prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1397

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

👆👆👆
ወዳጆቼ ጀግናው መሪያችን ዶ/ር ዐብይ የችግኝ ጋሻ የአካፋ ጦርና የፅናት ሰይፍ ትጥቅ ይዘን በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ይዘን እንድንሰበሰብ ባዘዙን መሰረት 2ቀን ቀረው። ዘመቻው ከፀሀይ ጀንበር እሰከ ጨረቃ ጀንበር ነውና ወገብ ጠበቅ እናድርግ

#ዐብይ_አህመድ
#ነሐሴ_17
#ስድስት_መቶ_ሚሊዮን
#በአንድ_ጀምበር
#አረንጓዴዓሻራ 
#GreenLegacy

@AbiyAhmedAli 💪🌴💪


🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

👆👆👆
ኢትዮጵያን አረንጓዴ ምድር እናደርጋታለን!   ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም 600 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር እንተክላለን!! 

#ዐብይ_አህመድ
#ነሐሴ_17
#ስድስት_መቶ_ሚሊዮን
#በአንድ_ጀምበር
#አረንጓዴዓሻራ 
#GreenLegacy

@AbiyAhmedAli 💪🌴💪

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሁሉም የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት በጻፈው ደብዳቤ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር መመርያ መሠረት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ አሳሰበ፡፡

ሚኒስቴሩ ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ፣ የዲፕሎማሲና የቆንስላ አገልግሎት የሚሰጡ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት፣ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቧቸው ተሽከርካራች የኤሌክትሪክ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመታገል በምታደርገው ቁርጠኝነት፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት የተከለከለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በመሆኑም የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ፣ በዚህም መሠረት ከቀረጥ ነፃ የማስገባት መብታቸውን እንዲጠቀሙ ሲል ገልጿል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚኒስትር ደኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ተፈርሞ ለጉምሩክ ኮሚሽን የላከው ደብዳቤ፣ የገቢ ንግድን በይበልጥ እንዲያሳልጥ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ በሕግ ከተከለከሉ ዕቃዎች፣ የነዳጅ አውቶሞቢሎችና ከፀጥታና ከደኅንነት ዕቃዎች ውጪ ሌሎች ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሪ ክፍያ (ፍራንኮ ቫሉታ) ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በመንግሥት የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ይህንን ውሳኔ በርካታ የአውሮፓ አገሮች የሚደግፉት ሐሳብ መሆኑንና አገሮች የአስተናጋጅ አገርን ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ውሳኔው የዲፕሎማሲ ሥራን ለመሥራት የሚያውክና የአገሮችን ሉዓላዊነትን የሚጥስ ባለመሆኑ፣ እንደ እነዚህ ዓይነት ሕጎች ሲወጡ ዲፕሎማቶች ያንን ሕግ አክብረው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡     
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 38 የገቢ ንግድ ምርቶች ዕግድ እንዲነሳላቸው ባሳለፈው ውሳኔ ቢያሳውቅም፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ግን በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ዕግዱ እንደማይነሳ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ለብሔራዊ ባንክ፣ ለገቢዎች ሚኒስቴርና ለጉምሩክ ኮሚሽን አስተላፎት በነበረው ሰርኩላር፣ በተወሰኑ ምርቶች ላይ የውጭ ምንዛሪ ገደብ ተጥሎ እንደነበር አስታውሶ፣ ዕገዳው ከሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ መሻሩን ገልጾ ነበር፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ በነዳጅ የሚሠሩ የቤት አውቶሞቢሎችና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው ዕገዳ እንደሚቀጥል ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አረንጓዴ አሻራ ሌላኛው ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበቻ

በአረንጓዴ አሻራ በተሰራው የንቅናቄ ስራዎችና በተጨባጭ በተመዘገቡ ለውጦች ችግኝ መትከልና መንከባከብ የአንድ ግብርና ሴክተር አድርጎ የሚመለከት አስተሳሰብን በማረቅ የባህል ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡፡

ችግኝ መትከል አንዱ የሕይወት አካል አድርጎ በመቁጠር አገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄዎችን ከመሳተፍ ባለፈ በየጓሮውና በየደጁ የመትከልና የመንከባከብ ባህል እያደገ መጥቷል፡፡

በርካታ ወጣቶችም በአረንጓዴ አሻራ የኔነት ስሜት እንዲዳብር በማድረግ የገቢ ማግኛ መንገድ አድርገው እየሰሩበት ይገኛል፡፡ ችግኝ በማፍላትና በማቅረብ፣ ጉድጓድ በማዘጋጀትና ችግኞችን በመንከባከብ የራሳቸውን ገቢ እንዲያገኙ እድል ፈጥሯል፡፡

በግላቸውም ይሁን በማህበራት ተደራጀው ችግኝ የሚያፈሉ ወጣቶች በፍጥነት የሚደርሱ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን ዓመቱን በሙሉ በማፍላትና በመሸጥ ገቢያቸውን ማሳደግ ችለዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በወጣቱ ዘንድ መነሳሳትን በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸውን ችግኞች በመትከል ለሌሎች ዜጎችም ተጨማሪ የስራ ዕድሎችን መፍጠር የቻለ ነው፡፡ በመሆኑም ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ብዙሃ ህይወትን ከማስጠበቅ ባለፈ ተጨማሪ ኢኮኖሚዊ አቅምን ማጎልበቻ መንገድ በመሆኑ ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ አብነታዊ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

#Prosperity

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመሪያችንን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለን ነሀሴ 17 በተደመረ አቅም ታሪክ ሰርተን ታሪክ እንፅፋለን !

በታሪክ መነፀር ወደ ኋላ ብንመለከት የኢትዮጵያ ከፍታ ቁልፉ በህብረት መቆም ነው። ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን አቻችለው ሀገርን እና ህዝብን ባስቀደሙባቸው ጊዜያት ሁሉ ለትውልድ የሚሻገር ደማቅ ታሪክ ሰርተዋል።

ለአብነትም የአድዋ ድል የሁላችንም ኩራት ሆኖ የዘለቀው እናት አባቶቻችን በተደመረ አቅም ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰው በፃፉት ደማቅ አሻራ ነው፡ ፡

ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም እርስ በእርስ ማበላላትን እንደ ዋና ስልት የሚጠቀሙት ። እንዳይላላ ሆኖ የተጋመደው ፣ እንዳይለያይ ሆኖ የተሰባጠረው ህብረብሔራዊው የኢትዮጵያውያን ማንነት ግን ዛሬም እንደትናንቱ ሲፈትኑት ይበልጥ ይጠብቃል።

የእኛ ትውልድ ሀገራዊ ለውጡ ያመጣቸውን መልካም አጋጣሚዎች ሳያባክን የራሱን አሻራዎች የሚያሳርፍባቸው ብዙ ዕድሎች አሉ።

ወንድማማችነት ፣ እህትማማችነት እና አብሮነት እንዲጎለብትና ብሔራዊነት ገዥ ትርክት እንዲሆን እንደ ፓርቲም እንደ መንግስትም የተጀማመሩ አበረታች ስራዎች በተደመረ አቅም አኩሪ ታሪክ ለማስመዝገብ አሰባሳቢ ናቸው፡፡

ሀገሬን እወዳለሁ የሚል ሰው የሀገሩን ልማት ይናፍቃል ፤ የሀገር ልማት ደግሞ ራስን ከመለወጥና አካባቢን ከማልማት ይጀምራል። እፅዋትን መትከል ደግሞ ለአሁኑ ብቻም ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስብ ዜጋ ቀዳሚው እርምጃ ነው።

ችግኝ መትከል ትውልድን የማስቀጠል የህልውና ጉዳይ ነው።

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በቀላል ወጪ ለሀገራችን ቀጣይነት ያለው ዕድገት መሰረት የምናፀናበት እንዲሁም ለትውልድ እና ለዓለም ንፁህ አየር የምንለግስበት የዋጋ ተመን የማይወጣለት ውድ ስጦታችን ነው።

በአንዲት ፕላኔት ውስጥ የምንኖር ፣ የምንጋራቸው ብዙ ነገሮች ያሉን የሰው ልጆች ሁሉ እጣፈንታችን የተሳሰረ በመሆኑ በጋራ መክረን በህብረት የምንመልሳቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም በተለይም የሀገር ድንበር ሳይገድበው ሀገራት የሚጋሩት የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የሁሉም የቤት ስራ ነው።

ኢትዮጵያውያን የዓለም ሰላም ግድ የሚለን ፣ ፍትሀዊ የዓለም ስርዓት እንዲዘረጋ የታገልን ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ነፃነትና እኩልነት ዋጋ የከፈልን ፣ የራሳችንን የማናስደፍር የሌሎችን የማንወስድ ፣ አብሮ መብላትን ፣ አብሮ ማደግን ፣ መረዳዳትና መከባበርን እሴቶቻችን ያደረግን ነን።

ዛሬም ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላም ትታገላለች፣ ፍትሀዊ ስርዓት እንዲዘረጋ ፅኑ አቋም ታራምዳለች ፣ ከተገፉት ጎን ትቆማለች ፣ ከምንም በላይ ደግሞ አረንጓዴ አሻራዋን በማሳረፍ ንፁህ አየር ለዓለም ለመለገስ እየታተረች ትገኛለች ::

ዓለም ተራቁታለች ፤ በብዙ መልኩ ተበክላለች። የምትለመልመው እና የምትፈወሰው ችግኝ በመትከል ነው ፡ ፡

ለዚህም ነው በፓርቲያችን ሊቀመንበር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አሻግሮ የመመልከት ብቃት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በጎርቤት ሀገራት እና በሌሎችም እንዲስፋፋ መሪዎቻችን በሄዱበት ሁሉ አረንጓዴ አሻራቸውን በማሳረፍ በአርያነት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት።

ሀገራችን ለነሀሴ 17 / 2016 ዓ/ም ዜግነታዊ ብቻም ሳይሆን ትውልዳዊ ሀላፊነታችንንና ግዴታችንን የምንወጣበትን ፣ ታሪክ ሰርተን ታሪክ የምንፅፍበትን ጥሪ ሰርቶ በሚያሰራው መሪያችን አቅርባልናለች።

ከጠዋት እስከ ማታ ባለው ጊዜ አዋቂዎች በትንሹ 20 ፣ ታዳጊዎች ደግሞ በትንሹ 10 ችግኞችን በመትከል አፈር በሚነኩ እጆቻችን አሻራ ደማቅ ታሪክ እንፅፋለን።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት
#aa_prosperity

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

👆👆👆
አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኒዴዝ በገዛ ፈቃዳቸው ከስልጣን ለመልቀቅ ደብዳቤ አስገቡ

አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜኒዴዝ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ከስልጣናቸው ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተሰምቷል።

አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሚኒንዴዝ በቀጣዩ ህዳር ወር በሚካሄዳው የአሜርካ ምርጫ እንደማይሳተፉም እየተነገረ ነው፡፡

አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሚኒንዴዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ በኒውጄርሲ በንግድ ስራ ላይ ከተሰማሩ 3 የግብጽ ሰዎች እጅ ወርቅ እና ጥሬ ገንዘብ ጉቦ መቀባላቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ይህም ሴናተሩ ራሳቸውን ለግብጽ መንግሥት ወኪል አድርገው በመቆም ሰርተዋል የሚል ክስ ሲቀርብባቸው ነበር።

ሴናተር ቦብ ሚኒንዴዝ በዘረፋ፣ ጉቦ በመቀበል፣ ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም፣ በሴራ፣ ፍትህን በማደናቀፍና መሰል 16 ወንጀሎች ተሳትፎ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑንም ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም በሚቀጥለው ህዳር ወር በሚካሄደው የአሜርካ  ምርጫ ዴሞክራቶችን ወክለው የሚወዳደሩት ቦብ ሜኒዴዝ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው  እንዲለቁ ጥሪ የተደረገላቸው ሲሆን፤ በሌላ እጩ እንደሚተኩም ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎም ሴናተሩ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ከስልጣን ለመልቀቅ  ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሲቢሲ  ኒውስ ዘግቧል፡፡

የ70 ዓመት አዛውንቱ ቦብ ሚኒንዴዝ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ከሀገሪቱ ወታደራዊ እርዳታ ለመውሰድ አመቻችተዋልም ተብለዋል።

አጋሮቻቸውን ከወንጀል በመከላከል፣ አለአግባብ እንዲበለጽጉ በባለቤታቸው በኩል ከግብጽ የደህንነት ሰዎች ጋር ግኑኝነት በመፍጠር  ስልጣንን አላግባብ ተጠቅመዋል ሲል አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ግኑኝነት ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር ሆነው  ስራቸውን እየሰሩ ስለመሆናቸው የሚናገሩት ቦብ ሚኒንዴዝ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለ9 ሳምታት ምርመራ ሲደረግባቸው ቢቆይም አልፈጸምኩም እያሉ ይገኛሉ፡፡

ሴናተሩ “እኔ በህዝብ ፊት የገባሁትን ቃል አልጣስኩም፣ ከሀገር ወዳድነቴና አርበኝነቴ  ውጭ ምንም አልሆንኩም፡፡ ለማንም ሀገር የምሰራው ጉዳይ የለኝም” ብለዋል፡፡

አሜርካዊው ሴናተር በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ የማምሻ እድሜያቸውን አስርት ዓመታት ወደ ማረሚያ ቤት ሊያመሩ እንደሚችሉ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል

🇪🇹💪

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ቃል በተግባር 👆

AbiyAhmedAli 💪

🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አየር መንገዱ ወደ እስራኤል የሚያደርገውን በረራ አቆመ።

የአሜሪካ አየር መንገድ እስከ ሚያዚያ 2025 ድረስ ወደ እስራኤል የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ገልፆአል።

የአሜሪካ አየር መንገድ በቀጠናው እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ እስከመጪው አመት ሚያዚያ ድረስ ምንም አይነት በረራ ወደ እስራኤል እንደማይኖረው ነው ያስታወቀው።

ከአሜሪካ በተጨማሪ በትንሹ 20 አየር መንገዶች ከእስራኤልም ሆነ ወደ እስራኤል የሚደረጉ በረራዎችን ማቆማቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይህ እርምጃ በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከ40ሺህ በላይ ሰዎች ከተገደሉ እና ከ92ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቆሰሉ በኋላ በቀጣናው እየበረታ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ የተወሰደ ነው።

አየርመንገዱ እስከ ሚያዝያ 2025 ወደ እስራኤል በረራ እንደማያደርግ ይግለፅ እንጂ ተጨማሪ ጉዳዮችን ግን አላብራራም።

እስራኤል ባለፈው ወር በኢራን መዲና የሀማስን የፖለቲካ መሪ ኢስማኤል ሀኒዬህን ከገደለች በኋላ ከኢራን ጥቃት ይደርሳል በሚል በከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ ትገኛለች።

ኢራን እና ሀማስ ግድያውን እስራኤል ፈፅማዋለች በሚል ክስ ቢያቀርቡም ፤ እስራኤል በበኩሏ ለግድያው ሀላፊነት ከመውሰድም ሆነ ክሱን ከማስተባበል ተቆጥባለች።

🇪🇹 💪 🌴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የምናብ ግድያና ድምሰሳቸውን እየሰማን፤ የድል ማማችን ላይ አለን"

የማህበራዊ ሚዲያ  ምንደኞች ለከት የለሽ የፈጠራ ድርሰት በጣም አስቂኝ እየሆነ መጥቷል።

በእጁ የያዘው ብርጭቆ በድንገት ወድቆበት በሚፈጠረው ድምጽ "ልቡ የሚከዳው ድንጉጥ"  ውሎበት ስለማያውቀው ጦርነት የሩቅ አዝማች ሆኖ በቃላት ናዳ ብዙ ሲናገር ይገርማል።

በማገዳደል፣ደም በማፋሰስና የህዝብን የሰቆቃ ዕንባ በማብዛት "ምኞቴ ይሳካልኛል" ባይ የስደት አውደልዳይ ከክረምቱ ዝናብ የበዛ የሀሰት ዶፍ ቢያዘንብ ያው "ምኞት አይከለከልም" ይሉት ሀገራዊ ብሂል አለና ከዚያ የሚያልፍ አይደለም።

ግን ግን " ሁሉም ነገር እኮ ለከት አለው።" ስለ ውትድርና እና ስለ ውጊያ ግንዛቤ ያለው ሰው በእርግጠኝነት የሚያወራው ነገር ያሳስበዋል።

እነዚህ "ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ" ይሉት አይነት ከንቱ ኳታኞችን እኩይ መሻት የወለደው ቅዠታዊ ሀሰትን ዕውን የሚያምን ካለ እጅግ በጣም ያሳዝናል።

ለነገሩ እኛ የምንሰራውን የምናውቅ፣ግብ ያለን፣እያንዳንዷ እንቅስቃሴያችን ከሀገርና ህዝብ ጥቅም ውልፊት እንዳይል አድርገን የምናስኬድ ነን።እናም በወሬ ናዳ ኪሱን ለማድለብ የሚጥር  የሀሰት ነጋዴ ድርሰት ብዙም አያሳስበንም ሥራችን ሠላምን ማምጣት ነውና።

ይህን ጠንቅቀን ስለምናውቅም በግዳጅ አፈጻጸም ስምሪቶቻችን ሁሉ፤ባለማወቅ የተሸነገለን ወጣት እኩያኑ እንደቀመሩለት ለማገዶነት እንዳይዳረግ እና እውነቱ ተገልጦለት ወደ ቀልቡ እንዲመለስ ሰፊ ዕድል በሚሰጥ አርቆ አሳቢነት ማስኬዳችን በብዙ አትርፎልናል።

ብዙዎች ከሸንጋዮች የጥፋት መንገድ ወጥተው ዛሬ ላይ ግንባር ቀደም የህዝብ ሰላም አስከባሪነት ሚናን መወጣት እንዲችሉ ማድረግ መቻላችን በእጅጉ ያስደስተናል።

በዚህም በርካታታ አስተዋዮች ከከረሙበት የውሸትና የውንብድና ህይዎት በመውጣት የሩቅ አሳቢነትን ማዕረግ በመጎናፀፍ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በየቀኑ የሰላምን አማራጭ ትክክለኛነት ተገንዝበው ራሳቸውን ከእንግልትም ከወንጀልም ታድገው ማህበራዊ ህይዎታቸውን መምራት ጀምረዋል።

Via - አማራ ፖሊስ ኮሚሽን

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ግራ የተጋባው የዓድዋና ጀሌዎቹ ነፃ አውጪ ግለሰብና ድርጅቶች በምስል ሲገለፁ 🤔

🇪🇹 💪

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የሽማግሌዎችን ህይወት ለማቆየት ዳግም ህይወቱን የሚከፍል የትግራይ ወጣት አይኖርም" - ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ

🇪🇹💪

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እንኳን ለደብረ ታቦር /የቡሄ/ በአል አደረሳችሁ!

ቡሄ ማለት ገላጣ ማለት ነው። ከሰኔ አጋማሽ ጀመሮ ያለው ዝናብ እና ጭጋግ እየቀለለ የብርሃኑ የመስከረም ዘመን የቀረበበት መሸጋገርያ ጊዜ በመሆኑ ቡሄ ወይም ገላጣ ተብሏል። “ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት፣ ሁሄ ከዋለ የለም ክረምት” እንዲሉ። ሙልሙል የሚጋገርበት ሊጥ ወይም ቡሆ ጋር ተያይዞም ቡሄ መባሉን ሊቃውንት ያስተምራሉ።

ቡሄ ጌታ በአስፈሪ ነጎድጓዳማ ድምጽ ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት በዓል በመሆኑ እሱን እንዲያስታውሱ ጅራፍ ይጮሃል፣ ችቦ ይበራል። ጅራፍ ሲጮህ ድምጽ አለው። ሆን ተብሎ ድምጽ እንዲሰጥ ሆኖ ነው የሚገመደው።

ይሄ ድምጽ ጌታ በደብረ ታቦር በተገለጸ ጊዜ ያሰማውን ድምጽ እንዲያስታውስ ነው። ማስደንገጡም ብርሃነ መለኮቱንና ድምጸ መንግስቱን በሰሙ ጊዜ እነ ጴጥሮስ መደንገጣቸውን እንዲያስታውስ ነው። ችቦውም የሚለኮሰው እንደ ፀሐይ ደምቆ የታየውን ብርሃነ መለኮቱን በሚታይ ምድራዊ ብርሃን (እሳት) ለማስታውሰ እንደሆነ ይነገራል።

ትውፊታችን እንደሚነገረን - ጌታ በደብረ ታቦር ተራራ ብርሃነ መለኮቱን ሲገልጥ፣ በአካባቢው የነበሩ እረኞች ይሄን ተዓምር ለማየት ወደ ደብረ ታቦር ሄደው ነበር። በምስጢሩም ተገርመው እጅግ በመቆየታቸው ቤተሰቦቻቸው ዳቦ ይዘው ልጆቻቸውን ሊጠይቁ እንደ ሄዱና ያንንም ለማስታወስ ሙልሙል ዳቦ ተጋግሮ በዚህ ቀን ይበላል ይህም እንደ ባህል ሆኖ መቀጠሉን ትውፊቶች ይናገራሉ።

በድጋሜ እንኳን ለደብረ ታቦር /የቡሄ/ በአል አደረሳችሁ! አደረሰን!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ነሃሴ 17!
4 ቀናት ቀርተውታል!
ሁላችንም አረንጓዴ አሻራችንን
ለማሳረፍ ተዘጋጅተናል!
#Ethiopia 📷
#አረንጓዴ_አሻራ
#600_ሚሊዮን_ችግኝ
#Worldrecord
#GreenLegacy

@AbiyAhmedAli 💪🌴💪

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል አደረሰን / አደረሳችሁ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ቸር ምድር፣ ታታሪ ሕዝብ እና ብሩህ ሀገር ባለቤቶች ነን። ፈተና ያልበገረው ፅናታችን ቁጭትን ወልዷል፣ ቁጭታችን ደግሞ ነጋችንን ይገነባል" - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

@TemesgenTiru 🙏🙏🙏

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://x.com/ProsperityKera/status/1826210191731277837?t=I8d53af-rUNCPMFAuhPtyw&s=35

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://x.com/ProsperityKera/status/1826208644901253162?t=R09CF3pUH31wyC7bP1qZbw&s=35

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢዜማ የፖለቲካ አካዳሚ ሊከፍት መሆኑ ተነገረ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፖለቲካ አካዳሚ በመክፈት ስልጠናና ትምህርት ለመስጠት ማቀዱን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።

የፖለቲካ አካዳሚው ማንኛውም ፍላጎት ላለው የፖለቲካ ፓርቲም ይሁን ፖለቲካ ላይ ለሚሰራ ግለሰብ ትምህርት ወይም ስልጠና ለመስጠት በሚል አላማ የሚከፈት መሆኑን የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኢዩኤል ሰለሞን ለጣቢያችን ገልጸዋል።

በመጪው 2017 ዓ.ም ተመርቆ ስራ ይጀምራል የተባለው አካዳሚ ማንኛውም ፍላጎቱ ያለው ግለሰብ የሚማርበት ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ለፓርቲው አባላት ቅድሚያ እንደሚሰጥ የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊው ተናግረዋል።

ዘርፉን ለማገዝ ታልሞ የሚከፈት ነው በማለት የሚናገሩት አቶ ኢዩኤል ፓርቲዎች በሃሳብ ልእልናና በእውቀት ተሻጋሪ ህልምና ራእይ እንዲኖራቸውም ያግዛል ብለዋል። ዘመን ተሻጋሪ የፖለቲካ ስርአት በእውቀትና በሃሳብ ልእልና ብቻ እንዲመጣ እንሰራለን ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ልማድ በግለሰቦች ሃሳብና በስልጣን የበላይነት ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ ለዘርፉ እውቀትና ስልጠና በማበርከት ዘላቂ ስርዓት ለመዘርጋት አካዳሚ መገንባት ማስፈለጉን በመጥቀስ በርካታ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ፓርቲዎች በአካዳሚው እንደሚጠቀሙ ተመላክቷል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመሪያችንን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለን ነሐሴ 17 በተደመረ አቅም ታሪክ ሰርተን ታሪክ እንፅፋለን !

በታሪክ መነፀር ወደ ኋላ ብንመለከት የኢትዮጵያ ከፍታ ቁልፉ በህብረት መቆም ነው።
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
@aa_prosperity
@AbiyAhmedAli
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኩሩግ ንጌቡል 👆 በኢንዶኖዢያ በምዕራብ ጃቫ የሚገኝ ፏፏቴ ነው 😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://x.com/ProsperityKera/status/1826019804152557631?t=Mf47vI_TSQ-wo0K7yuqpqQ&s=35

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

https://vm.tiktok.com/ZMrWf7PwW/

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"መከላከያ የሰላም ምንጭ ብቻ ሳይሆን የልማት ምንጭ፣ የፈጠራ ምንጭ መሆን አለበት" - ጠ/ሚንስትር ዐብይ አህመድ

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ሉኣላዊነት እና ሰላም ከማረጋገጥ በተጨማሪ በልማቱ ላይ እያደረገ ያለው አበረታች ነው

@AbiyAhmedAli 💪

🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"Oromiyaan Baha Biiftuu dirree Nagaafi Jaalalaa,Uummata keenyaa Harargee Biyya Misooma" - PMNO Obbo Shimallis Abdiisa

🌴 @ShimelisAbdisa 🌴

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የባህር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ የግንባታ ሂደት ጉብኝት።

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳና የባህር ሃይሉ ከፍተኛ አመራሮች ጃል ሜዳ እየተገነባ የሚገኘውን የባህር ሃይል ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ የግንባታ ሂደቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
  
በጉብኝቱ ዕለት የጠቅላይ መምሪያው ግንባታ ከተጀመረ በጣም ቅርብ ጊዜ ቢሆንም አሁን ያለበት የግንባታ ደረጃ ጥሩ የሚባልና በተፈለገው ልክ እየሄደ እንዳለ ተናግረው የፕሮጀክቱ የግንባታ ፍጥነት ደግሞ ለሌሎች የጥሩ ሥራ አፈፃፀም ተምሳሌት ነው ብለዋል።
 
ኮሞዶር ጀማል እየተገነባ ያለው የቢሮ ግንባታ በተቀመጠለት ጊዜ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ የግንባታውን ሠራተኞች አበረታተዋል።
  
የባህር ሃይል ቢሮ የግንባታ ሂደትና አሁን ላይ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ የባህር ሃይል ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል በቀለ መለሰ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡

🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴🇪🇹🌴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ አካል ሟቋቋሚያ ህጋዊ ማእቀፍ ላይ ምክክር ተጀመረ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀ የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ ማቋቋሚያ ህጋዊ ማእቀፍ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረክ ተጀመረ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የከተማ ውሃ አገልግሎትና የሳኒቴሽን አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ከአስተዳደር፣ የራስን የጥገናና ሌሎች አቅሞች ከመገንባትና የውሃ ሀብትን ከመንከባከብ፣ ተደራሽ ከመሆንና ውጤታማነትን ከማሳደግ አንጻር አስቻይ ተቋምና ህጋዊ ማእቀፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ የከተማ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችም ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ አንስተዋል።

መድረኩ ክቡር ሚኒስትሩ ጨምሮ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አየለች እሸቴ፣ በሕ/ተ/ም/ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር አወቀ አምዛዮ፤ ከሀገር ውስጥና ከአፍሪካ ሀገራት የተጋበዙ እንግዶች በተገኙበት በ አዳማ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🌴🌴🌴 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ የተተከለ ችግኝ ለትውልድ የሚያብብ የውርስ ቃል ኪዳን ነው።

ችግኞችን የምንተክለው ለመጪው ትውልድ የበለፀገች ሀገር ለማኖር ነው።

የምንወዳት ሀገራችን በአንድ ቀን 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካችንን ዳግም የምናድስበትን ልዩ ቀን ነው።

@AbiyAhmedAli 🌴💪🌴

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አተይ @reda_getachew ዛሬ 👇
‘የትግራይን ህዝብ የሰላም ፍላጎት ወደጎን በመተው ለግዜው ማን መሆኑ በግልፅ ከማይታወቅ እና እነሱ ደጀን ይሆነናል ያሉት የውጭ ኃይል ተማምነው የትግራይን ህዝብ አደጋ ውሰጥ የሚከት የተወሰነ ግለሰቦች ጠባብ ፍላጎት ነው “

🇪🇹 💪

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ልዩ ዜና❗️

“ለጥቂት ስልጣን ፈላጊዎች ሲል የትግራይ ወጣት ዳግም ህይወቱን አይገብርም”
ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፣ መቐለ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ከተናገሩት የተወሰደ ...

@reda_getachew 💪💪💪

🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ሀገሬን_አለብሳለሁ
#ነሐሴ_17 እንገናኝ
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

🇪🇹

Читать полностью…
Subscribe to a channel