prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1397

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ ለመሰልጠን ተመዝግበዋ? ካልተመዘገቡ ዛሬውኑ በመመዝገብ የዚህ ታላቅ እድል ተቋዳሽ ይሁኑ!!

በርካታ ኢትዮጵያውያን የ “አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ'' ስልጠናዎችን በመሰልጠንና የዲጂታል ክሕሎታቸውን በማዳበር ለአሁናዊና ለመጪው ጊዜ እራሳቸውን ብቁና ዝግጁ አድርገዋል፡፡ እርስዎስ “የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ” ለመሰልጠን ተመዝግበዋ? ካልተመዘገቡ ዛሬውኑ በመመዝገብ የዚህ ታላቅ እድል ተቋዳሽ ይሁኑ!!
በመርሃ ግብሩ መሰረት እ.ኤ.አ በ2026 አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክሂሎት የሚያስጨብጥ ይሆናል።

ለመመዝገብ 👇
http://www.ethiocoders.et

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Anis Waa'ee Biyya Kiyyaa Nan Mari'adha!!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ቲክቶክ የሚታገድበት ቀን መቅረቡን ተከትሎ ትራምፕ ዋና ሥራ አስኪያጁን ሊያናግሩት ነው!

የግዙፉ ማኅበራዊ ሚድያ ቲክቶክ ሥራ አስኪያጅ ሹ ዚ ቺው ሰኞ ዕለት ትራምፕን በማራላጎ ያገኛቸዋል ተብሎ ተጠብቆ እንደነበር የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

እየተገባደደ ባለው የአውሮፓውያኑ መባቻ የወጣው ሕግ ቲክቶክ ካልተሸጠ በሚመጣው ጥር አሜሪካ ውስጥ ጥቅም እንዳይውል ይታገዳል ይላል።
የቲክቶክ ባለቤት ቻይናዊው ባይትዳንስ የተባለ ኩባንያ ነው። ኩባንያው ለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባስገባው ይግባኝ ዕገዳው እንዲዘገይ ጠይቋል። አሜሪካ ቲክቶክን ለማገድ የወሰነችው ባይትዳንስ ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት አለው በሚል ምክንያት ነው። ቲክቶክም ሆነ ባይትዳንስ ግን ይህንን ውንጀላ ያስተባብሉታል።

በአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የፀደቀው ሕግ "የዩናይትድ ስቴትስን ብሔራዊ ደኅንነት በውጭ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ካሉ መተግበሪያዎች ለመጠበቅ" የወጣ ነው ይላል። ቲክቶክ ከታገደ ፌስቡክ ይበለፅጋል ይላሉ። ፌስቡክ በ2020 ምርጫ ለመሸነፋቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ ነው ትራምፕ የሚያምኑት።

ኩባንያው ቲክቶክን አሜሪካ ውስጥ ካሉ "እጅግ አስፈላጊ የንግግር መድረኮች" አንዱ ነው ያለው ሲሆን ይህንን ማገድ ለኩባንያውም ሆነ ለተጠቃሚዎቹ "ትልቅ ጉዳት" መሆኑን ተናግሯል።ትራምፕ ሰኞ ዕለት በነበራቸው አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ አስተዳደራቸው "ቲክቶክ እንደሚያጤነው" ተናግረዋል።

"እኔ ለቲክቶክ የተሻለ ቦታ አለኝ። ምክንያቱ 34 በመቶ ወጣቶች ድምፃቸውን ለኔ ሰጥተዋል" ብለዋል። "አንዳንድ ሰዎች [ለማሸነፌ] ቲክቶክ ትልቅ አስተዋፅፆ ነበረው ይላሉ። ቲክቶክ ትልቅ ተፅዕኖ አለው።"

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፌደራል የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት የሆኑ ክቡራን ሚኒስትሮች በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በእርሻ ስራ ላይ...

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዘመኑን የዋጀ፣ ሀገራዊ መሰረት ያለው ትውልድ አሻጋሪ እሳቤ፡ መደመር!

የኢትዮጵያን ልዕልና ለማረጋገጥ ቅንነት የተላበሰ፣ ከህፀፅ የራቀ፣ የኢትዮጵያን ህብር ብዝሀነት የተገነዘበ እና የህዝቦችን ተጨባጭ ፍላጎት ያማከለ የመበልፀግ ትርክትና አስተሳሰብ ማነፅ ያስፈልጋል፡፡

ኢትዮጵያ ውብ ባህሎች፣ ሃይማኖቶች እና ልዩ ልዩ ማንነቶች ያሏት፣ ልዩነትን በአንድነት ውስጥ፣ አንድነትን በልዩነት ውስጥ ያጣመረ ኅብረ ብሔራዊ ተፈጥሮ ያላት አንድም ብዙም የሆነች ድንቅ ሀገር ናት፡፡

ልዩና ተምሳሌታዊ ረቂቅነት ያላቸው ማህበረሰባዊ እሴቶችን እንዴት አድርገን የህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማስጠበቂያ እናድርጋቸው? ለእንዲህ ዓይነት ሀገር እና ህዝብ ምን ዓይነት ትርክት፣ ምን ዓይነት የአመራር እና የአስተደዳር ፍልስፍና ያስፈልጋል? የሚለውን በጥሞና በማሰብ፣ በስክነት በመመርምር ምላሽ መስጠት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

የህብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ አስተሳሰብ (ሶሻሊዝም) ጥቂት ነገሮችን አስተካክሎ ብዙ ነገሮችን አበላሽቶ ሄዷል፡፡ የምሥራቁን እና የምዕራቡን ዓለም ፍልስፍና ለማጣመር የሞከረው ቅይጡ የኢሕአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲም፣ ውሱን ነገሮችን አስተካክሎ ቁልፍ ነገሮችን አወሳስቦ ከስፍራው ገለል ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ የርዕዮተ ዓለም ትርክት የዕድገት ባህሪይ ከንጉሠ ነገሥታዊ ወደ ማርክሲስት ሌኒኒስት ርእዮተ ዓለም፣ በመጨረሻም ወደ መደመር የተደረገ ነው፡፡

ፍትሀዊነት፣ ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት፣ ህብረ ብሔራዊነት ለመደመር ዋና ዕሴቶቹ ናቸው፡፡ ነጠላ ቡድናዊ አስበሳሰብን ወደ ሀገራዊ አሸናፊት የሚቀይር ነው የመደመር እሳቤ፡፡

የቀደመ ትውልዳዊ ዕዳን በምክክር፣ በድርድር እና በይቅርታ ዘግቶ፣ የኢትዮጵያ እና የሕዝቦቿን የትናንት ስብራት የሚጠግን አዲስ ዕይታ ነው፡፡ ዛሬን በትጋት እና በህብረት አጎልብቶ ለነገ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያበቃ ሀገር በቀል ዕሳቤ ነው፡፡

መደመር በውስብስብ ሀገራዊ ችግሮች ውስጥ የተወለደ ሀገራዊ መድኃኒታችን ነው፡፡ መደመር ህብረ ብሔራዊ ብዝሀነት ነው፡፡ መደመር አብሮነት ነው፡፡ መደመር ለሀገር በቀል ችግሮቻችን ሀገር በቀል መፍትሄ የሰጠ ዘመኑን የዋጀ ትውልድ አሻጋሪ እሳቤ በመሆኑ ለመደመር አቅምንም ጊዜንም አስተባብሮ መረባረብ ይበጃል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"በአሁኑ ሰአት የገላን ጉራ መንደር ለኑሮ እጅግ ተፈላጊ ከሆኑ መንደሮች ወይም አካባቢዎች አንዱ ለመሆን በቅቷል" - ወ/ሮ መኪያ ሁሴን - የአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 10 ዋና ስራ አስፈጻሚ

ከቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ከካሳንችስ የልማት ተነሺ በመሆን ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የመጡ ነዋሪዎች ህይወታቸውን በተደላደለ መንገድ መምራት መጀመራቸው የወረዳዋ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተገለጹ።

የአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 10 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መኪያ ሁሴን "ወደ ወረዳችን የመጡ ነዋሪዎችን 'እንኳን ደህና መጣችሁ' ብለን ከተቀበልናቸው ሰአትና ጊዜ አንስቶ ከክፍለ ከተማና ከማዕከል እንዲሁም ከሌሎችም ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መንደራቸውን ለኑሮ አመቺ ለማድረግ ሰፋፊ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል" ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አክለውም "ሁሉም በሚባል ደረጃ የታቀዱና የተሰሩት ስራዎች ነዋሪዎቹን በእጅጉ ያስደሰቱና ስኬታማም ነበሩ። በአሁኑ ሰአት በ #ገላን_ጉራ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች ተሟልተዋል። በዚህም የተነሳ በአሁኑ ሰአት የገላን ጉዳ መንደር ለኑሮ እጅግ ተፈላጊ ከሆኑ መንደሮች ወይም አካባቢዎች አንዱ ለመሆን በቅቷል" ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለውናል።

ወ/ሮ መኪያ "እንደ ማንኛውም የከተማችን አካባቢዎች የጎደሉ፣ የሚታረሙ፣ የሚስተካከሉ፣ የሚያስፈልጉ፣ ... ጥቃቅን ነገሮች ካሉም ከነዋሪዎች ጋር በመነጋገር እንደ አስፈላጊነታቸው ቅደም ተከተል በመስጠት፣ ደረጃ በደረጃ የምንሰራቸው ይሆናሉ" በማለት ሃሳባቸውን ለዝግጅት ክፍላችን አድርሰዉናል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በዶንቴስክ ሪፐብሊክ ተገኝተው “ዩክሬን ምእራባዉያን መተው አለባት። አሜሪካ በተለይ የባይደን አስተዳደር ችግር ፈጣሪ ነው “ብለዋል

የኢትዮጵያ የፓርላማ አባል እና የፖን አፍሪካ ፓርላማ አመራር ውስጥ ያሉት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ሰሞኑ በሩስያ መንግሰት ግብዣ የፖን አፍሪካ ፓርላማ አባላት በሩስያ በተያዘችው ቀደም ብላ የዩክሬን ግዛት ወደ ነበረችው ፓርላማ ተገኝተው ለጋዜጠኛች እንደተናገሩት “የሩስያ እና የዩክሬን ግጭት በምእራብውያን የተቀመመ ነው። ሁለቱ ሀገራት ወዳጅ እንደሆኑ እናውቃለን ዩክሬን ችግር ፈጣሪ የሆኑትን ምእራባውያንን መተው አለባት። አሜሪካ በተለይ የባይደን አስተዳደር ችግር ፈጣሪ ነው። የፖን አፍሪካ ፓርላማ አባላት ዩክሬን እና ሩስያን ለማሸማገል ዝግጁ ነው“ ብለዋል

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የአስቸጋሪው ጊዜያችሁ ውበት!

በሕይወታችሁ እጅግ አስቸጋሪ በተባለው ጊዜአችሁ ውስጥ የምታዩት ውብ የሆነ ነገር ቢኖር፣ በአካባቢያችሁ የሚገኙ ሰዎችን እውነተኛ ቀለምና ማንነት የማየታችሁ እውነታ ነው፡፡

ተጠቀሙበት!


🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ናይጀሪያዊው የአታላንታ አጥቂ አደሞላ ሉክማን የ2024 የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ።

የዩሮፓ ሊግን ከጣሊያኑ አታላንታ ጋር ያነሳው ተጫዋቹ በ2024 የውድድር ዘመን 27 ጎሎች አስቆጥሮ 12 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አቀብሏል።

አደሞላ ሉክማን የአታላንታ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርን ያገኘ ሲሆን ለቡድኑ በዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ሶስት ጎሎች አስቆጥሮ የዋንጫ ባለቤት ሜድረጉን ቲኤንቲ ስፖርት ዘግቧል።

የባለፈው ዓመት የአፍሪካ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠው ያገሩ ልጅ ቪክቶር ኦሲመን እንደነበር ይታወሳል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ያዘጋጀዉ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ በአዳማ ከተማ ይጀመራል።

ከታህሳስ 7/2017 ዓም ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደዉ የምክክር መድረክ ላይ ከክልሉ 356 ወረዳዎች ከአስር የማህበረሰብ መሰረቶች የተመረጡ ከ7,000 በላይ የማህበረሰብ ወኪሎች አጀንዳዎቻቸውን በምክክር ይለያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም የተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ምክክር የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ከእሑድ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ 1ሺ 700 የክልል ባለድርሻ አካላት ለተከታታይ ሦስት ቀናት በክልሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ተመካክረው ያደራጃሉ።

በክልሉ በሚደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የመጡ 48 ሞደሬተሮች (መምህራን) ውይይቶቹን የሚያስተባብሩ ሲሆን 356 የክልሉ ተባባሪ አካላትም ለሂደቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ከ100 በላይ የኮሚሽ ሰራተኞችና 150 በጎ ፈቃደኛ የዩንቨርስቲ ተማሪዎችም ሂደቱን በተለያየ መልኩ ያግዛሉ፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከአርባ ምንጭ ፀጋዎች በጥቂቱ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#የመደመርትውልድ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ቆራጥነት ይኑርህ!

በአለማችን ውስጥ በርካታ አስገራሚ እውነተኛ ታሪኮች ይሰማሉ፡፡ አንዳንዶቹ አስቀውን፣ ሌሎቹ አሳዝነውንና አስለቅሰውን ያልፋሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን አዝናኝም፣ አሳዛኝም፣ አስተማሪም ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ አስተማሪ ገጽታ ያለው አንድ አጭር ታሪክ ላጋራችሁ፡፡

ሁለት ሕጻናት ከየራሳቸው ወላጆች በአንድ ሆስፒታል ተወለዱና የሆስፒታል ቆይታቸውን ሲጨርሱ ወላጆቻቸው ወደየቤታቸው ወሰዷቸው፡፡ ለካ አልፎ አልፎ የሚከሰተው ስህተት ተከስቷል፡፡ እነዚህ ወላጆች እቤታቸው ይዘው የሄዱት የራሳቸውን ልጅ ሳይሆን ሃኪሞቹ በሰሩት ስህተት ምክንያት ተቀያይረው ነው፡፡ ሁኔታው የታወቀው ግን ልጆቹ እደግ ብለው መልክ እየለዩ ሲሄዱ ነው፡፡

ልጆቻቸው እያደጉ ሲሄዱና መልካቸው እየለየ ሲመጣ ሁለቱም የማይተዋወቁ ወላጆች በየራሳቸው ጥያቄ ፈጠረባቸው፡፡ ከብዙ ማንገራገር በኋላና ልጆቹ አደግ ካሉ በኋላ አንደኛው ቤተሰብ ሁኔታው ስላሳሰበው ወደ ሆስፒታሉ በመሄድ የማጣራት ስራ እንዲሰራለት ይጠይቅና ሲጣራ መቀያየራቸው ተረጋገጠ፡፡ ይህ ወደመታወቅ የመጣው እውነት በብዙ ጭቅጭቅና የክስ ሂደት ውስጥ አለፈ፡፡ ጭቅጭቁና ክሱ ልጆቹ ይመለሱ አይመለሱ ነው፡፡ በመጨረሻ ዳኛው አንድ ፍርድ አስተላለፈ፡፡ “ሁለቱም ልጆች ይቅረቡና እውነቱ ተነግሯቸው ይጠየቁና የእነሱን ሃሳብ ሰምቼ እፈርዳለሁ” አለ፡፡

ልጆቹ ቀርበው ሲጠየቅ ሁለቱም አሁን ያሉበትን ቤትና ቤተሰብ እንደሚወዱና በፍጹም ወደ ትክክለኛ ቤተሰባቸው መመለስ እንደማይፈልጉ ተናገሩ፡፡ የአንዱ ቤተሰብ እጅግ ሃብታም የአንዱ ቤተሰብ ደግሞ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ናቸው፡፡ ለልጆቹ ግን ይህ ሁኔታ ከቁጥርም አልገባም ነበር፡፡ የለመዱትን ስለወደዱት የእነሱ ከሆነው ነገር ውጪ ለመኖር ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፡፡

የእነዚህ ልጆች ታሪክ እውነተኛ ቤተሰብ ማለት የለመድነው፣ የቀረብነውና ፍቅርና እንክብካቤ ያገኘንበት የመሆኑን አስገራሚ እውነት የመጠቆሙን ጉዳይ አልዘነጋሁትም፡፡ እንዲሁም አንድ ሰው የተቀበለውን ሰውም ሆነ ኑሮ ከሃብትና ከገንዘብ አስቀድሞ ደስተኛ ሆኖ ሊኖር የመቻሉን እውነታም አልሳትኩትም፡፡ ሆኖም ግን ታሪኩ ሌላ እውነታ ጨምሮ እንዲስተምረኝ ራሴን ክፍት ለማድረግ ፈለኩኝ፡፡ 

ይህ የሰውን ልጅ ሁል ጊዜ የማይለቀውን ትግል የሚጠቁም ታሪክ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በፍጹም “የእኛ” ያልሆነውን ነገር እና “እኛ” ያልሆንነውን ነገር ስለለመድነው ብቻ እንቀበለዋለን፡፡

የተወለድነው “ሌላ ቤት” የምንኖረው ግን “ሌላ ቤት”! . . . የተፈጠርነው ለሌላ ነገር፣ የምንኖረው ግን ሌላ ነገር! . . . የሚገባን ከፍ ያለ ነገር፣ እኛ ግን ወርደንና ተቀብለን የምንኖረው ሌላ ነገር! . . . የሚመጥነን ሰው ሌላ፣ መልቀቅ ያልፈለግነው ሰው ግን ሌላ ሰው! . . . የውስጣችን ጩኸት ሌላ፣ ስለለመድነው መልቀቅ ያቃተን ነገር ግን ሌላ!

ልክ እነዚህ ልጆች በሕጻንነታቸው እንደሆኑት ምርጫው ባይኖረን ምንም ችግር አልነበረውም፡፡ ነገር ግን ልክ እንደነሱ አድገን የመምረጥ አቅሙም ሆነ መብቱ ኖሮን ከምናውቀው እውነታ ይልቅ የለመድነው ነገር ሲያይልብንስ !?

እውነታውና ትክክለኛው ሲታይህ ስለለመድከው ብቻ የወደድከው፣ ለአንተ የማይመጥንንና የአንተ ያልሆነውን የሕይወት ዘይቤና አቅጣጫ ትተህ ለመሄድ ቆራጥነት ይኑርህ፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እስራኤል በህገወጥ በያዘችው የሶርያ ጎላን አካባቢ ዜጎቿን ለማስፈር ውሳኔ አሳለፈች

የእስራኤል መንግስት በህገወጥ መንገድ በተያዘው የጎላን ኮረብታማ ስፍራዎች ላይ የእስራኤል ሰፋሪዎችን ቁጥር ለመጨመር የያዘውን እቅድ አጽድቋል። የሶሪያ የረዥም ጊዜ መሪ በሽር አል አሳድ ከስልጣን መውረድ በኋላ እና እስራኤል ተጨማሪ የሶሪያ ግዛት ከተቆጣጠረች ከቀናት በኋላ ይህንን ውሳኔ አፅድቃለች። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት መንግስት በተያዘው ግዛት ውስጥ ያለውን የእስራኤል ህዝብ ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ እና የሚፈለገውን "የሕዝብ ልማት" ለማምጣት ውሳኔውን በአንድ ድምጽ አጽድቋል ብሏል።

አዲሱ እቅድ እ.ኤ.አ. ከ1967 ጀምሮ እስራኤል ለያዘችው የጎላን ክፍል ብቻ ተግባራዊ የሚሆን ነው። በ1981 የእስራኤል ክኔሴት የእስራኤልን ህግ በግዛቱ ላይ ለመጫን ተንቀሳቅሷል። ዕቅዱ ተግባራዊ የሆነው ከሳምንት በፊት በአል አሳድ መውደቅ ምክንያት እስራኤል ከያዘችው የሶሪያ ክፍል ጋር አይገናኝም ተብሏል። ከ1973 ጦርነት በኋላ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከወታደራዊ ኃይል ነፃ የሆነውን የሄርሞን ተራራን የሚያካትት ሲሆን ይህ ግዛት የሶሪያ ዋና ከተማን ደማስቆን ለመመልከት የሚያስችል ነው።

ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ የሰፋሪዎችን ቁጥር ለመጨመር ከ40 ሚሊዮን በላይ ሼክል ወይም 11ሚሊዮን ዶላር በላይ ፈሰስ የሚደረግበትን እቅድ አድንቀዋል።በጎላን ውስጥ ወደ 31 ሺ የሚጠጉ እስራኤላውያን ሰፋሪዎች በደርዘን በሚቆጠሩ ህገወጥ አካባቢዎች ይኖራሉ። በአብዛኛው ሶሪያዊ እንደሆኑ ከሚታወቁት ድሩዜን ጨምሮ ከአናሳ ቡድኖች ጋር አብረው እስራኤላውያኑ ሰፋሪዎች ይኖራሉ።

እስራኤላውያን የጎላን ኮረብታዎችን መያዛቸው በአለም አቀፍ ህግ ህገወጥ ቢሆንም፣ በስልጣን ዘመናቸው ከ2017 እስከ 2021 ድረስ በዋይት ሀውስ የነበሩት ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስን ከአለም ቀዳሚ ያደረጋትን ውሳኔ በማሳለፍ ለእስራኤል የአከባቢውን ሉዓላዊነት በይፋ እውቅና በመስጠት ነበር።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኤርዶጋን አዲስ አበባ ሊመጡ ነው
                                       
የኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ውዝግብ በሽምግልና የፈቱት የቱርክ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያንና ሶማሊያን  እንደሚጎበኙ ተገለጸ፥የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ማምሻውን እንደዘገቡት የቱርክ ፕሬዚዳንት ጤይብ ኤርዶጋን በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 2025 አዲስ አበባ እና ሞቃዲሾን ለመጎብኘት መርሃ ግብር ይዘዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኝ ጫካ ውስጥ  የሩሲያ ከፍተኛ የሚሳኤል ኤክስፐርት በጥይት ተመቶ ህይወቱ አለፈ

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትጠቀመውን ኬ ኤሽ-59 እና ኬ ኤች-69 ሚሳኤሎችን ሲያዘምን የነበረው ሚካሂል ሻትስኪ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል።

ክሬምሊን በዩክሬን ጦርነት ጥቅም ላይ ስታውለው የነበረውን የክሩዝ ሚሳኤሎችን ለመስራት የረዳ ሩሲያዊ የጦር መሳሪያ ኤክስፐርት ነበር።

የዩክሬን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ሚካሂል ሻትስኪ ከክሬምሊን 13 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የኩዝሚንስኪ ጫካ ውስጥ  በጥይት ተመቷል።

በፓለቲካ ምክንያት ከሀገሩ የተሰደደው ሩሲያዊ ጋዜጠኛ አሌክሳንደር ኔቭዞሮቭ ሻትስኪን በደም የተበከለ በረዶ ላይ ተኝቶ የሚያሳይ ፎቶግራፍ በቴሌግራም ላይ አጋርቷል።  ተመሳሳይ ፎቶግራፎች በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ በበርካታ የዩክሬን ደጋፊ ቻናሎች ላይ ታይተዋል። ገለልተኛው የሩሲያ ጋዜጣ ኢምፖንት ታሪስ በበኩሉ አስከሬኑ የተገኘበትን ቦታ እውነታነትን አረጋግጧል።

ሻትስኪ በ2022 ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት ቀን አንስቶ የተጠቀመችውን የኬ ኤች-59 እና ኬ ኤች 69 ክሩዝ ሚሳኤሎችን በማዘመን እና በመቆጣጠር ደረጃ ኃላፊ ሆኖ ሲያገለግል ነበር። በተጨማሪ ሟቹ ኢንጂነር ለሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ስራ ሲሰራ እንደነበረ ተነግሯል።

ዩክሬንካ ፕራቭዳ እና ኪየቭ ኢንዲፔንደንት ጨምሮ በርካታ የዩክሬን መገናኛ ብዙሃን ማሰራጫዎች ጥቃቱ የተፈፀመው በዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ኤጀንሲ መሆኑን ማንነታቸው ያልታወቁ የዩክሬን የመከላከያ ምንጮችን ጠቅሰው ዘግበዋል።

"በሩሲያ ወታደራዊ ኢንዱስትሪን ለማዘመን የተሳተፈ እና በዩክሬን ውስጥ የሩስያ ጥቃትን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የሚደግፍ ማንኛውም ሰው የዩክሬን መከላከያ ሰራዊት ኢላማ ነው" ሲል አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ከፍተኛ ባለስልጣን ለኪዬቭ ኢንዲፔንደንት ተናግሯል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከሞስኮ ወይም ከኪዬቭ ባለስልጣናት በግልፅ የተባለ ነገር የለም።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሞስኮ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሩሲያ የኒውክሌር ኃይል አዛዥ ተገደሉ

ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ አንድ አፓርትመንት ሕንፃ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፤ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ ከረዳታቸው ጋር መገደላቸው ተገልጿል፡፡

ኢጎር እና ረዳታቸው የተገደሉት ከክሬምሊን በስተደቡብ ምስራቅ 7 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኘው የመኖሪያ አፓርትመንታቸው ውጭ በደረሰ ፍንዳታ ነው ተብሏል።

ጄነራሉ የተገደሉት በመኖሪያ ቤታቸው መግቢያ ላይ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ በተጠመደና ቤት ውስጥ የተሰራ ቦንብ መሆኑን በሩሲያ መንግሥት የሚተዳደረው ታስ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር፤ በኮስትሮማ ከፍተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የኬሚካል መከላከያ ትምህርት ቤት ወታደራዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ከፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 ጀምሮ የጦር ኃይሉን እንዲመሩ ተሹመዋል።

ጄኔራሉ የሩሲያ ጦር የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ጨምሮ ከአደገኛ ፈንጂዎች ጋር በተዛመደ በሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ውስጥ በተለያዩ ሚናዎች አገልግለዋል። በትላንትናው ዕለት የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ዩክሬን ውስጥ የተከለከለ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ሲል ጄኔራል ኢጎርን ከሶ ነበር፡፡የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት በኪሪሎቭ መሪነት ሩሲያ 5 ሺሕ ያህል የኬሚካላዊ መሳሪያዎችን ተጠቅማለች ሲል ተናግሯል።

ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር "በዩክሬን በሩሲያ ጦርነት ላይ አውዳሚ ኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ተጠቅመዋል" በሚል በብሪታኒያ፣ ካናዳ እንዲሁም በሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ማዕቀብ ተጥሎባቸው ቆይቷል

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Nageenya ni waaressina, Misooma ni dhugoomsina!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስኬታማነትና ደስተኛነት

በአንድ ወቅት በአንድ የትምህርት ተቋም ውስጥ አንድ ጥናት ተደረገ፡፡ ከትምህርት ቤቱ ሶስት አስተማሪዎች ካለምንም የጉብዝና ቅድመ-ሁኔታ ተመረጡና እንዲህ ተባሉ፣ “እናንተ ሶስታችሁ በትምህርት ቤቱ አሉ ከተባሉ ጎበዝ አስተማሪዎች መካከል ዋናዎቹ እንደሆናችሁ አጥንተን ደርሰንበታል፡፡

ስለሆነም፣ ከዚሁ ትምህርት ቤት ውስጥ እጅግ ጎበዝ እንደሆኑ የደረስንባቸው 90 ተማሪዎች ተመርጠውላችኋል፡፡ እነዚህን ጎበዝ ተማሪዎች በዚህ አመት በእናንተ ጉብዝና ልክና ለእነሱ ጉብዝና በሚመጥናቸው መልኩ እንድታስተምሯቸው እንፈልጋለን ተባሉ፡፡

ለተመረጡት 90 ተማሪዎችም እንዲሁ ጎበዝ መሆናቸው በጥናት እንደተረጋገጠ ከተነገራቸው በኋላ የትምህርት ቤቱ አሉ የተባሉ ጎበዝ አስተማሪዎች እንደተመደበላቸው ተነገራቸው፡፡

በአዲሱ ምደባ መሰረት ትምህርቱ አመቱን ሙሉ ቀጠለና በአመቱ መጨረሻ ሁለት ነገር እውን ሆነ፡፡

1.  ዘጠናዎቹም ተማሪዎች ቀድሞ ያመጡት ከነበረ ውጤት በብዙ እጥፍ የተሻለ ውጤትን አስመዘገቡ፡፡

2.  ሶስቱ አስተማሪዎች ከዚህ በፊት ከነበራቸው በስራቸው ደስተኛ የመሆ ሁኔታ በብዙ እጥፍ ጨምረው ተገቡ፡፡

የዚህ ጥናት ጥቆማ፡-

1.  በራሳችን ላይ ያለን አመለካከትና ለራሳችን የምንናገረው ነገር መልካም ሲሆን ይህ አመለካከት በምናደርገው ነገር፣ በስኬታማነታችን ላይና በደስተኛነታችን ላይ ትልቅ አዎንታዊ ተጽእኖ አለው፡፡

2.  በሰዎች ላይ ያለን አመለካከትና ለእነሱ የምንናገረው ነገር መልካም ሲሆን ይህ አመለካከት ሰዎቹ በሚያደርጉት ነገርና በስኬታማነታቸው፣ እንዲሁም በደስተኛነታቸው ላይ ትልቅ አዎንታዊ ተጽእኖ አለው፡፡

እስቲ ዛሬ ለራሳችሁ የወረደውንና የደከመውን ነገር ከምትናገሩና ያንን ሃሳብ ከምታሰላስሉ መልካም መልካሙን አስቡ፣ ተናገሩ!

እስቲ ዛሬ አጠገባችሁ ላሉት ሰዎች የወረደውንና የደከመውን ነገር ከምትናገሩና ያንን ሃሳብ ከምትዘሩባቸው መልካም መልካሙን እየተናገራቸው ያንን ሃሳብ ዝሩባቸው!

ይህንን ብናደርግ ቤተሰባችን፣ ጓደኝነታችን፣ ስራ ቦታችን፣ ሰፈራችንን ሃገራችን ወደ ስኬታማነትና ወደ ደስተኛነት አለም ቀስ በቀስ ይሸጋገራሉ!

ከራሳችንና አጠገባችን ካሉት እንጀምር

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሀም ታደሰን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተው የሱፐርቪዥን ቡድን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ያደረጉት የመስክ ምልከታ በጥቂቱ 👌👌👌

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የቃሊቲ እስረኞች ወደ ሌላ እሥር ቤት ሊዛወሩ ነው           

የቃሊቲ ወህኒ ቤት  እሥረኞች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሌላ እሥር ቤት እንደሚዛወሩ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አስታወቀ፥ እስረኞቹን ገላን አካባቢ ወደ ተሰራው ማረሚያ ቤት የማዛወሩ ሥራ እስከ ታህሳስ 13/2017 እስኪጠናቀቅ ቤተሰብ እስረኞቹን መጠየቅ እንደማይችልም አስታውቋል።

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እስረኞቹ የሚዛወሩበትን ምክንያት እና የቤተብ ጥየቃ የሚመለስበትንም ቀን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ከመጪው ሰኞ ታህሳስ 14/2017 ጀምሮ መደበኛው  አገልግሎት እንደሚቀጥል እና ቤተሰብ እስረኞቹን መጠየቅ እንደሚችልም ኮሚሽኑ  አስታውቋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በዶንቴስክ ሪፐብሊክ ተገኝተው “ዩክሬን ምእራባዉያን መተው አለባት ።አሜሪካ በተለይ የባይደን አስተዳደር ችግር ፈጣሪ ነው “ብለዋል

የኢትዮጵያ የፓርላማ አባል እና የፖን አፍሪካ ፓርላማ አመራር ውስጥ ያሉት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ሰሞኑ በሩስያ መንግሰት ግብዣ የፖን አፍሪካ ፓርላማ አባላት በሩስያ በተያዘችው ቀደም ብላ የዩክሬን ግዛት ወደ ነበረችው ፓርላማ ተገኝተው ለጋዜጠኛች እንደተናገሩት

“የሩስያ እና የዩክሬን ግጭት በምእራብውያን የተቀመመ ነው ።ሁለቱ ሀገራት ወዳጅ እንደሆኑ እናውቃለን ዩክሬን ችግር ፈጣሪ የሆኑትን ምእራባውያንን መተው አለባት ። አሜሪካ በተለይ የባይደን አስተዳደር ችግር ፈጣሪ ነው ። የፖን አፍሪካ ፓርላማ አባላት ዩክሬን እና ሩስያን ለማሸማገል ዝግጁ ነው “ብለዋል

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ዶክተርበየነአበራ👏

" ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝን ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም " - ዶ/ር በየነ አበራ

በሰርጉ ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች ከጠሩት የመልስ ፕሮግራም ላይ ላይ ተነስቶ በመሄድና የተሳካ ቀዶ ሕክምና በማድረግ እናትና ልጅን የታደገዉ የማህፀንና ፅንስ ስፖሻሊስቱ ዶክተር በብዙዎች ምስጋና ተችሮታል።

ይህ የሚያስመሰግን ተግባር የተፈጸመው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው።

በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር በየነ አበራ በትላንትናው ዕለት በሰርጋቸው ማግስት የሙሽሪት ቤተሰቦች በጠሩት የመልስ ዝግጅት ላይ ነበሩ።

በዚህ ዝግጅት ላይ እንዳሉ ነው ከሚሰሩበት ሆስፒታል የስልክ ጥሪ የደረሳቸው።

የስልክ ጥሪውም እናትና ልጅን እንዲታደጉ የቀረበ ነበር።

ዶክተር በየነ ስለሁኔታው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ " መልስ በሀገራችን ባህልና ወግ ትልቅ ቦታ እደሚሰጠዉ አዉቃለሁ በዕለቱ አማቾቼ አክብረው ጠርተዉን ፕሮግራሙ እየተካሄደ ነበር ስልክ የተደወለልኝ " ብለዋል።

" የመጀመሪያውን ዙር አላነሳሁም ፤ በድጋሚ ሲደወልልኝ አነሳሁት አንዲትን እናት ምጥ እንዳስቸገራትና ቀዶ ሕክምና የግድ እንደሚያስፈልጋት  ተነገረኝ፤ ለመሄድ አላመነታሁም " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

በኃላም ዶክተር የመልስ ዝግጅቱን አቋርጠው የእናት እና ልጅን ሕይወት ለመታደግ እየከነፉ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ይወስናሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ጉዳዩን እንዴት ለሙሽሪት እንዳስረዱና ሙሽሪትን እንዳሳመኗት ጠይቋቸዋል።

እሳቸውም ፤ " በፍቅር ሕይወታችን ወቅት የትዳር አጋሬን በተደጋጋሚ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ እነግራት ነበር፤ በሰርግ መልሳችን ቀን ግን ይሆናል ብዬ አሰቤ አላዉቅም ነበር " ብለዋክ።

" ለሙሽራዋ ባለቤቴና ለሚዜዎቼ ነገርኳቸዉና ወደ ሆስፒታሉ አመራሁ። ባለቤቴን ጨምሮ ጓደኞቼና ጓደኞቿ ለሙያው ያለኝ ፍቅርና ቁርጠኝነት ስለሚያዉቁ ሊጫኑኝ አልፈለጉም " ሲሉ ተናግረዋል።

ዶክተር በየነ " ቤተሰቦቿን ግን ተመልሼ ይቅርታ ለመጠየቅ ወስኜ ነበር ወደ ሆስፒታል የሄድኩት " ብለዋል።

" ወደ ሆስፒታሉ ስደርስ የቀዶ ሕክምና ቲሙ ዝግጁ ስለነበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌ ቀዶ ሕክምናውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀናል " ሲሉ ተናግረዋል።

ዶክተር በየነ አበራ የመጀመሪያ ዲግሪያቸዉን በሕክምና ትምህርት ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ያገኙ ሲሆን የስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ደግሞ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለማሟላት እየሰራን ያለነው ስራ ...

Via - ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

😭😭😭😭😭😭😭😭😭
Balaan Tiraafikaa Aanaa Dodolaatti mudate lubbuu namoota 12 galaafate.

Balaa Tiraafikaa Aanaa Dodolaa toora Magaalaa Eddoo, laga Ukkumaatti dhaqqabeen namoonni 12 du'an.

Balaan dhaqqabe kaleessa galgala sa'atii 1:45tti konkolaataan ummataa gaarii Harreerraa goruun walitti bu'ee mudachuu, Itti gaafatamaan Kutaa Nageenna Tiraafikaa Godina Arsii Lixaa Komaandar Kamaal Amaan himan.

Konkolaataan ummataa Roobee Baaleerraa gara Shaashamannee deemuufi Shaashamanneerraa gara Gadab Hasaasaa imalu walitti bu'uun namoonni 12 du’uun, namoota 9 irraan miidhaa cimaan qaqqabeera, namoonni 10 ammoo miidhaa salphaaf saaxilamaniiru jedhan.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Daandiin Nagaa fageenya hin qabu!

Godina Shawaa Kaabaa Aanaa Hidhabuu Abooteeetti walii galtee nageenya waaressuu MNO fi WBO gidduutti taasifame bu’uureffachuudhaan miseensonni garichaa karaa nagaatiin galuu itti fufaniiru.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ለምን አልመረጣቹኝም? "በማለት ለተወለደችበት አካባቢ የሰጠችውን አምቡላንስ ከህዝቡ የወሰደችው ኡጋንዳዊት ፖለቲከኛ

ነገሩ እንዲህ ነው;

አሁን  የየኡጋንዳ የኢንቨስትመንት እና የፕራይቬታይዜሽን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ  ሆና የምትሰራው ኤቭሊን አኒቴ ካጂክ በተለምዶ ኤቭሊን አኒት የምትጠራው ፖለቲከኛ ከከሶስት አመት በፊት ለምርጫ ቅስቀሳ እንዲረዳት ለአደገችበት አካባቢ በነፃ አምቡላንስ ሰጠች።

በምርጫው ስትሸነፍ "ይሄ ለእኔ አይገባም ።ላልመረጠኝ ህዝብ እኔ ማነኝ በነፃ አምቡላንስ መኪና ማበረክተው? " በማለት ከሁለት ወር በፊት መኪናውን የወሰደች ሲሆን ነገሩ  በኡጋንዳ ህዝብ መሀል አግርሞትን ጭሮ አልፏል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ የሚሊዮን ዶላሮች ሎተሪ ያሸነፈ ባል፡፡

ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመቀጠል ወሰነች።

ሆኖም የፍቺ ሰነዶችን ከፈረመ ከአንድ ቀን በኋላ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የሚለዉጥለትን ሎተሪ ሊያሸንፍ ችሏል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዘመን የማይሽረው አርቲስት፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ እና አፍሮ-ጃዝ ላይ ድንቅ አስተዋዕዖ ያበረከተውን #ጋሽ_ማህሙድ_አህመድ የኢትዮጵያ የመጨረሻውን የመድረክ ስራ በሚሊኒየም አዳራሽ ጥር 3፣ 2017ዓም ያቀርባል!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Gachanni Sirnaafi Milishaan wabii nageenyaa uummata keenyati!

Bulchinsa Magaalaa Bishooftuu Kutaa Magaalaa Dhibaayyuutti miseensonni Gaachana Sirnaafi Milishaa leenjii gahuumsa qaamaafi tooftaalee diina qolachuu leenji'aa taran eebbifaman.

Sirna Eebba Gaachana Sirnaa kanarratti Bulchaan Kutaa Magaalaa Dhibaayyuu Obbo Lammaa Kafanii humni kun humna nageenya hawaasaa murteessaa ta'e sirna jijjiiramaa ittiin tikfannu, nageenya waloo keenyaa ittiin eegannuudha jedhan.

Waan kana ta'e kaayyoo keessan beektanii ergama isinirra jiru imaanaa nageenyaa guuttanii fakkeenya gaarii hawaasa keessatti qabaachuun naamusaan dursitanii akka waardiyaa nageenya ta'uu qabdu jedhan.

Dabalataan, milishoonni keenyaa akkuma kaleessaa nageenya waaraa mirkaneeasuuf gaachana hawaasa taatanii olaantummaa heera biyyatti akka kabajamuuf aarsaa kaffalamuu qabu kaffaluu akkuma kanaan duraa diina nageenyaafi misoomaa hawaasaaf gufuu tahuuf yaaluu kamiyyuu dura dhaabachuun nageenya aanaa keessaniifi ummata keessaniif wabii ta'uu keessan akka mirkaneessitan abdiin qaba jedhan.

Kantiibaa Magaalaa Bishoftuu Obbo Alamaayyoo Asaffaa gamasaaniin Milishaan har’a eebbifnu kunneen mallattoo humnaafi kutannoo waloo keenyaati.

Dhiironni fi dubartoonni jajjaboon kun magaalaa keenya tajaajiluufi eeguuf gara fuulduraatti tarkaanfataniiru, Magaalaan Bishooftuutti kutaan Magaalaa Dhibaayyuu jiraattota ishee hundaaf bakka nageenya qabuufi dagaagaa tatee akka itti fuftu mirkaneessaaa jirtis jedhan.

Kominikeeshinii Bulchinsa Magaalaa Bishooftuu

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…
Subscribe to a channel