የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሁለተኛ ተከታታይ ግዜ በ “Arabian Cargo Awards” ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን ተቀዳጀ። የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብሩ በዱባይ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በገልፍ ሀገራት ለሚሰጡ ምርጥ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎቶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ ነው ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Good Luck سيد Mr. Muse Bihi Abdi - President of the Republic of Somaliland 🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሙዝ ጭኖ ሲመለስ የነበረ ጀልባ ጫሞ ሐይቅ ሰምጦ ከተሳፈሩ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ መገኘታቸውን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙት እና ገጽታ ግንባታ ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደገለጹት ትላንት ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ የጀልባውን አሽከሪካሪ እና 15 የቀን ሠራተኞችን ከሙዝ ጋር ጭኖ ከአማሮ ዞን አቡሎ አልፋጮ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ጀልባው መስጠሙን ተናግረዋል ።
በጀልባው ላይ ከነበሩ 16 ሰዎች ሁለቱ በጀርካን ላይ ተንሳፈው የተረፉ ሲሆን 14ቱ ባለመገኘታቸው ፖሊስ በፍለጋ ላይ መሆኑን ኮማንደር ረታ ተናግርዋል ።
15 ተሳፋሪዎች በሙሉ ሙዝ ለመጫን ከአርባምንጭ ዙሪያ አካባቢ የሄዱ መሆናቸውን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡
1. ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስ፦ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር
2. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፦ የቱርዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር
3. ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ፦ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Badhaadhinaaf Tokkummaan Murteessa dha!
Imala keenya waliinii yeroo qaaccessinuu humni keenya tokkummaa keessa akka jiru hubatama. Tokkoomnee heddumina keenya gaafa fudhannu, aadaan, afaanii fi safuun hundi eenyummaa waloo keenya ni guddisa.
Mul’ata waloo boruu keenyaa karaa dammaqina qabuun mirkaneessuf tumsi waloo barbaachisaa dha. Kallattii kanaan nageenyaafi badhaadhina hunda galeessa mirkaneessuf hundi keenya waliin haa kaanu.
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተከበረ ነው
የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሃሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተከበረ ይገኛል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተከበረ በሚገኘው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴን ጨምሮ አባት አርበኞች፣ የመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አካል የሆነውን እና በቅርብ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አፈፃፀም ገምግመናል። ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት ችለናል። በተመሳሳይም የገቢ ግባችንም የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል። በአጠቃላይም ያለፉት ሁለት ወራት ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል።
The macroeconomic committee met this morning to review the performance of the new macro policy measures introduced as part of our homegrown economic reform agenda. In the two months since the policy's implementation, we have observed a stable forex regime. Likewise, our revenue objectives are on track, meeting the set targets. Overall, the past two months indicate a successful rollout of the policy.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ሰፉ" .
የኦሮሞ ህዝብ ከተቃኘባቸው መሪ መስተጋብሮች ትልቁን ቦታ የሚይዘው "ሰፉ" ነው።
‘ሰፉ’ በኦሮሞ ዘንድ ማህበራዊ ስርዓት የሚጠበቅበት፤ የግለሰቦች ባህሪ፤ አመለካከት እና ምግባር ማረቂያ፤ ነውር የሆነውን ካልሆነው የሚለይበት ማህበረ እምነታዊ እሳቤ (concept) ነው። ሰፉ የኦሮሞ ማህበረሰብ መሰረት ነው ማለትም ይቻላል!
በዚህ ማህበረ እምነታዊ እሳቤ ውስጥ ሰዎች ከማህበረሰቡ ጋር ሊኖራቸው የሚገባ ጤናማ የሆነ መስተጋብር ምን መምሰል እንዳለበት ያልተጻፈ ግን የሚታወቅ ህግ አለ። በሰፉ ሰዎች ስልጣናቸውን በምን አግባብ መጠቀም እንዳለባቸው፣ አቅመ ብርቱዎች አቅመ ደካሞችን እንዴት መርዳት እንዳለባቸው ስርዓት ተበጅቶለታል። በዚህ እሳቤው ሰፉ ህሊና ነው።
ኦሮሞ ሰፉ የሁሉ ፈጣሪ የሆነው ዋቃ ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ለሰው ልጆች የሰጠው የማህበራዊ ስረዓት ህግ ነው ብሎ ያምናል። በጥንት የኦሮሞ ማህበረሰብ እምነት እያንዳንዱ ፍጥረት የራሱ ayyaana (መንፈስ) አለው ተብሎ ይታመናል። በመሆኑም እያንዳንዱ ፍጥረት (ሰው፣ እንሰሳት፣ እጽዋት ወዘተ) የራሱ የሆነ መለያ ባህሪ አለው። ፈጣሪ ምድርን ሲፈጥር ሰው በስነ-ስርዓት እንዲኖር ሕግንም አብሮ ፈጠረ። እነዚህም ሕጎች የሰው ሕግ፣ የከብቶች ሕግ፣ የፈረሶች ሕግ፣ የዱር አራዊት ሕግ፣ የእጽዋትና የፀሀይና የከዋክብት ሕግ ይሰኛሉ።
"ሰፉ" የማይቀየር የፈጣሪ ሕግ ነው። ይህም ክልክል የሆኑትን ሰውን መግደል፣ መስረቅ፣ ዝሙት እና መዋሸትን ተላልፎ መገኘት ነው። ፈጣሪን፣ ምድርን እንዲሁም ሌሎችን ፍጥረቶች ሁሉ ማክበር የፈጣሪን ሕግ መጠበቅ ነው። ክልከላዎች 'ለጉ' የሚባሉት የማህበረሰቡን አይነኬ ተግባራት ለመጠበቅ የወጡ ናቸው። አንድ ሰው ሀጥያት ሰራ የሚባለው እነዚህን የፈጣሪን ሕግና ክልከላዎች ሲጥስ/ ሲተላለፍ ነው።
ሰፉ ሚዛን ነው። ታላቅና እና ታናሽ፣ ትልቅ እና ትንሽ፣ ሃብታም እና ደሃ፣ ጌታ እና ሎሌ አንዱ ለአንዱ ሰፉ ነው። ሚዛን! ሚዛን ነው ሲባል ሁሉንም በእኩል ያስቀምጣል ለማለት ግን አይደለም። በሰፉ ተመዝኖ ማረፊያው ጎራው ይለያል። ምክንያቱም ሰፉ የሁለት ጎራዎችን መቀላቀልና መዋሃድ የሚፈቅድ እሳቤ አይደለምና።
በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ሰው በሰፉ ይመዘናል። ታላላቆችን ማክበር፣ ወላጆችን ማክበርና መታዘዝ፣ ወዘተ ሰፉ ነው። ከሰው አዕምሮ በላይ የሆኑ ጉዳዮች ሲያገጥሙም ሰፉ ናቸው ይባላል። ሰፉ እንዲህ ነው ተብሎ በአንድ ዐረፍተ ነገር የሚበየን ነጠላ ሃሳብ አይደለም። ኦሮሞ አንድን ጉዳይ “safuu dha” (ሰፉ ነው) ሲል በውስጡ ብዙ ትርጉም ያለው ነው።
ሰው ሰፉ የሚለውን ቃል መደነቁን፣ ፍርሃቱን፣ ህመሙን፣ ሃዘኑን አሊያም ሀፍረቱን ለመግለፅ ሊጠቀምበት ይችላል። "Oromoon safuu qaba." የሚባለው ይህን ሃሳብ ለመግለጽ ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሰበር መረጃ
ሰበር ኢራን ወደ እስራኤል የባላስቲክ ሚሳዔሎችን መተኮስ ጀመረች
በመቶዎች የሚቆጠሩ የባላስቲክ ሚሳዔሎች ወደ እስራኤል ተተኩሰዋል
ኢራን እስራኤልን ለመበቀል ወደ ቴል አቪቭ በርካታ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን እና ሮኬቶችን መተኮስ ጀምራለች።
እስራኤል ባሳለፍነው አርብ ሌሊት በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት የሊባኖሱ ሄዝቦላህ መሪ ሼክ ሀሰን ናስራላህን መግደሏ ይታወሳል።
የሄዝቦላህ መሪው ሀሰን ናስራላህ እስራኤል በቤሩት በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸውን አረጋግጦ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱም አይዘነጋም፡፡
ይህን ተከትሎም በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የነገሰ ሲሆን እስራኤል እና ሂዝቦላህ ከአየር ላይ ጥቃቶች በተጨማሪም በእግረኛ ጦር የታገዘ ውጊያ ጀምረዋል፡፡
የእስራኤልን ጥቃት ስታወግዝ የቆየችው ኢራን ዛሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ የባላስቲክ ሚሳዔሎች ወደ እስራኤል ተኩሳለች።
በመላው እስራኤል የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ሳይረኖች እየተሰሙ ሲሆን፤ የፍንዳታ ድምጾች እና በሰማይ ላይ እሳቶችም እየታዩ እየታዩ ነው።
ኢራን ለእስራኤል "የወንጀል ተግባር" ምላሽ ትሰጣለች- የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ኢራን ጥቃት ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ ካደረሰችው የባሰ ሊሆን ይችላልም ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ጦር በእስራኤል ላይ ሊደርስ የሚችልን ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኑን የገለጸ ሲሆን "ኢራን በቀጥታ ለምታደርሰው ጥቃት እና ሊወሰድባት ለሚችለው የአጸፋ እርምጃ የከፋ ሊሆን ይችላል" ሲል ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የእስራኤል ጦር በሶሪያ መዲና ደማስቆ በሚገኘው የኢራን ኢምባሲ ለይ ባደረሰው ጥቃት ኢራን የቀጥታ ጥቃት የፈጸመች ሲሆን ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የሐማሱ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሀኒየህ በቴህራን እያለ በኢራን መገደላቸው ይታወሳል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከሁለት ሳምንታት ጀምሮ እስራኤል በሊባኖስ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ባደረሰችው ጥቃት የሂዝቦላህ ዋና ዋና መሪዎች ተገድለዋል፡፡
የሂዝቦላህ እና ሐማስ ዋነኛ አጋር እንደሆነች የሚገለጸው ኢራን እስራኤልን እንደምትበቀል በተደጋጋሚ ዝታለች፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ሄቦ " የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ፡ የህብር ኢትዮጵያ ድምቀት !
ህብር ተፈጥሯችን ውበታችንም ድምቀታችንም ነው። ኢትዮጵያ በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መስህቦች የታደለች ሀገር ናት።
መልከዓ ምድራችን ጭምር የህብር ማንነታችን ነፀብራቅ ነው:: ከህብረብሔራዊቷ አዲስ አበባ ወደ ሁሉም አቅጣጫ ብንጓዝ የኢትዮጵያን ህብር ስሪት እናገኛለን።
አቅጣጫችን ወደ ጅማ መስመር አድርገን ነፋሻማውን አየር እየማግን በጠዋቱ ስልጣኔም እንደ ወንዙ ጅረት ከፈሰሰበት ከጊቤ ወንዝ አካባቢ ተከስተናል።
የአዲስ ዓመት ብስራት የሆነው መስከረም ወር ተፈጥሮው ልምላሜ ሲሆን የበርካታ የሀገራችን ብሔረሰቦችም የዘመን መለወጫ በዓላት የሚከበሩበት እንደመሆኑ የተለየ ድምቀት አለው።
ከጊቤ ባሻገርም የታሪክ እና የባህል ሀብታም የሆነው በውብ የተፈጥሮ መስህብ የተዋበው የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሄቦ የሚከበርበት ወቅት እንደመሆኑ ይበልጥ ደምቋል።
ጥቅጥቅ ጥብቅ ደኖች ፣ በጥበብ እጆች የተሳሉ የሚመስሉ ውብ ተራራዎችና ኮረብታዎች ፣ ከአዝመራው እሸት ጋር ተደማምሮ መአዛው ያውዳል ።
ሄቦ የብሔረሰቡ ውብ ባህልም ጎልቶ የሚታይበት እንደመሆኑ አካባቢው ተጨማሪ ማራኪ ገፅታ ተላብሶ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች የፌዴራልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም የየም ብሔረሰብ ዞን አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ዞኖች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ለመግለፅ የመጡ እንግዶች እና የበዓሉ ባለቤት የሆኑት የየም ብሔረሰብ ተወላጆች በታደሙበት ባህላዊ ትውፊቱን በሚያጎሉ የተለያዩ ትዕይንቶች እየተከበረ ይገኛል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ ቤት
#aa_prosperity
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዛሬ ማለዳ ከቦሌ ካርጎ እስከ ቡልቡላ አቃቂ ድልድይ ድረስ ተገንብተው ለነዋሪዎቻችን አገልግሎት ክፍት የተደረጉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ጎብኝተናል።
በቦሌ ክፍለከተማ እየተገነባ ያለውን 13 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን የጎበኘን ሲሆን ይህም አራት ዘመናዊ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች፣ ሁለት የህጻናት የመጫዎቻ ሜዳዎች፣ አንድ የስፖርት ሜዳ፣ አምስት ዘመናዊ የህዝብ መገልገያ የጋራ መጸዳጃ ቤቶች፣ ደረጃውን የጠበቀ ሰፊ የእግረኞች መንገድ፣ በከተማው ስታንዳርድ መሰረት የተከናወኑ የህንጻዎች እድሳት፣ ፋውንቴኖች፣ የመዝናኛ ፓርኮች እንዲሁም የህዝብ መናፈሻ ቦታዎች የተካተቱበት ነው።
ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎች በመደገፍ ይህን ስራ ያሳካችሁ የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ ባለሀብቶችን እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎችን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የምናከናውናቸውን ስራዎችን ከነዋሪዎቻችንን ጋር በመተባበር መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Via 👇
ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የታላቅ ወንድሜን የስጋ እረፍት ተከትሎ አጠገቤ ለነበራችሁ ወዳጆቼ በሙሉ ከልብ አመሠግናለሁ። በይበልጥም ደግሞ ከመሀል ከተማ አዲስ አበባ #ሰበታ ድረስ መጥታችሁ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ 🙏🙏🙏
ታዬ፣ ካስሽ፣ ቶማስ፣ ሳራ 🙏🙏🙏
😭😭😭😭😭
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አድሲና ጋር ተወያይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በምግብ ዋስትና ፕሮጄክቶቻችን እና ጥረቶቻችን ላይ ስላለው ሰፊ ትብብር ዛሬ ጠዋት ከጓደኛዬ አኪንዉሚ አድሲና ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዛሬ ከከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ጋር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን ስራን ጎብኝተናል።
አዲስ አበባ ቅድሚያ ትኩረት የሰጣቸውን 16 ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለይቶ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ የሪፎርም እና የተቋም ግንባታ ስራ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል። ከነዚህ ተቋማት መካከል የመሬት ልማት አገልግሎትን ፈጣን፣ ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እንዲሁም ዲጂታላይዝ በማድረግ በኩል የጀመርነዉ ስራ ውጤታማ መሆኑን አይተናል።
በተለይም እስከ ዛሬ ድረስ የተፈጠሩ መብቶችን ወደ ዲጂታል የመቀየር፣ አዳዲስ የተፈጠሩ መብቶችን በግልፅነትና በታወቀ ውሳኔ ብቻ መብት እዲፈጠር የማድረግ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ፋይል በፎርጂድ ተደራጅቶ ሲመጣ ወደ ሲስተም እንዳይገባ የመከላከል፣ በተጭበረበረ እና በህገወጥ መንገድ መብት ፈጠራን የመለየት፣ በህገ ወጥ መንገድ መብት ቢፈጠር እንኳን በቀላሉ ውድቅ የሚሆንበት፣ ለጀርባ ማህተም ተገልጋይ የማይንገላታበት፣ የደብዳቤዎች ስወራን እንዲሁም ከሰው ማህደር ውስጥ ፋይል ማጥፋትና በህገወጥ መንገድ ፋይል የመጨመር እና ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን በሚያስቀር ደረጃ የተሟላ የዲጂታል ስራ እየተተገበረ ይገኛል።
ስለዚህ ውድ ተገልጋዮቻችን ይህ ከፍተኛ እንግልት የነበረበት አገልግሎት፣ እንግልቱ ቀንሶ ዉሳኔ የሚያስፈልገዉ ካልሆነ በስተቀር በያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መገልገል የምትችሉበትን ስርዓት የዘረጋን ሲሆን አገልግሎቱን በመረዳት በህጋዊ መንገድ መገልገል የምትችሉ መሆኑን እገልጻለሁ።
አገልግሎቱን ከዚህ በላይ የላቀ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሲስተሙን እኩል መጠቀም እንዲችሉ እነሱንም የማናበብ ስራ እየሰራን የምንገኝ ሲሆን አሁን የሊዝና የመሬት አገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ሁሉም ክፍያዎች ግለሰብ ጋር ሳይደርስ በባንክ እና ቴሌብር በኩል እንዲከፈል ማድረግ ስለተቻለ ተገልገሉበት።
ይህንን መልካም ጅማሮ ተደራሽ ለማድረግ ይበልጥ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ከኢራን የሚሳኤል ጥቃት በኃላ በቴህራን ጎዳናዎች ከፍተኛ የሰዎች የደስታ ስሜት ታይቷል
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#DV2026
የ2026 የአሜሪካ ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ማመልከቻ ከነገ ጀምሮ ክፍት ይደረጋል።
ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አዘጋጅታለች።
ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ አያስፈልግም።
አሜሪካ በየዓመቱ ከኢትዮጵያ ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) አማካኝነት እንደምትቀበል ይታወቃል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢፌዴሪ መንግስት በካርቱም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር መኖሪያ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አወገዘ።
የኢፌዴሪ መንግስት በቅርቡ በሱዳን ካርቱም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር መኖሪያ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አውግዟል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ሁሉም ሀገራት የዲፕሎማቲክ ሚስዮኖች ግቢን ከጉዳት የመጠበቅ እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ሰራተኞችን ደህንነት የማረጋገጥ ግዴታ እንዳለባቸው በቪየና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ኮንቬንሽን በማያሻማ ሁኔታ መደንገጉን ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉም የሱዳን ኃይሎች ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ደንቦችን ሙሉ በሙሉ እንዲያከብሩና ዲፕሎማሲያዊ ሠራተኞችን ወይም ተቋማትን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጥሪው አቅርቧል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
39ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው ብሔራዊ የመካከለኛ ዘመን 2017-2020 የገቢ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የታክስ ሥርዓቱን ለማዘመን እና ለግል ኢንቨስትመንቱ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የታለመ ሲሆን አጠቃላይ የታክስ ፖሊሲዎችን እና አስተዳደራዊ ሪፎርሞችን እንዲሁም ማሻሻያዎችን ለመተግበር የሚያስችል ነው፡፡ ሰትራቴጂው ከ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተደርጎ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ውሳኔ ካገኘበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ከማልታ ሪፐብሊክ መንግስት እና ከቻድ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የተፈረማቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን ለማጽደቅ የቀረቡ 2 ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ስምምነቶቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ማንኛውም የማልታ ከተማ እና ወደ እንጃሜና ከተማ በ3ኛና 4ኛ ትራፊክ መብት የመንገደኛ እና የጭነት የበረራ ምልልስ ለማድረግ፣ ተወካይ አየር መንገዶችን በሽርክና ለማሰራት፣ በ5ኛ ትራፊክ መብት ወደ ተመረጡ መዳረሻዎች በረራ ለማድረግ የሚያስችል እና አገራችን ከሁለቱ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት፣ ለወጪ ንግድ፣ ለቱሪዝም፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ስምምነቶች ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡
3. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን ለማጽደቅ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የፓሪስ ኢንዱስትሪያዊ ንብረት ኮንቬንሽን በአባል አገራት መካከል ሕብረት በመፍጠር የኢንዱስትሪ ንብረትን ለመጠበቅ፣ የፈጠራ ባለቤትነት፣ የግልጋሎት ሞዴሎች፣ የኢንዱስትሪ ንድፎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ የንግድ ስሞች፣ የምርቶች ምንጭ አመልካች ምልክቶች ለመጠበቅ እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ውድድር ለመከላከል እና ለግብርና እና ሁሉንም የተመረቱ ወይም ተፈጥሯዊ ምርቶች የሚያካትት ነው፡፡ የኮንቬንሽኑ መጽደቅ ሀገራችን ለምታደርገው የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድጋፍ የሚሆን ሲሆን ከአባል ሀገራቱ ለሚነሱ የኢንዱስትሪያዊ ንብረት ጥበቃን ለሚመለከቱ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ለመስጠት ያስችላል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የዓለም አቀፍ ምልክቶችን ከሚመለከተው የማድሪድ ስምምነት ጋር የተዛመደውን ፕሮቶኮል ለማጽደቅ በወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ፕሮቶኮሉ የንግድ እና የአገልግሎት ምልክቶች በአገር ውስጥ ሕግ ከሚደረግላቸው ጥበቃ አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ ምርቶች እና አገልግሎቶች ያላግባብ ለሌሎች ጥቅም እንዳይውሉ በቂ ጥበቃ የሚደረግበትን ሁኔታ የሚፈጥር፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችና አገልግሎቶች እንዲኖሩና የሀብት ምንጭ እንዲሆኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ምክር ቤቱ በፕሮቶኮሉ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
5. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደንብ እና የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች ደንብ ላይ ነው፡፡ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት ለመወጣት፤ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት እንዲሁም ከፓስፖርት የቆይታ ጊዜ ጋር በተያያዘ ያሉ ጥቄዎችን መፍታት እንዲችል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የጀመረውን ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ፣ ሪፎርሙ በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ለማስቻል የአገልግሎቱን ልዩ ባህሪይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በዝርዝር ከተወያየባቸው በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹