prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1397

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኢትዮጵያ የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደህንነቱንና ጠራቱን የጠበቀ ዘመናዊ፣ ተደራሽ የውጭ ዜጎች አገልግሎት በመዘርጋት የሀገራችን የውጭ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍስት በመጨመር የተጀመሩትን የልማትና የለውጥ ጉዞ በማፋጠን የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ የበኩሉን ሚና ለመወጣት የሚያስችለውን የሪፎርምና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏት ተፈጥራዊና ታሪካዊ የቱሪዝም እምቅ ሀብቶች እና ኢንቨስትመንት ተጠቃሚ ለማድረግና የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ በሀገር ደረጃ በሚደረግ ጥረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቱሪስት ቪዛ፣ ኮንፈረን ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው የቪዛ ክፍያ ተመን ከ23 በመቶ በላይ እንዲቀንስ መደረጉን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የክፍያ አገልግሎት ደንብ ቁጥር 550/2016 መገንዘብ ይቻላል።

መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው መልካም ጉርብትናና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ካለው ቁርጠኛ አቋም በድንበር አካባቢ ከሚደረጉ ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ መፍቀድ በተጨማሪ መግቢያ ቪዛ ሳይጠየቁ በቀን ማህተም (ያለ ቪዛ ከፍያ) ገብተው ለ90 ቀናት እንዲቆዩ መፍቀዱ ይታወቃል።

በተለይ ከኤርትራ (አስመራ ወደ አዲስ ኣበባ ኢትዮጵያ) የሚመጡ ኤርትራዊያን ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ ማድረጉ በሁለቱም ህዝቦች ያለው ግንኙነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ምን ያህል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ስደተኞች በጥገኝነት እንደሚኖሩ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ፣ ሚዛኑን ባልጠበቀ እና ኃላፊነት በጎደለው አግባብ ተቋማችን ኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውን ሰዎች የተለየ በደል እና አድልዎ እየፈጸመባቸው እንደሆነ፣ ለመውጪያ ቪዛ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ፣ በስደተኝነት የተመዘገቡ ኤርትራዊያን ዲፖርት እየተደረጉ እንደሆነ አድርገው ሲዘግቡ ተስተውሏል።

በርካታ የውጭ ሀገር ሰዎች በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ በመግባትና ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ሀገር ውስጥ ሲቆዩ የሚስተዋሉ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ ሀገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ከመሰማራት ጀምሮ በህገወጥ የማዕድን ዝውውር፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በአደገኛ እፅ ዝውውር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በኮንትሮባንድ፣ በሀሰተኛ ሰንዶች ዝግጅት ወዘተ የመሳሰሉ የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራት ከባድ እና የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ሲፈፅሙ መገኘታቸውን ማርጋገጥ ችለናል።

በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር በመግባትና በህጋዊ መንገድ ገብተው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እነዚህን አካላት ወደ ህጋዊ መንገድ ለማስገባትና ለመመዝገብ በተደጋጋሚ ጥሪ ማድርጉ የሚታወቅ ቢሆንም ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ስርዓቱ የገቡ ግን በጣም ጥቂት ናቸው።
ስለሆነም የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጉላት አስፈላጊ ነው።

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሐሰተኛ ወይም የተጭበረበረ ማንነት በመያዝ ለውጭ ሀገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ተገኝተዋል።

በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች በሻንጣ በማስገባትና በማስወጣት የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር በርካታ ፍልሰተኞችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩና በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።

የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነድና ማንነት በመጠቀም ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሲያከናውኑ እና ከህግ ውጭ ሰነዶችን ሲጠቀሙ መገኘታቸው።
ስለዚህ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የሀገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ይታወቃል።

በመሆኑም ህጉ ተፈጻሚ የሚሆነው በሁሉም የሚመለከታቸው የውጭ ሀገር ሰዎች እንጂ በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው። ስለሆነም ለኤርትራዊያን ዜጎች እንደማንኛውም የጎረቤት ሀገር ዜጎች በቀን ማህተም ገብቶ በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ (90) ቀናት ቆይቶ ለሚሔድ ሰው ምንም ዓይነት የቪዛ ክፍያ እንደማይጠየቅ ለመግለጽ እንወዳለን።

ከተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ቆይተው የሚጣልባቸው ቅጣት ቢሆንም የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎችን ጨምሮ ለጎረቤት ሀገራት እንዲከፍሉት የሚጠየቀው ክፍያ በእጅጉ (በ200 በመቶ) የቀነሰ ሆኖ እያለ ለኤርትራዊያን የተለየና የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ተደርጎ መዘገቡ ከእውነታ የራቀ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተም ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ ጥላ ከለላ መሆን የቆየ ታሪኳና ባህሏ እንደሆነና የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ስደተኞችን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች በጥገኝነት እንድሚገኙ ይታወቃል።

በመሆኑም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከሀገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲከፍል የተረገ ሰው የሌለ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

እውነታው ይህን ሆኖ እያለ በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ያለ አግባብ ክፍያና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ መዘገቡ ከእውነት የራቀ ነው።

የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በመጠበቅ ህጋዊ የውጭ ሀገር ሰዎች እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ ለሚሰራው ስራ ላይ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችን እያቀረብን በተለይ ሚደያዎች ሚዛናዊ በመሆን የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በጠበቀ መልኩ አወንታዊ ሚና እንዲወጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በአዲስ አበባ ከተማ የፅንፈኛው የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በተደረገባቸው ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለፀ።

በሽብር ወንጀል የተጠራጠሩት አራቱ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ሊውሉ የቻሉት በአዲስ አበባ ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ከፅንፈኛው የሽብር ቡድን የወሰዱትን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ 120 የክላሽንኮቭ ጥይት እና ኤፍ ዋን ቦንብ ይዘው ሲንቀሳቀሱ እንደሆነ ነው ፌዴራል ፖሊስ ባወጣው መረጃ ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ጠንካራ ክትትል ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍጅ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የምርመራ ቡድኑ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሕብረተሰቡ እስከአሁን እያደረገ ላለው ተሳትፎ ምስጋና እያቀረበ፣ ተመሳሳይ የወንጀል ተግባር ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የአፍሪካ መዲና እና የፅናት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ ዘመናዊነቷ ጎልቶ እየታየ ነው" - የደቡብ አፍሪካው ምሁር

በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቡሳኒ ንግካዌኒ ዴይሊ ማቭሪክ ለተሰኘ በደቡብ አፍሪካ ለሚዘጋጅ መጽሔት እንዳሉት የአፍሪካ መዲና እና የፅናት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ ዘመናዊነቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጎልቶ እየታየ ነው።

ቡሳኒ ንግካዌኒ አዲስ አበባ እንደ ደርባን፣ ሉዋንዳ፣ ሞምባሳ እና ኪንሻሳ ላሉ ከተሞች የልማት እና የዕድገት ምልክት እየሆነች መምጣቷን ባሰፈሩት ትንታኔ ገልጸዋል።

በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን በአድናቆት እንደሚያዩ የገለጹት ምሁሩ፣ በፈተናዎች ውስጥ ማደግ፣ በተቃርኖዎች መካከል መታደስ የሚታይባት እንደነ ካይሮ እና ኬፕታውን ዕድገት እና ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ያለች ከተማ ናት ብለዋል።

የአዲስ አበባ ለውጥ ጎልቶ የሚታይ መሆኑን እማኝነታቸውን ያስቀመጡት ቡሳኒ ንግካዌኒ፣ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከቀያቸው መለወጥ ጋር በተያያዘ በዋጋ ንረት እና በትራንስፖርት እጥረት እንዳይቸገሩ በማድረግ ለውጡን በስኬት እየመራች መሆኑን መታዘባቸውን ነው የገለጹት።

መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት እና በመሠረተ ልማት ግንባታው ከተማዋ ሌላ ማራኪ ገፅታ እንድትላበስ እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

ብልህ እና ታታሪ የሆነው የከተማዋ አስተዳደር በመዲናዋ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ከንቲባ ጽ/ቤት ያለው መንገድ ፅዳቱን የጠበቀ እና በሥርዓት የተሰደረ እንዲሆን መደረጉን መታዘባቸውንም ጠቁመዋል።

ከእያንዳንዱ አስፋልት ሥር አዳዲስ የውኃ ቱቦዎች እና የፋይበር ኦፕቲክ ኬብሎች መዘርጋታቸውን አመልክተው ይህም የከተማዋን ዕድገት ቀጣይነት ያመለክታል ብለዋል።

የከተማዋን ነዋሪዎች፣ የባንኮች እንዲሁም የኤምባሲዎችን ድንበር እና ግድግዳ በመግፋትም ጭምር እየተገነባ ያለው የአስፋልት መንገድ የትራፊክ መብራቶች እና አደባባዮች የተካተቱበት፣ ከመኪና በተጨማሪ የሳይክል እና የእግረኛ መንገድ ያሉት መሆኑንም መመልከታቸውን ነው ሐሳባቸውን ያሰፈሩት።

የአዲስ አበባ የዕድገት መሠረት የሆኑት ነዋሪዎቿ መሆናቸውን የሚገልጹት ምሁሩ፣ የመዲናዋ ጎዳናዎች የደከመ ጉልበትን የሚያበረቱ፣ ሕይወት የሚዘሩ መሆናቸውን መስክረዋል።

እንደ ስሟ አዲስ የትውልድ ሀገር ልትሰኝ የምትችልም ሆናለች ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለልዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ትምህርት ሚኒስቴር የፕሮፌሰርነት እድገት በጊዚያዊነት መታገዱን ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከላከው ደብዳቤ ተመልክተናል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Nageenyi bu’uura waan hundaati!

Garaagarummaa siyaasaa mariidhaan hiikuudhaan nageenya waaressuuf murteessuun ammayyummaadha!
Godina shawaa Kaabaa Aanaalee garaa garaatti walii galtee Mootummaafi WBO gidduutti taasifame bu’uura godhachuun miseesonni WBO karaa nagaan galaa jiru.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ለሚደረገው ምርጫ ሦሥት እጩዎች ቀርበዋል፡፡ እጩዎቹም በነገው ዕለት ክርክር ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ይህንን ታላቅ አህጉራዊ ሁነት በቀጥታ ያስተላልፋል፡፡ 

እጩዎቹም 👇

* የኬንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ

*  የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሀሙድ አሊ የሱፍ

*  የቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ጀምስ ናቸው

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የውጭ ዲፕሎማሲያችን ሌላኛው ስኬት
በመርህና በመሪ የፀና ጉርብትና
እውነት አሸነፈች
ጥበበኛና ብልህ መሪ

አቶ ሞገስ ባልቻ
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት በዘመቻ መልክ መስጠት መጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት እድሜቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕጻናት በሙሉ ከዛሬ ታሕሳስ 03 እስከ 06/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 4 ቀናት ቤት ለቤት፣ በትምህርት ቤት፣ በማቆያ እና በማሳደጊያ ቦታዎች እና በሌሎች ሕጻናት በሚገኙበት ሁሉ በአፍ ጠብታ ክትባቱ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የፖሊዮ በሽታ የሕጻናትን እግር እና እጅ ጡንቻ በማልፈስፈስ ለሽባነት እና ለከፋ የጤና ችግር የሚዳርግ በመሆኑ፤ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናትን ከዚህ በፊት ቢከተቡም ባይከተቡም እንዲያስከትቡ ቢሮው ጥሪውን አቅርቧል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሰላም ደማቅ ቀለሞች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዚደንት በቱርክ ያደረጉት ስምምነት በምስል 🙏

🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ሶማሊለንድ ፤ ሀርጌሳ ገብተዋል።

አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ለተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በአቶ ሙስጠፋ የተመራውን ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋቸዋል።

ልዑኩ በሀርጌሳ ቆይታው ተመራጩ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አቶ አብዱረህማን መሀመድ አብዱላሂ በዓለ ሲመት ላይ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሊ  ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሊ (ዶ/ር) በቱርክዬ አንካራ የተደረገላቸው አቀባበል በከፊል እነሆ ...

🇪🇹 🇹🇷 🇪🇹 🇹🇷 🇪🇹 🇹🇷 🇪🇹 🇹🇷🇪🇹 🇹🇷

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እሕመድ እና ልዑካቸው ዛሬ ከቀትር በኋላ አንካራ ቱርክ ገብተዋል። ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጽሕፈት ቤታቸው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed and his delegation arrived in Ankara, Turkey, this afternoon. The Prime Minister was later welcomed at the Presidential Palace by President Recep Tayyip Erdoğan where the two leaders then held a bilateral meeting accompanied by their respective delegations.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የቀድሞዋ ካዛንችስ ወደ አዲስ ገፅታ ጉዞ …

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

9 የመንግስት ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት እና የደህንነት ስራን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ። የትብብር ስምምነቱ ብሄራዊ ደህንነትን ብሎም ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ እንደሆነ ተመላክቷል።

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች ጊዜ ቆጣቢና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ትራንዚት የሚያደርጉ ተጓዦች እግረ መንገዳቸውን በኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ እና ሰዉ ሰራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ዕድል ይፈጠራልም ተብሏል።

ኢትዮጵያ ያላትን ድንበር በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ በመጠበቅ ህገወጦች በአንድ የትራንስፖርት አማራጭ ገብተው በሌላ አማራጭ እንዳሻቸው መውጣት እንዳይችሉ በማድረግ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያስችል ቅንጅታዊ አሰራርን እንደሚፈጠርም ተጠቁሟል።

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር፣ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ኢንፎርሜሽን እና መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬይሽን ባለስልጣን፣ አርቲሻል ኢንተለንጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናቸው ስምምነቱን የፈረሙት።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ክፍት የሆኑ የማንሆል ክዳኖች እየተጠገኑ ነው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአስፋልት መንገድ ጥገና ስራ ጎን ለጎን በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሆል ክዳኖች በመለየት የጥገና ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ አስኮ፣ አዲስ ሰፈር፣ ብርጭቆ ኮንደሚኒየም እና ከኮልፌ 18 መዝናኛ በኢትዮ ጠቢብ እስከ ኪዊንስ ሱፐር ማርኬትአካባቢ የሚገኙ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተጎዱና ክፍት የሆኑ የውሃ መፋሰሻ መስመር ክዳኖች ተጠግነዋል፡፡

የጥገና ሰራው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑትን ሙሉ በሙሉ በአዲስ የመተካት እና እድሳት የሚያስፈልጋቸውን ደግሞ መልሶ በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡

በቀጣይም ክፍት የሆኑ እና በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የማንሆል ክዳኖች የመጠገንና የመቀየር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የማንሆል ክዳን የድሬኔጅ መስመሮች የዝናብ ውሃን በአግባቡ እንዲያስተናግዱ እና የመዲናዋ ጎዳናዎች ውብና ጽዱ ሆነው ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል በመሆኑ ሕብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆነውን መንገድ እና የመንገድ አካላትን በባለቤትነት ስሜት ከጉዳት እንዲጠብቅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ለጥንቃቄም ለመረጃም እንዲረዳ ያህል

ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸው የግል ኮሌጆች ስም ዝርዝር ይፋ ሁኗል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አሜሪካ ኢትዮጵያና ሶማሊያ ያደረጉትን ስምምነት እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡

አሜሪካ በትናትናው ዕለት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት የሀገራቱን ሉዓላዊነት በጋራ ጥቅሞች ላይ የሚደረግን ትብብር መሰረት ያደረገውን ስምምነት እንደምትደግፍ ገልጻለች፡፡

በዚህም ሂደት ላይ ጉልህ ሚና የተጫወተውን ቱርክን አመስግናለች፡፡

የሶማሊያን የግዛት አንድነት በማክበር ለጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ኢትዮጵያ አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን ሚያስችለውን ተግባራዊነት እንጠብቃለን ብላለች፡፡

ቀጣይነት ያለው ውይይት እና ተሳትፎ ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የወደፊት መረጋጋትና ብልጽግና አስፈላጊ መሆናቸውንም አሜሪካ ጠቁማለች፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በጋራ የጸጥታ ጉዳዮች በተለይም አልሸባብን በመዋጋት ላይ ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩ እናበረታታለን ለች አሜሪካ ፥ ከሁለቱም ሀገራት ጋር ያለኝን የጠበቀ የሁለትዮሽ ትብብር እቀጥላለሁ ብላለች።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ በኢትዮዽያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት ቼይ ሃይ እና የሲጂሲኦሲ ግሩፕ (CGCOC group) በተገኙበት የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን በፍጥነት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ጋር ተወያይተናል::

የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት በ2008 ዓ.ም ከኤግዚም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ይገነባል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ብድሩ እስከ ዛሬ ባለመለቀቁ ምክንያት ሳይጀመር በመዘግየቱ ከተማው አስተዳደር በራሱ በጀት ለመገንባት ወስኗል ።

በከተማዋ ያለውን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም የከተማ አስተዳደሩ በራሱ በጀት ለመገንባት ዛሬ ከቻይና ኤምባሲ እና ከ‍ኮንትራክተሩ ሲጂሲኦሲ ግሩፕ ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል::

የከተማችንን የውሃ አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ከፍተኛ በጀት መድበን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን የገርቢ መጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታም ሲጠናቀቅ ይህንን ጥረታችንን ይበልጥ ውጤታማ እንደ ሚያደርግ እና ያለብንን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ይበልጥ እንደሚፈታ እናምናለን::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

Har'a Itoophiyaatti Ambaasaaddara Chaayinaa kan ta'an Chey Hay fi garee CGCOC irraa kan irratti argaman ijaarsa piroojektii hidha bishaan dhugaatii Garbii saffisaan eegalchiisuun karaa danda'amu irratti mari'anneerra.

Piroojektiin hidha bishaan dhugaati garbii bara 2008 deeggarsa baankii EXZIM irraa argamuun ijaarama jedhamee kan karoorfame ta'uyyuu liqichi hamma ammaatti sababa gadi hin dhiifamaniif osoo hin eegalamin turuusaatiif bulchiinsi magaalaa baajata isaatiin ijaaruuf murteesseera.

Fedhii fi dhiheessii bishaanii magaalattiin qabdu guutuuf bulchiinsi magaalaa baajata isaatiin ijaaruuf har'a Imbaasii Chaayinaa fi garee kontiraaktaraa CGCOC waliin waliigalterra geenyeerra.

Hirdhina dhiheessii bishaanii magaalaa keenyaa hambisuuf baajataa guddaa ramadnee hojjechuu irratti kan argamnu yemmuu ta'u ijaarsi Piroojektii hidha bishaan dhugaatii Garbii yemmuu xumuramu dadhabbii keenya kana daran bu'a qabeessa akka taasisuu fi fedhii fi dhiheessaa bishaanii nurra jiru caalmaan akka furu ni amanna.

Waaqni Itoophiyaa fi Uummata Ishee Haa Eebbisu.

Today, we held a productive meeting with Mr. Chen Hai, Chinese Ambassador to Ethiopia and CGCOC Group to expedite the construction of the Gerbi Dam Water Supply Project.

While the initial plan to construct the Gerbi Dam in 2016 GC with funding from the Export-Import Bank of China not yet released, the City Administration has now decided to finance and undertake this crucial project.

To bridge the significant gap between water supply and demand in our city, a substantial budget has been allocated. The City Administration believes that the construction of the Gerbi Dam is a key step towards addressing the pressing water supply problem in the City.

May God Bless Ethiopia and its People!

ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሞባይል ባንኪንግ የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች መከላከያ መንገዶች

● ሞባይላችንን /የመገልገያ መሳሪያችንን/ መቆለፍ፡- በተለይም ግብይቶች በምንፈፅምበት ግዜም ይሁን በማንኛውም ግዜ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መያዝ፤ በጠንካራ የይለፍ ቃል ወይም በባዮሜትሪክ አማራጮች መቆለፍ፤

● ግብይቶች /ክፍያዎች/ ስንጨርስ ከክፍያ መተግበርያዎች (Web Pages) ዘግተን በመውጣት የይለፍ ቃላችን እነሱ ላይ ሴቭ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፤

● የባንክ ሒሳቦቻችን ሁኔታ (ታሪክ) በየግዜው መፈተሽ/መመልከት (Statements)፤

● ባለ ሁለት ደርዝ ማረጋገጫ /Two-factor or Multi-factor Authentication/ ተግባራዊ ማድረግ፤ ወደ ባንክ ሒሳብዎ ከመግባትዎ በፊት የአንድ ግዜ ይለፍ ቃል /SMS OTP/ ወደ ስልክዎ ወይም የኢሜይል አድራሻ እንዲላክ ማድረግ፤

● የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎቻችንን ማዘመን፡- የሞባይል ባንኪንግ ይሁኑ ሌሎች ሞባይላችን ውስጥ የምንጭናቸው መተግበሪያዎች ወቅታዊ ዝማኔዎች ማድረግ እንዲሁም ከታማኝ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፤ ካልሆነ ማልዌሮች ሊይዙ እና ሚስጥራዊነት ያላቸው መረጃዎች ለመመንተፍ ሊያመቻቹ ይችላሉ፤

● ሞባይላችንን ላለመጠቀም ወይም ለሌላ ሰው ለመስጠት ስንወስን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያውን እና ታሪኩን ማስወገድ እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን ማጥፋት፤

● የአሳሽዎችን ካች /cache/ በመደበኛነት ማፅዳት፡- አንዳንድ ሞባይል ስልኮች እና ታብሌቶች የባንክ መረጃዎን ሊይዙ የሚችሉ የድረ-ገጾች ቅጂዎችን ያከማቻሉ ይህን አለመፍቀድ፤
● ስልካችንን ለመክፈት እና የባንክ መተግበሪያዎችን ለመክፈት የተለያዩ የፒን ቁጥሮችን (የይለፍ ቃል) መጠቀም፤

● ሀሰተኛ የክፍያ ማረጋገጫ የጽሑፍ መልዕክቶችን መጠንቀቅ፡- (Fake payment confirmation text messages /Payment Successful Messages)- የሽያጭ ክፍያ በሚፈፀምበት ግዜ ገንዘቡ ወደ ባንክ ሒሳባችን በትክክል መግባቱ/አለመግባቱ ወደ ባንክ ሂሳባችን በመግባት ማረጋገጥ። ክፍያ እንደተፈፀመ በማስመሰል ተመሳስለው የተሰሩ መልእክቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ መጠንቀቅ፤ ለምሳሌ ሰዎች እቃ ከኛ ሲገዙ ክፍያው በባንክ/ሞባይል ክፍያ መንገድ እንደከፈሉ በማስመሰል የእነዚህ የክፍያ ማረጋገጫ መልእክቶችን በማስመሰል ለማጭበርበር ሊሞክሩ ይችላሉ በመሆኑም መልዕክቶቹ ትክክለኛ መሆናቸዉን ማረጋገጥ፤

● ደንበኞች ግብይት/ክፍያዎች በሚፈፅሙበት ግዜ ወድያውኑ ክፍያ/ግብይት እንደፈፀሙ የሚያሳውቁ መልእክቶች ወደ ስልካቸው እንደደረሳቸው ማረጋገጥ፡ እነዚህ መልእክቶች በተለያየ ምክንያቶች እክል ገጥሟቸው ሳይደርሱ ሲቀሩ የባንክ አካውንታቸው በመግባት ሒሳብዎን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል:: በሌላ አባባል የባንክ ሂሳቦችዎን እና ግብይቶችዎን ገብተው እስካልፈተሹ ድረስ የክፍያ ማረጋገጫው የሚገልፅ የጽሑፍ መልእክት ሁሉ ህጋዊ/እውነተኛ ነው ብለው አያስቡ::

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በመንገዳችን ላይ
አዲስ አበባ
ቦሌ ቦሌ ቦሌ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያን ስኬታማና ጠንካራ የዲፕሎማሲ ውጤት እንድታመጣ ያስቻላት ለትብብር እና ለመግባባት ሁሌም ዝግጁ የመሆን መርህን በመከተሏ ነው!!

ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሠረት የሆነው ስኬታማና ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገራችንን ሉዓላዊነት ያስከበረና የመልማት ፈላጎትን እያሳደገ የመጣ ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እውን ያደረገ ነው ።

ኢትዮጵያ በነበራት መልካም የውጭ ግንኙነት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ መልካም ስም እንዲኖራት አስችሏታል።

ይህ የመርህ ወጥነት በመንግሥታት መቀያየር ውስጥ ነባሩን ጥሩ ስራ በማስቀጠል እና በአዲስ ጅምር መካከል ሚዛናዊነት የነበረው የውጭ ግንኙነት ልምድ እንዲኖረን አድርጓል። በዚህም ምክንያት የውጭ ግንኙነታችን የብክነት ታሪክ ሳይሆን መደመር የታየበት የክምችት ውርስ ይዞ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት በዋናነት በመነጋገርና በመተባበር ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ነው።

ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላትና የገናና ሥልጣኔ ባለቤት ነበረች። ቅኝ ግዛትን የመከተችና በድል የመለሰች የዓድዋ ድል ባለቤት የሆነች ሀገርም ናት። ይህ ታሪኳም በመግባባት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ለመፍጠር ያላትን ተሰሚነት ከፍ እንዲል አስችሏል።

ኢትዮጵያን ስኬታማና ጠንካራ የዲፕሎማሲ ውጤት እንዲመጣ ያስቻላት ለትብብርና ለመግባባት ሁሌም ዝግጁ የመሆን መርህ ነው። ለዚህ ማሳያ ደግሞ አንዱ በአሁኑ ሰዓት ከጎረቤት አገር ከሶማሊያ ጋር በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር በሰላም መጠናቀቁ ተጠቃሽ ነው።

ኢትዮጵያ በተሻለ የዲፕሎማሲ ውጤት ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናን አረጋግጣ የልዕልና ጉዞዋን እውን ታደርጋለች!!

#aa_prosperity
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሶርያው በኤርትራ ይደገማል ሲሉ ቲቦር ናጊ ተናገረ

ይህን ያሉት ከዚህ ቀደም የአሜሪካ አምባሳደር በመሆን በኢትዮጲያና በጊኒ ያገለገሉት ዲፕሎማቱ ቲቦር ናጊ ሲሆኑ አነጋጋሪውን አስተያየት በኤክስ ገፃቸው ላይ አጋርተዋል።

"የባሽር አል አሳድን ውድቀት ሶርያውያን በደስታ እንዳከበሩት ሁሉ አምባገነኑ ኢሳያስ አፍወርቂ ሲወድቅም ኤርትራውያን በተመሳሳይ መንገድ ደስታቸውን ይገልፃሉ ሲሉ ዲፕሎማቱ በኤክስ ላይ ፅፈዋል

አክለውም "ከጥቂት ቀናት በፊት የባሽር አልአሳድ ደጋፊዎች የነበሩት አሁን ስርዓቱን ሲቃወሙት እንደነበር የተናገሩ ሲሆን፤ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው ይህ በኤርትራ ላይ ይደገማል ሲሉ የአሜሪካ መንግስትን ለበርካታ ዓመታት ዲፕሎማት ሆነው ያገለገሉት ቲቦር ናጊ ተናግረዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"... ጠላት አይኑ እያየ፣ ጆሮው እየሰማ..." የሚለውን መዝሙር ድምፁን ከፍ አድርጉልኝማ? Pls ጨምሩበት? አሁንም? ትንሽ ከፍ? ከፍ? ኸረ ከፍ አድርጉት???
👇👇👇 🇪🇹🇸🇴 👇👇👇
በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት ተጠናቅቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ግብዣ ዛሬ ምሽት በአንካራ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ውይይቱን ካደረጉ በኋላም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። 

መሪዎቹ በመግለጫቸውም፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ከፍተኛ አስታዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡  

የኢትዮጵያ የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡
 
ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በበኩላቸው፤ የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት አይዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል፡፡ 

ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት ሰነድ ትብብርን፣ የኢኮኖሚ እድገትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴🇸🇴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሰላም ደማቅ ቀለሞች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዚደንት በቱርክ ያደረጉት ስምምነት በምስል 🙏

🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴🇪🇹🇸🇴

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ፌስቡክ የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ‼️

ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ተጠቃሚዎች ችግር እንዳጋጠማቸው በተለያየ ሁኔታ ሲገልፁ ተስተውሏል።

በሜታ ኩባንያ ስር የሚንቀሳቀሰው የፌስቡክ መተግበሪያም የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው በራሱ ገፅ ላይ ለተጠቃሚዎቹ ይፋ አድርጓል።

ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለፀው ተቋሙ፤ ለተፈጠረው ችግር ተጠቃሚዎቹን ይቅርታም ጠይቋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Ibsa Gaddaa

Waajjira Paartii Badhaadhinaa Damee Oromiyaa irraa

Hundeessitoota Dhaabbata Diimokiraatawaa Uummata Oromoo keessaa tokko kan turan qabsaa’aan gameessi Obbo Ibraahim Malkaa addunyaa kanarraa du’aan boqachuu isaaniitiin Paartiin Badhaadhinaa Damee Oromiyaa gadda itti dhagahame ibsa.

Imala qabsoo uummata Oromoo wal harkaa fuuchaa dhalootaatiin har’a qaqqabe keessatti ashaaraa guddaa kaa’anii kan darban Obbo Ibraahim Malkaa bara 1952 Godina Shawaa kibba Lixaa Magaalaa Diilallaatti kan dhalatan yemmuu ta’u, dhiibbaa fi cunqursaa uummata Oromoorra qaqqabaa ture falmuudhaan umrii dargaggummaa isaaniitiin dirree qabsootti makamanii sirna mootummaa abbaa irree Dargii kuffisuudhaan qabsoo uummataa gara boqonnaa haaraatti ceesisuudhaaf sochii godhame keessatti gahee ol’aanaa kan bahatanidha.

Gaaffileen bu’uuraa uummanni Oromoo kaasaa ture deebii argatee qabsoon uummatichaatis fuula duratti tarkaanfatuuf hawwii fi mul’ata guddaa qabatanii qabsoo yerochi gaafatu kutannoo cimaadhaan kan gaggeessan Obbo Ibraahim Malkaa Dhaabbatni Diimokiraatawaa Uuummata Oromoo akka hundaahuuf gahee isaanii bahachuudhaan qabsoo bu’aa bahiiwwan hedduu cehee injifannoo har’aatiif qaqqabe keessatti gumaacha seenaan yaadatu taasisanii darbuu kan danda’anidha.

Qabsoon uummataa sadarkaa har’a irra jirutti tarkaanfatee daandiin injifannoof milkaahinaa akka saaqamuuf gaheen qabsaahota kaleessaa ol’aanaa ta’uu kan hubatuufi beekamtiis kennu Paartiin Badhaadhinaa du’aan boqachuu Obbo Ibraahim Malkaatiin gadda itti dhagahame ibsaa maatii fi firoottan isaaniitiif jajjabina guddaa hawwa.

Waajjira Paartii Badhaadhinaa Damee Oromiyaa

OPP

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የተከፈተው የሠላም በር 👆👆👆

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

🤔 የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ቢትኮይን ወደ 1 ሚሊዮን ዶላር ያድጋል ሲል ተደምጧል 🤔

አባቱ አሜሪካን የአለም ክሪፕቶ ዋና ከተማ እንደሚያደርጋት ያምናል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Nageenya keenya, aadaa fi duudhaa keenyaan!

Aadaa fi duudhaaleen bu’uura sirna gadaa ta’an lammiilee gidduutti tokkummaa fi jaalala cimsuudhaan gamatti nageenya waaraa mirkaneessuuf shoora guddaa ta’e qabu.

Rakkoolee jiran marii fi marabbaadhaan furuu, nageeya labsuu fi waliin jirrenya jabeessuudhaan qormaatilee imala keenyaa ta’an hundaaf furmaata kaa’uuf aadaa fi duudhaalee gaarii qabnutti qixaan gargaaramuun murteessaadha.

Misooma biyyaa dhugoomsuu fi galmoota imala badhaadhinaa fiixaan baasuudhaaf bu’uura kan ta’e nageenyi, qabeenya waloo tumsaa fi hirmaannaa lammii hundaa gaafatudha.

Rakkoolee nageenyaa kallattii garaa garaatiin mul’atan bu’uuraan furuudhaan nagaa waaraa bu’uuressuudhaaf qaama biraa eeggachuu caalaa, duudhaalee gaggaarii furtuu rakkoolee maraa ta’an waan qabnuuf isaanitti qixaan dhimma bahuu fi hojiirra oolchuun barbaachisaadha.

Aadaa fi duudhaalee keenyaan nageenya keenya waaressuuf jalqabbiiwwan gaarii eegalaman caalmaatti itti fufsiisuudhaan mul’ata qabanne galmaan gahuuf gahee nurraa eegamu haa bahannu.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የፌደራል እና የክልሉ የአመራሮች ቡድን በምስራቅ ባሌ የልማት ሥራዎችን እየጎበኘ ነው፡፡

ቡድኑ ጉብኝቱን የጀመረው በዳዌ ቃቸን ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን የዌብ ግድብ ፕሮጀክት በመመልከት ነው፡፡

የአመራሮቹ ቡድን በምስራቅ ባሌ እየተከናወኑ የሚገኙ የግብርና እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…
Subscribe to a channel