‼️አስገራሚዎቹ ጡረተኞች!
ከስራ ፈትነት በአንድ ቀመር ከራሳቸው አልፎ የመንደራቸውን ህዝብ በአንድ ግዜ ሚሊየነር ማድረግ የቻሉት ጥንዶች!
https://twitter.com/ProsperityKera
ሚያዝያ 02/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም እንገናኝ። መግቢያ በነፃ ነው።
https://twitter.com/ProsperityKera
#የጭንቀት_ሱስ
የጭንቀት ሱስ ማለት፣ “ሁሉም ነገር አሁኑኑ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል” በማለት የመጨናነቅ ልማድ ማለት ነው፡፡
ከዚህ አይነቱ የጭንቀት “ሱስ” ለመላቀቅ በየዕለቱ የሚገጥሙንን ሁኔታዎች ከፋፍሎ ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
1. አፋጣኝ ትኩረት የሚፈልጉ ነገሮች
ትኩረት ሰጥተን መፍትሄ ካላገኘንላቸው አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች፡፡
“ምን አስጨነቀኝ” በሚል ሰበብ እነዚህን ሁኔታዎች ችላ ካልን ጊዜው ከዘገዬ በኋላ እንድንባንን እንሆናለን፡፡ ለምሳሌ፣ እንደ ህመም ያለ፣ ወይም ደግሞ የልጆች ባህሪይ ሲበላሽ እንደማየት ያሉትን ሁኔታዎች እያዩ ከመጨነቅም ሆነ ከመዘናጋት ይልቅ በቶሎ መፍትሄ የሚገኝበትን መንገድ መፈለግ ተገቢ ነው፡፡
2. ትንሽ ጊዜ የሚሰጡን ነገሮች
ከእነሱ ለባሱ ነገሮች ትኩረት ብንሰጥ ጊዜን የሚሰጡን ሁኔታዎች፡፡
ከአስቸኳይ ሁኔታዎች እኩል ለእነዚህ ሁኔታዎች መጨናነቅ መስመር ወደሳተ ስሜታዊነት ይጨምረናል፡፡ ለምሳሌ ከአንድ አመት በኋላ የሚከፈል መጠኑ አነስተኛ የሆነ ብድር ካለብን አሁን በእጃችን ላይ ያሉ ሌሎች አጣዳፊ ሁኔታዎች ላይ ለማተኮር ጊዜ ሊሰጠን ስለሚችል ከመጨነቅ ይልቅ እቅድ ማውጣቱ ተመራጭ ነው፡፡
3. ዝም ብንላቸው በራሳቸው ጊዜ መስመር የሚይዙ ነገሮች
መጨነቅም ሆነ ምንም ምላሽ ልንሰጣቸው የማይገባን ሁኔታዎች፡፡
አንዳንድ ሁኔታዎች የራሳቸውን ጊዜ ጨርሰው እስኪተነፍሱ ድረስ መተው ያለብን ነገሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ በየጊዜው የሚቀያየር ባህሪይ ያላቸው ሰዎች ይህ እንደነፋስ እየመጣ የሚሄደውን ባህሪያቸውን እያሰቡ ለመፍትሄ ከመጨነቅ ይልቅ ዝም ብሎ በሌሎች ወሳኝ ነገሮች ላይ ማተኮር ይበጃል፡፡ እነሱ ሲበቃቸውና ሲሰለቻቸው ያቆማሉ፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ሰላም የጋራ ሀብታችን ብቻ ሳይሆን የሁለንተናዊ ብልፅግና ጽኑ መሰረት ነው!
ሰላም ህዝቦች በአንድነት አብረው የሚያፈሩት ፣ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጽኑ መሰረት ነው ። ሰላም መተማመናችን ነው፤ ሰላም የሁላችንም የአብሮነት ጉዞ ነው፤ ሰላም አለመግባባትና ተቃርኖዎችን በሰለጠነ መንገድ መፍታት የሚያስችል መንገድና ግባችን ነው።
ሰላም በእያንዳንዳችን እጅ እና ልቦና ውስጥ የሚገኝ ውድ ሀብት ነው። በመሆኑም ሌት ተቀን እንደ ዓይናችን ብሌን ልንከባከበው የሚገባ ፣ አንዳችን ለአንዳችን የሰላም ምንጭ እንጂ የስቃይ ምንጭ እንዳንሆን ከቆረጥንና ለተግባራዊነቱ ከተጋን ሰላም በደጃችን፣ በእጃችን ያለ ሀብት ሆኖ ይቀጥላል።
ለሀገራችን የሁሉ ነገር መሰረት የሆነው ብቸኛ መፍትሄና አማራጭ ሰላምን ማስፈን ነው ፤ አሁንም ይሁን ለቀጣይ ለሀገራችን ፍቱን መድሃኒት የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ የተረጋገጠበት ዘላቂ ሰላምን እውን ማድረግ ስለሆነ በቀጣይም ዘላቂ ሰላም እንዲፀና ሁላችንም ስለ ሰላም የበኩላችንን አዎንታዊ አሻራ ማሳረፍ ይኖርብናል።
ሳምንታዊ መልዕክታችንም ፣ ሰላምን ከፍ ማድረግ ነው። ዛሬም እንዳ ትላንቱ ፅኑ የሰላም ቃፊሮች ነን !!
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!!
እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ሁለተኛዋ ልጃችን ምድርን ከተቀላቀለች 10 ቀናት ሞልቷታል። ፈጣሪ በክብር፣ በፀጋና በሙላቱ ያሳድጋት ዘንድ የሁልጊዜ ፀሎትና ትጋቴ ይሆናል።
🙏 ጌታ ሆይ እኔ ልጅህን አምነህ ተጨማሪ ኃላፊነትና ክብር ስለሰጠኸኝ አመሠግናለሁ 🙏
Itoophiyaa badhaate dhugoomsuuf aadaa ummatoota hundaa akka qaama eenyummaa keenyaatti fudhachuu qabna. -Obbo Shimalis Abdiisaa Pt. Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa
Читать полностью…ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማትን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምርጫ ወቅት “ አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ አበባ ለማድረግ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ” እንድትሆን ለመስራት ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት አዳዲስ መሰረተ ልማቶችን አቅዶ በመስራት እና ነባሮቹን በማደስ ሌት ተቀን እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከተማዋ ካለባት የመሰረተ ልማት እጥረት እና የህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ እንዲሁም ዘመናት ያስቆጠሩ መሰረተ ልማቶችን ለማዘመን፣ ለማደስ እና የነዋሪዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የኮሪደር ልማት ማከናወን መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የከተማ ነዋሪዎች የአኗኗር ዘይቤ ለማሻሻል እና ከተማዋን የሚመጥን፤ ዘመኑን የሚዋጅ፤ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ለመጨመር የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በጥናት ላይ ተመርኩዞ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ የተጀመረው ስራ በመገባደድ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ትግበራ ከማህበረሰቡ ጋር በመወያየት፣ በመግባባት እና በትብብር እያከናወንን እንገኛለን፡፡
በኮሪደር ልማትና በመልሶ ማልማት የሚነሱ የከተማችን ነዋሪዎችም የተሻለ መኖሪያ ቤት፣ ምትክ መሬት፣ ካሣ፣ የመስሪያ ቦታ፣ ሼዶች፣ የትራንስፖርት ወጪ፣ የሞራል ካሣ በቦታቸው በኮሪደር ልማቱ ጥናት መሰረት ማልማት ለሚችሉ መልሶ የማልማት መብት ተጠብቆላቸው እና ለግል የመኖሪያ ቤት ተነሺዎች እስከሚገነቡ የቤት ኪራይ ወጪ ጭምር እንዲያገኙ በማድረግ የተተገበረ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ሕዝቡን በተዛባ መረጃና ማስረጃ ማጭበርበር የሚፈልጉ እና የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው አንዳንድ ሰዎች፤ በግልፅ ተወስኖ ከተነገረው ከአምስቱ የኮሪደር ልማት አካባቢዎች ውጪ በሌሎች አካባቢዎችም የኮሪደር ልማት ነው በማለት የልማት ተነሺዎች እንዳሉ አስመስለው የተዛባ መረጃ በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር እየሞከሩ እንደሆነ ደርሰንበታል፡፡
በዚህ መሰረት የተወሰኑ ግለሰቦች ተይዘው ተጠያቂ የተደረጉ በመሆኑ፤ በኮሪደር ልማት ተወያይተው ምትክ ቦታ፣ ካሣ፣ ቤቶች እና ሌሎች ወጪዎች እየሰጠን ካስነሳናቸው ነዋሪዎች ውጪ ምንም ዓይነት የኮሪደር ልማት ተነሺ እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች በግልፅ መድረክ ተፈጥሮ ውይይት ተደርጐ ስምምነት ከተደረሰባቸው አምስቱ የኮሪደር ልማት ቦታዎች ውጪ፣ ውዥንብር የሚፈጥሩ ሰዎችና አካላትን በከተማ አስተዳደሩ ጥቆማና በቅሬታ ማቅረቢያ ነፃ ስልክ ቁጥር 9977 እንድትጠቁሙ፣ እንዲሁም በከንቲባ ጽ/ቤት ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ እንድታሳውቁ እየገለፅን፤ ከዚህ ባለፈ የከተማችን ነዋሪዎች አሁን እየተሰራ ያለውን የልማት ስራ ለመስራት ሲባል የተፈጠረውን መጠነኛ እና ጊዜያዊ ውጣ ውረድ በመታገስና በመተባበር አብረን መስራታችንን እንድንቀጥል በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
እኛም ቃላችንን ጠብቀን ሌትና ቀን በመስራት “አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ” ለነዋሪዎቿ ምቹ በማድረግ እንክሳችኋለን፡፡
ሶስቱ ሳታስቡት የተቆጣጠሯችሁ ሰዎች
በሕይወታችሁ በሰዎች አጉል ቁጥጥር ስር ሆናችሁ እንድትኖሩና ነጻነታችሁን እንድትቀሙ ከሚደርጓችሁ አጉል ልምምዶች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
1. ለመቆጣጠር የምትሞከሯቸው ሰዎች
የት እንደገቡ፣ ምን እንዳደረጉ፣ ከማን ጋር ወዳጅነት እንደጀመሩ፣ ምርጫቸው ምን እንደሆነና የመሳሰሉትን ነገር ካላወቃችሁና በጉዳዩ ላይ እናንተ ከሌላችሁበት ቅር የሚላች ሰዎች እናንተ የተቆጣጠራችኋቸው ይመስላችኋል እንጂ የተቆጣጠሯችሁ እነሱ ናቸው፡፡ እነሱን መከታተል፣ ሳታስቡት ጊዜያችሁን፣ ስሜታችሁንና ጉልበታችሁን ስሚወስደው ቀስ በቀስ በእነሱ ቁጥጥር ስር እንዳላችሁ አትርሱ፡፡
2. ቂም የያዛችሁባቸው ሰዎች
በቂምና በጥላቻ የምታስቧቸውን ሰዎች እነሱ በሚሄዱበት መንገድ ላይ ማለፍ፣ እነሱ በሚውሉበት አካባቢ መገኘትና እነሱ በሚሳተፉበት ነገር ላይ መሳተፍ ስለማትፈልጉ ብትወዱም ባትወዱም በእነሱ ቁጥጥር ስር ናችሁ፡፡ በተጨማሪም እነሱን ባሰባችሁ ቁጥር በስሜት ስለምትንተከተኩ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከዋናው ዓላማችሁ ስምትገቱ በእነሱ ቁጥጥር ስር ናችሁ፡
3. የምትቀኑባቸው ሰዎች
በፍቅር ጓደኝነት ሆነ በሌሎች ዘርፎች በጣም የምትቀኑባቸውን ሰዎች ካሉ የእነሱን ውሎ፣ ስኬትና የመሳሰሉትን ነገር ከመከታተል ማረፍ ስለማትችሉ እነዚህ ሰዎች በተዘዋዋሪ መንገድ ሕይወታችሁን ተቆጣጥረው እንደያዙት አትዘንጉ፡፡ ትኩረታቸውን ከእናንተ ይልቅ ለሌላ ሰው እንደሰጡ፣ ስኬትና ዝናቸው ከእናንተ የበለጠ እንደሆነና የመሳሰሉት ስሜቶች ካልተገቱ እጅጉን የወረደና በቁጥጥር ስር የዋለ ሕይወት እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡
የምትቆጣሯውን ሰዎችን ትንሽ ለቀቅ አድርጉ፣ በሰዎች ላይ ያላችሁን ቂምና ጥላቻ ተወት አድርጉ፣ በሰዎች የመቅናታችሁን ጉዳይ ጣል አድርጉትና ራሳችሁን ከቁጥጥር ነጻ አድርጉ!
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት አቶ አደም ፋራህን ከመጋቢት 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማእረግ የዴሞክራሲ ስርአት ማስተባበሪያ ሃላፊ አድርገው ሾመዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
Ethiopia's vision towards Food Sovereignty through massive wheat production is a significant milestone for the country's economy and agricultural sector. We thank @AbiyAhmedAli for his leadership and global recognition #FAO
Читать полностью…የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሀገር ወሳኝ ርምጃዎችን ተራምደናል። "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ለፈጠራ ሰዎች ድጋፍ በማስገኘት እና ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር በዲጂታል ኢኮኖሚ እንድንበረታ ዐቅም ሆኖናል። ዛሬ ያደረግነው የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ተግዳሮቶቻችንን ለመፈተሽ ብሎም የጉዟችንን ስኬታማ እጥፋቶች ለማክበር ዕድል ፈጥሮልናል።
We have made significant strides as a nation since beginning our digital transformation journey. Digital Ethiopia 2025 empowers us to thrive in the digital economy, necessitating support for innovators and the creation of digital enablers. Today's mid-term review allows us to assess our challenges and celebrate the remarkable milestones we've reached in a short span.
© ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
የብልጽግና ፓርቲ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በህዝቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተከታታይ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን የብልጽልና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አባላት ክልላዊ ማጠቃለያ ኮንፍረንስ "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና እየተካሄደ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ለማከናወን ያቀዳቸውን ተግባራት በተገቢው መንገድ እየፈጸመ ነው።
ፓርቲው አባላትንና ህዝቡን በማስተባበር የብልጽግና ጉዞ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ማድረግ ያስቻሉ ስራዎች መከናወን እንደቻለም ተናግረዋል።
ክልሉ ተመስርቶ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሁሉም መስክ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በህዝቡ ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ተከታታይ ምላሽ እየሰጠ መሆኑንም አስረድተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው ፓርቲው በስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ለህዝቡ ቃል የገባቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው እየመለሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ሁሉም አመራርና አባል በክልሉና በሃገር ሰላም ጉዳይ ላይ የጸና አቋም በመያዝ ባለፉት ሁለት ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
ከልማት ስራዎች አንጻርም በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ላይ በማተኮር መሰራቱን ጠቁመዋል።
የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የተሰራው ስራ ለውጥ እንደተመዘገበበትና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ የተከናወኑ የግብርና፣ የመሰረት ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎችንና በሌሎች ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን የሚያመላክት የፎቶ አውደ ርዕይም ተከፍቷል።
https://twitter.com/ProsperityKera
"ቤትሽን ከቤቴ ላይ አንሺ" መባባል ፒያሳ ላይ ቀረ ያልከኝ ልጅ አሁን ንፁህና ለኑሮ አመቺ ቦታና ቤት ኑሮ ሲጀመር አዲሱ አባባል ምን እንደሆነ መረጃ ካለህ ብትነግረኝ?
ይመስለኛል ግን "አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ፣ አለምሽ ዛሬ ነው ..." በሚለው ጨዋታው የተቀየረ ይመስለኛል። ጨዋታው ከዚህ ቢበልጥ እንጂ ከዚህ እንደማያንስ ግን 100% እርግጠኛ ነኝ።
https://twitter.com/ProsperityKera
Hordoftoota amantaa Islaamaa mara, baga ayyaana Iid Alfaxrii 1445ffaa ittiin isin gahe.
Iid Mubaarak!
ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።
ኢድ ሙባረክ!
https://twitter.com/ProsperityKera
ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት ነው!
ህብረ _ብሄራዊነት በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት የሚያጠናክር ይበልጥ ሊጎለብት የሚገባ እሴታችን ነው፡፡
ህብረ -ብሄራዊነት ሀይማኖትን ፣ ብሄርን፣ ቋንቋን እና የባህል ብዝሀነትን በግንባር ቀደምትነት ያጠቃልላል፡፡
ከአባቶቻችን የወረስነውን የሀገራችንን ብዝሀነት ይበልጥ በማጎልበት የአሁኑ ትውልድ የቤት ስራ ነው፡፡
ህብረ-ብሄራዊነት በሀገራችን እውን ስሆን ለምንሻው ሰላም፣ ልማትና ለዲሞክራሲ መስፈን ወሳኝ መሰረት ይጥላል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የእኛ ምርጥ ጀግና 👏💪🇪🇹👏💪🇪🇹👏💪🇪🇹
አባዬ ድሬ ብቻ አይደሉም የተለያዩ ቦታዎች ጀግና የፖሊስ አባላት አሉን። ለምሳሌ ይህ ቪዲዮ የተቀረፀው ቂርቆስ ክ/ከተማ ቡልጋሪያ መብራት ላይ ነው። በአካባቢው መብራት ጠፍቷል። እሱን ተከትሎ ደግሞ የትራፊክ መብራቱ አይሰራም። ታዲያ ዶፍ ዝናብ እየዘነበ ቢሆንም መብራቱን ተክቶ የትራፊክ ማሳለጡን የተያያዘችው አንዲት ጀግና የፖሊስ አባልን እያየን "WOW የእኛ ጀግና" አልን። ጀግንነቷንም በምስል በመረጃ እንዲህ አጋራናችሁ። 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሰላም አስከባሪ በመሆን ጭምር ሩዋንዳን ከችግር ለመታደግ አግዘዋል - ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወጣትነት ዘመናቸው በሰላም አስከባሪነት ተሰማርተው ሩዋንዳን ከችግር ለመታደግ አግዘዋል ሲሉ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የሩዋንዳውያን የ"ኪዊቡካ 30" ዓመት መታሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ታድመዋል፡፡
መርኃ ግብሩ በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ 30ኛ ዓመት የሚያስብ ሲሆን የአካባቢው አገራት መሪዎችም በመታሰቢያው ስነ-ስርዓት ላይ ታድመዋል፡፡
በመርኃ ግበሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ሩዋንዳን በወቅቱ የገጠማትን ችግር ለመታደግ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እገዛ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል።
Visit to Kigali, Rwanda
© ዐቢን አህመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ 🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር
https://twitter.com/ProsperityKera
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፊቼ ጨምበላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
Читать полностью…የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ጉልህ ሚና ባላቸው ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ተወያይቶ አጽድቋል:: በዚህም መሰረት:-
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የተሽከርካሪ አስተዳደር ህግ እና ሥርዓት ለማስከበር የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ ደንብን ለአሰራር በሚያመች መልኩ ሀሳብ ተሰጥቶበት ደንቡ ፀድቋል።
2ኛ. የከተማዋን ስታንዳርድ እና መዋቅራዊ ፕላን ለማስጠበቅ እንዲሁም መልሶ ማፍረስ እንዳይገጥም ፤ ግንባታዎች ከመንገድ ያላቸው ርቀት ከዚህ በኋላ ወጥነት ያለው የከተማ አሰራር አንዲኖር በማሰብ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን 3 ደረጃዎች ለማውጣት በቀረበው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በመወያየት ፤ ከአሁን በኋላ የሚገነቡ ማንኛውም ግንባታዎች ከዋና ከመንገድ በ10 ሜትር ርቀት መሆን እንደሚገባው ፤ ከንዑስ ዋና መንገድ 5 ሜትር ርቀት፤ ሰብሳቢ መንገድ ደግሞ 3 ሜትር ርቀት በተጨማሪም የውስጥ ለውስጥ መንገድ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸው ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
3ኛ. የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ ማዕከሉን በተለይም ለጎዳና ህይወት ፤ ለፆታዊ ጥቃት ሰለባ እና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያ እና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማደስ የሚያስችል የሙያ እና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለዉ ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል በሚያግዘው ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ካቢኔው ተወያይቶ አጽድቋል::
https://twitter.com/ProsperityKera
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት እና ከተማ ማደስ ስራዎች ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ ዛሬ ምሽት ይጠብቁን።
https://twitter.com/ProsperityKera
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በከተማ አቀፍ የአባላት ኮንፈረንስ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ ፦
👉በፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በግማሽ የምርጫ ዘመን ያስመዘገብነውን ስኬት እና የገጠሙንን ተግዳሮቶች በመገምገም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የምንግባባበት ኮንፈረንስ ነው::
👉በ 6 ተኛው አገራዊ ምርጫ ህዝባችን አሸጋሪ ሀሳቦቻችንን ተግባራዊ የምናደርግበት ዕድል እና ፈተናዎችን ተቋቁመን የኢትዮጵያን ብልፅግና የማረጋገጥ አደራም ነው የሰጠን ።
👉 የፓርቲያችንን ማኒፌስቶ ተግባራዊ በማድረግ ቃልአችንን ለመተግበር ህዝባችንን አሳትፈን ተረባርበናል።
👉በግብርናው ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል።
👉በማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያ ታምራት በሚል ንቅናቄ ዕምቅ አቅማችንን ተጠቅመን ብልፅግናን ለማረጋገጥ ጥረት ተደርጓል ።
👉ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ብልፅግና ያለውን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም በርካታ መዳረሻዎች ተሰርተዋል ፤ በአይሲቲ እና በማህበራዊም በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
👉በኢኮኖሚው በጂዲፒ ኢትዮጵያ ከአምስት የአፍሪካ አገራት አንዷ ሆናለች።
👉 ከአዲስ አበባ አንፃር ፓርቲያችን ሁለት ዋና ዋና ግቦችን አስቀምጦ እየሰራ ነው:: አንደኛው የብሔራዊነት ትርክት የበላይነት እንዲረጋገጥ የአድዋ ድል መታሰቢያን የመሳሰሉ አሰባሳቢና አስተሳሳሪ ትርክቶች እየተሰሩ ነው::
👉ሁለተኛው አዲስ አበባ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ብልፅግና ማሳያ እንድትሆን ዓለም አቀፍ የከተማነት ስታንዳርድ እንዲኖራት እየተሰራ ነው::
👉በቀጣይ የአስተሳሰብ ፣ የስነ ምግባር ፣ እና የተግባር አርበኛ መሆን፣ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲያችንን አደረጃጀቶች ማጠናከር እንዲሁም ለህዝባችን አንገብጋቢ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት ከፓርቲያችን አመራርና አባላት ይጠበቃል።
👉ከህዝባችን ጋር በተደረጉ ውይይቶች አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ እንረባረብ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል ። ፓርቲያችንም ለግጭቶች ሰላማዊ አማራጭ እንዲኖር ፣ የህግ የበላይነንትን ማረጋገጥ እንዲጠናከር፣ አካታች ብሄራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን አቅጣጫ ማስቀመጡን አውስተዋል።
👉 የኑሮ ውደንቱን ለማረጋጋት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የግብይት ስርዓቱን የማሻሻል አቅጣጫ ተቀምጧል።
👉በአስተሳሰብ ለውጥ እና ስራ ፈጣሪዎችን በመደገፍ የስራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር እንደሚሰራ ተብራርቷል።
👉 ግልፀኝነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ርብርብ ይደረጋል።
👉የተጓተቱትን በማፍጠንና ህዝብንና የልማት አጋርን በማስተባበር የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እንተጋለን ።
👉በዕቅድ የያዝናቸውን በውጤታማነት እንዲተገበሩ የውስጠ ፓርቲ ዲሲፕሊንን በማጠናከር ፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን በአርአያነት ማጎልበት ይገባል ::
https://twitter.com/ProsperityKera
ብልፅግና ህብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት እየሰራ ያለ ፓርቲ!
ብልጽግና ፓርቲ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፤ ፓርቲው የተቋም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር በተለይ በአመራሩና በአባሉ ዉስጥ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለማምጣት በተሰራው ሥራ እጅግ አመርቂ ውጤቶች ታይተዋል፡፡
በከተማችን የመንግስት ተቋማት ተቋማዊ አሰራርን ተከትሎ እንዲፈጸሙ ለማድረግ ከተማውን የሚመጥ የአሰራር የመዋቅር ማሻሻያ በማድረግ ረገድ በርካታ የረፎረም ሥራዎችን በመሰራት ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ተግባራዊ በመደረጉ ምክንያት የመፈጸም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ መጥቷል፡፡
በከተማችን የሚገኙ ሶስቱም የመንግስት አካላት ማለትም ህግ አዉጪ፤ ህግ ተርጓሚና ህግ አስፈጻሚ አካላት የተቀመጠውን አሰራር ስርዓትን በመጠበቅ በህግ ተርጓሚና በህግ አስፈጻሚ አካላትን በህግ አዉጪው አማካይነት ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ በመምራቱ ተቋማቱ ነጻነታቸውን በጠበቀ አግባብ እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
የዴሞክራሲ ተቋማትን ከመገንባት ረገድ በሀገረ አቀፍ ደረጃ የወጡ ህጎችና አዋጆች በከተማችን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ጠንካራ ክትትል እየተደረገ የተመራ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በከተማ ደረጃ የተለያዩ አዋጆችንና ደንቦችን በማዉጣት ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በከተማችን የወንድማማችነትና የእህታማማችነት አስተሳሰብ እንዲጎለበት ሰፋፊ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ፤ ውጤትም ታይቶበታል፡፡
ከተማችን አዲስ አበባ የጋራ ቤታችን የሚል መርህ ቃል በመያዝ ወደ ተግባር የገባን ሲሆን በከተማችን የሚከናወኑ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላት በሚከበሩበትም ወቅት በአብሮነት፤ በወንድማማችነትና በእህታማማችነት መንፈስ በሚያጎለብት መልኩ እየተከበሩ ይገኛል፡፡
ብልፅግና ህብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ጠንክሮ እየሰራ ያለ ፓርቲ ሲሆን በቀሪው የምርጫ ዘመንም አጠናክሮ የሚያስቀጥል ይሆናል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
https://twitter.com/ProsperityKera