"ABO Shaneen qabsoo galma hin qabneen ummata Oromoo dararaa guddaaf saaxileera" Miseensota ABO Shanee qabsoo daandii nagaa filatan.
https://twitter.com/ProsperityKera
የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኦሮሚያ ክልል ቢሻን ጉራቻ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የደቡብ ግንባር ሆስፒታል የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
የሆስፒታሉን የግንባታ ሂደትና አሁን ያለበትን ደረጃ በተመለከተ በተቋራጩ ገለፃ እንደተደረገ ተገልጿል፡፡
የሆስፒታሉ ግንባታ ከተጀመረ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም አሁን ያለበት የግንባታ ደረጃ ጥሩ የሚባልና በተፈለገው ልክ እየሄደ መሆኑን ተናግረው ፥ ሆስፒታሉ በተቀመጠለት ጊዜ ተገንብቶ መጠናቀቅ እንዳለበት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አሳስበዋል፡፡
በጉብኝቱ ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በተጨማሪ የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼን ጨምሮ የደቡብ ዕዝና የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዦች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ / ፅ /ት በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አመራሮች የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የፓርቲና የድርጅት ስራዎች አፈፃፀምን መገምገም ጀምረዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ እና የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔና ምክትል አፈጉበዔ፣ የተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ የኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች፣ የዲሞክራስ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የተፈፀሙ ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ቁርሾዎች እንዲጠገኑ እንዲሁም ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው ሽግግር እንዲሳካ የተሟላ የሽግግር ፍትሕ መተግበር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመድረኩ ገልጸዋል።
አስተዳደራዊ ፍትሕ ከወንጀል እና ፍትሐ ብሔራዊ ክርክሮች በላይ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ወይም እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር የፍትሕ ዘርፍ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ምክር ቤቱ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰጠው የድጋፍ፣ የቁጥጥር እና የክትትል ዓይነቶችን ለመለየት ያስችለው ዘንድ በአዋጁ ዙሪያ ውይይት መደረጉ ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አመላክተዋል።
የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ የፌደራል ሥነ-ሥርዓት አዋጅ አፈፃፀምን በተመለከተ በአዋጁ የተሰጡትን ኃላፊነቶች ከመወጣት ጎን ለጎን በአዋጁ ተፈፃሚነት ላይ የክትትል ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ተቋሙ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን አዘጋጅቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ቀርቦ መጽደቁንም አመላክተዋል።
አያይዘውም አዋጁ እና ፖሊሲው በመንግስት አካላት ዘንድ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር እንዲሁም ተቋሙ በትግበራ ሂደት የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ምክር ቤቱ የበኩሉን ድጋፍ በማድረግ ያግዘው ዘንድ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ይዘት እና ዳሰሳ፣ አስፈላጊነት፣ የሽግግር ፍትሕ ዓላማ እና መርሆዎች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በሚኒስትሩ ቀርበዋል።
ከግጭት ወደ ሰላማዊ ሁኔታ በሚደረግ ሽግግር፣ ከሽግግሩ በፊት በደረሱ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች የተሟላ መፍትሄ ለመስጠት የሽግግር ፍትህ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን የሚያመላክቱ በርካታ ሃሳብ እና አስተያየቶች መነሳታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera
“በጎነታችን ለዘላቂ አብሮነታችን“
የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ሊግ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ዕድሳት ፕሮግራሙን የከተማ እና የክ/ከተማው አመራሮች በተገኙበት አስጀምሯል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ አስተባበሪ አቶ የኋላሸት በቀለ በመርሀ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ፅ/ ቤት ወጣቶች ሊግ የአቅመ ደካማ አረጋዊያንን ቤት በማደስ እና በመሳሰሉት የበጎ ፈቃድ ተግባርን ባህል ለማድረግ የሚያደርጉትን ግንባር ቀደም እንቅስቃሴ እንዲያጠናክሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ የ ክ/ከተማው ወጣቶች ሊግ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር አቅመ ደካማ ወገኖችን ለመደገፍ እያደረጉት ያለውን ጥረት አድንቀው ዛሬ የተጀመረውን የቤት ዕድሳትም በአጠረ ጊዜ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎቹ ለማስተላለፍ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ሊግ ፅ/ቤት ሀላፊ ወጣት መለሰ አባተ
በበኩላቸው በአቅም ምክንያት የወገናቸውን እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን ችግር ከመቅረፉ ባሻገር የወጣቶችንም አብሮነት የሚያጠናክር ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ ዘጠኝ አሰተዳደር በዛሬው ዕለት የተጀመረው የቤት ዕድሳት መርሀ -ግብር በ ክ /ከተማው በ12ቱም ወረዳዎች የሚገኙ 14 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመለየት ወደ ስራ መገባቱን የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ሊግ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ግዛቸው አስረድተዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት፣ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ዙሪያ መክረዋዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ÷የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉንና የቻይናው ኮሙኒስት ፓርቲ አጋርነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደመጣ አንስተዋል።
ከዚህ በፊት በሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት መሰረት በትምህርት፣ በስልጠና እንዲሁም በተሞክሮና ልምድ ልውውጥ አብሮ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
በቅርቡ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት የልዑካን ቡድን ውጤታማ ቆይታ አድረጎ መመለሱም የዚህ ስምምነት አካል መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ለልዑካን ቡድኑ ለተደረገው አቀባበልና ስኬታማ የቆይታ ጊዜ ያላቸውን ምስጋናም መግለጻቸውንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቶች በመሰል የስልጠና እና የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሮች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብልፅግና ፓርቲ ፍላጎቱ እንደሆነ አብራርተዋል።
አምባሳደር ዣዎ ዢዋን በበኩላቸው÷ የብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየሰራቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎችን አድንቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቻይና ጠንካራ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ጠቅሰው÷ይህ ግንኙነት በፓርቲ ለፓርቲም ሆነ በመንግስታዊ ወዳጅነት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
የኬንያ ጦር አባላትን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲን ጨምሮ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፤ “ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ገደማ ላይ አገራችን እጅግ አሳዛኝ የሄሊኮፕተር አደጋ አስተናግዳለች” ብለዋል።
“የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋውም የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ኦጎላ ህይወታቸው ማለፉን ስገልጽ በትልቅ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ነው” ብለዋል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ።
ሄሊኮፕተሩ የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ኦጎላን ጨምሮ 11 የኬንያ ጦር አባላትን አሳፍሮ በመብረር ላይ እያለ መከስከሱንም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
በአደጋውም የኬንያ ጦር ዋና አዛዥን ጨምሮ የ 9 የኬንያ ጦር አባላት ህይወት ማለፉንም ነው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በመግለጫቸው ያስታወቁት።
በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል 2 የኬንያ ጦር አባላት በህይወት መትረፋቸውንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በመግለጫቸው፤ “ኬንያ ውድ ልጇን አጣች” ያሉ ሲሆን፤ እንደ ኬንያ ጦር ጠቅላይ አዛዥነታቸው ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማቸውም ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የብሔራዊ ሀዘን ጊዜ ይፋ ባደረገበት ወቅት "የመላው የኬንያ ህዝብ ከባድ ሀዘን ውስጥ ነው" ማለታቸውን አል አይን በዘገባው ገልፆአል።
https://twitter.com/ProsperityKera
መዲናን የረገጠ ሁሉ የማይረሳቸው ሼክ ኢስማኤል አል ዛይም አረፉ #RIP
በሶሪያ ሃማ የተወለዱት “አቡ አል ሳባ” በለጋስነታቸው ታዋቂነትን አትርፈው ነበር
ሶሪያዊው ሼክ ኢስማኤል አል ዛይም አቡ አል ሳባ በ96 አመታቸው አረፉ።
የሳኡዲ አረቢያዋን መዲና ከተማ የረገጠ ሁሉ ያውቃቸዋል አልያም ደግነታቸውን ሰምቷል የሚባልላቸው ሼክ ኢስማኤል የማይነጥፍ ችሮታቸው እስከህልፈታቸው ድረስ ዘልቋል።
ለሀጂና ኡምሯ ከተለያየ የአለም ክፍል የመጣ ሙስሊምም ሆነ መዲናን የሚጎበኝ የሌላ እምነት ተከታይ የሼህ ኢስማኤልን የነጻ በረከት ተቋድሷል ነው የሚባለው።
እኝህ አባት ባለፉት 40 አመታት በቀን ከ300 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ውሃ፣ ቡና፣ ወተት፣ ሻይ፣ ዳቦና ቴምር በነጻ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
አንድም ቀን የምሰጠው አጥቼ አላውቅም የሚሉት ሼህ ኢስማኤል፥ ለበጎ ስራቸው ከማንም ክፍያ እንደማይጠይቁ ለሳኡዲ መገናኛ ብዙሃን ተናግረው ነበር።
የነብዩ ቀብር ከሚገኝበት መስጂድ አጠገብ በፕላስቲክ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው ጎብኝዎችን በፈገግታ እየተቀበሉ ማስተናገድ በፈጣሪያቸው የሚያስገኝላቸውን በረከት ብቻ ነበር የሚያስቡት።
የአራት አስርት አመት ልግስናቸውና በጎ ምግባራቸው መዲናን በረገጠ ሁሉ ተወዳጅ ያደረጋቸው ሼህ ኢስማኤል አል ዛይም በሶሪያዋ ሃማ ከተማ መወለዳቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በርካቶች “አቡ አል ሳባ” እያሉ የሚጠሯቸው አባት በህመም ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በዱባይ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በከተማዋ እንቅስቃሴ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ።
በከተማዋ ወደ ዱባይ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደውን መንገድ ጨምሮ አውራ ጎዳናዎችና መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።
የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዘገባው እንደጠቀሰው ማክሰኞ ምሽት ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ የአየር ሁኔታ ምዝገባ ከተጀመረበት ከፈረንጆቹ 1949 ጀምሮ ከፍተኛው ነው።
በከተማዋ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጥለው ዝናብ በ24 ሰዓት ውስጥ በመጣሉ ጉዳት ያስከተለ ጎርፍ መከሰቱን ሮይተርስ እና ስካይ ኒውስ በዘገባቸው ጠቁመዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera
በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ማሪን ኮማንዶ በወሰደው እርምጃ በፅንፈኛ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አዲሚራል ናስር አባድጋ ገልፀዋል፡፡
ማሪን ኮማንዶ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ማለትም በሰሜን ሸዋ ውስጥ ባሉ ወረዳዎችና አካባቢዎች ተሰግስጎ የሚገኘውን የፅንፈኛውን ቡድን ለማጥፋትና የአማራን ክልል ከዘራፊው ቡድን ነፃ ለማድረግ በሁሉም አከባቢ ዘመቻ በማድረግ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብለዋል ፡፡
ማሪን ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሃይል መሆኑን ገልፀው አባላቱ ከክልሉ የፀጥታ ሃይል ጋር በመቀናጀት ባደረጓቸው ዘመቻዎች የቀጠናው ሠላም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ መጥቷል።
ሬር አዲሚራል ናስር አባድጋ የባህር ሃይል ማሪን ኮማንዶ የተሰጠውን ግዳጅና ተልዕኮ በብቃት እንዲወጣ የውጊያ ሰጪ ክፍልና የውጊያ አገልግሎት ክፍሉ የላቀ ሚና ተጫውቷል ይህንን ጥንካሬ ጠብቆ ለቀጣይ ግዳጅና ተልዕኮ የበለጠ መዘጋጀትም ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል ፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
#እውነት
👉 Dhugaan yeroo isaa eegee akkasitti cabsee baha hangasitti hin raafamin.
https://twitter.com/ProsperityKera
"አሳምነው እኮ ተራ ገንዘብ ወዳጅ ነው" አንዳርጋቸው ፅጌ
ሙት ሙትን ሲወቅስ ግን ጥሩ ነው? ቤቲ "አምስት ጉዳይ" በሚለው መፅሐፏ ላይ አንዳርጋቸውን ፅጌ ያላትን ስትከትብ "አሳምነው ፅጌን ማነው ጀግና አደረገው፣ ተራ ገንዘብ ወዳድ ነው። መፈንቅለ መንግስት አደርጋለሁ ሲል ትንሽ ብር ብሰጠው በደስታ ሊያብድ ነበረ" ሲል ስለ አሳምነው ፅጌ አውግቷት ነበረ።
ኸረ ግን የቁም ሟቹ በስጋ ሟቹን ሲቦጭቅ አያምርበትም ብዬ ዝም አልኩ።
እኔማ ሃሳቤ የአሳምነው ፅጌን ስልክ የሚያቀብለኝ ካገኘሁ ደውዬ ስለ ወንድሙ ማለቴ ስለ ተግባር ወንድሙ ሹክ ልል ነበረ ሃሳቤ ...
እስኪ ስልኩን ላኩልኝ ሹክ ልበለው¿¿¿
https://twitter.com/ProsperityKera
የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባ በህቡዕ በተደራጀው ፅንፈኛ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ የተባለው የፅንፈኛው ቡድን አመራር እና አቤነዘር ጋሻው አባተ የተባለ የቡድኑ አባል ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ ሕጋዊ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ የተባለው የቡድኑ አባል ደግሞ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባና አካባቢዋ ተወጥኖ ለከሸፈው ህቡዕ የጥፋት ተልዕኮ ዋነኛ ጠንሳሽ የሆነው ናሁሰናይ አንዳርጌ የተባለው ግለሰብ የጽንፈኛ ቡድኑ መሪ እንደነበር የጋራ ግብረ-ኃይሉ በመግለጫ አረጋግጧል።
ናሁሰናይ አንዳርጌ የጽንፈኛ ቡድኑ እኩይ ዓላማ እንዲሳካ የሽብር ጥቃት እንዲፈጽሙ የመለመላቸው ወጣቶች ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ የፋይናንስና የሎጅስቲክስ ድጋፎችን ከሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚገኙ ደጋፊዎቻቸው በማሰባሰብ ሁኔታዎችንም እንዳመቻቸ መግለጫው አትቷል፡፡
የፅንፈኛ ቡድን አባላት የተለያዩ የሽብር ጥቃት ለማድረስ በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ህቡዕ እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል እይታ ውጭ አልነበሩም ብሏል መግለጫው።
የሸብር ቡድኑ አባላት በዛሬው ዕለት በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ መኪናን በመጠቀም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ የሽብር ተግባራቸውን ለመፈፀም በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በፀጥታ ኃይሉ በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ከመሆን ይልቅ በፀጥታ አካላት ላይ ቶክስ በመክፈት በሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አደርሰዋል ብሏል መግለጫው።
በተጨማሪም አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ የሽብር ቡድኑ አባላት በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም አልተባበር በማለታቸው በፅንፈኛ ቡድኑ አባላት ተገድለዋል፡፡
ጽንፈኛ ቡድኑ በአማራ ክልል እያደረሰ ያለው ጥቃት እንደማያዋጣው በመረዳቱ ራሱን ወደ ሽብርተኝነት ቀይሮ በአዲስ አበባ እና አከባቢዋ የመጨረሻ መፍጨርጨር እያደረገ እንደሚገኝ የገለፀው የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል መግለጫ የከተማዋን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሰላም ወዳዱ የአዲስ አበባ ነዋሪ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን እስከአሁን ድረስ እያደረገ ላለው ትብብር ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረበ ሆቴሎች፣ ገስት ሀውሶች፣ የቤት እና የመኪና አከራዮች እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ኅብረተሰቡ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ቀና ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን አቅርቧል።
#ለተቀናጀ _ልማት
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
https://twitter.com/ProsperityKera
በዛሬው እለት የቂርቆስ ክፍለከተማ የልማት ተነሺዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በመገኘት 4ኛ ዙር የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አውጥተዋል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ታይዋን 17 ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ርዕደ መሬት አደጋ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ በድጋሚ ለሰዓታት ከባድ በሆነ ተከታታይ ርዕደ መሬት መመታቷ ተገልጿል፡፡
በመጀመሪያ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 5 ሆኖ የተመዘገበ ሰኞ ምሽት በደሴቲቱ ምስራቃዊ ሁዋሊን ግዛት የደረሰውን ርዕደ መሬት ተከትሎ አነስተኛ መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተመላክቷል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 0 እንዲሁም 6 ነጥብ 3 ሆነው የተመዘገቡ የርዕደ መሬት አደጋዎች መከሰታቸውን የደሴቲቱ የአየር ሁኔታ አስተዳደር የርዕደ መሬት ማዕከል አስታውቋል፡፡
በፈረንጆቹ ሚያዝያ 3 በደረሰው ርዕደ መሬት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሕንፃዎችም ከዛሬ ጠዋቱ ክሰተት በኋላ በከፊል መውደቃቸውን የሁዋሊን ግዛት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የማዕከላዊ የአየር ንብረት አስተዳደር የርዕደ መሬት ማዕከል በአደጋው የተጎዱ ሰዎች እንደሌሉና በሁዋሊን ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ እንደተላለፈ ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡
ቀደም ሲል የደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ በታይዋን ከ25 ዓመታት በፊት በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 ሆኖ ከተመዘገበውና 2 ሺህ 400 ሰዎችን ለህልፈት በመዳረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ህንፃዎችን ካወደመው ርዕደ መሬት በኋላ ከባዱ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለሚገጥሙን የውስጥና የውጪ ፈተናዎች ሁሉ የመፍትሄ መንገድ ነው!!
የሀገራችን ህዝብ አንድነቱን በማጠናከር ከውስጥም ከውጪም አብሮ ሲሰራ ማንኛውንም ችግር መሻገር እንደሚችል በአንድነታችን የተመዘገቡት ስኬቶች እና ትልቅ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉ ማሳያዎች ናቸው።
ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ አካላት አላማቸው ሊሳካ የሚችለው የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ሲዳከም ብቻ እንደሆነ ይረዳሉ። ለዚህም ህዝብ እንዲከፋፈል የሚያደርጓቸውን የሀሰት አጀንዳዎችን በማሰራጨት ሰላም ለማደፍረስ ይጥራሉ።
ሀገራዊ አንድነታችን ህብረብሄራዊነት ብዝሃነትን ያረጋገጠ ሀገራዊ አንድነት ጠንካራ ስርዓት የገነባች እና ዘላቂ ልማትን ያረጋገጠች ሀገር ለመፍጠር ትልቅ ሚና ይጫወታል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ሲጠናከርና በውስጡ መረጋጋት ሲሰፍን ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር መሆን እንደምትችል ከለውጡ በኋላ የተገኙ ውጤቶች ትልቅ ማሳያ ናቸው።
ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ለሁሉም የምትመች፣ ህብረ ብሔራዊነት እና ወንድማማችነት የምታስተናግድ ሀገር እንድትሆን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።
የሚያጋጥሙንን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እና ተግዳሮቶችን በመቅረፍ በዘላቂነት ለመፍታት አንድነትን ማጠናከር እንደ ህዝብና እንደ ሀገር ሰላምና መረጋጋትን እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማስፈን ትልቅ ሚና ይጫወታል። ስለሆነም በአንድ በኩል የሚገጥሙንን ፈተናዎች በመመከት፣ በሌላ በኩል ሀገሪቱን ለትውልድ የማሻገር ኃላፊነት ለመወጣት ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች አንድነታችንን በማጠናከር ጠንካራ ሀገረ መንግስት መፍጠር እና መገንባት የሁላችንም ድረሻ ሊሆን ይገባል።
በህብረ ብሄራዊነት የደመቀች ሀገር ሰላም ፍትህ ዲሞክራሲ የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ተግባር በህብረት መስራት ይጠበቅብናል!
https://twitter.com/ProsperityKera
በመጪው ክረምት ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል ።
ስልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍና የመምህራን ብቃትን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ይሰጣል ነው የተባለው።
በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አመራር መሪ ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) መምህራኑ የሚሰለጥኑት በሚያስተምሩት ትምህርትና በማስተማሪያ ዘዴዎች መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል ።
ለ42 ሺህ መምህራን 120 ሰዓት፤ ለ8 ሺህ የትምህርት አመራሮች ደግሞ የ60 ሰዓት ስልጠና እንደሚሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን ÷ሲያጠናቅቁም ፈተና እንደሚወስዱ ነው ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡
ስልጠናው በመምህራንና የትምህርት አመራሩ ላይ ያለውን የማስተማር ዘዴዎችና የእውቀት ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ በመደመር ዕሳቤ በአዲስ ጉልበትና ምዕራፍ መትጋት ይገባናል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ተናገሩ።
የለውጡን መንግስት ለመደገፍ ያለመ ህዝባዊ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ በሀገር ግንባታ ሂደት የጉራጌ ማህበረሰብ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ዴሞክራሲያዊ ስርአት ባልነበረበት ጊዜም ጭምር በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ግንባታ ጉልህ አበርክቶ እንደነበረው ተናግረዋል።
ከስድስት ዓመታት በፊት ለውጥ እንዲወለድ በማድረግ ረገድም ከለውጥ ፈላጊ አካላት ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።
በለውጡ ማግስትም ራሱን ችሎ በክልል ለመደራጀት መንቀሳቀሱንና በኋላም በተደረጉ ውይይቶች የክላስተር አደረጃጀትን መርጦ ከሌሎች ወንድምና እህት ህዝቦች ጋር መደራጀቱን አስታውሰዋል።
በዚህም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተመስርቶ በአዲስ ጉልበት በአዲስ ምዕራፍ ለለውጥ እየተጋ መሆኑን ገልጸዋል።
ዛሬም በዘመነ መደመር ከለውጡ መንግስት ጎን በመቆም የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ስር እንዲሰዱ ለማድረግ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።
የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግም ቁርጠኝነቱን ያረጋግጣል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ጉዞ የጉራጌ ማህበረሰብ እንደሚደግፍም ነው የተናገሩት።
የትጋትና የልማት ተምሳሌት የሆነው የጉራጌ ማህበረሰብ የለውጡን መሪና መንግስት በመደገፍ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ልማት ይተጋል ብለዋል።
ህዝቡ በቀጣይም የተጀመሩ ልማቶችን በማጠናከር አገራዊ ብልጽግናን እውን የማድረግ ጉዞውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው የጉራጌ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም እንደ ስንቅ ይዞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ተሰማርቶ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የመደመር ዕሳቤን የተረዳና እየተገበረ የሚገኝ ማህበረሰብ መሆኑን ገልጸው በመረዳዳት መንፈስ ሁል ጊዜ ለለውጥ የሚተጋ ነው ብለዋል።
ስራ ሳይንቅ በመስራት የይቻላልን መንፈስ በተግባር ያስተማረ ማህበረሰብ መሆኑንም ተናግረዋል።
የጉራጌ ማህበረሰብ አገራዊ ለውጡ እንዲወለድ ከለውጥ ፈላጊ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ዋጋ መክፈሉን ገልጸዋል።
አሁን ደግሞ ለውጡን በማጽናትና ብልጽግናን በማረጋገጥ ረገድ በበለጠ ትኩረት መስራት ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።
https://twitter.com/ProsperityKera
#ተሳስታችኋል!
• አንድ ሰው ትቷችሁ ስለሄደ ብቻ ከዚያ ሰው ውጪ መኖር እንደማትችሉ የምታስቡ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!
• አንድ ሰው ስለጎዳችሁ ብቻ ሰው ሁሉ ሊጎዳችሁ እንደሚችል ወደማመን ፍርሃት የመጣችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!
• አንድና ሁለት ነገሮች ስላልተሳኩላችሁ ብቻ ስኬተ-ቢስ እንደሆናችሁ አምናችሁ ተቀብላችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!
• ፈተናን ስለወደቃችሁ ብቻ ውዳቂ እንደሆናቸው ወደማሰብ መጥታችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!
• አንድ ሰው ወይም ሁኔታ ስላስቆሟችሁ ብቻ ወደፊት መቀጠል እንደማትችሉ ወደማመን ዝቅታ ወርዳችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!
ፈጣሪ የሰጣችሁ ሕይወት ከየእለት የልምምድ ውጣ-ውረዳችሁ በላይ ነች . . . ሰዎች ከሚያደርጉባችሁ፣ ከሚያስቡባችሁና ከሚያወሩባችሁ በላይ ነች . . . ከሆነላችሁና ካልሆነላችሁ ነገር በላይ ነች . . . ከተሳካውና ካልተሳካው ነገር በላይ ነች!
ሕይወታችሁ የሚሽከረከረው ከሰዎችና ከሁኔታዎች መለዋወጥ አንጻር ወደሆነ ሕይወት የወረዳችሁ ጊዜ የስህተትን ሁሉ ትልቅ ስህተት እንደሰራችሁ አትዘንጉ፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
በአምራች ኢንደስትሪዎች የተደረገ ጉብኝት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር Abiy Ahmed Ali (ዶ/ር)
https://twitter.com/ProsperityKera
የፕላስቲክ እና የቆሻሻ ብክለት ሥነ ምኅዳራችንን እና ጤናችንን አደጋ ላይ ይጥላል። በኃላፊነት ስሜት ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ እና ዘላቂ አማራጮችን በመምረጥ ተፈጥሮን ለትውልድ ማቆየት እንችላለን። ከተሞቻችን እና አካባቢያችን ጽዱ ለማድረግ እንተባበር።
Plastic and waste pollution threatens our environment, ecosystems, and health. By consuming consciously, disposing responsibly, and choosing sustainable alternatives, we can preserve our natural world for generations to come. Let's unite to keep our cities and environment clean.
© የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
https://twitter.com/ProsperityKera
የፍትህ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀውን የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘት እንዲሁም ቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ በቀጣይ ቀናት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ ጉልህ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ቁርሾዎች አግባብነት ባለው፣ ሁለንተናዊ፣ የተቀናጀና አሳታፊ በሆነ መልኩ ሳይፈቱ ሲንከባለሉ መምጣታቸውን ገልጿል፡፡
በደሎች እንዲሽሩ፣ ቁርሾዎች እንዲጠገኑ እና ወደ ዲሞክራሲ የሚደረገው ሽግግር እንዲሳካ፤ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እንዲቻል የተሟላ የሽግግር ፍትህ ሂደት መተግበር ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክቷል፡፡
ይህንንም በማመን በተሟላና በተቀናጀ መልኩ የሚዘረጋ አሳታፊ፣ ተጎጂዎችን ማእከል ያደረገ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መርሆዎችንና ድንጋጌዎችን ያከበረ፣ የሀገራችንን ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ አውድን መሰረት ያደረገ የሽግግር ፍትህ ሂደት መቀመር እና በግልፅ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲመራ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው ያለው ሚኒስቴሩ ስለሆነም የሽግግር ፍትህ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድንን በማቋቋም የባለሙያዎች ቡድኑ ባደረገው ሀገራዊ ግብአት የማሰባሰብ የምክክር መድረኮች ያገኘውን ግብአት እና የባለሙያዎች ቡድን ምክረ ሀሳብን የያዘ ሪፖርት ይፋ ያደረገ መሆኑን አመልክቷል፡፡
ከዚህም ባሻገር ቡድኑ ረቂቅ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሰነድን በማዘጋጀት ለፍትህ ሚኒስቴር በማስረከብ የተሰጠውን ሀላፊነት በከፍተኛ ደረጃ በመወጣት ተሰናብቷል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
የፍትህ ሚኒስቴርም ቀጣዩን የድህረ ረቂቅ ፖሊሲ ተግባራት በመረከብ የተዘጋጀው ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት በተገኘው ግብአት መሰረት ረቂቅ ፖሊሲውን በማዳበር የመጨረሻ ረቂቅ ፖሊሲን በማዘጋጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አመልክቷል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤትም በዛሬው እለት በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ሊሻሻሉ የሚገባቸውን አንዳንድ ጉዳዮችን በማካተት ፖሊሲውን በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
የፍትህ ሚኒስቴር የጸደቀውን የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘት እንዲሁም ቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ በቀጣይ ቀናት ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera
በጣም ያሳዝናል
እስክንድር ነጋ የገባው የሰላማዊ አማራጭ ለጃውሳው አመራሮች አልተዋጠላቸውም፡፡ ለሰላም የሰጠውን አማራጭም አጨናግፈዋል
#ጃዉሳ_ይወቀጣል
#መከላከያችን_መከታችን
https://twitter.com/ProsperityKera
አቶ ማለቴ እከሌ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ትዳርና ፖለቲካ የማይፀናለት ግን ለምንድነው?
ለነገሩ እኮ እሱ ከትዳሩ ብቻ አይደለም በእየዘመኑ የሚይዙትን / የሚይዛቸውን ፍቅሮች አንጠባጥቧቸዋል።
የሆነ የሚጫነው አዙሪት ይኖር ይሆን? 🤫
ከቅንጅት፣ ከኢሳት፣ ከእስክንድር፣ ከኤርትራ (ይህቺ እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም)፣ ከግብፅ፣ ከኢዜማ፣ ከዐብቹ መኪና፣ ከኢትዮጵያ፣ ከእንግሊዝ፣ ወዘተ ኸረ ከቅሊንጦም፣ እኔ ከቤቲም አላልኩም። ምናልባት እሷ ብላ ይሆናል። መሠለኝ ነው።
ግን ወጣቱ 🤣🤣🤣 ከስንቱ ተፋቅሮ ከስንቱ ተጣላ?
አሁን ደግሞ ተረኛው መሳይ እና ... ይመስላሉ 🤭🤭🤭
https://twitter.com/ProsperityKera
በፅንፈኛው የፋኖ አመራርና አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን ፖሊስ ገለፀ፡፡
የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው አመራርና አንድ የቡድኑ አባል ላይ እርምጃ መውሰዱንና አንደኛውን ደግሞ መቆጣጠሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
የፅንፈኛው ቡድን አባላት የሆኑት ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ በከተማችን አዲስ አበባ የሽበር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው እየተንቃሰቀሱ መሆኑን የፀጥታ አካላት ክትትል ሲያደርግባቸው መቆየቱ ተጠቅሷል።
አሸባሪዎቹ የሽብር ተግባራቸውን ሳይፈፅሙ በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ/ም ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ ፅንፈኞች እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸውና ከፖሊስ አባላት ጋር ቶክስ በመክፈታቸው የፅንፈኛው ፋኖ መሪ ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት ፅንፈኛው ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል መገደሉን ፖሊስ ገልጿል።።
አቤኔዘር ጋሻው አባተ የተባለው የቡድኑ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉንም አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፅንፈኞቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ሲቆስሉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ፅንፈኞቹ በመኪናቸው እንዲጭኗቸው ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በፅንፈኛው አባላት መገደላቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ በቀጣይ የደረሰበት ዝርዝር መረጃ አሳውቃለሁ ብሏል።
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን በሁሉም ዘንድ የተመረጠች ና የተወደደች ለማድረግ በተለይም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ኩራት ና ውበትን የተላበሰች ከተማን ለመፍጠር እንዲሁም የአዲስ አበባን ዘመናዊነት፣3ኛዋ የአለም የዲፕሎማት ከተማነቷን ያመላከተና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫነቷን መመጥን በሚችል ደረጃ ቀን ከሌት በስራ ላይ ትገኛለች። የአለም አቀፍ ቱሪስቶች መስህብና ተፈላጊነትን የተጎናፀፈች ከተማን ዳግም ከመገንባት አንፃር ክብርት ከንቲባችን ከተለያዩ አውሮፓና አሜሪካ ታላላቅ ና ታሪካዊ ከተማዎች ጋር የልምድ ልውውጥና የእህታማማችነት ፊርማን በመፈራረም ዘርፈ ብዙ ልምዶችን በመቅሰም እየተተገበረ ይገኛል። በቅርቡም በዋሽንግተን ዲሲ በቼሪ ብሎሰም የከተማ ኮሪደር ልማት ና ሙዚየም ለከተማውና ለአከባቢው ማህበረሰብ ያጎናፀፈውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሚታውን በ March 21/2024 ክብርት ከንቲባ ጉብኝት አድርገው በርካታ ልምዶችን ቀስመውና ቀምረው በስራ እያሳዩን ይገኛሉ።
በየጊዜው ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ጎብኝዎች ይኼን ስፍራ ይጎበኛሉ። በቱሪስት መስህብነትና ታሪክ አስተማሪነት የሚታወቀው ይህ ስፍራ በርካታ የጉብኝት አይነቶችን ያካተተ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለግማሽ ቀን በእግር የሚጓዙበት ውብ ስፍራ ፣ የሊንከን መታሰቢያ፣ የኮሪያ ጦርነት ዘማቾች መታሰቢያ፣ የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር መታሰቢያ ፣ የዋሽንግተን ሀውልት፣ የሁለተኛው የአለም ጦርነት መታሰቢያ እና የብሄራዊ የጸሎት ቦታን ያጠቃለለ ውብ ና ድንቅ የእጅ ጥበቦች የተለኩበት ስፍራ ነው። ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደነዚህ የመሳሰሉትን አለም አቀፍ መስህብነትን ከታሪካዊ ዳራ ጋር ያጣመሩ ስፍራዎችን በመጎብኘት የስራ ባህላችንን በመቀየር በ 24 ሰዓትና እና 7ቀን( 24/7) በመስራት በተጨባጭም የቀሰሙትን ልምድ ከነባራዊ እሴቶቻችን ጋር በመቀመር በስራ ላይ እያሳዩን ይገኛሉ። አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብና ያበበች በሁሉም ተመራጭ የሆነች ነዋሪዎቿ የሚኰሩባት ከተማ በቅርብ ጊዜ እውን እንደሚሆን ጥርጥር የለንም።