#ባሌ #አርሲ የግብርና ስራችን በውጤታማነት ቀጥሏል
Gareen miidiyaa daawwannaa hojii qonnaaf godina Baaleefi Arsiitti bobba'an Oomishni yeroo ammaa jiru imalli birmadummaa nyaataa mirkanaa’aa jiraachuu agarsiiftuu ta'uu ibsan.
Oomishni Qonna Gannaan Godina Arsii fi Baaleetti oomishamaa jiru imalli birmadummaa nyaataa Itiyoophiyaa mirkanaa’aa jiraachuu agarsiiftuu ta'uu Tajaajilli Kominikeeshinii Mootummaa beeksise.
Deeggarsi mootummaan qonnaan bultootaaf taasise Badhaadhina gamhedduu Itiyoophiyaan eegalte mirkanaa’aa jiraachuu mul’iftuu ta’uu Ministir Deetaan Ministira Tajaajila Kominikeeshinii Mootummaa Obbo Kabbadaa Deessisaan ibsaniiru.
Garbuu fi Qamadiin Godina Baalee fi Arsiitti oomishamaa jiran fakkeenya ta’uu himaniiru.
Birmadummaa nyaataa mirkaneessuuf hojiilee bu’aa qabeessa ta’anirratti xiyyeeffachuun hojjetamaa jiraachuu kaasaniiru.
Miidiyaaleen Muuxannoo gaarii kana babal’isuurratti hojjechuu akka qaban hubachiisaniiru.
#Oromia
#Ethiopia
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት የተከበሩ ሳልቫኪር ማያርዲት ለክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል አበረከቱ፡፡
የተበረከተላቸው የፕሬዚደንታዊ የትብብር ሜዳል ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል የሁለቱን ሀገራት የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነት በማጠናከር፣ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን በመከላከል እንዲሁም የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ሪፎርም ሂደትን በመደገፍ የአገልግሎቱን ከፍተኛ መኮንኖች አቅም ለመገንባት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰጡት የትምህርትና ስልጠና እድሎች አስተዋፆ መሆኑን ተገልጿል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱም ላይ የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር አምባሳደር ቾል ማውትን ጨምሮ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ነቢል መሀዲ እና የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ኢንስፔክተር ጀነራል ክቡር አተም ማሮል ተገኝተዋል ፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አሁን ያለው የኢትዮጵያ እውነት ፈጣን እድገት እንጂ ሚሊዮኖች የሚያልቁበት የረሀብ ታሪክ አይደለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ህዳር 17/2017(ኢዜአ)፦ አሁን ያለው የኢትዮጵያ እውነት በአርአያነት የሚጠቀስ ፈጣን እድገት እንጂ ሚሊዮኖች የሚያልቁበት የረሀብ ታሪክ እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
በኢትዮጵያ በ1977ቱ ድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ተቀንቅኖ ድጋፍ የተሰበሰበበት Do they know its Christmas? መዚቃ አሁን ላይ ዳግም መለቀቁ የኢትዮጵያን አሁናዊ የልማት ጉዞ ያላገናዘበ ገጽታን የሚያበላሽ ተረክ መሆኑንም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በ1977 የተከሰተው ድርቅ ያስከተለውን ሰፊ ጉዳት ተከትሎ አይርላንዳዊው ሙዚቀኛ ቦብ ጊልዶፍና መሰል እውቅ ሙዚቀኞች ለኢትዮጵያ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል Do they know its Christmas? የሚል ሙዚቃ አቀንቅነው ከፍተኛ ድጋፍ አሰባስበዋል።
የዚህ የሙዚቃ 40ኛ ዓመት ዘንድሮ የተከበረ ሲሆን በወቅቱ የተሰራው ሙዚቃ ዳግም ተለቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሙዚቃው 40ኛ ዓመት ሲዘከር ሙዚቃው ዳግም እንዲለቀቅ መደረጉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መናገራቸውን "ዘ ታይምስ" የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ሙዚቃው ላይ እንደተገለጸችው ሳይሆን በፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ መሆኗን ገልጸዋል።
ሙዚቀኞቹ በወቅቱ የሰሩት ሥራ የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም ሙዚቃው ዛሬ ላይ ከጊዜው ጋር አብሮ አለመሄዱ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ሙዚቃው የኢትዮጵያን አሁናዊ ሁኔታ ያቃለለና ሰዋዊነትን ዝቅ የሚያደርግ ተረክ የያዘ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ ያለ የኢኮኖሚ ባለቤት፣ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎቿ ከሚጎበኙ ሥፍራዎች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን እንዲሁም በአፍሪካ ትልቁን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እየገነባች ያለች ሀገር ሆና ብትታወቅ ይጠቅም ነበር ብለዋል።
ሙዚቃው አሁን እኛ ለምንፈልገው ኢንቨስትመንት የሚጠቅም አይደለም፤ ድርቅ አሁን ላይ እኛን አንደ አህጉርም እንደ ሀገርም አይገልጸንም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ በረሃብ ልትታወቅ አትችልም ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንፆት ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እና በሌሎች መስኮች እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ዳግም ረሃብ እንዳይፈጠር የሚያደርጉ መሆናቸውንም ጠቅሰል።
ኢትዮጵያ በስንዴ ራሷን ችላለች፤ ሌሎች ምርቶችንም በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት አቅም ፈጥራለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ በአፍሪካ ሊጠቀስ የሚችል የግብርና ዘርፍ አብዮት እያካሄደች መሆኑንም ነው ጠቀላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተናገሩት።
ይህ ሙዚቃ የተለያዩ ወቀሳዎች እየደረሰበት መሆኑንም "ዘ ታይምስ" ጋዜጣ በዘገባው አስነብቧል።
ሙዚቃው አንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 እንደ አዲስ ሲሰራ እውቁ እንግሊዛዊ ኢድ ሺራን በሙዚቃው ከተሳተፉ አርቲስቶች መካከል አንዱ ነበር።
ይሁንና አሁን ላይ ሙዚቃው የአፍሪካን ወቅታዊ ሁኔታ እንደማይገልጽ በሚሰነዘርበት ወቀሳ በወቅቱ በሙዚቃው ተሳትፎ ባላደርኩ እስከማለት መደርሱም በዘገባው ተጠቅሷል።
በመድረክ ስሙ ፉስ ኦ ዲ ጂ የተሰኘው የጋና ሙዚቀኛ፤ ሙዚቃው የተጠቀማቸው የግጥም ስንኞች አፍሪካን በተመለከተ አሉታዊ መልዕክት እንዳላቸው ገልጿል።
ይህም የአፍሪካን ልማት፣ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት አድገት ያቀጭጨዋል ነው ያለው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለትግራይ ክልል 200 አምቡላንሶች ድጋፍ መደረጉን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ
ለትግራይ ክልል 200 አምቡላንሶች ግዢ ተፈፅሞ ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ላይ እንደሚገኙና የተወሰኑትም አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ገልጿል።
ከአሐዱ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ፣ ዲፕሎማሲና የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ መስፍን ደረጄ፤ "የተገዙት አምቡላንሶች ከዚህ በፊት በጦርነቱ ምክንያት የወደሙትን 200 የሚደርሱ አምቡላንሶች የሚተኩ ናቸው" ብለዋል።
በግጭቱ ምክንያት እንደ ቀይ መስቀል ማኅበር ብቻም ሳይሆን አጠቃላይ የአምቡላንስ አገልግሎት ያቆመበት ጊዜ እንደነበር ጠቅሰው፤ "በርካታ የሕብረተሰብ ክፍል በችግር ውስጥ ነበር፤ አሁን ላይ ያንን ችግር ለመቅረፍ አምቡላንሶች ገብተዋል" ብለዋል።
የአምቡላንሶች ግዢ የተፈፀመውም በአንድ የአሜሪካ ባለሀብት በኩል መሆኑን አክለዋል። "ባሳለፍነው ዓመት ከ500 በላይ አምቡላንሶች በመላው ሀገሪቱ ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር" ብለዋል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበርና እህት ማኅበራት አማካኝነትም በሁሉም ክልሎች አምቡላንሶች እንደተከፋፈሉ ያስታወሱት ኃላፊው፤ በቅርብ ጊዜም ሀያ አምቡላንሶች ግዢ ተፈፅሞ ለክልሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሚኒኬሽን ኃፊው "የያዝነውን ዓመት ጨምሮ ባሳለፍነው ዓመት በግጭትና በድርቅ የተጎዱና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና ከአደጋ ስጋት ለማላቀቅ ሰፊ ሥራና ርብርብ ተደርጎ አመርቂ ውጤት አስገኝቷል" ብለዋል።
ማሕበሩ በእንግሊዝና በአሜሪካ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለግጭት፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ የተጋለጡ አካባቢዎች ተለይተው በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤንሻንጉል ክልሎች የጤና ምርመራ ድጋፍ እያከፋፈለ እንደሚገኝ አክለዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ብልፅግና ከፍተኛ የለውጥ መሻት ያለው ፓርቲ በመሆኑ የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓሉ አከባበርም ከሰራው በላይ ለመስራት አጋዥ ነው" - አቶ ሞገስ ባልቻ
ብልፅግና ከፍተኛ የለውጥ መሻት ያለው ፓርቲ በመሆኑ የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓሉ አከባበርም ከሰራው በላይ ለመስራት አጋዥ ነው ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡
"በሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች በድምቀት የተከበረው የብልፅግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል የታለመለትን ተልዕኮ ማሳካቱ ተመላክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር የበዓሉን አከባበር በገመገሙበት ወቅት እንደተናገሩት በታላላቅ ስኬቶችና በአጓጊ ተስፋዎች ታጅቦ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው ፓርቲያችን የበዓሉ አከባበርም ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅና የታለመለትን ግብ ያሳካ መሆኑን ገልፀዋል።
የአሻጋሪ እሳቤዎች ባለቤት የሆነው ብልፅግና ከፍተኛ የለውጥ መሻት ያለው ፓርቲ ነው ያሉት አቶ ሞገስ የአምስት ዓመታት የምስረታ በዓሉ አከባበርም ከሰራው በላይ ለመስራት አጋዥ መሆኑን አስገንዝበዋል።
አመራሩ፣ አባላት፣ ደጋፊዎች እና መዋቅሮች በተቀናጀ መልኩ ለበዓሉ ስኬት የድርሻቸውን መወጣታቸውን ያመሰገኑት ሀላፊው የተፈጠረውን መነሳሳት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለበዓሉ ስኬታማነት የተደራጁ ዓብይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ዕቅዶቻቸውን በማውጣት እና የጋራ በማድረግ በተቀናጀ መልኩ መከወናቸው በቀረበው ሪፖርት የተገለፀ ሲሆን ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሀይምኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙባቸው የውይይት መድረኮች በየደረጃው መደረጋቸው ተጠቅሷል።
የፓናል ውይይቶች፣ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች፣ የጥያቄና መልስ ውድድር፣ የእግር ኳስ ውድድሮች፣ የፎቶ ኢግዚቪሺኖች እንዲሁም ቤት እድሳት፣ ደም ልገሳ፣ ማዕድ ማጋራት፣ የትራፊክ አገልግሎት እና የመሳሰሉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችም በዓሉንም በማስመልከት መከናወናቸውም ተገልጿል።
በመልዕክቶች፣ በዘገባዎች እንዲሁም በዶክሜንተሪዎች አሰባሳቢውን የብሔራዊነት ገዥ ትርክት ለማስረፅ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የበዓሉ አከባበር የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በአግባቡ ለመጠቀም ሊጎለብት የሚገባው አበረታች ጥረት መደረጉም ተወስቷል።
የበዓል ዝግጅቱ የታለመለትን ዓላማ በማሳካቱ ትምህርት የተወሰደበት መሆኑ የተመላከተ ሲሆን በተለያየ አግባብ የድርሻቸውን ለተወጡት ሁሉ ምስጋና መቅረቡን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ 15 ሺህ የአሜሪካ ጦር አባል ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ተገለጸ‼️
ከአንድ ወር በፊት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ጥር አጋማሽ ላይ ስልጣን የሚይዙ ሲሆን ካቢኔያቸውን ከወዲሁ እያዋቀሩ ነው።
የፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጁ ፔቴ ሄግሴትን የመከላከያ ሚንስትር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።
ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው የሚያምኑት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ታይምስን ዋቢ አል አይን አስነብቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።
ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውት ነበር።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና
5ኛ አመት የብልፅግና ፖርቲ የምስረታ በዓል የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዳዋ መታሰቢያ ሙዚየም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ነገ ጠዋት በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ክፍለ ከተማችን እንደ ተለመደው የነቃ እና የደመቀ ተሳትፎ ያደርጋል" - አቶ ዮናስ ስዩም - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
ነገ ጠዋት ከ 12:00 ጀምሮ በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ይከናወናል።
ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቡ በሚሳተፍበት በዚህ ፕሮግራም ላይ ክፍለ ከተማችን አዲስ ከተማ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ የነገዋን ወጋገን እየጠበቀ እንደሚገኝ የክፍለ ከተማችን ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ዮናስ ስዩም ገለፁ።
የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮናስ ስዩም "ነገ ጠዋት በቸርቸር ጎዳና ከ 200ሺህ በላይ ነዋሪዎች በሚሳተፉበት ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ክፍለ ከተማችን እንደ ተለመደው የነቃ እና የደመቀ ተሳትፎ ያደርጋል። ለዚህም አስፈላጊ ዝግጅት ሁሉ ከወዲሁ ተጠናቋል" በማለት ክፍለ ከተማችን የነገ የከተማ አቀፍ ፕሮግራም ድምቀትና ውበት እንደሚሆን ሃሳባቸውን አካፍለውናል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ መቐለ ከተማ ገቡ
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ የተመራ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ መቐለ ከተማ መግባቱ ተሰምቷል።
ልኡኩ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ በትግራይ ክልል ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት ትናንት ትግበራውን የተጀመረው የዲሞቢላይዜሽን ሂደት ይታዘባል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪ ልኡኩ ግንባታው 40 በመቶ የደረሰውንና የገበታ ለሀገር አካል የሆነውን የገርዓልታ ፕሮጄክትንም ተመልክቷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።
ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።
Before officially inaugurating ‘Quality Village ‘today, I had the opportunity yesterday to visit and review the National Quality Infrastructure we have developed.
This critical institution is designed to catalyze the competitiveness of our local products in global markets and enhance our participation in global value chains.
As one of our leading national institutions, it will play a vital role in strengthening our export capabilities and ensuring we remain competitive in the international arena.
Via - Dr. Abiy Ahmed Ali - FDRE PM
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጤናማ ትውልድ ግንባታ አስፈላጊ ነው። በባህር ዳር ቆይታችን በግዙፉ ስቴዲየም ቅጥር ግቢ ውስጥ ኳስ ተጫውተናል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የገበያ ማረጋጋት የጋራ ግብረ-ሃይል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ዙሪያ በመወያየት የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የጋራ ግብረሃይሉ ሰብሳቢ ወ/ሮ አይዳ አወል የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተከፈቱ እሁድ ገበያዎች በማቅረብ ሸማቹ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የኑሮ ውድነቱን በማቃለል የተረጋጋ የገበያ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም የእህድ ገበያን በማጠናከር እንዲሁም ምርቶችን በስፋት በማስገባት የተረጋጋ ገበያ እንዲፈጠር መስራት እንደሚገባ የጋራ ግብረሃይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉትን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ ይመዝገቡ፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#የፎረንሲ_ሳይንስ_ኢንስቲትዩት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት 👌
ዛሬ የፌዴራል ፖሊስ የፎሬንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከልን መርቀናል። ከአንድ አመት ተኩል በፊት እንደ ሀገር የዲኤንኤ ምርመራ ሲያስፈልግ ወደ ውጭ ይላክ ከነበረበት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከዲኤንኤ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲገጥማት በራሷ መስራት ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም ገንብተናል። ይህ በጸጥታ እና ደህንነት ዘርፍ ባለፉት አመታት የሰራናቸው የሪፎርም ስራዎች ውጤት ነው።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር Abiy Ahmed Ali (phd)
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዛሬ ማለዳ ከቦሌ ካርጎ እስከ ቡልቡላ አቃቂ ድልድይ ድረስ ተገንብተው ለነዋሪዎቻችን አገልግሎት ክፍት የተደረጉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ጎብኝተናል።
በቦሌ ክፍለከተማ እየተገነባ ያለውን 13 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን የጎበኘን ሲሆን ይህም አራት ዘመናዊ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች፣ ሁለት የህጻናት የመጫዎቻ ሜዳዎች፣ አንድ የስፖርት ሜዳ፣ አምስት ዘመናዊ የህዝብ መገልገያ የጋራ መጸዳጃ ቤቶች፣ ደረጃውን የጠበቀ ሰፊ የእግረኞች መንገድ፣ በከተማው ስታንዳርድ መሰረት የተከናወኑ የህንጻዎች እድሳት፣ ፋውንቴኖች፣ የመዝናኛ ፓርኮች እንዲሁም የህዝብ መናፈሻ ቦታዎች የተካተቱበት ነው።
ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎች በመደገፍ ይህን ስራ ያሳካችሁ የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ ባለሀብቶችን እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎችን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የምናከናውናቸውን ስራዎችን ከነዋሪዎቻችንን ጋር በመተባበር መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Via 👇
ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"የኢፌዴሪ አየር ኃይል በበርካታ ጀግኖች መስዋዕትነት የፀና ታላቅ ተቋም ነው" -ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ
"የተከበረች ሀገር የማይደፈር አየር ኃይል" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 89ኛውን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ቀንን በማስመልከት ከመከላከያ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይል ተመስርቶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በርካታ ጀግኖች ላባቸውን እና ደማቸውን ከማፍሰስም በላይ ውድ ህይወታቸውን ሰውተው ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር ማድረግ ችለዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አዛዡ በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰውን አየር ኃይል ይበልጥ በማዘመንና ለታላቅ ሀገር የሚመጥን አየር ኃይል ገንብተን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማሸጋገር በሁሉም ዘርፉ ጠንካራ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ነው ያሉት።
በቀጣይም ሰራዊታችን አሁን ተቋሙ እየሰራ ያለውን እና ያስመዘገበውን ውጤት እንደመነሻ በመያዝ በቀጣይ የበለጠ ተግቶ በመስራት የላቀ ውጤት ሊያስመዘግብ ይገባል ሲሉም ሌተናል ጄኔራል ይልማ ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከመፍጠር ጀምሮ የአባላቱን አቅም በስልጠና ለማዳበር ብሎም በራስ አቅም ታላላቅ ስራዎችን እየሠራ የሚገኝ መሆኑን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ በተለይም ምቹ የሥራ አካባቢን በመፍጠርና በሁሉም መስክ ዝግጁ እና ቀልጣፋ የሆነ ሠራዊት በመገንባት ለታላቅ ሀገር የሚመጥን ታላቅ አየር ኃይል እየተገነባ እንደሚገኝም አመላክተዋል።
አየር ኃይል ወቅቱ የሚጠይቀውን የውጊያ መሠረተ ልማት በማሟላት እና የትጥቆቻችንን አቅም በማዘመን የኢትዮጵያን የአየር ክልል ከየትኛውም ጥቃት በንቃት እየጠበቀ የሚገኝ መሆኑን የተናገሩት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ሃይል በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት ለመወጣት በሚያስችል ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን ተናግረዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"መሠል የብልፅግና ፓርቲ ዕሴቶች የሆኑ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ስራዎችን በቀጣይም ተጠናክረው ይቀጥላሉ" - ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ህብረተስብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት #በጎነት_በሆስፒታል በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ተበርክቷል፡፡
በድጋፍ ስጦታው ፕሮግራም የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተገኝተው ህሙማኑን በማጽናናት የቁሳቁስ ድጋፍ አበርክተዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር ህብረተስብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሐብታሟ ቡልቻ በበኩላቸው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በመገኘት ከበጎ ፈቃድ ለጋሾች ያሰባሰቡት፤ ፍራሽ፣ ብርድልብስ፣ አንሶላ እና የንጽህና መጠበቂያ ለተኝቶ ታካሚዎች ህሙማን እንዲውል ታስቦ ለሆስፒታሉ አስተባባሪ አብርክተዋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዴንማርክ አየር ይበክላል በማለት በላም ፈስ ላይ ቀረጥ ልትጥል ነው።
የላም ፈስ አየር ሚቴን የተባለ በካይ ጋዝ ያለው ሲሆን ሚኒስትሮች ከተስማሙ ከሰባት አመት በኋላ ላሞቻቸው በሚያመርቱት ሚቴን ለአንድ ቶን 43 ዶላር ገደማ እንዲከፍሉ መታቀዱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአፍሪካ የሰላም ኮንፈረንስ "የበለጸገና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ፣ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴዎዬ፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የአፍሪካ የሰላም ስብሰባ ሰላም የሰፈነባት፣ የበለጸገችና የለማች አፍሪካን እውን ለማድረግ በጋራ የሚመክሩበት መድረክ ነው።
በመድረኩ ኢትዮጵያ ለዓለምና ለቀጣናው ሰላም ከኮሪያ ዘመቻ እስከ ሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ይቀርባል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ ለመላው የክፍለ ከተማችን የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የከበረ ምስጋናቸውን አቀረበ።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ "ባለፉት ሳምንታት የፓርቲያች 5ተኛ አመት ክብረ በዓልን በክፍለ ከተማችን ደረጃ እና በከተማ ደረጃም በመገኘት በተለያዩ ኩነቶችና የፓርቲያችን እሴቶች ላይ ተመርኩዘን በስኬት አክብረነዋል። ለዚህ ደግሞ መላው የክፍለ ከተማችን የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና የፓርቲያችን ደጋፊዎች አስተዋጽኦ እጅግ የሚደነቅና የሚያስመሰግንም ጭምር ነው" ብለዋል
ኃላፊው አክለውም "በእነዚህ ውጤታማ ስራዎች ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ መላው የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎችን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም ከልብ እናመሠግናለን ለማለት እፈልጋለሁ" ብለው ሃሳባቸውን ቋጭተዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ከመላው ነዋሪያችን፣ አመራራችን፣ ሰራተኞቻችን፣ መዋቅራችን እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሁሉም መስክ የክፍለ ከተማችንን ብልፅግና ማስቀጠሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል" - የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እየተሰሩ ያሉ #ብልፅግና ተኮር ስራዎች ተጠናክረው በመቀጠል ላይ እንደሚገኙ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ገለፁ።
የኮሚቴ አባላቱ "ከመላው ነዋሪያችን፣ አመራራችን፣ ከመላው ሰራተኞቻችን፣ እንዲሁም የበርካታ ስኬቶቻችን ቁልፍ ከሆነው መላው መዋቅራችን ጋር ሲልቅም ከሚመለከታቸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ክፍለ ከተማችን #አዲስከተማ ን የአዲስ አበባ #ብልጽግና እምብርት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ" ብለዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።
ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።
Before officially inaugurating ‘Quality Village ‘today, I had the opportunity yesterday to visit and review the National Quality Infrastructure we have developed.
This critical institution is designed to catalyze the competitiveness of our local products in global markets and enhance our participation in global value chains.
As one of our leading national institutions, it will play a vital role in strengthening our export capabilities and ensuring we remain competitive in the international arena.
Via - Dr. Abiy Ahmed Ali - FDRE PM
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ሁሉ አቀፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪህ ቃል የተዘጋጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ካውንስል ጉባዔ አካሂደናል::
ሌተቀን የከተማቸውን ሰላም በመጠበቅ፣ የጎደሉ በየአካባቢው ያሉ መሰረተ ልማቶችን በህብረተሰቡ ተሳትፎ በመስራት እና በማሰራት በልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ፣ ማህበራዊ ጫናዎችን በመቀነስ እና በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው እንዲሁም በእውቀታቸው ተሳትፎ እያደረጉ ያሉ የከተማችንን ነዋሪዎችን እና የብሎክ አደረጃጀቶችን እስከ አሁን ለሰሩት ስራ እውቅና ሰጥተን የ2017 እቅድ ላይም ተወያይተናል።
ቀና ልብ ያላቸው በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር የበርካቶችን የመኖር ተስፋ ያለመለሙ ስራዎችን ለሰራችሁና ላስተባበራችሁ ሁሉ በነዋሪዎቻችን ስም እያመሰገንኩ የከተማችንን ፈጣን ለውጥ ቀጣይነት ባለው መንገድ ለማስቀጠል ከህብረተሰባችን ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Yaa'ii kaawunsilii hirmaannaa hawaasaa mata duree "Hirmaannaa hawaasa hunda hammataa misooma itti fufaaf" jedhuun qophaa'e geeggeessineerra.
Halkanii fi guyyaan nageenya magaalaasaanii eeguun,bu'uuraalee misooma bakka garagaraatti hir'atan hirmaannaa hawaasaatiin hojjechuun fi hojjechiisuun, hojiiwwan misoomaa irratti dammaqinaan hirmaachuun,dhiibbaalee hawaasummaa hir'isuun fi hojiilee tola ooltummaa hedduurratti qarshii isaaniitiin, humna isaaniitiin akkasuma beekumsa isaaniitiin hirmaannaa taasisaa kan jiran jiraattota magaalaa keenyaa fi gurmaa'insa bilookiilee hojiiwwan hamma ammaatti hojjetaniif beekamtii laannee karoora bara 2017 irrattis mari'anneerra.
Tola ooltota onnee gaarii qaban qindeessuun hojiiwwan jireenyaa hedduuwwaniitti abdii horan kan hojjettan fi kanneen qindeessitan hunduu maqaa jiraattota keenyaatiin isin galateeffataa jijjiirama saffisaa magaalaa keenyaa karaa itti fufiinsa qabuun itti fufsiisuuf hawaasa keenya waliin tumsaan hojjechuu itti fufna.
Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu!
Via ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
"ፓርቲያችን ብልፅግና ባለፉት 5 አመታት የገጠሙትን ችግሮች ወደ ዕድል በመቀየር በተጨባጭ በርካታ ስኬቶችን ማግኘት የቻለ ኢትዮጵያን የመሠለ ህብረ ብሔራዊ ደማቅ ቀለም ያለው ፓርቲ ነው" - ወ/ሮ አይዳ አወል - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለሁለተኛ ተከታታይ ግዜ በ “Arabian Cargo Awards” ምርጥ የአፍሪካ ካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን ተቀዳጀ። የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብሩ በዱባይ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በገልፍ ሀገራት ለሚሰጡ ምርጥ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎቶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ ነው ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹