prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1397

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመደመር የኢኮኖሚ ገጽ የባለፉት ዓመታት የሀገራችንን የኢኮኖሚ ድል ጠብቆ የማስፋት ዓላማ አለው።

የሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት በዋናነት በብድር ላይ የተመሠረተና በከፍተኛ መንግሥታዊ ወጭ በተስፋፋ መሠረተ ልማት አማካኝነት የመጣ ነው።

የተመዘገበውን የኢኮኖሚ እድገት በሌላ አማራጭ የኢኮኖሚ ምሰሶ ላይ እድገቱ ወደኋላ ሳይመለስ ማስቀጠል ያስፈልጋል።

ይህም እድገት በተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ድባብ ውስጥ መሆን ይኖርበታል። እድገቱ አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር አለበት።

እነዚህን ግቦች ለማሳካት የኢኮኖሚውን ምርታማነትንና ተወዳዳሪነት ማጎልበት አማራጭ የለውም። በመሆኑም ልማታዊ መንግሥትና ገበያን መሠረት ያደረጉ ሁሉንም ተዋንያን የሚያሳትፍ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል።

ይህ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ ደግሞ ድምር ሀገራዊ ፍላጎት ከማሳደግ መሳ ለመሳ አቅርቦትን በማስፋፋት ሚዛኑን የጠበቀ እድገትን፣ ልማትን እና ብልጽግናን ደረጃ በደረጃ የማረጋገጥ የመደመር ትልም ነው።

መደመር ገፅ 238

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሪፎርሙ ልክ እንደ ኮሶ መድሀኒት ነው ለትንሽ ጊዜ መሮን መዳን አለብን!!

#ታላቁ_ኢኮኖሚክ_ሪፎርም
#ዐብይ_አህመድ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የቂርቆስ ክ/ከተማ ሴቶች ሊግ "በጎነት ለእህትማማችነት ለትውልድ ግንባታና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ - ግብር አካል የሆነ የደም ልገሳ አከናወነ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የቂርቆስ ክ/ከተማ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሃዊ ጌታቸውን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የሊጉ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ዛሬ በጠዋት ከ 200 በላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሴቶች ሊግ አባላት በተሳተፉበት የደም ልገሳ ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ደም ዩኒት የተሰበሰበ ሲሆን፣ በዚህ ስኬታማ ስራ ላይ ለተሳተፉ አባላት የሊጉ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ሐዊ ጌታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ከአመት በፊት በረሃብ የሚታወቀው የቦረና ከባቢ ዘንድሮ በስንዴ ምርት ተትረፍርፎ ማየት፣ ተስፋችን የሚጨበጥ፣ ከሰራን ሀገራችንን መለወጥና የምግብ ሉአላዊነት ማረጋገጥ የምንችል መሆኑን ያመለክታል።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ ጠዋት የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ። ውይይታችን ተጠናክረው በቀጠሉት የሁለቱ ሀገሮቻችን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ነበር።

@AbiyAhmedAli (phd)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የአፍሪካ ኩራት‼️

የአፍሪካ መዳረሻዎች 👆🇪🇹👆

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የዓለም ባንክ ይፋ ያደረገው የእርዳታ፣ የዕዳ ሽግሽግ እና የረጅም ጊዜ ብድር በጥቅሉ 16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው።

በዚህ መሰረት፥

• 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ስጦታ (grant)

• 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ እንዲራዘም፤

• 320 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር (IFC)

• 1.15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ

• 6 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት (ሁለት ቢሊዮን በየዓመቱ ) ለበጀት ድጎማ

• 2.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን በቀጥታ ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላርን ጨምሮ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂.6 ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ሰበር

የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን መገደሉ ተሰማ

የሃማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን መገደሉን የፍልስጤም ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሃማስ ሃኒህ የተገደለው በቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ በተፈጸመ ተንኮለኛ የጽዮናውያን ወረራ ነው ሲል የፍልስጤም አስተዳደር ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሃኒዬህ ከአንድ ጠባቂው ጋር መገደሉን አረጋግጧል ሲል የኢራን መንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

እስማኤል ሃንዬ የጋዛ ሰርጥን የሚገዛው የፍልስጤም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ በ2017 እንዲመራ ተመርጧል።በጋዛ ሻቲ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የእስራኤል መንግስት ከተመሰረተ በኋላ ከአስቃላን ከተማ ሸሽተው ከነበሩ ወላጆቹ በ1948 የተወለደው ሀኒዬ በጋዛ አል-አዝሃር ኢስላሚክ ዩኒቨርሲቲ በአረብኛ ስነ-ጽሁፍ ተመርቋል።እ.ኤ.አ. በ 1983 በዩኒቨርሲቲ ውስጥ እያለ ለሃማስ ቀዳሚ የሆነውን እንቅስቃሴ በመቀላቀል ለሀማስ መስራች ሟቹ ሼክ አህመድ ያሲን የቅርብ ረዳት በመሆን በሃማስ ውስጥ ያለውን ደረጃ አሳድጓል።

ሃኒየህ በርካታ የግድያ ሙከራዎችን ከዚህ ቀደም ያመለጠ ሲሆን በእስራኤል ባለስልጣናት ብዙ ጊዜ ታስሮ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ኖሯል። በጥር ወር መጀመሪያ ላይ በሰሜናዊ ጋዛ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ሶስት ልጆቹ ተገድለዋል።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ቁልፍ ዓላማዎችና ግቦች ...

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሉሲ(ድንቅነሽ) ግኝት የሳይንሱን ማኅበረሰብ ብሎም መላውን አለም ስለምድራችን እና ስላሳለፈችው የሕይወት መልክ ለማወቅ ያስቻለ መሥራች ሁነት ነበር። ግኝቱ ብዙ ጥያቄዎችን የመለሰ ብዙ አዳዲስ ጥያቄዎችን ያነሳሳ ሲሆን በጥያቄዎቹም ለብዙ ምርምሮች መነሻ መሆኑ እስከዛሬ እንደቀጠለ ነው።
Lucy’s discovery, was a groundbreaking event that captivated both the scientific community and the world at large, providing invaluable insights into the evolution of life on Earth. It answered many questions while also prompting new inquiries that continue to drive research and exploration.

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"Seenessa biyyaalessummaa guddummaa Itoophiyaaf"

Dameen Sab-qunnamtii Ummataa fi Idil-addunyaa Paartii Badhaadhinaa, Waajjira Paartii Badhaadhinaa Damee Finfinnee waliin ta'uun leenjii  "Seenessa biyyaalessummaa guddummaa Itoophiyaaf" jedhuun qopheesse irratti sirni muuxxannoo wal-jijjiirraa gaggeeffame.

Leenjii guyyaa har’aatiin Waajjira Paartii Badhaadhinaa Damee Oromiyaatti hojileen muuxxannoo gaarii Damee Sab Qunnamtii hirmaattotaaf dhiyaatanii jiru.

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ ወደ ተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ ገባች!
@AbiyAhmedAli 💪💪💪

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በሶማሌ ክልል 👌

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ለሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ቤተሰብና ለመላው ዊቢውልድ ግሩፕ መጽናናትን ተመኝተዋል። 

ሳሊኒ ለኢትዮጵያ የነበራቸው ፍቅር በተግባር የተገለጠ እንደሆነ ጠቅሰው በሀገር ግንባታ ሂደት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ማከናወናቸውንም አንስተዋል።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የገቢ አፈፃፀም በተመለከተ:-

በ2016 በጀት ዓመት 151 ነጥብ 68 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ146 ነጥብ 84 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል፤ አፈፃፀሙ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ44.16% ዕድገት አሳይቷል።

#የከንቲባ_አዳነች_አቤቤ_ማብራርያ
#aa_prosperity

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለሕዝብ መዝናኛ አገልግሎት እንዲውል የተገነባውን ፋውንቴይን መረቁ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮስኮ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ለሕዝብ መዝናኛ አገልግሎት እንዲውል የገነባውን ፋውንቴይን መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እንደ ከተማ አስተዳደር ከተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተጨማሪ ስራው በሌሎች የግል እና የመንግስት ተቋማት በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል::

ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ አካባቢ በብራዘርስ ኮንስትራክሽን እና ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ስር በአሰር ኮንስትራክሽን በተመሳሳይ ለሕዝብ መዝናኛ እንዲውሉ በራሳቸዉ ወጪ የገነቡልንን ፋውንቴኖችን ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረጋችን ይታወሳል ሲሉም ጠቁመዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በእነዚህ ስራዎች ላይ ለተሳተፉት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮስኮ)፣ ብራዘርስ ኮንስትራክሽን እና አሰር ኮንስትራክሽን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሌሎች የግል እና የመንግስት ተቋማትም ከዚህ ልምድ በመውሰድ አካባቢያቸውን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል::

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዘላቂ እና የተረጋጋ የኢኮኖሚ ስርዓት ለመፍጠር ጉልህ ሚና አለው።

ክብርት ከንቲባ አዴ @AdanechAbiebie
🙏🙏🙏🙏🙏

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እሁድ ሐምሌ 28 በሱስ የተጠቁ ወገኖችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመው የጎዳና ላይ ሩጫ ይደረጋል!

#ሐምሌ_28

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን ጋር ያደረጉት ውይይት
🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ መልዕክት

የአዲስ አበባ ለውጥ ሃብትን በመቆጠብ፣ ለተገቢው የጋራ ልማት ብቻ በማዋልና ለዜጎች ትኩረት በመስጠት እየተተገበረ ያለ፣ ፈጠራና ፍጥነት ላይ የተመሰረተ፣ ቀጣይነት ያለው ነው።

ስራው የከተማችን ነዋሪዎች ትብብር ጎልቶ የታየበት እና ከከተማ እስከ ፌደራል ያሉ የመሰረተ ልማት መስሪያ ቤቶች ቅንጅት የተረጋገጠበት ነው።

በመሆኑም፣ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንጻዎቻችሁን በከተማችን ስታንዳርድና ዲዛይን መሰረት ያሳመራችሁ እንዲሁም ለእግረኛ መተላለፊያ እንዲሆን ምቹ በማድረግ የሰራችሁ የህንጻ ባለቤቶች፣ ከሁሉም በላይ የመገልገያ ቦታዎችን ክፍት በማድረግ ከተማችን 24 ሰዓት የማትተኛ እና የምትንቀሳቀስ እንድትሆን አገልግሎት አሰጣጣችሁን የለወጣችሁ፣ በአጠቃላይ የኮሪደር ልማቱን ዓላማ ያሳካችሁ የከተማችን ነዋሪዎችን ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ስንተባበር እንዲህ አይነት ፈጣን፣ ሰፊ ፣ ጥራትና ቀጣይነት ያለው ለውጥ ማስመዝገብ እንችላለን። አሁንም ይህን ስራ በሌሎች የከተማችን አካባቢዎችም ስለምናስፋፋው በላቀ ትብብር እና በቅርበት እጅ ለእጅ ተያያዘን መስራታችንን እንድንቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ሐምሌ 26 ቀነ 2016 ዓም

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በምስሎቹ የምንመለከተው በመልማት ላይ ያለ የሻይ ተክል ማሳ ነው። በቡና ያሳካነውን አመርቂ ድል በሻይ ምርትም እንደግመዋለን።

These images show a tea plantation in progress. We aim to replicate the success we've had with coffee productivity in our tea production.

Via Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ የመጨረሻ ቀን ነው

የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል ዛሬ ይጠናቀቃል።

በመሆኑም ዛሬን ብቻ በመጠቀም በአቅራቢያዎ በሚገኝ ወረዳ ሄደው በመመዝገብ ከቅጣት ይዳኑ ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ነገ ይጠናቀቃል‼️

የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል‼️

የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ ነገ እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

በመሆኑም ተመዝጋቢዎች ዛሬን እና ነገን በመጠቀም በአቅራቢያቸው በሚገኝ ወረዳ በመመዝገብ ከቅጣት እንዲድኑ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተመንግስት እድሳት ተጀምሯል። በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይም ይገኛል። በአጭር ግዜ ውስጥ ፋሲልን ወደ ቀደመ ግርማ ሞገሱ እንመልሰዋለን።

Magaalaa Gondaritti haaromsuun Masaraa Mootummaa Faasiil jalqabameera. Sadarkaa gaariirrattis argama. Yeroo gabaabaa keessatti Faasiiliin gara surraafi ulfinasaa duraaniitti ni deebisna.

Renovation of Fasil Ghebbi has commenced in Gonder city and is progressing very well. In no time, Fasil will be elevated to its former glory.

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በ2017 በጀት ዓመት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 74 ሚሊዮን 661 ሺህ 037 ወደ 80 ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል። በዚህም ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሠራል።

በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ የገጠር ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 54 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ወደ 64 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል ያሉት ኢንጅነር ሃብታሙ (ዶ/ር)፤ በ2016 በጀት ዓመት ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን የኅብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ በማድረግ አጠቃላይ የገጠር መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 52 ነጥብ አራት ሚሊዮን ወደ 54 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ የከተማ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 19 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ወደ 20 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ለማሳደግ መታቀዱንም ገልጸዋል።

እንደ ኢንጅነር ሃብታሙ (ዶ/ር) ገለፃ፤ ሀገራዊ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በስታንዳርድ ደረጃ ከነበረበት 69 ነጥብ አምስት በመቶ ወደ 78 ነጥብ ሁለት በመቶ ለማሳደግ ይሠራል። የገጠር መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በስታንዳርድ አገልግሎት ደረጃ ከነበረበት 66 ነጥብ ሁለት በመቶ ወደ 77 ነጥብ አምስት በመቶ ለማሳደግ ታቅዷል።

የከተማ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በስታንዳርድ አገልግሎት ደረጃ ከነበረበት 79 በመቶ ወደ 80 በመቶ ለማሳደግ እንደሚሠራም ገልጸዋል።

አዲስ ዘመን ሐምሌ 21 /2016 ዓ.ም

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የ4 ኪሎ የመሬት ውስጥ  እግረኛ መተላለፊያ መንገድ ግንባታ በማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡
               
በኮሪደር ልማት ሥራው ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የልማት ስራዎች መካከል የእግረኞች መተላለፊያ መንገድ ግንባታ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ዋና መንገድ በሚያቋርጡ እግረኞች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ አደጋ ስጋት በእጅጉ የሚቀንስና ደህንነትን የሚያስጠብቅ ነው።

ከዚሁ በተጨማሪ  በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚኖረውን የትራፊክ ፍሰት በማሳለጥ ረገድ የመሬት ውስጥ የእግረኞች መተላለፊያ መንገድ ግንባታ ጉልህ ሚና  ይኖረዋል፡፡

ይህ በአራት ኪሎ ትምህርት ሚኒስቴር ፊት ለፊት፤ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የመሬት ውስጥ  እግረኛ መተላለፊያ መንገድ ግንባታ ምቹና ዘመናዊ ሲሆን ፤ሰዎች በውስጡ ከመተላለፍ ባሻገር አረፍ ብለው ሻይ ቡና የሚሉበት እና ሌሎች ግብይቶችን ማካሄድ የሚያስችል  ሱቆች ግንባታን ያካተተ እና በአይነቱ ልዩ የሆነ መሰረተ ልማት ሲሆን፤ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የብርሃን እና የጨለማ ትንቅንቅ
#ኢትዮጵያ 🇪🇹 #Ethiopia
#አዲስአበባ #Addisababa
@AbiyAhmedAli
@AdanechAbiebie
@HItefa
💪💪💪💪💪💪💪💪

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

“ግድቤን በደጄ” ፕሮጀክት ዜጎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲያገኙ፣ ጽዱ ሀገርና አካባቢ እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ

የ"ግድቤን በደጄ"ፕሮጀክት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ቆላማ ፣ ከፊል ቆላማና ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች በስፋት ይተገበራል ብለዋል ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፡፡

ከ4 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚደርገው “ግድቤን በደጄ” ፕሮጀክት በ5 ቢሊየን ብር ወጭ ለ5 ዓመታት የሚተገበር ሲሆን በሀገሪቱ ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ከቧንቧ ውሃ በተጨማሪ የዝናብ ውሃን በማሰባሰብ ዜጎችን የንፁህ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

“ግድቤን በደጄ” በሱማሌ ክልል፤በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤በሀረሪ ክልል በሚገኙ የጤና ተቋማት ትምህርት ቤቶች ግንባታ መከናወኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በሌሉች ክልሎችም ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡

በውሃ ችግር ምክንያት የሚከሰቱ የመማር መስተማር ችግሮችን በመፍታት የተረጋጋ የመማር ማስተማር ስርዓት እንዲፈጠር ፤የወጣቶች ፤የሴቶች የስራ እድል ከማስፋት አኳያም ሆነ ለአካባቢው አርብቶ አደሮች ለከብቶቻቸው ያለድካም ውሃ እንዲያገኙ በማስቻል በውሃ ምክንያት የሚከሰት ግጭትንም እንደሚቀንስም ተነግሯል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ “ግድቤን በደጄ” ዜጎችን በመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በኢነርጂ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እና ጽዱ ሀገርና አካባቢ ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ይላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት አማካኝነት ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ በሀገሪቱ የተመረጡ አካባቢዎች 81 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል ብለዋል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት ያለውን የውሃ ችግር በመቀነስ የተቋማቱ አገልግሎት አሰጣጥ በውሃ እጥረት ምክንያት እንዳይስተጓጎል ማድረግ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡

ከመጠጥና ንጽህናን ከመጠበቅ ባለፈ የሚኖረውን ትርፍ ውሃ የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ምርታማነትን ለማሳደግም አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ የውሃ አማራጭ የሌላቸው፣ ዝናብ አጠር የሆኑና ችግሩ በስፋት የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች ቅድሚያ ይሰጣል ያሉት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በ5 ዓመቱ የፕሮጀክት ማስፋፋት ሂደት 4.8 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከ5ቢሊየን ብር በላይ ወጭ ይደረግበታል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ትምህርት ቤቶች ላይ ሲተገበር ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ከ2 እስከ 4 ሰዓት የሚሄዱበትን ድካም ከመቀነስ ባሻገር በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ ነው ብለዋል።

ይህ ብቻ አይደለም የ"ግድቤን በደጄ"ፕሮጀክት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ቆላማ ፣ ከፊል ቆላማና ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች በስፋት ይተገበራል ሲሉም ያክላሉ፡፡

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ የአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ሚኒስትር የሆኑትን ሚካኤል ማርቲን እና ልዑካን ቡድናቸውን አግኝቼ በርከት ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት በማድረጌ ደስ ብሎኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
#aa_prosperity

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ህዝቡ የሰላም ባለቤት እንዲሆን ከማድረግ አንፃር...!

"ሕዝባችን የሠላም ባለቤት በመሆኑ፡ በሕዝብ ለሕዝብ መከባበርና መቻቻል፣ በአብሮነት እሴት፣ በሠላም ግንባታ እና በግጭት አፈታት እንዲሁም በወንጀልና ደንብ መተላለፍ ቅድመ መከላከል ዙሪያ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል።

በሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጎልበት በየአካባቢው፣ በብሎክ፣ የማኅበረሰብ አቀፍ ምክክር መድረኮች እና የአካባቢን ፀጥታ በመጠበቅ፣ ለወንጀለኞች መደበቂያ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችንና የሥጋት ቦታዎችን ለይቶ መከላከል እንዲቻል በድግግሞሽ ከ6.3 ሚሊዮን የሚደርሱ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ ማረጋገጥ ተችሏል።

የወንጀል ድርጊቶችን በመቀነስ ረገድ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሃሰተኛ ሰነድ፣ ከከባድና ቀላል ወንጀል፣ የትምህርት ቤቶችን ደህንነት ከሚያውኩ ድርጊቶች፣ ከቤቲንግ ቤቶች፣ ከግጭቶች፣ ከኢኮኖሚ አሻጥርና ህገ ወጥ የንግድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ከሌሎች ሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት 22,251 የወንጀል ድርጊቶችን በመለየት፣ የመከላከል እና እርምጃ የመውሰድ ሥራ ተሰርቷል!"

#የከንቲባ_አዳነች_አቤቤ_ማብራርያ

Читать полностью…
Subscribe to a channel