I warmly welcome the Foreign Minister of Denmark, Lars Rasmussen, to Ethiopia. Our countries share longstanding ties that provide a solid foundation for further collaboration. Our discussions have been productive, covering a wide range of bilateral and multilateral issues.
© Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል። ዛሬ ማለዳ ባንኩ በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ላይ ከዶክተር አብዱል ካማራ ጋር ተወያይተናል። በተጨማሪም ወንድሜ ዶ/ር አኪንዉሚ አዴሲና የኦባፌሚ አዎሎው የአመራር ሽልማትን በማግኘቱ ይህን ዕድል ተጠቅሜ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት እወዳለሁ።
Ethiopia's partnership with the African Development Bank continued to be productive. This morning, I received and held discussions on AFDB's projects in Ethiopia with Dr. Abdul Kamara. Additionally, I seize this opportunity to congratulate my brother, Dr. Akinwumi Adesina, on receiving the Obafemi Awolowo Prize for Leadership.
© Abiy Ahmed Ali (phd) FDRE 🇪🇹 PM
https://twitter.com/ProsperityKera
ሚዲያዉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞችና የመዳረሻ ትልሞች እንዲገነዘብ የሚያስችል ሥልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና የሚዲያ ሚና” በሚል ጭብጥ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለሚዲያ ዋና አዘጋጆች፣ ምክትል ዋና አዘጋጆችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡
ከ25 በላይ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የተውጣጡ ዋና አዘጋጆች፣ ምክትል ዋና አዘጋጆችና ከፍተኛ ባለሙያዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንና ከአገልግሎቱ የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም እየተሳፉ ነው፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ “የሀገራዊ ገዥ ትርክት ግንባታ ምንነትና የሚዲያ ሚና” በሚል ርእስ ሥልጠና እየሰጡ የሚገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ማስተባበሪያ ማእከል አስተባባሪ ሚኒስትር ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ብዝኃነትንና አንድነትን በማዋሐድ ብሔራዊነትንና ዐርበኝነትን ማእከል ያደረገ ትርክት ግንባታ ላይ እንደምትገኝና ለዚህም ሚዲያዉ ጉልህ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡
ሚዲያ ትርክትን የማስረጽ ዐቅሙን ተጠቅሞ ፍጹማዊ አንድነትና ፍጹማዊ ልዩነት ላይ ከማተኮር ይልቅ አካታች የወል ትርክት ላይ በመቆም ብዝኃነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት እንዲተጋም አስገንዝበዋል፡፡
የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው ሥልጠናዉ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችና የመዳረሻ ትልሞች የወል መረዳት እንዲኖራቸዉ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ቀናት ሥልጠናዉ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችና የሚዲያ ሚና፣ የኢትዮጵያ የሚዲያ ዓውድ እና የኢትዮጵያ የሚዲያ አፈጻጸም ምልከታ” በሚሉ ሌሎች ይዘቶች ላይ አተኩሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
መምህራን በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል ከነገ ጀምሮ የማደራጀት ስራ እንደሚጀምር የአዲምህራንባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፤የከተማው መምህራን ማህበር እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኮሚሽን ጉዳዩን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እንዳስታወቁት ከተማ አስተዳደሩ መምህራን የቤት ባለቤት ሆነው ከተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ተላቀው ትውልድ የመገንባት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ከ30ሺ በላይ ቤት ፈላጊ መምህራን መረጃ መደራጀቱን አስታውቀዋል።
ዶክተር ዘላለም አክለውም ቤት ፈላጊዎቹን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው ወደ መደራጀት እንዲገቡ ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርትና የህብረት ስራ ኮሚሽን መዋቅሮች ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት አድርገዋል ፡፡
መምህራን የማደራጂያ ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት የቁጠባ ባህላቸውን አሳድገው ወደ ግንባታ መግባት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ በተለይም ክብርት ከንቲባና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
መምህራንም የመኖሪያ ቤት ሁለተኛ የስራ ቦታቸው እንደመሆኑ በአግባቡ በመቆጠብ የቤት ባለቤት የሚያደርጋቸውን ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሀብተየስ ዲሮ ኮሚሽኑ የመምህራንን ጥያቄ ለመመለስ በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት በመዘጋጀቱን ተናግራዋል ፡፡
ኮሚሽኑ ሁሉንም ቤት ፈላጊዎች በማደራጀት 30 ፐርሰንቱን የሚቆጥቡትን በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ እንደሚያደርግና ሌሎች እየቆጠቡ የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን ማሙዋላት ሲችሉ ወደ ግንባታ እንዲገቡ የሚደረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ የቤት ፈላጊዎቹን አጠቃላይ መረጃ የያዘ ሰነድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሀብተየስ ዲሮ ማስረከባቸውንም ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የዛሬ ትውልድ ዓድዋ ሀገራችን የባህር በር እንድታገኝ መተባበር መቻል ነው።
ዶ/ር ሚኤሳ ኤለማ ሮቤ
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የሚዲያና ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ሀላፊ
https://twitter.com/ProsperityKera
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም(ዶ/ር) ለጋዜጠኞች በወቅታዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
አምባሳደር መለስ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቀጣናው በኢነርጂ እና አቬሽን ዲፕሎማሲ ጠንካራ ትስስር እንዲፈጠር እየሠራች መሆኑን አንስተዋል።
ቃል አቀባዩ የሰሞኑ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኬንያ እና የታንዛኒያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የተፈረሙ ሥምምነቶች መካከል የኢነርጂ እና አቬሽን ዘርፎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል። ይህ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት መሥጠቱን ያመለክታል ብለዋል።
አምባሳደር መለስ(ዶ/ር) የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የኢትዮጵያ በቀጣናዊ ትስስር እና ትብብር ላይ ያላት ተፈላጊነት ከፍተኛ መሆኑን ያረጋገጠ መሆኑን አብራርተዋል።
ጉብኝቱ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ አስፈላጊ አጋር መሆኗ የታየበት እንደሆነም አምባሳደር መለስ(ዶ/ር) ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ለኬንያ የምታካሂደው የኃይል ሽያጭ የደቡባዊና ምዕራብ አፍሪካ የሚያሻግር የኢነርጂ ትስስር( Energy Connectivity) የአህጉሩ ፕሮጀክት አካል ይሆናል ብለዋል። አምባሳደር መለስ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በቀጣይ ኤሌክትሪክ ኃይል ለዳሬሰላም አራት መቶ ኪሎ ቮልት በሽያጭ መልክ ለማቅረብ መስማማቷ ኢነርጂ ዲፕሎማሲ አንዱ አካል መሆኑን አስረድተዋል።
በአቪየሽን የዲፕሎማሲ መስክ በበረራ ያለውን ትብብር ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስምምነቱ ያግዛል ነው ያሉት።
ከአውሮፓውያኑ 2016 እስከ 2023 ድረስ 75 የታንዛኒያ አብራሪዎች እና 25 በዘርፉ የሚሰሩ የበረራ ቴክኒሺያን በኢትዮጵያ ሥልጠና ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።
ቃል አቀባዩ ሌሎች በሳምንቱ በሚኒስትር ዴኤታዎች የተከናወኑ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተም ማብራርያ መስጠታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በ2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት በሀገሪቱ 1 ሺህ 536 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች የማምረት ስራ መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 የሁለተኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግመገማ እየተካሄደ ነው።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፤ የግምገማው ሂደት ትኩረት ካደረገባቸው ኢኮኖሚያዊ መስኮች መካከል አንዱ የኢንዱስትሪ ዘርፉ አፈጻጸም መሆኑን ገልጸዋል።
የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም በተለያዩ ችግሮች ደካማ እንደነበር ጠቅሰው በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በስፋት ወደ ምረት አንዲገቡ መደረጉን አስታውሰዋል።
በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድና በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተወሰዱ እርምጃዎች የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ወደ 56 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ማለቱንም ገልጸዋል።
ከፋይናንስ፣ ከጥሬ እቃ አቅርቦት፣ ከሰው ኃይል፣ ከገበያ ትስስር፣ ከኤሌክትሪክና መሰል መሰረተ ልማቶች ማሟላት አኳያ ያሉ ችግሮችን በተቀናጀ መንገድ በመፍታት በውጤቱ የማመረት እቅም ማደጉን ተናግረዋል።
የፍጆታ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ለወጪ ንግድ ብቻ ሳይሆን ገቢ ምርት መተካት ላይ የተሰጠው ትኩረት በግምገማው በአዎንታዊ አፈጻጸም መነሳቱን ጠቅሰዋል።
በበጀት አመቱ ስድስት ወራት በተኪ ምርት 1 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 994 ሚሊዮን ዶላር መሳካቱን ጠቅሰው አፈጻጸሙም 93 በመቶ መሆኑን አንስተዋል።
በግማሽ ዓመቱ 67 የውጭ ባለሀብቶችን በኢንዱስትሪ ዘርፉ በኢንቨስትመንት ለመሳብ ታቅዶ 127 ባለሀብቶች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ መደረጉንም ገልጸዋል።
ከሀገር ውስጥ ደግሞ 2 ሺህ 300 አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ኢንቨስትመንት ለማስገባት ታቅዶ 1 ሺህ 490 ያህል ወደ ዘርፉ መሰማራታቸውን ተናግረዋል።
በኢንቨስትመንት ከማሰማራት ባለፈ ባለፉት ስድስት ወራት የውጭና ሀገር በቀል ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት እንዲገቡ በተሰራው ስራ 1 ሺህ 536 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ማምረት መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለ142 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ121 ሺህ የስራ ዕድል መፈጠሩንም ገልጸዋል።
በመድረኩ ከተዳሰሱ የዘርፉ ተግባራት መካከል የኢትዮጵያ ታመርት ንቅናቄ አፈጻጸም ይገኝበታል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ንቅናቄው ባለፉት ሁለት ዓመታት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል።
የሀገሪቱን ሀብት በማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ ለሀገር ውስጥ ምርት ቅድሚያ በመስጠት፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፣ የቅንጅት ችግሮችን በመፍታት፣ የፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ ረገድ ውጤቶች መመዝገባቸውን አመላክተዋል።
አምራች ኢንዱስትሪው በሀገራዊ ጥቅል ምርት ያለውን ድርሻ ለማሳደግ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት፣ የመንግስት ግዥ ለሀገር ውስጥ ምርት ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲስተካከል፣ መሰረተ ልማትን ጨምሮ ምቹ ሁኔታ የመስጠት ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ መቀመጡን ገልጸዋል።
ከወጪ ንግድ አኳያ ዘርፉ ያለው ዝቅተኛ አፈጻጸም እንዲያድግ በልዩ ትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ኢትዮጵያ በየዓመቱ በበርሊን ጀርመን በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፈች ነው
ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን (ITB) በመላው ዓለም የሚገኙ ስመጥር የቱሪዝም ኩባንያዎች እና ሀገራት ያላቸውን መዳረሻ እና የቱሪዝም አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኤግዚቢሽኑ ተገኝተው ኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናውነች ያለችውን የመዳረሻ ልማቶች እና የቱሪስት መስህቦችን እያስተዋወቁ ይገኛሉ።
ሚኒስትሯ በመድረኩ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋርም በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውይይት ማድረጋቸውን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ የሀገር ውስጥ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።
https://twitter.com/ProsperityKera
estifopp" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp
Читать полностью…ማቀድ፣ በወቅቱና በጥራት መፈጸም፣ ለህዝቡ ግልጋሎት ማዋል፦ የብልፅግና ፓርቲ መለያ ባህሪያት!
https://twitter.com/ProsperityKera
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያና ታንዛኒያ ቆይታ
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera
ድንኳን ወስጥ ሲያድሩ ውጪ ያደረጉት ጫማ በላም የመወሰዱ ዕድል እጅግ የጠበበ ነው።
ዜሮ ፐርሰንት ግን አይደለም።
https://twitter.com/ProsperityKera
በታንዛኒያ የነበረን ቆይታ
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን Abiy Ahmed Ali (phd)
https://twitter.com/ProsperityKera
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፕሮጀክት ሳይሆን ታሪክ ነው!
ቀደምት አባቶችና እናቶቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀና ብለን እንድንሄድ ያስቻለንን የዓድዋ ድልና ታሪክ አውርሰውናል፡፡ ድሉን ሊያጎናፅፉን የቻሉት በታጠቁት ዘመናዊ መሣሪያ ወይም አደረጃጀት ሳይሆን ለጋራ ዓላማ በፅናትና በአንድነት በመሰለፋቸው ነው። በመሆኑም የዓድዋ ድል ትውልድ ሊማርበት የሚገባው የዓላማ አንድነትና የፅናት ውጤት ነው፡፡
የአሁኑ ትውልድም ታዲያ በዓድዋ መንፈስ ሆነን፤ በድሉ ብስራት ጠንክረን፣ ኢትዮጵያ የምትጠብቅብንን ደማቅ ታሪክ ዳግም መስራት መቻል አለብን፡፡ ብዙ ያልሰራነው ፣ ገና ያልፈጸምነው በርካታ የቤት ስራዎች አሉብን፡፡ አባቶቻችንና እናቶቻችን ያወረሱን የዓድዋ ድል ፍሬ ከጫፍ እንዳይደርስ ብልፅግናችን በቅርበት እውን እንዳይሆን በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ ወደ ኋላ የሚጎትቱን ነገሮች ብዙ ናቸው፡፡ የዓድዋ ጀግኖች እንዳደረጉት ትልቁን መዳረሻችንን አልመን የስኬትን ማማ እንድንቆናጠጥ የብልፅግና ሳንካዎችን ከራሳችን በማራገፍና በመታገል በጋራ አብረን መቆም ይኖርብናል፡፡
የዚህ ትዉልድ ትልቁ ዓድዋ የስራ ባህላችንን በመሰረታዊነት በማሻሻል ድህነት ከሚባል ታሪካዊና አዋራጅ ጠላታችንን ድል በማድረግ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን ማድረግ መቻል ነዉ፡፡
የመደመር ትውልድም ከአባቶቹ በመማር በዓለም አደባባይ እውቅና የተቸራቸውን በርካታ ስኬታማ ገድሎችን እየፈጸሙ ወደ ብልፅግና ማማ እየገሰገሱ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት፡- በጠቅላይ ሚኒስተር ዓብይ አሕመድ ( ዶ/ር ) ሀሳብ አመንጪነት እና በከንቲባ አዳነች አቤቤ የቅርብ ክትትል ዳግማዊ ዓድዋ የሆነውን የዓድዋ የድል መታሰቢያ እውን ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፕሮጀክት ሳይሆን ታሪክ ነው!
የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ያከበርነው እንደ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን ድሉን በሚመጥን መልኩ መታሰቢያ ገንብተን የዓድዋን ጀግኖች እየዘከርን በመሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል፡፡ የዓድዋ ድል የኢትዮጵያዊያን ብቻም ሳይሆን የሁሉም አፍሪካዊያን እና ጥቁር ሕዝቦች ኩራት በመሆኑ ሙዚየሙ በአለም አቀፍ ደረጃ ድሉን ለማስተዋወቅ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው፡፡
የአሁኑ ትውልድም አንድ ሁነን እንደ ብዙ፣ ብዙ ሁነን እንደ አንድ በመሆን ልክ እንደ ዓድዋ ድል መታሰቢያ በሌሎች የልማትና የሰላም መስኮች በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊና በፖለቲካው መስክ የሀገራችንን ብልፅግና ሊያረጋግጡ የሚችሉ ሌሎች የዓድዋን
ድል ፍሬ ደጋግመን ማሳካት ይኖርብናል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
128ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በማስመልከት የቀረቡ ትርዒቶች በምስል
https://twitter.com/ProsperityKera
አንብብልኛ ማለቴ አዳምጥልኛ?
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
https://twitter.com/ProsperityKera
ኢትዮጵያና ሞሮኮ በሰላም ግንባታና የመከባበር ባህልን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን ተስማሙ።
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ነዢህ አላመሐመዲ ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሀገራቱ በትብብር በሚሠሯቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።
ሞሮኮ እና ኢትዮጵያ ያላቸውን መልካም የዲፕሎማሲ ግንኙነት አጠናክረው የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡና በተለይም የሰላም ግንባታውን ውጤታማ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የምክክር ባህል እንዲዳብርና ልዩነቶችንም በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ልምድ እንዲገነባ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ሚኒስትር ዴዔታው ለአምባሳደሯ ገልፀዋል።
ይህንን መልካም ጅማሮ ለማጠናከር በሁለቱ ሀገራት መካከል መከናወን ስላለባቸው ኃላፊነቶችና ድጋፎች ዙሪያም ተነጋግረዋል።
የሞሮኮ አምባሳደር ነዢሀ አልመሀመዲ በበኩላቸው ሞሮኮ በመቻቻልና በአብሮነት ዙሪያ ጥሩ ልምድ እንዳላት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያም ካላት ረጅም ታሪክ በተለይ በሀይማኖቶች መካከል የዳበረ የመከባበር ባህልና ከሀገሪቱ ብዝሀነት አቅም በርካታ ተሞክሮ መውሰድ እንደምትፈልግም ተናግረዋል።
በሀገራቱ መካከል ያለውን መቀራረብ የበለጠ ለማጠናከር የንጉስ መሀመድ ስድስተኛ ፋውንዴሽን መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ለመክፈት ፍላጎት እንዳለውም አምባሳደሯ ገልፀዋል።
በሀገራቱ መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከርም በትኩረት እንደሚሰሩም አምባሳደሯ ጨምረው መግለጻቸውን ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
8ኛው ኢትዮ ኸልዝ አውደ ርዕይ እና ጉባኤ በአዲስ አበባ ተከፈተ።
የሀገር ውስጥ የጤና ተቋማት፣ የመድሀኒት አምራችና አቅራቢዎችና የውጪ ሀገራትም እየተሳተፋበት ይገኛል። አውደርዕዩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።
በአውደርዕዩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ፤ አውደርዕዩ በጤናው ዘርፍ ላይ የሚታዩ የግብዓት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ነው።
የግል ዘርፉን ከጤና ባለሞያው ጋር በማቀናጀት የህክምና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
አወድርዕዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂና አቅራቢዎችን በማስተዋወቅ የእውቀት ሽግግርን ለማምጣትና የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግ የሚያስችል ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የአልጀሪያ አባሳደር በኢትዮጵያ ሞሀመድ ላሚን ላባስ፤ አውደርዕዩ በአፍሪካ የጤናውን ዘርፍ ለማሳደግና የልምምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ነው።
አፋሪካ ውስጥ ለጤና የሚውል ግብዓት የሚመረተው ሶስት በመቶ ብቻ ነው ያሉት አባሳደሩ የጤናውን ዘርፍ ችግር ለመቅረፍ በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ ከተማ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተወጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር በከተማ ልማት፣ በምግብ ዋስትና ሥራዎች፣ የወጣቶች ተሳትፎ፣ የቤቶች ልማት ሥራዎችና በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ "መዲናችን ከከተማ መስፋፋት ጋር የሚመጣ ፍላጎትን የሚያጎሉ ወሳኝ የሆኑ የዕድገት እና የለውጥ ሒደት ውስጥ ትገኛለች" ብለዋል።
የዛሬው ዓይነት ስብሰባዎች በሚታዩ ክፍተቶች የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ብሎም መልካም አጋጣሚዎችን ለመለየት እጅግ አስፈላጊ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
አፍሪካን በእግሩ ለማቋረጥ ላለፉት 310 ቀናት በሩጫ ላይ የሚገኘው የ26 ዓመቱ እንግሊዛዊ ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ሩሰል ኮክ አፍሪካን ከደቡብ ወደ ሰሜን በሩጫ ለማቋረጥ ከደቡብ አፍሪካ የተነሳው እ.አ.አ ሚያዚያ 22 ቀን 2023 ነበር፡፡
ወጣቱ ሩጫውን ከመጀመሩ በፊት አስፈላጊውን የጤና ምርመራ ማድረጉን እና የቪዛ ጉዳዮችን መጨረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እ.አ.አ ሚያዚያ 7 ቀን 2024 በቱኒዚያ ሰሜናዊ ጫፍ ሩጫውን ለማጠናቀቅ የወጠነው ሩሰል በአሁኑ ሰዓት በሞሪታኒያ የሰሃራ በረሃን በማቋረጥ ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡
እንግሊዛዊው የበረሃውን ሙቀት ለመቋቋም ሩጫውን ከአመሻሽ አንስቶ እስከ ማለዳ ድረስ በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሩጫ 310 ቀናትን ማሳለፉ የግል ህይወቱ ላይ ተጽእኖ ፈጥሮበት እንደሆነ የተጠየቀው ሩሰል “አሁን ቱኒዚያ ከመድረስ ውጪ ምንም ነገር አያስጨንቀኝም” ሲል መመለሱን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡
ከአትሌቲክስ ጋር ለተያያዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች ሩጫውን መጀመሩን የሚናገረው ወጣቱ እስካሁን ለዓላማው ከ190 ሺ ዩሮ በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ከዚህም ውስጥ የሲቪል ሥራው 98 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራው 78 በመቶ መድረሱ ተገልጿል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ የተጣለበት 13ኛ ዓመት "በኅብረት ችለናል!" በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል።
የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር በሰጡት መግለጫ፤ የግድቡ አጠቃላይ አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሕዳሴ ግድብ ላይ መግባባት የተደረሰበት የከፍታችን ምልክት ነው ብለዋል።
የመሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልፀዋል።
ባለፉት 13 ዓመታት 18 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ከሕዝብ ተሳትፎ ተሰብስቧል ብለዋል።
የመንግሥት ቁርጠኛ አቋምና የዲፕሎማሲ ጥረት እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ውጤት መሆኑን ገልፀዋል።
የይቻላል መንፈስ የፈነጠቀ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀው፤ በቀጣይም መሰል ፕሮጀክቶችን በተባበረ ክንድ መፈፀም ይገባናል ብለዋል።
በ13ኛው ክብረ-በዓል የቦንድ ሳምንት፣ አውደ-ርዕዮች፣ የምስጋና፣ ዕውቅናና ሌሎች የድጋፍ ማሰባሰብ የንቅናቄ መድረክ ዝግጅቶች እንደሚደረጉ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በቀጣይ የንቅናቄ ዝግጅቶችም 300 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ መታቀዱን ገልፀው፤ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በኢትዮጵያ የቀጥታ ትስስር የቡና ወጪ ንግድ ተግባራዊ በመደረጉ እንደ ሀገር የሚገኘውን ገቢ በእጥፍ ማሳደግ መቻሉ ተገለጸ።
የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ በተለይ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ አዲስ አሠራር ከመዘርጋቱ በፊት የቡና ወጪ ንግድ ይከናወን የነበረው በኢሲኤክስ በኩል ብቻ ነበር። በዚህም የተነሳ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ወደ ውጪ የተላከው ከፍተኛ የቡና ምርት መጠን ሁለት መቶ ሺ ቶን ብቻ ነው። ሲገኝ የነበረው ገቢም በዓመት በአማካይ ከስድስት መቶ እስከ ሰባት መቶ ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። ይህም ከሌሎቸ ቡና አምራች ሀገራት ጋር ሲተያይ ዝቅተኛ ነው። ለዚህ ደግሞ ቡና ከአርሶ አደሩ ተነስቶ ቡና ላኪው ጋር እስኪደርስ የነበረው የግብይት ሥርዓት የተንዛዛ መሆኑ ዋነኛው ምክንያት ነበር።
በቀደመው ሥርዓት አርሶ አደሩ ቡናውን እንዲሸጥ የሚፈቀድለት ማሳው ላይ ብቻ ሆኖ ዋጋውን የሚወስነው ደግሞ ሰብሳቢው ነው። ሰብሳቢው ለአቅራቢ ሲሸጥ የታጠበና የደረቀ የተፈጥሮ ቡና በሚለው በኢሲኤክስ በኩል ሲሆን፤ ቡናው መጋዘን ከገባ በኋላ ሰብሳቢው ዋጋውን የመወሰንም ሆነ የመደራደር መብቱ ይቀርና ዋጋው የሚወሰነው የቡናው ደረጃ የሚቀመጠው በኢሲኤክስ ውስጥ ባለ ባለወንበር በሚባል ወኪል በኩል ይሆናል። በተመሳሳይ ላኪውም ኢሲኤክስ ውስጥ ባለ ባለወንበር በሚባል ወኪል በኩል በመሆኑ የገዛውን ቡና አይነትና ደረጃ ማረጋገጥ እንኳን የሚችልበት እድል አልነበረም።
ይህም ለውጪ ገበያ የሚቀርበውን የቡና ምርት በመጠንም በገቢም ስለቀነሰውና በዘርፉ ተሳታፊዎች ቅሬታ በመቅረቡ ከኢሲኤክስ ውጪ የቡና ገበያ አማራጭ እንዲኖር በፖሊሲ ደረጃ ተወስኗል። ከእነዚህም መካከል በ2013 ዓ.ም ወደ ሥራ የገባው በቀጥታ ትስስር በአቅራቢና ላኪ መካከል የሚደረግ የግብይት ሥርዓት አንዱ ነበር ብለዋል።
ሥራው ሲጀመር የቀጥታ ትስስር ገበያ የነበረው ድርሻ ኢትዮጵያ ከምትልከው ከሁለት መቶ ሺ ቶን ቡና 20 በመቶ ብቻ ሲሆን፤ 80 በመቶ በኢሲኤክስ በኩል ይከናወን ነበር ። በቀጣይ ዓመት ምርቱም ጥራቱም ተሻሽሎ በ2014 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ 300 ሺ ቶን ቡና በመላክ በቡና የወጪ ንግድ ከፍተኛው መጠን አንድ ነጥብ አራት ሁለት ቢሊዮን ዶላር ማስገኘት ተችሏል። ይህም ከወጪ የቡና ንግድ ከ80 እስከ ዘጠና በመቶ ድርሻ እንዲይዝ አድርጎታል።
የግብይት ሥርዓቱ ተግባራዊ መሆን በ4 ሺ 900 ዶላር ሲሸጥ የነበረው አንድ ቶን ቡና 5 ሺ 400 ዶላር ያሳደገ ሲሆን፤ በ2015 ዓ.ም የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በ32 በመቶ በወረደበት ወቅት እንኳን ኢትዮጵያ የምታቀርበው በ18 በመቶ እንዲጨምር አስችሏል። ተጠቃሚነቱም ወደ አርሶ አደሩ ወርዶ ከ2013 ዓ.ም በፊት አንድ ቀይ እሸት ቡና በኪሎ ከአስር እስከ 12 ብር ይሸጥ የነበረውን በ2014 ዓ.ም እስከ 60 ብር ከፍ ብሏል። አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እየሆነ በመምጣቱም በ2013 ዓ.ም 600 ሺ ሄክታር የነበረው የቡና ማሳም በአሁኑ ወቅት አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን መድረሱን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እየተሳተፉ ነው።
በሩሲያ ሶቺ ከተማ እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉ ይገኛል።
በፌስቲቫሉ ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ20ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሳተፋ ይገኛል።
በዚህ ፌስቲቫል ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም እየተሳተፋ ሲሆን÷ መድረኩ ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲያስተዋውቁ እና እርስ በእርስ ልምድና ተሞክሯቸውን እንዲለዋወጡ የበኩሉን እገዛ የሚያደርግ ይሆናል።
ከፌስቲቫሉ ጎን ለጎን የባህል፣ የስፖርት፣ የሙዚቃ፣ የፋሽንና የዲዛይን ትዕይንቶች እየተካሄዱ መሆኑ ተገልጿል።
ይህም የኢትዮጵያን የቡና ስርዓትን ጨምሮ ሌሎች እሴቶችን ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ ፋይዳው የጎላ መሆኑም ታምኖበታል፡፡
ፌስቲቫሉ ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ 7 ቀን 2024 ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
በየዘመኑ ታሪካዊ አሻራ ላሳረፉ ጀግኖች ተገቢውን ክብር ልንሰጣቸው ይገባል፡፡
ዶ/ር ሜኤሳ ኤሌማ
https://twitter.com/ProsperityKera
የድሮ ምኞታችሁና የዛሬ ኑሯችሁ ሲለያዩ!
ያን ጊዜ፣ ድሮ፣ ስለወደፊቱ ስታስቡ እኖረዋለሁ ብላችሁ ታስቡት የነበረውን ኑሮ አሁን እየኖራችሁ ካልሆነ ይህንን ፈጽሞ እኖረዋለሁ ብላችሁ ያልጠበቃችሁትን የወቅቱን የኑሮ ሁኔታ ለመለወጥ ከመቻላችሁ በፊት በቅድሚያ መውሰድ ያለባችሁ እርማጃዎች አሉ፡፡
1. ያላችሁበትን የኑሮ ሁኔታ ባትቀበሉም እውነታውን ግን በፍጹም ሳትክዱ መቀበል . . .
2. ያን ጊዜ ያለማችሁትን ሕይወት አሁን ላለመኖራችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ መሞከር . . .
3. በአሁን ጊዜ ስላላችሁበት የኑሮ ሁኔታ ራስን ወይም ሰውን መውቀስ በማቆም ሃላፊነት መውሰድ . . .
4. ትንሽ ብታቅዱና ብትሰሩ ልትለውጡት በምትችሉትና ምንም ብትታገሉ በማትችሉት ሁኔታ መካከል መለየት . . .
5. ምንም ብትታገሉ በፍጹም ልትለውጡት የማትችሉትን ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመወሰን መቀበል . . .
6. በሚገባ አስባችሁበትና አቅዳችሁ ብትሰሩ ልትለውጡ በምትችሉት ነገር ላይ ትእግስት የተሞላበት የለውጥ እርምጃ መጀመር፡፡
7. የሚስከፍላችሁን ዋጋ ከፍላችሁ ስልጠናን፣ ኮቺንግን፣ ሜንቶርሺፕና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች መጠቀም፡፡
አሁን ያላችሁበት ሁኔታ ቀሪውን ዘመናችሁን የምታሳልፉበት የመጨረሻው ምእራፍ አይደለምና አይዟችሁ! ፈጣሪ ይረዳችኋል!
https://twitter.com/ProsperityKera
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን Abiy Ahmed Ali (phd) በኬንያ የነበራቸው ቆይታ 👌
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኬንያ እና ታንዛኒያ ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
128ኛው የዓድዋ ድል በዓልን በመከላከያ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ እጅግ ደማቅ በሆነ ስነስርአት አክብረናል።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
https://twitter.com/ProsperityKera
የዓድዋ ድል የዓላማ አንድነትና የጽናት ውጤት ነው!
ኢትዮጵያ በታሪኳ አንድም ጊዜ የሌላውን ፍለጋ ጥቃትና ወረራ ፈፅማ አታውቅም፡፡ በአንፃሩ ጠላቶችዋ በተለያዩ ዘመናት በተደጋጋሚ ከሩቅና ከቅርብ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ሆኖም ግን ኢትዮጵያዊያን ተሸንፈው እጅ የሰጡበት ወቅት የለም፡፡ ሁሉንም ወራሪዎች ድል አድርገው አንገት በማስደፋት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር አስጠብቋል፡፡
ከእነዚህ የወረራ ታሪክና የድል አድራጊነታችን የሁል ጊዜ ኩራታችን የሆነው ውቅያኖስን አቋርጠው ኢትዮጵያ ላይ ወረራ በመፈፀም ሉዓላዊነታችንን ለመጋፋት የተንቀሳቀሱ የቅኝ ገዢ ሕልምና ምኞት ያከሰመው የዓድዋ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን ነፃነታቸውን ለማስጠበቅ የተቃጣባቸዉን የኢጣሊያን ወረራ በመመከት ዓለምን ጉድ ያሰኘ ታላቅ ጀብዱ በዓድዋ ተራሮች ላይ የፈጸሙት የዛሬ 128 ዓመት፣ በየካቲት 23/1888 ዓ.ም ነበር።
የዓድዋ ድል የመላ ጥቁር ሕዝቦችን ነጻነት ያበሰረ የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ድል ነበር። ውርደትና ሽንፈትን የተከናነበው የኢጣሊያን ጦር ሞትና ምርኮኛ ሆኖ በዓድዋ ተራሮች ላይ ቀርቷል። በዚህም ሮምን ጨምሮ የዓድዋ የድል ችቦ በመላው ዓለም ላይ ተቀጣጥሏል። ጥቁሮች ነጭን ማሸነፍ እንደሚችሉ በተግባር ያስመሰከሩበት የተጋድሎ ውጤትም ሆኖ በታሪክ ተመዘገበ። በመሆኑም የዓድዋ ድል የአይበገሬነት፣ የአትንኩኝ ባይነት የጋራ ኅብረት የተንፀባረቀበት በደመቀ የደም ቀለም የተጻፈ የመላው የጥቁር ሕዝቦች የትግል ታሪክ ነው።
የዓድዋ ድል በመላው ኢትዮጵያውያን ተሳትፎና ተጋድሎ የተገኘ አስተሳሳሪ ድል ነው። የብሔር፣ የቋንቋ፣ የአካባቢና የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ሳይገድባቸው አባቶቻችን ለጋራ ዓላማ በአንድነት መስዋዕትነት ከፍለው ነፃ ሀገር እንድንረከብ ያደረገን ድል ነው፡፡ በአንድነት በከፈሉት መስዋዕትነትና በደማቸው የተፃፈ የጋራ ድልና ታሪክ አውርሰውናል፡፡ ድሉን ሊያጎናፅፉን የቻሉት በታጠቁት ዘመናዊ መሣሪያ ወይም አደረጃጀት ሳይሆን ለጋራ ዓላማ በፅናትና በአንድነት በመሰለፋቸው ነው። በመሆኑም የዓድዋ ድል ትውልድ ሊማርበት የሚገባው የዓላማ አንድነትና የፅናት ውጤት ነው፡፡
የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያዊያንም አልፈው ቅኝ ለተገዙ ሕዝቦችም የነፃነት ጮራ ሆነዋል፡፡ ዛሬ ላይ ዓድዋን ስናስብ የጋራ ድልና ታሪክ መሆኑን በመገንዘብ የሚገባዉ ክብር በመስጠት በሚመጥነዉ ዓለማቀፍ ከፍታ ልክ በድምቀት ልንዘክረው ይገባል፡፡
ዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓልን ስናከብር፤ የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተመርቆ ሥራ በጀመረበት ማግሥት ነው፡፡ የፓን አፍሪካኒዝም ምልክትነቱን የሚመጥን መታሰቢያ ሙዚዬም ተገንብቶ በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ወቅት ልዩ ልዩ ጉባኤዎችን አስተናግዷል፡፡ ይህም መንግሥት የሀገር አንድነትን ለማጽናት ለጋራ ድልና ትርክት የተሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ ነው፡፡ የዚህ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱ ይህንን አኩሪ የድል ታሪክ ለትውልድ ከማሸጋገርም ባሻገር በዓድዋ ድል ዙሪያ ለሚደረጉ ጥናቶችና ምርምሮች የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል።
የዓድዋ ድልን ስንዘክርና ስናከብር ልንማራቸው ከሚገቡ ቁምነገሮች አንዱ ሀገራችን በማንኛውም ወቅት የሚገጥሟትን ፈተናዎች በድልና በስኬት መወጣት እንደምትችል የዓድዋ ድል ዋነኛ ተምሳሌት መሆኑን ነው። ፈተናዎችን በድል ለማጠናቀቅ ነጠላ ትርክቶችን ወደ ጎን በመተው እንደ ዓድዋ ጀግኖች ከሰፈር አስተሳሰቦች በመላቀቅና ሀገርን በማስቀደም አንድ ላይ መቆምን ይጠይቃል፡፡ እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በድል ለማጠናቀቅና የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ ከዓድዋ ጀግኖች ፅናትና አንድነት መማር ያስፈልጋል፡፡
እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የካቲት 23/2016 ዓ/ም
https://twitter.com/ProsperityKera