እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ሁለተኛዋ ልጃችን ምድርን ከተቀላቀለች 10 ቀናት ሞልቷታል። ፈጣሪ በክብር፣ በፀጋና በሙላቱ ያሳድጋት ዘንድ የሁልጊዜ ፀሎትና ትጋቴ ይሆናል።
🙏 ጌታ ሆይ እኔ ልጅህን አምነህ ተጨማሪ ኃላፊነትና ክብር ስለሰጠኸኝ አመሠግናለሁ 🙏
Itoophiyaa badhaate dhugoomsuuf aadaa ummatoota hundaa akka qaama eenyummaa keenyaatti fudhachuu qabna. -Obbo Shimalis Abdiisaa Pt. Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa
Читать полностью…ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማትን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምርጫ ወቅት “ አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ አበባ ለማድረግ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ” እንድትሆን ለመስራት ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት አዳዲስ መሰረተ ልማቶችን አቅዶ በመስራት እና ነባሮቹን በማደስ ሌት ተቀን እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከተማዋ ካለባት የመሰረተ ልማት እጥረት እና የህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ እንዲሁም ዘመናት ያስቆጠሩ መሰረተ ልማቶችን ለማዘመን፣ ለማደስ እና የነዋሪዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የኮሪደር ልማት ማከናወን መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የከተማ ነዋሪዎች የአኗኗር ዘይቤ ለማሻሻል እና ከተማዋን የሚመጥን፤ ዘመኑን የሚዋጅ፤ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ለመጨመር የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በጥናት ላይ ተመርኩዞ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ የተጀመረው ስራ በመገባደድ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ትግበራ ከማህበረሰቡ ጋር በመወያየት፣ በመግባባት እና በትብብር እያከናወንን እንገኛለን፡፡
በኮሪደር ልማትና በመልሶ ማልማት የሚነሱ የከተማችን ነዋሪዎችም የተሻለ መኖሪያ ቤት፣ ምትክ መሬት፣ ካሣ፣ የመስሪያ ቦታ፣ ሼዶች፣ የትራንስፖርት ወጪ፣ የሞራል ካሣ በቦታቸው በኮሪደር ልማቱ ጥናት መሰረት ማልማት ለሚችሉ መልሶ የማልማት መብት ተጠብቆላቸው እና ለግል የመኖሪያ ቤት ተነሺዎች እስከሚገነቡ የቤት ኪራይ ወጪ ጭምር እንዲያገኙ በማድረግ የተተገበረ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ሕዝቡን በተዛባ መረጃና ማስረጃ ማጭበርበር የሚፈልጉ እና የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው አንዳንድ ሰዎች፤ በግልፅ ተወስኖ ከተነገረው ከአምስቱ የኮሪደር ልማት አካባቢዎች ውጪ በሌሎች አካባቢዎችም የኮሪደር ልማት ነው በማለት የልማት ተነሺዎች እንዳሉ አስመስለው የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር እየሞከሩ እንደሆነ ደርሰንበታል፡፡
በዚህ መሰረት የተወሰኑ ግለሰቦች ተይዘው ተጠያቂ የተደረጉ በመሆኑ፤ በኮሪደር ልማት ተወያይተው ምትክ ቦታ፣ ካሣ፣ ቤቶች እና ሌሎች ወጪዎች እየሰጠን ካስነሳናቸው ነዋሪዎች ውጪ ምንም ዓይነት የኮሪደር ልማት ተነሺ እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች በግልፅ መድረክ ተፈጥሮ ውይይት ተደርጐ ስምምነት ከተደረሰባቸው አምስቱ የኮሪደር ልማት ቦታዎች ውጪ፣ ውዥንብር የሚፈጥሩ ሰዎችና አካላትን በከተማ አስተዳደሩ ጥቆማና በቅሬታ ማቅረቢያ ነፃ ስልክ ቁጥር 9977 እንድትጠቁሙ፣ እንዲሁም በከንቲባ ጽ/ቤት ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ እንድታሳውቁ እየገለፅን፤ ከዚህ ባለፈ የከተማችን ነዋሪዎች አሁን እየተሰራ ያለውን የልማት ስራ ለመስራት ሲባል የተፈጠረውን መጠነኛ እና ጊዜያዊ ውጣ ውረድ በመታገስና በመተባበር አብረን መስራታችንን እንድንቀጥል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
እኛም ቃላችንን ጠብቀን ሌትና ቀን በመስራት “አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ” ለነዋሪዎቿ ምቹ በማድረግ እንክሳችኋለን፡፡
ሶስቱ ሳታስቡት የተቆጣጠሯችሁ ሰዎች
በሕይወታችሁ በሰዎች አጉል ቁጥጥር ስር ሆናችሁ እንድትኖሩና ነጻነታችሁን እንድትቀሙ ከሚደርጓችሁ አጉል ልምምዶች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
1. ለመቆጣጠር የምትሞከሯቸው ሰዎች
የት እንደገቡ፣ ምን እንዳደረጉ፣ ከማን ጋር ወዳጅነት እንደጀመሩ፣ ምርጫቸው ምን እንደሆነና የመሳሰሉትን ነገር ካላወቃችሁና በጉዳዩ ላይ እናንተ ከሌላችሁበት ቅር የሚላች ሰዎች እናንተ የተቆጣጠራችኋቸው ይመስላችኋል እንጂ የተቆጣጠሯችሁ እነሱ ናቸው፡፡ እነሱን መከታተል፣ ሳታስቡት ጊዜያችሁን፣ ስሜታችሁንና ጉልበታችሁን ስሚወስደው ቀስ በቀስ በእነሱ ቁጥጥር ስር እንዳላችሁ አትርሱ፡፡
2. ቂም የያዛችሁባቸው ሰዎች
በቂምና በጥላቻ የምታስቧቸውን ሰዎች እነሱ በሚሄዱበት መንገድ ላይ ማለፍ፣ እነሱ በሚውሉበት አካባቢ መገኘትና እነሱ በሚሳተፉበት ነገር ላይ መሳተፍ ስለማትፈልጉ ብትወዱም ባትወዱም በእነሱ ቁጥጥር ስር ናችሁ፡፡ በተጨማሪም እነሱን ባሰባችሁ ቁጥር በስሜት ስለምትንተከተኩ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከዋናው ዓላማችሁ ስምትገቱ በእነሱ ቁጥጥር ስር ናችሁ፡
3. የምትቀኑባቸው ሰዎች
በፍቅር ጓደኝነት ሆነ በሌሎች ዘርፎች በጣም የምትቀኑባቸውን ሰዎች ካሉ የእነሱን ውሎ፣ ስኬትና የመሳሰሉትን ነገር ከመከታተል ማረፍ ስለማትችሉ እነዚህ ሰዎች በተዘዋዋሪ መንገድ ሕይወታችሁን ተቆጣጥረው እንደያዙት አትዘንጉ፡፡ ትኩረታቸውን ከእናንተ ይልቅ ለሌላ ሰው እንደሰጡ፣ ስኬትና ዝናቸው ከእናንተ የበለጠ እንደሆነና የመሳሰሉት ስሜቶች ካልተገቱ እጅጉን የወረደና በቁጥጥር ስር የዋለ ሕይወት እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡
የምትቆጣሯውን ሰዎችን ትንሽ ለቀቅ አድርጉ፣ በሰዎች ላይ ያላችሁን ቂምና ጥላቻ ተወት አድርጉ፣ በሰዎች የመቅናታችሁን ጉዳይ ጣል አድርጉትና ራሳችሁን ከቁጥጥር ነጻ አድርጉ!
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት አቶ አደም ፋራህን ከመጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማእረግ የዴሞክራሲ ስርአት ማስተባበሪያ ሃላፊ አድርገው ሾመዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
Ethiopia's vision towards Food Sovereignty through massive wheat production is a significant milestone for the country's economy and agricultural sector. We thank @AbiyAhmedAli for his leadership and global recognition #FAO
Читать полностью…የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሀገር ወሳኝ ርምጃዎችን ተራምደናል። "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ለፈጠራ ሰዎች ድጋፍ በማስገኘት እና ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር በዲጂታል ኢኮኖሚ እንድንበረታ ዐቅም ሆኖናል። ዛሬ ያደረግነው የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ተግዳሮቶቻችንን ለመፈተሽ ብሎም የጉዟችንን ስኬታማ እጥፋቶች ለማክበር ዕድል ፈጥሮልናል።
We have made significant strides as a nation since beginning our digital transformation journey. Digital Ethiopia 2025 empowers us to thrive in the digital economy, necessitating support for innovators and the creation of digital enablers. Today's mid-term review allows us to assess our challenges and celebrate the remarkable milestones we've reached in a short span.
© ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
የብልጽግና ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተከታታይ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን የብልጽልና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አባላት ክልላዊ ማጠቃለያ ኮንፍረንስ "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና እየተካሄደ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ለማከናወን ያቀዳቸውን ተግባራት በተገቢው መንገድ እየፈጸመ ነው።
ፓርቲው አባላትንና ህዝቡን በማስተባበር የብልጽግና ጉዞ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ማድረግ ያስቻሉ ስራዎች መከናወን እንደቻለም ተናግረዋል።
ክልሉ ተመስርቶ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሁሉም መስክ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በህዝቡ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ተከታታይ ምላሽ እየሰጠ መሆኑንም አስረድተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው ፓርቲው በስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ለህዝቡ ቃል የገባቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው እየመለሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ሁሉም አመራርና አባል በክልሉና በሃገር ሰላም ጉዳይ ላይ የጸና አቋም በመያዝ ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
ከልማት ስራዎች አንጻርም በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ላይ በማተኮር መሰራቱን ጠቁመዋል።
የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የተሰራው ስራ ለውጥ እንደተመዘገበበትና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ የተከናወኑ የግብርና፣ የመሰረት ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎችንና በሌሎች ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን የሚያመላክት የፎቶ አውደ ርዕይም ተከፍቷል።
https://twitter.com/ProsperityKera
"ቤትሽን ከቤቴ ላይ አንሺ" መባባል ፒያሳ ላይ ቀረ ያልከኝ ልጅ አሁን ንፁህና ለኑሮ አመቺ ቦታና ቤት ኑሮ ሲጀመር አዲሱ አባባል ምን እንደሆነ መረጃ ካለህ ብትነግረኝ?
ይመስለኛል ግን "አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ፣ አለምሽ ዛሬ ነው ..." በሚለው ጨዋታው የተቀየረ ይመስለኛል። ጨዋታው ከዚህ ቢበልጥ እንጂ ከዚህ እንደማያንስ ግን 100% እርግጠኛ ነኝ።
https://twitter.com/ProsperityKera
#Breaking
#ሞስኮ
በዛሬው እለት በሩሲያ ሞስኮ ከባድ እና ዘግናኝ የሽብር ጥቃት ተፈፀመ!!
ዛሬ አርብ ታጣቂዎች በሞስኮ ከተማ ወደሚገኝ ህዝብ ወዳለበት ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በመግባት አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በመተኮስ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።
አንዳንድ ሪፖርቶች እስካሁን ድረስ ባለው በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል። በአዳራሹ ውስጥ ሰዎች ተሰባስበው የነበረው ለአንድ የሙዚቃ ድግስ ነበር።
ታጣቂዎቹ ቦንብም ሲወረውሩ ነበር የተባለ ሲሆን አዳራሹ ያለበት ህንፃ በእሳት ሲያያዝ ታይቷል። የሩሲያ ሀገር ውስጥ ስለላ አገልግሎት ከጥቃቱ በኋላ #ሞት እና #የአካል_ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል ፤ የሟቾች ቁጥርን ግን አልገለጸም።
የሩስያ ጤና ሚኒስቴር የተጎዱ ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አሳውቋል።
በስፍራው የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ፥ ታጣቂዎቹ አውቶማቲክ መሳሪያ እየተኮሱ መግባታቸውን ፤ የእጅ ቦምብ / ተቀጣጣይ ቦምብ ሲወረውሩም እንደነበር ገልጿል። ጋዜጠኛው ፤ " በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለ15 እና 20 ደቂቃዎች እራሳቸውን ከጥይት ለመከላከል ወለል ላይ ተኝንተው እንደነበር በኃላ ሁኔታው ጋብ ሲል እና የፀጥታ ኃይል ሲመጣ መውጣታቸውን አስረድቷል።
የሩስያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ድርጊቱን " የሽብር ተግባር " ብሎታል። እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወይም ሩስያ ይህ አካል ነው ያለችው የለም።
https://twitter.com/ProsperityKera
#ድንቁርና_ያስፈራኛል አሉ ሎሬቱ 👉 “ጥበብ ይናፍቀኛል፤ ተቻችሎ የሚኖር ህዝብ ያስቀናኛል፤ ጦርነት ያስጠላኛል፤ ድንቁርና ያስፈራኛል" - ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
ከዚህ የሎሬቱ ድንቅ አባባል #ድንቁርና_ያስፈራኛል የምትለው ከሁሉም ውስጤ ትሰርፃለች። ምክንያቱም የድንቁርናን ያህል ምን አስፈሪ ነገር አለ ጃል?
አንዳንድ ጥናቶች እኮ ያስቁኛል 👇
ለምሳሌ 👇
አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ወንዶች የተኙበትን የሆቴል ክፍል ሲያስረክቡ ክፍላቸው ከሴቶች በተሻለ ንፁህ ነው።
በመንግስት ላይ ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት ያደረሰ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በታክስ ሥርዓቱ ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ባደረገው ክትትል ነው ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው፡፡
ተጠርጣሪው ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ እና ቴዎድሮስ ንጉሴ ወልድሀዋሪያ በተባሉ ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተመላክቷል፡፡
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ሐሰተኛ ስሞቹን በመጠቀም ከሌሎች ግብረ-አባሮቹ ጋር በመሆን ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ በሚለው ስም ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሲሆን÷ የወንጀል ድርጊቱ እንዳይደረስበትም ለማድረግ የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን ሲጠቀም ቆይቷል ተብሏል፡፡
ተጠርጣሪው ከታክስ ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ክትትል ለመሰወር በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት በመቀየር ህጋዊ በመምሰል የዕቃ እና አገልግሎት ግብይት ሳይኖር የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የመለያ ቁጥር LB 0019300 ከሆነው የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ በ1 ሺህ 270 ደረሰኞች አማካይነት ምንም ሽያጭ ሳያካሄድ ደረሰኞችን ብቻ በመሸጥ መጠኑ 2 ቢሊየን 951 ሚሊየን 53 ሺህ 749.86 ብር የሚሆን ሽያጭ ማከናወኑ ታውቋል፡፡
በኢኮኖሚ ላይ ከሚፈጸሙ ግንባር ቀደም ወንጀሎች መካከል የታክስ ወንጀል አንዱ ሲሆን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ለጉዳዩ ቅድሚያ ሰጥቶ ክትትል እያደረገበት እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡
ከሪፖርት አቅራቢ፣ ከባለድርሻ እና ከተለያዩ አካላት ከደረሱት መረጃዎች እና ከዳታቤዙ በመነሳት በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ አገልግሎቱ የክትትል፣ የፍተሻና የመረጃ አቅርቦቱን አጠናክሮ የሚቀጥልና ከሌሎች የህግ አስከባሪ አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሚሠራ መሆኑንም እንዳረጋገጠ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።
https://twitter.com/ProsperityKera
Visit to Kigali, Rwanda
© ዐቢን አህመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ 🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር
https://twitter.com/ProsperityKera
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ጉልህ ሚና ባላቸው ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ተወያይቶ አጽድቋል:: በዚህም መሰረት:-
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።
2ኛ. የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ለማውጣት በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በመወያየት ፤ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት በተጨማሪም የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
3ኛ. የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ለጎዳና ህይወት ፤ ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል::
https://twitter.com/ProsperityKera
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት እና ከተማ ማደስ ስራዎች ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ ዛሬ ምሽት ይጠብቁን።
https://twitter.com/ProsperityKera
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በከተማ አቀፍ የአባላት ኮንፈረንስ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ ፦
👉በፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በግማሽ የምርጫ ዘመን ያስመዘገብነውን ስኬት እና የገጠሙንን ተግዳሮቶች በመገምገም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የምንግባባበት ኮንፈረንስ ነው::
👉በ 6 ተኛው አገራዊ ምርጫ ህዝባችን አሸጋሪ ሀሳቦቻችንን ተግባራዊ የምናደርግበት ዕድል እና ፈተናዎችን ተቋቁመን የኢትዮጵያን ብልፅግና የማረጋገጥ አደራም ነው የሰጠን ።
👉 የፓርቲያችንን ማኒፌስቶ ተግባራዊ በማድረግ ቃልአችንን ለመተግበር ህዝባችንን አሳትፈን ተረባርበናል።
👉በግብርናው ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል።
👉በማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያ ታምራት በሚል ንቅናቄ ዕምቅ አቅማችንን ተጠቅመን ብልፅግናን ለማረጋገጥ ጥረት ተደርጓል ።
👉ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ብልፅግና ያለውን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም በርካታ መዳረሻዎች ተሰርተዋል ፤ በአይሲቲ እና በማህበራዊም በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
👉በኢኮኖሚው በጂዲፒ ኢትዮጵያ ከአምስት የአፍሪካ አገራት አንዷ ሆናለች።
👉 ከአዲስ አበባ አንፃር ፓርቲያችን ሁለት ዋና ዋና ግቦችን አስቀምጦ እየሰራ ነው:: አንደኛው የብሔራዊነት ትርክት የበላይነት እንዲረጋገጥ የአድዋ ድል መታሰቢያን የመሳሰሉ አሰባሳቢና አስተሳሳሪ ትርክቶች እየተሰሩ ነው::
👉ሁለተኛው አዲስ አበባ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ብልፅግና ማሳያ እንድትሆን ዓለም አቀፍ የከተማነት ስታንዳርድ እንዲኖራት እየተሰራ ነው::
👉በቀጣይ የአስተሳሰብ ፣ የስነ ምግባር ፣ እና የተግባር አርበኛ መሆን፣ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲያችንን አደረጃጀቶች ማጠናከር እንዲሁም ለህዝባችን አንገብጋቢ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ከፓርቲያችን አመራርና አባላት ይጠበቃል።
👉ከህዝባችን ጋር በተደረጉ ውይይቶች አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ እንረባረብ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል ። ፓርቲያችንም ለግጭቶች ሰላማዊ አማራጭ እንዲኖር ፣ የህግ የበላይነንትን ማረጋገጥ እንዲጠናከር፣ አካታች ብሄራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን አቅጣጫ ማስቀመጡን አውስተዋል።
👉 የኑሮ ውደንቱን ለማረጋጋት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የግብይት ስርዓቱን የማሻሻል አቅጣጫ ተቀምጧል።
👉በአስተሳሰብ ለውጥ እና ስራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ የስራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር እንደሚሰራ ተብራርቷል።
👉 ግልፀኝነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ርብርብ ይደረጋል።
👉የተጓተቱትን በማፍጠንና ህዝብንና የልማት አጋርን በማስተባበር የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እንተጋለን ።
👉በዕቅድ የያዝናቸውን በውጤታማነት እንዲተገበሩ የውስጠ ፓርቲ ዲሲፕሊንን በማጠናከር ፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በአርአያነት ማጎልበት ይገባል ::
https://twitter.com/ProsperityKera
ብልፅግና ህብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት እየሰራ ያለ ፓርቲ!
ብልጽግና ፓርቲ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፤ ፓርቲው የተቋም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር በተለይ በአመራሩና በአባሉ ዉስጥ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለማምጣት በተሰራው ሥራ እጅግ አመርቂ ውጤቶች ታይተዋል፡፡
በከተማችን የመንግስት ተቋማት ተቋማዊ አሰራርን ተከትሎ እንዲፈጸሙ ለማድረግ ከተማውን የሚመጥ የአሰራር የመዋቅር ማሻሻያ በማድረግ ረገድ በርካታ የረፎረም ሥራዎችን በመሰራት ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ተግባራዊ በመደረጉ ምክንያት የመፈጸም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መጥቷል፡፡
በከተማችን የሚገኙ ሶስቱም የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አዉጪ፤ ህግ ተርጓሚና ህግ አስፈጻሚ አካላት የተቀመጠውን አሰራር ስርዓትን በመጠበቅ በህግ ተርጓሚና በህግ አስፈጻሚ አካላትን በህግ አዉጪው አማካይነት ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ በመምራቱ ተቋማቱ ነጻነታቸውን በጠበቀ አግባብ እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
የዴሞክራሲ ተቋማትን ከመገንባት ረገድ በሀገረ አቀፍ ደረጃ የወጡ ህጎችና አዋጆች በከተማችን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ጠንካራ ክትትል እየተደረገ የተመራ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በከተማ ደረጃ የተለያዩ አዋጆችንና ደንቦችን በማዉጣት ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በከተማችን የወንድማማችነትና የእህታማማችነት አስተሳሰብ እንዲጎለበት ሰፋፊ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ፤ ውጤትም ታይቶበታል፡፡
ከተማችን አዲስ አበባ የጋራ ቤታችን የሚል መርህ ቃል በመያዝ ወደ ተግባር የገባን ሲሆን በከተማችን የሚከናወኑ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላት በሚከበሩበትም ወቅት በአብሮነት፤ በወንድማማችነትና በእህታማማችነት መንፈስ በሚያጎለብት መልኩ እየተከበሩ ይገኛል፡፡
ብልፅግና ህብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ጠንክሮ እየሰራ ያለ ፓርቲ ሲሆን በቀሪው የምርጫ ዘመንም አጠናክሮ የሚያስቀጥል ይሆናል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera
Waadaa Gochaan; Badhaadhina Itoophiyaatif!!!
Paartiin Badhaadhinaa, sirna dinagdee gabaan durfamu hordofudhan guddina dinagdee qulqullina qabuu fi badhaadhina waloo mirkaneessuu danda’an heddu galmeessisee jira.
https://twitter.com/ProsperityKera
አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ በ1 ቢሊዮን ብር የወላጅ አልባ ልጆች ማዕከል ልትገነባ ነው።
አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ "መቅደስ የልጆች አድማስ" የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ልታቋቁም እንደሆነ ዛሬ መጋቢት 12/2016 ዓም በካፒታል ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ድርጅቱን ለማቋቋም ሃሳቡ የተፀነሰው ከ6 ዓመታት በፊት እንደሆነ አርቲስቷ ገልጻለች፣ ድርጅቱ በዋናነት ልዩ ትኩረት እና ጥበቃ ለሚያስፈልጋቸው ወላጅ አልባ ህፃናት ልጆች አስፈለጊውንና ሁሉን አቀፍ እንከብካቤ በመስጠት በቀጣይ የሕይወት ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንደሆነ የድርጅቱ የቦርድ አባል ደራሲ ውድነህ ክፍሌ ተናግሯል።
በማዕከሉ ውስጥ ለሚቆዩ ልጆች ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ፣ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ከመስጠትና፣ የአካል ብቃት ማጎልመሻ ከማደራጀት ባሻገር፣ የማኅበራዊ ሕይወትና የአእምሮ ማበልፀጊያ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙሉ ጤንነታቸው የተረጋገጠ፣ በአካላዊ እድገታቸው የበቁ፣ በሥነ ልቦና፣ በግልና በማሕበራዊ ሕይወታቸው ጠንካራ የሆኑ እንዲሁም በአእምሮአዊ የተጠራ ችሎታቸው የተደነቁ እና በዕውቀት የዳበሩ ሆነው የመጪው ጊዜ ብሩህ እና ስኬታማ ዜጎችን እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ተብሏል።
መቅደስ የልጆች አድማስ በማእከሉ የሚያድጉ ልጆች በሁሉም ረገድ ኢትዮጵያው እሴቶችን የተላበሱና አዎንታዊ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ትኩረቱ እንደሆነ ተገልጿል።
ድርጅቱን ሙሉ ለሙሉ በመገንባትና በሙሉ አቅሙ ስራውን እንዲጀምር ለማድረግ እስከ አንድ ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በሃያ አንድ ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ተቋም ነው::
ይህ ድርጅት የመጀመሪያ ተቋሙን የሚገነባውና ስራውን የሚጀምረው በአዲስ አበባ ሲሆን ቀስ በቀስም ወደ ከልሎች ቅርንጫፎቹን የሚያሰፋ ይሆናል። በመጀመሪያው ዙር 200 ህፃናትን ከመላው ኢትዮጵያ የሚቀበል ሲሆን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ 1000 ህፃናትን የመቀበል አቅም የሚኖረው ይሆናል።
ማእከሉ እውን የሚሆንበትና በይፋ ገቢ በማሰባሰብ ወደ ስራ የሚገባበት ቀን መጋቢት 26 በስካይ ላይት ሆቴል ሲሆን በዝግጅቱም ላይ ከፍተኛ የሀገራችን መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ባለሃብቶች፥ የኤምባሲ ተወካዩች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሐሳቡን የሚደግፉና ቀና ልብ ያላቸው ግለሰቦችም ይታደሙበታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በመንግስት ላይ ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት ያደረሰ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በታክስ ሥርዓቱ ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ ባደረገው ክትትል ነው ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው፡፡
ተጠርጣሪው ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ እና ቴዎድሮስ ንጉሴ ወልድሀዋሪያ በተባሉ ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተመላክቷል፡፡
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ሐሰተኛ ስሞቹን በመጠቀም ከሌሎች ግብረ-አባሮቹ ጋር በመሆን ቴዎድሮስ ንጉሴ ሀያርያ በሚለው ስም ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሲሆን÷ የወንጀል ድርጊቱ እንዳይደረስበትም ለማድረግ የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን ሲጠቀም ቆይቷል ተብሏል፡፡
ተጠርጣሪው ከታክስ ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ክትትል ለመሰወር በቦሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት በመቀየር ህጋዊ በመምሰል የዕቃ እና አገልግሎት ግብይት ሳይኖር የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የመለያ ቁጥር LB 0019300 ከሆነው የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ በ1 ሺህ 270 ደረሰኞች አማካይነት ምንም ሽያጭ ሳያካሄድ ደረሰኞችን ብቻ በመሸጥ መጠኑ 2 ቢሊየን 951 ሚሊየን 53 ሺህ 749.86 ብር የሚሆን ሽያጭ ማከናወኑ ታውቋል፡፡
በኢኮኖሚ ላይ ከሚፈጸሙ ግንባር ቀደም ወንጀሎች መካከል የታክስ ወንጀል አንዱ ሲሆን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ለጉዳዩ ቅድሚያ ሰጥቶ ክትትል እያደረገበት እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡
ከሪፖርት አቅራቢ፣ ከባለድርሻ እና ከተለያዩ አካላት ከደረሱት መረጃዎች እና ከዳታቤዙ በመነሳት በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ አገልግሎቱ የክትትል፣ የፍተሻና የመረጃ አቅርቦቱን አጠናክሮ የሚቀጥልና ከሌሎች የህግ አስከባሪ አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሚሠራ መሆኑንም እንዳረጋገጠ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በክብርት ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል የተመራው የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በድሬዳዋ በአስተዳደር ቢዮአዋሌ ገጠር ወረዳ የመስክ ምልከታውን እያደረገ ይገኛል።
የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ከመጋቢት 11/2016 ጀምሮ እስከ መጋቢት 15/ 2016 በሚካሄደው ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምልከታው ባለፉት ጊዜያት በአስተዳደሩ የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት እንቅስቃሴዎች የመስክ ቡድኑ ምልከታ ያደርጋል።
በዛሬው መርሃግብርም ሱፐርቪዥን ቡድኑ በቢዮአዋሌ ወረዳ ኢጃነኒ ገጠር ቀበሌ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የአርቲስት ዶ/ር አሊ ቢራ መታሰቢያ የትምህርት ቤት ግንባታ ገንደ ገበታ ትምህርት ቤት ከ0 እስከ 8ኛ ክፍል በድምሩ 1,084 ተማሪዎች ያለውና በፍቃደኛ ተቋማት ወጪው የተሸፈነለት ምገባ ፕሮግራም ጎብኝተዋል።
በተጨማሪም በአስተዳደሩ ትኩረት የተሰጠውና በህብረተሰብ ተሳትፎ በአጭር ጊዜ ለውጥ የተገኘበት፣ 1,668 አባወራ ሊያገለግል የሚችል የአዳዳ የተፋሰስ ልማት በአጠቃላይ 12 ሺ ነዋሪዎችን በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ 50 ሄክታርን ያካለለ ስራ በመስራት ግድቡ እንዲያገግም የተደረገበት ይገኙበታል።
እንዲሁም ውጤታማ የሆኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ፣ 12 መሰረታዊ ማህበራት ወደ አንድ የተዋሀዱበትና 130 አባላት ያሉት የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ሪፎርም በማድረግ በገበያ ዋጋ ንረትን ማረጋጋት እና ኑሮ ውድነት ከመቀነስ አንጻር ድርሻ እንዲኖራቸው የተደረገበት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
ልዑኩ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የሌማት ትሩፋት እንዲሁም በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ ስራዎችን የተመለከተ ሲሆን ምልከታው በቀጣይ ቀናትም በከተማ ወረዳዎች እንደሚቀጠል እና ጠንካራ እምርታዎችን ለማስቀጠል ውስንነቶችን ለማረም ግብረ መልሳዊ አቅጣጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
#prosperity
https://twitter.com/ProsperityKera