prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1397

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የፈረንጆችን ገና ለሚያከብሩ ሁሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የፈረንጆችን ገና ለሚያከብሩ ሁሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በዓሉ ሰላምን፣ ደስታን እና ተጨማሪ በረከቶችን እንዲያመጣም ተመኝተዋል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በጋዛ እና በዌስት ባንክ የሚገኙ ክርስቲያኖች የእስራኤል የዘር ፍጅት እንዲያበቃ የፀሎት ስነ ስርዓት አደረጉ

የክርስቶስ የልደት ስፍራ በሆነችው የፍልስጥኤም ግዛት የዌስት ባንክ ከተማ ቤቴልሄም እና በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ክርስቲያኖች የእስራኤል የዘር ፍጅት እንዲያበቃ የፀሎት ስነ ስርዓት አድርገዋል።በጋዛ የሚኖሩ ክርስቲያኖች እስራኤል የምትፈፅመው ሞትና ውድመት እንዲያበቃ በመጸለይ የገናን በዓል አክብረዋል። በዌስት ባንክ ከተማ ቤተልሔም የኢየሱስ የትውልድ ቦታ በርካቶች ጸሎታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በእስራኤል “የዘር ማጥፋት” ሰለባዎችን በማስታወስ ፀሎት አድርገዋል።

የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ቦታ በሆነችው በ
ቤተልሔም በየዓመቱ የፍልስጤም ከተማን ይጎበኙ የነበሩ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች በጋዛ ጦርነት እና በዌስት ባንክ የእስራኤል ጥቃት እየተባባሰ በመቀጠሉ ለመገኘት አልቻሉም። በጋዛ በቀጠለው የእስራኤል ጥቃት በአደጋ ጊዜ አገልግሎት እና በፍልስጤም ግዛት ውስጥ የፍለጋ እና የማዳን ስራዎችን የሚያከናውነው የፍልስጤም ሲቪል መከላከያ ቢሮዎች ላይ ደርሷል።

ጸጥታ የሰፈነበት ምሽት(Silent Night) የሚለው መዝሙር በቤተልሔም ውስጥ ሰላማዊና ጸጥታ የሰፈነበት ምሽት እንደነበረ የሚናገር የታወቀ የክርስቴስ ልደት መዝሙር ሲሆን ይህም ከ 2,000 ዓመታት በፊት የመጀመሪያውን የውልደት በዓልን በመጥቀስ ይዘመሬል።አሁን 2024 ነው፣ እናም እንደገና በቤተልሔም ጸጥ ያለ ምሽት አልፏል። ፀጥታው ስለ ሰላም አይደለም። ግን የሰላም እጦት ነው። እስራኤል በጋዛ ላይ ያካሄደችው ጦርነት እና በዌስት ባንክ ውስጥ ያለው ጥቃት በዚህ አመት በተለምዶ ቤተልሔምን የሚጎበኙ ቱሪስቶችን አስፈራርቷል

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በፍቅር ፍርሃት የለም ...

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ፓስፖርት‼️

ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአዲስ ፖስፖርት አመልካቾች አሻራና ፎቶ ለመስጠት በቀጠሮ ቀናቸው ያልተገኙ ሰዎች እንደገና እንደሚያመለክቱ ታውቋል።

በዚህም በዋና መስሪያ ቤትም ይሁን  በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቻች በቀጠሮ ቀን ሲመጡ የታደሰ መታወቂያ እና የልደት የምስክር ወረቀት ኦርጅናል ይዞ መቅረብ ግዴታ ነው።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

👆 የከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለ ኮሪደር አረንጓዴ ልማት ስራዎች ምን ይላሉ? 👆

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Hiriira Waamicha Nagaa Godina Gujiitti!

Hawaasni Godina Gujii qaama hidhatee bosonatti hafeef waamicha nagaa marsaa 2ffaa taasise.

Hiriirri waamicha nagaa kun Abbootii Gadaa, Jaarsolii biyyaa, Abbootii Amantaa, Haadholii Siinqeefi kutaa hawaasa garaa garaa hirmaachisee gaggeeffameera.

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የስደተኛው ፕሬዚዳንት ባለቤት ፍቺ ጠየቁ           

በቅርቡ ከሥልጣን የተባረሩት የሶርያ ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ  ባለቤት የፍቺ ጥያቄ  ለሩሲያ ፍርድ ቤት  አቀረቡ፥ የብሪክስ  ልሳን እንደዘገበው የበሽር አልአሳድ ባለቤት አስማ አል አሳድ  ከስደተኛው ባለቤታቸው ከተፋቱ በኋላ ክሞስኮ ወደ ትውልድ ከተማቸው ለንደን መመለስ አቅደዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በአዝናኝ ቪዲዮ ከመጠን በላይ በመሳቁ አንድ ቻይናዊዉ የሳንባ መሰንጠቅ አጋጠመው

ሰውዬው የመተንፈስ ችግር ገጥሞት ሆስፒታል ሄዶ አስቂኝ ቪዲዮዎችን በኢንተርኔት እያየ እንደ ፈረስ እየሳቀ ነበር ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ራስ ምታት ያዘውና መተንፈስ አስቸጋሪ ሆነበት።

የኤክስሬ ውጤት በሳምባው ላይ ስንጥቆችን አሳይቷል። ይህም ከመጠን በላይ በመሳቅ ምክንያት ነው ሲሉ ሰሞኑ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ስንስቅ በመጠኑ ይሁን 😁🤔

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች 8 ሺህ 843 መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለመምህራን መሰጠታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የተለያዩ ኢኒሼቲቮች ተቀርጸው እየተተገበሩ ነው።

የመማሪያ መጻሕፍት ሥርጭት፣ አዳዲስ ት/ቤቶችን መገንባትና ነባሮችን የማጠናከር እንዲሁም የተማሪዎችን ምገባ ማስፋፋት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል የመማር ማስተማር ሒደቱ የጀርባ አጥንት ለሆኑት መምህራን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም በክልሉ የሚገኙ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የመስሪያ ቦታና የተገነቡ ቤቶች እየተሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም ቢሮው በተለያዩ የወረዳና ገጠር ከተሞች 8 ሺህ 843 መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለምህራን ማስረከቡን ነው የተናገሩት።

የግንባታ ወጪው ከመንግስት፣ ከህብረተሰቡና ከባለሃብቶች የተገኘ መሆኑን አቶ ሃሰን አስረድተዋል።

የትምህርት ጥራትን በዘላቂነት ለማሳደግ ከመምህራን በተጨማሪ ወላጆችና የትምህርት ማህበረሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#አዲስአበባ በህብረብሔራዊነት የፍቅርና የሰላም ከተማ የሆነች ከተማችን የአፍሪካ መዲና እና የዓለም ዲፕሎማቲክ የስበት ማዕከል 🙏🙏🙏

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ማሳየት ድርድር  ዉስጥ የሚገባ አይደለም" - ኢማኑኤል ማክሮን
#ዐብይ_አህመድ
#ከእዳ_ወደ_ምንዳ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ብልጽግናዊ ተምሳሌትነት ያፀና ሌላው የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ ማሳያ #አዲስአበባ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሞሀመድ ሳላህ በፕሪሚየር ሊጉ በውድድር ዓመቱ ከገና በዓሉ አስቀድሞ 15ግቦችና 11ለግብ የተመቻቹ ኳሶችን ማቀበል የቻለ የመጀመሪያው ተጫዋች ሁኗል

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

estifopp?_t=8sR1bQDedgj&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@estifopp?_t=8sR1bQDedgj&_r=1

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ከእየሱስ ክርስቶስ ቀጥሎ የእኔ አባት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ታላቅ ነው" - የኡጋንዳ መከላከያ አዛዥ

ይህን ያለው የኡጋንዳ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ እና የኘሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ሌተናንት ጀነራል ሙሃንዚ ካይነሩግባ ነው።

ከደቂቃዎች በፊት በትዊተሩ የአባቱን ታላቅነት ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ያነፃፀረበትን እንዲሁም ሱዳናውያንን ያስቆጣበትን ሌላ መልዕክት አሰራጭቷል።

አባቱ ዩዌሪ ሙሴቬኒን ከክርስቶስ በመቀጠል ታላቅ ናቸው ያለው ሙሃንዚ "  ካርቱምን እንድንይዝ እርሱ ካዘዘን ፥ነገውኑ እናደርገዋለን !! " ብሏል።

ጀነራሉ ባለፈው ሳምንት ጦራችንን አዝምተን ካርቱምን መቆጣጠር እንችላለን በማለት በትዊተር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት ብዙ ትችቶች ቀርቦበታል።

በጀነራሉ መልዕክት ክፉኛ የተበሳጨው የሱዳን መንግስት ኡጋንዳ በይፋ ይቅርታ እንድትጠይቅ መግለጫ አውጥቶ ነበር።

አወዛጋቢው ጄነራል ሙሃንዚ ግን ይለይላቸሁ በማለት መልዕክቱን በማስረገጥ ደግሞታል።

ያልተለመዱ እና ወጣ ያሉ ንግግሮችን በመናገር ውዝግብ የሚፈጥረው ማሁንዚ በመሰለው መንገድ መጓዝን ቀጥሏል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ 7መቶሺህ ኢትዮጵያዊያን መካከል 4መቶ50ሺዎቹ መደበኛ ያልሆኑ ናቸዉ ተባለ፡፡

ከ2017 እስከ 2023 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ከ5መቶ61ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉም ተገልጿል፡፡

93ሺህ 5መቶ የሚሆኑ ዜጎች በ2022 በግዴታ ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

በ2023 ደግሞ 43ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በግዴታ ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉን ዘ ፍሪደም ፈንድ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታዉቋል፡፡

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፤1መቶ33 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከሳዑዲ መመለሳቸዉን የገለጸ ሲሆን፤ 46 የሚሆኑት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ነበሩ ብሏል፡፡

ህጻናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ 6ሺህ ኢትዮጵያዊያንም ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታዉቋል፡፡

ከሱዳን ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ ወደ 47ሺህ 8መቶ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል ያለዉ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከየመን ከ4ሺህ በላይ ዜጎቻችን ተመልሰዋል ብሏል፡፡

በሁለት ዙር በተደረገ ስራ 2መቶ80ሺህ ዜጎች ወደ አገር መመለሳቸዉንም ሰምተናል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት በታሪክ ሂደትና በትላልቅ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ የተመሰረተ ነው" - ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

" ከከባዱ አደጋ አንዲትም ጭረት ሰውነታችንን ሳይነካን ነው የወጣነው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው !! " - ሳቢር ይርጉ

ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ እና ሳቢር ይርጉ አስከፊ ከሆነ የመኪና አደጋ አንድም ነገር ሳይሆኑ በህይወት ተረፉ።

ዛሬ ምሽት ከሱሉልታ አቅጣጫ አጣና ጭኖ ቁልቁለቱን ሲምዘገዘግ የነበረ ኤኔትሬ ከባድ መኪና ከነጭነቱ እነ ኡስታዝ ሲጓዙበት በነበረችው መኪና ላይ ከባዱ አደጋ አድርሷል።

ሳቢር ይርጉ ፤ " እንሆ የአላህን ኒዕማ አውጀናል። በአላህ ፈቃድ ሁለታችንም ከከባዱ አደጋ ምንም ሳንሆን ተርፈናል። ሁለታችንም አንዲትም ጭረት ሰውነታችን ላይ ሳይደርስ በሰላም ወጥተናል አልሀምዱሊላህ !! ወደ የቤታችንም ገብተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህይወት ስንተርፍ ሞትን አንዘንጋው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው። አልሀምዱሊላህ ጀዛኩሙላሁ ኸይር ! " ሲሉ አክለዋል።

አደጋው የደረሰባቸው ዛሬ ምሽት ለጥቂት ቀናት የሊደርሺፕ ስልጠና ለመካፈል እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።

መኪናዋን ሲያሽከረክሩ የነበሩት ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ ሲሆኑ ሁለቱም ከከባዱ አደጋ አንድም ጭረት ሰይነካቸው በህይወት ተርፈው ወደ ቤት ገብተዋል።

መረጃውን ያካፈሉን በድምጻችን ይሰማ የሰለማዊ እንቅስቃሴና ትግል በእጅጉ የሚታወቁት ሳቢር ይርጉ ናቸው

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሰላም ሲኖር ሁሉም ነገር ይኖራል

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሶማሊያ‼️

ሶማሊያና ኢትዮጵያ በቱርክ አንካራ ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ የስምምነቱን አፈፃፀም ለማጠናከር በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አሊ ኦማር የተቋቋመ ልዑክ በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አሥተዳደሩ ከ4 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ ፈጸመ

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በ4 ቢሊየን 415 ሚሊየን 778 ሺህ 750 ብር ወጪ ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ በርካታ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ግዥ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

እነዚህ ግዥ የተፈጸመባቸው ተሽከርካሪዎች ለቢሮ እና ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሙሉጌታ ይመር አስታውቀዋል፡፡

በአጠቃላይ ከታዘዙት መካከልም እስከ አሁን ከ214 ተሽከርካሪዎች በላይ ርክክብ መፈጸሙን እና አገልግሎት እየሠጡ መሆኑን ዳይሬክተሩ ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

ቀሪዎቹን ተሽከርካሪዎችም እስከ ሁለት ወር ባለው ጊዜ እንደሚረከቡ አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል ከምታከናውናቸው ዘርፈ-ብዙ ተግባራት መካከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት መጠቀም አንዱ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት እስከ አሁን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በግንባር ቀደምነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በብዛት በመጠቀም ቀዳሚ ሆኗል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር ገለፀ‼️

“ህዝባችን ወደ አመፅ እና ግርግር እንዲገባ ሌትና ቀን እየሰራ ያለው ቡድን ፥  ከዚህ ፀረ ሰላም ተግባሩ ካልተቆጠበ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር ከእንግህ እንደማይታገሰው” ገልጿል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ዛሬ ማለዳ 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ከፍ ባለ ሁኔታ ለማስተናገድ የመዲናችንን ቅድመ ዝግጅት ገምግመናል።

የአፍሪካዊያንና የዓለም የዲፕሎማቲክ ማዕከል፤ የህብረብሄዊነት አርማ የሆነችዉ ከተማችን አዲስ አበባ ይህንን ታሪካዊ ጉባኤ በደመቀ እና ባማረ መልኩ ለማስተናገድ ከወትሮ በተሻለ መልኩ እንግዶቿን ለመቀበል አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናት።

የከተማችን ነዋሪዎችም እንግዶችን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና እንገዳ ተቀባይነት ለመቀበል፣ በየአካባቢዉ ከወዲሁ ከተማችንን ውብ እና ፅዱ በማድረግ እንዲሁም በእንኳን ደህና መጣችሁልን መንፈስ ሃላፊነታችንን በመወጣት የሃገራችንን ስም እና ክብር ከፍ ለማድረግ ተባብረን እንስራ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ክብርት ከንቲባ አዴ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል

የዛሬዋ ቀን ሳታልፍ አንድ ነገር ላሳስብ፡- በዚህ አመት የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡

“ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” – Brian Tracy

አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡

ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡

የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡

ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡

“ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” –Henry David Thoreau

“የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” – Nora Roberts

“ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” - Unknown Source

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ህብር የገነባት መደመር ያፀናት የሁለንተናዊ ከፍታ ማሳያ ከተማ #አዲስአበባ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#አዲስአበባ ን የብልፅግና ተምሳሌት በማድረግ ተወዳዳሪ ለነዋሪዎች ምቹ ከተማ ትሆን ዘንድ እየተሰራ ነው።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

እነ ከቡ የቀደመውንም ፣ የዛሬውንም፣ የመጪውንም ዘመን እሳቤ ያልተረዱት የትየለሌ ጉዳዮች አሉ። ካለፈው ተምረው እስከመጡ ድረስ ችግር የለውም። የተሻላ ሀሳብ፣ ወንድማማችነትንና ብሔራዊነትን የሚያፀና ተወዳዳሪ ሆኖ የሚቀርብ ሀሳብ እስከሆነድረስ ችግር የለውም። ቀዳሚው ጉዳይ ኢትዮጵያ ናት። በስሟ የሚነግድባት ሳይሆን የሚሠራለት አዕምሮ መቼም ቢሆን አይንጠፍ። ለዚህ ቅዱስ ዓላማ የሚመጣ የትኛውም እሳቤ እንኳንም ዳህና መጣ ያስብላል። የቀደመው እኩይ ተግባር ግን መቼም አይሰራም፤ቅቡልነት የለውም። ምክንያቱም ያ እኩይ ድርጊት ለጉስቁልና ዳርጓታል። ያን አስከፊ ዘመን በተለየ ጥበብ አልፈንዋል፤ ችግሩንም አልፈን አስዳናቂ አሻራም አኑረናል። የነበረውንም እያደስን፣አዳዲስም እየፈጠርን ለመጪው ዘመን ተስፋ የሚያለመልሙ እርምጃዎችን እየወሰድን ነው። ቀጣዩ ጉዛአችን በኢትዮጵያ ተአምር ለመፍጠር እየተዘጋጀን ነው። መጪው የኢትዮጵያ ዘመን አዲስ እሳቤ፣ እይታና ከፍታ ይጠይቃል። ታላቋን ኢትዮጵያ ወደፊት የሚያራምዱ እና የሚያሸግሩ አስተሳሰቦች ሁሉ ቀና መንገድ አላቸው። እርግማን እየወረደባቸው፣ በችግሮች ሳይበገሩ አሻራ እያኖሩ ያሉ እንቁ መሪዎች ኢትዮጵያን እየገነቡ ነው። ይህን መቀልበስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ዛሬ ኢትዮጵያ ደርሳለች። ፈጣሪ ምርጥ መሪ ሰጥቷታል። ይህን መጠበቅና መጽናት የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለሚሹ ሁሉ በእጅጉ አስፈላጊ ነዉ።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የቲክቶክ ቻናላችን 👆👆👆

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አስቸጋሪ ሰዎችና ሁኔታዎች

በሕይወታችሁ በራሳቸው በሚሄዱ ችግሮችና መፍትሄ ካልፈለጋችሁላቸው እየባሱ በሚሄዱ ችግሮች መካከል የመለየትን ጥበብ አዳብሩ፡፡

አንዳንድ ሁኔታዎች ትኩረት ስትነፍጓቸውና ዋና ዓላማችሁ ላይ ስታተኩሩ በራሳቸው እየደከሙ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን የግድ ተገቢው ትኩረት ሊሰጣቸውና መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

የችግር ፈጣሪ ሰዎችንም ሁኔታ በዚሁ መልኩ በማየት በጥበብ ያዙት፡፡

ዛሬ ከመተኛታችሁ በፊት ያሉባችሁን ከሁኔታዎችም ሆነ ከሰዎች የሚመጡ ችግሮች ከእነዚህ ከሁለቱ የመፍትሄ መንገዶች መካከል በየትኛው መልኩ እንደምትቀርቧቸው አስባችሁ እደሩ፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሁሉ የሰላም ስምምነትን ፈፅመው በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን" - ጃል ሰኚ ነጋሳ 

ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሁሉ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ ገለጸ።

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ሁለተኛው ምዕራፍ የባለድርሻ አካላት ምክክር በአዳማ ከተማ ጨፌ ኦሮሚያ መሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት አባላት በምክክሩ እየተሳተፉ ሲሆን የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡ ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረመው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ የምክክሩን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥቶ፤ የኦሮሞ ህዝብም ምክክሩ ሰላም ያመጣል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡

ምክክሩ ምሉዕ የሚሆነው ሁሉም ዜጋ ሲሳተፍበት መሆኑን የተናገረው አመራሩ፤ ለዚህም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሁሉ እንደነሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በዚህ የምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በምክክር መድረኩ ሃሳቦችን በነፃ አንስተን፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከራክረን፣ ለዜጎች ሰላምና ደህንነት የሚጠቅሙ ሀሳቦችን ይዘን ስንወጣ ነው ምክክሩ የተሳካ የሚሆነው ያለው ጃል ሰኚ ነጋሳ፤ ለዚህም ሁላችንም ለምክክሩ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ሲል ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መድረኩን በማመቻቸቱ ጃል ሰኚ ነጋሳ ምስጋና አቅርቧል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…
Subscribe to a channel