ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሐፊ ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዛሬ ጠዋት ከኃላፊዎቹ ጋር በአህጉራዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መወያታቸው ነው የተገለጸው።
https://twitter.com/ProsperityKera
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ እና የኢንስፔክሽ ኃላፊ የነበረው ተስፋዬ ደረጄ ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
የፍትህ ሚኒስቴር የሙሰና ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመቆጣጠር እና ለመከላክል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1 እና 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፏል በማለት በከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ዝርዝር ክስ አቅርቦበታል።
በዚህም ተከሳሹ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የፍርድ ምርመራና ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ዳኛ ሆኖ ሲሰራ የማይገባውን ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የግል ተበዳይ የሆነው ሀ/ማርያም ገ/መስቀል የተባለ የግል ተበዳይ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት በስልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጉዳዩን በማረሚያ ቤት ሆኖ መከታተል በነበረበት ጊዜ ተከሳሹ በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም ተበዳይ ወደ ሚገኝበት የፌደራል ማረሚያ ቤት በመሄድ "እኔ በስራዬ ዳኛ ነኝ የአንተን ጉዳይ እያዩ የሚገኙትን 3 ዳኛዎች መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አብሬያቸው ስለተማርኩኝ አውቃቸዋለሁኝ" በማለት ማግባባቱ በክሱ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም "ከዳኞቹ ጋር ተነጋግሬ በነፃ እንዲለቁህ አደርጋለሁ'' በማለት የግል ተበዳዩን ካናገረው በኋላ በድጋሚ ወደ ተበዳይ በመሄድ "ዳኞቹን አናግሬ በብይን በነፃ እንድትለቀቅ 1ሚሊየን 200 ሺህ ብር ጠይቀውኛል በማለትና "እኔ ተደራድሬ 600 ሺህ ብር አስደርጋለሁ" ማለት ማግባባቱም በክሱ ተመላክቷል።
ከዚህም በኋላ ደግሞ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ላይ "ዳኞቹ አሁን በቅድሚያ 400 ሺህ ብር ካልተከፈለን ምንም አናደርግም ብለዋል" በአስቸኳይ ብር አምጣ በማለት አሳሳች ነገር በመናገር እና የተበዳይን የተሳሳተ ዕምነት በመጠቀም አታሎ 2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ከሆነው የግል ተበዳይ ወንድም በሆነው ግለሰብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም 400 ሺህ ብር የተቀበለ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ በከባድ ማታለል የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶበታል።
ተከሳሹም ችሎት ቀርቦ ማንነቱን ካረጋገጠ በኋላ የቀረበበት ክስ ዝርዝር እንዲደርሰው ተደርጓል።
ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ለፊታችን ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በሶማሌ ክልል እስከ 10 ሚልዮን ሄክታር ሊታረስ የሚችል መሬት አለን።
https://twitter.com/ProsperityKera
ኢትዮጵያ የተባለችው አውሮፕላን ...
https://twitter.com/ProsperityKera
በአጭር ጊዜ ተጀምረው እየተጠናቀቁ በሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የመፈፀም አቅዎችንን የተረዳው ህዝባችን የመልማት ፍላጎቱም እያደገ እንደሚሄድ በመገንዘብ ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን መረባረብ ይገባል - አቶ አለማየሁ እጅጉ
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ እና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎችን በመገምገም የቀጣይ ወራት አቅጣጫዎችን የጋራ አድርገዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ም/ሀላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ሁለገብ በሆኑት የፓርቲ ስራዎች አቅምን በማስተባበር ለህዝባችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት መጐልበት መረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በአጭር ጊዜ ተጀምረው እየተጠናቀቁ በሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የመፈፀም አቅዎችንን የተረዳው ህዝባችን የመልማት ፍላጎቱም እያደገ እንደሚሄድ በመገንዘብ ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን መረባረብ እንደሚገባ ያመላከቱት አቶ አለማየሁ ስኬቶችን ለሌላ ስኬት ግብአት በመጠቀም ጉድለቶችን ደግሞ እየሞሉ መጓዝ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።
የተቋም ግንባታ ስራ ሁሌም እያደገ ሊሄድ እንደሚገባ ያስረዱት ሀላፊው የሚደረጉ የህዋስ ውይይቶችም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታትና የወል ትርክትን ከመገንባት አንፃርም በውጤት ሊመዘኑ እንደሚገባም ገልፀዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ የኋላሸት በቀለ በበኩላቸው ለአገር ግንባታ ስራዎች ውጤታማነት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የትብብርንና የፉክክር ሚዛንን ጠብቆ የመጓዝና ሲቪል አደረጃጀቶችን የማገዝ ተግባርን ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል።
ከሲቪል ማህበራት እና ከብዙሀን ማህበራት ጋር ተባብሮ በመስራት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታን ዕውን ለማድረግ እንዲሁም የወጣቶችን ፣ የሴቶችንና የአጠቃላይ ህዝባችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ የነበሩ ጉድለቶችንም በሚያካክስ መልኩ በቀሪ ወራት የተቀናጀ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደገፋ ገ /መድህን ባቀረቡት የቀሪ ወራት የዘርፉ ዕቅድ ላይ ተመላክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ም/ ሀላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ በበኩላቸው ውጤቶቻችንን የምንመዝነው ለመሳካት ካስቀመጥናቸው ስትራቴጂካዊ ግቦች ስኬት አንፃር በመሆኑ ባስመዘገብነው ሳንኩራራ መረባረብ እንደሚገባ አስረድተዋል።
ህዝብን የመምራትና ሰርቶ የማሰራት ሚናቸውን በአግባቡ በመወጣት ለህዝባችን ህይወት መለወጥ እንደሚተጉ የወይይቱ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በኢንዶኖዢያ በእግር ኳስ ሜዳ ላይ በመብረቅ የተመታ ተጫዋች ህይወቱ ማለፉ ተሰማ
ከኢንዶኔዢያ ‘ፐርሲካስ ሱባንግ’ የሚጫወተው የ30 ዓመቱ የእግር ኳስ ተጫዋች ባሳለፍነው እሁድ በወዳጅነት ጨዋታ ላይ በመብረቅ ተመቶ ህይወቱ ማለፉን VoiID ዘግቧል።
ተጫዋቹ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ዶክተሮቹ ህይወቱን ማዳን አልቻሉም።
ክለቡ በኢንዶኔዥያ ሶስተኛ ዲቪዚዮን ውስጥ የሚወዳደር ነው።
ሦስተኛው የኢትዮ-ሩዋንዳ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ መጠናቀቁን አስመልክቶ ሀገራቱ በአምስት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።
ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ እና የሩዋንዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንስት ቢሩታ ፈርመውታል።
ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በአደጋ መቀነስና ማስተዳደር፣ በስፖርት፣ በፖለቲካና በኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ሀገራቱ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ለላቀ ድል መረባረብ እንደሚገባ ተገለፀ
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በወቅታዊ ጉዳዮች፣ ለወጣቶች እና ለሴቶች የስራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም የህዝባችንን ኑሮ ለማሻሻል በሚከናወኑ ስራዎች እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከከተማ እና ክ/ከተማ የፓርቲ አመራሮች ጋር መክረዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም አቀፍዊ ሁኔታ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ መያዝና ለህዝባችን ጠቃሚውን አቅጣጫ መቀየስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በከተማችን በዓላት አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ መከበራቸው ፣ የአድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ መጠናቀቃቸውና እየተጠናቀቁ መሆናቸው በአመራራችንና በህዝባችን ላይ ተጨማሪ ተነሳሽነት መፍጠራቸውን የጠቆሙት አቶ ሞገስ ስኬቶቻችንን አጠናክሮ ለማስቀጠል የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል እና በሌሎችም የተጀማመሩ ዘርፈ-ብዙ ጥረቶችን ማጎልበት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ከተማችን ያሏትን የመልማት አቅም በአግባቡ እንድትጠቀምና ለወጣቶች እና ለሴቶችም ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር የተጀመሩ ቅንጅታዊ ጥረቶች እንዲጠናከር ያሳሰቡት አቶ ሞገስ ህዝባችንም ከከተማ አስተዳደሩ ጐን የሚያደረገውን ርብርብ እንዲያጠናክር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ም/ሀላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር ተግባራትን አቀናጅቶ የመምራት ባህል እያደገ ቢሆንም 24 ሰዓት እየተጋ ተልዕኮን ወደ ውጤት የመቀየር የአመራርነት ቁመናን መላበስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አመራሩ ከፈፃሚዎች ጋር ያለውን ቅንጅት ሊያጠናክር እንደሚገባ ያመላከቱት አቶ አለማየሁ አባላትም ግንባር ቀደም ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በውይይቱ ላይ የክፍለ ከተሞች የፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊዎች በየክፍለ ከተሞቻቸው የሚደረጉ የልማት እና የመልካም አሰተዳደር እንዲሁም የፀጥታ ስራዎች እየተመሩበት ያለውን አግባብ የሚያመላክቱ አጠር ያሉ ሪፖርቶችን ያቀረቡ ሲሆን የህዝባችንን ህይወት ለማሻሻል የአመራሩ ከጠዋት እስከ ማታ የመስራት እና ተግባራትን በተቋማዊ አቅም አስተሳስሮ የመምራት ባህል ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ተመላክቷል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት 44ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እና በ37ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ፀሃፊው ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንደተቀበሏቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት ከ‘ገበታለትውልድ’ የልማት ቁልፍ ስፍራዎች አንዱ ሆኖ በሶማሌ ክልል የሚገኘውን የሸበሌይ ሪዞርት ግንባታ ስፍራ ጎበኙ።
https://twitter.com/ProsperityKera
የአድዋ ድል መታሰቢያ
የሁላችንም ኩራትና ውበት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://twitter.com/ProsperityKera
ትናንት በአድዋ ድል መታሰቢያ ላይ የነበራችሁ 👇
የቡሩንዲ የባህል ቡድን ነፍሴን ነው ያስደሰታት 👇
--------------------------------------------------
Honored to participate in Ottawa’s #BlackHistoryMonth celebration in the presence of PM @JustinTrudeau, highlighting Black Canadians’ contributions and resilience.
© Fitsum Arega
በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር
https://twitter.com/ProsperityKera
ከአዳማ፣ ወለንጭቲ፣ መተሃራ እስከ ቦርደዴ ድረስ የተዘረጋ የህገወጥ መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ቡድን በህገ-ወጥ መንገድ ሊያሻግሩት የነበረ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ተያዘ፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ከነተጠርጣሪዎቹ የተያዘው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር ባደረገው ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተጠርጣሪዎች ክላሽ፣ ቦምብና ከ9 ሺህ 600 በላይ ጥይቶች እንዲሁም የመሳሪያ ግዥ ይፈፀምበት የነበረ 600 ሺህ ብር መያዙን የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ገልፀዋል፡፡
ለፀረ-ሰላም ሃይሎች የሚደርሰውንና ለአካባቢው ብሎም እንደ ሀገር የሰላም ጠንቅ የሆነውን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ከምንጩ ለማድረቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
በዚህም ህገ-ወጥ ዝውውሩ እጅግ ውስብስብና የተደራጀ መሆኑን መገለጹን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ለጊዜያዊ ጥቅሞች ሲባል ዘላቂ ሰላሙን የሚያናጋ ህገ-ወጥ የመሳሪያ ዝውውር በአካባቢው እንዳይፈፀም የማድረግ ዜግነታዊ ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመተባበር የተጀመረውን ኦፕሬሽን እንዲያግዝ ተጠይቋል፡፡
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው የአስፈፃሚ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በማድመጥ እንደሚያፀድቅና ተጨማሪ በጀትም ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ አንኬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ምክር ቤቱ የ5ኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳ ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
በአዲስ አበባ ከተማ ከየካቲት 8 ቀን ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ክልከላው የጸጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን እንደማያካትት ነው የተገለጸው፡፡
ስለሆነም የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ተጠይቋል፡፡
የተቀመጠውን ክልከላ በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የዝቅተኝነት ስሜት ድብቅ ምልክቶች
ብዙ ሰው ከሚታገላቸው ስሜቶች አንዱ የዝቅተኝነት ስሜት (Inferiority complex) ነው፡፡ የዝቅተኝነት ስሜት ማለት እኛ ከሌላው ሰው እንዳነስን ወይም በሌላው ሰው እንደተበለጥን ሲሰማን ማለት ነው፡፡ ይህ ስሜት በትክክለኛው መንገድ ካልተያዘ እያንዳንዱ ንግግራችን እና ተግባራችን ውስጥ ጣልቃ የመግባት አቅም አለው፡፡ ይህ ጣልቃ ገብነቱ ደግሞ ከዓላማችን እንድንወጣና እንዲሁም ከባድ የሆነ ማሕበራዊ ቀውስ ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል፡፡
የዝቅተኝነት ስሜት እንዳለብን ለማወቅ ከፈለግን የሚከተሉትን መመዘኛዎች እንመልከታቸው፡-
1. ስለሰዎች ጤና-ቢስ ወሬን ማራባት፡፡
ይህ የዝቅተኛነት ስሜት መገለጫ መነሻው እኛ የምንነሳው ሌላውን ስንጥልና የእኛ ሁኔታ የሚደምቀው የሌላውን ሰው ስም ስናጠፋ ሲሆን ብቻ ሲመስለን ነው፡፡ ይህ ስህተት የሚመጣው ደግሞ በራሳችን መቆምና ማደግ እንደማንችልና የተበለጥን እንደሆንን ስናስብ ነው፡፡ ስሆነም ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ሌላውን ማደናቀፍ፣ ለማደግ ከመስራት ይልቅ ሌላውን ማድቀቅ . . . ይቀናል፡፡
በራሱ የሚተማመን ሰው የሰውን ነገር በማውራትና ሰውን በማሳነስ እሱ የሚተልቅ ስለማይመስለው የራሱ ስራ ላይ የሚያተኩር ሰው ነው፡፡
2. ስለገቢ መጠንና ስለ ቁሳቁስ ጉራ መንዛት፡፡
ይህ የዝቅተኛነት ስሜት መገለጫ መነሻው ያለንን ነገር አጉልቶ በማሳየት ከሰዎች በላይ እንደሆንን የማሳየት ጡዘት ነው፡ ስለደሞዛችን፣ ስላለን ቤት፣ ሰለምናሽከረክረው መኪናም ሆነ ስለሌሎች ንብረቶቻችን ለሰው የማውራትና ሰዎች እንዲያውቁሉን የመጦዝ ዝንባሌ መነሻው ከፍተኛ የዝቅተኛነት ስሜት ነው፡፡
በራሱ የሚተማመን ሰው ባለው ቁሳቁስ የመደሰት፣ ቤተሰብን የመገንባት፣ ችግረኞችን የመርዳትና ለወደፊቱ የበለጠ የመሻሻሻል ስራ ስለሚበዛበት ለእዩልኝና ለእወቁልኝ ጊዜም የለው፡፡
3. ተግባርንና ግብን አጋንኖ ማውራት፡፡
ይህ የዝቅተኛነት ስሜት መገለጫ መነሻው ከሌሎች ጋር ተፎካክረን እንዳሸነፍንና ስኬታማ ሰዎች እንደሆንን በማሳየት ያለንን የዝቅተኝነት ስሜት የመሸፈን ጥማት ነው፡፡ የዚህ ቀውስ ትልቁ ክስረት ያለው እንዳደረግንና እንደምናደርግ የምናንጸባርቃቸውን ነገሮች አእምሯችን በርግጥም እንዳከናወንናቸው ስለሚተረጉማቸው ምንም ሳንሰራና የትም ሳንደርስ በወሬ ብቻ እንደደረስን አምነን በመቀበል ኋላ መቅረት ነው፡፡ እኛ ስለሆነውም ስላልሆነውም የተጋነነ ጀብዳችን ስናወራ አለም አምልጦን ይሄዳል፡፡
ያለብን የዝቅተኝነት ስሜት መገለጫው እነዚህም ሆኑ ለሎች ዋናው ቁም ነገር የዚህ የስሜት ቀውስ ምንጩን በመለየት የነጻነት መንገድ መጀመሩ ላይ ነው
https://twitter.com/ProsperityKera
ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የትራፊክ ፍሠቱን የተሳለጠ ለማድረግ እንዲቻል ለኮንስትራክሽንና ለጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ቀደም ሲል በከተማው ላይ በደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የተከሰተውን ተመሣሣይ ጥፋት መነሻ አድርጎ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክት ማስተላለፋ ይታወሳል።
በመሆኑም የትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ባሻገር ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እንዲሁም በመዲናዋ በቀጣይ ቀናት ለሚካሔደው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የፀጥታ አካላት ለሚያከናውኑት የፀጥታ ስራ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲቻል ከዚህ በታች በተገለፁት መንገዶች፤
👉 ቦሌ ድልድይ አካባቢ
👉 ከቦሌ ድልድይ እሰከ ሩዋንዳ ድልድይ
👉 ከቦሌ ድልድይ በወሎ ሰፈር ደንበል አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ
👉 ከመስቀል አደባባይ እስከ አራት ኪሎ
👉 ከኡራኤል አደባባይ እስከ አትላስ ሆቴል
👉 ከኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እስከ ልማት ባንከ
👉 ከአራት ኪሎ እስከ አምባሳደር መናፈሻ
👉 ከብሄራዊ ቴአትር እስከ ሜክሲኮ አደባባይ
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እና
👉 ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እስከ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ባሉት መንገዶች ላይ ተለዋጭ መረጃ እስኪተላለፍ ድረስ የኮንስትራክሽን ከባድ እና የጭነት ተሽከርካሪንዎችን ማሽከርከርም ሆነ ማቆም የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
ይህንን ተላልፈው በተገኙት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም በማስቀደምና በዘላቂ ሰላም ግንባታ ሂደት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ ገለጹ።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ፤ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ ክብር፣ አንድነት፣ ዘላቂ ሰላምና ልማት ላይ ሀገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ የተለየ አቋም እንደሌለው ያምናሉ።
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትም የተቋቋመበት ዋነኛ አላማ በእነዚሁ ጉዳዮች ዙሪያ ለመስራት መሆኑን ጠቁመው በተለያዩ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በሀገሪቱ የዳበረ የዴሞክራሲ ስርአት እንዲገነባና በፖለቲካ ፉክክሩም በሃሳብ የበላይነት የማሸነፍ ባህል እንዲስፋፋ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ አሁን ላይ በተለይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና በሰላም ጉዳይ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑንም ሰብሳቢው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ ማናቸውም ፓርቲዎች በሀገር ብሄራዊ ጥቅምና በሰላም ጉዳይ የተለየ አቋም ሊኖራቸው አይገባምም ነው ያሉት።
የህዝቡ ፍላጎት ሰላምና ልማትን እንዲሁም የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በዚሁ መልኩ መንቀሳሰቅ አለብን ነው ያሉት።
የጋራ ምክር ቤቱ አባልና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄር፤ ፓርቲያቸው በሰላም ጉዳይ ላይ አበክሮ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምና ዘላቂ ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ሁላችንም የድርሻችንን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናልም ነው ያሉት።
https://twitter.com/ProsperityKera
በኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል ለረጅም ዓመታት የቆየው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር መጠናከር እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በጀርመን ፓርላማ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የእርስ በርስ ግጭት መከላከል ኮሚቴ ሃላፊ ሞኒካ ግሩተርስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ የትብብርና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ምክክር አድርገዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ የሁለቱን ሀገራት የቆየ ግንኙነት አውስተው በሀገራቱ መካከል ለረጅም ዓመታት የቆየው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር መጠናከር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ስለ ፕሪቶሪያው ስምምነት ለልዑኩ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ መተግበር መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ከአጋር አካላት ጋር ለመስራት ያላትን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል።
የልዑኩ መሪ ሞኒካ ግሩተርስ በበኩላቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ትረፊ ያላት ነፍስ! !!
https://twitter.com/ProsperityKera
የዓድዋን ድል ለህብረብሔራዊ አንድነታችንና ሁለንተናዊ ብልጽግናችን ለማረጋገጥ መጠቀም የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ሀላፊነት ሊሆን ይገባል!
የዓድዋ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በከፍተኛ ተጋድሎና መስዋትነት ሀገራችንን ያስከበሩበት ለጥቁር ህዝቦች ሁሉ አንፀባራቂ የሆነ ድል ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በጋራ መታገል እና በጋራ ድል መቀዳጀት የካበተ ልምድ ያለን ህዝቦች መሆናችን የዓድዋ ድል ትልቅ ታሪካዊ ማሳያ ነው። ጀግኖች አባቶች በከፈሉት መሰዋእትነት ድልን አጎናጽፈውናል፤ ለዚህ ክብር ላበቁን አርበኞች ክብር ይገባቸዋል፡፡
ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን የአብሮነት፣ የአሸናፊነትና ፅናት ተምሳሌት ነው። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መግስታችን ደግሞ መስዋትነት ለከፈሉ ጀግኖች አባቶቻችን ክብራቸውን የሚመጥን ትልቅ እና ማስተማሪያ የሆነ የዓድዋ ድል መታሰቢያ በማቆም ሌላ ደማቅ የታሪክ አሻራ ማኖር ተችሏል።
እኛም የዛሬ ትውልዶች ለአርበኞቻችን ክብር እየሰጠን ዘመኑን በመዋጀት ከአባቶቻችን ልቀን እንጂ አንሰን እንዳንገኝ የዛሬውን የጋራ ጠላት የሆነዉን ድህንትን በማሸነፍ ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ኢትዮጵያን የማስረከብ ሃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል።
የዓድዋ ድል ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለሚገጥሙን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች ሁሉ መሻገሪያ ድልድይ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየ ታሪካዊ ኩነት ነው።
የዓድዋን የታሪክ ዕጥፋት ለህብረብሔራዊ አንድነታችን መጠቀምና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።
እንደ ዓድዋ ድል ሁሉ ኢትዮጵያን ወደላቀ ከፍታ ለመውሰድና ታሪኳና ክብሯን የሚመጥን ሁለንተናዊ ከፍታ ለማብሰር የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የጋራ አስተዋጽኦ ስለሚጠይቅ ዘመን ተሻጋሪና አካታች የሆነ ብሔራዊ ገዥ ትርክት በመገንባት ለትውልድ ማውረስ ወሳኝ ነው፡፡
የዓድዋ ድል ስኬታማ የሆነው በመላው ኢትዮጵያውያን የተደመረ የአንድነት መንፈስ በመሆኑ አሁንም ሆነ ወደፊት የአገራችንን እድገትና ብልጽግና የምናረጋግጠው አሰባሳቢ በሆነ ብሔራዊ ገዥ ትርክት የወል እውነቶቻችንን እያፀናን በአብሮነታችን ፀንተን ከእዳ ወደ ምንዳ በምናደርገው የመደመር ጉዞ ነው።
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም መንግሥታት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቆይታቸው ወቅት በከተማ ፕላን እንዲሁም የወደፊት ከተሞችን በተመለከተ ከሚኖራቸው ውይይት በተጨማሪ በሌሎች መድረኮች እና የፓናል ውይይቶች ላይ በመታደም የወደፊት የአስተዳደር ዘርፎች ላይ የሚያተኩሩ የጎንዮሽ ውይይቶች ላይ የሚሳተፉ ይሆናል::
በውይይት መድረኩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሃመድ እንዲሁም የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ተሳታፊ ሆነዋል::
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሸበሌይ ሪዞርት ግንባታ ስፍራን ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት ከ‘ገበታለትውልድ’ የልማት ቁልፍ ስፍራዎች አንዱ ሆኖ በሶማሌ ክልል የሚገኘውን የሸበሌይ ሪዞርት ግንባታ ስፍራ ጎብኝተዋል።
ከጂግጂጋ ከተማ 29 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ 385 ሄክታር በሚሸፍን ስፍራ ላይ የሚገነባው ኘሮጀክት የጂግጂጋ ከተማ እና አካባቢውን ወደ ግምባር ቀደም የቱሪዝም መዳረሻነት የሚለውጠው የቱሪዝም ስራ አንድ አካል ነው።
ይህ ስራ ኢትዮጵያ የያዘችውን የዘላቂ ቱሪዝም ስራ እና የኢኮኖሚ እድገት መንገድ አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
#አዲስአበባ
#ፒያሳ
በዚህ ሰአት
https://twitter.com/ProsperityKera
እስከ 10 ሚሊየን ሄክታር የሚደርስ ሊታረስ የሚችል መሬት ያለው ሱማሌ ክልል።
Lafti qotamuu danda'u hektaara miliyoona 10 ta'u kan argamu Naannoo Somaaleettidha.
© @AbiyAhmedAli (phd)
FDRE 🇪🇹 PM
https://twitter.com/ProsperityKera
የሴት ምሳሌ፣ ብርቱና ማርሽ ቀያሪዋ አዳነች አቤቤ ቀን ከሌት ሰርታ ታሪካችንን ስለገነባች አመሰግናታለው!
ጠቅላይ ሚንስትር @AbiyAhmedAli ( ዶ/ር )
https://twitter.com/ProsperityKera
የትኩረት ለውጥ አድርጉ
ሁል ጊዜ እውነታን ተመልኩዞ ሳይሆን ከመሰለውና ከገመተው እየተነሳ ካለማቋረጥ የወቀሳን ሃሳብ በመሰንዘር ለሚረብሻችሁ ሰው የመጨረሻው መፍትሄ በዚያ ሰው ሁኔታና ንግግር ስሜታችሁ ሳይነካ በራሱ መላ-ምትና ግምት እንዲኖር መፍቀድ እንደሆነ አስታውሱ፡፡
እንደዚህ አይነት ሁል ጊዜ በእናንተ ላይ ጫናን የሚያስከትል ንግግር ለመናገር አጀንዳ የማያጣ ሰውን በዝምታ በማለፍ ራሳችሁና አላማችሁ ላይ እንድታተኩሩ ትመከራላችሁ፡፡
ስሜታዊ በሆናችሁና ምላሽን በሰነዘራችሁ ቁጥር እንደገና የሚነሳበትን አቅርቦት እንደምትሰጡት አትዘንጉ፡፡
መልካም እንቅልፍ ተመኘሁላችሁ!
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
"ታሪክን መዘከር ብቻ ሳይሆን ከታሪክ መማር አለብን" - ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp