prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1422

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ከሸማችነት ወደ አምራችነት 422 ነዋሪዎችን የሌማት ቱሩፋት ተጠቃሚ አድርገናል" -አቶ ናሆም መንግስቱ - በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ዋና ስራ አስፈጻሚ

በቂርቆስ ወረዳ አራት ዛሬ ከሰአት ከ 2,528,000 ብር በላይ ከባለሃብቶች እና ከመንግስት ድጋፍ የተደረገበት ዶሮ፣ ኬጅ እና የዶሮ መኖ ስርጭት ተካሂዷል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ከሸማችነት ወደ አምራችነት በሚል መርህ በ6ኛ ዙር የሌማት ቱሩፋት ንቅናቄ መርሃ ግብር ለ422 የወረዳው ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረገ ማዕድ ማጋራት ተችሏል።

በሰርቶ ማሳያነት በአብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት 1572 ካሬ መሬት የጓሮ አትክልት በከብት እና በዶሮ እርባታ በቂ ስልጠና በመስጠት በአሁኑ ሰዓት ከቤተሰብ ፍጆታ ተርፎ ለቅዳሜና እሁድ ገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ እንደሆነ አቶ ናሆም ገልፀዋል።

ለክፍለ ከተማ አስተባባሪ ለወረዳው አመራር ለባለሀብቶች በጎአድራጎት ወጣቶች ባለድርሻ አካላት በእኔናና በወረዳው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል አቶ ናሆም

የዜጎቻችንን የኑሮ ጫና ለመቀነስ መንግስት እያከናወናቸው ካሉት እቅጆቹ አንዱ የከተማ ግብርናና የሌማት ቱሩፋት መርሃ ግብር አንዱ ነው ይህንንም መርሃ በቂርቆስ ወረዳ 04 በግንባር ቀደምትነት እየተተገበረ እንደሚገኝ እና ሌሎችም ከዚህ ተሞክሮ መውሰድ እንዳለባቸው የክፍለ ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ፅህፈት ቤት ወይዘሮ በለጠች ተሰማ ገልፀዋል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"አዲስ አበባን መልሶ የማልማቱ እቅድ በንጉሱ ጊዜም ነበር። ይሄንን የሚገልጽ በንጉሱ ጊዜ የታተመ ጋዜጣ በእጃችን ላይ አለ። ጋዜጣውን በማንኛውም ጊዜ ለሚዲያ መስጠት እንችላለን። እኛ ያደረግነው የኮራደር ልማቱ ነዋሪ ህዝባችንን በሚጠቅም መልኩ ነው እያከናወንን ያለነው። ስራው በጥናትና በእቅድ እየተመራ ስለሆነ ሁልጊዜም እንደምንለው ቅድሚያ ለሰው ሰጥተን በሰው ተኮር እይታ እየተከናወነ ይገኛል!" - ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ - በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ

Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ 👏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

“የኮሪደር እና የመልሶ ማልማቱ ለከተማችን ነዋሪዎች በርካታ ፋይዳዎች አስገኝቷል”፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

“የኮሪደር እና የመልሶ ማልማቱ ለከተማችን ነዋሪዎች በርካታ ፋይዳዎች አስገኝቷል” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ የኮሪደር ልማቱን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት ከንቲባ አዳነች፣ “የኮሪደርና የመልሶ ማልማቱ ለከተማችን ነዋሪዎች ካስገኛቸው ፋይዳዎች መካከል በልማቱ ምክንያት ተነሺ የሆኑ እጅግ በተጎሳቆሉ እና ለመኖር በማይመቹ ቤቶች፣ ለተደጋጋሚ የእሳት እና የጎርፍ አደጋ እንዲሁም ለብክለት ሲዳረጉ የነበሩ የመሠረተ ልማት ጉድለቶች ባሉበት ሁኔታ ሲኖሩ የነበሩ የበርካታ ከተማችን ነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ ቤት አግኝተዋል” ብለዋል።

በዚህ አጋጣሚ በሺዎች የሚቆጠሩ ተከራይ የነበሩ ነዋሪዎችም የቤት ባለቤት መሆን ስለመቻላቸውም ገልጸዋል።

ከተማን ከተማ የሚያሰኘው የከተማ ፕላን መሆኑን በመግለፅ በተለይም የድሬኔጅ፣ ስዌሬጅ፣ የቴሌኮም፣ የመብራት፣ የደኅንነት መጠበቂያ ካሜራዎች በተቀናጀ መንገድ በመሬት ውስጥ እየተሠሩ ነው ብለዋል።

ይህ ደግሞ የከተማ ሥርዓትን የሚያሳልጥ እንደሚሆን እና ከተማዋን ከድንገተኛ፣ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎችም ለመታደግ አስተዋፅኦው ትልቅ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ለከተማዋ ነዋሪ ውብ እና ማራኪ የአረንጓዴ እና ሰፋፊ የሕዝብ የጋራ መገልገያዎች፣ መዝናኛ ቦታዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች፣ የከተማችንን ገፅታ የሚያሻሽሉ ናቸው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ የትራፊክ ፍሰቱን እና የትራንስፖርት ችግርን የሚያቃልሉ የአውቶቢስ እና ታክሲ ተርሚናሎች፣ የምድር ውስጥ ፓርኪንግ፣ የታክሲ ማውረጃ እና መጫኛ ቦታዎች፣ የመሮጫ ትራኮች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ የሳይክል መንገድ፣ የእግረኛ መሿለኪያ እና መሸጋገሪያ ድልድዮች፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱን የሚያሻሽሉ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

በዚህ ሂደት አዲስ አበባ አህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሚናዋን እንድትወጣና ተወዳዳሪ እንድትሆን ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ አሁን ያለበትን ሁኔታ ሲያብራሩም፣ “በ5ቱም የኮሪደር ልማት፣ ከመኖሪያ ቤት እስከ መስሪያ ቦታዎች 5 ሺህ 135 በማንሣት ቦታውን አፅድቶ ለልማት ዝግጁ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ እስካሁን ለ4000 (80%) የልማት ተነሺዎች ካሣ፣ ምትክ ቦታ፣ ምትክ ቤት እና ምትክ መሥሪያ ቦታ በመስጠት እንዲስተናገዱ ተደርጓል” ብለዋል።

ለ307 የግል ይዞታ ተነሺዎች በብር 2.8 ቢሊዮን ብር ካሣ ፀድቆ 1.5 ቢሊዮን ብር ካሣ መከፈሉን የገለፁ ሲሆን ቀሪዎቹ በሒደት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ለ417 የቀበሌ ንግድ ቤቶች እና ለ393 ለፌዴራል ኪራይ ቤቶች በድምሩ ለ1 ሺህ 117 የግል እና የመንግሥት ባለይዞታዎች 30 ሔክታር ምትክ መሬት ተዘጋጅቶ እየተስተናገዱ መሆኑን ከንቲባዋ ጠቅሰዋል።

በዚህ አጋጣሚ የቀበሌ እና የኪራይ ቤት ተከራይ ነጋዴዎችም ወደ ባለይዞታነት መሸጋገራቸውን ነው የጠቆሙት።

ከሥራ ዕድል አንፃር፣ በኮሪደር ልማቱ እና በመልሶ ማልማት፣ እንዲሁም በአረንጓዴ እና ውበት ዘርፎች ባጠቃላይ በቋሚነት ለ1 ሺህ 485 እና በጊዜያዊነት ለ13 ሺህ 784 በድምሩ ለ15 ሺህ 269 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ በተሟላ ሁኔታ ሲጠናቀቅ ደግሞ በነዚህ ቦታዎች ከመልሶ ማልማት በፊት ተፈጥሮ የነበረውን የሥራ ዕድል በ51 በመቶ የሚያሳድግ ይሆናል ያሉት ከንቲባዋ፣ የከተማዋ ገቢ እና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እንደሚጨምርም ጠቁመዋል።

እንዲሁም ከተማዋን የስማርት ሲቲ አገልግሎት አሰጣጥን ለመተግበር መሠረት ይጥላል ነው ያሉት።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለኮሪደር ልማቱ ትግበራ ከከተማዋ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ጥናት እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናዋ የኮሪደር ልማቱን ተግባራዊ ለማድረግ በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው፡ ባለሙያዎች ተሞክሮዎችን በመቀመር ከከተማዋ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ጥናት እንዲዘጋጅ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል

በጉባኤውም በከተማዋ እየተከናወነ ካለው የኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሪፖርት አቅርበዋል ፡፡

ከንቲባዋ ባቀረቡት ሪፖርትም ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ 2014 ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በገባው ቃል መሰረት የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ፡፡

አዲስ አበባን፣ እንደ ስሟ አበባ፣ ፅዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ በከተማ ኘላን የምትመራና የተሟላ የከተማ ስርዓት ያላትና፣ ለአፍሪካ ከተሞች የብልጽግና ተምሣሌት ለማድረግ የተያዘው ራዕይ እውን እንዲሆን በተደረገ ጥረት በርካታ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ማስመዝገብ ተችሏልም ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በ2ዐ16 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት የመጪውን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ አዳጊና ዘመን ተሻጋሪ ማህበራዊና ኢኖሚያዊ ተግባራት ማከናወን ችሏልም ነው ያሉት ከንቲባዋ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በከተማ ታቅደው ከተሰሩ ታላላቅ ታሪካዊና ዘመን ተሻጋሪ ፕሮጀክቶች አንዱ በሆነው፡ በአደዋ ድል መታሰቢያ ግንባታ የተገኘውን ልምድ፡ በሌሎች የልማት ስራዎች እንዲሰፋ፡ በከተማዋ እስከአሁን በየቦታው የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን የሚያገናኝ የኮርደር ልማት እንዲተገበር ከ2ዐ15 ጀምሮ ተገቢው ጥናት ተደርጎ ወደ ተግባር ተገብቷልም ብለዋል።

የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን መነሻ በማድረግ በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው፡ ባለሙያዎች ተሞክሮዎችን በመቀመር፡ ከከተማዋ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የኮሪደር ልማት ተጠንቶ እንዲዘጋጅ መደረጉንም አንስተዋል ፡፡

ጥናቱ በየደረጃው ላሉ ባለድርሻ አካላት ቀርቦ በውይይት የተገኙ ግብዓቶች ተካተው እንዲዳብር በማድረግ ለከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ቀርቦ እንዲጸድቅ ተደርጓልም ብለዋል ከንቲባዋ በሪፖርታቸው።

ጥናቱ በተደረገባቸው ኮሪደሮች የተገኘው የጥናቱ ውጤትም ፡ ትላልቅ የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ያልተገናኙ መሆኑን፣ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ መፈጠሩን፣ የከተማ ኘላን አተገባበርና የከተማ ስርአት መጓደልን፡ በተለይም ደካማ የፍሳሽና የጐርፍ ማስወገጃ አለመኖሩን መመላከቱን አስረድተዋል፡፡

እንደ ሸረሪት ድር የተጠላለፉ የመብራትና የቴሌ መስመሮች፡ የመፀዳጃና የማብሰያ ስፍራ ያለመኖር፡ ሰዎች በቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በቆጥ ላይም ለመኖር የተገደዱበት፣ ለሰው ሰራሽና ለተፈጥሮ አደጋዎችም በተደጋጋሚ ተጋላጭ የሆኑበት አስቸጋሪ ሁኔታዎች መኖራቸውንም ጥናቱ አሳይቷል ብለዋል ከንቲባዋ።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የስራ ባህላችንን እያሻሻለች እየቀየረች የመጣች ከተማ #አዲስአበባ #ፊንፊኔ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉባዔውን በቀጥታ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (አዲስ ቲቪ) AMN-Addis Media Network መከታተል ይችላሉ።

@AdanechAbiebie 💪💪💪

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አልዳባቢያን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል። በውይይታችን ወቅት በቀጠናዊ የሰላም እና መረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የሰው ኃይል ልውውጥ እና በሌሎች የጋራ ፍላጎት ጉዳዮችን አንስተናል።

I am pleased to welcome Prime Minister Abdul Hamid Al-Dabaiba of the State of Libya. During our meeting, we engaged in discussions regarding regional peace and stability, economic cooperation, workforce exchange, and other areas of mutual interest.

© ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እንደ ስሟ ሁለንተናዋ እየበለፀገ የምትገኝ ከተማ #አዲስአበባ #ፊንፊኔ

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ይሄንን ነባር ልማድ ቀይሮታል። ጦርነትን በፖለቲካዊ መፍትሔ የመቋጨት ባህል አምጥቷል። ይሄ የሰላም ስምምነት ለትውልድ የአሸናፊ ተሸናፊ ትርክትን ከቂም ጋር ላለማውረስ የተደረገ በሳልና ቆራጥ ውሳኔ ነው። ይሄንን አማራጭ ተከትለን፣ ደም መፋሰስ እና ግጭትን ማቆም ችለናል። በአማራ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ተጀምረዋል። ሰብአዊ ድጋፍም ያለመሰናከል ወደ ትግራይ መድረስ የሚችልበትን ዐውድ ፈጥረናል። የሰላም ስምምነቱ በተፈረመ ማግሥት መንግሥት በሰላም ስምምነቱ ከገባው ግዴታ ያለፈ፣ መተማመን ለመፍጠር እና ሰላምን ለማጽናት አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ርምጃዎች በተከታታይ ወስዷል። በሰላም ስምምነቱ እስካሁን የተገኘው ውጤት እና እፎይታ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀሪ ሥራዎችም አሉ። በተለይ በስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው። የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት። በጦርነቱ የተፈናቀሉትን ለመመለስና ለማቋቋም የተጀመረው ሥራ እልባት ማግኘት አለበት። ካለፈ ስሕተተ አለመማር የመጀመሪያውን ስሕተት ከመሥራት የባሰ ነው። ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ሁላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይኖርብናል። ከትዕግሥት በኋላ የሚከሠት ሕግ የማስከበር ሥራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባልና።

መንግሥት የተቋረጡ መሠረት ልማቶችን እና አገልግሎቶችን ለመጠገን እና መልሶ ለማስጀመር ወገቡን አሥሮ እየሠራ ነው። የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በትግራይ ክልል ለማሣለጥ እጅግ ከፍተኛ ወጪ አውጥቷል። የሰላም የትርፍ ድርሻው ታላቅ በመሆኑ መንግሥት ከሚጠበቅበትም አልፎ ቁስልን ለመሻር የሚያስችል ሥራ እየሠራ ነው። ይሄ ግን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንጂ ፍርሃት ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
በፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተገለጸው፣ በሕገ መንግሥታችንም እንደተደነገገው፣ እንደ ሀገር የሚኖረን አንድ የመከላከያ ሠራዊት ብቻ ነው። ክልሎች በክልል ደረጃ ሕግ ለማስከበር ከሚያስፈልጋቸው ፖሊስ እና ሚሊሺያ ያለፈ የታጠቀ እና የተደራጀ ሠራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባምም። በዚህ መሠረት ትጥቅ መፍታት እና ተያያዥ ሂደቶች በተሐድሶ ኮሚሽኑ ዕቅድ መሠረት በፍጥነት ሊተገበሩ ይገባል።

ወንድሞቻችን/እኅቶቻችን በተለይም ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍተው በጽንፈኞች እና በግጭት ጠማቂዎች ወደ ጦር ዐውድማ የሚማገዱበት አጋጣሚ አለ። መንግሥት ይሄንን ሁኔታ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ አያየውም። እንቅስቃሴያቸው ሕገ ወጥ ስለሆነ ብቻ ጉዳዩን በጉልበት ብቻ ይፈታ ማለት እንደሌለበት ይገነዘባል። ስለዚህ ከጥፋት መንገድ ለመመለስ እና ማኅበረሰቡን ተቀላቅለው ሰላማዊ ሕይወት ለመኖር ፍላጎት ያላቸውን ታጣቂዎች ሁሉ፣ በተዘረጋ እጅ ለመቀበል መንግሥት ፈቃደኛ ነው። ይሄንን ፈቃደኝነቱን እና ፍላጎቱን በተግባር በተለያዩ ክልሎች አሳይቷል። በቤነሻንጉል ጉሙዝ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጥተዋል። እነዚህም የተሐድሶ ሥልጠና ወስደው፣ ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። ይሄንንም በተሐድሶ ኮሚሽን በኩል ከክልሎች ጋር በመቀናጀት አጠናክረን እንቀጥላለን። ጥረቱን የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እንዲደግፉ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ እናደርጋለን።

እነዚህን ዘላቂ መፍትሔ አምጪ ሥራዎች በአንድ በኩል እያከናወንን የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት የሚያስከብሩ አሁናዊ ተግባራትንም ማከናወናችንን እንቀጥላለን። ጽንፈኛ የፖለቲካ አመለካከቶች እንዲሁም የተደራጁ የወንጀል እና የዘረፋ ፍላጎቶች በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ናቸው። እነዚህን በገጠርም ሆነ በከተማ የሕዝብን ሰላም የሚያውኩ እንቅስቃሴዎች ለመቆጣጠር መንግሥት ሰፊ ሥራ እየሠራ ነው። የዚህ ሥራ አንዱ አካል፣ የሕግ አስከባሪ ተቋማትን እያሻሻሉ ፤ ቅንጅታቸውን እና ከሕዝብ ጋር ያላቸውን ትሥሥር እያጠናከሩ እንዲሄዱ ማድረግ ነው። በገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮች፣ የየአካባቢው ነዋሪ በአግባቡ ሠልጥኖ አካባቢያዊ ሰላሙን ለማስከበር እንዲችል ይደረጋል። በዚህ ረገድ በአንዳንድ ክልሎች በጎ ጅምር አለ። እንደ ኢትዮጵያ ላለ እጅግ ሰፊ እና ብዙ ሕዝብ ላለበት ሀገር፣ የአካባቢ ሚሊሽያ እና ሌሎች አጋዥ ሰላም አስከባሪ አደረጃጀቶች አካባቢያዊ ሰላም እና ጸጥታን ለማስከበር ትልቅ ሚና አላቸው።

ከዚያ በተጨማሪ፣ የክልል ፖሊስ ኃይሎችን መልሶ በማደራጀት እና በሁለንተናዊ መልኩ በማጠናከር፣ ሕገ መንግሥታዊ ተልዕኳችውን በአግባቡ እንዲወጡ እየተደረገ ነው። በየአካባቢው ካሉት ሚሊሺያዎች እና የክልል ፖሊሶች ጋር በመቀናጀት፣ የፌደራል ፖሊስ የሀገር ውስጥ ሰላም እና ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ቀጣይነት ያለው ተቋም ግንባታ እና ማሻሻያ እየተካሄደ ነው። ከእነዚህ ሕግ አስከባሪ ተቋማት ያለፈ ሥጋት ካጋጠመ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰላም የማስጠበቅ እና ሕግ የማስከበር ተግባሩን እየተወጣ ይገኛል።

ይሄንን ዓይነት የጸጥታ አካላትና የሕዝብ ቅንጅት በመኖሩ፣ በአማራ ክልል የክልሉን መንግሥት አፍርሶ በኃይል ሥልጣን ለመያዝ ያሰበው ኃይል ፍላጎቱን ለማሳካት እንዳይችል ተደርጓል። በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ፣ የክልሉን መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመታደግ ተችሏል። በኦሮሚያ ክልልም በአንዳንድ የክልሉ ዞኖች የነበረው የታጣቂ ኃይሎች ሰፊ እንቅስቃሴ እና አንዳንድ ወረዳዎችን የመቆጣጠር አዝማሚያ ተቀልብሷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም የጸጥታና የደኅንነት ሁኔታው በእጅጉ ተሻሽሏል። በአዲስ አበባ እና በሌሎችም የሀገሪቱ ትላልቅ ከተማዎች የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም አቅደው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ዕቅድ ለማክሸፍም ተችሏል።

የተሠራው ሥራ ወሳኝ ቢሆንም በቂ ግን አይደለም። ፖለቲካ ቅብ የሆኑ የተደራጁ የዝርፊያ እና የወንጀል ቡድኖችን በሚገባ መቆጣጠር ይገባናል። ይሄንን ለማድረግም ጠንካራ እና ውጤታማ ሕግ አስከባሪ እና የጸጥታ መዋቅር እንዲኖረን የተጀመረው ሥራ ይቀጥላል። በዚህ ረገድ የሕዝብ ተሳትፎ እና እገዛ ወሳኝ ነው። እየዘረፈ፣ እየነጠቀ እና እያገተ ያለን ቡድን በተለያየ ሰበብ መሸከም እና ማባባል ማብቃት አለበት። በድኻ ገንዘብ የተሠሩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን የሚያወድም ቡድን የማንንም ፍላጎት አያስከብርም። ሕዝቡ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር የሕግ የበላይነትን ማስከበር ይገባዋል። በየአካባቢው የሚገኙ የፖለቲካ እና የአስተዳደር መዋቅሮችም፣ ሌላ አካል መጠበቅ ሳይሆን፣ ሕግን ማስከበር ቀዳሚ ኃላፊነታቸው እንደሆነ ተገንዝበው ሊንቀሳቀሱ ይገባል።

በአንድ በኩል ሕግ የማስከበርና ሰላምና ደኅንነትን የማጽናት ሥራ እያከናወንን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተፈናቀሉ ሰዎችን የመመለስ ተግባር መከናወን አለበት። ሰላምና ጸጥታ ሕዝብ ሲረጋጋ የሚፈጠሩ ሥርዓቶች በመሆናቸው። በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች፣ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል። እነዚህ ዜጎች ከመጠለያ ካምፖች ወጥተው ወደቀያቸው መመለስ ይኖርባቸዋል። በዘላቂነት ተረጋግተው ወደ መደበኛ ኑሮ መግባት አለባቸው። ይሄንን እውን ለማድረግ መንግሥት ሲተጋ ቆይቷል፣ አሁንም ሰፊ ሥራ እየሠራ ይገኛል። ለምሳሌ በሶማሌ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች፣ እንዲሁም በጌዴኦ አካባቢ ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ABO Shaneen qabsoo galma hin qabneen ummata Oromoo dararaa guddaaf saaxileera" Miseensota ABO Shanee qabsoo daandii nagaa filatan.

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኦሮሚያ ክልል ቢሻን ጉራቻ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የደቡብ ግንባር ሆስፒታል የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡

የሆስፒታሉን የግንባታ ሂደትና አሁን ያለበትን ደረጃ በተመለከተ በተቋራጩ ገለፃ እንደተደረገ ተገልጿል፡፡

የሆስፒታሉ ግንባታ ከተጀመረ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም አሁን ያለበት የግንባታ ደረጃ ጥሩ የሚባልና በተፈለገው ልክ እየሄደ መሆኑን ተናግረው ፥ ሆስፒታሉ በተቀመጠለት ጊዜ ተገንብቶ መጠናቀቅ እንዳለበት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አሳስበዋል፡፡

በጉብኝቱ ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በተጨማሪ የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼን ጨምሮ የደቡብ ዕዝና የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዦች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ / ፅ /ት በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ አመራሮች የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የፓርቲና የድርጅት ስራዎች አፈፃፀምን መገምገም ጀምረዋል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር በፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ እና የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔና ምክትል አፈጉበዔ፣ የተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ የኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች፣ የዲሞክራስ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የተፈፀሙ ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ቁርሾዎች እንዲጠገኑ እንዲሁም ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው ሽግግር እንዲሳካ የተሟላ የሽግግር ፍትሕ መተግበር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመድረኩ ገልጸዋል።

አስተዳደራዊ ፍትሕ ከወንጀል እና ፍትሐ ብሔራዊ ክርክሮች በላይ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ወይም እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር የፍትሕ ዘርፍ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ምክር ቤቱ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰጠው የድጋፍ፣ የቁጥጥር እና የክትትል ዓይነቶችን ለመለየት ያስችለው ዘንድ በአዋጁ ዙሪያ ውይይት መደረጉ ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አመላክተዋል።

የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ የፌደራል ሥነ-ሥርዓት አዋጅ አፈፃፀምን በተመለከተ በአዋጁ የተሰጡትን ኃላፊነቶች ከመወጣት ጎን ለጎን በአዋጁ ተፈፃሚነት ላይ የክትትል ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ተቋሙ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን አዘጋጅቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ቀርቦ መጽደቁንም አመላክተዋል።

አያይዘውም አዋጁ እና ፖሊሲው በመንግስት አካላት ዘንድ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር እንዲሁም ተቋሙ በትግበራ ሂደት የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ምክር ቤቱ የበኩሉን ድጋፍ በማድረግ ያግዘው ዘንድ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል።

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ይዘት እና ዳሰሳ፣ አስፈላጊነት፣ የሽግግር ፍትሕ ዓላማ እና መርሆዎች እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በሚኒስትሩ ቀርበዋል።

ከግጭት ወደ ሰላማዊ ሁኔታ በሚደረግ ሽግግር፣ ከሽግግሩ በፊት በደረሱ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች የተሟላ መፍትሄ ለመስጠት የሽግግር ፍትህ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን የሚያመላክቱ በርካታ ሃሳብ እና አስተያየቶች መነሳታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሰባራ ሳንቲም አስተዋጽኦ ያላደረጋችሁ ቆሞ ቀሮች ይህ ንግግር ይሰማል? 👆

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ 👆

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የከተማዋን የልማት ኮሪደርን አስመልክቶ ከተናገሩት 👇

- ለንግድ ቤቶች እና ለግል ባለይዞታዎች ምትክ መሬትና የካሣ ክፍያዎችን መፈጸም፣ የልማት ተነሺዎች ወደ ተዘጋጀላቸው የመኖሪያና የመስሪያ ቦታ የሚያጓጉዝ ትራንስፖርት ማዘጋጀት ፣ በገቡበት አካባቢ ልዩ አቀባበል እየተደረገላቸው ፣ በአብዛኛው ማህበራዊ ትስስራቸው ተጠብቆ የማዘዋወር ሥራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄና የኃላፊነት ስሜት ተከናውኗል

- ግልፅና ዝርዝር የማስፈጸሚያ እቅድ በማዘጋጀት የዲዛይን ዝግጅት፣ በጀትና ለልማት ተነሺዎች መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ መስሪያ ቦታና ምትክ መሬት የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል፡፡

- ከመኖሪያ እና መስሪያ ቦታቸዉ የሚነሱ የልማት ተነሺዎችን መረጃ ማደራጀት፣ ተነሺዎችን ማወያየት፣ በምርጫቸዉ መሰረት በተቀላጠፈ አግባብ የሚስተናገዱበት ስርዓትና የሚያጋጥሙ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ተዘርግቶ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

- የልማት ተነሺዎች የገቡባቸዉ የመኖሪያ ቤቶች የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው ስለመሆኑና የቅርብ ክትትል በማድረግ ተነሺዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡

- የከተማው ከፍተኛ አመራር የመኖሪያ ቦታዎችን ሁኔታ እና የልማት ተነሺዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመጎብኘትና አገልግሎት ስለመሟላቱና ጉድለቶችም ካሉ ለማረም የሚያስችል ጉብኝት በሁሉም ሳይቶች ላይ በተደጋጋሚ አድርጏል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

48.7 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

48.7 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት በተመረጡ የከተማዋ አምስት ኮሪደሮች በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮሪደር ልማቱን የአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ሪፖርት ለከተማዋ ምክርቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ አቅርበዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ባቀረቡት ሪፖርትም አምስቱ የኮሪደር ልማቶች ከ4 ኪሎ ፒያሳና የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ መልሶ ማልማት፣ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ በመገናኛ፣ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣ ከአራት ኪሎ መስቀል አደባባይ እና ከቦሌ ድልድይ፣ በመገናኛ አስከ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን/ እግዚቢሽን ማእከልን ያካተተ መሆኑን አንስተዋል፡፡

መሰረታዊ የሆኑ የመንገድ የኮሪደር ልማት ስራዎቹ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረግ እንዲቻል 24/7 እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች የመልሶ ማልማት ስራዎች በሚቀጥለው በጀት ዓመትና በቀጣይ ጊዜያት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተተገበረ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማት ስራው በከተማ ማዕከል እና ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚፈጸም በመሆኑ፡ ብቁ የሰው ሃይል ስምሪት፣ የግብዓት፣ የማሽነሪ፣ የፋይናንስ አቅርቦት እና የፕሮጀክት አመራር ክህሎት እንዲሁም፣ የብዙ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፡፡

ጊዜ ተወስዶ ለማቀድና በሂደቱ ሚና ያላቸው በባለድርሻ እና ተባባሪ አካላትን ተሳትፎ ለማረጋገጥ፡፣ግልፅና ዝርዝር የማስፈጸሚያ እቅድ ማዘጋጀት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣:በጀትና ለልማት ተነሺዎች መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ መስሪያ ቦታና ምትክ መሬት በማዘጋጀት፣ ስራ መሰራቱን አውስተዋል።

ከመኖሪያ እና መስሪያ ቦታቸው የሚነሱ የልማት ተነሺዎችን መረጃ ማደራጀት፣ ተነሺዎችን ማወያየት፣ በምርጫቸው መሰረት በተቀላጠፈ አግባብ የሚስተናገዱበት ስርዓት እና በሂደቱ የሚያጋጥሙ ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ተዘርግቶ ወደ ተግባር መገባቱንም ገልጸዋል።

ስራውን በተደራጀ አግባብ ለመምራት: የመረጃ ማጥራት፣ የልማት ተነሺዎች ፈጣን አገልግሎት የመስጠት፣ የመልካም አስተዳደርና ቅሬታ ሰሚ፣ የሥራ እድል ፈጠራ፣ ህንፃዎች እድሳት፣ የማሽነሪ እና የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ኮሚቴዎች ተደራጅተው በቅንጅት እንዲመራ ተደርጓልም ብለዋል።

በትግበራ ሂደቱ፡ መኖሪያ ቤት ማስተላለፍ፣ ለንግድ ቤቶች እና ለግል ባለይዞታዎች ምትክ መሬትና የካሣ ክፍያዎችን በመፈጸም፣ የልማት ተነሺዎች ወደ ተዘጋጀላቸው የመኖሪያና የመስሪያ ቦታ የሚያጓጉዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ተዘጋጅቶ፣ በገቡበት አካባቢ ልዩ አቀባበል እየተደረገላቸው እና በአብዛኛው ማህበራዊ ትስስራቸው ተጠብቆ የማዘዋወር ሥራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄና የኃላፊነት ስሜት መከናወኑንም ጠቅሰዋል።

መረጃ በማሳሳት፣ አገልግሎቱን በማጓተትና ለልማት ተነሺዎች የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ቅሬታ በፈጠሩ በየደረጃው ባሉ አመራሮች ላይ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉንም ከንቲባዋ በሪፖርታቸው አንስተዋል።

የልማት ተነሺዎች የገቡባቸው የመኖሪያ ቤቶች የመንገድ፣ የመብራት፣ የውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው ስለመሆኑና የቅርብ ክትትል በማድረግ ተነሺዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጣቸው መደረጉንም አንቲባዋ አውስተዋል።

የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች የመኖሪያ ቦታዎችን ሁኔታ የልማት ተነሺዎች አገልግሎት ስለመሟላቱና ጉድለቶችም ካሉ ለማረም የሚያስችሉ ጉብኝቶች በሁሉም ሳይቶች ላይ ማድረጋቸውን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ከመሰረተ ልማትና ከስራ እድል ፈጠራ ጋር የተያያዙ ጉድለቶችንም እንዲታረሙ የማድረግ ስራ መሰራቱን ጠቅሰዋል።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ለ417 የቀበሌ ንግድ ቤቶች እና ለ393 ለፌዴራል ኪራይ ቤቶች በድምሩ ለ1,117 የግልና የመንግስት ባለይዞታዎች 30 ሔክታር ምትክ መሬት ተዘጋጅቶ እየተስተናገዱ ነው፡፡ የቀበሌና የኪራይ ቤት ተከራይ ነጋዴዎችም ወደ ባለይዞታነት ተሸጋግረዋል፡፡"

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአምስት ኮሪደሮች እና በዓደዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ እየተካሄደ ለሚገኘው የመልሶ ማልማት ስራ አሰተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፌደራል ፖሊስ በ19ኛው የINTERPOL ዓለም አቀፍ ዓመታዊ ኮንፍረንስ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡- የINTERPOL ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ፈረንሳይ ሊዮን ከተማ ከሚያዝያ 15 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው 19ኛው የብሔራዊ ኢንተርፖል ቢሮ ኃላፊዎች (Heads of Interpol National Central Bureau) ዓመታዊ ኮንፈረንስ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ብሔራዊ ኢንተርፖልና ዓለም አቀፍ የፖሊስ ትብብር መምሪያ ኃላፊ ክቡር ረዳት ኮሚሽነር ደጀኔ በቀለ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኢንተርፖል ከተመሠረተ አንድ መቶ ዓመት ያለፈው ሲሆን 196 አባል ሀገራትን ያቀፈና ሀገራችን ኢትዮጵያም እ.ኤ.አ. ከ1958 ጀምሮ የድርጅቱ ዋና ዓላማ ለሆነው ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል እና ተጠርጣሪዎች ወንጀል ፈጽመው በሌላ ሀገር እንዳይደበቁ እና ለፍትህ እንዲቀርቡ ከማድረግ በተጨማሪ በመረጃ ልውውጥ የበኩሏን አስተዋጽኦ እያበረከተች እንደምትገኝ ታውቋል።

ክቡር ረዳት ኮሚሽነሩ ከኮንፈረንሱ ጎን ለጎን ከኢንተርፖል አገልግሎት ማስፋፋት ፕሮጀክት አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የአገልግሎት ማስፋፋት ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ ፖሊስ እስካሁን ላደረገው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበው በሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ የኢንተርፖል አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስላለበት ሁኔታ እና ስለሌሎች ወደ ኢሚግሬሽን፣ ኤርፖርት፣ ጉሙሩክ፣ የድንበር ሴኩሪቲ እና የኢንተርፖል አገልግሎትን ወደ ክልል የፖሊስ ተቋማት በማስፋፋት በድርጅቱ ዳታ ቤዝ የሚገኙ መረጃዎችን በሚጠቀሙበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል፣ የፎረንሲክ እና የሳይበር ወንጀል ምርመራን አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እያካሄደ ባለው ሪፎረም በተለይ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና በሰው ኃይል አቅም ግንባታ እንዲሁም በድርጅቱ ዳታ ቤዝ አጠቃቀም ላይ ከኢንተርፖል ጋር በትብብር ለመስራት ረዳት ኮሚሽነሩ ምክክር አድርገዋል።

የኢንተርፖል አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ለኢትዮጵያ ፖሊስ የሚያደርገውን የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የማቴሪያል ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል፡፡

“የብሔራዊ ኢንተርፖል ቢሮዎችን ግንኙነት በማጠናከር የዓለም ወንጀል ስጋቶችን መቀነስ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የድርጅቱ ዓመታዊ ኮንፍረንስ ላይ የሀገራት የብሔራዊ ኢንተርፖል ቢሮ ኃላፊዎች እና ከፖሊስ ጋር በአጋርነት የሚሰሩ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን የየሀገራቱ ኢንተርፖል ቢሮዎች ባለፈው ዓመት ስላከናወኗቸው እና በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት እንዲሁም የሀገራት ምርጥ ተመክሮዎች እየቀረቡ ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን ከውይይቱ በኋላ ልዩ ልዩ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል፡፡

© Ethiopian Federal Police

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሚያዚያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

31ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ለኢንደስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ፣ በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በማበረታታት ረገድ የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ እና የዘርፉን ተዋንያን የሚያበረታታ ሥርዓት በመዘርጋት ተወዳዳሪነት ማላቅ ይቻል ዘንድ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም ረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፣ የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጣውን ወጪ በከፊል መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

3. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የጤና ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በስራ ላይ ያለው የጤና ፖሊሲ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ፖሊሲው በጸደቀበት ወቅት ከነበረው ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ፣ እየተከሰቱ ያሉ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መበራከት፣ በሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና ዙሪያ የሚከሰቱ ለውጦች፤ዘርፉ ጥራት እና ፍትሀዊነት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ችግሮች የሚስተዋሉበት በመሆኑ እንዲሁም ከሀገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር የሚጣጣም የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

4. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው በግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በስራ ላይ የነበረው የግብርና ፖሊሲ ከአዳጊ የምርትና ምርታማነት ፍላጎት ጋር አብሮ መጓዝ የቻለ ባለመሆኑ፤ ለግብርናው ዘርፍ እድገት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን መለወጥ አስፈላጊ በመሆኑ እንዲሁም ሀገራችን ከምትከተለው ብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ስርአት ጋር የሚጣጣም ፖሊሲ ማስፈለጉ ታምኖበታል፡፡ ስለሆነም የግብርና ዘርፍን ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የበለጠ የሚያስተሳስር፣ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል፤ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም በገጠር መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የሚያግዝ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ብልጸግና አሰባሳቢ ትርክትን በመቅረፅ የበለጸገች ኢትዮጵያ ይገነባል!

ሀገራችን ኢትዮጵያን የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር አስተማማኝ መሰረት ዛሬ ላይ በመገንባት ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሕ እና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባት ሀገር መሆን ይኖርባታል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔና የቀደመ ሀገረ-መንግስት ባለቤት ብትሆንም አሰባሳቢ የሆነ ሀገራዊ ትርክት መገንባት ባለመቻሏ ትርክቶቿ በስርዓታት ፖለቲካ ፍላጎት ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ ሆነው በመቆየታቸው ስርዓታት በወጡ እና በወረዱ ቁጥር የሚገለባበጡ ነጠላ ትርክቶች ገዥ እየሆኑባት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ተግባሯን ያለ ተቃርኖ ለማስቀጠል አልታደለችም። በአንፃሩ የአሜሪካን፣ የቻይናን የፈረንሳይን ሀገራዊ ገዥ ትርክቶች የሚነግሩን ስርዓቶች ቢቀያየሩም ገዥ ሀገራዊ ትርክታቸው መሰረቱ ሀገረ-መንግስቱ ላይ በመገንባቱ በየወቅቱ የሚነሱ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች አይለዋወጥም።

ሀገራት ህዝባቸውን ከየት እንደተነሱና ወዴት እንደሚደርሱ በአሰባሳቢ ገዥ ትርክት በመገንባት ከአስተዳደራዊ ወሰናቸው አልፈው በዓለም ላይ የበላይነታቸውን ቅቡልነት አረጋግጠዋል።
የዓለማችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚዘውሩት የትርክት የበላይነት በያዙ ሀገራት እና ተቋማት ፍላጎት ነው። እነዚህ ሀገራትም ይሁኑ ተቋማት የትርክታቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሁሉንም ዓይነት ሀይል የማስጠበቂያ አማራጮችን ይጠቀማሉ።

ትርክት ቻይናን ከወደቀችበት አንስቶ የዓለም ተፆዕኖ ፈጣሪ ሀገር አድርጎ ከፊት አስቀምጧታል። ትርክት ሶሪያ ከዓለም ቀደምት ሀገርነት ወደ ፍርስራሽነት ቀይሩታል። ትርክት ኢትዮጵያን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲነገር የሚኖረውን በቅኝ-ገዥዎች ቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንዲትሰራ አስችሏታል።

ትርክት በህዝብ ውስጥ ለጋራ ዓላማና ራዕይ በአብሮነት በማነሳሳትን በአርበኝነት እንዲፈፅሙ የሚያንቀሳቅስ ታላቅ ሀይል መሆኑን በመረዳት ብልጽግና ፓርቲ በተራራቀ ዋልታ የሚገኙትን የሀገራችን ትርክቶች ወደ አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ለማምጣት በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረት ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችን ገዥ ትርክት እንዲሆን እየሰራ ይገኛል።

ብልፅግና በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችንን ያልፈውን የጉዞ ምዕራፍ ፣ የዛሬን ነባራዊ ሁኔታ እና የነገን መዳራሻ የምንመለከትበት የጋር አሰባሳቢ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ብሎ ያምናል።

በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት ገዥ ትርክት የትላንቱን ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ መሰረት አድርጎ የዛሬውን አስተሳስሮ ነገን ማመልከት የሚችል የህዝባችንን ዋና ዋና የጋራ እሴቶችን፣ ፍላጎቶችንና ግቦችን የሚያሳካና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ያደርጋል።

ፓርቲያችን ህዝባችን የጋራ ታሪክ ያለው፣ ብዙ ትላንቶችን በጋራ የተሻገረ አሁን ስንቅ ልናደርጋቸው የሚገቡ አያሌ ታሪኮችን እንዳሉት ያምናል።

በዚሁ አግባብ ብልፅግና በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ አማካይነት ነባር የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት፣ ታሪካዊ እሴቶችን አውጥቶ በማበልፅግ እና በማህበራዊ ካፒታላችንን በመጠቀምና በእነዚህ ላይ እሴቶችን በመጨመር ለነገ ብልጽግናችን በሚሆን መንገድ ማልማት በሰፊው ቀጥሏል።

ከትላንት የተሻለ ሀገራችንንና ህዝቡቿን የሚጠቅም ታሪክ እንድሰራ፣ የትውልዶችን ድካም በማረም ለትወልድ የበለፅገች ሀገር ለማስረከብ እንትጋ። ስለዚህ ትርክታችን ያለፈውን ብቻ ሳይሆን የዛሬን ዕድል እና የገነን ተስፋ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ቀያቸው እንዲመለሱ እና ዘላቂ መኖሪያ እንዲያገኙ ለማድረግ ተችሏል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባጋጠመው ግጭት፤ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች አሉ። እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እየሠራን ነው። የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በጋራ ሠርተው ብዙዎችን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርገዋል። በዚህ ሂደት በማኅበረሰቡ ዘንድ ወትሮም የነበረውን መተሳሰብ እና ጥብቅ ትሥሥር ለማየት ተችሏል። የተፈናቀሉ ጎረቤቶቻቸው እንዲመለሱ በየአካባቢው ከፍተኛ ፍላጎት አለ። ለሚመለሱት ተፈናቃዮች የየአካባቢው ማኅበረሰብ የሚያደርገው አቀባበል ልብ የሚጠግን ነው። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለምሳሌ በራያ እና አላማጣ አካባቢ ከተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥትን ሳይጠብቁ በማኅበረሰባዊ መተሳሰብ ብቻ በርካታዎች ወደ ቤታቸው ገብተዋል።

በዚህ ሂደት የተፈናቃዮችን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ሊጠቀሙ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ታይቷል። ተፈናቃዮች ከተመለሱ የልመናና፣ የተቃውሞ አጀንዳችን ይከስራል ብለው ይፈራሉ። እነዚህ ኃይሎች ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ፕሮፖጋንዳ እና ማስፈራሪያ ይደረድራሉ። አንዳንዴም በኃይል ጭምር የተፈናቃዮችን መመለስ ለማሰናከል ይቃጣቸዋል። መንግሥት ካለበት የሞራል እና የሕግ ኃላፊነት የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸውና ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ይቀጥላል። ከክልሎች ጋር የተጀመረው ሥራም ይጠናከራል።

ሰላምና ጸጥታን ለማደፍረስ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች እንዳይመለሱ ለማድረግና የልማት ተግባራትን ለማሰናከል አንዱ የመዋጊያ መሣሪያ የተዛባ፣ የተሳሳተና የተመረዘ መረጃን ማሠራጨት ነው። እንደሚታወቀው የመገናኛ ቴክኖሎጂ ዕድገት ዕድልም፣ አደጋም ይዞ መጥቷል። በዚህ ዘመነ መረብ ሽኩቻ እና ፉክክር ይበዛል። ነባር ተቋማት እና ሥርዓቶች በእጅጉ ፈተና ላይ ይወድቃሉ። በዚህ ዐውድ ውስጥ ሀገራት ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር ያለ ይሉኝታ እና ያለ ብዙ ልጓም የቻሉትን ሁሉ ያደርጋሉ።

በዚህ ወቅት ሁኔታውን በአግባቡ በመረዳት፣ ይሄንን ማዕበል እና ወጀብ እንዴት ማለፍ አለብን የሚለውን በጥንቃቄ ተልመን ካልተንቀሳቀስን አደጋው ከባድ ነው። በዚህ ረገድ ውጤታማ ለመሆን የውስጥ አንድነት እጅግ ወሳኝ ነው። እንደ ኢትዮጵያ ያለ ትልቅ ሀገር የውስጥ አንድነት ካለው ነጥሮ ይወጣል። እንደ ሀገር እና እንደ ሕዝብ ለአንድ ዓላማ በጋራ ከተሰለፍን ወቅቱ ሀገራችንን ከፍ ለማድረግ የራሱን በጎ አጋጣሚዎች ይዞ ይመጣል። ከተከፋፈልን ደግሞ የሀገር ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል። ስለዚህም የሚመጡ መረጃዎችን መምረጥ፣ መመዘንና ማንጠር አስፈላጊ ነው። በምድር ያሸነፍናቸው ጠላቶቻችን በአየር እንዲመጡ መፍቀድ የለብንም።

እነዚህን ሁሉ የምናከናውነው መጀመሪያ ዘላቂ ሰላም፤ በዘላቂ ሰላም በኩልም ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ነው። እንደ መንግሥት ግባችን በአቋራጭ መንገድ፣ ከላይ ከላይ በሆነ እድሳት የሚመጣ ጊዜያዊ ጸጥታ አይደለም። ዘላቂ ሰላም ነው። ዘላቂ ሰላም የጦርነት አለመኖር ብቻ አይደለም። በመርሕ እና በሥርዓት ላይ የተመሠረተ፣ በቀላሉ የማይናወጥ ሰላም ነው። ግጭትን፣ እና አለመግባባትን በሰላማዊ እና በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዐቅም እና ሥርዓት መኖር ነው። በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በመግባባት፣ ያለፈን ቁርሾ እና የታሪክ ጠባሳን አልፎ ወደፊት ለመሄድ መቻል ነው።

ይሄንን ዘላቂ ሰላምና ዘላቂ ብልጽግና ለማምጣት አዲስ የፖለቲካ ባህል የግድ ነው። ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክር፣ የሽግግር ፍትሕ እና የተሐድሶ ተግባራት የዚህ ማከናወኛ ዋነኞቹ መሣሪያዎች ናቸው። ማንም እንደሚያውቀው አካታች የሆነ መንግሥታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ፈር ቀዳጅ እየሆንን ነው። ይህ ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ግን የመንግሥት ተግባር ብቻውን በቂ አይሆንም። ገዢው ፓርቲ አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስተዋወቅ - አብረን እንሥራ፣ እንምከር፣ በጋራ ለሀገራችን ጉዳዮች መፍትሔ እንፈልግ እያለ ነው። አንዳንዶች ደግሞ በድሮ በሬ እያረሱ በጉልበት፣ በኃይልና በጠመንጃ መንግሥትን ጥለን ሥልጣን ጠቅልለን ካልወሰድን እያሉ ናቸው። እንደዚህ በተቃራኒ መንገዶች ተጉዘን የተጀመሩት ጥረቶቻችን ሊሳኩ አይችሉም። የ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ባህልን ይዞ በ22ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሄድ ርግማን እንጂ ለውጥ አያመጣም።

ጦርነት ሁላችንንም ያከስራል። ሰላም ሁላችንንም አትራፊ ያደርጋል። እኛ ከአባቶቻችን ስለጦርነት እየሰማን አደግን፤ ይበቃናል። በእኛ ትውልድ እንኳን ሁለትና ሦስት ከባድ ጦርነቶች አለፉ። ለቀጣይ ትውልድ ግን ብልጽግናን እንጂ ቁስልን ማውረስ የለብንም። የኢትዮጵያን ዘመናዊ የፖለቲካ ቅኝት ለሃምሳ ዓመት የበየነው የ1966ቱ አብዮት ከተከሠተ ግማሽ ምእተ ዓመት ሆኖታል። አዙሪቱ ያልለቀቃቸው ግን አሁንም አሉ። ካለፈው ተምረን፣ የራሳችንን እና የዘመናችንን ዐውድ ተገንዝበን፣ በራሳችን ቅኝት እና አጀንዳ ወደፊት ልንራመድ ይገባል። የዚህ ትውልድ የሃምሳ ዓመት አጀንዳ ዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ነውና።

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት
ሚያዚያ 16፣ 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣

ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትነት ታሪኳ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን፣ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ፣ በንግግር፣ በውይይት እና በሕጋዊ አግባብ የመፍታት ልምምድ የላትም። እንደ አለመታደል ሆኖ ፖለቲካችን የዜሮ ድምር ፖለቲካ ነው። በሀገራችን የተለመደው በጉልበት አሸንፎ ሥልጣን የያዘ ኃይል፣ በጉልበት ተሸንፎ ሥልጣን እስኪለቅ ድረስ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚቆጣጠርበት እና የፈቀደውን የሚያደርግበት የፖለቲካ ባህል ነው።

የለውጡ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጣው በጉልበት አይደለም። ይሄም አዲስ የፖለቲካ ባህል ነው። ይሄን አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ የሚያጸና ሌላ ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሕዝብ ይሁንታ አግኝቶ መንግሥት በመመሥረት አሳይቷል። ከዚህም በመሻገር ልዩ ልዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላትን በመንግሥት ኃላፊነት በመመደብ፣ ኢትዮጵያ የጋራ ቤት መሆንዋን አስመስክሯል።

ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር ብቻውን ግብ አይደለም። ሌሎች ግቦችን ለማሳካት መሣሪያ እንጂ። የኢትዮጵያ ችግር የአሁኑን አካሄድ በማስተካከል ብቻ አይፈታም። በታሪክ ውስጥ የወረስናቸውን ስብራቶች መጠገንም የግድ ይለናል። እነዚህን የታሪክ ስብራቶች ለመጠገን ሦስት ዓይነት መፍትሔዎች ተቀምጠዋል። ነባሩን ፖለቲካዊ ችግር በሀገራዊ ምክክር መፍታት፤ የቅርብ ዘመናችንን የፖለቲካ ችግር ደግሞ በሽግግር ፍትሕ እና በተሐድሶ ማረም።

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንድ መንግሥት በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን ቢይዝም እንኳን ብቻውን ሊወስናቸው የማይገቡ፣ ሀገራዊ እና አካታች ምክክር የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉ። ይሄ ድምጽ መሰማት ከጀመረ ግማሽ ምእተ ዓመት እየዘለቀው ነው። የለውጡ መንግሥት እስከመጣበት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ግን ሰሚ አላገኘም ነበር። የለውጡ መንግሥት ሐሳቡን መቀበል ብቻ ሳይሆን ይሄንን የሚያሣልጥ ገለልተኛ ተቋምም አቋቁሟል።

በዚህ ተቋም ውስጥ በኃላፊነት የተሰየሙት ክፍተኛ ልምድ እና ብቃት ያላቸው ገለልተኛ ኮሚሽነሮች ናቸው። እነዚህ ኮሚሽነሮች አካታች ሀገራዊ ምክክሩን የማከናወን ሰፊ ሥልጣን በሕግ ተሰጥቷቸዋል። በዚሁ መሠረት ባለ ድርሻ አካላትን በማማከር ሂደቱ ምን መምሰል አለበት የሚለውን ዝርዝር አካሄድ እና አሠራሩን ነድፈዋል። በአሁኑ ወቅት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በነደፈው አካሄድ መሠረት በ10 ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ከየወረዳው በምክክሩ ሂደት የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራ አጠናቋል። በእያንዳንዱ ክልል እጅግ ጥብቅ እና አድካሚ የሆነ ሥራ ተከናውኗል። ማኅበረሰቡን ከታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ጀምሮ አሳትፏል። በዚህም በምክክሩ አካሄድ የሚሳተፉ ዜጎች ተለይተዋል። ከ679 ወረዳዎች፣ እስካሁን 12,294 ተሳታፊዎች ተለይተዋል።

ይሄ አካሄድ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ሕዝብ ማዕከል ያደረገ ነው። አጀንዳዎች እና የመፍትሔ ሐሳቦች ከላይ ወደ ታች ብቻ ሳይሆን ከማኅበረሰቡም ፈልቀው፣ በውይይት ዳብረው ወደ መሐል የሚመጡበት አካሄድ ነው። በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ የሚደረጉ የምክክር መድረኮችን ማካሄድ እንደሚጀምር ይጠበቃል። እንዲሁም የተሳታፊ ልየታ ባልተደረገባቸው ሁለት ክልሎች ላይ የተሳታፊዎች ልየታ በቅርቡ ይጠናቀቃል። በጉጉት የሚጠበቀው አካታች ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተስፋ ይደረጋል።

ይሄንን በትውልድ መካከል አንዴ የሚገኝ ዕድል ሳናባክን፤ እያቃናንና እየደገፍን፣ ለኢትዮጵያ ነባር ችግሮች መፍትሔ አዋላጅ እንዲሆን፣ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል። ዕድሎችን በሰበብ አስባቡ እያባከንን፣ ራሳችንን በችግር አዙሪት የማክረም አካሄድ ማብቃት አለበት።

ሁለተኛው የሽግግር ፍትሕ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በደል፣ ግፍ እና መሠረታዊ የመብት ጥሰቶች ተከሥተዋል። ይህ በሌሎች ሀገራት ታሪክም የሚታይ ክሥተት ነው። እስከዛሬ ባለው አካሄዳችን በጉልበት አሸናፊ ሆኖ ሥልጣን የያዘው አካል፣ ሌሎችን በዳይ እና አጥፊ አድርጎ ይኮንናል፤ ይቀጣል። ይህ አካሄድ ግን ፍትሕን አያሰፍንም። እልህን፣ ቁጭትን እና የበቀል ጥማትን ያገነግናል እንጂ። የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት፣ የተበዳይነት እና የብሶት ትርክት በሀገራችን ዋነኛው የፖለቲካ ማጠንጠኛ የሆነበት አንዱ ምክንያትም ይሄው ነው። ይሄንን የበዳይ ተበዳይ አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ስልት ነው። ስለዚህም የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት የፖሊሲ ማሕቀፍ ጸድቋል።

የፖሊሲው ዝግጅት የሚመለከታቸውን አካላት ያሳተፈ፣ ዓለም አቀፍ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው። በቅድመ ፖሊሲ ማርቀቅ ሂደቱ ብቻ 60 የክልል እና 20 ሀገራዊ የግብአት ማሰባሰቢያ መድረኮች ተካሂደውበታል። የፖሊሲው ዓላማ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሰላምን፣ ዕርቅን፣ የሕግ የበላይነትን፣ ፍትሕን እና ዴሞክራሲን ማረጋገጥ ነው። ይሄንን ዓላማ ለማሳካት እንደ አግባብነቱ የወንጀል ምርመራ እና ክስ፣ እውነት ማፈላለግ፣ ዕርቅ፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ምሕረት፣ ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ እንደ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች በሀገራችን ተግባራዊ ይደረጋሉ።

እንደሚታወቀው በሀገራችን ከመንግሥት ውጭ የሚኖር የታጠቀን ኃይል ሕገ መንግሥታችን አይፈቅድም። የመንግሥትም አንዱ መብት በብቸኝነት ኃይልን መጠቀም ነው። ነገር ግን በሀገራችን በወረስነው የፖለቲካ ስብራት የተነሣ የታጠቁ ኃይሎች ተፈጥረዋል። ሰላማችንን የጸና ለማድረግ፣ እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ ፈትተው፣ የተሐድሶ ሂደት ውስጥ መቀላቀል አለባቸው። የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውንም በሀገራዊ ምክክር ሂደት በመሳተፍ መፍታት ይችላሉ። ለዚህ የሚሆን የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ዓላማውም መሣሪያ ማስፈታት፣ የትጥቅ ቡድኖችን ሰላማዊ ማድረግና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀላቀል ናቸው። ይሄንን የተሐድሶ ሥራ በማሳካት ፖለቲካችን ከግንባር ወደ ጠረጴዛ፣ ከጫካ ወደ አዳራሽ እንዲመለስ ማድረግ አለብን። እነዚህን ስልቶች በሚገባ ተግባራዊ በማድረግ፣ ከበዳይ ተበዳይ አዙሪት ልንወጣ ያስፈልጋል። በምሕረት፣ በይቅርታ፣ በካሣና፣ በፍትሕ ታክመን ወደፊት መጓዝ መቻል አለብን። ለዚህ ስኬትም ኢትዮጵያውያን ሁሉ በንቃትና በብቃት ልንሳተፍ ይገባናል። መንግሥትም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አተገባበርን ከሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጋር የተናበበ እና የሚመጋገብ እንዲሆን በማድረግ ኃላፊነቱን ይወጣል።

ነባር ሀገራዊ ችግሮቻችንን በሀገራዊ ምክከር እና በሽግግር ፍትሕ እያረምን የገጠሙን የግጭትና የጦርነት ፈተናዎች ለመሻገር ደግሞ ሰላማዊ የፖለቲካ አካሄዶችን ተመራጭ ማድረግ አለብን። ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ስምምነት ለመፍታት የተፈለገውም ለዚህ ዓላማ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ በተለያዩ ወቅቶች የእርስ በርስ ግጭቶች እና ጦርነቶች በተደጋጋሚ ተከሥተዋል። በእነዚህ ጦርነቶች እንደ ሀገር ከባድ ኪሣራ ደርሶብናል። የዚህም ምክንያቱ ግጭቶችን በንግግር እና በስምምነት የመፍታት የፖለቲካ ልምምድ ብዙም ስለሌለን ነው። የለመድነው በጠላታችን መቃብር ላይ ሐውልት መገንባት ነው።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በዛሬው እለት የቂርቆስ ክፍለከተማ የልማት ተነሺዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በመገኘት 4ኛ ዙር የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ አውጥተዋል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ታይዋን 17 ሰዎችን ለህልፈት ከዳረገው ርዕደ መሬት አደጋ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ በድጋሚ ለሰዓታት ከባድ በሆነ ተከታታይ ርዕደ መሬት መመታቷ ተገልጿል፡፡

በመጀመሪያ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 5 ሆኖ የተመዘገበ ሰኞ ምሽት በደሴቲቱ ምስራቃዊ ሁዋሊን ግዛት የደረሰውን ርዕደ መሬት ተከትሎ አነስተኛ መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተመላክቷል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ከተወሰኑ ሰዓታት በኋላ በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 0 እንዲሁም 6 ነጥብ 3 ሆነው የተመዘገቡ የርዕደ መሬት አደጋዎች መከሰታቸውን የደሴቲቱ የአየር ሁኔታ አስተዳደር የርዕደ መሬት ማዕከል አስታውቋል፡፡

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 3 በደረሰው ርዕደ መሬት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሕንፃዎችም ከዛሬ ጠዋቱ ክሰተት በኋላ በከፊል መውደቃቸውን የሁዋሊን ግዛት ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የማዕከላዊ የአየር ንብረት አስተዳደር የርዕደ መሬት ማዕከል በአደጋው የተጎዱ ሰዎች እንደሌሉና በሁዋሊን ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ትዕዛዝ እንደተላለፈ ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

ቀደም ሲል የደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ በታይዋን ከ25 ዓመታት በፊት በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 ሆኖ ከተመዘገበውና 2 ሺህ 400 ሰዎችን ለህልፈት በመዳረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ህንፃዎችን ካወደመው ርዕደ መሬት በኋላ ከባዱ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለሚገጥሙን የውስጥና የውጪ ፈተናዎች ሁሉ የመፍትሄ መንገድ ነው!!

የሀገራችን ህዝብ አንድነቱን በማጠናከር ከውስጥም ከውጪም አብሮ ሲሰራ ማንኛውንም ችግር መሻገር እንደሚችል በአንድነታችን የተመዘገቡት ስኬቶች እና ትልቅ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉ ማሳያዎች ናቸው።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ አካላት አላማቸው ሊሳካ የሚችለው የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ሲዳከም ብቻ እንደሆነ ይረዳሉ። ለዚህም ህዝብ እንዲከፋፈል የሚያደርጓቸውን የሀሰት አጀንዳዎችን በማሰራጨት ሰላም ለማደፍረስ ይጥራሉ።

ሀገራዊ አንድነታችን ህብረብሄራዊነት ብዝሃነትን ያረጋገጠ ሀገራዊ አንድነት ጠንካራ ስርዓት የገነባች እና ዘላቂ ልማትን ያረጋገጠች ሀገር ለመፍጠር ትልቅ ሚና ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ሲጠናከርና በውስጡ መረጋጋት ሲሰፍን ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር መሆን እንደምትችል ከለውጡ በኋላ የተገኙ ውጤቶች ትልቅ ማሳያ ናቸው።

ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ለሁሉም የምትመች፣ ህብረ ብሔራዊነት እና ወንድማማችነት የምታስተናግድ ሀገር እንድትሆን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

የሚያጋጥሙንን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እና ተግዳሮቶችን በመቅረፍ በዘላቂነት ለመፍታት አንድነትን ማጠናከር እንደ ህዝብና እንደ ሀገር ሰላምና መረጋጋትን እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማስፈን ትልቅ ሚና ይጫወታል። ስለሆነም በአንድ በኩል የሚገጥሙንን ፈተናዎች በመመከት፣ በሌላ በኩል ሀገሪቱን ለትውልድ የማሻገር ኃላፊነት ለመወጣት ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች አንድነታችንን በማጠናከር ጠንካራ ሀገረ መንግስት መፍጠር እና መገንባት የሁላችንም ድረሻ ሊሆን ይገባል።

በህብረ ብሄራዊነት የደመቀች ሀገር ሰላም ፍትህ ዲሞክራሲ የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ተግባር በህብረት መስራት ይጠበቅብናል!
https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በመጪው ክረምት ለ50 ሺህ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል ።

ስልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍና የመምህራን ብቃትን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ይሰጣል ነው የተባለው።

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አመራር መሪ ስራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ(ዶ/ር) መምህራኑ የሚሰለጥኑት በሚያስተምሩት ትምህርትና በማስተማሪያ ዘዴዎች መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል ።

ለ42 ሺህ መምህራን 120 ሰዓት፤ ለ8 ሺህ የትምህርት አመራሮች ደግሞ የ60 ሰዓት ስልጠና እንደሚሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን ÷ሲያጠናቅቁም ፈተና እንደሚወስዱ ነው ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡

ስልጠናው በመምህራንና የትምህርት አመራሩ ላይ ያለውን የማስተማር ዘዴዎችና የእውቀት ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

https://twitter.com/ProsperityKera

Читать полностью…
Subscribe to a channel