አትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ አባል ሆና ተመረጠች።
28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉባኤ የአዲስ አበባ በእጩነት ያቀረባት አትሌት መሰረት ደፋር 18 ድምጽ በማግኘት የኢትዮጵያ ሥራ አስፈጻሚ አባል በመሆን ተመረጠች።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።
በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት ለመምራት ምርጫ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በዚህም ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉት አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አሜሪካ የራሷን የጦር ጀት ቀይ ባህር ላይ መታ ጣለች‼️
የአሜሪካ ባህር ሀይል የራሱን F/A -18 ተዋጊ ጀት መቶ መጣሉን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን ) አሳውቋል፡፡
በየመን የሁቲ ይዞታዎች ናቸው በተባሉ ስፍራዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ነው F/A 18 ተመቶ መውደቁ ይፋ የሆነው፡፡
የተዋጊ ጀቶቹ ሰራተኞች ህይወት እንዳላለፈ እና አንደኛው ቀላል ጉዳት ብቻ እንደደረሰበት ተወስቷል፡፡
አብራሪዎቹ ከጀቶቹ መውጣታቸው የተነገረ ሲሆን በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ሁቲ መግለጫም እየተጠበቀ ነው፡፡
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አደጋው መድረሱን በይፋ ማመኑ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በስፔን ባርሴሎና ባዶ ራቁት ተሁኖ ፊልም ለማየት የሚገባበት ሲኒማ ቤት መከፈቱ ተሰማ
የመክፈቻው ቀን አርባ ሰዎች በሲኒማው አዳራሽ ፊልም ለማየት መግባታቸው የተነገረሲሆን ሲኒማ ቤቱ ላብ መጥረጊያ ፎጣ ፊልሙን ለሚያዩት ሰዎች እንደሰጠ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
'ሰው ራቁቱን መሆን ለምን ያፍራል? ስንፈጠር ራቁታችን ነበርን? ልብስ ሰለጠንን ብለን ያደርግነው ነገር ነው "በማለት የሲኒማ ቤቱ ሀላፊ ተናግረዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የጅምላ መቃብር (Mass grave)‼️
በሶሪያ የተገኘው የጅመላ መቃብር በዓለም ላይ ትልቁ የጅምላ መቃብር ሳይሆን አይቀርም ዘኪኖሚስት‼️
ሶሪያዊያን በከፍተኛ ደረጃ ተሰቃይተው ከተገደሉ በሗላ በጅምላ የተቀበሩበት የቁተይፋ መቃብር ነው።
በዚህ መቃብር 150,000 ሶሪያዊያን በጅምላ ተቀብረዋል። እንደዚህ አይነት የጅምላ መቃብር ናዚ አይሁዶችን በጅምላ ከቀበረ በሗላ ታይቶ አይታወቅም።
150,000 የጠፉ ሶሪያዊያን እዚህ ጅምላ መቃብር ውስጥ በስብሰው ተገኝተዋል።
የሶሪያው መሪ በሽር አላሳድ መገርሰሳቸውን ተከትሎ የተከፈተው ጉዷ አለምን ያስደነገጠ የጭካኔ ጥግን ያሳየ ሆኖ አልፏል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ኢትዮጵያ ገቡ።
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።
ማክሮን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታቸው በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እድሳት የተደረገለት የእዩቤልዩ ቤተመንግስትን መርቀው እንደሚከፍቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የድግግሞሽ አዙሪት
በየቀኑ እየተነሳችሁ ከቤት ወጥታችሁ በሚኖራችሁ ስምሪት፣ የምትሰሩት ስራ፣ የምትውሉበት አካባቢ፣ የምታገኟቸው ሰዎችና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከሰለቻችሁና የትም እንደማያራምዳችሁ ካሰባችሁ “የድግግሞሽ አዙሪት” ውስጥ እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡
የድግግሞሽ አዙሪት ምልክቶች፡-
1. ተስፋ መቁረጥ፣
2. ሁሉም ነገር የማስጠላት ስሜት፣
3. ነገሮች እንደማይለወጡ ማሰብ፣
4. ኋላ የመቅረት ስሜት እና የመሳሰሉት ስሜቶች ናቸው፡፡
ከዚህ አዙሪት ለመውጣት መውሰድ የምንችላቸው እርምጃዎች፡-
1. ራእያችን ወይም የሕይወታች ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ መለየት፣
2. ከራእያችን አንጻር ወደ አዲስ ነገር ለመግባት መወሰን፣
3. በወሰንነው ውሳኔ ዙሪያ በየእለቱ የሚወሰዱን ትንንሽ እርምጃዎች መጀመር፣
4. የጀመርነውን እርምጃ በፍጹም አለማቆም፣
5. በምክር ሊያግዘን የሚችል ሰውን በመለየት ምክርን መቀበልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ሀይማኖት ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለአብሮነት ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ ይካሄዳል፡፡
በሰላም ኮምፍረንስ ለመሳተፍ ማምሻውን የኢትዮጲያ የሰላም ሚኒስትሮች፣ የኢትዮጲያ የሀይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ የክልል እና የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ድሬዳዋ ገብተዋል ።
በመረሀ ግብሩም ታህሳስ 11 የፓናል ውይይት እንዲሁም ደግሞ ታህሳስ 12 ሀገር አቀፍ የሰላም ኮምፍረንስ እንደሚካሄድም ለማወቅ ተችሏል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በኦሮሚያ ክልል ለ4 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ።
ከ7 ሺ በላይ የማህበረሰብ ተወካዮችም ላለፋት 4 ቀናት ሀገራዊ መግባባት ሊደረስባቸው ይገባል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ ሰንብተው ዛሬ አጠናቀዋል።
ተሳታፊዎች ያለምንም ነፃነት እና ጣልቃ ገብነት ለሀገር ሰላምና አንድነት መሰረት የሆኑ አጀንዳዎችን ማንሳታቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ አስተባባሪ ኮሚሽነር አምባዬ ኡጋቶ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የአራት ቀናት ቆይታው "እጅግ ተስፋ ሰጪ" የሚባል ስለመሆኑም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የማህበረሰብ ተወካዮች ለቀጣዩ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር የሚመካከሩ 320 ተወካዮችን መርጠዋል፡፡
ላለፉት 4 ቀናት ያሰባሰቧቸውን አጀንዳዎችም ለመረጧቸው 320 ወኪሎች አስረክበዋል።
በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ውስጥ የሚስተዋለው ነፃነትና በተወካዮች ምርጫ ላይ የሚታየው ግልፅነት አዲስ የዴሞክራሲ ልምምድ ስለመሆኑ ደግሞ የማህበረሰብ ተወካዮች ተናግረዋል።
ተወካዮች በቀጣዮቹ ቀናት የክልል ባለድርሻ አካላት ከሚባሉት ማለትም ከኦሮሚያ ክልል መንግስት አካላት፣ ከማህበራት እና ተቋማት፣ ከታዋቂ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከአባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ጋር በመምከር የኦሮሚያ ክልል አጀንዳዎችን በመለየት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚያቀርቡ ይሆናል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"በቃን ያሉ ድምጾች፤ ለሰላም የጮኹ አንደበቶች"
ግፍ የሰለቻቸው አደባባይ ወጥተዋል። መከራ የበዛባቸው በቃን ብለዋል። መገፋት የመረራቸው ተውን እያሉ ጮኸዋል። ልጆቻቸው የሚታገቱባቸው፣ መንገዶች የሚዘጉባቸው፣ የእለት ጉርሳቸው የሚወሰድባቸው የዓመት ልብሳቸው የሚገፈፍባቸው ተውን እያሉ በአደባባይ ውለዋል።
አዎን በቃን፣ አዎን ሰልችቶናል፣ አዎን ግጭት አጉብጦናል፣ መከራ በዝቶብናል፣ አዎን የመከራ ጽዋው ይደፋልን ያሉ ድምጾች ዳር እስከ ዳር ተሰምተዋል። ስሙን፣ ሰላማችን መልሱልን፣ ልጆቻችንን ተውልን፣ አረጋውያን በሰላም ይመርቁን፣ የሃይማኖት አባቶች ያስተምሩን፣ ይገስጹን፣ የሀገር ሽማግሌዎች ያስታርቁን፣ አታግቱን፣ አትዝረፉን፣ አትቀሙን፣ አባቶቻችንን አታዋርዱብን፣ አትግደሉብን፣ የአባቶቻችን ወግና ሥርዓት አትናዱብን፣ ተወልደን ባደግንባት፣ ልጆች ወልደን ወግ ማዕረግ ባየንባት ቀዬ እንዳንኖር አትፍረዱብን እያሉ ወጥተዋል።
ሰላምን የናፈቁ አንደበቶች፣ ግጭትን የጠሉ ልቦች፣ ለሰላም የተዘረጉ እጆች በጎዳናዎች ተመላልሰዋል። በየአደባባዮች ጎልተዋል። የጠፋች ሰላማቸውን በአደባባይ እየፈለጉ ውለዋል።
በቃን ያሉ ድምጾች፣ ለሰላም የጮኹ አንደበቶች በርክተዋል። ከፍ ብለው ተሰምተዋል። ጦርነት ይብቃን፣ ሰላም ይምጣልን እያሉ ጎዳናዎችን አጣበዋል።
የሚታገቱት ፣ የሚዘረፉት በርክተዋል፣ በጉልበተኞች ሃብት እና ንብረታቸውን የሚያጡት በዝተዋልና ከእንግዲህስ በቃን ብለዋል። የግፍ ጽዋ መረራቸው። በመከራ ውስጥ መኖር ሰለቻቸውና ተውን ብለው በአደባባይ ውለዋል።
እንደ ፈጣሪ የሚከበሩት የሃይማኖት አባቶች ሲገደሉ እያዩ እንዴት አይበቃቸው? ዝናብ ያፈራቸው፣ ሀገር ምድሩ የሚታዘዝላቸው፣ በቀጭን ዘንግ ጥላቻ የሚወድቅላቸው፣ ደም የሚደርቅላቸው የሀገር ሽማግሌዎች ክብራቸው ሲዋረድ፣ በእንብርክክ ሲሄዱ እያዩ ያማቸዋል እንጂ ለምን አያማቸው? ሕጻናት ከእናቶቻቸው ጡት እየተነጠሉ ሲታገቱ እየተመለከቱ ይቆጫቸዋል እንጂ ለምን አይቆጫቸው ? አረጋውያን ሀገር ከሚመርቁበት፣ ትውልድን ከሚያስተምሩበት ጎጆ እየታፈኑ ሲወሰዱ ያንገበግባቸዋል እንጂ ለምን አያንገበግባቸው?
የአማራ አርሶ አደሮች በቀያቸው የደረሰባቸው ግፍ ተነግሮ አያልቅም። በሬዎቻቸውን እነ ወይኖን፣ እነ ዘገርን፣ እነ ደባስን፣ እነ ፈንዛን፣ እነ ደግፍን ሲነዱባቸው፣ እነ ይመርቀንን ከቀንበሩ ፈትተው ሲያርዱባቸው፣ ሞፈር ሲያሰቅሉዋቸው፣ ላሞቻቸውን እነ ቦራን፣ እነ ሻሸልን፣ እነ ዛጎልን፣ ከጥጆቻቸው ነጥለው ሲወስዱባቸው ይበቃቸዋል እንጂ ለምን አይበቃቸውም?
የተስፋ ብርሃን የሚያዩባቸውን ልጆቻቸውን ከትምህርት ገበታ ሲነጥሉባቸው፣ ከትወልድ ሁሉ ወደ ኋላ ሲያስቀሩባቸው፣ ተቋሞቻቸውን ሲያፈርሱባቸው፣ ወግና ባሕሎቻቸውን ሲያጠፉባቸው፣ ለልጆቻቸው በመሶብ ያስቀመጧትን ጭብጦ ሲነጥቋቸው፣ በጎቻቸውን እና ፍየሎቻቸውን ወስደው ሲጨርሷቸው በቃን ይላሉ እንጂ ለምን አይበቃቸውም?
ከቀን ቀን ለሚያቆረቁዛቸው ጦርነት ሳይወዱ በግድ ቀለብ ሰፋሪ ሲኾኑ ይበሽቃቸዋል እንጂ ለምን አይበሽቃቸውም? ለልጆቻቸው ሳያጎርሱ ተገድደው ሌሎችን ሲያጎርሱ የኖሩት፣ ልጆቻቸውን እያስራቡ ሌሎችን የመገቡት ይበቃቸዋል እንጂ ለምን አይበቃቸውም? በቃን ብለው በጎዳናዎች መሙላታቸው፣ አደባባይ ማስጨነቃቸው፣ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ማሰማታቸው፣ ከዚህ በኋላ በሰላማችን የሚመጣብንን እንደ አባታችን ገዳይ እናየዋለን ማለታቸው ይፈረድባቸዋልን? መከራ እኮ ሲበዛ ይገነፍላል፣ ትዕግሥትም እኮ ያልቃል፣ መከራን የተሸከመ ትክሻም እኮ ይዝላል።
" አወይ ልጅ ማሰሪያው አወይ ልጅ ገመዱ
ጎጆማ ምን ይላል ጥለውት ቢሄዱ" እያሉ ለልጆቻቸው ሲሉ መከራን የተቀበሉት፣ ጀግኖች ሳሉ ቀን ይለፍ ብለው አንገታቸውን ደፍተው የከረሙት፣ ዘመን ይሽረዋል ብለው በትዕግሥት የጠበቁት፣ ምድሩ ሰው አጥቷልን፣ መካሪ ጠፍቷልን እንባላለን፣ በውስጣችን ይዘን በቀስታ እንፍተው ብለው ዝም ብለው የባጁት አልኾን ሲል በቃን ብለው መውጣታቸው የተገባ አይደለምን? ደግ አደረጉ አያስብልምን? የትልቅ ሕዝብ ልኩ ይህ ነው አያሰኝምን?
ዘመን ያመጣውን ዘመን እስኪወስደው እያሉ የመከራ ጽዋን መጋት እኮ ይሰለቻል። የመከራ ጽዋ ሞልቶ ሲፈስ እኮ በቃን ብሎ መነሳት ይመጣል።
በአማራ ክልል የኾነው ይህ ነው። ከአንድ ዓመት በላይ በግጭት ውስጥ ኾኖ የከረመው ሕዝብ በቃን ብሎ ወጥቷል። ሰላማችን መልሱልን እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ አሰምቷል። የአማራ ክልል ከተሞች ሰላምን በሚሹ ሰዎች ተሞልተው ውለዋል። ከዳር ዳር ሰላም ሰላም የሚሉ ድምጾች ተስተጋብተዋል። ጦርነት ተወግዟል። ግጭት ተንቋል። በልጆቻቸው ዕድሜ የሚመጣው ሁሉ ተወግዟል።
በአማራ ክልል ሰላምን የናፈቁ ግጭትን የጠሉ እና የጣሉ ሰልፎች በስፋት ተካሂደዋል። በሰልፎችም ሰላም ተሰብኳል። አንድነት ተቀንቅኗል። ፍቅር ተዘምሯል። ጦርነት እና ጥላቻ ይቀር ዘንድ ተለፍፏል። ለችግሮች ሁሉ መፍቻው ውይይት ይኾን ዘንድ ተጠይቋል።
ሰልፎቹ እልፍ ትርጉም አላቸው። ሰልፎቹ መፈክር ይዞ ከመውጣት በላይ ናቸው። ድምጽ አሰምቶ ከመመለስ ያልፋሉ። ሰልፎቹ መሬት ላይ ያለውን ዕውነት ይገልጻሉ፣ መፍትሔውን ይጠቁማሉ። የነገውንም ይተነብያሉ። ሰልፎቹ እልፍ መልክ አላቸው። የሕዝብን ምሬት ያሳያሉ። የከረመውን መከራ ይገልጻሉ። ዕውነትን በአደባባይ ይገልጣሉ። የግፉን መጠን ይነግራሉ። ከዚህ በላይ አንታገስም የሚል መልዕክት ይነግራሉና።
ዝም ብሎ የኖረ ፣ ያልፋል ብሎ አንገቱን ደፍቶ አንድ ዓመትን የተሻገረ ሕዝብ ሰላም ይሻላል ጦርነት በቃን ብሎ ሲወጣ ያወቀበት ይድናል። ድምጹን የሰማ መልካም ነገርን ያደርግ ዘንድ ይወዳል። በታሪክ ላይም ስሙን ያጽፋል።
ከዳር ዳር የተሰሙትን የሰላም ድምጾች የናቀና የተወ ቢኖር ግን መንገዱ የከበደች፣ ዘመኑም የተጨነቀች ትኾናለች። ስለ ምን ቢሉ ጫካ ለአንበሳ ሞገሱና ግርማው፣ መጠጊና ደጀኑ እንደኾነ ሁሉ ታጋይም ያለ ሕዝብ ምንም ነውና።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኤሌክትሪክ አደጋን ለመከላከል የሚያግዙ የጥንቃቄ መንገዶች
የኤሌክትሪክ አደጋ በኤሌክትሪክ ምክንያት የሚመጣ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በሰው ህይወትና አካል፣ እንዲሁም በንብረት ላይ ጊዜያዊ ወይም ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡
በመሆኑም ራስዎን ከኤሌክትሪክ አደጋ ለመጠበቅ 👇
👉 በረገቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ሾልኮ ለማለፍ አይሞክሩ፤
👉 ኃይለኛ ንፋስ በሚነፍስበት ወቅት ከኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ርቀትዎን ጠብቀው ይንቀሳቀሱ፤
👉 ተበጥሶ የወደቀና የተንጠለጠለ የኤሌክትሪክ ገመድ ወይም ሽቦ ሲያዩ ከመንካት በመቆጠብ ለሚመለከተው አካል ያሳውቁ፤
👉 በከፍተኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ወይም አጠገብ ማንኛውንም የግንባታ ሥራ ከማከናወን ይጠበቁ፤
👉 ህንፃዎች ሲገነቡ ከኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ፤ ዛፎች ሲቆረጡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ያድርጉ፤
👉 የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ከቆርቆሮ ጣሪያ፣ አጥር፣ ከልብስ ማስጫ ገመዶች ጋር እንዳይገናኙ ያድርጉ፤
👉 የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት በባለሞያ እንዲከናወን ያድርጉ፤
👉 ደረጃቸውን የጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን ይጠቀሙ፤
👉 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መሳሪያዎች ላይ ቃጠሎ ሲነሳ በውሀ ከማጥፋት በመቆጠብ ትክክለኛውን የእሳት ማጥፊያ ይጠቀሙ፤
👉 የኤሌክትሪክ መስመሩን ከመቆጣጠሪያው ሳያጠፉ በኤሌክትሪክ የተያዘን ሰው ለማዳን አይሞክሩ፤
👉 የኤሌክትሪክ ሀይልን ከራስዎ ቆጣሪ ወደ ሌላ ሰው ቤት አሳልፎ ከመዘርጋት ይቆጠቡ፤
👉 ብረት ነክ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከኤሌክትሪክ ሶኬቶች ወይም ማከፋፈያዎች ጋር በፍፁም አያገናኙ፤
👉 በአንድ ማከፋፈያ ላይ ብዙ ኬብሎችን ማገናኘት ለአደጋ ስለሚያጋልጥ በፍፁም አያድርጉ፤
👉 በኤሌክትሪክ ሥራ ሲሰሩ ርጥብ ነገሮች ለአደጋ ሊያጋልጥዎ ስለሚችሉ መጠንቀቅ አይዘንጉ፤
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ኤር ኮንጎ”ን ሥራ አስጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ በይፋ ስራ ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡
ኤር ኮንጎ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት ጀምሯል ተብሏል።
ይህ ጥምረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2035 አንዱ አካል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚህም በፊት በሎሜ አስካይ አየር መንገድ፣ በሊሎንግዌ የማላዊ አየር መንገድ እንዲሁም በሉሳካ የዛምቢያ አየር መንገድን በጋራ ማቋቋሙ ይታወሳል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አቶ ዱቤ ጅሎ 0 ድምጽ አገኙ። የምርጫው ውጤት ምን ይመስላል ?
💧 አትሌት ስለሺ ስህን 👉 11 ድምጽ (ከኦሮሚያ ክልል)
💧 አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም 👉 9 ድምጽ (ከትግራይ ክልል)
💧 ያየህ አዲስ 👉 4 ድምጽ (ከአማራ ክልል)
💧ሪሳል ኦፒዮ 👉 1 ድምጽ (ከጋምቤላ ክልል)
💧 ኮማንደር ግርማ ዳባ 👉 1 ድምጽ (ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል)
💧 አቶ ዱቤ ጂሎ 👉 0 ድምጽ (ከአዲስ አበባ)
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
እርቅ የፈፀሙ የኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል የሀገራዊ ምክክር ላይ መሳተፍ ጀመሩ።
በቅርቡ ከመንግስት ጋር እርቅ በመፈፀም የገቡ የኦሮሚያ ክልል ታጣቂ ኃይሎች በክልሉ እየተካሄደ ባለው የሀገራዊ ምክክር ላይ እየተሳተፉ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮምሽን ኮምሽነር አምባሳደር ሞሀመድ ድሪ የራቁት ቀርበዋል፣የቀረቡትም ገብተዋል፣የገቡት እዚሁ እንዲቀሩ አበክሮ መስራት ይገባል ብለዋለል።
አባሳደር ባስተላለፉት መልእክት "አንድ ቤት ለመስራት የሚጣደፉ ሰዎች ለቤቱ ግብአት የሚሆን ቁሳቁስ አይሰራረቁም" ነው ያሉት።
በመሆኑ የምንሰራው፣የምንገነባው አንድ ቤት ነውና በሃሳብ ተለያይታቹ በጫካ ውስጥ ያላቹ አሁንም ቅረቡልን ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮምሽን ዋና ኮምሽነር ፕ/ር መስፍን አርዐያ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣
የመንግስት ተወካዮች ለሀገር የሚሆነውን ሁሉ እንደምትሰጡን እናምናለን ብለዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ በተከፋፈለ ሳይሆ አንድ ሆናቹ፤ ለኦሮሞ ህዝብና ክልል እንዲሁም ለኢትዮጵያ የሚበጃትን ሃሳብና ምክር እንድት ሰጡን እንፈልጋለን ብለዋል።
ለሀገር እድገትና ሁለንተናዊ ልማት የናተ ተፅኖፈጣሪዎች ሚና ላቅ ያለ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዚህ መድረክ የተመረጡ የህብረተሰብ ወኪሎች፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት ተወካዮች፣ የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች እንዲሁም የማህበራትና ተቋማት ወኪሎች ተገኝተዋል።
በመጨረሻም በሶስት ቀናት ውይይት ውስጥ ለሀገራዊ ምክክር ጉባዬው ተወካዮቻቸውን እና አጀንዳዎቻቸውን እንደሚያስረክቡ ተነግሯል ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ቢሮው ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እውቅና ተበርከተ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እውቅና ሰጠ።
በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በቢሮ እና በፌዴሬሽኑ የተዘጋጀ የክብር ካባ እና የአንገት ሃብል ሽልማት ተበርክቶላታል።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባለፉት አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑ በብቃት በመምራት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዲል ላበረከተችው አስተዋጽዖ የተበረከተ ሽልማት መሆኑን ገልጸዋል።
በኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የሚመራው ፌዴሬሽኑ በአዲስ አበባ ስፖርት ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳበረከቱ ያወሱት አቶ በላይ ለአገር የከፋሉትን ዋጋ ጀግኖችን ማክበር በሁሉም መስክ ሊለመድ ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለዓለም አትሌቲክስ እና ለአትሌቲክስ ስፖርት ላበረከተችው አስተዋፅኦ እውቅና መሆኑን ገልጸዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ካላችሁ ነገር ጀምሩ!
ያለፈው ታሪካችሁ የሰጣችሁ ልምድና ያስተማራችሁ ትምህርት አላችሁ፡፡ እሱን ለወደፊት ስኬታማነት እንዴት እንደምትጠቀሙና እንደምታተርፉበት በማሰብ ከእሱ ጀምሩ!
ዛሬ የሚባል ፈጣሪ የሰጣችሁ ጊዜ አላችሁ፡፡ እሱን በምን መልኩ እንደምትጠቀሙበትና እንደምታተርፉበት በማሰብ ከእሱ ጀምሩ!
ነጋችሁን ስታስቡ መሆንና ማድረግ የምትፈልጉት ነገር በውስታችሁ አለ፡፡ እሱን እንዴት እንደምታሳድጉትና ትርፋማ እንደምታደርጉት በማሰብ ጀምሩ፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
ዛሬ ከቀኑ 5 ሠዓት ከ20 ላይ በፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡
ከአሁን ቀደም የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰትበት በነበረው ፈንታሌ አካባቢ ዛሬም ክስተቱ መስተዋሉን በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ገልጸዋል፡፡
በሬክተር ስኬልም 4 ነጥብ 3 መመዝገቡን አረጋግጠዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ ያደረሰው ጉዳት መኖሩ ወይም አለመኖሩ በቀጣይ እንደሚገለጽም መናገራቸው ፋና ዘግቧል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ኢትዮጵያ ውስጥ እርስ በእርስ መባላት፣ መጠላላት፣ መገፋፋት፣ መፈናቀል፣ መቆም አለበት። አደገኛ ነገር ነው" የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ፓርቲያችን ብልፅግና በመደመር መንገድንና እሳቤ ለጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ ሰፋፊ ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። ብዝኃነት ለሰፈነባት ኢትዮጵያ ታሪክን፣ ተረክን እና ትርክት በመረዳት የጋራና የሚያግባባ ብሔራዊነት እጅግ ወሳኝ ነው" - አቶ ዘሪሁን ዘለቀ - በብልፅግና ፓርቲ የቂርቆስ ወረዳ 02 ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቅርብ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜይክ ጋር በልዩ ልዩ የትብብር መስኮች ዙሪያ በሚኖረን የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ተወያይተናል።
በትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ በተመሰረተው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲሁም የፈረንሳይ መንግስት በከተማችን በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ዙሪያ ስለሚያደርገው ድጋፍ ከአምባሳደር ላሜይክ ጋር የተወያየን ሲሆን፣ አዲስ አበባ ከተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች ጋር ያላትን የጠበቀ ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያም ተነጋግረናል፡፡
Today, we held a discussion with the recently appointed Ambassador of France to Ethiopia, Alexis LAMEK, focusing on strengthening the bilateral relations between our two nations across various fields of cooperation.
Our conversation emphasized the strong partnership built on mutual benefit and the French government's valuable support for the development initiatives in Addis Ababa. We also explored opportunities to further enhance Addis Ababa's ties with various French cities, fostering deeper collaboration and friendship.
ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በሸገር ከተማ ከመለስተኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 5 ሺሕ 287 መምህራን፤ ምግብ እየቀረበ መሆኑን የሸገር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የመምህራን ምገባ መርሐ-ግብር ዋና ዓላማ በትምህርት ጥራት ላይ ለውጥ ማምጣት መሆኑንም የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍረኪያ ካሳሁን፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተወዳዳሪ ትውልድ ለማፍራት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች በመተግበር ላይ እንደሚገኙ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል።
ከመርሐ-ግብሮቹ መካከል የተማሪና መምህራን ምገባ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአሁኑ ወቅት በከተማው በሚገኙ 268 ትምህርት ቤቶች ከ151 ሺሕ በላይ ተማሪዎች በምገባ መርሐ-ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም "ከመለስተኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ 5 ሺሕ 287 መምህራን ምግብ እየቀረበ ነው" ብለዋል።
ይህም የመምህራን ምገባ መርሐ-ግብር ከመምህራን ጥቅማጥቅም ጋር ተያያዥነት የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል።
የምገባ መርሐ-ግብሩን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ መምህራን፤ የምግብ አቅርቦቱ ለትምህርት የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡ ያስቻላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የመማር ማስተማር ሂደቱን በተረጋጋ መንፈስ ለማከናወን እንዳስቻላቸው ገልጸው፤ "የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ ትልቅ ሚና እየተጫወተ በመሆኑ ሊጠናከርና ሊስፋፋ ይገባል" ማለታቸውን ዘገባው አመላክቷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"ተነሣሽነት"ከመደመር እስቤ አንፃር!
ከመደመር መሠረታዊ አንዱና ትልቁ ጉዳይ "ተነሣሽነት"ነው፡፡ ተነሣሽነት ማለት ማንኛውም ግለሰብ ወይም ንዑስ ሥርዓት ከከባቢው ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ውስጥ የግንኙነቱ ለኳሽ መሆን ማለት ነው። በርን ዘግቶ በለውጥ ዕጦት በብቸኝነት ጉድለት ውስጥ ከመበስበስ ይልቅ፣ የጎረቤትን በር ማንኳኳት ማለት ነው። ተነሣሽነት ከአልህ፣ ከኩርፊያ፣ ከጠባቂነት እና ከፍዝ ባሕርይ ወጥቶ ለመጀመሪያው ግንኙነት እጅ መዘርጋት ማለት ነው።
ሥርዓቶች ከብቸኝነት አዙሪት ተላቀው ወደ ለውጥ ለማምራት የለውጥ ምንጮች የሆነውን ከባቢያቸውን ለግንኙነት የሚቀሰቅሱ ሰዎች ያስፈልጓቸዋል። ልሂቃን ንዑስ ሥርዓቱ ከሌሎች ንዑሳን ሥርዓቶች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማወቅ መዋቅራዊ ዕድል ያላቸው በመሆናቸው ሁሌም ግንኙነትን ለመለኮስ መጣር አለባቸው። ጥቂት ወይም ደካማ ልሂቃን ያሉበት ሥርዓት ተነሣሽነት ወስደው ከከባቢው ጋር የሚያገናኙት አስተዋይ ሰዎች አያገኝም። በአንጻሩ ንቁና ብዙ ልሂቃን ያሉበት ሥርዓት የብቸኝነት ጉድለትን በቶሎ ተገንዝበው ሥርዓቱን ከከባቢው ጋር ለማገናኘት ተነሣሽነት ያላቸው ሰዎች ይኖሩታል።
መደመር የልሂቃንንና እነሱ የሚመሩትን ሕዝብ ጉልህ ተሳትፎና ተነሣሽነት የሚፈልግ ሂደት ነው። ቃሉም ሌሎችን መሳብ ሳይሆን የራስ መሄድን ታሳቢ የሚያደርግ ነው። አባቶች ሲያስታርቁ “አስኪ ባንተ ይቅር” እንደሚሉት ሁሉ “በእኔ ይቅር" ብሎ ለግንኙነት መነሣሣትን የሚያመለክት ነው። ስለዚህም በመደመር ውስጥ ነገሮችን በሌላው ወገን ማላከከ ትርጉም የለውም። “አልመጣ ብሎኝ ነው" ከሚል ክስ ተላቀን የራሳችንን መሄድ ይፈልጋል። በዚህ ተነሣሽነት ውስጥ ነው መደመር ዕውን የሚሆነው።
የሰዎችን የተነሣሽነት መጠን ተከትሎ መደመር በተለያዩ ደረጃዎች ሊከፋፈል የሚችል ሂደት ነው። በዋናነትም የመደመርን ሂደት በሦስት ደረጃዎች ከፋፍሎ መመልከት ይቻላል፤ እነሱም “አልፎ ሂያጅነት"፣ "እንግድነት" እና "ቤተኛነት" ናቸው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ትብብር እና ፉክክር ለዴሞክራሲያችን መዳበር!
በኢትዮጵያ የዳበረ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማህበራት ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡ ሀገራችን የነበሩባት በርካታ ፖለቲካዊ ስብራቶች የሚጠገኑት በአንድ አካል ርብርብ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ተዋንያኖች ትብብር መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ሁሉንም አሳታፊ ያደረገ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመፍጠር በመንግሥት በኩል ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል። አሳሪ ህጎች ተወግደዋል፤ ለሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መጠናከር ሰፊ ድርሻ ያላቸው ገለልተኛ እና ነፃ ተቋማትም ተገንብተዋል፡፡
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህጋዊ በሆነ መንገድ ተደራጅተው ሰላማዊ በሆነ አካሄድ በሃሳብ የበላይነት አሸናፊ መሆን የሚችሉበት አሠራርም ተዘርግቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የስልጣን ምንጭ የህዝብ ድምፅ መሆኑን የማይቀበል የትኛውም የፅንፈፅነት አካሄድ የትም እንደማያደርስ በተለይም ከለውጡ በኋላ ዴሞክራሲን ለማፅናት በተደረጉ ጥረቶች ተረጋግጧል፡፡
ፅንፈኝነት የትናንት ተቸካይ አስተሳሰብ ስለሆነ ከዘመኑ ጋር መራመድ አይችልም፡፡ ፓርቲያችንም ደጋግሞ እንደሚለው ጥራት ያለው አሻጋሪ ሀሳብ የፖለቲካ ፓርቲዎች የህልውና መሰረት ነው፡፡ የሀሳብ ድርቀት ለትውልድም ሸክም ለሀገር ደግሞ እዳ ነው፡፡
የሀገራችን የፖለቲካ ባህል እንዲያብብ ለህግ የበላይነት ተገዥ እንዲሆን የትብብር እንዲሁም የፉክክር ባህልን መገንባት ወሳኝ ነው፡፡
ፓርቲያችን ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ከወሰዳቸው አበረታች እርምጃዎች በተጨማሪ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በፉክክርና በትብብር ለመስራትም በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ አጠናክሮም ይቀጥላል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት
#aa_prosperity
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የመራራነት ጣጣ
የነጮች የበላይነትና ባርነት ሕጋዊ በነበረበት ዘመን አንዲት ለነጮች ብቻ የተዘጋጀች የመዝናኛ መርከብ ነበረች፡፡ እነዚህ ነጮች እጅግ ዘረኞች ስለነበሩ አንድም ጥቁር አብሯቸው እንዲዝናና አይፈቅዱም ነበር፡፡
አንድ ቀን በመዝናናት ላይ እያሉ ባልተጠበቀ አደጋ በድንገት መርከቧ ተናወጠችና መስጠም ጀመረች፡፡ ነጮቹ በፍርሃት ተሰበሱቡና ምን እናድረግ ሲሉ፣ አንዱ፣ “ጥቁሮቹ የሚያደርጉትን እናድረግ” በማለት መከረ፡፡ ግራ የገባው ሌላኛው፣ “ጥቁሮች የሚያደርት ምንድን ነው?” ሲለው፤ “ጥቁሮችማ ሁል ጊዜ በመከራ ውስጥ ስላሉ እንደጸለዩ ነው፡፡ እኛም ዛሬ መከራ ውስጥ ስላለን እንጸልይ!” በማለት አብራራ፡፡
እነዚህ ነጮች ችግራቸው፣ በመካከላቸው ማንም ሰው ከዚህ በፊት ጸልዮ የሚያውቅ ሰው ስለሌለ ጸሎት የሚያደርስ ጠፋ፡፡ ትዝ ሲላቸው በመርከቢቱ ውስጥ ለአብሳይነት የተቀጠረ አንድ ጥቁር እንዳለ አስታወሱ፡፡ ይህ ጥቁር በመርከቧ የታችኛው ክፍል ተዘግቶበት ለማብሰል ብቻ ነው የሚጠቀሙበት፡፡ ወደላይኛው ክፍል እንዲመጣ በፍጹም ባይፈቀድለትም ለዚያ ጊዜ ግን ለጸሎት ሲሉ ህጋቸውን በመጣስ አስጠሩት፡፡
ይህ ጥቁር ግራ ገብቶት እየተደናበረ መጣ፡፡ እንዳይመጣ በማስጠንቀቂያና በዛቻ ወደተነገረው ቦታ በክብር መጠራቱ አስገርሞታል፡፡ ፊቱ ግን ሊፈታ አልቻለም፤ ምክንያቱም መልቀቅ የማይፈልገው የብዙ አመት የመገለል መራራነት ውስጡ አለ፡፡
ቶሎ ጸሎቱን እንዲያደርግ ሲያጣድፉት እንዲህ አለ፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ በራበኝ ጊዜ ወደ ምግብ ቤት ለመመገብ ስሄድ፣ ምልክቱ ለነጮች ብቻ
ይላል፡፡ ወደ ሕዝብ መጸዳጃ ቦታ ስሄድ፣ ምልክቱ ለነጮች ብቻ
ይላል፡፡ እዚህም መርከብ ውስጥ ወደላይኛው መዝናኛ ክፍል ለመምጣት ሞክሬ፣ ምልክቱ፣ ለነጮች ብቻ
ያላል፡፡ ሁሉም ነገር ለነጮች ከሆነ፣ ፈጣሪ ሆይ! አሁን የምጸልየው ጸሎት ምንም እንኳን ኃይማኖቴ ካስተማረኝ ትምህርት ጋር ባይስማማም እባክህ ስማኝ፣ ሁሉም ነገር ለነጮች ብቻ ሲባል እንደከረመው ሁሉ፣ ይህች መርከብ ስትሰጥም የሚከሰተው ችግር ሁሉ ለነጮች ብቻ እንዲሆን እለምንሃለሁ”፡፡
ማንኛውም ሕብረተሰብም ሆነ ግለሰብ (እኛንም ጨምሮ) ከውስጡ የሚያወጣውን ሃሳብ በሚገባ ካጤንነው አምቆ የያዘውን ስሜት ጠቋሚ ነው፡፡ ማንኛውም በውስጣችን አምቀን የያዝናቸው አሉታዊ ስሜቶች በየጊዜው በትክክለኛው መንገድ ካላናፈስናቸውና ካልተነፈሱ በየእለት ንግግራችንና ተግባራችን መገለጣቸው አይቀርም፡፡
አየህ ያልተናፈሰና የታመቀ የመራራነት ስሜት ምንም ነገር ከማድረግ እንዳንመለስ “በቂ ምክንያት” ይሰጠናል፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ ያልተናፈሰ መራራነት፣ “የማድረግ መብቴ ነው” እና “የይገባቸዋል” ስሜትን በውስጣችን የመፍጠር ጉልበት ስላለው ከትክክለኛው ጎዳና ያወጣናል፡፡ ቤተሰብ መክሮ ያሳደገን ሌላ፣ ንግግራችንና ስራችን ግን ሌላ … ኃይማኖታችን ያስተማረን ሌላ ንግግራችንና ስራችን ሌላ … ማድረግ እንደሚገባን የምናውቀው እውነታ ሌላ፣ የእኛ ተግባር ግን ሌላ … የሚሆነው በውስጣችን የተጠራቀመ መራራነት ሲኖረን ነው፡፡
ለመራራነት ሊኖረን የሚገባ ብቸኛ ምላሽ ከውስጣችን ማውጣት ብቻ ነው፡፡ ያማረሩህ ቤተሰቦች፣ ፍቅረኛህ፣ አለቃህ፣ የአካባቢህ ባለስልጣን፣ የሕዝብ አገልግሎት መስሪያ ቤት ሰራተኞች፣ ዘረኝት የተጠናወታቸው የሃገርህ ዜጎች . . . ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ይህ መራራነትህ በክፉ ቃላትና በጭካኔ ተግባር ከመገለጡ በፊት አናፍሰው፣ አስተንፍሰው! የእነሱ ሰለባ ከመሆን ይልቅ ከዚያ በላይ እንደሆንክ ራስህን አሳምን፣ አቅጣጫ ቀይር፣ ተሽለህ ተገኝ፡፡ ይህንን ማድረገ ከባድ የሆነ ነገር ነው፤ ነገር ግን ምርጫው ይህ ብቻ ነው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።
በደሴ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡ ከየክፍለ ከተማው በተለያየ አቅጣጫ በመውጣት ወደ ሆጤ ስታዲየም እያቀና ነው፡፡
የድጋፍ ሰልፈኞቹ መንግስት በተደጋጋሚ የሚያደርገውን የሰላም ጥሪ እንደግፋለን፣ ፅንፈኛ ሀይሎች ለህግ ይቅረቡልን፣ ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን፣ መንግስት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን የሚሉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛሉ።
መንግስት ህግ በማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል፣ ፅንፈኛው ሀይል በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ግድያ፣ ማገትና ማፈናቀል ሊቆም ይገባል፣ መከላከያ ሰራዊታችን፣ የፌዴራልና የክልላችን የፀጥታ ሀይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን የሚሉም እንዲሁ።
በተመሳሳይ በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ ለክልሉ ሰላም መስፈን የመከላከያ ሰራዊት የክልልና የፌዴራል የፀጥታ ሃይሎች ለከፈሉት ዋጋ ክብር እንሰጣለን፣ ሰላማችንን እናፅና ልማታችንን እናስቀጥል የሚሉና ሌሎችም መልክቶችን በማስተላለፍ ነዋሪዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውኃ ከተማም እንዲሁ ህዝባዊ ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፉ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በዚህም ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተሳታፊዎቹ ክልላችንን የሰላምና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን!፣ መንግስት ለሰላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን! የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች እየተስተጋቡ ነው።
በሌላ በኩልም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችም የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛሉ።
ነዋሪዎቹ በከተማው ፋሲለደስ ስታዲየም እያካሄዱት ባለው የድጋፍ ሰልፍ ክልላችንና ከተማችን የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ልማትና ሠላም ነው ሲሉ በያዙዋቸው መፈክሮች አስተጋብተዋል።
መንግስት ለሠላም መስፈን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች እንደግፋለን፣ የመከላከያ ሠራዊቱና የክልሉ የጸጥታ ሀይል ለሠላም መስፈን እየከፈሉት ላለው መስዋእትነት ክብር እንሰጣለን ብለዋል እያስተጋቡት ባለው መልዕክት።
በክልሉ የተለያዩ ከተሞቹ የሚገኙ የኢዜአ ሪፖርተሮች ተዘዋውረው እንደተመለከቱት በሰልፉ ላይ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ተማሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ቪኒሺየስ ጁኒየር የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ
የፊፋ የ2024 ምርጥ እግር ኳስ ሽልማት አሸናፊዎች በዛሬው ዕለት በኳታር ዶሃ ከተማ በተካሄደ ስነ ስርዓት ይፋ ሆነዋል።
በዚሁ መሰረት፤ ለሪያል ማድሪድ ክለብ የሚጫወተው ብራዜላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ቪኒሺየስ ጁኒየር የ2024 የውድድር ዘመን የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ወንድ ተጫዋች ሆኖ በአብላጫ ድምፅ ተመርጧል።
የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ደግሞ የ2024 የውድድር ዘመን የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ወንድ አሰልጣኝ ሽልማትን አሸንፈዋል።
በሌላ በኩል የማንቺስትር ዩናይትድ ተጫዋች አልሃንድሮ ጋርናቾ የዓመቱ ምርጥ ጎል ሽልማትን ሲያሸንፍ፣ የአርጀንቲናው ግብ ጠባቂ ኤሚ ማርቲኔዝ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሽልማትን አሸንፏል፡፡ የፊፋ የዓመቱን ምርጥ ደጋፊ ሽልማት የ8 ዓመቱ ታዳጊ ጉሄርሜ ጋንድራ ሞራ ሲያሸንፍ፤ ብራዜላዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ቲያጎ ማያ የዓመቱ የፊፋ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማትን ወስዷል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጥብቅ የጥንቃቄ መልዕክት !
ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ደንበኞች በሙሉ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ያልሆኑ አካላት የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ነን በማለት ለተከራይ ደንበኞቻችን የተሳሳተ መረጃ በመስጠት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከአንዳንድ ደንበኞቻችን ጥቆማ ደርሶናል፡፡
በመሆኑም ጉዳዩን አጣርተን እርምጃ እስከምንወስድ ድረስ የኮርፖሬሽኑን መታወቂያ ያልያዙ ማንኛውንም ሰው እንዳታስተናግዱ እናሳስባለን፡፡
ኮርፖሬሽኑ!!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹