prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ሱስዋ ናሮክ ወረዳ የሚገኘውን እና ከኢትዮጵያ በኩል ከወላይታ ሶዶ የ500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኃይል መለወጫ ጣቢያ መስመር ማብቂያ የሆነውን የኬትራኮ ኮንቨርተር ስቴሽንን ጎብኝተዋል።›› - ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኦቪድ ግሩፕ 5 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመሸጥ የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ።

ኦቪድ ግሩፕ በመንግስትና የግሉ ዘርፍ አልሚነት ከሚያስገነባቸው ቤቶች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመሸጥ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት አድርጓል::

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ታደሰ እና የሁለቱ ተቋማት የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ከ17 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት በመግለጽ ተቋሙ የሰራተኞቹን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል::

በዚህም አየር መንገዱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ሰራተኞቹ መኖሪያ ቤት የሚያገኙበትን ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሰዋል፡፡

ነገር ግን የሰራተኞቹ የቤት ፍላጎት ሰፊ በመሆኑ ከኦቪድ ግሩፕ ጋር መግባቢያ ስምምነት መፈፀሙን ገልፀዋል::

የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ በበኩላቸው በመንግስትና የግሉ ዘርፍ አልሚነት ኦቪድ ግሩፕ ለመገንባት ካቀዳቸው 60 ሺህ ቤቶች ውስጥ 5 ሺ ቤቶችን ለአየር መንገዱ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ገንብቶ እንደሚያስረክብ ገልፀዋል::
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ወንድሜ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ። ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያካተተው የዛሬው ውይይታችን የቆየውን ትስስራችንን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ቁልፍ የትብብር መስኮችንም የለየ ነበር። የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመስራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል።

I extend my heartfelt gratitude to my brother, President William Ruto, for his gracious welcome to Kenya. Our comprehensive discussions today have not only strengthened our existing ties but also highlighted key areas for future collaboration. As neighbors sharing a unified vision and destiny, our commitment to working together remains steadfast.
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ ‘ሳልሳይ ወያነ ትግራይ’ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. መስጠቱን ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል::

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የዛሬ ጠዋት ውይይት ሰፊ መጠነ ርዕይ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከሶማሌ፣ አፋር፣ ሀረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተደርጓል፡፡ ውይይታችን በልማት፣ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር፡" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሀገር አቀፍ የፍትሕ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፍትሕና የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የፍትሕ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ተሳትፈዋል።

ለአራት ተከታታይ ዙሮች የተካሄዱት የፍትሕ ተቋማት የጋራ መድረኮች ወጥ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጎለብት ማስቻሉም ነው የተነሳው።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው 5ኛው የፍትሕ ተቋማት መድረክ ደግሞ በርካታ ጉዳዮች እንደሚነሱበት ኢዜአ ዘግቧል።

የ2016 ዓ.ም የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ተግባራት፣ ሀገራዊና የክልሎች የተጠቃለለ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስንተባበር ታሪክ ሰርተናል፤ እንሰራለንም!

ከውይይት ይልቅ ጦርነትን የማስቀደምን ኋላቀር አስተሳሰብ ብዙ አገራት ታሪክ አድርገውታል። አንዳንዶች ካሳለፉት ታሪክ ተምረው ሌሎቹ ደግሞ ከሌሎቹ ትምህርት ወስደው ላለመገዳደል ተማምለዋል።

የማሰብና የማሰላሰል ህሊና እያላቸው ከእንስሳት በታች ወርደው ወንድም ወንድሙን በመግደል የሚመፃደቁ፣ መግደል መሸነፍ መሆኑን የማይረዱ ቡድኖች ያሉባቸው አገራት ደግሞ ጦርነትን ታሪክ ማድረግ ባለመቻላቸው ፈራርሰው ታሪክ ሆነዋል።

በየአገሩ ያሉ አሸናፊ ሀሳብ የሌላቸው ጦር ሰባቂዎች ጭምር የሚረዱት እውነታ በንፁሀን መስዋዕትነት ሀብትን የማገባስ ጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ እንጅ ጦርነት ትናንትም ሆነ ዛሬ ነገም ወደፊትም የሚፈታው ችግር አለመኖሩን ነው።

ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ቱባ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የውይይት ባህል ባለመዳበሩ እንጅ በንግግር የማይፈታ አንዳች ችግር አለመኖሩን በመገንዘብ ፓርቲያችን ለትብብርና ለፉክክር ፖለቲካ ይተጋል።

የውይይትን ባህልን ለማዳበር አገር በቀል እውቀቶችን ከዴሞክራሲያዊ መርሆች ጋር በማቀናጀት ለመጠቀም ከሚደረገው ጥረት ባሻገር መሰረቱን ለማፅናት ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኛ ትውልድ የህዝባችንን ህይወት የመቀየር እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ ደረጃ የማሻገር ሀላፊነት ያለበት የተንከባለለ ዕዳ ከፋይ ጭምር ነው።

ብርቱ ስንሆን ኢትዮጵያን ለወዳጅነትና ለሽርክና የሚፈልጋት ብዙ ነው። ስንደክም ግን ደካሞች ጭምር ውክልና ተሰጥቷቸው ይጎነትሏታል።

ዓለም አንድ መንደር በሆነችበትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከሉዓላዊ አገራት የገዘፈ ፈርጣማ ጡንቻ በያዙበት በዚህ ዘመን የውጭ ተፅዕኖ ቀላል ባይሆንም የአገራት አስተማማኝ ሰላም፣ ዕድገትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚወሰነው በውስጥ አቅም ነው።

አገራችን በቅርቡ ገብታበት ከነበረው ውስጣዊ ፈተና እና ውጫዊ ጫና በድል ተሻግራ ብሪክስን ከመሰለ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስብ አባል የሆነችው፣ በቅርቡም ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መረህ ወደብ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ተጨባጭ ጥንካሬዋንና የወደፊት ተስፋዋን አመላካች ነው።

ዲፕሎማሲያችን ወይም አጠቃላይ የውጭ ግንኙነታችን ውስጣችን ሲደክም የሚዳከም ስንጠነክር ደግሞ የሚጠነክር በመሆኑ ቁልፉ በጃችን ነው።

ያለችን አንዲት አገር ናት፤ አንድ አይን ያለው በአፈር አይጫወትም እንዲሉ አበው መቼም ይሁን የትም ማንም ኢትዮጵያን ለድርድር ማቅረብ አይገባም። ሲመቸን የምንወዳት ሳይመቸን የምንረግማት ሳይሆን የከፍታዋም የዝቅታዋም ምክንያት እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ድህነቷን ቀርፈን ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ታሪካዊ አሻራችንን እናሳርፍ!


https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመዲናችን አዲስ አበባ አስደማሚ የምሽት ገፅታ፤

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሒማሊያ ተራራ ላይ አጥንት የሚሰብረውን ቅዝቃዜ እንዲህ የሚዳፈር አይጠፋም።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#በአንድነት ወደ ብልግና ማማ እንደርሳለን !!
ታላቋን ኢትዮጵያ እንደ ስሟ በሁሉም መስኮች ታላቅ የማድረጉ ጥረት የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን አስተዋጽኦ ይጠይቃል።
@AbiyAhmedAli

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በትላንትናው ዕለት በኔዘርላንድስ ፤ ሄግ ከተማ የኤርትራን መንግሥት በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ኤርትራውያን ቡድኖች መካከል በተከሰተ ግጭት የፖሊስ ተሽከርካሪዎች በእሳት ጋይተዋል።

የኔዘርላንድስ ፖሊስ ግጭቱን ለመቆጣጠር ሲል አስለቃሽ ጋዝ ለመጠቀም ተገዷል። የኔዘርላንድ ፖሊስ መኪኖችም መቃጠላቸው ተነግሯል።

የአይን እማኞች ግጭቱ በተካሄደበት ስፍራ በርካታ ሰዎች በጎዳና ላይ እንደነበሩ ፤ አንዳንዶች ድንጋይ ሲወረውሩ እንደነበር ፤ በእሳት የተያያዙ መኪኖችም መመልከታቸውን ታናግረዋል።

በግጭቱ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም።

የሄግ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ግጭቱ የተከሰተው የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች ስብሰባ እያካሄዱ ሳለ ተቃዋሚዎች ወደ ስብሰባው ስፍራ በመሄድ ጥቃት በመፈጸማቸው ነው።

ሁኔታው አሳሳቢ ሆኖ ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን የገለፀው ማዘጋጃ ቤቱ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል።

መሰል ግጭት ከዚህ ቀደምም በኤርትራውያን መካከል አውሮፓ ውስጥ መከሰቱ የሚዘነጋ አይደለም።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሳምንቱ የተከናወኑ አበይት ወታደራዊ ዜናዎች 👇

👉 የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከጣሊያን መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር  ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉት ባሳለፍነው ሳምንት ነው ።

በውይይቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጣሊያን እና ኢትዮጵያ የቆየና የተሻለ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀው የጣሊያን ካምፓኒዎች በእኛ አገር ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጨምሮ በበርካታ የልማት ስራዎች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ ብለዋል።

ውይይቱ ፍሬያማ እንደነበር የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ከዚህ በፊትም ከጣሊያን ጋር በስልጠና እና በሌሎች ዘርፎች በጋራ የሚሰሩ ስራዎች እንደነበሩ ጠቁመው በአካባቢያዊ  ፀጥታ እና በወታደራዊ ስልጠና አብረን ለመስራት ተስማምተናል ሲሉም ተናግረዋል።

የጣሊያን መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ በበኩላቸው በተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተሞክሮ መውሰድ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

የጣሊያን መከላከያ ኤታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ በቀጣይ ከኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት ጋር የሳይበር ደህንነትን ጨምሮ በሌሎች ወታደራዊ ጉዳዮች በጋራ እንሰራለን  ብለዋል።

👉  የጎጃም ኮማንድ ፖስት ዘወትር የሚፈለገውን ሰላም ለማምጣት ተልዕኮውን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሊ ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ የተናገሩት እየተገባደደ ባለው ሳምንት ነው።

በውይይቱ የምስራቅ ዕዝ አዛዥና የጎጃም ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ፣ ዕዙ በሶማሌ ክልል፣  በምስራቅ ሀረርጌና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች በተጨማሪ በሶማሊያ ምስራቅ አፍሪካን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚንቀሳቀሰውን አልሸባብ በመዋጋት እንዲሁም በአማራ ክልል በህዝብ አጀንዳ ስም ለዘረፋ የተደራጀና ክልሉን ለመበተን ሲንቀሳቀስ የነበረውን ፅንፈኛ ቡድን የማፅዳትና ክልሉን የማዳን ተልዕኮ በስኬት መፈፀሙን ገልፀዋል።

ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ዕዙ በሁሉም ግዳጆች  የሠላም ጠል ሃይሎችን ሴራ በማጋለጥ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ህዝቡ ከወገን ሀይል ጎን እንዲሰለፍ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል።

👉 ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የዕዙን ግዳጅ አፈፃፀም አስመልክተው ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደሰጉት ባሳለፍነው ሳምንት ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ ፍላጎታቸውን በኃይል ለማሳካት የሚጥሩ የውስጥም ሆነ የወጪ የጥፋት ኃይሎችን መቼም ቢሆን መታገስ አያሥፈልግም ብለዋል።

ዕዙ ለኢትዮጵያ ሠላም ዛሬም እንደትላንቱ በፅናት ዘብ ቆሟል ያሉት  አዛዡ በከሃዲያን የሚፈፀምበትን የውስጥ ጥቃት አምክኗል፤ የኢትዮጵያን ድንበር ሳያስደፍር ዘርፈ ብዙ ግዳጆችን ተቀብሎ በአስተማማኝ ብቃት ተልዕኮውን ፈፅሟል ብለዋል።

እኛ የኢትዮጵያ ሠራዊት ነን፤ተልዕኳችንም ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ መጠበቅ እንዲሁም የህዝባችንን ሰላምና ደኀንነት ማረጋገጥ  ነው ያሉት ሌተኔል ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ  ፅንፈኛውና ዘራፊው ቡድን በአማራ ክልል መንግስትና ህዝብ ላይ  አሳካዋለሁ ብሎ የወጠነው የጥፋት ህልም በሠራዊታችን ቆራጥ ተጋድሎ መክኗልም ነው ያሉት።

👉  በተቋሙ ላይ የስም ማጥፋትና አሉባልታ የወሬ ዘመቻ በመክፈት ሰራዊቱን በመበተን ሀገር የማፈራረስ አላማ አንግበው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የጥፋት ሀይሎች ሴራ በአመራሩ ያላሰለሰ ጥረት ማምከን መቻሉን የማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ የገለፁት በዚሁ ሳምንት ነው።

ለሰራዊታችን ጥንካሬ እና ፅናት ህገ-መንግስቱን መሰረት ያደረገ የግንባታ አቅጣጫ መጠቀም ስለተቻለ ነው ያሉት ዋና አዛዡ ሰራዊቱ በሀገሪቱ የሚካሄዱ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያላቸው ጉዳዮች ሰላማዊ እና ሀገርን አደጋ ላይ በማይጥል በሀገሪቷ የህግ አግባብ እንዲፈቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ከተገነባበት ዓላማ በማይጋጭ አፈፃፀም ከሀሜትና ከአሉቧልታ በራቀ አካሄድ የሚሰራ ህዝባዊ ሰራዊት ነው ብለዋል።

👉  በሬጅመንቶች የሥልጠና ማጠናቀቂያ የተገኙች የደቡብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ዕዙ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች አኩሪ ታሪክ በመስራት የሃገራችንን ሰላም በማረጋገጥ ህዝቦች ሰላምና ልማትን እንዲያፋጥኑ በማድረግ ረገድ ጠንካራ ስራ እየተሰራ መገኘቱን ገልፀዋል።

ሠራዊቱ ህዝባዊነቱን ጠብቆ ሚዛናዊ የሆኑ ተልእኮዎችን እየተወጣ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ተግባሩ ያልተዋጠላቸው ፅንፈኛ ሃይሎች የሰራዊታችንን ስም በማጠልሸት በማህበራዊ ሚዲያ የተለያዩ ተግባራትን ቢፈፅሙም ሰራዊታችን ግን በፀና አለት ላይ የተገነባ በመሆኑ ተልዕኮውን በድል እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮሩ እየተዋጋ እየሰለጠነ ይገኛል በአሁኑ ወቅት አለማችን በሽብርተኝነትና በፅንፈኝነት ተወጥራ ትገኛለች ይህ ወቅቱ የፈጠረው ፅንፍ በሃገራችንም ተከስቷል ይህን ፅንፈኝነት ለማክሸፋ መሰልጠን መዘጋጀት ስላለብን ኮሩ በስልጠና ራሱን እያበቃ በመሆኑ ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።

👉   የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት በመከላከያ መኮንኖች ክበብ አውደ ጥናት ያዘጋጀው በተገባደደው ሳምንት ነው።

በዐውደ ጥናቱ ማጠቃለያ የተገኙት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ ሃላፊ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጅ ለመታጠቅና በአለማችን ላይ የሚስተዋለውን የሳይበር  ጥቃት ለመከላከል በጥናት ላይ የተመሠረተ ውይይት ማድረግ አሥፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በተደራጀ አግባብ በአጭር በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሥልጠና ራስን ማብቃት የሚያሥችል መነሻና መድረሻ ያለው ዕቅድ ከነ ችግር ፈችነቱ በማዘጋጀት ብሎም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ሃሳብ በመለዋወጥ እንደ ተቋም ብሎም እንደ ሀገር የሳይበር ደህንነት ስጋትን ማሥቀረት እንደሚቻል አመላክተዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ከዐውደ ጥናቱ የሳይበር ደህንነትን መጠበቅና መከላከል ብሎም የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትን ማሥቀረት የሚያሥችል ግብዓት መሠብሠብ መቻሉን ገልፀዋል።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከእሱ ኡፍ 🤫 ማለቴ ኡቭ 😉 ብሎ መውደቅ፣ የእሷ ግልምጫ 😁😁😁 ምን እሼ ነው ግን 🙃🙃🙃

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው የአረንጓዴ ልማት መርሀ-ግብር ለሌሎች አገራት ትምህርት የሚሆን ነው ሲሉ የፖርቱጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ገለጹ።

የፖርቱጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ከቀናት በፊት የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት የኢትዮ-ፖርቱጋል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ ነው ብለዋል።

የሁለቱን አገራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ፖርቱጋል ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በኢኮኖሚውና በአራንጓዴ አሻራ ስራ እያከናወነች ያለችው ስራ ዓለማቀፍ ትኩረትን እየሳበና የሚደነቅ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአረንጓዴ አሻራ የልማት መርሃ ግብር እያከናወነች የሚገኘው ሰፊ ተግባርም ለታዳሽ ኃይል ልማት የሰጠችውን ትኩረት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ለሌሎች አገራትም ኢትዮጵያ እያካሄደች የምትገኘው ውጤታማ የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር ትምህርት ሊወስዱ እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

ፖርቱጋልና ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል፣ በአረንጓዴ እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የልማት መስኮች በጋራ በመስራት ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ፖርቱጋል በህዝብ አስተዳደር፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ሌሎች መስኮች የሚሰሩ በርካታ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ይደረጋል ብለዋል።

የሁለቱን አገራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ፖርቱጋል ቁርጠኛ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ለአብነትም ከኢትዮጵያ አቻቸው ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር የሁለቱን አገራት የቆየ ዲፖሎማሲያዊ ወዳጅነት አጠናክሮ ማስቀጠል የሚስችል ፍሬያማ ውይይት በማድረግ ከስምምነት መድረሳቸውን ተናግረዋል።

በውይይታቸውም በአገራቱ የትብብር ፍኖተ ካርታ መነሻነት ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በሚያጠናክሩ 'ቢዝነስ ፎረሞች' ላይ በጋራ ለመስራት እንደተስማሙም አንስተዋል።

ከቀናት በፊት የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከፖርቱጋል አቻቸው ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል።

የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች የትብብር መስኮች በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ይታወቃል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼም ምንዳን አወርሳለሁ!

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሴት አመራሮችና ሰራተኞች የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼም ምንዳን አወርሳለሁ በሚል መሪ ቃል የጋራ ምክክር መድረክ አካሄዱ፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የፌደራል የሴቶች ከፍተኛ አመራር ወ/ሮ መስከረም አበበ በበኩላቸው ሴቶች ሰላምን ከማስጠበቅ አንፃር ያለንን ጠንካራ ሚና ተገንዝበን በተደራጀ መልኩ ልንሰራ እንደሚገባ እንዲሁም ሴቶች ሰላምን ማስጠበቅ የሚችሉት በቅድሚያ የራሳቸውን ጤና ሲጠብቁ መሆኑን ገልፀው በተለይም የማህፀን በር ካንሰር ምርምር እንዲያደርጉ እራሳቸውን ከማህፀን በር ካንሰር በሽታ እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ደም ልገሳ በማድረግ ለሌሎች ወገኖች ያላቸውን ድጋፍ ሊያሳዩ እንደሚገባ እና በቀጣይም የሀገር አርማ የሆነውን የህዳሴው ግድብ የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩ ባሉበት ሁኔታ ላይ እኛ ሴቶች ድጋፋችንን አጠናክረን የምንቀጥልበትን ስራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አክለዋል፡፡

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒሰቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ ሴቶች ሰላምን ለማስጠበቅ ያላቸው ድርሻ የጎላ መሆኑን ይህም የሚመነጨው ሴቶች የቤተሰብ መሰረት ከመሆናቸው ጋር የሚያያዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሴቶች የሰላም እሴቶችን በልጆቻቸው እና በአካባቢያቸው ላይ የማስረፅ ሚናቸውን ተረድተው ተግባራቸውን ተፅእኖ በሚፈጥር ደረጃ ለማሳካት እንዲችሉ በተደራጀ ሁኔታ መስራት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ፣ የድል ምልክትና የኩራታችን መገለጫ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጋዜጠኞች ገለጹ።

የአድዋ ድል አፍሪካውያን በነጮች የበላይነት በቅኝ ግዛት ይረገጡበት የነበረውን የግፍ ስርአት ታግሎ በማሸነፍ ለመላ ጥቁር ህዝቦች ነፃነትን ያወጀ ታላቅ ታሪካዊ ሁነት ነው።

ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ለቅኝ ገዥዎች አንበረከክም በማለት በዱር በገደሉ ተዋግተው በማሸነፍ ለአፍሪካዊያን የነፃነት ፋና ወጊ መሆንም ችለዋል።

በዚህም አድዋ አፍሪካዊያን በትግላቸው ነፃነታቸውን እንዲያረጋግጡ የድል አድራጊነት መነሻ በመሆን የመላ ጥቁር ህዝቦች የድል ተምሳሌት ተደርጎም ይወሰዳል።

የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጀግኖች ለነፃነታቸው ተዋግተው ያሸነፉበት ታሪካዊ እለት ሆኖ እየተከበረ እስካሁንም ዘልቋል።

የአድዋን ድል በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የጋና፣ ኒጀርና ሴኔጋል ጋዜጠኞች የአድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ፣ የድል ምልክትና የኩራታችን መገለጫ ነው ብለዋል።

በጋና ጆይ ኒውስ ቲቪ የውጭ ጉዳዮች ዘጋቢ ጋዜጠኛ ብለስድ ሶጋህ፤ የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የጀግንነት ማሳያና የአህጉሪቷ የነፃነት ብስራት መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም የአድዋ ድልን የጥንካሬና የይቻላል ስነ-ልቦና በመሰነቅ የሁላችንም ችግር የሆነውን ድህነት በጋራ መዋጋት አለብን ብሏል።

የኒጀሯ ጋዜጠኛ፣ የፊልም ዳይሬክተርና ኤዲተር ራህማቱ ኬይታ፤ የአድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ፣ የድል ምልክትና የኩራታችን መገለጫ ነው ብላለች።

የአድዋ ድል የቅኝ ግዛትንና ጭቆናን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሸነፍ ያስቻለ፤ የመላ አፍሪካውያን የድል ተምሳሌት ስለመሆኑም አንስታለች።

ሴኔጋላዊው ጋዜጠኛ የአፍሪካ 24 ሚዲያ ማናጀር አሊ ጉይንዶ፤ የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን በጀግንነት ታሪክ የሰሩበት የሁላችንም የጋራ ታሪክና የነፃነታችን አርማ ነው ብሏል።

የጋና ጆይ ኒውስ ቲቪ የውጭ ጉዳዮች ዘጋቢ ጋዜጠኛ ብለስድ ሶጋህ፤ የአፍሪካን አንድነት እውን በማድረግና ለነፃነት ግንባር ቀደም ትግል በማድረግ የኢትዮጵያ ሚና በታሪክ ሲወሳ የሚኖር መሆኑን ገልፃል።

ኢትዮጵያ አሁንም የአፍሪካን አንድነት፣ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ ፓን አፍሪካ ሚዲያ መፍጠር ያስፈልጋል የሚል አቋም ይዛ እየሰራች መሆኑ ይታወቃል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ ከዓረብ ኤሚሬቶች እና ከእንግሊዝ ንግድ ሚኒስትር ዴኤታዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ውይይቱ በአቡዳቢ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

በዚህ መሰረትም ልዑካኑ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የንግድ ሚኒስትር ዴዔታ ታኒ ቢን አህመድ አል ዘዩዲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት መስፈርቶችን ለማጠናቀቅ እያደረገች ያለውን ጥረት እና ሒደቱ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል::

በተመሳሳይ የኢትዮጵያልዑክ ከእንግሊዝ የንግድ ፖሊሲ ሚኒስትር ዴዔታ፣ የፓርላማ አባል እና የለንደን ሚኒስትር ግሬግ ዊሊያምስ ሃድስ ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱም የእንግሊዝ ልዑካን ቡድን አባላት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት ለማጠናቀቅ ለጀመረችው ጥረት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

እንግሊዝ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን ጥረት እና የእስካሁኑን ጉዞ ማድነቃቸውም ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ካላት ጉልህ የገበያ ስፋትና ኢኮኖሚ አንፃር የዓለም ንግድ ድርጅትን መቀላቀሏ ለራሷም ሆነ ለሌሎች አባል ሀገራት ሁለንተናዊ ጥቅም እንዳለውም አፅንኦት ሰጥተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስንተባበር ታሪክ ሰርተናል፤ እንሰራለንም!

ከውይይት ይልቅ ጦርነትን የማስቀደምን ኋላቀር አስተሳሰብ ብዙ አገራት ታሪክ አድርገውታል። አንዳንዶች ካሳለፉት ታሪክ ተምረው ሌሎቹ ደግሞ ከሌሎቹ ትምህርት ወስደው ላለመገዳደል ተማምለዋል።

የማሰብና የማሰላሰል ህሊና እያላቸው ከእንስሳት በታች ወርደው ወንድም ወንድሙን በመግደል የሚመፃደቁ፣ መግደል መሸነፍ መሆኑን የማይረዱ ቡድኖች ያሉባቸው አገራት ደግሞ ጦርነትን ታሪክ ማድረግ ባለመቻላቸው ፈራርሰው ታሪክ ሆነዋል።

በየአገሩ ያሉ አሸናፊ ሀሳብ የሌላቸው ጦር ሰባቂዎች ጭምር የሚረዱት እውነታ በንፁሀን መስዋዕትነት ሀብትን የማገባስ ጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ እንጅ ጦርነት ትናንትም ሆነ ዛሬ ነገም ወደፊትም የሚፈታው ችግር አለመኖሩን ነው።

ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ቱባ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የውይይት ባህል ባለመዳበሩ እንጅ በንግግር የማይፈታ አንዳች ችግር አለመኖሩን በመገንዘብ ፓርቲያችን ለትብብርና ለፉክክር ፖለቲካ ይተጋል።

የውይይትን ባህልን ለማዳበር አገር በቀል እውቀቶችን ከዴሞክራሲያዊ መርሆች ጋር በማቀናጀት ለመጠቀም ከሚደረገው ጥረት ባሻገር መሰረቱን ለማፅናት ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኛ ትውልድ የህዝባችንን ህይወት የመቀየር እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ ደረጃ የማሻገር ሀላፊነት ያለበት የተንከባለለ ዕዳ ከፋይ ጭምር ነው።

ብርቱ ስንሆን ኢትዮጵያን ለወዳጅነትና ለሽርክና የሚፈልጋት ብዙ ነው። ስንደክም ግን ደካሞች ጭምር ውክልና ተሰጥቷቸው ይጎነትሏታል።

ዓለም አንድ መንደር በሆነችበትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከሉዓላዊ አገራት የገዘፈ ፈርጣማ ጡንቻ በያዙበት በዚህ ዘመን የውጭ ተፅዕኖ ቀላል ባይሆንም የአገራት አስተማማኝ ሰላም፣ ዕድገትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚወሰነው በውስጥ አቅም ነው።

አገራችን በቅርቡ ገብታበት ከነበረው ውስጣዊ ፈተና እና ውጫዊ ጫና በድል ተሻግራ ብሪክስን ከመሰለ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስብ አባል የሆነችው፣ በቅርቡም ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ወደብ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ተጨባጭ ጥንካሬዋንና የወደፊት ተስፋዋን አመላካች ነው።

ዲፕሎማሲያችን ወይም አጠቃላይ የውጭ ግንኙነታችን ውስጣችን ሲደክም የሚዳከም ስንጠነክር ደግሞ የሚጠነክር በመሆኑ ቁልፉ በእጃችን ነው።

ያለችን አንዲት አገር ናት፤ አንድ አይን ያለው በአፈር አይጫወትም እንዲሉ አበው መቼም ይሁን የትም ማንም ኢትዮጵያን ለድርድር ማቅረብ አይገባም። ሲመቸን የምንወዳት ሳይመቸን የምንረግማት ሳይሆን የከፍታዋም የዝቅታዋም ምክንያት እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ድህነቷን ቀርፈን ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ታሪካዊ አሻራችንን እናሳርፍ!

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአዲስ አበባ አዲስ ገፅታ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በቂርቆስ የተገነባው #የቂርቆስ_ፓርክ ለእኛ ለአዛውንቶች እንደ ካንጋሮ ፍራሽ ተመችቶናል፣ማረፊያም ሆኖናል" በፓርኩ ሲዝናኑ ያገኘናቸው #አዛውንቶች ምስክርነት

የኢፊዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተሰሩ የሰው ተኮር ተግባራትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ትኩረት ከሰጡባቸው ስራዎች አንዱ በ4 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈውና ከ150 በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረው #የቂርቆስ_ፓርክ ዋናው ነበር።

ፓርኩ ከፈጠረው የስራ እድል ባለፈ ዛሬ ላይ የወጣቱ ፣የሴቱ፣ የህፃናቱ ፣ የአዛውንቱና የአካል ጉዳተኛው የመዝናኛ ማዕከልም ሆኗል።

ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የክልልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በጉብኝታቸው ወቅት ያረጋገጡት ይህንኑ ነው።

በስፍራው በመዝናናት ላይ የነበሩ አዛውንቶችን በጎበኙ ወቅት የተሰጣቸው ምስክርነትም ይሄው ነው።

ቂርቆስ_ፓርክ ለእኛ ለአዛውንቶች እንደ ካንጋሮ ፍራሽ ተመችቶናል፣ማረፊያም ሆኖናል፣ ጡረታዎች እንገናኝበታለን ፣ እንመካከርበታለን ፣አረፍም ብለን አዕምሯችንን አድሰን ወደቤታችን እንመለሳለን ። ለኛ ከዚህ በላይ ስጦታ የለምና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን እናመሰግናለን ብለዋል።

በየአካባቢው እንዲህ ዓይነት ተግባራት እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

ቂርቆስ ሚዲያም እንዲህ ዓይነት ተግባራት የህዝቡን ጥያቄ የሚፈቱ ናቸውና ተጠናክረው ይቀጥሉ ይላል።

መልካም ውሎ ይሁንላችሁ!

© ቂርቆስ ኮሙኒኬሽን/Kirkos Communication

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እንሰሳትም ለካ ወዳጃቸው ሲሞትባቸው እንደ ሰው ያለቅሳሉ


ኮዋላ የተባለው እና በአውስትራሊያ የሚገኘው  ድብ የሚመስል አጥቢ እንሰሳ ሴት ጓደኛው  ስትሞትበት እንዲህ ሲያለቅስ በዚህ ቪዲዮ ላይ ይታያል።


https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመዲናችን አዲስ አበባ አስደማሚ የምሽት ገፅታ፤

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

© @AbiyAhmedAli (phd)

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ፈራችሁም አልፈራችሁም . . .

በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደገሰገሱት ሃገራት በእኛም ሃገር ጥርት ያሉ ጥናቶች እየተዘጋጁ የሚቀርብልን ሁኔታ እያደገ እንደሚሄድ ተስፋ በማድረግ፣ እስከዚያው ግን በጥናታዊ አቅርቦት ከበለጸጉት ሃገሮች አንዳንድ መረጃዎችን በመበደር ለእንቆቅልሾቻችን መፍቻ መፈለጋችንን እንቀጥላለን፡፡

እንደምሳሌ ለመውሰድ፣ በአሜሪካን ሃገር ውስጥ በተደረገው አንድ ጥናት (የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ውጤቶችን የማንጸባረቃቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ) የሚከተለውን የፍርሃትን ገጽታ ከሃገራችን አውድ አንጻር እንድንመለከተው የሚያደርገንን መረጃ እናገኛለን፡፡

• ስልሳ በመቶው (60%) የምንፈራቸው ነገሮች ፈጽሞ ወደመሆን አይመጡም፡፡

• ሰላሳ በመቶው (30%) ከዚህ በፊት ፈርተናቸው የደረሱብን ሁኔታዎች ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ከመሆን የማንቀይራቸው ነገሮች ናቸው፡፡

• ዘጠና በመቶው (90%) የምንፈራቸው ነገሮች ቢደርሱም ሆነ ባይደርሱ ብዙም የማይነኩንና አናሳ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

• ሰማኒያ ስምንት በመቶው (88%) ከጤንነታችን ጋር በተያያዘ ሁኔታ ይደርስብናል ብለን የምንፈራቸው ሁኔታዎች በፍጹም የማይደርሱብን ሁኔታዎች ናቸው፡፡

በዚህ ዓለም ላይ ምንም ሳይፈራ የሚኖር ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ነገር ግን የፍርሃትን እውነታ በመቀበል፣ ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ምንም ለውጥ ስለማናመጣባቸው ነገሮች መፍራትን በማቆም፣ የፍርሃትን ስሜት ለጥቅማችን በማዋል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ሕይወትን ቀና ብሎ በማጣጣም መኖር ፍርሃትን ያሸነፉ ሰዎች ልምምድ እንደሆነ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡

ፈራችሁም አልፈራችሁም . . . ወደፊት!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በመላው የክልሉ አካባቢዎች በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር በክልሉ የገጠሙ ቁልፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ ውይይት አድርገናል።
በቀረቡ በርካታ ጉዳዮች ላይ ምላሽ በመስጠት ለጋራ አላማ የጋራ ጥረት የማድረግን አስፈላጊነት በአፅንዖት አንስተናል።

Following region-wide discussions held in the Amhara Region, led by PP Executive Members, I have convened representatives from all zones of the region this morning to address critical current issues facing the region. Providing responses on a number of issues, we have underscored the importance of uniting efforts for a common purpose.

© ዶ/ር ዐብይ አህመድ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የእርስ በእርስ የስልጣን ሽኩቻ የገባው ትግል

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ግልፅ ምስክርነት

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ ለልዑካን ቡድኑ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ሂደት ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም የሽግግር ፍትህ እና ብሔራዊ ምክክር ሂደት ዝግጅቶች ያሉበትን ደረጃም አብራርተዋል።

በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በምስራቅ ጉጂ ዞን የኦነግ ሸኔ ሎጂስቲክስ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የነበረው ገመዳ ዱጎ ወይም በቅጽል ስሙ ሎንግ እጁን ሠጠ።

በምስራቅ ጉጂ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ በነበረው የሸኔ ቡድን ላይ ሠራዊቱ እየወሰደ በሚገኘው የተቀናጀ ወታደራዊ እርምጃ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እጃቸውን እየሰጡ እንደሚገኙ የክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ገብሬ ጋሞ ገለፀዋል።

ሰራዊቱ በሳባቦሩና ዳዋ በሚባሉ አካባቢዎች በጠላት ላይ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን ነው የተናገሩት፡፡

የሰራዊቱን ብርቱ ክንድ መቋቋም ያቃተው የቡድኑ ታጣቂ ላይ ተፅዕኖ መፍጠር በመቻሉ በምስራቅ ጉጂ ዞን የሸኔ ሎጂስቲክስ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የሆነው ገመዳ ዱጎ ወይም ሎንግ በሚል ቅፅል ስሙ የሚታወቀው የቡድኑ አመራር ለሰራዊቱ እጁን ሰጥቷል ብለዋል።

ሰራዊቱ አስቸጋሪና ፈታኝ በሆኑ መልክዓ ምድሮች ላይ ግዳጁን በብቃት ከመወጣቱም ባሻገር የቡድኑን እኩይ አላማ በመበጣጠስ እና ጠላትን እፎይታ በመንሳት ተገደው እጃቸውን እንዲሰጡ እየተደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ለሰራዊቱ እጁን የሰጠውና በጉጂ ዞን የሸኔ ሎጂስቲክስና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የነበረው ገመዳ ዱጎ ምንም ዓላማ በሌለው እና ሕዝብን በሚጎዳ ተግባር ላይ መሳተፉ ምንም ጥቅም የሌለው መሆኑን ተናግሯል፡፡

ያለምንም ትርጉም ሕዝብን መበደል እንደማያዋጣ በማመን ለሰራዊቱ እጁን እንደሰጠም ነው ያስረዳው፡፡

ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ የሽብር ቡድኑን እንደተቀላቀለ የሚናገረው የቡድኑ ከፍተኛ አመራር ላለፉት በርካታ ዓመታት ህዝብን በማሰቃየትና በመዝረፍ ላይ የተሰማራው ሸኔ በሰራዊቱ በተወሰደበት እርምጃ እየተበታተነ እና አመራሩም ጭምር በሃሳብ እየተፈረካከሰ እንደሚገኝ አብራርቷል።

ቡድኑ አሁን ላይ ህዝብን ከመዝረፍ ውጪ ምንም ዓላማ ስለሌለው እጁን እንደሰጠ መጥቀሱንም የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

በየጫካው ተበታትነው የሚገኙ ርዝራዥ የቡድኑ ታጣቂዎች ለሰራዊቱ እጃቸውን በመስጠት ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው ሊመለሱ እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel