilateral, regional and multilateral issues. Our continued engagements are testament to the growing cooperation between our two countries.
https://twitter.com/ProsperityKera
በአዲስ ምዕራፍ ጉዞው የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም ለማሳወቅና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ይበልጥ መትጋት እንደሚገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት /ኢዜአ/ ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ አስመርቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢዜአ ዘመኑን በሚዋጅ ቴክኖሎጂ መደራጀቱን ገልጸዋል።
ኢዜአ ባለፉት በርካታ ዓመታት ዜናዎችን፣ መረጃዎችን ከአገር ውስጥ እና ከመላው ዓለም ለህዝብ ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የአገር ባለውለታ አንጋፋ ተቋም መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ኢዜአ ዘመኑን የሚዋጁ ቴክኖሎጂዎችን ማሟላቱን መመልከታቸውን ጠቁመው፤ የኢትዮጵያን እውነታ ለመላው ዓለም ለማሳወቅ አስተማማኝ ደረጃ ላይ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል።
ኢዜአ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጎን ለጎን በሰው ሃይል እና በሌሎችም ቁሳቁስ ተደራጅቶ መመልከታቸውንም አክለዋል።
የኢትዮጵያን እውነታ ከፍ ማድረግ የሚችሉ ስራዎችን በመስራት በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን እውነታ ለማሳወቅ ይበልጥ መስራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
የኢዜአ ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ለአካባቢው ተጨማሪ ውበት መፍጠር መቻሉን ጠቁመው፤ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢዜአ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ሦስት የቴሌቪዥንና አራት የሬዲዮ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችን አካቷል።
በተጨማሪም ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ክፍሎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ቤተ-መጽሀፍት፣ የመዝናኛ ማዕከልና ዘመናዊ ጂምናዝየም አሉት።
ከተመሠረተ 82 ዓመታት የሆነው አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ብሔራዊ መግባባት የመፍጠርና የሀገር ገፅታ ግንባታ ተልዕኮውን ለማሳካት ዜና እና ዜና ነክ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ተቋሙ ያስገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስም በዛሬው እለት በደማቅ ሥነ- ስርዓት ተመርቋል።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚዲያ አመራሮችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) ያስገነባውን ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ የምረቃ ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሚዲያ አመራሮችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።
የሚዲያ ኮምፕሌክሱ ዘመኑ የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ያሟላ ሲሆን ሦስት የቴሌቪዥንና አራት የሬዲዮ ዘመናዊ ስቱዲዮዎችን አካቷል።
በተጨማሪም ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ በርካታ ክፍሎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ቤተ-መጽሀፍት፣ የመዝናኛ ማዕከልና ዘመናዊ ጂምናዝየም አሉት።
ከተመሠረተ 81 ዓመታትን የተሻገረው አንጋፋው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ብሔራዊ መግባባት የመፍጠርና የሀገር ገፅታ ግንባታ ተልዕኮውን ለማሳካት ዜና እና ዜና ነክ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ተቋሙ ያስገነባው ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስም በዛሬው እለት በደማቅ ሥነ ስርአት እየተመረቀ ነው።
https://twitter.com/ProsperityKera
ምርታማነትን እናሳድጋለን ፤ የምግብ ዋስትናችንን እናርጋግጣለን፤ ብልፅግናችንም እውን እናደርጋለን !
የአገራችን መጠሪያ እስከመሆን የደረሰውን የድህነትን ታሪክ በመቀየር ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ አልሞ እየተረባረበ የሚገኘው የለውጡ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ አገራችንን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ ያሸጋገሩ ስኬቶችን ማስመዝገብ ጀምሯል ::
ለውጡ አልጋ በአልጋ አይደለም በበርከታ ተግዳሮቶች ውስጥ ነጥሮ እየወጣ የሚገኝ እንጂ ፍሬ የበዛበት ዛፍ ድንጋይ ይበዛበታል እንደሚባለው የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ዕድገት ዕረፍት የሚነሳቸው ታሪካዊ ጠላቶቿ ከውስጥ ተላላኪዎቻቸው ጋር ተቀናጅተው የሚቻላቸውን ሁሉ በማድረግ ቢፍጨረጨሩም አገራዊ ለውጡ በአስተማማኝ ጉዞ ላይ ይገኛል ።
በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በነበርንበት ወቅት ስንዴን ኤክስፖርት እናደርጋለን ስንል ቀልድ የመሰላቸው ብዙ ነበሩ።
የስንዴ እሸት ብዙም የማይታይባቸው የነበሩ አካባቢዎች ጭምር በበጋ የመስኖ ስንዴ ሲሸፈኑና በክረምቱ የዝናብ ወቅት ተመዝግቦ የማያውቅ ምርት እያመረትን ጭምር ኢትዮጵያ በትክክለኛው የልማት ሀዲድ ላይ መግባቷ ለአንዳንዶች አልተገጠላቸውም ነበር።
አንዳንዶች ደግሞ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንደሚባለው በአገራችን የብልፅግና ጉዞ መኩራት ሲገባቸው የሚያዩትን ልማት እና የአገራችን ለውጥ በማደብዘዝ '' ኢትዮጵያ አበቃላት " ከሚለው ሟርታቸው ላይ ተተክለዋል:: ኢትዮጵያ ግን ዕዳዋን ወደ ምንዳ እየቀየረች በእኛም ትውልድ ታሪክ እየሰራች ትገኛለች ።
ከበጋ እስከ ክረምት ያለማቋረጥ የሚፈሱ አዋሽ፣ ዋቢሸበሌ ፣ ኦሞ እና መሰል ታላላቅ ወንዞቻችንን አሁንም ገና በሙሉ አቅማቸው ለልማት ለማዋል ብዙ ቢቀርንም ለበጋ መስኖ ስንዴ በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ትክክለኛውን መንገድ እንደተያያዝነው ግን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።
ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ተግዳሮቶች ሲደራረቡን በአገራዊ አቅም ተቋቁመን መዝለቅ ብቻም ሳይሆን የስንዴ ምርታችን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤክስፖርት ማድረግ የመጀመራችን ሚስጥር በአንድ በኩል የተከተልነው ትክክለኛ አቅጣጫ ውጤት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቀን እና ሌት ከህዝባችን ጋር ላብአችን ጠብ አድርገን እየሰራን በመሆኑ ነው።
የኢትዮጵያን እምቅ የመልማት አቅም የተረዱና የፓርቲያችን ኢትዮጵያን የማበልፀግ ራዕይ የተረዱ አንዳንድ አገራትም ከስንዴ ምርታችን ለመሸመት ፍላጎታቸውን ከገለፁልን ስነባብተዋል ።
በርሀብ የሚጠቀሰው የአገራች ስም አሁን ላይ በልማት ሽልማት መነሳትም ጀምሯል ።
ጠ / ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ዕውን ለማድረግ እያደረጉት ባለው ጥረት እና በሰጡት የአመራር ጥበብ በተለይም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባደረጉት ጥረት እና እየተመዘገበ ባለዉ ውጤት የተባባሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) በድርጅቱ ከፍተኛ የሆነውን አግሪኮላ ሜዳልያ ከሰሞኑ አበርክቶላቸዋል።
ሽልማቱ አገራችንን በድህነት ሳይሆን በልማት ያስጠራ የሁለችንም የላብ አሻራ ውጤት በመሆኑ ሁለችንንም የሚያኮራ ለላቀ ድልም የሚያንሳሳ ነው: :
የእኛ ትውልድ ታሪክ ከመዘከር በተጨማሪ ምርታማነትን እያሳደገ ፤ የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ ብልፅግናችንም እውን እያደረገ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ታሪክ እየሰራ ይገኛል!
Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና
https://twitter.com/ProsperityKera
ከሀገር አቀፍ ወደ አለም እዉቅና 💪
ሀገር ሻጭ ባንዳ በስንዴ ፕሮጀክታችን ሲያላግጥ ሲያንጋጥጥ #FAO ግን በአለም አቀፍ ደረጃ ሸልሞታል!
#ፅንፈኝነት_ይውደም
#አንድነትUnity
https://twitter.com/ProsperityKera
Xiyyeeffannoon bulchiinsi magaalaa keenyaa injifannoo waloo keenya Aduwaa fi #Projektii _Kana #Yaadanno Injiffannoo Aduwaa giddugala magaalaa keenya #finfinnee keessatti, kan mallattoo injifannoo waloo sanaa ta'ee hojjetame, kanaafis, waan baay'ee nama boonsudha hojii bakka seena qabeessa gootonni giddu gala biyyaa irraa hanga Adwaatti imalanitti dhalootaa dhalootatti galateeffamaa jirudha.
#Hoggantuu Keenya Bulchinsaa Magaala Finfinnee Siin Galateefanna🙏🙏
https://twitter.com/ProsperityKera
የፀሐይ አውሮፕላን ወደ እናት ሃገሯ #ኢትዮጵያ ልትመለስ ከስምምነት መደረሱ፤ የአዲሱ የውጭ ዲፕሎማሲያችን ታላቅ ድልና ስኬት አንድ ማሳያ ነው።
https://twitter.com/ProsperityKera
ትኩረቱን በስርዓተ ምግብ ላይ ያደረገ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በሮም ያገኙት ሽልማት የምግብ ዋስትና ብቻ ሳይሆን ስነ ምግብ ስርዓት ላይ እየተደረገ ላለው ጥረት እውቅና የሠጠ መሆኑን ጠቁመዋል።
ትልቅ አቅም ፈጥሮ ወደ ፊት ለመጓዝ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በተወካያቸው ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በኩል ባስተላለፉት መልእክት፣ በኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ በመንደፍ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
የሰቆጣ ዲክላሬሽን ትግበራ ውጤት መገኘቱንም ነው የገለፁት ።
የህጻናት፣ የወጣቶችና የእናቶችን ስርዓተ ምግብ ማሻሻል ላይ ሰፊ ስራ መሰራቱን ጠቁመዋል። በተለይም በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ መስጠቱንም ተናግረዋል።
አሁንም የስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን ፈተና ሆኖ መቀጠሉን የጠቆሙት ሚኒስትር ደኤታው ከሚሞቱ ህጻናት መካከል 50 በመቶ በላይ የሚሆኑት በመቀንጨር ችግር እንደነበር አመልክተዋል።
እንደ ዶ/ር ደረጄ ገለጻ የመቀንጨር ችግር በዜጎች ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ይፈጥራል። አእምሯዊና አካላዊ አደጋ ያጋልጣል። የታዳጊዎችን የፈጠራ አቅምም ይቀንሳል።
በመሆኑም የመቀንጨር ችግርን ለመቀነስ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝና በመቀንጨር ምክንያት የሚደርሰውን የህጻናት ሞት ከ50 ወደ 39 በመቶ መቀነስ መቻሉንም ነው የተነገሩት።
በመቀንጨር ችግር ምክንያት ኢትዮጵያ 16 በመቶ አጠቃላይ አገራዊ እድገት በማሳጣት ተጽእኖ እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።
መርሃ ግብሩን በጣምራ ያዘጋጁት የግብርና ሚኒስትር፣ የጤና ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ናቸው።
https://twitter.com/ProsperityKera
ዓድዋ ለሁለተኛዉ የኢትዮጵያ አርበኝነት ምዕራፍ መሰረት የጣለ ታላቅ ድል!
ለአሁኑ የኢትዮጵያ ትዉልድ ሁለተኛዉ የአርበኝነት ምዕራፍ የብሄራዊነት ትርክትን በመትከልና በማጽናት የኢትዮጵያን እንድነት በጽኑ መሰረት ላይ ማኖር ነዉ፡፡
የዓድዋ ድልን በትክክለኛ ይዘቱ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ማስተላለፍ መቻል ደግሞ ለዚህ ራዕይ እዉንነት ሊያገለግሉ ከሚችሉ ወሳኝ መሰረታዊያን መካከል አንዱና ወሳኙ ነዉ፡፡ አድዋ የእዉነተኛ ህብረ-ብሄራዊነት መገለጫ ነዉ፡፡
ዓድዋ ከጊዜያዊ ፍላጎቶች በመሻገር ለዘላቂ ሀገራዊ ድል እዉንነት ድርና ማግ ሆኖ የመቆም፣ የአርቆ አሳቢነት አብነት ነዉ፡፡ ዓድዋ የእዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት አርማ ነዉ፡፡ የዚህ ትዉልድ አድዋ ምን ይሆን ወሳኙ ጥያቄ ይህ ነዉ፡፡
የዚህ ትዉልድ ዓድዋ ከብሄር፣ ከሀይማኖትና ፖለቲካ ጽንፈኝነት በመሻገር ነጻነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መገንባት መቻል ነዉ፡፡ ለዚህ እዉንነት ያለን አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነዉ፡፡ እሱም ቀደም ሲል በሀገራችን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ተሞክረዉ ያላዋጡትን የቀኝና የግራ ፖለቲካ ጽንፈኝነትን በአግባቡ በመግራትና በማረቅ አሰባሳቢ የብሄራዊነት ትርክትን መትከልና ማጽናት ነዉ፡፡
በዉኑ ብሄራዊነት ምንድነዉ? ብሄራዊነት መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብሄራዊ መግባባት (National Consensus) በመፍጠር በመከባበርና በመተባበር አብሮ የመኖር፣ በተናጠል ማንነቶችና በሀገራዊ ማንነት መካከል ሚዛን ጠብቆ ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምንና ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዳይ ነዉ፡፡
ብሄራዊነት ፓርቲያችን ብልጽግና ገና ከመመስረቱ ጀምሮ ኅብረ ብሔራዊነት፣ አካታችነት፣ ፍትሐዊነት እና እኩልነት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ህልዉና የሚያስፈልጉ መሆናቸዉን በየሰነዶቹ ያረጋገጠዉን በተግባር በማጽናት ኢትዮጵያን ከፍጹማዊ አንድነትና ፍጹማዊ ልዩነት ሰለባነት በመታደግ ዘላቂና ቅቡልነት ያለዉን ሀገረ-መንግስት በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት የቀመረዉ አሰባሳቢ ትርክት ነዉ፡፡
ብሔራዊነት የህዝቦችን የጋራ ጉዳይ ማጉላት ነው፡፡ ብሔራዊነት በአንድነት የሚፀና ብዝኃነት ነው፡፡ ብሄራዊነት በብዝኃነት የሚዋብ አንድነት ነው፡፡ ብሄራዊነት ኢትዮጵያውያን የቋንቋ፣ ባህል፣ ራስን በራስ ማስተዳደር እና ሌሎችም ፍላጎቶች በነጻነት እንዲተገብሩ እኩል ዕውቅና ይሰጣል፡፡ ብሄራዊነት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሀገር ጉዳይ ላይ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው የሚያስችል እሳቤ ነው፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
"ፀሐይ" እ.አ.አ በ1935 በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራ አውሮፕላን።
"Tsehay" is the first aircraft built in Ethiopia in 1935.
© Abiy Ahmed Ali
FDRE 🇪🇹 PM
https://twitter.com/ProsperityKera
#የጊዜ_አጠቃቀም_ጥበብ 👇
ምንም ነገር ብትከስር መጨረሻ ላይ የምትከፍለው በጊዜህ ነው፡፡ የስልጣኔ ሁሉ ስልጣኔ ጊዜን በተገቢው መንገድ የመጠቀም ስልጣኔ ነው፡፡ በሕይወትህ እቅድ የሞላው ኑሮ ለመኖርም ሆነ ማንኛውንም ተግባርህን በወቅቱና በተዋጣለት ሁኔታ ለማከናወን ከፈለክ የጊዜ አጠቃቀምን መሰረታዊ እውነታዎች ከዚህ መጽሐፍ የማግኘት ምርጫ አለህ፡፡
ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . .
የጊዜ ትርጉምና አስፈላጊነት
“ጊዜ ከሁሉ ነገር በላይ እጅግ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ በተበላሸ ሁኔታ የምንጠቀምበት ነገር ነው” - William Penn
• የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀው፤
• የአንድን ወር ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ካለወሩ የተወለደን ሕጻን የወለደችን ሴት ጠይቃት፤
• የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በየሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቀው፤
• የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ የወሳኝ ፈተናን ውጤት ነገ ለመስማት የሚጠብቅን ተማሪ ጠይቀው፤
• የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸው፤
• የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ አውቶቡስ ለትንሽ ያመለጠውን ሰው ጠይቀው፤
• የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰው ጠይቀው፤
• የአንድን ሚሊ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀው፡፡ - Unknown Source
ሰው ለምንም ነገር የሚከፍለው በገንዘብ ሳይሆን በጊዜ ነው፡፡ ይህ እውነት ቀድሞውኑ ገንዘቡን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣው “ጊዜ” የተባለው ነገር የመሆኑን እውነታ ጠቋሚ ነው፡፡ ጊዜ በአለም ላይ ውድ ከተባሉ ነገሮች ቀደምተኛውን ስፍራ የያዘ ጉዳይ ነው፡፡ ጊዜውን ያባከነ ሰው ሕይወቱን ያባከነ ሰው ነው፡፡
ጊዜን በአግባቡ ባለመጠቀም ምክንያት ሰዎች ገንዘብን ይከስራሉ፣ ወዳጅነትን ያበላሻሉ፣ ከዚያም አልፎ፣ አንዳንድ ጊዜ፣ በሞትና በሕይወት መካከል የሚወስን ገጠመኝ ውስጥ ራሳቸውን ይጨምራሉ፡፡
የጊዜ አጠቃቀማችን ሁኔታ ተጽእኖው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ጊዜ አንድና አንድ በመሆኑ ነው - ጊዜ አንዴ ካለፈ በፍጹም ተመልሶ አይመጣም፡፡ ጊዜ በብዙ እድሎች የተሞላ ሃብት ነው፡፡ ጊዜ እንዲሁ ሲያልፍና ሲባክን ከዚያው ጋር አስገራሚ እድሎችና ሌሎች ውብ ነገሮች አብረው ያልፋሉ፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
13ኛው የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና የንግድ ሚኒሰትሮች ም/ቤት ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ ደርበን ከተማ እየተካሄደ ነው።
በስብሰባው ኢትዮጵያን በመወከል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በስብሰባው በስምምነቱ ማዕቀፍ ሀገራት የሁለትዮሽ የሙከራ ንግድ የሚጀምሩበትና የሚያጠነክሩበት፣ የድጅታል ግብይት ተቋማዊ ሆኖ የሚጀምርበት እና በሌሎች ተያያዥነት ባላቸው አጀንዳዎች ዙርያ ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድር ሊካሄድ ነው
የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቦክስ ማኅበር ከዓለም አቀፍ አሊያንስ ቦክስ ማኅበር እና ከሶሎ ኢንተርናሽናል ስፖርት ኃላ/የተ/የግል ማኅበር ጋር በመተባበር ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድር ሊያካሂድ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአፍሪካ-ካናዳ ዓለም አቀፍ የቦክስ ፌዴሬሽን ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ኢንስትራክተር ዮሴፍ ነጋሽ ÷ በውድድሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ የብሪታንያ፣ የኬንያ፣ የዩጋንዳና የአይቬሪኮስት ቦክሰኞች እንደሚሳተፉ ገልፀዋል፡፡
በውድድሩ ታዋቂ ቦክሰኞች በአፍሪካ የከባድና የቀላል ሚዛን ሻምፒዮና የሆኑት ኮፊል ሚካኤል እና ዱኩ ሮናልድ በከባድ ሚዛን በ71 ኪሎ እንደሚወዳደሩና ኢትዮጵያም በከፊል ፕሮፌሽናልነት በ57 እና በ63 ኪሎ የምትወዳደር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የአፍሪካ-ካናዳ ዓለም አቀፍ የቦክስ ፌዴሬሽን ማኅበር ምክትል ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ መላከ ተሰማ በበኩላቸው÷ ውድድሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ የሚካሄድ በመሆኑ ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡
ውድድሩ÷ በሀገሪቱ መካከል የስፖርታዊ አጋርነትንና የባህል ልውውጥ ለመፍጠር እንደሚያግዝ፤ በኢትዮጵያ መካሄዱም ተተኪና ፕሮፌሽናል የቦክስ ስፖርተኞችን ለማፍራት ብሎም የሀገሪቱን በጎ ገፅታ ለመገንባትና በቦክሱ ስፖርት ዘርፍ መነቃቃት ለመፍጠር እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡
ከውድድሩ ጎን ለጎንም ለቦክስ ዳኞች ስልጠናና ለፕሮጀክቶች ድጋፍ ይደረጋል መባሉን ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ውድድሩ “ሰላም በአፍሪካ” በሚል መሪ ሐሳብ መጋቢት 15 ቀን 2016ዓ.ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ከቀኑ 10 ጀምሮ የሚካሄድ መሆኑን ተገልጿል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተውን የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደር ኤክስፖ ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ከፕሬዝደንቷ በተጨማሪ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
"አርብቶ አደርነት- የምስራቅ አፍሪካ ሕብረ-ቀለም" በሚል መሪ ሀሳብ በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተው የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደር ኤክስፖ አምስተኛ ቀኑን ያያዘ ሲሆን በበርካቶች እየተጎበኘ ይገኛል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንዲቀመጡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ተወካዮች በእጃቸው የሚገኙ ቅርሶችን ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል::
የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተለያዩ ዞኖች ያሰባሰባቸውን ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ስላበረከቱ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
ሌሎችም የነዚህን አርዓያ በመከተል ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች ትውልድ እንዲማርባቸው በዓድዋ ድል መታሰቢያ እንዲቀመጡ በእጃቸው የሚገኙ ቅርሶችን እንዲያበረክቱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::
https://twitter.com/ProsperityKera
"የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳን አስረክባለሁ" በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅ/ቤት አዘጋጅነት በዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እና በሴቶች የኢኮኖሚ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረው ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
መድረኩ በአማራ፣በሲዳማ፣በአፋር እና በቤኒሻንጉል ክልል ጅማሬውን ያገኘ ሲሆን በሌሎች ክልሎችም እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
በሐሰተኛ ሰነድ ከባለሃብት 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር አጭበርብሮ ተቀብሎ የተሰወረውንና ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ የተባለውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታ ሴንትራል ማተሚያ ቤት አካባቢ በሐሰተኛ ሠነድ አጭበርብሮ ከባለሀብቱ ገንዘቡን ተቀብሎ የተሠወረውን ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታን የተባለውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዚህ ግለሰብ ተታለልኩ ወይም ተጭበረበኩ የሚል ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ ተቋሙ አስታውቋል።
ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር እንዳይታለል ራሱን እንዲጠብቅና በወንጀል መከላከል ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ከዓለም ባንክ በተገኘ የ145 ሚሊዮን ዶላር ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የከተማችን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምስራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ከሲ ጂሲ ኦሲ የግንባታ ተቋራጭ ጋር ተፈራርመናል።
ፕሮጀክቱ በዋነኛነት ከዚህ ቀደም የፍሳሽ መሰረተ ልማት ያልተዳረሰባቸው የካ፣ ቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ግንባታው በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።
አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ ለህዝባችን የገባነውን ቃል በተግባር እየፈፀምን በትጋት ማገልገላችንን የምንቀጥል ይሆናል። የዓለም ባንክ ለከተማችን የተለያዩ ዘርፎች እያደረገ ላለው አስተዋፅዖ በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግን እወዳለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
https://twitter.com/ProsperityKera
“መጫወት ስታቆሙ ታረጃላችሁ”
ሰው መጫወት የሚያቆመው በእድሜ ሲያረጅ አይደለም፣ መጫወት ሲያቆም ግን ወዲያው ማርጀት ይጀምራል፡፡
ደስተኞችና ስኬታማዎች መሆን ከፈለጋችሁ፣ ምስጢሩ ግልጽ ነው፡- በየቀኑ የሚያስቅ ነገር ፈልጋችሁ መሳቅና መጫወት አለባችሁ፡፡ በዙሪያችን ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሰዎች ይህንና ያንን ሳያደርጉ እድሜያቸው በማለፉ ምክንያት ሲጸጸቱ ይታያሉ፡፡ መለወጥ የማይችሉትን ነገር እያወጡና እያወረዱ ቢጸጸቱ ምንም ለውጥ እንደማያመጡ እያወቁት እንኳን ወደ ፊት መራመድ እስከሚያቅታቸው ድረስ የስሜት ቀውስ ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ አመለካከትን በመለወጥ ግን ባሉበት ሁኔታ ማድረግ የሚችሉትን ወደማድረግና በዚያም ወደመደሰት መዝለቅ ይችላሉ፡፡
“ማለም ስታቆሙ ትሞታላችሁ”
ሰው ማለም የሚያቆመው ሲሞት አይደለም፣ ማለም ሲያቆም ግን ወዲያው መሞት ይጀምራል፡፡
የነቃና የሞቀ ኑሮ መኖር ከፈለጋችሁ መንገዱ አንድ ነው፡- ሕልም ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ሕልማችሁን ስታጡ ትሞታላችሁ፡፡ በዙሪያችን በርካታ ሰዎች ሞተው እንኳን እንደሞቱ አልገባቸውም፡፡ መኖር ማለት መተንፈስ፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መተኛትና መነሳት ብቻ አይደለም፡፡ መኖር መለወጥና ማደግን ይጨምራል፡፡ መለወጥ ገጽታ ብቻ አይደለም፣ አመለካከትንና ባህሪይንም ይጠቀልላል፡፡ የዚህ አይነቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማስተናገድ ደግሞ ሕልምንና ራእይን አለመልቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡
“ማደግ ስታቆሙ ወደኋላ ትቀራላችሁ”
ሰው ማደግ የሚያቆመው ወደኋላ ሲቀር አይደለም፣ ማደግ ሲያቆም ግን ወዲያው ወደኋላ መቅረት ይጀምራል፡፡
በእድሜ በመግፋትና በማደግ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ በእድሜ መግፋት የግድ ነው፣ ማደግና መብሰል ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን እውነት ስንገነዘብ በእድሜ በመግፋትና በመብሰል መካከል ያለውን ልዩነት ስለምንገነዘብ በዚያ ምክንያት ከሚመጡ ባሉበት የመርገጥ፣ አልፎም ወደ ኋላ የመንሸራተት ጠንቆች እንድናለን፡፡
አድሜ መግፋት ለሁሉም የተሰጠ እውነታ ነው፡፡ እድሜን መቁጠር ምንም አይነት ልዩ ስጦታና ችሎታ አይጠይቅም፡፡ የእድሜህ ቁጥር በጨመረ መጠን ለማደግና ለመብሰል ራስህን ካላዘጋጀህ ትሄዳለህ ግን አትደርስም፣ ትባክናለህ ግን አታከናውንም፣ ታስቀምጣለህ ግን አታጠራቅምም፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera