#ህዝብ_መጋቢው_መንግሥት 👌 #ብልፅግና 👌
በኦሮሚያ ክልል በአሁኑ ወቅት 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ እንዳሉት፥ በጀት ዓመቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ትምህርት 11 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በትምህር ገበታ ላይ ይገኛሉ፡፡
ተማሪዎች በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድ በሕብረተሰቡ ተሳተፎ እና በመንንግስት ድጎማ የሚቀርበው የትምህር ቤት ምገባ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡
በአሁኑ ወቅትም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች 5 ነጥብ 3 ሚሊየን ተማሪዎች የት/ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሆኑ አቶ ሃሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስረድተዋል፡፡
የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በአርብቶ አደር አካባቢዎች ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል እና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ሰላማችንን በመጠበቅና ጽንፈኝነትን በጋራ በመታገል የሀገራችንን ብልጽግና እውን እናድርግ!
ሰላምን እውን የማድረግም ሆነ ሰላምን የማጣት ወሳኙ እኛው ራሳችን ነን። ዛሬ በእጃችን ያለው ሰላም ነገም በአስተማማኝ ደረጃ ሊቀጥል የሚችለው ሁሉም ለሰላም ተግቶ ሲሰራና ሰላምን የሚያፈርሱ ነገሮችን ያለ ምህረት ሲታገል ብቻ ነው፡፡
ሰላምን ከሚያደፈርሱ ነገሮች አንዱ ደግም ጽንፈኝነት ነው። ጽንፈኝነት ከመደመር ሳንካዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ሲሆን የራስን ፍላጎት በሌሎች ላይ የመጫን ወይም የማስገደድ አባዜ የተጠናወተው ጫፍ የሚይዝ የኋላቀርነት መገለጫ ነው፡፡
መነሻው በተናጠል ፍላጎቷቶች ላይ የሚመሰረትና የሌሎችን መስተጋብሮች ለመቀበል የሚቸገር ነው። ኢትዮጵያ ደግም ብዝሃ ሀሳብ፣ ብዝሃ ባህል፣ ብዝሃ ቋንቋና ብዝሃ ሃይማኖት ባለቤት ናት።
በመሆኑም የአዲሱ የብልፅግና እሳቤ መሰረት የሚያደርገው የመደመር ትውልድ አስተሳሰብ ትርክቱ የትስስር ትርክት፣ የአብሮነት ትስስር ነው፤ በማናቸውም የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ የሀገር ደህንነትና ውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች እኔም፣ እኛም፣ ባጠቃላይ ሁላችንም በጋራ መጠቀም አለብን ማለት መቻል አለብን።
በመሆኑም ከጽንፈኝነት በመራቅ፣ ሰላማችንን መጠበቅ እና መንከባከብ አማራጭ የሌለው የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን ሰላም ከሆነች የምንናፍቀውን ብልጽግና በአጭር ጊዜ እውን ከማድረግ የሚከለክለን ምድራዊ ሀይል አይኖርም። ሰላማችንን በመጠበቅና ጽንፈኝነትን በጋራ በመከላከል የሀገራችንን ብልጽግና እውን እናድርግ!
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ለቆሞ ቀሮች
ያማል ቅኔው
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ፅንፈኛ ሃይሉ በመከላከያ ሠራዊቱና በሚሊሺያው ጥምረት በቁጥጥር ስር እየዋለ ነው።
የክፍለ ጦሩ የ1ኛ ሬጅመንት እና አድማ ብተና አባላት በጋራ በመቀናጀት በጃማ ደጎሎ ቀይ አፈር የሚባል ቦታ ከፅንፈኛው ቡድን ጋር በተፈጠረ ግጭት በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል ።
በዚህም የቡድኑን ዋና አክቲቪስት አብዱ ሰዒድን ጨምሮ የጠላት 17 ሰው የተማረክ ሲሆን 01 ክላሸ = 11 ቁመህ ጠብቀኝ 02 አርባ ጎራሸ 02 ሰሜን ኦፍ መሳሪያ መማረክ ተችሏል።
በአጠቃላይ በቀጠናው ችግሮችን ለመቅረፍና ሠላምን ለመመለስ እየተሄደ ባለው እንቅስቃሴ ውጤት ማምጣት እየተቻለ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራር ተናግረዋል።
በሌላ ኬላ ፍተሻና ቁጥጥርን በማጠናከር ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውርን መቆጣጠር እንደተቻለ በእሽታይሽ የሚገኘው ክፍለ ጦር አሥታውቋል። ከጋይንት ወደ ሰሜን ወሎ በመግባት ላይ የነበረ 81 ሽጉጥ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ለማወቅ ተችሏል።
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
በጀኔራል አበባው ታደሠ የተመራውና በሳዑዲ ዓረቢያ ተዘጋጅቶ ለእይታ በቀረበው ዓለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት (WDS) ተሳታፊ የነበረው ልዑክ ቆይታውን አጠናቆ ተመልሷል።
በሳዑዲ ዓረቢያ መከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ አታሼ አስተዳደር አስተባባሪነት እ.አ.አ በ04.02.2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ105 ባላይ ለሚሆኑ አገራት ልዑካን ቡድን እና ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ የቆየው አለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት ተጠናቋል።
የዓለም አቀፍ መከላከያ ትዕይንት (WDS) አጀንዳዉ ዓለም አቀፍ በመሆኑ ከስድስት ወር በፊት ጀምሮ ሠፊ ዝግጅት ሲደረግበት እንደቆየና የፕሮቶኮል ሁኔታን በተመለከተ በሳዑዲ ዓረቢያ ለሚገኙ የወታደራዊ አታሼ ማህበር አባለት የመድረክ ገለፃ ሲሰጥ መቆየቱም ተገልጿል።
በትዕይንቱ ለመካፈል በጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ የተመራው ልዑካን ቡድን ሪያድ ንጉስ ካሊድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በሳዑዲ ዓረቢያ መከላከያ ጄኔራል መኮንኖች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎለታል።
የዝግጅቱን በይፋ መከፈት ተከትሎ በጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አባበዉ ታደሰ የተመራ አራት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ልዑካን ቡድን መክፈቻዉን ጨምሮ ትዕይንቱን በመታደም ቆይታውን አጠናቆ ተመልሷል ።
ትዕይንቱ በሁለት ቀናት ቆይታው በተዋሰነ መልኩ የነገው የዓለም ሀገራት መከላከያ ዝግጅት እና ትጥቅ ምን ሊመስል እንደሚችል ያመላከተ ሥለመሆኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ልዑካን ቡድን ግንዘቤ ይዟል ።
ቀጣይ አለም ላይ ሊኖሩ የሚችሉ የመከላከያ ትጥቆች ከነፍስ ወከፍ ትጥቅ ጀምሮ፣ የግንኙነት መሳሪያና ሁሉ አቀፍ የተናጠል እና የቡድን ትጥቆች ከዘመኑ ጋር አብረው የሚራመዱ ስለመሆናቸው ትዕይንቱ አመላካች መሆኑም ተገልጿል፣
ሳዑዲ ዓረቢያ በ2030 ተግባራዊ ለማድረግ ከያዘችው ራዕይ አንጸር 50% የመከላከያ ምርቷን በአገር ዉስጥ የማምረት ውጥኗን የማሳካት ጉዞዋ ተስፋ ሰጪ መሆኑ የተመላከተበት ትዕይንት መሆኑ ከልዑካን ቡድኑ የደረሠን መረጃ ያመለክታል።
ጄኔራል አበባው ታደሠ እና ልዑካናቸው በሳውዲ አረቢያ ቆይታቸው የሳውዲ የካዴት ትምህርት ቤትን ፣የወታደራዊ አልባሳት አምራች ኩባንያን ፣ የኢንዱስትሪ የምርምር ማዕከላትን የተመለከቱ ሲሆን ድርጅቶች ሁኔታዎች ከተመቻቹ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ልዑካን ቡድኑ የሳውዲ ዓረቢያ አለም አቀፍ የመከላከያ ትዕይንት ጉብኝቱን አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሱ በፊት በሁለቱ አገራት ተወካዮች አማካኝነት ልዩ ስጦታ መለዋወጣቸውም ተገልጿል።
#እንደምን_አደርሽ_አዲስአበባዬ 👌👌👌
#ውብ_አዲስአበባ 👌👌👌
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ዉይይቶች ቁልፍ ሚና አላቸዉ!!
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ነገ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ይሰጣሉ 🙏
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ከ2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ያዕቆብ ወልደሰማያት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በስብሰባውም በምክር ቤቱ አሠራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 መሠረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባለት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች በቃል ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡
/channel/ProsperityFirst
አዳም አባታችን እና ሔዋን እናታችን አትክልት ተመጋቢዎች ነበሩ ልበል? ስጋ ስንበላ እኮ ነው ፊጋ የሚያደርገን። ሲመስለኝ ሲመስለኝ እኛማ የተረጋጋን ፍጡራን መሆናችን ነው የሚገባኝ። ግን አሁን ላይ ፊጋ እየሆንን ነው። ስለዚህ አትክልት መመገብን ማበረታታት አለብን። አትክልት እኮ የሰላም አምባሳደር ነች። ፀብ የላት፣ ወጭ የላት፣ ጥቅሟ ደግሞ WOW...
/channel/ProsperityFirst
#ላትጨርሱ_አትጀምሩ!
“ስለ አንተ ትክክለኛ ማንነት የሚመሰክረው አደርገዋለሁ በማለት የምታወራው ነገር ሳይሆን በእርግጥም የምታደርገው ነገር ነው” - Carl Gustav Jung
“የማትጀምረውን ነገር አትጨርሰውም፣ ለመጨረስ ራስህን ሙሉ ለሙሉ ያልሰጠህለትን ነገር ደግሞ ቀድሞውኑ መጀመር የለብህም” - Gary Ryan Blair
በሃገሩ በከፊል በግብርና ስራ ይተዳደር የነበረው ጆን (John Stephen Akhwari) በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1968 ዓ/ም በሜክሲኮ ከተማ ውስጥ በተደረገው የማራቶን ውድድር ለመሳተፍ በሄደበት ጊዜ በውድድሩ መካከል ላይ በደረሰበት ችግር ምክንያት በመውደቁ ጉልበቱንና ትከሻው ላይ ጉዳት ይደርስበታል፡፡ በዚህ ጉዳት ውስጥ ሆኖ እንኳን የጀመረውን ሳይጨርስ ላለማቆም የነበረው ቁርጠኝነት እስካሁን ድረስ በዓለም ዙሪያ በምሳሌነት ይነገርለታል፡፡
በታዋቂው ኢትዮጲያዊ ሯጭ በማሞ ወልዴ አሸናፊነት በተጠናቀቀው በዚህ የማራቶን ውድድር ወቅት በወቅቱ የ26 ዓመት እድሜ የነበረው ጆን በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በድንገት ቢወድቅም ከወደቀበት ተነስቶ እያነከሰ ውድድሩን ለማጠናቀቅ በቃ፡፡ ይህ ሁኔታ ከተከሰተ ከ52 ዓመታት በኋላ በተደረገለት ቃለ-መጠይቅ ላይ ልምምዱን በማስታወስ ሲገልጽ፣ “የ42 ኪሎሜትሩን ሩጫ ጀምሬ 30 ኪሎሜትር እንደሮጥኩኝ ነበር እጅግ በጣም የህመም ስሜት የተሰማኝ፡፡ እኔ ግን ውድድሩን ማቆም የሚባለውን ነገር በፍጹም አላሰብኩም” ይላል፡፡ በደረሰበት ድንገተኛ ህመም ወድቆ የነበረው ጆን፣ በዚህ ጉዳትና ስቃይ ውስጥ ሆኖ ነበር ከወደቀበት ተነስቶ እያነከሰ፣ምንም እንኳን መጨረሻ ቢወጣም ውድድሩን የጨረሰው፡፡
ይህ አንደኛ ስለወጣ ሳይሆን የጀመረውን ሳይጨርስ ባለማቆሙ ምክንያት በዓለም ዙሪያ እስካሁን ብዙዎችን በማነሳሳት የሚታወቀው ሰው በየጊዜው የሚጠቀስለት ታዋቂው ንግግሩ እንዲህ የሚል ነው፡- “ሃገሬ የላከኝ የሩጫ ውድድሩን እንድጀምር ሳይሆን እንድጨርስ ነው”፡፡
ጆን “መጨረሻ የወጣው አሸናፊ” በመባል ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን ሩጫውን በተዘጋጀበትና በፈለገበት መልኩ ባያሸንፍም በነበረው ጀምሮ የመጨረስ ቁርጠኝነት አንጻር ግን ጨርሶታል፡፡ በወቅቱ ከቁጥጥሩ ውጪ ከነበረው ሁኔታ በላይ በመነሳት ሩጫውን ጨርሷል፡፡ ሩጫውን አላቋረጠም፣ ሩጫውን የጨረሰው ደግሞ በሃፍረት አንገቱን በመድፋት አልነበረም፡፡ በወቅቱ የነበረውን አቅም በሙሉ በመጠቀም ጥጉ ድረስ በመሮጡ በኩራት ቀና ብሎ ነው፡፡
ጆን ያንን ሩጫ እስከ ጥጉ ከሮጠ በኋላ መጨረሻ ሆኖ በማጠናቀቁ ምንም አይነት የደረጃ ሽልማት ባያገኝም ከዚያ በኋላ ግን የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት ሆኗል፡፡ በአለም ዝነኛና ለብዙ ሰዎች ጀምሮ የመጨረስን ምስጢር ያስተዋወቀ ሰው ሆኖ ይነገርለታል፡፡ በአለም ዙሪያ ይህንን መሰል ተቀባይነት ያገኘው የጀመረውን ሩጫ ሳይጨርስ ለማቆም አሻፈረኝ በማለቱ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች አንድን ተገባር ጀመሩም አልጀመሩም፣ ጀምረው ጨረሱም አልጨረሱም፣ ሲጨርሱ ደግሞ በጥራት ይለቅ አይለቅ ግድም አይሰጣቸው፡፡ ከዚያም ይህንን ሁኔታ በቸልተኝነት ካለፉት በኋላ ልክ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ መንገዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ለእነሱ ስህተት ማለት አንድን የተጀመረ ነገር መነካካትና ማበላሸት ብቻ ነው፡፡ አንድን ነገር አለመጀመር፣ የተጀመረን ነገር አለመጨረስና ሲጨርሱም አልኮስኩሶ መጨረስ በራሱ ትልቅ ስህተት መሆኑን ይዘነጉታል፡፡ ከዚያም የተወሰኑ ዓመታትን ካባከኑ በኋላ በሕይወታቸው ለምን እንደማይሳካላቸው በማሰብ አእምሯቸው ሊመለስ በማይችል ጥያቄ ሲጦዝ ይኖራል፡፡
የጀመራችሁትን ነገር ጥጉ ድረስ ሳታደርሱት የማቋረጥ ችግር ካለባችሁ ጊዜያችሁን በከንቱ ከማቃጠላችሁ በፊት ነቃ!!!
“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ (መጽሐፉን በየመደብሩ ያገኙታል)
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ደስታ ላይ ነን። እንደዚህ 😁 ላይ ነን። ትልቅ ፈገግታ ላይ። ፈገግታ ደግሞ የነገ ብሩህነት መነሻም መዳረሻም ነው።
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
#ኢትዮጵያዊነት 🇪🇹
Vs
#ጥሬ_ስጋ 👌
https://twitter.com/ProsperityKera
#ባህሎቻችንን_ማወቅ_ስብራቶቻችንን_መጠገን
በጊዮን ሆቴል
https://twitter.com/ProsperityKera
“እንደዚህ የምሆነው ለምንድን ነው?” ለምትሉ!
ከራሳችሁ ጋር ባላችሁ የየእለት ልማድና ልምምድም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት አንድን ነገር ካሰባችሁ ወይም ካደረጋችሁ በኋላ፣ “ለምን እንደዚህ አስባለሁ … እሆናለሁ … እናገራለሁ … አደርጋለሁ …” የማለት ሁኔታ የየእለት ሁኔታችሁ ከሆነ ችግሩ ከስር መሰረቱ ለመንቀል ትክክለኛውን ሂደት መከተል አስፈላጊ ነው፡፡
በውልደት ያገኘነው የፈጥሮ ዝንሌያችን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ዛሬ የምናሳያቸው ሁኔታዎች የሁለት ነገሮች ድምር ናቸው
1. የአስተዳደጋችን ሁኔታ
ይህ ሁኔታ የሚወክለው ለራሳችን፣ በራሳችን መወሰን በማንችልባቸው አመታቶችን ወቅት ወላጅ (አሳዳጊዎቻችን) ያደረጉብንን ወይም ያላደረጉልንን ነገር ነው፡፡
2. በሕይወት ጎዳና ላይ ያጋጠሙን ሁኔታዎች
ይህ ሁኔታ የሚወክለው እያደግን ስንመጣና በራሳችን ውሳኔ መንቀሳቀስ ስንጀምር ከሰዎች እና ከኑሮ ያለን ንክኪና ልውውጥ ያሳደረብንን ተጽእኖ ነው፡፡
እነዚህ ሁለት እውነታዎች ዛሬ ባለን ምልከታ ላይ ጥልቅ የሆነ ተሳትፎ አላቸው፡፡ ለሁኔታዎች የምንሰጠውን ምላሽ፣ የምንፈራውን ነገር፣ በፍቅር ግንኙነት ላይ ያለንን አመለካከት፣ ስጋቶቻችንን፣ ጀምሮ ያመጨረስ ትግላችንን፣ የባህሪያችንን መለዋወጥ፣ የማንፈልገው ስሜት የመመላለሱን፣ ሌሎች በቀላሉ የሚያልጉት ሁኔታ እኛን የማመሳቀሉ . . . እና የመሳሰሉትን፣ “ለምንድን ነው ሁል ጊዜ እንደዚህ የምሆነው?” የምንላቸው ነገሮች ይወስናሉ፡፡
በራሳችን ወደ ኋላ መለስ በማለት፣ ካልቻልን ደግሞ የባለሞያን እገዛ በማግኘት ከስር መሰረቱ በመቆፈር እስከምናስተካክለው ድረስ የዛሬውንና የወደፊታችንን የማዛባት አቅሙ ቀላል አይደለም፡፡
ሁኔታዎች ከልክ አልፈው፣ እድያችን ተበልቶና ለማስተካከል ብንሞክርም ሆነ ባንሞክር ምንም ለውጥ እንደሌለው የምናስብበት የተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ ከመድረሳችን በፊት እናርመው
በዚህ ጉዳይ ላይ የሕይወታችሁን ልምምድ ከውልደት ጀምሮ ቆፍሮ የሚያሳያችሁ መጽሐፍ ከፈለጋችሁ፣ በዚህ ወር ያወጣሁትን፣ “ራስን ማወቅና መምራት” የተሰኘው መጽሐፍ ጥሩ ጅማሬ ይሰጣችኋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
እንኳን ደስ አለሽ እህትአለም
ወ/ሮ ሰምሃል ገ/መድህን የቂርቆስ ብልፅግና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ወ/ሮ ሰምሃል ገ/መድህን ከወረዳ ባለሙያነት እስከ ወረዳ አስተባባሪነት ድረስ ፓርቲ እና ሃገራቸውን በቅንነት፣ በታታሪነት እና በውጤታማነት ያገለገሉ በአባላትና በመላው መዋቅር፣ በስራ ባልደረቦቻቸውም ጭምር የተወደዱ ጀግና እንስት አመራራችን ናቸው።
አሁን የተሰጣቸውን ኃላፊነትም በጥሩ ብቃትና ተነሳሽነት እንደሚወጡት እምነታችን የፀና ነው።
መልካም የስራ ጊዜ ሰሙ
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
#አርበኝነት
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
"የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሁለተኛው የአርበኝነት ዘመን መጀምር ማብሰሪያ ፣የኢትዮጵያዊያን የአንድነት ምልክት ነው።"
የጥቁሮች ነፃነት በነጮች ተገሎ በጀርመን ከተማ ተመክሮ ተዘክሮ ሀሳብ ተውጠንጥኖ ሁሉም የአውሮፓ ሀገር ያላንዳች መጋጨት አፍሪቃን እንደ ቅርጫት ስጋ ተከፋፈለ።
ይህን መሰል የጭቆና መልህቅ የተጣለው ቀደም ብሎ ቢሆንም በጉባኤ ነፃነትን ለመግፈፍ የተመከረው በበርሊን ነበር።
በጠቅላይ ሚኒስቴር ፍራንሲስኮ ክሪስፒ ትመራ የነበረችው ጣሊያን ኢትዮጵያን በሀይል ለማንበርከክ ተወሰነላት።
ድፍረቱ እና ኃይሉ የመጣው ጣሊያኖች ቀደም ብለው ኢትዮጵያዊያንን በአጭበርባሪ መልዕክተኛቸው ኮንት ፒውትሮ አንቶኔሊ በኩል ውጫሌ ላይ የተጭበረበረ ሰነድ ካስፈረሙ በኋላ ነው።
ክስተቱ ብዙ የሚያነጋግር፣ብዙ የተባለለት ነበረ። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ሀያል የጥቁር ምድር ልጆቿ በልዋላዊነት ጉዳይ የብረት መጋረጃዎች ናቸው እና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ፣ከደቡብ እስከ ሰሜን በኮራ እና በፍፁም ጀግንነት ተመሙ።
ጣሊያን ውሃ ዉሃ አለ፣ሀበሻ ለአንድነቱ ተማማለ፣አፍሪቃ ቆይቶ ነጭ ፍጡር መሆኑን አምኖ ለነፃነቱ ተነሳሳ።
የሶሎዳ
የእባላጌ
የአድዋ ተራሮች ለአርበኞቻቸው አዳሉ።ሞት አርግዞ የመጣው ጣሊያን በሞት ተቀበረ።
አለም ለኢትዮጵያ በሩን ከፈተ፣መወዳጀት ፈለገ።
ጣሊያናዊያን በአደባባይ ወተው የኢትዮጵያ መሪዎችን ዘላለም ያኑራችሁ አሉ።ክርስፒን አስወገዱ። ታሪኩ ብዙ ነው።
ይህ ታሪክ በዚህ የመደመር ትውልድ በሁለተኛው የአርበኝነት ዘመን በሀገሪቱ መዲና በመሀል አራዳ አንድም ሳይቀር እንደሚያገሳ አንበሳ በትልቅ ግርማ ሞገስ ታንፆ ለጠላትም ለወዳጅም በሚያስቀና አኳኋን ቁጭ አለ።
ጀግና የማይነጥፍባት ታላቅ ምድር 🇪🇹ኢትዮጵያ
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
Читать полностью…CONGRATULAT ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ 🙏 የጀግንነት፣ የትጋት፣ የውጤታማነት፣ የብልፅግና፣... ምልክት ኖት
"የዛሬው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ውሎ ለከተማችን ነዋሪዎች እና ለከተማ አስተዳደራችን ምርጥ ቀን ነበረ ተብሎ መውሰድ ይቻላል። ህዝባችን ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመሆን ያሳኩት የአድዋ ድል መታሰቢያ እና ሌሎችም ፕሮጀክቶች በአደባባይ በህዝብ እንደራሴዎችና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ትልቅ ክብርና አድናቆት የተሰጣቸው ቀን ነበረና።
ከሁሉም በላይ ደግሞ እንኳን ደስ አሎት ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ እንደ ሁሌውም ዛሬም እርስዎ የጀግንነት፣ የትጋት፣ የውጤታማነት፣ የብልፅግና፣ ... ምልክት መሆንዎት ሲወሳ ነበረ የዋለው። ይህም የልፋቶትና ምንም ያልተጋነነቷ ያልተጨመረበት ምስክርነት ነውና 👏👏👏👏
#የሕይወት_ዘይቤ_ምርጫ
“የወደፊት ሕይወትህ ምስጢር በየእለቱ በምትለማመዳቸው ልማዶችህ ውስጥ ተደብቀው ይገኛሉ” – Mike Murdock
የየዕለት የሕይወት ዘይቤ ምርጫ ለቀሩት ዋና ዋና ምርጫዎችህ መጋቢና ገባር ስለሆነ በሚገባ ልታስብበት ይገባል፡፡ የየዕለት ውሳኔዎችህ የሕይወትህን ዋና ዋና ምርጫዎች ወይ ያፈርሳሉ ወይም ደግሞ ይገነባሉ፡፡
ለየዕለቱ ገጠመኞች የምንሰጣቸው ምላሾችና ከሰዎችና እንዲሁም ከሁኔታዎች ጋር ያሉን አቀራረቦች ለዋና ዓላማዎቻችንና ምርጫዎችን እንደገባር ወንዞች ናቸው፡፡ በየእለቱ ወደ እኛ የመጣውን ነገር መቆጣጠር ባንችልም ወደየት አቅጣጫ እንደምንወስደው ግን መምረጥና መወሰን እንችላለን፡፡
ወስነን ለመከተል ለመረጥነው የሕይወት አቅጣጫ በየእለቱ መዋጮ የሚያደርጉትን ሁኔታዎች በተለያዩ መልኩ ከፋፍለን ማየት እንችላለን፡፡ ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸው ሃሳቦች አንዱ የእይታ አቅጣጫ ሊሆን ይችላል፡፡
1. ለሰዎች የምትሰጠው ምላሽ
በየእለቱ ሰዎች በተለያየ መልኩ ወደአንተ ይቀርባሉ፡፡ የተለያዩ አመለካከቶችን ያንጸባርቃሉ፡፡ በየእለቱ ሰዎች የተለያዩ ስሜቶችን የሚያነሳሱ ሁኔታዎችን ይዘውልህ ወይም ይዘውብህ ይመጣሉ፡፡ እነዚህን የሰዎች ሁኔታ በሚገባ የመያዝን ሁኔታ አስበህበት ትክክለኛውን ምርጫ ካልመረጥክ በአጠቃላይ የሕይወት አቅጣጫህ ላይ ተጽእኖ ማስከተሉ አይቀርም፡፡
2. ለአስቸጋሪ ገጠመኞች የምትሰጠው ምላሽ
በየእለቱ የማትጠብቃቸው ገጠመኞች ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡ አንዳንዶቹ መልካም ገጠመኞች ሲሆኑ፣ ሌሎቸ ደግሞ ደስ የማያሰኙ ገጠመኞች ናቸው፡፡ ለእነዚህ ገጠመኞች የምትሰጠውን ምላሽ በሚገባ አስበህ ትክክለኛ ውሳኔ በመወሰን ካልተራመድክ በሕይወትህ አቅጣጫ ላይ ጫና ያደርጋል፡፡ “አንድ እድል ወይም ችግር በሰው ውስጥ አዲስ ነገር አይጨምርም፣ ሰው ውስጥ ያለውን ነው የሚያወጣው” ይባላል፡፡ አስታውስ፣ ለየቀን ገጠመኞች የሚኖርህን ምላሽ የመምረጥ መብት አለህ፤ ምርጫህ ደግሞ ወሳኝ ነው፡፡
3. ለስሜቶችህ የምትሰጠው ምላሽ
ከስሜት ውጪ ውለህም ሆነ አድረህ አታውቅም፡፡ አሁን እንኳን ይህንን ጽሑፍ እያነበብክ ባለበት ሰዓት አንድ ስሜት በውስጥህ እንዳለ እሙን ነው፡፡ ይህ ስሜት ጥሩ ወይም መጥፎ “ሙድ” ውስጥ ይከትሃል፡፡ ይህ ስሜት እንዲሁ አልመጣም፡፡ በዚህ መልኩ በእለቱ የስሜት ውጣ ውረድና ተጋድሎ አለብህ፡፡ ለእነዚህ ስህተቶችህ የምትሰጣቸው ምላሾች የወደፊትህን ይወስናሉ፡፡
4. ለስኬት የምትሰጠው ምላሽ
አንዳንድ ሰዎች ስኬትን እንደ እድል ይቆጥሩታል፡፡ ሌሎች ደግሞ ስኬትን መልካም ባህሪንና ጠንክሮ መስራትን ተከትሎ የሚመጣ ነገር እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ይህንንም አመንክ ያንን፣ በሕይወትህ ነገሮች ሲሰምሩና ሲሳኩ የምትሰጠው ምላሽ ለወደፊትህ መዋጮ አለው፡፡ በጦርነቱና በፍልሚያው መካከል እንዳለው ልዩነት እንደማለት ነው፡፡ ጦርነቱ የዋናው ዓላማህ ምሳሌ ነው፤ ፍልሚያው ደግሞ በየእለቱ የምትኖረው ኑሮና ትግል፡፡ አንድ ቀን ስኬት ስላገኘህ (ፍልሚያን ስላሸነፍክ) ዋናው ዓላማህ የደረስክ (ጦርነቱን በድል ያጠናቀክ) መስሎህና ተኩራርተህ ታቆም ይሆን?
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ተያዘ
ተጠርጣሪው ከሸኔ የሽብር ቡድን ጋር በመመሳጠር እና በመገናኘት የጥፋት ተልዕኮ ለመፈፀም መነሻውን ከአማራ ክልል ወልዲያ ከተማ በማድረግ በግለሰብ እጅ የማይያዙ ሕገ-ወጥ የቡድን የጦር መሣሪያዎች ሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3 ኢት 10492 በሆነ ፒክ-አፕ መኪና ጭኖ ወደ ኦሮሚያ ክልል ኤጀሬ አካባቢ ለሽብር ቡድኑ ሊያደርስላቸው ሲንቀሳቀስ ልዩ ቦታው አሸዋ ሜዳ በተባለ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር የጦር መሣሪያዋቹን (አንድ RBG Launcher፣ አንድ ብሬን፣ አምስት የአጭር ርቀት መገናኛ ሬድዮ ከአራት ቻርጀሮች ጋር) ከነ-ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራበት እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።
እነዚህ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎች በሽብር ቡድኑ እጅ ቢገቡ ኖሮ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ይችሉ እንደነበር ፖሊስ ጠቁሟል።
ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመቆጣጠር በተለያዩ የበሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የፍተሻ ጣቢያዎች ላይ የሚደረገው ፍተሻ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፖሊስ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተገቢውን ቅንጅት በማድረግ በየትኛውም ደረጃ የሚወጠኑ የሽብር ተግባራትን ለመቆጣጠር የዜግነት ድርሻውን ይወጣ ዘንድ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
/channel/ProsperityFirst
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ #UAE በኢትዮጵያ 2.4 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ልታደርግ ነዉ። #እነ_እንቶኔ_አይዟችሁ 😜
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ኦማር ሁሴን አገሪቱ በኢትዮጵያ ከ2.4 ቢሊየን ዶላር የበለጠ ገንዘብ ኢንቨስትመንት ልታደርግ ነዉ ብለዋል፡፡
አምባሳደሩ አረብ ኤምሬትስ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ እያደረገች ያለቻቸዉን የተለያዩ ኢንቨስትመንቶች አንስተዉ ፤ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገትን አጠናክሮ ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ኦማር ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያላትን አቅም እና የአረብ አገራት የመጠቀም አቅምን በማንሳት አገሪቱ ተመራጭ የገበያ መዳረሻ ናት ብለዋል፡፡
በዱባይ በተካሄደዉ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለዉጥ የኮፕ28 ስብሰባ ላይ አረብ ኤምሬትስ ኢትዮጵያን በኢነርጂዉ ዘርፍ ለመደገፍ የ6መቶ ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት እንደምታደርግ ቃል ገብታ ነበር፡፡
በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአረብ ኤምሬትሱ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ ጋር በአየር ንብረት ለዉጥ ምክንያት የተጋረጡ ችግሮችን ለመፍታት የተባበረ ድጋፍ ያስፈልጋል ሲሉ መነጋገራቸዉ ይታወሳል፡፡
/channel/ProsperityFirst
ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ለሀገረ መንግስት ግንባታ ከፍተኛ ፋይዳ ኣለዉ።
ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነት እየተጠናከረ ሊሄድ የሚችለው ደግሞ የብሔር ማንነት እና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸዉን ጠብቀው ሲጓዙ ነዉ።
የብሔር፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ.. ብዝሃነት በገነባት ኢትዮጵያ ሚዛናዊነትን ያረጋገጠ፣ ከፅንፈኛ አስተሳሰብ እና ተግባር የተጠበቀ የፖለቲካ እሳቤን ባህል ማድረግ ኢትዮጵያን ለማፅናት መሠረት ነዉ።
ፅንፈኛ አስተሳሰብ እና ድርጊት ሚዛናዊነትን በማዛባት፣ አካታችነትን በማሳሳት ወደ አግላይነት ያሸጋግራል።
አግላይነት ወደ ጠቅላይነት በማምራት ብዝሃነትን ለመቀበል፣ ለማክበር እና ለማስተናገድ ተግዳሮት ይሆናል። በዚህም መነሻ ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባቱን ዕድል ይፈትነዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የብሔር ማንነት እና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸዉን ጠብቀዉ እንዲራመዱ በማድረግ በሂደቱም ጠንካራ አገረ መንግስት መገንባትን መሠረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የምትመች፣ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ያበበባት አገር እንድትሆን ብልጽግና ተግቶ ይሠራል።
ሚዛናዊ የፖለቲካ እይታ መርህ ሁሉንም ብዝሃነቶች የማስተናገድ የመሀል የፖለቲካ አስተሳሰብና ተግባር ነዉ።
ፅንፈኝነት ኢትዮጵያን ከማዳከም ያለፈ ዉጤት እንደማያስገኝ ከዚህ በፊት የፈተኑንን ችግሮች ዞር ብሎ በማየት መገንዘብ እንችላለን። የዘርፈ ብዙ ፀጋዎች ሀገር ኢትዮጵያ ሚዛናዊ የፖለቲካ እይታ መርህን እና ሙሉዕ እይታን በማጠናከር የለዉጥ ጉዞዋን እንድታፋጥን የዜግነት አደራ አለብንና የየበኩላችንን እናበርክት።
/channel/ProsperityFirst
የዚህ ትውልድ ዓድዋ የኢትዮጵያን ሰላምና ብልፅግናን እውን ማድረግ ነው!
የዚህ ትዉልድ ትልቁ ዓድዋ የስራ ባህላችንን በመሰረታዊነት በማሻሻል ድህነት የሚባል አዋራጅ ጠላታችንን ድል በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እዉን ማድረግ መቻል ነዉ!
በዓድዋ ላይ በክብር ያልወደቀ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ የዓድዋ ድል የህብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ ዘላለማዊ ድል የሆነው በአፈጻጸም ብቃት የጠነከረ፣ በተሳትፎ ስፋት የተዋቀረ፣ በዓላማ ጽናት የተቀመረ ትልቅ ድል ነው፡፡
ከዓድዋ ጀግኖች አሸናፊነታቸውን ብቻም ሳይሆን ለማሸነፍ ያበቋቸውን ጉዳዮች ከመረመርናቸው ለዛሬ ማንነታችን የተሰነቁ እኛም አጉልተን ልንጠቀምባቸው የሚገቡ ትምህርቶችን እናገኝባቸዋለን፡፡
ያሁኑ ትውልድም ታዲያ በዓድዋ መንፈስ ሆነን፤ በድሉ ብስራት ጠንክረን፣ ኢትዮጵያ የምትጠብቅብንን ደማቅ ታሪክ ዳግም መስራት መቻል አለብን፡፡ ብዙ ያልሰራነው ፣ ገና ያልፈጸምነው ሥራ አለብን፡፡ አየሩን በሚሞሉት አሉታዊ እሳቤዎች ወደ ኋላ እየተጓተትን የዓድዋን ፍሬ መብላት አንችልም፡፡ ልክ የዓድዋ ጀግኖች እንዳደረጉት ትልቁን መዳረሻችንን አልመን ለማስተካካል አብረን መቆም ይኖርብናል፡፡
የዚህ ትዉልድ ትልቁ ዓድዋ የስራ ባህላችንን በመሰረታዊነት በማሻሻል ድህነት ከሚባል ታሪካዊና አዋራጅ ጠላታችንን ድል በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እዉን ማድረግ መቻል ነዉ፡፡
የዚህ ትዉልድ ዓብይ ዓድዋ ኢትዮጵያን ከትርክት ተቃርኖ በማላቀቅ ብሄራዊ አሰባሳቢ ትርክትን በመትከልና በማጽናት የኢትዮጵያን ሰላም በዘላቂነት እዉን ማድረግ ነዉ፡፡
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
/channel/ProsperityFirst
ክብርት ከንቲባችን አዴ @AdanechAbiebie ከጎንደር ህዝብ ክብር ስለተበረከተልዎት ደስ ብሎናል።
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
ምን እሼ ነው ግን ቲክቶክ ላይ ጓደኛ ያልሆነው? 😡 👇
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈፃሚ አባላት በአዳማ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጉብኝት በምስል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ጉለሌን የሰላምና ብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በትጋት እንሰራለን !!
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል።
አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት የክፍለ ከተማውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ያከናወናቸውን አጠቃላይ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን ይገመግማል።
በግምገማው ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ፣ የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ታደሰ ፣ አጠቃላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የፍርሃታችሁና የቁስላችሁ ግንኙነት!
ከዚህ በፊት በማንኛው የሰው-ለሰው ግንኙት አማካኝነት የተጎዳችሁ ከሆነ እንደገና ሌላ ግንኙት ለመጀመር መፍራታችሁ ምንም ችግር የሌለበትም ጤናማ ስሜት ነው፡፡ ችግር ያለበት ግን የምትፈሩት ነገር ምን እንደሆነ አጥርታችሁ ካላወቃችሁ ነው፡፡
ሁኔታውን በዚህ መልኩ ተመልከቱት፡- ልክ በእንድ አካላችሁ ላይ ጉዳት ሲደርስባችሁ ቁስሉ እስከሚድን ድረስ ምንም ነገር ወደዚያ አካባቢ እንዲቀርብ አትፈልጉም፡፡ ምክንያቱም የነካችሁ ነገር ሁሉ ቁስሉን ስለሚቀሰቅሰው ነው፡፡
ምናልባት ያቆሰላችሁ የድንጋይ እንቅፋት ቢሆንም እንኳን ከዚያ በኋላ እቤት ያለውን ወንበር ሳይቀር ትሸሹታላችሁ፡፡ ይህ የፍርሃትና የሽሽት ስሜት ግን ቁስሉ ከዳነ በኋላ እየተቀረ መሄዱ አይቀርም፡፡ የምትፈሩት ሰዎችንና ሁኔታዎችን ሳይሆን ቁስላችሁ እንዳቀሰቀስ ስለሆነ ማለት ነው፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በአንድ ሰው አማካኝነት የስነ-ልቦናና የልብ መቁሰል ስሜት ሲደርስባችሁ ከሰዎች ጋር ንክኪን መፍራት ትጀምራላችሁ፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋነኛው ምክንያት የቆሰላችሁት ነገር
እንዳይቀሰቀስባችሁ ስለምትፈሩ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ሃሳባችሁን ቁስላችሁን ባደረሰባችሁ ሰው ላይ ከመጣላችሁ የተነሳ ያንን በማውጣትና በማውረድ ስለተጠመዳችሁ ሁኔታውን ለይታችሁ አላያችሁትም እንጂ የምትፈሩትና የምትጠነቀቁት ቁስሉ እንደገና እንዳይቀሰቀስ ነው፡፡
በአጭሩ ሲጨመቅ፣ ችግራችሁ ያልዳነ ቁሰል ችግር እንጂ በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ጉዳይ አይደለም፡፡ ስለሆነም፣ በአንድ በኩል ሃሳባችሁን፣ ትኩረታችሁንና ንግግራችሁን፣ “በዚህ አለም ላይ አንድ ጥሩ ሰው የለም” ከማለት አንሱና ሙሉ ጊዜያችሁን ቁስላችሁ የሚድንበትን መንገድ በመፈለግ ላይ አውሉት፡፡
ያን ጊዜ ብቻ ደግማችሁ በዚያ መልክ እንዳትቆስሉ ጥበበኛ ወደመሆንና የሚቀጥለውን የግንኙነት መስክ ቀና ብላችሁ ወደማየት ትሸጋገራላችሁ፡፡
የችግራችሁ ዋነኛው ምክንያት ያልዳው የስሜታችሁ ቁስል ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ ሁል ጊዜ የሚነካካችሁና የሚጎዳችሁ ሰው ስለማይጠፋ፣ አንደኛችሁን ከቁስል አልፎ የሚሄድን ማንነት ማዳበሩ አማራጭ የለውም፡፡
ይህ መርህ . . . በንግዱ አለም፣ በፍቅር ግንኙነት ዘርፍ፣ በጓደኝነት መስክም ሆነ በሌሎች ማንኛውም ማሕበራዊ ዘርፍ ተግባራዊነቱ ያው ነው፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera