የገባውን ቃል ለመፈፀም ያለ ዕረፍት ከመስራት ውጪ ለማይክሮ ሰኮንድ ተዘናግቶ አያውቅም ፡፡ እንዲህም ስለሆነ የሚገጥሙትን ጊዜያዊ ፈተናዎች በብቃትና በብልሀት በመለፍ በስኬት ጎዳና እየተጓዘ ነው፡፡
እናመሠግናለን @AbiyAhmedAli 🙏
መከላከያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ ኩራት ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለጠላቱ ስጋት ለህዝቡ ኩራት የሆነ ጀግና ሰራዊ ነው። ለዚያም ነው እንደአሸን የሚፈለፈሉ ሽፍታዎችን እያደነ ከጎራያቸው እንዳይወጣ እያደረገ ያኖረን!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የመደመር የኢኮኖሚ ገጽ የባለፉት ዓመታት የሀገራችንን የኢኮኖሚ ድል ጠብቆ የማስፋት ዓላማ አለው።
የሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት በዋናነት በብድር ላይ የተመሠረተና በከፍተኛ መንግሥታዊ ወጭ በተስፋፋ መሠረተ ልማት አማካኝነት የመጣ ነው።
የተመዘገበውን የኢኮኖሚ እድገት በሌላ አማራጭ የኢኮኖሚ ምሰሶ ላይ እድገቱ ወደኋላ ሳይመለስ ማስቀጠል ያስፈልጋል።
ይህም እድገት በተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ድባብ ውስጥ መሆን ይኖርበታል። እድገቱ አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር አለበት።
እነዚህን ግቦች ለማሳካት የኢኮኖሚውን ምርታማነትንና ተወዳዳሪነት ማጎልበት አማራጭ የለውም። በመሆኑም ልማታዊ መንግሥትና ገበያን መሠረት ያደረጉ ሁሉንም ተዋንያን የሚያሳትፍ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል።
ይህ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ ደግሞ ድምር ሀገራዊ ፍላጎት ከማሳደግ መሳ ለመሳ አቅርቦትን በማስፋፋት ሚዛኑን የጠበቀ እድገትን፣ ልማትን እና ብልጽግናን ደረጃ በደረጃ የማረጋገጥ የመደመር ትልም ነው።
መደመር ገፅ 238
ሪፎርሙ ልክ እንደ ኮሶ መድሀኒት ነው ለትንሽ ጊዜ መሮን መዳን አለብን!!
#ታላቁ_ኢኮኖሚክ_ሪፎርም
#ዐብይ_አህመድ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ
የቂርቆስ ክ/ከተማ ሴቶች ሊግ "በጎነት ለእህትማማችነት ለትውልድ ግንባታና ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ - ግብር አካል የሆነ የደም ልገሳ አከናወነ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የቂርቆስ ክ/ከተማ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሃዊ ጌታቸውን ጨምሮ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የሊጉ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ዛሬ በጠዋት ከ 200 በላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሴቶች ሊግ አባላት በተሳተፉበት የደም ልገሳ ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ደም ዩኒት የተሰበሰበ ሲሆን፣ በዚህ ስኬታማ ስራ ላይ ለተሳተፉ አባላት የሊጉ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ሐዊ ጌታቸው ምስጋና አቅርበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ከአመት በፊት በረሃብ የሚታወቀው የቦረና ከባቢ ዘንድሮ በስንዴ ምርት ተትረፍርፎ ማየት፣ ተስፋችን የሚጨበጥ፣ ከሰራን ሀገራችንን መለወጥና የምግብ ሉአላዊነት ማረጋገጥ የምንችል መሆኑን ያመለክታል።
ዛሬ ጠዋት የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ። ውይይታችን ተጠናክረው በቀጠሉት የሁለቱ ሀገሮቻችን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ነበር።
@AbiyAhmedAli (phd)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
የዓለም ባንክ ይፋ ያደረገው የእርዳታ፣ የዕዳ ሽግሽግ እና የረጅም ጊዜ ብድር በጥቅሉ 16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው።
በዚህ መሰረት፥
• 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ስጦታ (grant)
• 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ እንዲራዘም፤
• 320 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር (IFC)
• 1.15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
• 6 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት (ሁለት ቢሊዮን በየዓመቱ ) ለበጀት ድጎማ
• 2.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን በቀጥታ ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላርን ጨምሮ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂.6 ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች።
#ሰበር
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን መገደሉ ተሰማ
የሃማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬ በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን መገደሉን የፍልስጤም ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሃማስ ሃኒህ የተገደለው በቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ላይ በተፈጸመ ተንኮለኛ የጽዮናውያን ወረራ ነው ሲል የፍልስጤም አስተዳደር ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሃኒዬህ ከአንድ ጠባቂው ጋር መገደሉን አረጋግጧል ሲል የኢራን መንግስት ሚዲያ ዘግቧል።
እስማኤል ሃንዬ የጋዛ ሰርጥን የሚገዛው የፍልስጤም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ በ2017 እንዲመራ ተመርጧል።በጋዛ ሻቲ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የእስራኤል መንግስት ከተመሰረተ በኋላ ከአስቃላን ከተማ ሸሽተው ከነበሩ ወላጆቹ በ1948 የተወለደው ሀኒዬ በጋዛ አል-አዝሃር ኢስላሚክ ዩኒቨርሲቲ በአረብኛ ስነ-ጽሁፍ ተመርቋል።እ.ኤ.አ. በ 1983 በዩኒቨርሲቲ ውስጥ እያለ ለሃማስ ቀዳሚ የሆነውን እንቅስቃሴ በመቀላቀል ለሀማስ መስራች ሟቹ ሼክ አህመድ ያሲን የቅርብ ረዳት በመሆን በሃማስ ውስጥ ያለውን ደረጃ አሳድጓል።
ሃኒየህ በርካታ የግድያ ሙከራዎችን ከዚህ ቀደም ያመለጠ ሲሆን በእስራኤል ባለስልጣናት ብዙ ጊዜ ታስሮ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ኖሯል። በጥር ወር መጀመሪያ ላይ በሰሜናዊ ጋዛ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ሶስት ልጆቹ ተገድለዋል።
የሉሲ(ድንቅነሽ) ግኝት የሳይንሱን ማኅበረሰብ ብሎም መላውን አለም ስለምድራችን እና ስላሳለፈችው የሕይወት መልክ ለማወቅ ያስቻለ መሥራች ሁነት ነበር። ግኝቱ ብዙ ጥያቄዎችን የመለሰ ብዙ አዳዲስ ጥያቄዎችን ያነሳሳ ሲሆን በጥያቄዎቹም ለብዙ ምርምሮች መነሻ መሆኑ እስከዛሬ እንደቀጠለ ነው።
Lucy’s discovery, was a groundbreaking event that captivated both the scientific community and the world at large, providing invaluable insights into the evolution of life on Earth. It answered many questions while also prompting new inquiries that continue to drive research and exploration.
"Seenessa biyyaalessummaa guddummaa Itoophiyaaf"
Dameen Sab-qunnamtii Ummataa fi Idil-addunyaa Paartii Badhaadhinaa, Waajjira Paartii Badhaadhinaa Damee Finfinnee waliin ta'uun leenjii "Seenessa biyyaalessummaa guddummaa Itoophiyaaf" jedhuun qopheesse irratti sirni muuxxannoo wal-jijjiirraa gaggeeffame.
Leenjii guyyaa har’aatiin Waajjira Paartii Badhaadhinaa Damee Oromiyaatti hojileen muuxxannoo gaarii Damee Sab Qunnamtii hirmaattotaaf dhiyaatanii jiru.
በ2016 በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ስኬቶች (ቁጥር 16)
*******
ሐምሌ 29/2016
👉 የቂርቆስ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታው ተጠናቆ ስራ በመጀመር ላይ ነው። ለዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ትልቁን ኃላፊነት የወሰደውን የጤና ቢሮን በአስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ
👉 የካሳንቺስ ጤና ጣቢያ መለስተኛ እድሳት ተጠናቆ ስራ ጀምሯል፡፡
👉 በፈለገ ህይወትና በጎተራ ጤና ጣቢያ የድንገተኛ ህክምና ካርድ ክፍል ግንባታ ተጠናቆ ስራ ጀምሯል
👉 በፈረስ ሜዳ ጤና ጣቢያ የኦዲተብል ፋርማሲ ግንባታ እየተካሄደ ይገኛል
👉 በህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ከ17 እስከ 20 ሚሊዮን በሚደርስ ወጭ የከርሰ ምድር ውሀ ቁፋሮ ተጠናቆ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ላይ ነው፡፡
👉 ካሳንቺስ ፤መሿለኪያ ፤ፈረስ ሜዳ እና ጎተራ ጤና ጣቢያዎች ላይ የወረቀት አልባ ቴክኖሎጂ አገልግሎት መሰጠት ተጀምሯል፡፡ በሌሎቹም የዲጂታል ስራው እየተሰራ ይገኛል
👉 የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ብዛትን ወደ 664,987 ማድረስ ተችሏል
👉 7 የጤና ተቋማት የአገልግሎት መስጫ ክፍሎቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አድርገዋል ፡፡
👉 የጥራት ደረጃቸው የተረጋገጠላቸው የጤና ጣቢያ ላቦራቶሪዎችን 6 ማድረስ ተችሏል፡፡
👉 8 ጤና ተቋማት 43 እና ከዚያ በላይ የላብራቶሪ የምርመራ አይነት አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ተደርጓል ፡፡
👉 በ8 ተቋማት የመድሃኒትና የሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦት እና አገልግሎትን ማሻሻል ተችሏል፡፡
👉 በ8 ጤና ተቋማት የመሰረታዊ መድሃኒት አቅርቦት ማሟላት ተችሏል
👉 274936 የህብረተሰብ ክፍሎች በመንግስት ጤና ተቋማት መድሃኒት ታዝዞላቸው መድሀኒቱን ሙሉ ለሙሉ እንዲያገኙ ተደርጓል ፡፡
👉 9,185 እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል፡፡
የተከበራችሁ የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ፣በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶችና ወጣቶች ፣ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም የፀጥታ አካላት፣ በጋራ ስንቆም ሁሉን ማድረግ እንደምንችል ከላይ የተመዘገቡ ስኬቶቻችን ምስክር ናቸው"
ይህ የተመዘገበው ውጤት በጤና ጽ/ቤት አስተባባሪነት በእናንተ ትጋትና ድጋፍ በመሆኑ ይህ ድጋፋችሁ በ2017 በጀት ዓመት
አብሮን እንዲዘልቅና ቂርቆስን የአዲስ ፈርጥ የማድረግ ትልማችን እንዲሳካ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለው።
በቀጣይ በስፖርትና ወጣቶች ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ይዤ እመለሳለሁ።
አመሰግናለሁ!
ሙባረክ ከማል ዋና ስራ አስፈፃሚ
መከላከያ ሰራዊት ለኢትዮጵያ ኩራት ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለጠላቱ ስጋት ለህዝቡ ኩራት የሆነ ጀግና ሰራዊ ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለሕዝብ መዝናኛ አገልግሎት እንዲውል የተገነባውን ፋውንቴይን መረቁ።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮስኮ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ለሕዝብ መዝናኛ አገልግሎት እንዲውል የገነባውን ፋውንቴይን መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እንደ ከተማ አስተዳደር ከተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተጨማሪ ስራው በሌሎች የግል እና የመንግስት ተቋማት በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል::
ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ አካባቢ በብራዘርስ ኮንስትራክሽን እና ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ስር በአሰር ኮንስትራክሽን በተመሳሳይ ለሕዝብ መዝናኛ እንዲውሉ በራሳቸዉ ወጪ የገነቡልንን ፋውንቴኖችን ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረጋችን ይታወሳል ሲሉም ጠቁመዋል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በእነዚህ ስራዎች ላይ ለተሳተፉት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮስኮ)፣ ብራዘርስ ኮንስትራክሽን እና አሰር ኮንስትራክሽን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ሌሎች የግል እና የመንግስት ተቋማትም ከዚህ ልምድ በመውሰድ አካባቢያቸውን ለነዋሪዎች ምቹ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል::
የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዘላቂ እና የተረጋጋ የኢኮኖሚ ስርዓት ለመፍጠር ጉልህ ሚና አለው።
ክብርት ከንቲባ አዴ @AdanechAbiebie
🙏🙏🙏🙏🙏
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን ጋር ያደረጉት ውይይት
🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷🇪🇹🇹🇷
የከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ መልዕክት
የአዲስ አበባ ለውጥ ሃብትን በመቆጠብ፣ ለተገቢው የጋራ ልማት ብቻ በማዋልና ለዜጎች ትኩረት በመስጠት እየተተገበረ ያለ፣ ፈጠራና ፍጥነት ላይ የተመሰረተ፣ ቀጣይነት ያለው ነው።
ስራው የከተማችን ነዋሪዎች ትብብር ጎልቶ የታየበት እና ከከተማ እስከ ፌደራል ያሉ የመሰረተ ልማት መስሪያ ቤቶች ቅንጅት የተረጋገጠበት ነው።
በመሆኑም፣ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንጻዎቻችሁን በከተማችን ስታንዳርድና ዲዛይን መሰረት ያሳመራችሁ እንዲሁም ለእግረኛ መተላለፊያ እንዲሆን ምቹ በማድረግ የሰራችሁ የህንጻ ባለቤቶች፣ ከሁሉም በላይ የመገልገያ ቦታዎችን ክፍት በማድረግ ከተማችን 24 ሰዓት የማትተኛ እና የምትንቀሳቀስ እንድትሆን አገልግሎት አሰጣጣችሁን የለወጣችሁ፣ በአጠቃላይ የኮሪደር ልማቱን ዓላማ ያሳካችሁ የከተማችን ነዋሪዎችን ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ስንተባበር እንዲህ አይነት ፈጣን፣ ሰፊ ፣ ጥራትና ቀጣይነት ያለው ለውጥ ማስመዝገብ እንችላለን። አሁንም ይህን ስራ በሌሎች የከተማችን አካባቢዎችም ስለምናስፋፋው በላቀ ትብብር እና በቅርበት እጅ ለእጅ ተያያዘን መስራታችንን እንድንቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ሐምሌ 26 ቀነ 2016 ዓም
በምስሎቹ የምንመለከተው በመልማት ላይ ያለ የሻይ ተክል ማሳ ነው። በቡና ያሳካነውን አመርቂ ድል በሻይ ምርትም እንደግመዋለን።
These images show a tea plantation in progress. We aim to replicate the success we've had with coffee productivity in our tea production.
Via Abiy Ahmed Ali (phd)
FDRE 🇪🇹 PM
ዛሬ የመጨረሻ ቀን ነው
የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል ዛሬ ይጠናቀቃል።
በመሆኑም ዛሬን ብቻ በመጠቀም በአቅራቢያዎ በሚገኝ ወረዳ ሄደው በመመዝገብ ከቅጣት ይዳኑ ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ነገ ይጠናቀቃል‼️
የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል‼️
የመኖሪያ ቤት አከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ ነገ እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
በመሆኑም ተመዝጋቢዎች ዛሬን እና ነገን በመጠቀም በአቅራቢያቸው በሚገኝ ወረዳ በመመዝገብ ከቅጣት እንዲድኑ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።
በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተመንግስት እድሳት ተጀምሯል። በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይም ይገኛል። በአጭር ግዜ ውስጥ ፋሲልን ወደ ቀደመ ግርማ ሞገሱ እንመልሰዋለን።
Magaalaa Gondaritti haaromsuun Masaraa Mootummaa Faasiil jalqabameera. Sadarkaa gaariirrattis argama. Yeroo gabaabaa keessatti Faasiiliin gara surraafi ulfinasaa duraaniitti ni deebisna.
Renovation of Fasil Ghebbi has commenced in Gonder city and is progressing very well. In no time, Fasil will be elevated to its former glory.
በ2017 በጀት ዓመት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 74 ሚሊዮን 661 ሺህ 037 ወደ 80 ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል። በዚህም ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሠራል።
በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ የገጠር ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 54 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ወደ 64 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል ያሉት ኢንጅነር ሃብታሙ (ዶ/ር)፤ በ2016 በጀት ዓመት ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን የኅብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ በማድረግ አጠቃላይ የገጠር መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 52 ነጥብ አራት ሚሊዮን ወደ 54 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ የከተማ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 19 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ወደ 20 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ለማሳደግ መታቀዱንም ገልጸዋል።
እንደ ኢንጅነር ሃብታሙ (ዶ/ር) ገለፃ፤ ሀገራዊ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በስታንዳርድ ደረጃ ከነበረበት 69 ነጥብ አምስት በመቶ ወደ 78 ነጥብ ሁለት በመቶ ለማሳደግ ይሠራል። የገጠር መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በስታንዳርድ አገልግሎት ደረጃ ከነበረበት 66 ነጥብ ሁለት በመቶ ወደ 77 ነጥብ አምስት በመቶ ለማሳደግ ታቅዷል።
የከተማ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በስታንዳርድ አገልግሎት ደረጃ ከነበረበት 79 በመቶ ወደ 80 በመቶ ለማሳደግ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 21 /2016 ዓ.ም
የ4 ኪሎ የመሬት ውስጥ እግረኛ መተላለፊያ መንገድ ግንባታ በማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡
በኮሪደር ልማት ሥራው ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የልማት ስራዎች መካከል የእግረኞች መተላለፊያ መንገድ ግንባታ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ዋና መንገድ በሚያቋርጡ እግረኞች ላይ ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ አደጋ ስጋት በእጅጉ የሚቀንስና ደህንነትን የሚያስጠብቅ ነው።
ከዚሁ በተጨማሪ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የሚኖረውን የትራፊክ ፍሰት በማሳለጥ ረገድ የመሬት ውስጥ የእግረኞች መተላለፊያ መንገድ ግንባታ ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡
ይህ በአራት ኪሎ ትምህርት ሚኒስቴር ፊት ለፊት፤ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የመሬት ውስጥ እግረኛ መተላለፊያ መንገድ ግንባታ ምቹና ዘመናዊ ሲሆን ፤ሰዎች በውስጡ ከመተላለፍ ባሻገር አረፍ ብለው ሻይ ቡና የሚሉበት እና ሌሎች ግብይቶችን ማካሄድ የሚያስችል ሱቆች ግንባታን ያካተተ እና በአይነቱ ልዩ የሆነ መሰረተ ልማት ሲሆን፤ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የብርሃን እና የጨለማ ትንቅንቅ
#ኢትዮጵያ 🇪🇹 #Ethiopia
#አዲስአበባ #Addisababa
@AbiyAhmedAli
@AdanechAbiebie
@HItefa
💪💪💪💪💪💪💪💪