ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የአድዋ ጀግኖችን ገድል ውርስ አድርጎ ሃገሩን ለመጠበቅ ዘብ እንደሚቆም የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ‹‹ዓድዋ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት›› በሚል መሪ ሐሳብ ፒያሳ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው፡፡
በበዓሉ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደተናገሩት ጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት የአድዋ ጀግኖችን ገድል ውርስ በማድረግ ዛሬም በራሱ ዘመን በኢትዮጵያ ላይ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣ ትንኮሳን ለመመከት ዝግጁ ነው።
ሰራዊቱ በዚህ ታሪካዊ የድል በዓል ላይ ቃሉን እንደሚያድስ የገለጹት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከህዝብ አብራክ የተገኘውንና የሃገር ህልውና ዋልታ የመጨረሻ ምሽግ የሆነውን መከላከያ ሰራዊት መጠበቅና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ፊልድ ማርሻሉ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ባስተላለፉት መልዕክት መከላከያ ሰራዊትና የመከላከያን ተቋም እንደ ተቋም እንደ ቀደመው ጊዜ ሁሉ ልትጠብቀውና ድጋፍህን ልትቸረው እንደሚገባ አሳስባለሁ ብለዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
“በዛሬው ዕለት እየተከበረ ያለውው የዓድዋ ድል በስብሰባና በንግግር ብቻ ሳይሆን በሙዚየም ጭምር መዘከሩ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ልጅ ዳንኤል ጆቴ ገለጹ።
128ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል በተለያዩ ሥነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።
በድሉ በዓል ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጥንታዊ ኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ በንግግር ብቻ ሳይሆን መንግስት ህዝቡን የካሰበት ከአራቱም ማዕዘን በሚታይ የዓድዋ መታሰቢያ መከበሩ በዓሉን ልዩ እንደሚያደርገው አንስተዋል።
ዓድዋን ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ እንዲነገር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።
ለቀጣይ ትውልድ ሰላማዊ ሀገርን ለማስረከብ ሁላችንም መትጋት አለብን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አድዋ የጥቁር ህዝቦች የድል አርማ በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የቀድሞ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች ወታደራዊ አታሼዎች የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የሃይማኖት አባቶች የመዲናዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
128,ኛው የአድዋ ድል በዓል አከባበር የማለዳ ድባብ በምስል
https://twitter.com/ProsperityKera
የተለያዩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች 128ኛ የዓድዋ ድል በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል
የዓድዋ ድል የመላው ኢትዮጵያውያን ህብረትና አንድነት ፤ ቆራጥነትና ጀግንነት የታየበት፤ የጥቁር ህዝቦች ተጋድሎና አይበገሬነት በድል የተጠናቀቀበት ፤በባርነት ለሚማቅቁ ጥቁር ህዝቦች የነፃነትን መንገድ ለጠረገ በዓል ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንም ኢትዮጵያውያን እጅግ አኩሪ ድሎችና ታሪኮች ያሏቸው ህዝቦች ናቸው ያሉ ሲሆን ÷ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን ለሀገራቸው ያለስስት ራሳቸውን መስጠታቸውንም አንስተዋል።
የዓድዋ ድል ሲነሳ ከሁሉም የሚያስደንቀው ኢትዮጵያውያን በጉልህ የሚታወቁበት አንድነት በተግባር የተገለጠበት ድል መሆኑንም አቶ አሻድሊ ተናግረዋል።
የዓድዋ ድል በዓልን ስናከብር ከአባት እናቶቻችንን ትምህርት ወስደን አዲስ ታሪክ መጻፍ እንደምንችል በመገንዘብ ጭምር ሊሆን ይገባል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለፁ፡፡።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው፤ድሉ መላ ኢትዮጵያውያንን ከዳር እስከ ዳር በላቀ የሀገር ስሜት፤ ወኔ እና ጀግንነት በማሰባሰብ በተባበረ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የወራሪ ኃይል ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ድል ያደረጉበት በዘመን የማይደበዝዝ ዘላለማዊ ክብር እና ኩራት ያጎናጸፈን የሸናፊነት የጋራ አኩሪ ታሪካችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የዓድዋ ድል ልዩነቶችን በመሻገር ሀገርን የማፅናት ተምሳሌት ነው ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ተናገሩ፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በየእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ታቸው የዓድዋ ድል በዓል ከታላቅ የገድልና የጀግንነት ታሪክ አሻራነቱ ባሻገር ለአዳዲስ ሀገራዊ ስኬቶች መነቃቃትን የሚፈጥር፣ የሀገር ፍቅርንና የአንድነትን እሴቶችን ሸማ የሚያጎናጽፍ ነው ብለዋል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በበኩላቸው የዓድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ተምሳሌት እንደሆነ ገልፀው፤ ድሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር ቅኝ ገዢዎች በጥቁር ሕዝብ ተሸንፈው ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ የነፃነት አዲስ ምዕራፍ የከፈቱበት ታሪካዊ በዓል ነው ብለዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የዓድዋ ድል በዓለም ጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ድል ነው ሲሉ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ታጋይ የነበረው የማርከስ ጋርቬይ ልጅ ጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር) እንደተናገሩት÷ ኢትዮጵያ በፋሺስት ጣሊያን ላይ በአድዋ የተቀዳጀችው ድል በዓለም ጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
ድሉ ኢትዮጵያ እንዳትገዛ ከማስቻሉም በዘለለ የጥቁር ሕዝቦች ለነጻነታቸው እንዲነሳሱ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰው÷ ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ በጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ትልቅ ሥፍራ እንዳላት ተናግረዋል።
ድሉ ከአፍሪካ ውጭ በሚገኙ የጥቁር ሕዝቦች መካከል የፓን-አፍሪካኒዝም ጽንሰ ሃሳብን በማነቃቃት በኩልም ትልቅ ሚና እንደነበረው አብራርተዋል።
ይህን ታሪክ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ አካቶ በማስተማር ለአዲሱ ትውልድ በተገቢው ሁኔታ ማሳወቅ እንደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ለቅኝ ግዛት ባለመንበርከክ ያስመዘገበችውና ለጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምሳሌ በመሆኑ የዓድዋ ድል ሁሉም ጥቁር ሕዝብ የሚያከብረው መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያን የጣሊያንን ወራሪ ኃይል በአንድነት ተሰልፈው ድል ያደረጉበት 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በነገው ዕለት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ይከበራል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የአድዋ ድል የኢትዮጵያን ስብራቶች ለመጠገን ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ የታሪክ አሻራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ማጠቃለያ መርኃ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በአድዋ ጦርነት በተባበረ ክንዳቸውና በአልገዛም ባይነት ወኔያቸው ወራሪ ኃይልን አንበርክከዋል ብለዋል።
የአድዋ ድል በህብር፣ በፍቅርና በትብብር የተገኘ ግዙፍ ድል መሆኑን ጠቅሰው፥ የወቅቱ የኢትዮጵያ ጦር በህብረ ብሔራዊ አንድነት የተዋቀረ ሃይል መሆኑንም አንስተዋል።
በአድዋ ዘመን የታየው የሀገርና የወገን ፍቅር ዛሬም ፀንቶ እንዲቀጥል መሥራት ይጠበቃል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሀገር የሚከፈል ዋጋ ከምንም በላይ ነው ብለዋል።
የአድዋ ዘመን ጀግኖች የተለያየ ቋንቋ እየተናገሩ፣ የተለያየ ሃይማኖት እየተከተሉ፣ በአንድነት የዘመቱት ለሀገር ከመተባበር የሚበልጥ ነገር እንደሌለ ስለተገነዘቡ መሆኑንም አብራርተዋል።
አድዋ ሀገር የሚታደግና የሚያጸና ትምህርት ቤት መሆኑን ጠቅሰው፤ የአድዋ ድል የኢትዮጵያን ስብራቶች ለመጠገን ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ የታሪክ አሻራ ነው ብለዋል።
የሠላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፥ ኢትዮጵያውያን በታሪክ አጋጣሚ ግፈኞች የሰነዘሯቸውን ትንኮሳዎች በድል አድራጊነት መቋጨታቸውን የአድዋ ድል ህያው ምስክር ነው ብለዋል።
አድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ የሠላም መድረኮች ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ፣ ሰላሟ የበዛ እና ብልፅግናዋ የተረጋገጠ እንድትሆን የሚያስችል ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ማገዝ ነው ብለዋል።
አድዋ የአንድነታችን ሰንሰለት፣ የነፃነታችን ሰንደቅ የጀግንነታችን ልህቀት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ድሉ የአንድ ዘመን ክስተት ብቻ ሳይሆን ትውልዱ የሚማርበት የጀግኖች አሻራ መሆኑን ገልጸዋል።
ትውልዱ ኢትዮጵያን ለችግር የዳረጋትን መጥፎ የፖለቲካ ባህል ከመገዳደል ወደ መደራደር በመቀየር የራሱን የአድዋ ድል ሊያበስር እንደሚገባ መክረዋል።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) የአድዋ ድል ከኢትዮጵያውያን ባለፈ ለመላ ጥቁር ህዝቦች ሁሉ ኩራት የሆነ ድንቅ የታሪክ ክስተት መሆኑን ገልጸዋል።
የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግም የዛሬው ትውልድ፤ ከትናንት የአድዋ ጀግና አያቶቹ ትብብርና አንድነት ትምህርት ሊወስድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ የአድዋ ድል ታሪክ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት ግንባታ በብልሃት፣ በጥንቃቄና በትዕግስት ዕውን ለማድረግ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵን ህልውና የሚፈታተኑ ግጭቶችን መፍትሔ በመስጠት ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት ምሁራን ድርብ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ወጣቶች ከስሜታዊነት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም አለባቸው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ምሁራንም በዕውቀት ላይ ተመሰረተ ሃሳብ ያለው ዜጋ በማፍራት ቀጣዩን ትውልድ ማነጽ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩም የታሪክ ኢምሬትስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ "አድዋና ፓን አፍሪካኒዝም" እንዲሁም ፕሮፌሰር መስፍን ዓርአያ "አድዋ ለብሔራዊ መግባባትና ለሀገር ግንባታ" በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጽሁፍ አቅርበው ምክክር ተካሂዷል።
128ኛው የአድዋ ድል በዓል ነገ ቅዳሜ የካቲት 23/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ይከበራል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ 128ኛ ዓመት የዓድዋ ድል በዓልን "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል" በሚል መሪ ቃል ዛሬ አክብረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር አብዱ ያሲን በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ የምትታወቅባችው በርካታ ለጥቅስ የሚበቃ ታሪክ እና ገድል ያላት ብትሆንም ዓድዋ ከሁሉም ይበልጥ የጎላ፣ የኢትዮጵያን ገናናነትና ጀግንነትን የገለፀ፣ ለመላው ጥቁር ህዝቦች ያበረከተችው የአይበገሬነት፣ የነፃነት እና የአሸናፊነት ተምሳሌት ነው፡፡
ይህ ገድል ከተፈጸመ 128 ተዓመታት ቢያልፉትም ትርጉሙ የትናንት ያህል ጉልህ ነው ያሉት አምባሳደር አብዱ፤ የዓድዋ ድል የኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ፤ የጥቁር ሕዝቦች ከፍታም ጭምር ነው ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የእኛም ትውልድ እንደ ቀደምት አባቶቹ በርካታ የልማት ስራዎችን እየሰራ ተስፋ ፈንጣቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል ያሉት አምባሳደር አብዱ፤ እየተገነቡ የሚገኙ የአባይ ግድብና ሌሎችም ትላልቅ ፕሮጀክቶች በስኬት የሚጠቅሱ መሆናቸውን አንስተዋል።
በተለይም በዲፕሎማሲ ረገድ በቀጣናው ሰላምና ደህንነትን በማረጋገጥ እና ሸብርተኝነትን በመዋጋት፣ ያልተገቡ ውጭ ጣልቃ ገብነቶችን እምቢኝ በማለት፣ ሠላም በማስከበር ፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት ረገድ በዓለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካ ድምፅ በመሆን፣ ፓን አፍሪካኒዝም ማዕከል ያደረጉ በርካታ አኩሪ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን መደረጉ ዲፕሎማሲያዊ እመርታ የተመዘገበበት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እንድሪስ(ዶ/ር) እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ተገኝተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የማልታ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ፕሮሞሽን ተቋም ከሆነው ከትሬድማልታ እና ከኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የፊታችን መጋቢት 3 ቀን የኢንቨስትመንት ፎርም ያካሄዳል፡፡
በኢንቨስትመንት ፎርሙ ዙሪያ በተቋማቱ ሃላፊዎች ለጋዜጠኞች መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
በመግለጫው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ኮምሽነር ወ/ሮ ሀና አርአያስላሴ፣ በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ዋና ፅሀፊ አቶ ውቤ መንግስቱ ተገኝተዋል፡፡
ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር ዋነኛው አላማው መሆኑ ተገልጿል፡፡
በፎረሙ ከተለያዩ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተወጣጡ ከ30 በላይ የማልታ የንግድ እና አምራች ኩባንያዎች እና ከ40 በላይ የኢትዮጵያ አምራች ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተመላክቷል፡፡
በሁለቱ ሀገራት ተሳታፊዎች መካከልም የአንድ ለአንድ ውይይት እንደሚደረግ መገለጹን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ከ60 እስከ 3 ሺ ሜትር ድረስ ውድድር የሚካሄድበት 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ዛሬ 7፡30 ላይ ይጀመራል፡፡ በመክፈቻው የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡
ከእነዚህ መካከል የ1 ሺ 500 ሜትር እና የ800 ሜትር ማጣሪያዎች ተጠባቂ ናቸው፡፡
የሴቶቹን ውድድር የማሸነፍ ግምት ያገኘችው ፍሬወይኒ ኃይሉ በቋት አንድ፣ድርቤ ወልተጂ በቋት ሶስት እንዲሁም ብርቄ ኃየሎም በቋት አራት የ1 ሺ 500 ሜትር ማጣሪያቸውን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
በወንዶች የማሸነፍ ግምት ያገኘው ሳሙኤል ተፈራ በቋት አንድ ማጣሪያውን ያደርጋል፡፡
ብሪታንያዊ አዳም ፎግ እዚሁ ቋት ላይ ይገኛል፡፡ ሌላው ኢትዮጵያዊ ቢኒያም መሐሪ ቋት ሶስት ላይ ማጣሪያውን እንደሚያደርግ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ይጠቁማል፡፡
የ800 ሜትር ማጣሪያ ዛሬ የሚደረግ ሲሆን በሴቶች ከፍተኛ ልምድ ያካበተችው ሃብታም አለሙ እና ጽጌ ዱጉማ ሲሳተፉ በወንዶች ኤፍሬም መኮንን በብቸኝነት ማጣሪያውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የቀሪ እና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫን እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
ይኸዉም ምርጫ ባልተደረገባቸው እና በቦርዱ ውሳኔ ድጋሜ ምርጫ እንዲደረግባቸው በተወሰነው መሰረት እንደሆነ ተገልጿል።
ምርጫው በ4 ክልሎች ማለትም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር እና ሶማሌ ክልል እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚደረግ ሲሆን 9 የህዝብ ተወካዮችና 26 የክልል ምክር ቤት ተወካዮችን ለማሟላት የሚደርግ እንደሆነ የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሲያድርግ የእጮዎች ምዝገባ ከሚያዚያ 7 እሰከ 16 እንደሆነም አስታውቋል።
ቀሪና የድጋሜ ምርጫው በ29 የምርጫ ጣቢያዎች በ1 ሺህ 146 መደበኛ የምርጫ ጣቢያዎች እና በ34 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ጣቢያዎች ይከናወናል ተብሏል።
ቦርዱ በዚህ ምርጫ የተረጋጋጠውን ውጤት በሰኔ 16/2016 ዓ.ም ይፋ እንዲሚያድርግም ተጠቅሷል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት እንዲኖር ማድረግ ለዘላቂ ሰላም መሠረት መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ለሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮችና ሚኒስትሮች በተዘጋጀው መድረክ ላይ እንዳሉት÷ ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ለፌዴራል ሥርዓት መጠናከርና ውጤታማነት እንዲሁም ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ያለው አስተዋጽኦ የጎላ ነው፡፡
በክልሎች መካከል ያለው ፍትሐዊ የመሠረተ ልማት ሥርጭት ግልጽ በሆነ የአሠራር ሥርዓትና አሳታፊነት መመራቱ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት የሚያረጋግጥ፣ የሕዝቦችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እውን መሆን በር የሚከፍትና በሕዝቦች መካከል መተማመንን የሚፈጥር እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
ከሀገራዊ ለውጡ በፊት በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል ባለመኖሩ በሕዝቦች መካከል የተፈጠረው አለመተማመን የግጭት መነሻ ሆኖ እንደቆየ አስታውሰዋል፡፡
አቶ አገኘሁ ለውጡን ተከትሎ ግልጽ የአሠራር ሥርዓት ተግባራዊ በመሆኑና በክልሎች መካከል የነበረውን ቅሬታና አለመተማመን ማስወገድ ተችሏል ብለዋል፡፡
ክልሎች የገቢ ምንጫቸውን አሟጠው በመጠቀምና የወጪ ቅነሳ ሥርዓትን በመከተል ውጤታማ የሀብት ክፍፍል ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡
በፌዴራል ደረጃ በመሠረተ ልማት ዘርፉ ላይ የሚሠሩ ተቋማትም በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር የተዘረጋውን ግልጽ፣ አሳታፊና ፍትሐዊ የአሠራር ሥርዓት (ደንብ) በጥብቅ ዲስፕሊን ሥራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝቦች እኩልነትና በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር ለማድረግ እንዲቻል በክልሎች መካከል እኩል የመልማት እድል እና የተመጣጠነ ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል የፌዴራል የመሠረተ ልማት አውታሮች ሥርጭት ፍትሐዊነትን እንደሚከታተልም መገለጹንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
አራት ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሞባይል ስልኮችን መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀል ምርመራ ቲም ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አሰፋ ጎንፋ እንደገለጹት፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድረውን የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ብሏል ፓሊስ።
ፓሊስ ለህገወጥ ንግድ መበራከት ምክንያት የሆነውን የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል ባደረገው ክትትል ህጋዊነትን ባልጠበቀ መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የዋጋ ግምታቸው አራት ሚሊዮን ብር የሚያወጡ አንድ ሺህ 535 የተለያየ አይነት ሞባይል ስልኮችን በክትትል ብርበራ መያዙን አስታውቋል።
በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያለውን የንግድ ቤት ባለቤት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ እያጣራ አንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በሶማሌ ክልል ለሚገነባው የጅግጅጋ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተቀመጠ።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ በሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን÷ በአመት አንድ ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ተገልጿል።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የትምህርት ቤቱ ግንባታ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የጎላ አስተዋፆ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የሚገነባው የጅግጅጋ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ህዝባችንን አስተባብረን በአሻራችን ታሪክ መስራታችንን እናጠናክራለን!
ፓርቲያችን እና መንግስታችን የህዝባችንን ጥያቄዎች ቀረብ ብሎ የማድመጥ ባህላቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎለበቱ ቀጥለዋል::
የህዝባችንን ጥያቄዎች የዕቅዶቻችን አካል በማድረግም ለጋራ ስኬት ተቀናጅተን እየተረባረብን እንገኛለን።
ምን ሰርተን ምን አጎደልን የሚለውን ከህዝባችን ጋር እንገመግማለን። ለአብነትም በያዝነው የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ የከተማ አሰተዳደሩ ባለፈው ዓመት ያከናወናቸውን የልማት ስራዎች አፈፃፀም በተመለከተ በሁሉም ክ/ከተሞች ህዝባዊ ውይይቶች ተደርገዋል።
በብሎክ ደረጃ ጭምር በተለያዩ የልማት እና የሰላም ጉዳዮች ላይ ከህዝባችን ጋር መክረናል።
በቅርቡም ከፌዴራል እና ከክልሎች የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ከከተማች ህዝብ ጋር ውጤታ ውይይት አድርገዋል።
በህዝባዊ ውይይቶች በቀጣይ የመደበኛው ዕቅድ አካል የሚሆኑና የጋራ ርብረብ የሚደረግባቸው በርካታ ግብአቶችም ተገኝተዋል።
ህዝባችን የተሰሩትን አድንቆ ያልሰራናቸውን ደግሞ ለምን እንዳላከናወናቸው ጠይቆ በመፍትሄዎቹ ላይም የጋራ ግንዛቤ ይዘናል።
ባለፉት ወራት በልማትና በሰላም ስራዎቻችን ከጎናችን ተሰልፎ ለተመዘገቡ ስኬቶች የጐላ አሻራውን እንዳሳረፈ ሁሉ በቀጣይም ከከተማ አሰተዳደሩ ጐን ሆኖ የድርሻውን እንደሚወጣ ህዝባችን በተግባር ጭምር እያረጋገጠ ይገኛል።
ፓርቲያችን ቀይ መስመር ብሎ የለያቸውን ብልሹ አሰራሮችንና ሌብነትን ከመታገል አንፃርም ህዝባችንን በማሳተፍ የጀማመርናቸው ጥቆማን የመሳሰሉ አበረታች ስራዎች መኖራቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ሰላማችንን አስጠብቆ ከማስቀጠል አንፃርም የከተማችን ህዝብ ውጤታማ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም ህዝባዊ በዓላቶቻችን ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን በሚያጠናክር እንዲሁም የከተማችንን የቱሪስት ፍሰት በሚያሳድግ መልኩ በሰላምና በፍቅር እንዲከበሩ ከፀጥታ ሀይላችን ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ሰርቷል። የሰላም ሰራዊት አደረጃጀቱን ዘላቂ በማድረግ በቀጣይም ለከተማችን አስተማማኝ ሰላም ደጀንነቱን እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።
ቀንም ማታም የመስራት ባህላችንን እያዳበርን በከተማችን እያስመዘገብናቸው በሚገኙ አንፅባራቂ የልማት ስራዎቻችን ላይም የህዝባችን አሻራ ላቅ ያለ ነው::
የከተማችን ህዝብ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እንዲሁም በእውቀቱ ኑሮውን ለማሻሻል እና የከተማችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ ከሚያደረገው ጥረት በተጨማሪ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፓርቲያችን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት በሚገኘው ሰው ተኮር ፕሮግራሞቻችንም ርብርቡን አጠናክሯል።
ከህዝባችን ጋር ቅርርባችን ይበልጥ በማጎልበት በየጊዜው የሚያጋጥሙ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮችን በጋራ እየተጋፈጥን በአሻራችን ታሪክ መስራታችንን እናጠናክራለን ።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ / ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera
ከጀግኖች አርበኞች ለአዲሱ ትውልድ የባንዲራ ቅብብሎሽ፦
https://twitter.com/ProsperityKera
"ዓድዋ ኢትዮጵያውያን በአርበኝነት ተጋድሎ የሀገር ሉዓላዊነት ያጸኑበት ታላቁ ድል!"
እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!
የካቲት 23/1888 የአርበኝነት ተጋድሎ የታየባት፣ የባርነት ጥላ የተገፈፈባት እና የነፃነት ብርሃን የፈነጠቀባት ዕለት ናት።
መልካም የድል በዓል!!
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር ለ128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአል ቀን ላይ በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የመታሰቢያ ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ።
በተጨማሪም ሌተናል ጄኔራል አለምእሸት ደግፌ፣ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጅፕግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
128ተኛው ዓድዋ ድል በዓል ቀን ላይ አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!
የአድዋ ድል ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም አብሮነት የፀናበት ካስማ ነው!
የአድዋ ድል አርበኞቻችን የግል ፍላጎቶቻቸውን ለአገር ሉዓላዊነት እና ለህዝብ ነፃነት በማስገዛት የአስተሳሰብ ከፍታቸውን ያሳዩበት፣ በእኛ ትውልድ ብቻም ሳይሆን በመጭው ትውልድም ተመራማሪዎች ሊፈልቁበት የሚችሉ ትምህርት ቤት ነው።
የአድዋ ድል የምዕራቡም የሰሜኑም የምስራቁም የደቡቡም የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የጋራ ድል ነው::
የአድዋ ድል ሲታወስ የመሰማማት እና የመዳማመጥ ዋጋ ይታወሳል። በመሪዎችና በተመሪዎች ፣ በመሪዎችና በመሪዎች እንዲሁም በተመሪዎችና በተመሪዎች መካከል መደማመጥ ነበር ፤ የወራሪው የጣሊያን ፕሮፖጋንዳ በባንዳዎች ተከሽኖ ቢቀርብም የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ አልሰጠውም። መከባበር የዚህ ግዙፍ ድል መለያው ነው፤ ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ መናናቅ አልነበረም፡፡
ከጦርነቱ በፊት የነበረውን እረጅም አድካሚ ጉዞ በእግር በፈረስ የተጓዙት አርበኞቻችን ከፊት ለፊታቸው የአሸናፊነት ስነ -ልቦና እና የአይደፈርባይነት ቁጭት ሰንቀው ስለነበር በዱር በገደሉ ሲወጡ ሲወርዱ ወደፊት መገስገስን እንጅ ወደ ኋል ማፈግፈግን ምርጫቸው አላደረጉም።
አድዋ በአባት እና በእናት አርበኞቻችን የተመዘገበ የኢትዮጵያውያን ድል በመሆኑ በየትኛውም የዓለም ጫፍ አንገታችንን ቀና አድርገን በኩራት እንጓዛለን።
አድዋ የኢትዮጵያዊያን ፣ የአፍሪካውያን ፣ የመላው ጥቁር ህዝቦች እና የፍትህ ወዳድ ህዝቦች ሁሉ ድል ነው።
የቀለም ልዩነት በሚቀነቀንባት ፣ ፍትህ በጠፋባት ጭቁን ህዝቦች በድቅድቅ ጨለማ በነበሩባት ዓለም የበራ ሻማ ነው የአድዋ ድል።
አድዋ ላይ የተከፈለው መስዋዕትነት የህይወት፣ የፈሰሰው ደግሞ ደም ፣ የተከሰከሰውም አጥንት ነው። የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን አሸናፊነት በመጠናቀቁ በደስታ ብናከብረውም ለተከፈለልን መስዋዕትነት ፣ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ከሉዓላዊነቷ ጋር ያወርሱንን አገር የላብ መስዋዕትነት ከፍለን ድህነትን ድል ባለማድረጋችን በቁጭት ጭምር ነው የዓድዋን ድል የምንዘክረው።
የዓድዋ ድል የዓላማ ፅናት ከያዝን ሁሉንም ችግሮቻችን እንደምንቀርፍ ፅኑ እምነት የምንሰንቅበት ለላቀ ድልም ቃል የምንገባበት ነው።
ከድልም በላይ የሆነው የዓድዋ ድል በሚገባው ልክ ሳይዛከር ፣ በክብሩ ልክ ሳይከብር ፣ በጋራ መስዋዕትነት የተገኘው ድል በዓል አከባበር ጭምር አንዳንዴ የልዩነት እና የግጭት ምክንያት ሆኖ 128 ዓመት መቆየቱ እንቆቅልሽ ብቻም ሳይሆን ቁጭትን ያጭራል።
ህብረብሔራዊ አንድነትን ለማፅናት ቆርጦ የተነሳው የለውጡ መንግስት የወል ታሪኮቻችን ላይ የተራገፈውን አቧራ ለማራገፍ ጊዜ አላባከነም።
መልካም ወረቶችን የማብዛት ፣ ስህተቶችን ፈጥኖ የማረም አቅጣጫን የተከተለው የመደመር መንገድ አሰባሳቢ ነው።
ከአሰባሰቢ ትርክቶቻችን አንዱ የሆነው የአድዋ ድል ተገቢውን ክብር እንዲያገኝ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሀሳብ አመንጭነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈጻሚነት በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቅርብ ክትትል የኛ ትውልድ አሻራ ያረፈበት የአድዋ ድል መታሰቢያ ታሪክን የሚዘክር ቅርስ ሆኖ ተጠናቋል።
የአድዋ ድል መታሰቢያ የከተማች ድምቀት፣ የህዝባችን ኩራት፣ የአገር ውስጥና የውጪ አገር ቱሪስቶች መዳረሻ የሚሆን ታሪክንና ቅርስን አጣምሮ የያዘ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
የአድዋ ድል መታሰቢያ ታሪክን መዘከር ብቻም ሳይሆን ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ ሬስቶራንቶች፣ ከ 1000 በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ ፓርኪንግ ፣ የልጆች መዝናኛ ፣ የኪነ-ጥበብ ማሳያ እና መሰል አገልግሎቶች የሚሰጡ ክፍሎች የተካተቱበት ከምንም በላይ ቱሪስቶች የሚጎርፉለት ለትውልድ የሚተላለፍ ቋሚ ሀብታችንም ነው፡፡
ወንድማማችነትን ፣ እህትማማችነትን እና አብሮነትን በሚዘክረው አገራዊና አህጉራዊ ትርጉም ባለው በአድዋ ድል መታሰቢያ የዓድዋ ድል በዓል እንዲከበር መደረጉ ጥላቻ ቦታውን እንዲያጣ አድርጓል፤ ከፋፋይነትንም የሚያስተናግደው አይኖርም።
መሪና ተመሪ ተደማምጦ የተመዘገበ አኩሪ ድል እንደመሆኑ በዓሉን ስናከብረም በመደማመጥ ፣ በመከባበር ፣ ህግና ስርዓትን በመከተል በመከራ ጊዜ ጭምር የማይላላውን የተጋመደ ማንነታችን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን ግድ ይላል።
የዓድዋ ድል በፍቅር በመሰባሰብ እንጅ በጥላቻ በመገፋፋት የተገኘ ባለመሆኑ በዓሉን ስንዘክርም ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም አብሮነት የፀናበት ካስማ የበለጠ እንዲጠብቅ በማድረግ ሊሆን ይገባል !
እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን!
የዘንድሮውን የዓድዋ ድል በዓል የምናከብረው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን ድሉን በሚመጥን መልኩ መታሰቢያ ገንብተን የዓድዋን ጀግኖች እየዘከርን በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል::
ኢትዮጵያዊያን ልዩነቶችን ሁሉ ትተው በአንድነት “ሆ” ብለው ተነስተው የተዋደቁበት እና የጋራ ድል የተጎናጸፉበት ይህ ታላቅ የድል ታሪክ የአንድነት፣ የመከባበር፣ የፍቅር፣ የጀግንነትና የፅናት ምልክት ሆኖ በወርቅማ ቀለም የተፃፈ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የጋራ ታሪካችን ነው፡፡
የዓድዋ ድል ታሪክ ለእኛ እና ለመጪው ትውልድ በአንድነት አገርን የመጠበቅ የመውደድናለአገርን ቅድሚያ የመስጠት አደራም ጭምር በመሆኑ፣ በአንድነት፣ በመከባበር፣ በፍቅር፣ በጀግንነትና በፅናት ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ዳር በማድረስ የራሳችንን ዘመን የጀግንነት ታሪክ በጋራ እንድንፅፍ ያነሳሳናል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
በድጋሚ እንኳን አደረሰን!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
https://twitter.com/ProsperityKera
ከዛሬ ጀምሮ በቀጣዮቹ 10 ቀናት በበልግ አብቃይ አካባቢዎች የዝናብ መጠንና ስርጭቱ እየተስፋፋና እየተጠናከረ እንደሚሄድ ተመላከተ፡፡
በአጠቃላይ ጅማ፣ የኦሮሚያ ክልል ሁሉም የሸዋ ዞኖች፣ ምዕራብ አርሲና አርሲ ዞኖች፣ ባሌ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ አዲስ አበባ፣ ምሥራቅ ጎጃም፣ የሰሜንና የደቡብ ወሎ ዞኖች፣ የዋግኽምራ ዞኖች፣ የሰሜን ሸዋና የኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚኖራቸው ተጠቅሷል፡፡
በጥቂት ስፍራዎቻቸውም ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ መባሉን የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ቡኖ በደሌ፣ ኢሉአባቦር፣ ጉጂ፣ የቦረና ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ ሐረሪ እና ድሬዳዋ፣ የደቡብ ጎንደር ዞን፣ የአፋር ክልል ዞኖች፣ የደቡብ፣ የደቡብ ምስራቅ እና የምስራቅ ትግራይ ክልል ዞኖች፣ የሶማሌ ክልል ሲቲ፣ ፋፈን እና ዳዋ እንዲሁም ጥቂት የሊበን ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ 38 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የዓድዋ ድል ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ማንነት ግንባታ ትልቅ መሰረት የጣለ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ 128ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም÷ የዓድዋ ድል በታሪክ ዓለም የሚያውቀው እና ለሁሉም አፍሪካውያን የነጻነት አርማ ሆኖ እንደሚዘከር አውስተዋል፡፡
የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚናገሩበት እና ጥቁሮች ነጮችን ድል የተቀዳጁበት ሁነት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የምንጊዜም ታሪክ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ በኩራት የሚተላለፍ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የዓድዋ ድል መታሰቢያን ስናከበር ከልዩነት ይልቅ አንድነትን እንዲሁም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን በማጉላት መሆን እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
እንኳን ከ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፡፡
እናቶቻችንና አባቶቻችን ታላቁን የዐድዋ ድል ከሰጡን 128 ዓመታት አስቆጥረናል፡፡ የዐድዋ ድል የሰጠንን ዕሴቶች ግን በሚገባ የተጠቀምንባቸው አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ አራቱን ታላላቅ የዐድዋ ድል ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምባቸው የግድ ይለናል፡፡
የመጀመሪያው ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ነው፡፡ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያ ዋናው መልኳ መሆኑን ከዐድዋ ዘመቻ በተሻለ ለማሳየት የቻለ ክሥተት በዘመናዊ ታሪካችን አናገኝም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ ሁለት ጊዜ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አሳይቷል፡፡ የመጀመሪያው በጦርነቱ ዘመቻና ድል ጊዜ ነው፡፡ ዛሬ በምናውቃት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ማኅበረሰቦች መካከል ወደ ዐድዋ ያልዘመተ ወገን የለም ብሎ መናገር እውነትን መናገር ነው፡፡ ሁለተኛው ክሥተት ደግሞ የዐድዋ ድል በተገኘ በሰባት ዓመቱ የዐድዋ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሲከበር ትርዒቱን ያቀረቡት ከተለያዩ የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦችች የመጡ የኢትዮጵያ ጦር አባላት ነበሩ፡፡ በዚህ ትርዒት ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊት ሀገር መሆንዋን በዐደባባይ ሰልፈኛው አሳይቶ ነበር፡፡
ይሄንን በዐድዋ ዘመቻና በዓል የተንጸባረቀ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አጽንተን ልንይዘው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት ኅብረ ብሔራዊ ማነነት ያላቸው ሕዝቦች በአንድነት የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡ ኅብረ ብሔራዊነታቸው ከፈጣሪ ሲያገኙት ነው፡፡ አንድነታቸውን ደግሞ እነርሱ ራሳቸው በዘመናት ትሥሥርና መሥዋዕትነት ገንብተውታል፡፡ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁለቱን፣ ነገር ግን አንዱ ከሌላው ጋር ሳይነጣጠል የሚኖሩትን መገለጫዎቿን ትታ ኢትዮጵያ አትሆንም፡፡ በእያንዳንዱ ጉዞዋ ይሄንን እያረጋገጠች መጓዝ አለባት፡፡
ሁለተኛው ዕሴት ለታላቅ ሀገራዊ ዓላማ ሲባል ንኡስ ፍላጎቶችን መሠዋት ነው፡፡ ወደ ዐድዋ የዘመቱ ሁሉ በወቅቱ በነበረው ሥርዓተ መንግሥት የሚስማሙና የተደሰቱ አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ግጭትም ቅራኔም ነበራቸው፡፡ አንዳንዶቹም በነበረው ሀገራዊ ሁኔታ ቅር ተሰኝተው ከጠላት ጋር የሚሠሩ ነበሩ፡፡ ነገሩ የሀገር ጉዳይ ሲሆንባቸው ግን ሁሉም ንኡስ ፍላጎቶቻቸውን ትተው፣ ለታላቁ ፍላጎት ለሀገር ህልውና መሥዋዕት ለመሆን መጡ፡፡ ማንኛውም ፍላጎት ከሀገር ፍላጎት በታች መሆኑንም አሳዩን፡፡
እንኳን ዛሬ ብዙ ዓይነት መረጃ፣ ዕውቀትና የሐሳብ መንገዶች ባሉበት ዘመን ቀርቶ ከመቶ ዓመት በፊትም ሰዎች ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ነበሯቸው፡፡ በፍላጎቶቻቸው የተነሣም ቅራኔዎችና ግጭቶች ነበሩ፡፡ ሁሉንም ለአንድ ዓላማ የምታስተሣሥር ዓላማ ሀገር የምትባለው ናት፡፡ ዛሬም ንኡስ ፍላጎቶቻችን ከኢትዮጵያ አይበልጡም፡፡ ኢትዮጵያን የሚያዳክም፣ የሚያሳንስና የሚያሳጣ መንገድ ከትልቁ ዓላማ የሚጋጭ መንገድ ነው፡፡ ጦርነት የትልቁ ዓላማ የኢትዮጵያ ህልውና ማስከበሪያ እንጂ የንኡስ አካባቢያዊና ግላዊ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ ሊሆን አይገባም፡፡ ጦርነት ለትንሽ ነገር የሚወጣ ወጪ አይደለም፡፡ ዘመኑ ብዙ ፈተናዎች እንዳሉት ሁሉ ብዙ የመፍትሔ አማራጮችም አሉት፡፡ መከራከር፣ መነጋገር፣ መወያየት፣ በሕግ መዳኘት፣ አንዱ ሌላው መሸከም፣ የትየለሌ አትራፊ መንገዶች አሉት፡፡ ትልቋ ዓላማ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ስንል ንኡስ ዓላማዎቻችንን እያመሙን እንኳን ቢሆን መሠዋት አለብን፡፡
ሦስተኛው ዕሴት የጦርነትን ምርቅና ፍትፍት ማወቅ ነው፡፡ ጦርነት ምንም ያህል በአሸናፊነት ቢጠናቀቅ የሚያስከፍለው ዋጋ አለው፡፡ የዐድዋ ዘማቾች ሀገር ሆኖባቸው፤ ሉዓላዊነት ሆኖባቸው፤ የታላቅ ዓላማ ጉዳይ ሆኖባቸው እንጂ ጦርነት የመጀመሪያ አማራጫቸው አልነበረም፡፡ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ነገሩ በሰላም እንዲቋጭ ደጋግመው ጽፈዋል፤ ለምነዋል፡፡ አልሆነም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ የኢትዮጵያ ዘማቾች ግን ከድል የተመለሱት በደስታ ብቻ አይደለም፡፡ ከፊታውራሪ ገበየሁ ጀምሮ አያሌ ጀግኖች ለትልቁ ዓላማ ለኢትዮጵያ ህልውና ሲሉ ተሠዉተዋል፡፡ የሄዱት ሁሉ አልተመለሱም፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት በድልና በኀዘን ነው የተመለሰው፡፡ ብዙዎችም በየአካባቢያቸው በፌሽታ አልነበረም ድሉን ያከበሩት፡፡ እንኳን በራሳቸው ወገኖች፣ በጣልያኖች መሞት ኢትዮጵያውያን አዝነዋል፡፡
ጦርነት ተገድደን ብቻ ለትልቁ ዓላማ ስንል የምንገባበት የመጨረሻ አማራጭ እንጂ ከደረት ኪሳችን ቶሎ የምንመዘው አይደለም፡፡ እዚህም እዚያም የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በጠመንጃ ለመፍታት መነሣት የዐድዋ ዘማቾችን ኀዘን አለመጋራት ነው፡፡ የዐድዋ ዘማቾች ድልን ብቻ ሳይሆን ጦርነት የሚያስከትለውን መከራም ጭምር አስተምረውን አልፈዋል፡፡
አራተኛው ትዕግሥት፣ ዝግጅት እንጂ ፍርሐት አለመሆኑን ነው፡፡ ጣልያኖች ከሦስት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን ሲገፏት ነበር፡፡ በሀገሪቱ የደረሰውን የእንስሳትና የሰዎች ማለቅ ምክንያት አድርገው ትንኮሳውን አባብሰው ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እየተገፋች እንኳን ቢሆን ታግሣለች፡፡ ትዕግሥቷ ግን ከዐቅመ ደካማነቷ የመጣ አይደለም፡፡ ለባሰው ነገር እየተዘጋጀች ስለነበር እንጂ፡፡ እህል እስኪደርስ፣ ሰው እስኪያገገም፤ የተገዛው መሣሪያ እስኪደርስ፣ የደረሰው መሣሪያ ከጦሩ ጋር እስኪላመድ ታግሣለች፡፡ በመጨረሻ ግን የትዕግሥቷን ውጤት በዐድዋ ተራሮች ላይ አሳይታለች፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬም ትታገሣለች፡፡ እየተገፋችም እንኳን ቢሆን ትታገሣለች፡፡ የምትታገሠው ስለሚያቅታት አይደለም፡፡ ለባሰው ነገር ስለምትዘጋጅ ነው፡፡ ያ የባሰው ነገር ሲመጣ የዐደዋውን ድል በብዙ እጥፍ ትደግመዋለች፡፡
እነዚህን ዕሴቶች ዘወትር ማሰብ፣ አስበን መተግበር እንድንችል የሚያስታውሰን ነገር ያስፈልግ ነበር፡፡ ዐድዋን የሚመጥን ታሪኩንም ዕሴቱንም የምናስብበት መታሰቢያ ዘመቻው በተጀመረበት ሥፍራ ባስገነባን ማግሥት ነው በዓሉን የምናከብረው፡፡ ይሄም ለዘንድሮው በዓል ሞገስና ክብር ጨምሮለታል፡፡ ዛሬ መታሰቢያውን በከበረ ሁኔታ አከናውነናል፡፡ ነገ ግን የአድዋን ዕሴቶች በሚገባ በመጠቀም እንደ ዐድዋ ተራሮች የጸናች ኢትዮጵያን መገንባት ይቀረናል፡፡ ያ ደግሞ የሁላችንንም ስክነት፣ ብስለትና ጥምረት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ መልካም የዐድዋ ድል በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
የካቲት 22/2016 ዓ.ም
https://twitter.com/ProsperityKera
ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በተከሰበት የወንጀል ክስ በአንድ አመት ቀላል እስራት እና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወሰነ።
የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ተከሳሹ ያቀረበውን አምስት የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን ይዟል።
የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።
ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።
ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም የቀረበበት ክስ እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያውን በጽሁፍ ያቀረበ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሊሻሻል የሚችልበት የህግ አግባብ እንደሌለ ተጠቅሶ መልስ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።
ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማምረጃውን አቅርቧል።
የቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ የቀረቡበት ሶስት ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።
ሶስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣ በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሶ ነበር።
ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል።
ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።
ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱ ታስቦ የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ ቅጣቱ ከብዶ እንዲጣል ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ለአካባቢ ጥበቃ ያበረከተውን አስተዋጾኦ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለው ገልጾ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ይዞለታል።
ፍርድ ቤቱ በድርጊቱ የእርስ በእርስ ግጭት አለመፈጠሩንና ጉዳት አለመድረሱን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዕርከን 6 መሰረት በአንድ ዓመት ቀላል እስራትና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ከነሃሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ጊዜ ታሳቢ እንዲያደርግ ታዟል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ለ128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
በዓሉ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
• ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ
• ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ
• ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ
• ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ክብረ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግራሙ በሚካሄድበት በዓድዋ መታሰቢያ ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑንም ፖሊስ አሳስቧል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
'ዓድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ’ በሚል ሲካሄድ የቆው ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ የማጠቃለያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም በመድረኩ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወከሉ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የንቅናቄ መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርትና ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ለሳምንታት በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የሁለት ቀን ይፋዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ኬንያን ተሰናብተዋል::
Prime Minister Abiy Ahmed and First Lady Zinash Tayachew depart Nairobi, Kenya following a two-day State visit.
#PMOEthiopia
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የሁለት ቀን ይፋዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ኬንያን ተሰናብተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
WOW 👌 🇰🇪🇰🇪🇰🇪 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://twitter.com/ProsperityKera
የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያ ጉብኝትንና የኢትዮ ኬንያ ግንኙነት በተመለከተ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ የሰጡት ማብራሪያ
https://twitter.com/ProsperityKera