prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሊዊዝ ኢናሲዬ ሉላ ዳ ሲልቫ ዛሬ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአድዋ መታሰቢያ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ በጉብኝቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስለ ዓድዋ እና እለመታሰቢያው ገለፃ አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ሉላ በአዲስ አበባ የሚያደርጉትን የሥራ ጉብኝት በዓድዋ መታሰቢያ ጀምረዋል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ሰውነት
የሰው ልጅ ረዘመም፣ አጠረም፣ ወፈረም፣ ቀጠነም፣ አገኘም፣ አጣም፣ ቀላም፣ ጠቆረም፣ ... የሰው ልጅ የሰው ልጅ ነው።

ሰው ሁሌም ሰው ነው።
ሰው ሁሌም ህያው ነው።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

estifopp?_t=8juXqr9DP6b&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp?_t=8juXqr9DP6b&_r=1

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ምገባ ኤጀንሲ፣
"ከመመገብ ባሻገር... "

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አያሳቅቅም ???
አይገርምም ???
😁😁😁😁😁
ናይጀሪያ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ተበላህ አባቴ።
ምናለ አፍሽን ብትዘጊ ኖሮ ሚስቲት
😜😜😜😜😜😜😜

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሲቪክ ማህበራት ድርሻ የጎላ ነው" አቶ ሰዒድ ዓሊ
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሲቪክ ማህበራትን በማጠናከር የሀገራችንን ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ ገለጸ። አስተዳደሩ በክፍለ ከተማው ከሚንቀሳቀሱ ሲቪክ ማህበራት ባስመዘገቡት ውጤትና ባጋጠማቸው ተግዳሮት ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰዒድ ዓሊ እንደተናገሩት የሲቪክ ማህበራትመንግስትን በልማት፣በሰላም፣በዲሞክራሲያ ስርዓት ግንባታ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን በማምጣት ያላቸው ሚና ጉልህ መሆኑን በመግለፅ በሲቪክ ማህበራት የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን በጋራ ሆነን በመፍታት ሲቪክ ማህበራት የተቋቋሙለትን ዓላማ ግብ እንዲመታ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ድሪብሳ በበኩላቸው የሲቪክ ማህበራት የተቋቋሙለትን ዓላማ ለማሳካት ከፊታቸው ያሉ ተግዳሮቶችን ለማለፍ የመንግስት ድርሻ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ችግሮችን በመፍታት የሲቪክ ማህበራት ለዜጎች ተጠቃሚነት መስራት እንዲችሉና የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ እንዲችሉ በማድረጉ በኩል መንግስት ኃላፊነቱን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት መንግስት ለሲቪክ ማህበራት እየሰጡት ያለው ትኩረት አበረታች መሆኑን ገልጸው ሲቪክ ማህበራት የሚያከናዉኑትን ተግባር በማጠናከር በልማት፣ በሰላምና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ኃላፊነትን መወጣት ይገባል ብለዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በ2016 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የሚቀመጡ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 3 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የምዝገባ ሂደትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ዘንድሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ማከናወን የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ገልጸዋል።

ከዝግጅቱ መካከልም የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መመዝገብ የሚያስችል ስራ ማከናወን አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

የካቲት 3 የተጀመረው ምዝገባ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ምዝገባ የጀመሩ አካባቢዎች መኖራቸውን በማብራራት በቀጣይም ምዝገባ ያልተጀመረባቸው አካባቢዎች ምዝገባውን እንደሚያካሄዱ ገልፀዋል።

ፈተናው ላይ ለመቀመጥ በመደበኛ፣ በማታ፣ በርቀት እና በግል በሀገር አቀፍ ደረጃ መመዝገብ ከሚያስችሉ መስፈርቶች መካከል ዋነኛው የትምህርት ማስረጃ መሆኑን ተናግረዋል።

በመደበኛ እና በማታ ትምህርት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

የግል፣ የርቀት እና በበይነ መረብ ተምረው የሚፈተኑ ተማሪዎች ምዝገባ በክፍለ ከተማ፣ በልዩ ወረዳ እና በወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤቶች እንደሚካሄድ አክለዋል።

ከአገልግሎት ባገኘነው መረጃ በ2016 በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ህዝባዊ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።

ህዝባዊ የምክክር መድረኩ“ኅብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሠላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከህዝቡ ጋር ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ለመድረስ የሚያስችል መድረክ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ እና አቶ ሞገስ ባልቻ፣በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ ያለፈ ልምዷ ሲታይ ፈተናዎች ሲገጥሟት ተጋፍጣ የማለፍ ተሞክሮ ያላት ሀገር ናት ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበርያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ በመድረኩ ላይ ገልፀዋል።

በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ህዝባዊ ውይይት ላይ ሀገሪቱ የሚያጋጥማትን ፈተናዎች ተቋቁማ ለማለፏ መነሻው ህዝቦቿ በጋራና በአንድነት መተሳሰራቸው ብሎም አብሮ መቆማቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ሁሌም የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቀልበስና ለመሻገር ንግግሮች እንደሚያስፈልጉና ለዚህም ይህ አይነቱ ህዝባዊ ውይይት ሚናቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ በበከላቸው ገዥ ትርክት የኃያላኑ ሀገራት መሰረት እንደሆነ ጠቅሰው በተቃራኒው አሉታዊ ትርክቶች ጉዳታቸው የከፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን መነሻችንና የባህል እሴታችንን መሰረት በማድረግ ገዥ ትርክቶችን ማስፋፋት ብሎም ባህል ማድረግ ያስፈልገናል ብለዋል።

በሆሳዕና ከተማ "ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለሁለንተናዊ ሰላምና ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሲዳማ ክልል ህዝባዊ ውይይት ሀዋሳ ከተማ ላይ እየተካሄደ ነው!!

ብልፅግና ፓርቲ በሃገሪቱ በሁሉም የክልል ከተሞች የተለያዩ ህዝባዊ መድረኮችን በመፍጠር ከህዝብ ጋር በተለያዩ ጊዜያት ከህዝቡ በሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር እእንዲሁም (ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ) ጉዳዮችና በዴሞክራሲ ግንባታን መሠረት ያደረጉ ጥያቄዎችን ለቅሞ ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አህመድ ሺዴ ተናግረዋል።

በዛሬው እለተ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ህዝባዊ ውይይቱ የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያግዝና የሚደግፍ "ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በከተሞች እያደገ የመጣውን የህዝብ ጥያቄ ለመፍታት ከህዝብ ጋር ቀርቦ መወያየትና መመካከር የብልፅግና ፓርቲ ልዩ ባህርዩ ነው ያሉት ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ የሲዳማንና የሀዋሳን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በልዩ ትርጉምና ትኩረት ቀጥሎም ይፈታል ብለዋል።

ህዝባዊ ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት የፓርቲያችን ስራ አስፈፃሚ አሻላት አቶ አህመድ ሺዴና እና ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋገሾ ሲሆኑ እንደ ሀገር ያለውን እምቅ አቅምና ሀብት መፍጠር ለመበልጸግ መነሻ መንገድ እንደሆነ አንስተዋል።

የህዝባችን ጥያቄ በየደረጃው እየለየ ለመፍታት የክልሉ መንግስትና ፓርቲ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆነ የገለፁት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ኃላፊ አቶ አስፋው ጎነሶ በፓርቲያችን መሪነት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ከተሞችን የብልፅግና ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

በመድረኩ በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ ሰነድ መነሻ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የልማት ስራዎችን ታሳቢ ያደረገ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች" በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር ህዝባዊ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የሠላም፣ ልማት እና መልካም አስተዳደር ዕቅዶቻችን ትግበራ ሂደት የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች፣ ተባባሪና የልማት አጋሮቻችን እንዲሁም መላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች ለቀደመው ስኬታችን የነበራችሁን አወንታዊ ተሳትፎ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

አክለውም በአስተዳደሩ የተመዘገቡ ስኬቶች ይበልጥ አጠናክረን ለማስቀጠል እንዲሁም ድሬዳዋ አስተዳደር “ትንሿ ኢትዮጵያ” የሀገራችን የሁለንተናዊ ብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕያችን እውን እንዲሆን አሰባሳቢ እና ገዥ ትርክቶችን ሰንቀን የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለብን ብለዋል።

በመካሄድ ላይ ያለውን ሕዝባዊ የውይይት መድረክ በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት የፌደራል ገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝና አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ደቡብ ምዕራብ ኢ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ የአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በመምራት ላይ ይገኛሉ።

በመድረኩ ላይ ከ2,000 በላይ የሚሆን የአስተዳደሩ ነዋሪ ተወካዮች ተገኝተዋል።

#prosperit
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው!!

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በስብሰባው ማግስት ካስቀመጣቸው አቅጣጫዎች መሀል የህብረተሰባችንን ጥያቄዎች በአግባቡ በማድመጥ የሚነሱ ቅሬታዎች እንዲሁም ምላሽ የሚፈልጉ ነጥቦች ላይ በቀጥታ ከህብረተሰቡ ጋር ተመካክሮ መፍትሄ ማበጀት የሚለው ሀሳብ በዋናነት ይገኝበታል።

በዚህም መሰረት የህብረተሰባችንን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመፍታት በዛሬው እለት በ19 ከተሞች ከህብረተሰባችን ጋር በቀጥታ ውይይት በማድረግ ላይ እንገኛለን።

ለአብነት ያህልም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአማራ ክልልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) በተገኙበት ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

ህዝባዊ ውይይቱ "ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ነው በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው፡፡

በውይይቱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል ፡፡

ውይይቱ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ጉዳዮች የሚነሱበትና ሰላም ፍቅርና አንድነትን የሚያጎለብቱ ሀሳቦች የሚነሱበት ነው፡፡

ፓርቲያቸን ብልፅግና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በአጋርነት የተፈረጁ ክልሎችን ወደ ውህድ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ከቀላቀለ በኋላ በአካታች የብልፅግና ፖሊሲያችን ተጠቃሚ ከሆኑ ክልሎች መሀል የቤኒሻንጉል ክልል የሚጠቀስ ሲሆን በክልሉ ያለውን ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶች በተገቢው ሁኔታ አውጥቶ መጠቀም እንዲቻል ሰፋፊ ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ።

ይህ ህዝባዊ መድረክም የተገኙ ወረቶችን ለማስቀጠል፣የሚታዩ ህፀፆችን ለማረም ከፍተኛ ግብአት እንደሚሆን ይጠበቃል።

#prosperity

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሐረሪ ክልል ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ "ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር እንዳሉት መንግስት ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው።

በተለይም ህዝቡ የሚያነሳቸውን ችግሮች ለመፍታትና ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት እየሰራ ላለው ስራ የክልሉ ህዝብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ባልጂጌ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አደራጅ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፣የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣ የክልሉ አመራሮችን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ አካላት መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አዲሱ ያ ቴሌቪዥን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ዉድመት ደረሰበት

የሩቅ ምስራቅ ፊልሞችን በአማርኛ ትርጉም ለተመልካቾች ሲያቀርብ የነበረዉ ያ ቴሌቪዥን ጎተራ አካባቢ የቀድሞው አጎና ሲኒማን በመያዝ ወደ ስራ የገባዉ የቴሌቪዥን ተቋሙ መሆኑ ይታወቃል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሀገራችን ኢትዮጵያን የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር አስተማማኝ መሰረት ዛሬ ላይ በመገንባት ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሕ እና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባት ሀገር መሆን ይኖርባታል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔና የቀደመ ሀገረ-መንግስት ባለቤት ብትሆንም አሰባሳቢ የሆነ ሀገራዊ ትርክት መገንባት ባለመቻሏ ትርክቶቿ በስርዓታት ፖለቲካ ፍላጎት ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ ሆነው በመቆየታቸው ስርዓታት በወጡ እና በወረዱ ቁጥር የሚገለባበጡ ነጠላ ትርክቶች ገዥ እየሆኑባት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ተግባሯን ያለ ተቃርኖ ለማስቀጠል አልታደለችም።

በአንፃሩ የአሜሪካን፣ የቻይናን የፈረንሳይን ሀገራዊ ገዥ ትርክቶች የሚነግሩን ስርዓቶች ቢቀያየሩም ገዥ ሀገራዊ ትርክታቸው መሰረቱ ሀገረ-መንግስቱ ላይ በመገንባቱ በየወቅቱ የሚነሱ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች አይለዋወጥም።

ሀገራት ህዝባቸውን ከየት እንደተነሱና ወዴት እንደሚደርሱ በአሰባሳቢ ገዥ ትርክት በመገንባት ከአስተዳደራዊ ወሰናቸው አልፈው በዓለም ላይ የበላይነታቸውን ቅቡልነት አረጋግጠዋል።

የዓለማችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚዘውሩት የትርክት የበላይነት በያዙ ሀገራት እና ተቋማት ፍላጎት ነው። እነዚህ ሀገራትም ይሁኑ ተቋማት የትርክታቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሁሉንም ዓይነት ሀይል የማስጠበቂያ አማራጮችን ይጠቀማሉ።

ትርክት ቻይናን ከወደቀችበት አንስቶ የዓለም ተፆዕኖ ፈጣሪ ሀገር አድርጎ ከፊት አስቀምጧታል። ትርክት ሶሪያ ከዓለም ቀደምት ሀገርነት ወደ ፍርስራሽነት ቀይሯታል። ትርክት ኢትዮጵያን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲነገር የሚኖረውን በቅኝ-ገዥዎች ቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንዲትሰራ አስችሏታል።

ትርክት በህዝብ ውስጥ ለጋራ ዓላማና ራዕይ በአብሮነት በማነሳሳትን በአርበኝነት እንዲፈፅሙ የሚያንቀሳቅስ ታላቅ ሀይል መሆኑን በመረዳት ብልጽግና ፓርቲ በተራራቀ ዋልታ የሚገኙትን የሀገራችን ትርክቶች ወደ አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ለማምጣት በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረት ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችን ገዥ ትርክት እንዲሆን እየሰራ ይገኛል።

ብልፅግና በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችንን ያልፈውን የጉዞ ምዕራፍ ፣ የዛሬን ነባራዊ ሁኔታ እና የነገን መዳራሻ የምንመለከትበት የጋር አሰባሳቢ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ብሎ ያምናል።

በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት ገዥ ትርክት የትላንቱን ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ መሰረት አድርጎ የዛሬውን አስተሳስሮ ነገን ማመልከት የሚችል የህዝባችንን ዋና ዋና የጋራ እሴቶችን፣ ፍላጎቶችንና ግቦችን የሚያሳካና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ያደርጋል።

ፓርቲያችን ህዝባችን የጋራ ታሪክ ያለው፣ ብዙ ትላንቶችን በጋራ የተሻገረ አሁን ስንቅ ልናደርጋቸው የሚገቡ አያሌ ታሪኮችን እንዳሉት ያምናል።

በዚሁ አግባብ ብልፅግና በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ አማካይነት ነባር የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት፣ ታሪካዊ እሴቶችን አውጥቶ በማበልፅግ እና በማህበራዊ ካፒታላችንን በመጠቀምና በእነዚህ ላይ እሴቶችን በመጨመር ለነገ ብልጽግናችን በሚሆን መንገድ ማልማት በሰፊው ቀጥሏል።

ከትላንት የተሻለ ሀገራችንንና ህዝቦቿን የሚጠቅም ታሪክ እንድሰራ፣ የትውልዶችን ድካም በማረም ለትወልድ የበለፅገች ሀገር ለማስረከብ እንትጋ። ስለዚህ ትርክታችን ያለፈውን ብቻ ሳይሆን የዛሬን ዕድል እና የነገን ተስፋ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።

#Prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች አብሪ ኮከብ! አዲስ አበባ የዲፕሎማቶች ስበት!

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ለማስቀጠል ለዘመናት ባደረገችው ተጋድሎ የአፍሪካ የነፃነት ፣ የአይገዛም ባይነት እና የአይበገሬነት ተምሳሌት ናት።

የቀለም አድሏዊነት ሰፍኖበት በነበረው ዓለም ነጭ መሆን እና ጥቁር መሆን የበላይና የበታች ገዥ እና ተገዥ የሚል ልዩነት ለመፍጠር ምክንያት ሊሆን እንደማይገባው ብቻም ሳይሆን ሊሆን እንደማይቻል በእብሪት የመጣውን ወራሪ ሀይል አንኮታኩታ በዓለም ላይ የሰው ልጆች ሁሉ እኩል የሚታዩበት ፍትሀዊ የዓለም ስርዓት እንዲገነባ ፅኑ መሰረት አስቀምጣለች።

የአገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር መስዋዕትነት ለመክፈል ወደ ኋላ የማይለው ህዝባችን የሚሰነዘርበትን ጥቃት ለመመከት ወደ ጦርነት ይገባል እንጂ ሰላምን አጥበቆ የሚወድ ለሰላም የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከመክፈል ወደ ኋላ የማይል የማንንም አገር ሉዓላዊነት የማይጋፋ መሆኑን ያሳለፈናቸው ታሪኮች ሁሉ ምስክሮች ናቸዉ::

ኢትዮጵያውያን ከወል ትርክት ይልቅ የተናጠል ትርክቶችን በማጉላታችን አንዳችን ከአንዳችን አላስፈላጊ ግጭቶችንና ጦርነቶችን በማድረግ ተገቢ ያልሆነ መስዋዕትነት መክፈላችን እና አገራችንን ከስልጣኔ ማማ አውርደን የድህነት ማጣቀሻ ማድረጋችን የማይታበል ሀቅ ቢሆንም ማንንም አገር ወርረን አናውቅም ፤ ወደ ፊትም ቢሆን ካልነኩን አንነካም።

ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ክብረ ለማስጠበቅ ደምአቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው መስዋዕትነትን ከመክፈል ወደ ኋላ እንደማይሉት ሁሉ ለአፍሪካውያንና ለዓለም ሰላምም በጊዜና በሁኔታዎች የማይዋዥቅ ፅኑ አቋም አለን።

ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊታችን በተለያዩ አህጉሮች በተለያዩ አገራት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችን በመውሰድ በብቃት እየተወጣ መሆኑ ለዚሁ ማሳያ ነው::

ኢትዮጵያ ከጥንት እስከ ዛሬ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም እና አድሏዊነትን በማውገዝ ለአፍሪካውያንም ድምፅ ሆና እየታገለች ትገኛለች።

አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት ሲማቅቁ በነበረበት ዘመን ፋናወጊ የአፍሪካ መሪዎችን በማስተባበር በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አፍሪካን ለአፍሪካውያን የሚል አስተሳሰብ እና ተግባር ስታራምድ ቆይታለች።

ዛሬም አፍሪካውያን በውስጥ ድክመቶቻችንና በረጃጅም ስውር እጆች ምክንያት ሲንከባለሉ የመጡ እዳዎቻችንን ወደ ምናዳ የመቀየር አቅሙም ፍላጎቱም አለን በማለት የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን እንዲፈቱ በአርአያነት እየተንቀሳቀሳች ትገኛለች።

የቀደምት ስልጣኔ ፈንጣቂ የሆነችው ኢትዮጵያ አፍሪካውያንን በተለይም ጐረቤት አገሮችን በተፈጥሮ ሀብቷ በማስተሳሰር በፍትዊ ተጠቃሚነት አብሮ ማደግ እንደሚቻል ፅኑ አቋም ታራምዳለች።

በሰጥቶ መቀበል መርህ በጋራ ለማደግ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች የምትገኘው አገራች በምናከናውነው የመሰረተ ልማት ዝርጋታም ቀጠናዊ ውህደትን እያፋጠነች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ አፍሪካውያን በአንድ አዳራሽ ተሰባስበው በጋራ እጣፈንታቸው ላይ የሚመክሩበት እና ውሳኔዎችን የሚያሳልፉበት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ( የአሁኑ አፍሪካ ህብረት ) እውን እንዲሆን የላቀ ሚና ተጫውታለች። የህብረቱ አቅም እንዲጠናከርም እንደ አንድ አፍሪካዊት አገር የድርሻዋን እየተወጣች ነው።

በዲፕሎማቶች መቀመጫነት በዓለም በሶስተኛ ደረጃነት የምትገኘው እንደ ስሟ እያበበች የምትገኘው ከተማችን አዲስ አበባም ግዙፉ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪካ ህብረት የሚገኝባት በመሆኗ የአፍሪካ መዲና በመባል ትጠራለች።

ከተማችን በየጊዜው የምታስተናግዳቸው አህጉራዊና ዓለም አቀፍዊ ስብሰባዎች ካለምንም የፀጥታ ችግር በኢትዮጵያዊ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እያስተናገደ የሚገኘው የከተማችን ህዝብም ለአፍሪካዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም አብሮነት መዳበር ድርሻው ላቅ ያለ ነው።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ጊዜ_ደጉ
አጠቃላይ ድምሩ ስንት ይመስላችኋል?

የጥቁር አንበሳ ሆቴል (ኤደን መንገድ) የምግብና መጠጥ ዋጋ ዝርዝር (Menu)- በ1960ዎቹ

Via :- Ethiopian History and Tourism

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ወደ አፍሪካ ኅብረት መዲና እንኳን ደኅና መጣችሁ።

Ethiopia warmly welcomes you to the capital of the African Union!

© Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Sirni Gadaa sirna ittiin bulmaataa karaa diimookraatawaa ta’een gaggeeffamu yoo ta’u, falaasama siyaasni, dinagdeenii fi hawaasummaan ummata Oromoo ittiin murteeffamu, kan hawaasni mirgaa fi dirqama isaa beekee ittiin walii galu akkasumas tokkummaan ittiin waliin jiraatudha.

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ያልተዘመረለት የፎቶ ካሜራ ባለሙያ አቶ #ዳኜ_አበራ 👌

የስራ አጋጣሚዎቹ እና እውነተኛ ትዝታዎቹ 👌👌

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ላለፉት 592 ዓመታት ሳይዛነፍ የቀጠለው የጉጂ አባገዳ የስልጣን ወይም "የባሊ" ርክክብ ሥነ ሥርዓት ለ75ኛ ጊዜ በተለያዩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ኩነቶች እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከትናትናው ዕለት አንስቶ መካሄድ የጀመረው የሥነ ሥርዓቱ ጉባኤ፤ በቀጣዮቹ ቀናት በተለያዩ መርሐ-ግብሮች እና ምርቃቶች መካሄዱን ይቀጥላል፡፡

ከሥልጣን ርክክብ ሥነ-ስርዓቱ እና ሂደቱ በፊት የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ ባህል፣ ማንነት እሴት እና ጥንታዊ እምነት መሰረት ባደረገ መልኩ የተለያዩ ሥርዓቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

ሥነ ሥርዓቶቹ ከተካሄዱ በኋላ ሦስቱ የጉጂ ገዳ የሚባሉት ኡራጋ፣ ማቲ እና ሆኩ በየመንደሮቻቸው ከሥልጣን ሽግግር ሥነ-ሥርዓቱ አስቀድመው ስም የማውጣት ሥነ-ሥርዓቱን ያካሂዳሉ።

ሥልጣኑን የሚረከቡት አባ ገዳ ላለፉት 40 ዓመታት ሂደቶችን ጠብቀው እየተኮተኮቱ የሚዘጋጁ ሲሆን፤ ይህም ከሥልጣን ርክክቡ በኋላ ምንም ዓይነት የአስተዳደር ክፍተት እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡

በጉጂ የአባገዳ የሥልጣን ርክክብ ስነ ስርዓት መሰረት ላለፉት 8 ዓመታት አባገዳ ሆነው ያገለገሉት አባገዳ ጂሎ ማንዶ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ባሊውን ለ75ኛው አባ ጋዳ የሚያስረክቡ ይሆናል፡፡

ይህ ሥርዓት ላለፉት 592 ዓመታት ሳይዛነፍ የቆየ ሲሆን፣ በዚህም 74 አባ ገዳዎች አልፈውበት አሁን ላይ ለ75ኛ ጊዜ የሚካሄድ ነው፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ሕብረ ብሔራዊነት ወንድማማችነትና እህታማችነት ለዘላቂ ሰላም እና ሁላንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ህዝባዊ የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው"።

የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች ከፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በክልሉ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ተግዳሮቶች የሆነባቸው ጉዳዮች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እያደረጉ ነው።

በጅግጅጋ ከተማ ውይይቱን ከሚመሩት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች መካከል የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ፣ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ መለስ አለሙ እና የሱማሌ ብልጽግና ቅ/ጽ/ቤት ኃለፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ናቸው።

በክልሉ ከጅግጅጋ በተጨማሪ በደገህቡር፣ቀብሪደሃር እና ጎዴ ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮቹ እየተካሄዱ ነው ፡፡

የውይይት መድረኩ ምልአተ ህዝቡ ሀገራዊ፣ክልላዊ እና አካባቢያዊ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሰላማዊ ሁኔታን በመረዳት እስካሁን የተመዘገቡት ሁለንተናዊ ድሎች ፀንተዉ እንዲቀጥሉ፤ ከኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል የመነጩ ተግዳሮቶች እና እዳዎቻችን በጋራ ትግል አልባት አንድያገኙ የድርሻዉን አንዲወጣ ለማስቻል ነዉ።

በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው መንግስት በሀገራችን ሥር የሰደዱና የቆዩ ችግሮችን በመቅረፍ ወደ ብልፅግና ማማ ለመሻገር የሚያስችል ትክክለኛ አቅጣጫ ይዞ በመገስገስ ላይ ሲሆን መሰል ህዝባዊ መድረኮች መዘጋጀታቸው ከህብረተሰቡ ጋር ቅርበትን በመፍጠር ውጤታማ የብልፅግና ጉዟችንን ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በምስራቅ ወለጋ ዞን ዋትራና ብርንቃስ ከተሞች ጃኖጉሬ ቀበሌዎች በአሸባሪው የኦነግ ሸኔ ላይ በተወሰደው እርምጃ ቡድኑ ከጥቅም ውጪ መሆኑ ተገለፀ።

ሶስት የቡድኑን አመራሮች ጨምሮ በርካታ የቡድኑ አባላት ሲመቱ የተረፉት በክፍለጦሩ የሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር በምስራቅ ወለጋ ዞን ዋትራና ብርንቃስ ከተሞች በሰራዊታችን ላይ የጥፋት እጁን ለመሰንዘር የሞከረው የአሸባሪው ሸኔ ቡድንን ያልተጠበቀ እርምጃ በመውሰድ እንዲሽመደመድ አድርጎታል።

ክፍለጦሩ በርካታ የሸኔ አባላትን በመምታት የሽብር ቡድኑ ታጥቆት የነበረውን የነፍስ ወከፍ መሳሪያና የወገብ ትጥቅ መማረክ ችሏል።

ሻለቃ ዘመኑ አለባቸው እንደገለፁት የክፍለጦሩ ሰራዊት ምንግዜም ለሚሰጠው ተለዋዋጭ ግዳጅ አፋጣኝ መልስ ለመስጠት ዝግጁ በመሆኑ የሽብር ቡድኑን የጥፋት እንቅስቃሴ በማምከን በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።

በተወሰደው እርምጃም ከሰላሳ በላይ የሽብር ቡድኑ አመራርና አባላት መመታታቸውን የገለፁት ከፍተኛ መኮንኑ አሁንም የክፍለጦሩ ሰራዊት የጀመረውን ስምሪት በማጠናከርና ውጤታማ ግዳጆችን በብቃት በመፈፀም የጀመረውን ድል ያስቀጥላል ብለዋል።

ለስምሪቱ ስኬትም የአካባቢው ህዝብና የሚሊሺያ ሀይሉ ለነበረው ተሳትፎ ማመስገናቸውን ከሀገር መከላከያ ሠዊት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

መራሩ ሃቅ ይኼውልህ ...

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የውይይት መድረኩ ''ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል መሪ ሀሳብ ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የተዘጋጀው የህዝባዊ ውይይቱ የተሰጠውን ትኩረት ከማሳየቱም በላይ የተመዘገቡ ድሎችን በማስቀጠል፣ ተግዳሮቶችን በቀጣይም ለመፍታት የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው።

የውይይት መድረኩ ምዕላተ ህዝቡ ሀገራዊ፣ክልላዊ እና አካባቢያዊ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሰላማዊ ሁኔታን በመረዳት እስካሁን የተመዘገቡት ሁለንተናዊ ድሎች ፀንተዉ እንዲቀጥሉ፤ ከኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል የመነጩ ተግዳሮቶች እና እዳዎቻችን በጋራ ትግል አልባት አንድያገኙ የድርሻዉን አንዲወጣ ለማስቻል ነዉ።

በብልጽግና ፓርቲያችን የሚመራ መንግስት በሀገራችን ሥር የሰደዱና የቆዩ ችግሮችን በመቅረፍ ወደ ብልፅግና ማማ ለመሻገር የሚያስችል ትክክለኛ አቅጣጫ ይዞ በመገስገስ ላይ መሆኑን በመድረኩ ተገልፇል።

በግስጋሴ ሂደቱም አያሌና ውስብስብ በህልውናችን ላይ የተደቀኑ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ፈተናዎችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ባሳለፍናቸው አምስት ተከታታይ የተጋድሎ አመታት የውጭም ሆነ የውስጥ ፈተናዎችን በብቃት መክተን በርካታ ድሎችንም ማስመዝገብ መቻሉን ተጠቁመዋል።

በተለይም ፓርቲያችን ብልፅግና ያሉብንን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ዕዳዎቻችን በመክፈል አገራችንን ወደ ምንዳ ለማሸጋገር በታላቅ ቁርጠኝነት በሰራቸው ስራዎች ለመጭው ትውልድ አሻራ የሚሆኑና ለብልፅግናችን ሁነኛ መሠረት የሚሆኑ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ተመልክተዋል፡፡

ህዝባዊ የውይይት መድረኩ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ ሲሆን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰውና በሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ እንዲሁም በጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን እየተመራ ይገኛል።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ እና አንጎላ በዛሬው ዕለት ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ  እና የአንጎላ አቻቸው ቴቴ አንቶኒዮ ተፈራርመዋል፡፡

በዚህም ሚኒስትሮቹ  አጠቃላይ የትብብር ስምምነት እና የፖለቲካ ምክክር ማድረጊያ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ኀብረት 44ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተፈረመው፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው!!

ፓርቲያችን ብልፅግና የተለያዩ ህዝባዊ መድረኮችን በማዘጋጀት በተለያዩ ጊዜያት ከህዝብ የሚነሱ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው በሰላም በልማት፣ በዴሞክራሲ ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመፍታት ሰፊ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዛሬው እለትም የዚሁ እሳቤ ማስፈፀሚያ የሆነው "ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ 19 መድረኮችን በማዘጋጀት ህዝባዊ የምክክር መድረክ በማካሄድ ላይ እንገኛለን።

በዚህም መሰረት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ "ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ሃሳብ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ህዝባዊ ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንትና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥላሁን ከበደ ሀብት የመፍጠርና የመበልጸግ ጥያቄ የሉዓላዊነት ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ሀብት የመፍጠር ንቅናቄውን ሕዝቡ ሊደግፍ እንደሚገባና ወቅታዊ ችግሮችን በማለፍ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በጋራ መንቀሳቀስ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሀብታሙ ካፍቲን ሰፊ የመልማት ጥያቄዎችን በተለይም በከተሞች ላይ የሚታየውን የመሰረተ ልማት ፍላጎቶችን ለመመለስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በመድረኩ በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ ሰነድ እና በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የተሰሩ የልማት ስራዎች ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ እየተገነቡ የሚገኙት የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ እና ደንቢ ሎጅ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደታቸው ላይ ምልከታ ይደረጋልም ነው የተባለው። የደንቢ ሎጅ ፕሮጀክቶች የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል መሆኑ ይታወቃል።

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

The African Capital City!

Addis Ababa the residence of Africa Union!

The 3rd world's Diplomatic Hub!

አዱ ገነት the vibrant City!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከቱኒዚያ አቻቸው ናቢል አሚር ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስትርቹ እየተካሄደ ካለው 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተወያዩት፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ በሁሉም መድረኮች በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮ-ቱኒዚያ የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ በተቻለ ፍጥነት እንዲደረግ መግባባት ላይ መደረሱም ተጠቁሟል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በመርሕ ላይ ተመሥርቶ የአፍሪካን አጀንዳ በጋራ ማራመድ እንዲቻል መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአፍሪካን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በትምህርት ዘርፍ የሚደረገውን መዋዕለ ንዋይ ማስፋት እንደሚያስፈልግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ።

በ44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ዛሬ በአዲስ አበባ የሕብረቱ ዋና መስሪያ ቤት ተጀምሯል።

በስብሰባው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀስላሴ፣ የአገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና የሕብረቱ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፤ በስብሰባው ላይ አህጉራዊ የማኅበረ-ኢኮኖሚ ግቦችን ለማሳካት ትምህርት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።

አህጉራዊ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ ካልተቻለ የአፍሪካን ሁለንተናዊ ልማት ማሳለጥ እንደሚያስቸግርም አስገንዝበዋል።

በአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ላይ ቀሪ ስራ እንደሚጠይቅ ጠቁመው፤ የአህጉሪቷ መሪዎች በ1960ዎቹ በቅኝ ግዛት የትምህርት ሥርዓት ላይ የሚያነሱት ጥያቄ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

በዓለም የሚከሰቱ ተለዋዋጭ ሁነቶች የተሻለ የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት ለቴክኖሎጂና ፈጠራ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ አመላካች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘመናዊ ግብርና፣ ቴክኖሎጂ፣ የዲጂታል ሥርዓት፣ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ሌሎች የፈጠራ ሥራዎች ለበርካታ የኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ስኬት አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተለይም የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምህንድስና እና ሒሳብ የትምህርት መስኮች ቀጣይነት ያለውና ክህሎት የተላበሰ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝነት እንዳላቸው አብራርተዋል።

በአፍሪካ ያለውን አጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ከቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ጋር አቀናጅቶ ማስተማር ለፈጠራ ሥራ መሰረት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በአፍሪካ ውጤታማ የትምህርት ስርዓትን ተደራሽ በማድረግ ምርታማነትንና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ማደረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ለብዝሃ ኢንዱስትሪላይዜሽንና ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት መመደብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትልምን እውን ለማድረግም በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በፈጠራ የተደገፈ የክህሎት አብዮት ያስፈልገናል ብለዋል።

የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማስፋት ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ብቁ የሰው ሃይል ማፍራት እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel