prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በጊፍት ሪል ስቴት ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች እና ለሃገር ባለውለታ ነዋሪዎቻችን ያስገነባነውን ባለ 5 ወለል ህንጻ አስረክበናል።

ዛሬ የተላለፉትን 30 ቤቶችን ጨምሮ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ከአምስት ሺ በላይ ቤቶችን ገንብተናል።
ጥሪያችንን በመቀበል በዚህ በጎ ስራ ላይ በመሳተፍ ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በቂርቆስ ለነበረህ እጅግ ተወዳጅ ጊዜ #እናመሠግናለን 🙏

በቂርቆስ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ኣይተ #ብርሃነ ገ/ፃድቅ የአራዳ ክ/ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተሹመዋል 👏👏👏

የስራ ኃላፊው በክፍለ ከተማችን በነበራቸው ቆይታ በመላው አመራሩ፣ በፓርቲው አባላት፣ በተለያዩ የመዋቅር አባላት፣ በክፍለ ከተማው ነዋሪዎች፣ ... እጅግ የተወደዱና የተከበሩ እጅግም ቅን፣ የሰውነት ቁመናቸው ከፍ ያለ ታታሪና ውጤታማ አመራራችን ነበሩ።

ኣይተ #ብርሃነ_ገ_ጻድቅ አሁን ደግሞ ለላቀ የስራ ኃላፊነት ወደ አራዳ ክ/ከተማ በም/ዋና ስራ አስፈጻሚነት ተዘዋውረዋል።

ወንድም አለም #ወዲ_መረብ_አሕሰአ በአራዳ ክ/ከተማ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማቸው እየተመኘን በክፍለ ከተማችን በነበራቸው ቆይታ ላሳዩን መልካምነትና ቆራጥ መሪነት ከልብ እናመሠግናለን ለማለት እንፈልጋለን።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አመራሮች የ2016 ዓ/ም የ6 ወራት የፖለቲካ እና የድርጅት ስራዎችን እየገመገሙ ይገኛሉ ።

በግምገማዊ ውይይቱ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች ም በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን ጥንካሬና ድክመቶች በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚመላከቱ ይጠበቃል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://vm.tiktok.com/ZM6tYRNv7/

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ይህን እውነት ካላመንክ አንተ አማርኛ ተናጋሪ ጣሊያናዊ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለህም

አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ውስጥ የተሰሩትን የጀግኖች ሃውልት በተመለከተ ትችት የሚያወሩት ክፋት ብቻ በማሰብ ምን ያህል ቢታደሉ ነው? መቼም ክፋትን ባይታደሉ ገና ሳያዩ ባላወሩ ነበር።

ሚኒሊክ ስለያዘው ዱላ ምን አገባህ? ሚኒልክ ብቻ ስሙ በመነሳቱ ተጨማሪ ሃውልት እዛጋ በመሰራቱ ደስ ሳይልህ ስለሚኒልክ ዱላ ኡኡታ🤔🤔🤔...?

ነገስታት በእጃቸው ብዙ ነገር ይዘው ፎቶ አላቸው። ዱላም፣ ገጀራም፣ጎራዴም፣ጦርም ሌሎች ጌጣጌጦችንና ዘንጎችን ይዘው ታይተዋል። ሚኒሊክም እንደማንኛውም ነገስታት ብዙ አይነት ፎቶዎች አይተናል።ታድያ ምነው ተአምር ሆነባችሁ?ይሄኛውስ ፎቶ ላይ ያለው ብትር የሚኒልክ አይደለምን🤔🤔🤔?

ዋናው ሃሳብ እነኚህን ታሪካዊ ጀግኖችን በአንድ ስፍራ ላይ አምጥቶ ዓድዋን መዘከር መቻሉ ነው። ይሄ ሃሳብ ብቻውን ሊያስደምም የሚገባ ሆኖ ሳለ ስለጫማና ስለያዘው ዱላ ከተጨነክ አንተ በዓድዋ ታፍራለህ ማለት ነው። ሚኒሊክ እና ጣይቱን ጨምሮ 12 የጦር ጀነራሎች በአንድ ስፍራ አምጥቶ እንዲታሰቡ ማድረግን ምነው በአንድ ቃል ብትገልፅ?

ይሄን ማድረግ ካልቻልክ አንተ አማርኛ ተናጋሪ ጣሊያናዊ እንጂ ኢትዮጵያዊ ነህ ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል።

ስለተሰራ ትልቅ ነገር ሳታስብ ወርደህ ስለትናንሽ ነገር ስታስብ ክፋት እንጂ ፈፅሞ ሌላ ጉዳይ ሊሆን አይችልም። ዋናው አላማችሁ ችግር መፍጠር ብቻ እንደሆነ በግልፅ ያስታውቃል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

CONGRATULATIONS Asaminew Teshome (phd) 🙏 ታታሪው፣ ጀግናውና ቁርጠኛው ወንድምአለም እንኳን ደስ አለህ

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አሳምነው ተሾመ የአለም አቀፍ የመሬት ከባቢ አየር ስርዓት ጥናት ምርምር ፓናል /Global Land Atmosphere System study Research Panel/ አባል ሆኑ 👏👏👏👏👏👏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#የቂርቆስ_ክፍለከተማ_የምሽት_ገፅታዋ_በከፊል
ቂርቆስ እንግዶቿን ለመቀበል፣ አደባባዮቿን፣ ሆቴሎቿን፣ መንገዶቿን፣ ተቋሞቿን እንዲህ አሸብርቃ እየተጠባበቀች ነው

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ዓድዋ_የነጻነት1ዉሃ_ልክ!

"እምዬ ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም!" ያለዉ ማን ነበር?

የአዉሮፓ ወራሪ ሀይሎች እንደ ጎርጎሲያኑ የዘመን ቀመር ከ1884-1885 መካከል በዛሬይቱ ሀገረ ጀርመን በበርሊን ከተማ አፍሪካን የመቀራመት ዉይይት ሲያካሂዱ በነበሩበት ወቅት ወደ አፍሪካ የምንሄደዉ ለተቀደሰ ዓላማ (benevolent purpose) ነዉ የምል አንድ አስቂኝ አቋም ነበራቸዉ፡፡ በመሆኑም ወደ አፍሪካ መጥተዉ አፍሪካን ያለ አፍሪካዊያን ፍላጎት ቅኝ የሚገዙት የላቀ የበጎ አድራጎት (philanthropy) ተግባራት ለአፍሪካ ህዝብ ማበርከት ስላስፈለጋቸዉ መሆኑን በወቅቱ ባዘጋጇዋቸዉ ሰነዶች ሳይቀር አስፍረዋል (Matthew 2015: 34)
እስካሁንም ድረስ ወራሪነትን የሚያንቆለጳጵሱ ሀይሎች ከቅርብም ከሩቅም አልታጡም፡፡

አጀንዳቸዉ ግን ዉስጠ-ወይራ ነበር፡፡ ልክ በአፋቸዉ እንደተናገሩትና በስምምነቶቻቸዉ እንዳሰፈሩት ፍላጎታቸዉ አፍሪካን ከተቀሩት አህጉራት ጋር በንግድና በመሳሰሉት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች በማቆራኘት የአፍሪካን ህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሳይሆን የአፍሪካን ማዕድናት፣ ዉሃዎች፣ የእርሻ መሬቶች፣ ነዳጅና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን መበዝበዝ ነበር፡፡ ፍላጎታቸዉ በዚህ ብቻ አይቆምም፤ የአፍሪካን ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ የኑሮ ዘዬና ስነ-ልቦናን በማክሰም በራሳቸዉ መተካት ነበር፡፡ እነዚህን የጭቆና ተግባሮቻቸዉን በገዙዋቸዉ የአፍሪካ ሀገራት ላይ ተጨባጭ ማድረግ ችለዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ግን ያኔም ቢሆን ነቄዎች ነበሩ፡፡ “ዓለም አቀፋዊነትን እዉን እናደርጋለን” በሚል ሽፋን ሉዓላዊ ሀገራትን የመዉረር የምዕራባዊያንን ሴራ በልኩ በመረዳት ነዉ በተባበረ ክንድ መክተዉ መመለስ የቻሉት፡፡

የእኛም ትዉልድ መንቃት አለበት፡፡ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከታሪካዊ ጠላቶቻችንና ከዉስጥ ጀሌዎቻቸዉ የሚቃጣብንን የስነ-ልቦና ጥቃት ቀልብሰን የኢትዮጵያን ብልጽግና፣ ሰላምና ልዕልና በሚያጸኑ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደ ንብ ተሰባስባን ለጋራ ሀገር ግንባታ መረባረብ አለብን፡፡

እኛ እያለን አባቶቻችን ሳይማሩ የገነቡልንን ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያችን ታሪካዊ ጠላቶቻችንና የታሪክ አተላዎች ማፍረስ አይችሉም፡፡ የፖለቲካ ልዩነት ያለ፣የነበረና መቼም ቢሆን የሚኖር ነው፡፡

በኢትዮጵያ ግን ልዩነት አይኖረንም፡፡ ኢትዮጵያ የጋራ ማንነታችን ናት! እምዬ ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም ያለዉ ማን ነበር?

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የታችኛው ቤተመንግስት አሁናዊ ሁኔታ በመሀል አዲስ አበባ ላይ‼
#Fast_Growing_Ethiopia 🇪🇹
@AbiyAhmedAli 💪
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
#ቀይባህር_ህልውናችን

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለኢትዮጲያ ጸሀይን እያወጣ ያለው መሪ ጸሀይን ወደ ትውልድ ሀገሮ መልሶታል‼
#Fast_Growing_Ethiopia
@AbiyAhmedAli 💪
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
#ቀይባህር_ህልዉናችን 🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

History has changed well deserved and recognition!!
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
@AbiyAhmedAli 💪
#Fast_Growing_Ethiopia
#ቀይባህር_ህልዉናችን 🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የስኬት ቁልፉ ዕዳዎችን ወደ ምንዳ መቀየር መቻል መሆኑን የተረዳው ወጣት !

እንደ ግለሰብ ፣ እንደ ማህበረሰብ ወይም እንደ አገር በየጊዜው ችግሮች ያጋጥማሉ። ይህ ያለ ፣ የነበረ ወደፊትም የሚኖር ቢሆንም ዋናው ቁም ነገር ችግሮችን እንደመስፈንጠሪያ መጠቀም መቻል ነው፡ ፡

ብልፅግና እንደ ፓርቲ መንግስትም እንደ መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት አገራችን ያጋጠሟትን ውስብስብ ፈተናዎች ወደ ድል በመቀየር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጭምር አንፀባራቂ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።

ለአብነትም በከተማችን የሚስተዋለውንና ዓለም አቀፍዊ እና ተፈጥሯዊ እንዲሁም ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ያሉትን የኑሮ ውድነት ለማቃለል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠው የተለየ ትኩረት በከተማ ግብርና እና በሌማት ቱሩፋት ፕሮግራሞቻችን በውስን የከተማ መሬት ወደ ጐን ብቻ ሳይሆን ወደ ላይ ጭምር በማልማት ከቤተሰብ አልፎ ለገበያም ማቅረብ እንደሚቻል ብዙዎች በተግባር ማረጋገጥ ጀምረዋል።

ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ነዋሪ የሆነው ወጣት አሸናፊ ዋለ ሀይሌ በኤሌክትሪሲቲ በአድ ቫንስድ ዲፕሎም ተመርቆ ከአዲስ አበባ እየተመላለሰ በርካታ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የድርሻውን ማበርከቱን ይናገራል።

የኮሮና ቫይረስ መከስቱን ተከትሎ በነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ የሚወደውን ስራውን ትቶ ከቤት ለመዋል እንደተገዳደ ያስታውሳል።

ችግር መፍትሄን ይወልዳል እንዲሉ ወጣቱ እጁን አጣጥፎ ቢቀመጥ ህይወቱን መምራት እንደማይችል ሲረዳ ስራ ለመፍጠር ማሰላሰል ጀምሯል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘረጋው የሌማት ቱርፋት ኘሮግራም ደግሞ ትኩረቱን ከሳቡት የስራ መስኮች ቀዳሚ ምርጫው እንደነበር ወጣት አሸናፊ አጫውቶናል።

በ2013 ዓ/ም አንድ ሚሊዮን ብር በመበደር የከተማ ግብርና ስራውን እንደጀመረ የነገርን ወጣቱ ዛሬ ላይ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግቧል፡

ከ10 ሺህ በላይ ዶሮዎችን እያረባ ሲሆን በቀን በአማካኝ ከ8ሺህ በላይ እንቁላል ያመረታል። በሰባት የወተት ላሞች በቀን ከ150 በላይ ሊትር ወተት ያገኛል። 10 የስጋ በሬዎችን የሚያደልበው ወጣት አሸናፊ 15 በጐችን እና 5 ፍየሎችንም ያረባል።

ከእንስሳት እርባታ በተጨማሪ በጓሮ አትክልትም የተሰማራው ወጣት አሸናፊ ይህንን ሁሉ የግብርና ስራ የሚያከናውነው የተትረፈረፈ ቦታ ኖሮት አይደለም ::

በትምህት እና በስራ ዓለም ያገኘውን እውቀት ከዩቱብ ካገኘው መረጃ በማዳበር ጭምር የተከራየውን ቤት ወደ ላይ ሶስት ፎቅ በመስራት ለዶሮ እርባታ አመቻችቶታል:: ሌሎቹንም ስራዎችን ከተከራየው ቤት የሚያከናውን ሲሆን በየወሩ 88 ሺህ ብር እንደሚከፍል ነግሮናል።

አሁን ላይ ለ 16 ወንዶች እና ለ 10 ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሲሆን ስራውን በማስፋት የመኖ ማቀነባበር ስራ ላይ ለመሰማራት ማሽኖችን ማምጣቱንም አጫውቶናል ::

ለእንስቶቹ ክትባት ለምርቶቹ ደግሞ የገበያ ትስስር እየተፈጠሩለት በመሆኑ የወረዳ 6 አስተዳደርን የሚያመሰግነው ወጣት አሸናፊ በቀጣይ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የመሳሪያ ቦታ ጥያቄ አቅርቦ እየተጠባበቀ እንደሚገኝም ነግሮናል።

የስኬት ቁልፉ ዕዳዎችን ወደ ምንዳ መቀየር መቻል መሆኑን ከወጣት አሸናፊ ተሞክሮ በመቅሰም ብዙም ያልተነካውን የከተማ ግብርና ዕምቅ አቅም ወደፊትም ብዙዎች እንደሚለወጡበት ይታመናል።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ፀሐዬ_ደመቀች 🇪🇹💪🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች። የኢትዮጵያ ብልፅግና ቅርብ ነዉ 🔥

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ድህነት ጌጣችን አይደልም። የምንኮራበት ልዩ ሀብታችንም አይደልም 📝 ድህነትን ለቀጣዩ ትዉልድ በፍፁም በፍፁም አናስተላልፍም። ይልቁንም በሁሉም መስክ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናወርሳለን እንጂ።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአገው ፈረሰኞች ማህበር 84ኛ ዓመት በዓል በእንጅባራ ከተማ “የሰላም አርበኝነት ለወንድማማችነት” በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ተከብሯል።

በበዓሉ ከብሔረሰቡ ባህላዊ ጨዋታ በተጨማሪ የፈረስ ዝላይ፣ የስግሪያ ጨዋታ፣ ድንግል አንሳ፣ ጉግስና ሽርጥ የተሰኙ ትርኢቶች ለታዳሚው ቀርቧል።

በበዓሉ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታሁን (ዶ/ር) እንዲሁም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ጣሂር መሃመድ እና ሌሎች የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች መታደማቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ከሆኑት ሬሚ ማርሼ ጋር የደጎል አደባባይን መልሶ ማልማት እንዲሁም በከተማችን ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎትን በጋራ መስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል።

We engaged in a productive discussion with Remi Marechaux, the French ambassador to Ethiopia, focusing on the revitalization of Degol Square and to collaborate on the development of Bus Rapid Transit (BRT) system in our city.

© Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#አድዋ 🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዓድዋ የብሄራዊ ትርክት ምሰሶ፤ የህብረ-ብሄራዊነት ድርና ማግ!

የዓድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን ያለ ልዩነት ሆ ብለዉ በመነሳት ከዉጭ የተቃጣባቸዉን ጥቃት በመቀልበስ የሀገራችን ነጻነትና ሉዓላዊነት ያጸኑብት፣ ለሰዉ ልጆች ሁሉ አይበገሬነትን ያስተማሩበት በዘመናት ርዝማኔ የማይደበዝዝ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ዘላለማዊ ኩራት ነዉ፡፡

የዓድዋ ድል እና ሌሎች ድሎቻችን የመጀመሪያዉ ምዕራፍ የኢትዮጵያ አርበኝነት ማሳያዎች ናቸዉ፡፡ እነዚያ ድሎች የጀግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን መስዋዕትነት ውጤቶች ናቸዉ፡፡ ይሄ ትውልድ ደግሞ ድርብርብ ሃላፊነቶች አሉት፡፡ በአንድ በኩል የአባቶቹን ድሎች በልካቸዉ ሰንዶ ለሚመጣዉ ትዉልድ የማሸጋገር ሃፊነት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ልክ እንደ አባቶቹ ቀጣይ ትዉልድ የሚጽፍለትን የጀግንነት ተግባር ዛሬ ላይ በተጨባጭ የማከናወን ሃላፊነት ነዉ፡፡ በመሆኑም ይሄ ትዉልድ በብልጽግና መራሹ መንግስት ፖሊሲ ቀማሪነትና አቅጣጫ ቀያሽነት ሁለተኛዉ ምዕራፍ የአርበኝነት ስኬት እዉን ለማድረግ ሌትና ቀን እየሰራ ይገኛል፡፡

ሁለተኛዉ የአርበኝነት ምዕራፍ በኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደት ዉስጥ ያጋጠመዉን የትርክት ተቃርኖዎችን ከመሰረታቸዉ በማረቅ ብሄራዊ ትርክትን የመትከልና የማጽናት ራዕይ ነዉ፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እድሜህ ስንት ነው?

ራሱን በማወቅና ዓላማውን በመለየት የተደላደለ ሰው እና በዚህ ሁኔታ ያልበሰለ ሰው ጊዜን በእኩል ሁኔታ አይጠቀሙበትም፡፡ ስለሆነም ራእዩን በሚገባ አጥርቶ ለመለየት ራሱን ያላዘጋጀ ሰው የሚኖረውን የሕይወት ጎዳና አስመልክቶ የአንድን ሰው እይታ እናጢን፡፡ ይህ ሰው የአንድ ሰው የሕይወት ዘመን በአማካኝ 75 ቢሆን ብሎ ካሰላ በኋላ፣ እንዲህ ሲል ተናገረ፡-

• የመጀመሪያዎቹን 15 ዓመታት ራሳችንን ለማግኘት ስንጣጣር እናሳልፋለን፡፡

• ከ15 – 30 ዓመታችን ሌሎች የምናደንቃቸውን ሰዎች ለመምሰል ስንጣጣር እናሳልፋለን፡፡

• ከ30 – 45 ዓመታችን ላለፉት 15 ዓመታት ማንን ለመምሰል ስንጣጣር እንዳሳለፍነው ስናስብ እናሳልፋለን፡፡

• ከ45 – 60 ዓመታችን ሁለተኛ እድል የሚሰጠን ሰው ስንፈልግ እናሳልፋለን፡፡

• ከ60 – 75 ዓመታችን የኖርንባቸው ዓመታት በምንና እንዴት ፈጥነው እንዳለፉ ስናውጠነጥን እናሳልፋለን (Unknown Source)፡፡

ይህ ስሌት ምናልባት ሁላችንንም የሚወክል ባይሆንም እድሜያችንን የምናሳልፍበትን ነገር በጥንቃቄ እንድናስብ ልቦናችንን ያነቃዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ሰው ራሱን ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት በጊዜው ላይ ምን ያህል ተጽእኖ እንዳለው አመልካች ነው፡፡

በዚህች ባለችን ጥቂት ዘመን ጊዜያችን በቅጡ ተጠቅመንበትና ለግላችን፣ ለቤተሰባችንም ሆነ ለሕብረተሰቡ የሚረባን ነገር በመትከል አሻራችንን ትተን ለማለፍ በቅድሚያ መስመር ልናስይዛቸው የሚገቡን ጉዳዮች አሉ፡፡ ከእነዚህ ጉዳዮች መካከል ራስንና የሕይወትን ዓላማ የማወቅ ጉዳይ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

እድሜህ ከ15 ዓመታት በታች ከሆነ ራስህን ለማግኘጥ ያለህን ጥረት እንድትቀጥል እየተመከረክ በጥሩ ምሳሌና መካሪ ሰው ስር የመሆንህንም ጉዳይ በጥብቅ አስብበት፡፡

እድሜህ ከ15 – 30 ዓመት ከሆነ ሌሎችን ሰዎች የማድነቅህ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ራስህንና ማንነትህን በማግኘት ያንን የመሆንህን ጉዳይም ከዚያው ጋር በጥብቅ እንድታስብበት ትመከራለህ፡፡

እድሜህ ከ30 – 45 ዓመት ከሆነ በሕይወት የመደላደልህ ጉዳይና መሰረት የማጣልህ ጉዳይ ወሳኝ ወቅት ላይ ስላለ ያንን ለማድረግ ብዙ ጊዜ እንዳልቀረህ በማሳብ አስፈላጊውንና አስቸኳይ እርምጃ መውሰድህን አትርሳ፡፡

እድሜህ ከ45 – 60 ዓመት ውስጥ ከሆነ ስላለፈው ሁኔታ መጸጸት በማቆም ባለፈው እድሜያችን ስንዘራ የቆየናቸው ነገሮች የሚበቅሉበት ወቅት በመሆኑ የምትችለውን እርማት ካደረክ በኋላ ወደ ፊት እንድትመለከት ትመከራለህ፡፡

እድሜህ ከ60 – 75 ዓመት ከሆነ ስላለፈው ትዝታ የማወጣትና የማውረዱ አውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለሚቀጥለው ትውልድ ትተህ ስለምታፈው መልካም ነገር ማሰብ እንድትጀምር ትመከራለህ፡፡

(“የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከሚለው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስብራት ለመጠገን ያለ ቁርጠኝነት፤ ሳይጨርሱ ላለመቀመጥ ያለ ትጋት፤ ልክ የሌለው የኢትዮጵያ ፍቅር‼

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Adawaa Madaala Bilisummaa!
“Harmee too Itoophiyaa, kan birmadummaa keetitti bu’e haa barbadaa’u” kan jedhe eenyu ture?

Humnoonni weerartoota Awurooppaa Bara 1884-1885 ALA tti biyya Jarman har’aa tana, Magaalaa Barliin jedhamtutti walgahanii yeroo mari’atan “gara Afrikaatti kan imallu kaayyoo eebbifamaa (Benevolent Purpose)” dhaaf akka ta’etti eeruun qoosaa nama kofalchiisu kaayyeffatanii akka dhufan ibsanii turan.

Kanaanis gara Afrikaatti kan dhufan ergama dhoksaa; fuulleen isaa gocha gaarii, karaa naanna’aan garuu qabeenya Afrikaa qoqqoodanii saamuuf eeyyama Afrikaanotaatin ala Afrikaa fi Afrikaanotaaf hojjiilee gocha gaariin (philanthropy) kennuun badhaasuuf akka ta’etti sanadoota qopheeffatan keessatti illee kaa’atanii turan.(Matthew 2015:34)

Ammas taanan, weerara akkasii dhihoof fagoorraa kanneen leellisan hin dhabamne. Ajandaan isaan qabatanii dhufanii turan sun garuu ijoon isaa iccitiin kan guuttame ture. Kaayyoon isaanis akkuma afaanin kaasanii sanada isaanii irrattis kaahatan Afrikaa daldalaa fi diinagdeen aardilee biroo waliin walqunnamsiisuun jijjiirramaa fi badhaadhina Afrikaa dhugoomsuf osoo hin taane; qabeenya Albuudaa, Bishaan, Lafa qonnaa, Boba’aa fi qabeenyawwan uummamaa kanneen biroo saamuuf itti yaadamee kan hojiitti galame ture.
Fedhiin isaanii kanaan qofa kan hin daangeffamne yoo ta’u; Aadaalee, Duudhaa, Afaani, xiin-sammuu uummataa cabsuu, fi Seenaa Afrikaa dhabamsiisuun aadaa isaanii lafa qabsiisuf yaadanii hojjechuun isaanis mul’ateera. Gocha garbummaa isaanii kanas biyyoota Afrikaa gita bittaan qabamanii turan irratti qabatamaan lafa buusanii jiru.

Itoophiyaanotni garuu yeroo sanas abshaalotaa fi qaroowwan turan. Shira weerartootni kunneen “Ilaalcha Adunyaawaa dhugoomsina” jedhuun birmadummaa biyyootaa sarbuun wareera gaggeessuuf yaadan hubachuun gamtaan loluun ofirraa qolachuu danda’an.

Dhalootni ammaa dhalootni keenya kunis kana hubachuun abshaala ta’uu qaba. Gocha fi shira,akkasumas, waraana xiinsammuu diinota seenaa keessatti nu qoran kanneen fagoo jiranii fi ergamtoota isaanii kanneen keessoo keenyaa jiraniin nurratti aggaamamu qolachuun ajandaawwan Badhaadhina Itoophiyaa, Nageenya fi ol’aantummaa Itoophiyaa lafa qabsiisan duuka akka kanniisatti wal-utubuun biyya waloo ijaaruuf wal-tumsuutu nurraa eeggama. Nuti osoo jirruu biyya abaabayyuu fi abbootiin keenya osoo hin baranne ijaaranii nutti dabarsan diinotni keenyaa fi ergamtootni diinaa keessoo keenya jiran diiguu hin danda’an.

Garaagarummaan yaadama siyaasaa kan ture; kan jiru; fuulduratti waanuma mul’achuu danda’uu dha. Biyya teenya Itoophiyaarratti garuu garaagarummaan qabaannu hin jiraatu. Itoophiyaan Eenyummaa waloo keenyati!. Harmee too Itoophiyaa, kan birmadummaa keetitti bu’e haa barbadaa’u! kan jedhe eenyu ture?

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

A leader who overcomes the pressure that was put on Ethiopia and found a solution through diplomacy!!
#Fast_Growing_Ethiopia 🇪🇹
@AbiyAhmedAli 💪
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
#ቀይባህር_ህልውናችን

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

The Home-grown Economic reform increased dairy, meats, poultry, fish and honey productivity.
@AbiyAhmedAli 💪
#Fast_Growing_Ethiopia 🇪🇹 @FAOEastAfrica @FAOEthiopia @WFP @WFPUSA @WFP_Europe @WorldFoodPrize @WFP_Europe @WorldFoodPrize @FAO @FAOstatistics

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Despite the challenge Ethiopia today is among the fastest growing economies in the world.
#Fast_Growing_Economy
#No_More_Landlocked
@AbiyAhmedAli 💪
#No_More_Landblocked 🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያ አዲስ ገፅታ!!
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
#ዐብይ_አህመድ
#Fast_Growing_Ethiopia
#ቀይባህር_ህልዉናችን

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሁለንተናዊ ብልፅግናችን አንዱ ማሳያ 👇
የአድዋ ድል መታሰቢያ 🇪🇹 የሁላችን ታሪክ 🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጀግናው ሽልማቱን ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በጣልያን ተወስዳብን የነበችውን የመጀመሪያዋን አውሮፕላን ‘ፀሐይ’ ንም ጭምር ነው ይዞልን የሚመጣው።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በስንዴ ምርት እየታየ ያለው ለውጥ ከምግብ ያለፍ አውንታዊ ጥቅም እያስገኘልን ነው። በብዙ ችግር ውስጥ ሆነንም እየታየ ያለው ውጤታማ የስንዴ ምርት አብዮት በአለም አቀፍ ደረጃም ጭምር በርከት ያሉ ጥቅሞችን እያስገኘልን ይገኛል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከሀገር አቀፍ ወደ አለም እዉቅና 👏
ሀገር ሻጭ ባንዳ በስንዴዉ ፕሮጀክት ሲያላግጥ ሲያንጋጥጥ #FAO ግን መሪያችንን በክብር በአለም ደረጃ ሸልሞታል!

#ፅንፈኝነት_ይውደም
#አንድነትUnity

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel