prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት እንዲኖር ማድረግ ለዘላቂ ሰላም መሠረት መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ለሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮችና ሚኒስትሮች በተዘጋጀው መድረክ ላይ እንዳሉት÷ ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ለፌዴራል ሥርዓት መጠናከርና ውጤታማነት እንዲሁም ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ የጎላ ነው፡፡

በክልሎች መካከል ያለው ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ግልጽ በሆነ የአሠራር ሥርዓትና አሳታፊነት መመራቱ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት የሚያረጋግጥ፣ የሕዝቦችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እውን መሆን በር የሚከፍትና በሕዝቦች መካከል መተማመንን የሚፈጥር እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ባለመኖሩ በሕዝቦች መካከል የተፈጠረው አለመተማመን የግጭት መነሻ ሆኖ እንደቆየ አስታውሰዋል፡፡

አቶ አገኘሁ ለውጡን ተከትሎ ግልጽ የአሠራር ሥርዓት ተግባራዊ በመሆኑና በክልሎች መካከል የነበረውን ቅሬታና አለመተማመን ማስወገድ ተችሏል ብለዋል፡፡

ክልሎች የገቢ ምንጫቸውን አሟጠው በመጠቀምና የወጪ ቅነሳ ሥርዓትን በመከተል ውጤታማ የሀብት ክፍፍል ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡

በፌዴራል ደረጃ በመሠረተ ልማት ዘርፉ ላይ የሚሠሩ ተቋማትም በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር የተዘረጋውን ግልጽ፣ አሳታፊና ፍትሐዊ የአሠራር ሥርዓት (ደንብ) በጥብቅ ዲስፕሊን ሥራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝቦች እኩልነትና በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር ለማድረግ እንዲቻል በክልሎች መካከል እኩል የመልማት እድል እና የተመጣጠነ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል የፌዴራል የመሠረተ ልማት አውታሮች ሥርጭት ፍትሐዊነትን እንደሚከታተልም መገለጹንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አራት ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሞባይል ስልኮችን መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀል ምርመራ ቲም ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አሰፋ ጎንፋ እንደገለጹት፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድረውን የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ብሏል ፓሊስ።

ፓሊስ ለህገወጥ ንግድ መበራከት ምክንያት የሆነውን የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል ባደረገው ክትትል ህጋዊነትን ባልጠበቀ መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የዋጋ ግምታቸው አራት ሚሊዮን ብር የሚያወጡ አንድ ሺህ 535 የተለያየ አይነት ሞባይል ስልኮችን በክትትል ብርበራ መያዙን አስታውቋል።

በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያለውን የንግድ ቤት ባለቤት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ እያጣራ አንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሶማሌ ክልል ለሚገነባው የጅግጅጋ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተቀመጠ።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን÷ በአመት አንድ ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ተገልጿል።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የትምህርት ቤቱ ግንባታ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የጎላ አስተዋፆ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የሚገነባው የጅግጅጋ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ህዝባችንን አስተባብረን በአሻራችን ታሪክ መስራታችንን እናጠናክራለን!

ፓርቲያችን እና መንግስታችን የህዝባችንን ጥያቄዎች ቀረብ ብሎ የማድመጥ ባህላቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎለበቱ ቀጥለዋል::

የህዝባችንን ጥያቄዎች የዕቅዶቻችን አካል በማድረግም ለጋራ ስኬት ተቀናጅተን እየተረባረብን እንገኛለን።

ምን ሰርተን ምን አጎደልን የሚለውን ከህዝባችን ጋር እንገመግማለን። ለአብነትም በያዝነው የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ የከተማ አሰተዳደሩ ባለፈው ዓመት ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች አፈፃፀም በተመለከተ በሁሉም ክ/ከተሞች ህዝባዊ ውይይቶች ተደርገዋል።

በብሎክ ደረጃ ጭምር በተለያዩ የልማት እና የሰላም ጉዳዮች ላይ ከህዝባችን ጋር መክረናል።

በቅርቡም ከፌዴራል እና ከክልሎች የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ከከተማች ህዝብ ጋር ውጤታ ውይይት አድርገዋል።

በህዝባዊ ውይይቶች በቀጣይ የመደበኛው ዕቅድ አካል የሚሆኑና የጋራ ርብረብ የሚደረግባቸው በርካታ ግብአቶችም ተገኝተዋል።

ህዝባችን የተሰሩትን አድንቆ ያልሰራናቸውን ደግሞ ለምን እንዳላከናወናቸው ጠይቆ በመፍትሄዎቹ ላይም የጋራ ግንዛቤ ይዘናል።

ባለፉት ወራት በልማትና በሰላም ስራዎቻችን ከጎናችን ተሰልፎ ለተመዘገቡ ስኬቶች የጐላ አሻራውን እንዳሳረፈ ሁሉ በቀጣይም ከከተማ አሰተዳደሩ ጐን ሆኖ የድርሻውን እንደሚወጣ ህዝባችን በተግባር ጭምር እያረጋገጠ ይገኛል።

ፓርቲያችን ቀይ መስመር ብሎ የለያቸውን ብልሹ አሰራሮችንና ሌብነትን ከመታገል አንፃርም ህዝባችንን በማሳተፍ የጀማመርናቸው ጥቆማን የመሳሰሉ አበረታች ስራዎች መኖራቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሰላማችንን አስጠብቆ ከማስቀጠል አንፃርም የከተማችን ህዝብ ውጤታማ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም ህዝባዊ በዓላቶቻችን ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን በሚያጠናክር እንዲሁም የከተማችንን የቱሪስት ፍሰት በሚያሳድግ መልኩ በሰላምና በፍቅር እንዲከበሩ ከፀጥታ ሀይላችን ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ሰርቷል። የሰላም ሰራዊት አደረጃጀቱን ዘላቂ በማድረግ በቀጣይም ለከተማችን አስተማማኝ ሰላም ደጀንነቱን እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።

ቀንም ማታም የመስራት ባህላችንን እያዳበርን በከተማችን እያስመዘገብናቸው በሚገኙ አንፅባራቂ የልማት ስራዎቻችን ላይም የህዝባችን አሻራ ላቅ ያለ ነው::

የከተማችን ህዝብ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እንዲሁም በእውቀቱ ኑሮውን ለማሻሻል እና የከተማችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ ከሚያደረገው ጥረት በተጨማሪ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፓርቲያችን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት በሚገኘው ሰው ተኮር ፕሮግራሞቻችንም ርብርቡን አጠናክሯል።

ከህዝባችን ጋር ቅርርባችን ይበልጥ በማጎልበት በየጊዜው የሚያጋጥሙ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮችን በጋራ እየተጋፈጥን በአሻራችን ታሪክ መስራታችንን እናጠናክራለን ።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ / ቤት

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ሱስዋ ናሮክ ወረዳ የሚገኘውን እና ከኢትዮጵያ በኩል ከወላይታ ሶዶ የ500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኃይል መለወጫ ጣቢያ መስመር ማብቂያ የሆነውን የኬትራኮ ኮንቨርተር ስቴሽንን ጎብኝተዋል።›› - ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኦቪድ ግሩፕ 5 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመሸጥ የሚያስችለውን ስምምነት አደረገ።

ኦቪድ ግሩፕ በመንግስትና የግሉ ዘርፍ አልሚነት ከሚያስገነባቸው ቤቶች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመሸጥ የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት አድርጓል::

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮናስ ታደሰ እና የሁለቱ ተቋማት የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ከ17 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት በመግለጽ ተቋሙ የሰራተኞቹን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል::

በዚህም አየር መንገዱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ሰራተኞቹ መኖሪያ ቤት የሚያገኙበትን ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሰዋል፡፡

ነገር ግን የሰራተኞቹ የቤት ፍላጎት ሰፊ በመሆኑ ከኦቪድ ግሩፕ ጋር መግባቢያ ስምምነት መፈፀሙን ገልፀዋል::

የኦቪድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ በበኩላቸው በመንግስትና የግሉ ዘርፍ አልሚነት ኦቪድ ግሩፕ ለመገንባት ካቀዳቸው 60 ሺህ ቤቶች ውስጥ 5 ሺ ቤቶችን ለአየር መንገዱ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ገንብቶ እንደሚያስረክብ ገልፀዋል::
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ወንድሜ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ላደረጉልን ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ። ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያካተተው የዛሬው ውይይታችን የቆየውን ትስስራችንን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ቁልፍ የትብብር መስኮችንም የለየ ነበር። የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመስራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል።

I extend my heartfelt gratitude to my brother, President William Ruto, for his gracious welcome to Kenya. Our comprehensive discussions today have not only strengthened our existing ties but also highlighted key areas for future collaboration. As neighbors sharing a unified vision and destiny, our commitment to working together remains steadfast.
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ ‘ሳልሳይ ወያነ ትግራይ’ የክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. መስጠቱን ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠ/ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ኬንያ ናይሮቢ ገብተዋል::

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የዛሬ ጠዋት ውይይት ሰፊ መጠነ ርዕይ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከሶማሌ፣ አፋር፣ ሀረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ተደርጓል፡፡ ውይይታችን በልማት፣ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር፡" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሀገር አቀፍ የፍትሕ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፍትሕና የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የፍትሕ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ተሳትፈዋል።

ለአራት ተከታታይ ዙሮች የተካሄዱት የፍትሕ ተቋማት የጋራ መድረኮች ወጥ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጎለብት ማስቻሉም ነው የተነሳው።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው 5ኛው የፍትሕ ተቋማት መድረክ ደግሞ በርካታ ጉዳዮች እንደሚነሱበት ኢዜአ ዘግቧል።

የ2016 ዓ.ም የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ተግባራት፣ ሀገራዊና የክልሎች የተጠቃለለ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስንተባበር ታሪክ ሰርተናል፤ እንሰራለንም!

ከውይይት ይልቅ ጦርነትን የማስቀደምን ኋላቀር አስተሳሰብ ብዙ አገራት ታሪክ አድርገውታል። አንዳንዶች ካሳለፉት ታሪክ ተምረው ሌሎቹ ደግሞ ከሌሎቹ ትምህርት ወስደው ላለመገዳደል ተማምለዋል።

የማሰብና የማሰላሰል ህሊና እያላቸው ከእንስሳት በታች ወርደው ወንድም ወንድሙን በመግደል የሚመፃደቁ፣ መግደል መሸነፍ መሆኑን የማይረዱ ቡድኖች ያሉባቸው አገራት ደግሞ ጦርነትን ታሪክ ማድረግ ባለመቻላቸው ፈራርሰው ታሪክ ሆነዋል።

በየአገሩ ያሉ አሸናፊ ሀሳብ የሌላቸው ጦር ሰባቂዎች ጭምር የሚረዱት እውነታ በንፁሀን መስዋዕትነት ሀብትን የማገባስ ጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ እንጅ ጦርነት ትናንትም ሆነ ዛሬ ነገም ወደፊትም የሚፈታው ችግር አለመኖሩን ነው።

ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ቱባ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የውይይት ባህል ባለመዳበሩ እንጅ በንግግር የማይፈታ አንዳች ችግር አለመኖሩን በመገንዘብ ፓርቲያችን ለትብብርና ለፉክክር ፖለቲካ ይተጋል።

የውይይትን ባህልን ለማዳበር አገር በቀል እውቀቶችን ከዴሞክራሲያዊ መርሆች ጋር በማቀናጀት ለመጠቀም ከሚደረገው ጥረት ባሻገር መሰረቱን ለማፅናት ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኛ ትውልድ የህዝባችንን ህይወት የመቀየር እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ ደረጃ የማሻገር ሀላፊነት ያለበት የተንከባለለ ዕዳ ከፋይ ጭምር ነው።

ብርቱ ስንሆን ኢትዮጵያን ለወዳጅነትና ለሽርክና የሚፈልጋት ብዙ ነው። ስንደክም ግን ደካሞች ጭምር ውክልና ተሰጥቷቸው ይጎነትሏታል።

ዓለም አንድ መንደር በሆነችበትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከሉዓላዊ አገራት የገዘፈ ፈርጣማ ጡንቻ በያዙበት በዚህ ዘመን የውጭ ተፅዕኖ ቀላል ባይሆንም የአገራት አስተማማኝ ሰላም፣ ዕድገትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚወሰነው በውስጥ አቅም ነው።

አገራችን በቅርቡ ገብታበት ከነበረው ውስጣዊ ፈተና እና ውጫዊ ጫና በድል ተሻግራ ብሪክስን ከመሰለ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስብ አባል የሆነችው፣ በቅርቡም ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መረህ ወደብ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ተጨባጭ ጥንካሬዋንና የወደፊት ተስፋዋን አመላካች ነው።

ዲፕሎማሲያችን ወይም አጠቃላይ የውጭ ግንኙነታችን ውስጣችን ሲደክም የሚዳከም ስንጠነክር ደግሞ የሚጠነክር በመሆኑ ቁልፉ በጃችን ነው።

ያለችን አንዲት አገር ናት፤ አንድ አይን ያለው በአፈር አይጫወትም እንዲሉ አበው መቼም ይሁን የትም ማንም ኢትዮጵያን ለድርድር ማቅረብ አይገባም። ሲመቸን የምንወዳት ሳይመቸን የምንረግማት ሳይሆን የከፍታዋም የዝቅታዋም ምክንያት እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ድህነቷን ቀርፈን ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ታሪካዊ አሻራችንን እናሳርፍ!


https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመዲናችን አዲስ አበባ አስደማሚ የምሽት ገፅታ፤

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሒማሊያ ተራራ ላይ አጥንት የሚሰብረውን ቅዝቃዜ እንዲህ የሚዳፈር አይጠፋም።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#በአንድነት ወደ ብልግና ማማ እንደርሳለን !!
ታላቋን ኢትዮጵያ እንደ ስሟ በሁሉም መስኮች ታላቅ የማድረጉ ጥረት የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን አስተዋጽኦ ይጠይቃል።
@AbiyAhmedAli

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሁለት ቀን ይፋዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ኬንያን ተሰናብተዋል::

Prime Minister Abiy Ahmed and First Lady Zinash Tayachew depart Nairobi, Kenya following a two-day State visit.

#PMOEthiopia

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የሁለት ቀን ይፋዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ኬንያን ተሰናብተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

WOW 👌 🇰🇪🇰🇪🇰🇪 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያ ጉብኝትንና የኢትዮ ኬንያ ግንኙነት በተመለከተ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሰጡት ማብራሪያ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼም ምንዳን አወርሳለሁ!

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሴት አመራሮችና ሰራተኞች የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼም ምንዳን አወርሳለሁ በሚል መሪ ቃል የጋራ ምክክር መድረክ አካሄዱ፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የፌደራል የሴቶች ከፍተኛ አመራር ወ/ሮ መስከረም አበበ በበኩላቸው ሴቶች ሰላምን ከማስጠበቅ አንፃር ያለንን ጠንካራ ሚና ተገንዝበን በተደራጀ መልኩ ልንሰራ እንደሚገባ እንዲሁም ሴቶች ሰላምን ማስጠበቅ የሚችሉት በቅድሚያ የራሳቸውን ጤና ሲጠብቁ መሆኑን ገልፀው በተለይም የማህፀን በር ካንሰር ምርምር እንዲያደርጉ እራሳቸውን ከማህፀን በር ካንሰር በሽታ እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ደም ልገሳ በማድረግ ለሌሎች ወገኖች ያላቸውን ድጋፍ ሊያሳዩ እንደሚገባ እና በቀጣይም የሀገር አርማ የሆነውን የህዳሴው ግድብ የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩ ባሉበት ሁኔታ ላይ እኛ ሴቶች ድጋፋችንን አጠናክረን የምንቀጥልበትን ስራ ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አክለዋል፡፡

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒሰቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ ሴቶች ሰላምን ለማስጠበቅ ያላቸው ድርሻ የጎላ መሆኑን ይህም የሚመነጨው ሴቶች የቤተሰብ መሰረት ከመሆናቸው ጋር የሚያያዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሴቶች የሰላም እሴቶችን በልጆቻቸው እና በአካባቢያቸው ላይ የማስረፅ ሚናቸውን ተረድተው ተግባራቸውን ተፅእኖ በሚፈጥር ደረጃ ለማሳካት እንዲችሉ በተደራጀ ሁኔታ መስራት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ፣ የድል ምልክትና የኩራታችን መገለጫ ነው ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጋዜጠኞች ገለጹ።

የአድዋ ድል አፍሪካውያን በነጮች የበላይነት በቅኝ ግዛት ይረገጡበት የነበረውን የግፍ ስርአት ታግሎ በማሸነፍ ለመላ ጥቁር ህዝቦች ነፃነትን ያወጀ ታላቅ ታሪካዊ ሁነት ነው።

ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ለቅኝ ገዥዎች አንበረከክም በማለት በዱር በገደሉ ተዋግተው በማሸነፍ ለአፍሪካዊያን የነፃነት ፋና ወጊ መሆንም ችለዋል።

በዚህም አድዋ አፍሪካዊያን በትግላቸው ነፃነታቸውን እንዲያረጋግጡ የድል አድራጊነት መነሻ በመሆን የመላ ጥቁር ህዝቦች የድል ተምሳሌት ተደርጎም ይወሰዳል።

የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጀግኖች ለነፃነታቸው ተዋግተው ያሸነፉበት ታሪካዊ እለት ሆኖ እየተከበረ እስካሁንም ዘልቋል።

የአድዋን ድል በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የጋና፣ ኒጀርና ሴኔጋል ጋዜጠኞች የአድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ፣ የድል ምልክትና የኩራታችን መገለጫ ነው ብለዋል።

በጋና ጆይ ኒውስ ቲቪ የውጭ ጉዳዮች ዘጋቢ ጋዜጠኛ ብለስድ ሶጋህ፤ የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የጀግንነት ማሳያና የአህጉሪቷ የነፃነት ብስራት መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም የአድዋ ድልን የጥንካሬና የይቻላል ስነ-ልቦና በመሰነቅ የሁላችንም ችግር የሆነውን ድህነት በጋራ መዋጋት አለብን ብሏል።

የኒጀሯ ጋዜጠኛ፣ የፊልም ዳይሬክተርና ኤዲተር ራህማቱ ኬይታ፤ የአድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት አርማ፣ የድል ምልክትና የኩራታችን መገለጫ ነው ብላለች።

የአድዋ ድል የቅኝ ግዛትንና ጭቆናን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሸነፍ ያስቻለ፤ የመላ አፍሪካውያን የድል ተምሳሌት ስለመሆኑም አንስታለች።

ሴኔጋላዊው ጋዜጠኛ የአፍሪካ 24 ሚዲያ ማናጀር አሊ ጉይንዶ፤ የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን በጀግንነት ታሪክ የሰሩበት የሁላችንም የጋራ ታሪክና የነፃነታችን አርማ ነው ብሏል።

የጋና ጆይ ኒውስ ቲቪ የውጭ ጉዳዮች ዘጋቢ ጋዜጠኛ ብለስድ ሶጋህ፤ የአፍሪካን አንድነት እውን በማድረግና ለነፃነት ግንባር ቀደም ትግል በማድረግ የኢትዮጵያ ሚና በታሪክ ሲወሳ የሚኖር መሆኑን ገልፃል።

ኢትዮጵያ አሁንም የአፍሪካን አንድነት፣ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ ፓን አፍሪካ ሚዲያ መፍጠር ያስፈልጋል የሚል አቋም ይዛ እየሰራች መሆኑ ይታወቃል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ ከዓረብ ኤሚሬቶች እና ከእንግሊዝ ንግድ ሚኒስትር ዴኤታዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ውይይቱ በአቡዳቢ እየተካሄደ በሚገኘው 13ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

በዚህ መሰረትም ልዑካኑ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የንግድ ሚኒስትር ዴዔታ ታኒ ቢን አህመድ አል ዘዩዲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት መስፈርቶችን ለማጠናቀቅ እያደረገች ያለውን ጥረት እና ሒደቱ የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል::

በተመሳሳይ የኢትዮጵያልዑክ ከእንግሊዝ የንግድ ፖሊሲ ሚኒስትር ዴዔታ፣ የፓርላማ አባል እና የለንደን ሚኒስትር ግሬግ ዊሊያምስ ሃድስ ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱም የእንግሊዝ ልዑካን ቡድን አባላት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት ለማጠናቀቅ ለጀመረችው ጥረት አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

እንግሊዝ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን ጥረት እና የእስካሁኑን ጉዞ ማድነቃቸውም ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ካላት ጉልህ የገበያ ስፋትና ኢኮኖሚ አንፃር የዓለም ንግድ ድርጅትን መቀላቀሏ ለራሷም ሆነ ለሌሎች አባል ሀገራት ሁለንተናዊ ጥቅም እንዳለውም አፅንኦት ሰጥተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስንተባበር ታሪክ ሰርተናል፤ እንሰራለንም!

ከውይይት ይልቅ ጦርነትን የማስቀደምን ኋላቀር አስተሳሰብ ብዙ አገራት ታሪክ አድርገውታል። አንዳንዶች ካሳለፉት ታሪክ ተምረው ሌሎቹ ደግሞ ከሌሎቹ ትምህርት ወስደው ላለመገዳደል ተማምለዋል።

የማሰብና የማሰላሰል ህሊና እያላቸው ከእንስሳት በታች ወርደው ወንድም ወንድሙን በመግደል የሚመፃደቁ፣ መግደል መሸነፍ መሆኑን የማይረዱ ቡድኖች ያሉባቸው አገራት ደግሞ ጦርነትን ታሪክ ማድረግ ባለመቻላቸው ፈራርሰው ታሪክ ሆነዋል።

በየአገሩ ያሉ አሸናፊ ሀሳብ የሌላቸው ጦር ሰባቂዎች ጭምር የሚረዱት እውነታ በንፁሀን መስዋዕትነት ሀብትን የማገባስ ጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ እንጅ ጦርነት ትናንትም ሆነ ዛሬ ነገም ወደፊትም የሚፈታው ችግር አለመኖሩን ነው።

ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ቱባ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶች ያሏት ኢትዮጵያ የውይይት ባህል ባለመዳበሩ እንጅ በንግግር የማይፈታ አንዳች ችግር አለመኖሩን በመገንዘብ ፓርቲያችን ለትብብርና ለፉክክር ፖለቲካ ይተጋል።

የውይይትን ባህልን ለማዳበር አገር በቀል እውቀቶችን ከዴሞክራሲያዊ መርሆች ጋር በማቀናጀት ለመጠቀም ከሚደረገው ጥረት ባሻገር መሰረቱን ለማፅናት ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

የኛ ትውልድ የህዝባችንን ህይወት የመቀየር እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ ደረጃ የማሻገር ሀላፊነት ያለበት የተንከባለለ ዕዳ ከፋይ ጭምር ነው።

ብርቱ ስንሆን ኢትዮጵያን ለወዳጅነትና ለሽርክና የሚፈልጋት ብዙ ነው። ስንደክም ግን ደካሞች ጭምር ውክልና ተሰጥቷቸው ይጎነትሏታል።

ዓለም አንድ መንደር በሆነችበትና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከሉዓላዊ አገራት የገዘፈ ፈርጣማ ጡንቻ በያዙበት በዚህ ዘመን የውጭ ተፅዕኖ ቀላል ባይሆንም የአገራት አስተማማኝ ሰላም፣ ዕድገትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚወሰነው በውስጥ አቅም ነው።

አገራችን በቅርቡ ገብታበት ከነበረው ውስጣዊ ፈተና እና ውጫዊ ጫና በድል ተሻግራ ብሪክስን ከመሰለ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብስብ አባል የሆነችው፣ በቅርቡም ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ ወደብ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ተጨባጭ ጥንካሬዋንና የወደፊት ተስፋዋን አመላካች ነው።

ዲፕሎማሲያችን ወይም አጠቃላይ የውጭ ግንኙነታችን ውስጣችን ሲደክም የሚዳከም ስንጠነክር ደግሞ የሚጠነክር በመሆኑ ቁልፉ በእጃችን ነው።

ያለችን አንዲት አገር ናት፤ አንድ አይን ያለው በአፈር አይጫወትም እንዲሉ አበው መቼም ይሁን የትም ማንም ኢትዮጵያን ለድርድር ማቅረብ አይገባም። ሲመቸን የምንወዳት ሳይመቸን የምንረግማት ሳይሆን የከፍታዋም የዝቅታዋም ምክንያት እራሳችን መሆናችንን ተረድተን ድህነቷን ቀርፈን ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ታሪካዊ አሻራችንን እናሳርፍ!

#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአዲስ አበባ አዲስ ገፅታ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በቂርቆስ የተገነባው #የቂርቆስ_ፓርክ ለእኛ ለአዛውንቶች እንደ ካንጋሮ ፍራሽ ተመችቶናል፣ማረፊያም ሆኖናል" በፓርኩ ሲዝናኑ ያገኘናቸው #አዛውንቶች ምስክርነት

የኢፊዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተሰሩ የሰው ተኮር ተግባራትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ትኩረት ከሰጡባቸው ስራዎች አንዱ በ4 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈውና ከ150 በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረው #የቂርቆስ_ፓርክ ዋናው ነበር።

ፓርኩ ከፈጠረው የስራ እድል ባለፈ ዛሬ ላይ የወጣቱ ፣የሴቱ፣ የህፃናቱ ፣ የአዛውንቱና የአካል ጉዳተኛው የመዝናኛ ማዕከልም ሆኗል።

ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የክልልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በጉብኝታቸው ወቅት ያረጋገጡት ይህንኑ ነው።

በስፍራው በመዝናናት ላይ የነበሩ አዛውንቶችን በጎበኙ ወቅት የተሰጣቸው ምስክርነትም ይሄው ነው።

ቂርቆስ_ፓርክ ለእኛ ለአዛውንቶች እንደ ካንጋሮ ፍራሽ ተመችቶናል፣ማረፊያም ሆኖናል፣ ጡረታዎች እንገናኝበታለን ፣ እንመካከርበታለን ፣አረፍም ብለን አዕምሯችንን አድሰን ወደቤታችን እንመለሳለን ። ለኛ ከዚህ በላይ ስጦታ የለምና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን እናመሰግናለን ብለዋል።

በየአካባቢው እንዲህ ዓይነት ተግባራት እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

ቂርቆስ ሚዲያም እንዲህ ዓይነት ተግባራት የህዝቡን ጥያቄ የሚፈቱ ናቸውና ተጠናክረው ይቀጥሉ ይላል።

መልካም ውሎ ይሁንላችሁ!

© ቂርቆስ ኮሙኒኬሽን/Kirkos Communication

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እንሰሳትም ለካ ወዳጃቸው ሲሞትባቸው እንደ ሰው ያለቅሳሉ


ኮዋላ የተባለው እና በአውስትራሊያ የሚገኘው  ድብ የሚመስል አጥቢ እንሰሳ ሴት ጓደኛው  ስትሞትበት እንዲህ ሲያለቅስ በዚህ ቪዲዮ ላይ ይታያል።


https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመዲናችን አዲስ አበባ አስደማሚ የምሽት ገፅታ፤

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

© @AbiyAhmedAli (phd)

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ፈራችሁም አልፈራችሁም . . .

በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደገሰገሱት ሃገራት በእኛም ሃገር ጥርት ያሉ ጥናቶች እየተዘጋጁ የሚቀርብልን ሁኔታ እያደገ እንደሚሄድ ተስፋ በማድረግ፣ እስከዚያው ግን በጥናታዊ አቅርቦት ከበለጸጉት ሃገሮች አንዳንድ መረጃዎችን በመበደር ለእንቆቅልሾቻችን መፍቻ መፈለጋችንን እንቀጥላለን፡፡

እንደምሳሌ ለመውሰድ፣ በአሜሪካን ሃገር ውስጥ በተደረገው አንድ ጥናት (የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ውጤቶችን የማንጸባረቃቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ) የሚከተለውን የፍርሃትን ገጽታ ከሃገራችን አውድ አንጻር እንድንመለከተው የሚያደርገንን መረጃ እናገኛለን፡፡

• ስልሳ በመቶው (60%) የምንፈራቸው ነገሮች ፈጽሞ ወደመሆን አይመጡም፡፡

• ሰላሳ በመቶው (30%) ከዚህ በፊት ፈርተናቸው የደረሱብን ሁኔታዎች ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ከመሆን የማንቀይራቸው ነገሮች ናቸው፡፡

• ዘጠና በመቶው (90%) የምንፈራቸው ነገሮች ቢደርሱም ሆነ ባይደርሱ ብዙም የማይነኩንና አናሳ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

• ሰማኒያ ስምንት በመቶው (88%) ከጤንነታችን ጋር በተያያዘ ሁኔታ ይደርስብናል ብለን የምንፈራቸው ሁኔታዎች በፍጹም የማይደርሱብን ሁኔታዎች ናቸው፡፡

በዚህ ዓለም ላይ ምንም ሳይፈራ የሚኖር ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ነገር ግን የፍርሃትን እውነታ በመቀበል፣ ብንፈራም ሆነ ባንፈራ ምንም ለውጥ ስለማናመጣባቸው ነገሮች መፍራትን በማቆም፣ የፍርሃትን ስሜት ለጥቅማችን በማዋል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ሕይወትን ቀና ብሎ በማጣጣም መኖር ፍርሃትን ያሸነፉ ሰዎች ልምምድ እንደሆነ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡

ፈራችሁም አልፈራችሁም . . . ወደፊት!

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በመላው የክልሉ አካባቢዎች በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር በክልሉ የገጠሙ ቁልፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ ውይይት አድርገናል።
በቀረቡ በርካታ ጉዳዮች ላይ ምላሽ በመስጠት ለጋራ አላማ የጋራ ጥረት የማድረግን አስፈላጊነት በአፅንዖት አንስተናል።

Following region-wide discussions held in the Amhara Region, led by PP Executive Members, I have convened representatives from all zones of the region this morning to address critical current issues facing the region. Providing responses on a number of issues, we have underscored the importance of uniting efforts for a common purpose.

© ዶ/ር ዐብይ አህመድ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel