የኬንያው ፕሬዘዳንት የምድራችን ቁጥር 2 ሙሰኛ መሪ ተባሉ፡፡
የተደራጀ ወንጀልና ሙስና ሪፖርት ፕሮጀክት (Organized Crime and Corruption Reporting Project) ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ነው የኬንያው ፕሬዘዳንት ሩቶ በምድራችን ቁጥር ሁለት ሙሰኛ መሪ ተብለው የተቀመጡት፡፡
DWAfrica እንደዘገበው ከሆነ ይህ ደረጃ የወጣው ከህዝብ የተሰበሰበን ድምጽ መሰረት በማድረግ ነው፡፡ በዚህ ድምፅ አሰጣጥ ስርአት መሰረት ሩቶ 40 ሺህ ድምፅ ያገኙ ሲሆን ይህ በድርጅቱ ወይንም በ (Organized Crime and Corruption Reporting Project) ታሪክ ትልቁ ድምፅ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ዊልያም ሩቶን በመብለጥ የምድራችን ቁጥር 1 ሙሰኛ ተብለው የተመረጡት ደግሞ ባሳለፍነው ወር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው የተባረሩት የቀድሞው የሶሪያ ፕሬዘዳንት በሽር አል አሳድ ናቸው፡፡
የኬንያው መሪ ዊልያም ሩቶ አስተዳደር መጠነ ሰፊ በሆነ የሙስና ወንጀል በተደጋጋሚ ይከሰሳል፡፡ የተደራጀ ወንጀልና ሙስና ሪፖርት ፕሮጀክት (OCCRP) አለም አቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ ሲሆን በህዝብ ድምፅ ላይ ተመስርቶ የሙሰኛ መሪዎችን ደረጃ ያወጣል፡፡
ከዚህ ባለፈም መሪዎች በስልጣን መባለግ፣ ሙስና ውስጥ መዘፈቅ እና የተደራጁ ወንጀሎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ በመገምገምም ስማቸውን በዚህ ዝርዝር ውስጥ ይመዘግባል፡፡
ፕሬዘዳንት ሩቶ አሁሩ ኬንያታን በመተካት ሀላፊነት የተረከቡት በፈረንጆቹ መስከረም ወር 2022 ነበር።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የፈረንጆች አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ለአዲስ አበባ ፖሊስ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን የፈረንጆቹን የአዲስ ዓመት ዋዜማ በዓል ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 6:00 እስከ 6:15 ሰዓት ላይ ርችት ይተኮሳል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
“የጫካ እና የመሳሪያ ትግል የነገሰበት የሀገሪቱ የፖለቲካ ሰንኮፍ ለመጨረሻ ጊዜ ይነቀላል" - ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
ባለፉት ጊዜያት የስልጣን ሽግግር በተቃርኖ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ተመስርቶ ይመጣ እንደነበር በብልፅግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊው ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ይናገራሉ።
ሀገሪቱ ያደረገቻቸው ያልተሳኩ የስልጣን ሽግግሮች የድህነት ቅነሳ ስራችን ውጤታማ እንዳይሆን፣ ከግጭት አዙሪት እንዳንወጣ፣ ስልጡን የፖለቲካ ምህዳር መገንባት እንዳንችል አድርጎናል።
ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በሚል የህዝብን ጥያቄ ይዘናል የሚሉ አካላት ጥያቄ የሚያነሱበትን መንገድ ኢቢሲ በአዲስ ቀን ሾው "የሀገር ጉዳይ" አድርጎ ተመልክቶታል።
በጉዳዩ ላይ ሃሳብ የሰጡት ዶ/ር ቢቂላ፥ በቀደሙት ጊዜያት የስልጣን ሽግግር በጎዳና ላይ ነውጥ፣ በትጥቅ ትግል፣ በመፈንቅለ መንግሥት፣ በተንኮል እና ሴራ የሚፈፀም እንደነበር ይጠቅሳሉ።
የፖለቲካ ምህዳሩ በሰላማዊ መንገድ ሃሳብን ሸጦ እና የህዝብ ይሁንታን አግኝቶ ስልጣን መያዝ ያልተለመደበት እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይህ ታሪክ መፋቅ እንዳለበት ብልፅግና ፓርቲ ያምናል የሚሉት ኃላፊው፤ ለዚህም ተፈፃሚነት ማናቸውንም እርምጃ እንደሚወሰድ ነው የሚገልፁት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#አዲስአበባ_ስታዲየም 👌👌👌
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድር በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚጀመር ተገለፀ
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ስፖርታዊ ውድድሩን አስመልክተው በሰጡት የሥራ መመሪያ የኦሜድላ ስፖርት ክለብን ወደ ቀደመ ገናና ስሙ ለመመለስና የፖሊስ ስፖርትን ለማነቃቃት በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ስፖርታዊ ውድድሩ ሠራዊቱን ለማነቃቃትና አንድነቱን የበለጠ ከማጠናከር ባለፈ በቀጣይ ከክልል እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር የፖሊስ ተቋማት ጋር ለሚደረገው የስፖርት ውድድር ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ እንደሚያግዝ እና ለምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት የስፖርት ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ነብዩ ዳኜ በበኩላቸው ውድድሩን በስፖርታዊ ጨዋነት ለማካሄድና የፖሊስን ክብር ይበልጥ ከፍ ለማድረግ የስፖርቱ ቤተሰብ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው ውድድሩ በቀጣይ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ፖሊስ 116ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ ድምቀት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
የሎጂስቲክ ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር ረዳት ኮሚሽነር እሸቱ ፊጣ የኢትዮጵያ ፖሊስ 116ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ቀንን አስመልክቶ ለሚደረገው ስፖርታዊ ውድድር የሚያስፈልጉ ትጥቆችን በማቅረብ እና ሌሎች ግብዓቶችን በማሟላት ውድድሩ ስኬታማ እንዲሆን ዋና መምሪያው ከፍተኛ ሥራ መሥራቱን ተናግረዋል።
በነገው ዕለት ለሚደረገው ስፖርታዊ ውድድር የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብር በዋና መሥሪያ ቤት የተከናወነ ሲሆን በወንዶች እግር ኳስ፣ በወንዶችና በሴቶች መረብ ኳስ፣ የጠረጴዛ ቴኒስ እና ገመድ ጉተታ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አምነው የወደዱ፣
ወደው የተካዱ፣
ተክደው የራዱ፣
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው፣
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው?
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው፣
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው፣
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው፣
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው፣
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው፣
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው፣
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?
መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ፣
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ፣
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ፣
ተገፍትረው ወድቀው፣
ደቀው እንዳይቀሩ፣
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አርቲስት ጌትነት እንየው
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዮሐ 19:30
የቀድሞ የአሜሪካ ኘሬዝደንት ጂሚ ካርተር በ100 አመት እድሜያቸው ማረፋቸው ተገልጿል።
39ኛው የአሜሪካ ኘሬዝደንት በመሆን ከ1977 - 1981 ለአንድ የስልጣን ዘመን በመሪነት አገልግለዋል።
ካርተር ከአሜሪካ የቀድሞ ኘሬዝደንቶች ረጅም እድሜ በህይወት በመቆየት ክብረወሰኑን ይዘዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በዛሬው ዕለት ብቻ ሰባት የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዘገበ
በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ ከሰሞኑ ከደረሱት የመሬት መንቀጠጥ ክሰተቶች በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ርዕደ መሬት ዛሬ እሁድ ምሽት መከሰቱን የጀርመን የጂኦሳይንስ የምርምር ማዕከል አስታወቀ።
በአካባቢው ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ 10 ላይ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ በሬክተር ስኬል 5.0 የደረሰ እንደሆነ የማዕከሉ መረጃ አመልክቷል።
በሬክተር ስኬል የመለኪያ መሳሪያ ከ2.5 እስከ 5.4 መጠን ያላቸው የመሬት መንቀጥቀጦች አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እንደሆኑ በዘርፉ ምርምር የሚያደርጉ ተቋማት ይገልጻሉ። የምሽቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ጭምር ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየ ንዝረት አስከትሏል።
ከአዋሽ ከተማ 14 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ስፍራ የተከሰተው የምሽቱ ርዕደ መሬት፤ በዛሬው ዕለት ብቻ በአካባቢው የተመዘገቡ መሬት መንቀጥቀጦችን ቁጥር ሰባት አድርሶታል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ብሔራዊ ቤተ መንግስት 🇪🇹
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ!
ይህ የትናንትናችን የነበረ፣ መንገዳችንን የሚመሰክር፤ ለጉዟችን ጉልበት የሚሆን ነው። ትናነት ያለን ህዝቦች ነን፤ ለተሻለ ነገ የማናንቀላፋ። በዚህ ቦታ ታሪክ በአይን እንዲታይ አስችለናል። ኑ ታሪኮትን ይመልከቱ!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ስዊድን ጦርነት ይከሰታል በሚል ለብዙ ሰዎች የቀብር ቦታ ማዘጋጀት ጀመረች‼️
ኔቶን በቅርቡ የተቀላቀለችው ስዊድን በሩሲያ ምክንያት ብዙ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ውስጥ ነች።
አሁን ደግሞ ከሩሲያ ሊሰነዘር በሚችል ጥቃት ምክንያት ሰዎች በብዛት ሊሞቱ ይችላሉ በሚል የቀብር ቦታ ማዘጋጀት ጀምራለች ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።
በስዊድን ካሉ ከተሞች መካከል በግዙፍነቱ ሁለተኛው የሆነው ጎትቦርግ ከተማ ብቻ በድንገት በሚከሰት ጦርነት ለሚሞቱ ሰዎች አራት ሄክታር መሬት ለቀብር አዘጋጅቷል።
የሀገሪቱ ከተሞች የቀብር ቦታ በስፋት ወደማፈላለግ የገቡት የስዊድን ጦር እና ሌሎች ተቋማት ጦርነት ሊኖር ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ ካሰሙ በኋላ ነው።
ከአንድ ወር በፊት ሩሲያ ኦሬሽኒክ የተሰኘውን የኑክሌር ሚሳኤል ወደ ዩክሬን መተኮሷን ተከትሎ ስዊድን ዜጎቿን ከኑክሌር ጦርነት ራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ማስተማር ጀምራ ነበር።
ከስዊድን በተጨማሪም ፊንላንድ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ዜጎቻቸውን በጦርነት ወቅት እንዴት ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚችሉ በማስተማር ላይ ናቸው።
ዴንማርክ እና ኖርዌይ ጦርነት ሊከሰት ይችላል ከሚል ስጋት ውጪ በሚያስተምሩት የቅድመ ጥንቃቄ ማስተማሪያ ይዘቶች ላይ የሩሲያን ስም አልጠቀሱም ተብሏል።
ሶስት ዓመት የሆነው የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ሲሆን ምዕራባውያን ለዩክሬን የረጅም ርቀት ጦር መሳሪያዎች በማስታጠቅ ላይ ናቸው።
ዩክሬን ከኔቶ አባል ሀገራት በምታገኛቸው የጦር መሳሪያ ድጋፍ በሩሲያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የአየር ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ላይ ናት።
ሩሲያ በበኩሏ ለዩክሬን የሚሰጡ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎች ሶስተኛው የዓለም ጦርነትን ሊቀሰቅስ እንደሚችል በተደጋጋሚ አስጠንቅቃለች።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በህንድ መሀንነትን ያስቀርልሀል ተብሎ ጫጩት ከነነፍሷ የዋጠው ህንዳዊ መሞቱ ተነገረ።
እንደ ኢንዲያን ቱደይ ዘገባ ከሆነ ቻቲስጋርህ በተባለ የህንድ ግዛት ውስጥ የሚኖረው አንድ የ35 ዓመት ሰው መሃንነትን ለመቅረፍ በሚደረገው የአምልኮ ሥርዓት ውስጥ አንዲት ጫጩት ከዋጠ በኋላ ነው ሀኪሚ ቤት ሲሄድ ህይወቱ ያለፈው።
ጫጩቷ ጉሮሮው ላይ ተሰንቅራ ትንፋሽ በማጣቱ የሞተ ሲሆን ጫጩቷ ከጎሮሮው ስትወጣ በህይወት መገኘቷ ተነግሯል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሕይወት ከባድም ቀላልም ነች!
“ዛሬ ሕይወት ከበድ ተደርጋ ስትያዝ ነገ ቀለል ትላለች፣ ዛሬ ቀለል ተደርጋ ስትያዝ ደግሞ ነገ ከበድ ትላለች” – Dave Kekich
ሕይወትን ከበድ አድርጎ መያዝ ማለት የግል ዲሲፕሊንን በማዳበር ለመልካም ውጤት ሲባል ከበድ ያሉ ነገሮችን መጋፈጥና ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሕይወትን ቀለል አድርጎ መያዝ ማለት ደግሞ ካለምንም ዲሲፕሊን የመጣልንን፣ የቀለለንንና ለጊዜው ብቻ ጥሩ ስሜት የሰጠንን በማድረግ መኖር ማለት ነው፡፡
ከላይ በተጠቀሰው አውድ መሰረት ዛሬ ሕይወትን ቀለል አድርጎ መኖር ማለት ዛሬ ለመደሰትና ዛሬ ሁሉም ነገር እንዲቀለን ስንል ከነገ የተቀማጭ ሂሳባችን አውጥቶ መክፈል እንደማለት ነው፡፡ ስለሆነም “ዛሬ” አልፎ “ነገ” ሲመጣና “ዛሬ” “ትናንት” ሲሆን አሁን የደረሰውን “ዛሬን” “ትናንትና” ቀላል ኑሮ ለመኖር ስንል ስለከፈልነው ኑሮ እጅጉን ይከብደናል፡፡
በጣም ደካማ ፈቃድ ያለውን ሰው አስቡት፡፡ አንድ ነገር ለማድረግ ያስብና ሁኔታው ከበድ ካለው ይተወውና ወደቀለለው ነገር ዞር ይላል፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ምንም ነገር ማከናወን ካለመቻም በላይ ዛሬ የቀለለው ሕይወት ነገ እንደሚከብደው ግልጽ ነው፡፡
በተቃራኒው ዛሬ ሆን ብሎ ከባባድ ምርጫዎችን በመምረጥ ተግቶ የሚማር፣ ጠንክሮ የሚሰራ፣ ወጥሮ የሚያጠራቅምና ታግሶ ችግርን የሚያልፈውን ሰው ተመልከቱት፤ ይህ ሰው ዛሬ ስለሚከፍል ቢከብደውም ነገ ግን ስለሚከፈለው ይቀለዋል፡፡
መልካም ውሎ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያደርግ አሳሰበ፡፡
በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡ ይታወቃል።
በአዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀጽ 3 መሠረት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበ ፓርቲ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ ያዛል።
ቦርዱም የፓርቲውን በልዩ ሁኔታ መመዝገብ ባሳወቀበት ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ቁጥር አ1162/11/15180 በግልፅ እንዳስቀመጠው ፓርቲው ይህው ደብዳቤና የምዝገባ ሰርትፊኬት ከደረሰው አንስቶ ባሉት ስድስት ወራቶች ውስጥ የቦርዱ ታዛቢዎች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባውን ማድረግ አንዳለበት አስታውቋል።
በሌላም በኩል አዋጅ ቁጥር 1332/2016 ዓ.ም ለማስፈፀም ባወጣው መመሪያ ቁጥር 25/2016 አንቀፅ 12 መሰረት በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበ የፖለቲካፓርቲ ምዝገባውን ካገኘበት ጊዜ አንስቶ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እንዳለበት ያዛል።
ፓርቲው ከፍ ብሎ የተመለከተውን የአዋጁንና የመምሪያውን ድንጋጌዎችና ቦርዱ ልዩ ምዘገባ ሰርትፊኬቱን ሲሰጠው በፃፈው ደብዳቤ ላይ የተገለፀውን በስድስት ወር ውስጥጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ የሚለውን ግዴታ ያለተጨማሪ ማሳሰቢያ መፈፀም እንዳለበት የሚታመን ቢሆንም ቦርዱ ለፓርቲው ነሀሴ 3 ቀን በቁጥር 1162/11/15180፣ ነሀሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥር አ1162/11/15209 እና ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር አ1162/11/15278 በፃፋቸው ደብዳቤዎች ላይ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማከናወን ጠቅላለ ጉባኤውን እንዲያደርግ አስታውቋል፡፡
ፓርቲው በልዩ ሁኔታ የተመዘገበው ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤውን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ ይጠበቃል። በሌላ በኩልም ለዚሁ የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅት የሚያስፈልገውን የቅድመ ጉባኤ ዝግጅት የተመለከቱ ስራዎችን ቦርዱመከታተል እንዲችል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን ከማድረጉ 21 ቀናት በፊት ጉባኤው የሚደረግበትን ቀን ለቦርድ እንዲያሳውቅ የሚጠበቅ ነው። ይሁንና ይህ ደብዳቤ አስከተፃፈበት ቀን ድረስ ፓርቲው ከተመዘገበ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤማድረግ የሚያስችለውን እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ቦርዱ አያውቅም።
በመሆኑም ፓርቲው በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበበት ከነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ የሚገባው ወቅት ሊገባደድ ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ የቀረው በመሆኑ ፓርቲው ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በልዩ ሁኔታ በተመዘገበበት አዋጅ፣ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣው መመሪያና ቦርዱ ከነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ጊዜ ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤዎች ላይ የተሰጡ ውሳኔዎች በማክበር በቀረው አጭር ጊዜ የጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያደርግ ቦርዱ በጥብቅ ያስታውቃል።
ይህ በሕግ ፓርቲው ላይ የተጣለ ግዴታ በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ቦርዱ ሕጉን መሠረት በማድረግ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ በአክብሮት ያስገነዝባል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በሲዳማ ክልል ሰርገኞች ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ50 በላይ የሚሆኑት ተጎጂዎች የአንድ ቤተሰብ አባላትእንደሆኑ ተነገረ 😭😭😭
በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ሰርገኞች ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ካለፈ 71 ሰዎች ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ዘመዳሞች መሆናቸው ተነግሯል።
አደጋው የደረሰው በዞኑ ቦና ዙሪያ ወረዳ ትናንት ዕሁድ ታኅሳስ 20 ሲሆን ሰርገኞቹ ወራንቻ ወደ ተባለ አካባቢ ሲጓዙ ጋለና ወንዝ ድልድይ ላይ ተሽከርካሪው መስመር በመሳት ወደ ወንዙ መግባቱን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በአደጋው ሙሽራውን ጨምሮ የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ኃላፊው፤ አስከሬን እስከ ሌሊቱ 9፡00 ድረስ እንደተነሳ ተናግረዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ ትብብር 73 የአደጋው ተጎጂዎች ወደ ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ለማ ለጊዴ ገልጸዋል።
በአስከሬን ምርመራ በአደጋው 66 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን እንዳረጋገጡ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ከሟቾቹ ውስጥ ሙሽራውን ጨምሮ 61 ወንዶች እና አራቱ ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሰባት ሰዎች ቆስለው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የተናገሩት ዶ/ር ለማ አምስቱ ተጊጂዎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ሁለቱ ተጎጂዎች ደግሞ የዳሌ፣ የእጅ እና እግር ስብራት እንዳጋጠማቸው ገልፀው፤ ወደ ሀዋሳ ለሪፈር ህክምና መወሰዳቸውንም አክለው ተናግረዋል።
ከ50 በላይ የሚሆኑት ሟቾች የሚሪዴ ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ዘመዳሞች መሆናቸውን ምክትል ኢንስፔክተር ሹመቴ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አንድ ቤተሰብ አባለትን ጨምሮ ሰርጉን ለማጀብ የወጡ ጎረቤቶችም የአደጋው ተጎጅዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።
"አብዛኞቹ ወጣቶች ናቸው" ሲሉ ስለ ተጎጂዎች ማንነት የተናገሩት የቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር፤ ተጎጂዎቹ ከ15 ዓመት እስከ 30 ዓመት የሚሆኑ ወጣቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጠናቀቀ!
ለ3 ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባዉን አጠናቋል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ከውይይቶቹ በመነሳት የተለያዩ ውሳኔዎች አስተላልፏል አቅጣጫዎችም ሰጥቷል።
#Prosperity
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የ‘ኒው አፍሪካን’ መጽሔት የ2024 ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውን ሴቶች
በመጽሔቱ የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብለው የተመረጡት ረድኤት አበበ (ዶ/ር)፣ አበባ ብርሃኔ (ዶ/ር) እና ናርዶስ በቀለ ናቸው።
ረድኤት አበበ (ዶ/ር) በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ፣ በርክሌይ የኮምፒዩተር ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰር ስትሆን፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የመረጃ አጠቃቀም እና አልጎሪዝም ምርምር ላይ የምትሠራ ሳይንቲስት ናት።
ረድኤት በኤሌክትሪካል ምህንድስና እና የኮምፒውተር ሳይንስ ክፍል የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ፕሮፌሰር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ምህንድስና ኮሌጅ ታሪክ ደግሞ ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ናት።
ሒሳብ እና አልጎሪዝምን ከኢ-ፍትሃዊነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ተግባራዊ ምርምሮችን ሠርታ ተሸልማባቸዋለች።
በኢትዮጵያ በነበረችበት ወቅት ያስተዋለችውን ዕድል ማጣትን መነሻ በማድረግም ብዙ ወጣቶች የተለያዩ ዕድሎችን እንዲያገኙ የኑሮ ልዩነት ጥናቶችን ከኮምፒዩተር ሳይንስ ጋር ለማጣመር ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ያለች ተመራማሪም ናት ረድኤት።
የትምህርት ዕድል አግኝታ ወደ አሜሪካ ከማቅናቷ በፊት በናዝሬት ስኩል ስትማር የነበረችው ረድኤት፤ እ.አ.አ በ2016 ኪራ ጎልድነር ከተባለች ሌላ ተመራማሪ ጋር በመተባበር የኮምፒውተር ሳይንስን ለበጎ ማኅበራዊ ዓላማ ለማዋል የሚያስችል ባለብዙ ዲሲፕሊን የምርምር ማኅበር መስርታለች።
በዚያው ዓመት ከትምኒት ገብሩ እና ከ1 ሺህ 500 ተመራማሪዎች ጋር በመተባበር በሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ የሚሠሩ ሰዎች ያሉበት እና በማኅበራዊ ኢ-ፍትሃዊነት ላይ የሚሠራ የጥቁሮች ማኅበር (Blacek AI) መስርታለች።
ረድኤት አበበ (ዶ/ር) በዚሁ በተሰማራችበት ዘርፍ እያደረገችው ባለው ጥረት እና እያመጣችው ባለው ለውጥ ምክንያት ከዚህ ዓመት መቶ ተፅዕኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን መካከል አንዷ ሆና ተመርጣለች።
ሌላዋ በዚህ መጽሔት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆና የተመረጠችው ኢትዮጵያዊት "አልጎሪዝም በኮድ ውስጥ የታቀፈ አመለካከት" እንደሆነ የምትናገረው አበባ ብርሃኔ (ዶ/ር) ናት።
ኮዱ የሚፈጠረው በነጭ ወንዶች እንደሆነ የምትገልፀው አበባ፣ ብዙውን ጊዜ ነጭ ላልሆኑ ሰዎችና ለሴቶች የማይታይ ጥላቻ እንዳለው አመላክታ፤ በቀሪው ዓለም ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት በጣም ሰፊ በመሆኑ ይህን ለማጋለጥ መወሰኗን ትናገራለች።
በባህርዳር ተወልዳ ያደገችው እና ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዎቿን ያገኘችው አበባ፤ ወደ አየርላንድ በማቅናት በሥነ-ልቦና እና ፍልስፍና ሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ከደብሊን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በኮግኒቲቭ ሳይንስ የዶክትሬት ዲግሪዋን አግኝታለች።
ትውልደ ህንዳዊ ከሆነው ፕሮፌሰር ቪኔ ፕራህቡ ጋር በመተባበርም ሰው ሠራሽ አስተውሎት ሲስተም ውስጥ ያሉ እና ዘረኝነትን የሚያንፀባርቁ መጠነ ሰፊ የምስል መረጃዎችን በምርምር ለይተዋል።
የሰው ሠራሽ አልጎሪስቶች ባላቸው የተዛባ አመለካከት ምክንያትም በዕድሜ የገፉ ሠራተኞችን፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆነ ማኅበረሰብን፣ ስደተኞችን እና ልጆችን በአሉታዊ መልኩ እንደሳሉአቸው በምርምሮቿ ለይታለች።
በተደራጁ አጀንዳዎች ምክንያት ተፈጥሯል ስለአለችው ‘Algorithmic Colonization’ በስፋት የጻፈች ሲሆን፣ የኮምፒውተር ሳይንስን ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ለማድረግ ያደረገችው ጥረት በሥርዓቱ በተጎዱት ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አስገኝቶላታል።
እ.አ.አ በ2019 ተዛማጅ ሥነ ምግባርን አስመልክቶ ያከናወነችው ውጤታማ ምርምር በBlack In AI የምርምር ማኅበር ሽልማትን አስገኝቶላታል።
እ.ኤ.አ በ2021 ደግሞ የምርጥ ሴቶች ስብስብ በሆነው AI Ethics Hall of Fame መቶ ምርጥ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካትታለች።
በታይም መጽሔት የ2023 መቶ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ የተካተተችው አበባ፣ እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆች ዓመት በደብሊን ትሪኒቲ ኮሌጅ የሰው ሠራሽ ሥነ-ምግባራዊ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የምርምር ቡድን አቋቁማለች። አበባ በሞዚላ ፋውንዴሽን ስር ሰውሰራሽ አስተውሎትን ለበጎ ዓላማ ለማዋል በተቋቋመው ክፍል ውስጥ ከፍተኛ ተመራማሪም ነች።
ናርዶስ በቀለ የአፍሪካ ሕብረት አዲስ ትብብር ለልማት (AUDA-NEPAD) ዋና ዳይሬክተር ናቸው። በዚህ ኃላፊነታቸውም ሕብረቱ እ.አ.አ በ1963 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ተብሎ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የያዛቸውን ታላላቅ ራዕዮች እውን እንዲያደርግ ብዙ ይጠበቅባቸዋል።
የሕብረቱ የቴክኒክ አካል የሆነው ኔፓድ ድርሻው የፕሮጀክችን እቅድ ማዘጋጀት፣ ቴክኒካዊ እርዳታ ማድረግ እና ለአባል ሀገራት የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረግ ሲሆን፤ ዋና ዳይሬክቷራ ናርዶስ ይህን ኃላፊነታቸውን በብቃት እየተወጡ እንደሆነ ከመጽሔቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
እ.አ.አ በ2022 የኔፓድ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በደቡብ አፍሪካ የተመድ ማስተባበሪያ ቢሮን ጨምሮ በዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች ውስጥ ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ በኃላፊነት ሠርተዋል። በኬንያ እና በቤኒን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ተወካይ እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ቢሮ ከፍተኛ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል።
ኔፓድን ለመምራት የመጀመሪያዋ ሴት እንደመሆናችም፤ በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ የሴቶች እና የወጣቶች ተሳትፎ እንዲያድግ እና ፍትሃዊነት እንዲሰፍን እየሠሩ እንደሆነ ተጠቅሷል።
በአፍሪካ ሀገራት መካከል ቀጣናዊ ግንኙነት እንዲጠናከር፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን እንዲስፋፋ እና የወጣቶች ሥራ አጥነት እንዲቀንስ የክህሎት ሥልጠናዎች ላይ ትኩረት አድርገው መሥራታቸው ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸውን እንደሚያጎላው በመጽሔቱ ላይ የወጣው መረጃ ያመላክታል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#የተሰበረው_ገጻችሁ
መጽሐፍ አንባቢ ከሆናችሁ ምናልባት ይህንን ቀላል እውነታ አስተውላችሁት ይሆናል ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ አንድ ገጽ ላይ የተሰበረ መጽሐፍ ሁል ጊዜ ስትከፍቱት የሚከፈተው እዚያ የተሰበረው ገጽ ላይ ነው፡፡ ምናልባት አባባሉ ካልገባች አንድን መጽሐፍ አንሱና አንድ ገጽ ላይ ከፍታችሁ ግራና ቀኙን ይዛችሁ ወደ ኋላ በመለመጥ እዚያ የተከፈተው ገጽ ጋር እስኪላቀቅ ግፊት በማድረግ ስበሩት፡፡ ከዚያም እንደገና አንሱትና እዚያው ጋር ደጋግማችሁ ስበሩት፡፡ አለቀ!!! በሌላ ጊዜ መጽሐፉን ስታነሱት መጀመሪያ ራሱን ከፍቶ የሚቆያችሁ ይህ የተሰበረ ገጽ ነው፡፡
ቀላል የሆነ የሕይወትን እውነታ አስታዋሽ ምሳሌ!!! በሕይወታችሁ አንድ ደጋግሞ የተሰበረ ክፍል ካላችሁ ምንም ነገር ሲከናወን የሚከፈትባችሁ ይህ የተሰበረ ገጽ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የመገፋትና ያለመፈለግ (Rejection) ስብራት ካለባችሁ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ሁሉና በሕይወታችሁ የሚከናወነው ደስ የማይል ልምምድ ሁሉ የሚከፍትባችሁ ያንን የስሜት ገጽ ነው፡፡ ተሰብሮና በመከፈት ዝንባሌ ተዘጋጅቶ የተቀመጠው የሕይወታችሁ ክፍል እሱ ስለሆነ ማለት ነው፡፡
በሌላ አገላለጽ፣ አንድ ገጽ ላይ የተሰበረ መጽሐፍ ሌላ ገጽ ላይ ተከፍቶ እንዲቀመጥ ቢሞከር እንኳን ማንም ሳይጠይቀው ወደዚያ ገጽ የመከፈት ዝንባሌ አለው፡፡ ሕይወትም እንዲሁ ነች፡፡ ደጋግመን የተሰበርንባቸው የሕይወታችን “ገጾች” በሆነ ባልሆነ የመከፈት ባህሪይ አላቸው፡፡
ደጋግማችሁ የተሰበራችሁበትን የሕይወት “ገጽ” ለይታችሁ በማወቅ ይህ ስብራት በሚገባ የሚጠገንበትን መንገድ በቶሎ ካልፈለጋችሁለት በሁሉም የሕይወት ዘርፍ ውስጥ እየተከፈተ ያስቸግራችኋል፡፡ ከላይ ወደጠቀስነውን የመገፋትና ተቀባይነት የማጣት ስብራት ብንመለስ፣ ያንን ስብራት ይዛችሁ ወደ ጓደኝነት፣ ወደ ፍቅር ሕይወት ወይም ወደ ትዳር፣ ወደ ስራ አለም፣ ወደ ንግዱ መስክና ወደ መሳሰሉት ማሕበራዊ ስምሪቶቻችሁ ስትገቡ ገጹ እየተከፈተ ያስቸግራችኋል፡፡ ማለትም በሆነ ባልሆነው የመገፋት ስሜት ያጠቃችኋል ማለት ነው፡፡
ምናልባት በአካባቢያችሁ በአንድ ባህሪይ ዙሪያ እጅግ ስስ የሆነና ምንም ብታደርጉ መፍትሄ ልትሰጡት ያልቻላችሁት ሰበብ ያለበት ሰው ካጋጠማች የዚህ “የተሰበረ ገጽ” ችግር ሰለባ የመሆኑ እድ ሰፊ ነው፡፡
ምንም ነገር ውስጥ ከመግባታችሁ በፊት በመጀመሪያ የተሰበረውን “ገጻችሁን” ጠግኑ!!!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ማቴ 11:29
የድል ታሪክ መዘከሪያ
እንደ ሀገር ዜጋ መኩሪያ
በፒያሳ አፋፍ፣ በአዲስባ እምብርት
ድሉን የመጠነ፣ ነግሶበታል ውበት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አሳዛኝ ዜና‼️ 😭😭😭
ዛሬ 20/04/2017 ዓ.ም በሲዳማ ክልል በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው አደጋ ከ60+ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ‼️
አደጋ የተከሰተው አንድ አይሱዙ መኪና ከ60+ የሠርግ አጃቢዎች አሳፍሮ ወደ ዳዬ በንሳ መሥመር እየተጓዘ እያለ በጋላና ድልድይ ተምዘግዝጎ ወደ ወንዙ በመግባቱ እንደሆነ የዓይን እማኞች ገልፀዋል።
በጋላና ድልድይ ተመሳሳይ የትራፊክ አደጋ ሲደርስ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህ እጅግ የከፋ አደጋ ነው ብለዋል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እንደሚችል ምንጮች ገልፀዋል።
ነፍስ ይማር፣ መፅናናትን ይስጥልን።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
"በተሳሳተ መንገድ ወደ ትጥቅ ትግል ገብተን ባደረስነው በደል ህዝባችን ለመካስ ዝግጁ ነን።"- የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂ ሃይሎች
በምስራቅ አማራ ቀጠና አካባቢ የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ የታጣቂ ቡድኑ አባላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል ገብተዋል።
በአማራ ክልል የሰላም መደፍረስ ከተከሰተ ከአንድ ዓመት በላይ ዘልቋል። ይህንን ግጭት ለማስቆምም መንግስት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን በመቀበል እጃቸውን ለመንግስት እየሰጡ ይገኛሉ።
በዛሬው እለትም በምስራቅ አማራ ቀጠና ማለትም በዋግኽምራ ብሔረሰብ፣ በሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ወሎ፣ በደሴ ከተማ፣ በኮምቦልቻ ከተማ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ የታጣቂ ቡድኑ አባላት መንግስት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ተሀድሶ ማሰልጠኛው ማዕከል ገብተዋል።
ምንም እንኳ መመለስ የሚገባቸው የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ቢኖሩም ለማስመለስ የሄድንበት መንገድ የተሳሳተ ነው ያሉት ተመላሽ የታጣቂ ቡድኑ አባላት፤ የሕዝብ ጥያቄ እናስመልሳለን ብለን ጫካ ከገባን በኋላ የፈጸምነውን ድርጊት ስናስበው የተሳሳተ መንገድ እንደተከተልንና ሕዝቡ ላይ የከፋ በደል እንዳደረስን ተፀፅተናል ብለዋል።
በመሆኑም የበደልነውን ህዝብ ለመካስ መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለን መጥተናል ሲሉ አመልክተዋል።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለአመታዊው የቅዱስ ገብርኤል ንግሰ በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን።
#ሰበታ_ገብርኤል
⛪️ 💒 ⛪️
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አራቱ የግል ሕይወትን የማደራጀት ልምምዶች
1. መነሳሳት
ሕይወታችሁን ለማደራጀት ከፈለጋችሁ ከሁሉ በፊት የተደራጀ ሕይወትን አስፈላጊነትና ጥቅም፣ በተጨማሪም ያልተደራጀ ሕይወትን ጉዳት በማሰብ መነሳሳትን ይጠይቃል፡፡
2. ውሳኔ
ሕይወታችሁን ለማደራጀት በቀጣይነት የሚያስፈልጋችሁ ከምቹ ስፍራችሁ የመውጣት ውሳኔ ነው፡፡ ምቹ ስፍራ ልክ እንደ ስያሜው ይመቻል፡፡ ስለሆነም ከዚያ ስፍራ ለመውጣትና ወደ አዲስ የሕይወት ዘይቤ ለመግባት ውሳኔ ይጠይቃል፡፡
3. ክህሎት
ምንም ያህል ብንነሳሳ እና ብንወስንም፣ የአደረጃጀት ሂደት እንዴት እንደሆነ ካላወቅን ግራ ከመጋባት አናልፍም፡፡ ብዙ ሰዎች ያላቸው ችግር ይህ ነው፡፡ ሕይወታቸውን እንዴት ማደራጀት እንዳለባቸው አያውቁትም፡፡
4. ዲሲፕሊን
ሕይወትን የማደራጃው ወሳኙና የመጨረሻው ነገር ዲሲፕሊንን የማዳበር ጉዳይ ነው፡፡ መነሳሳቱ፣ ውሳኔውና ክህሎቱ ኖሮን ሳለ፣ የመጀመር፣ የመቀጠልና እስከጥጉ የመውሰድ ዲሲፕሊን ከሌለን የተደራጀ ሕይወት ለመኖር ያስቸግረናል፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የሶማሊያ ኘሬዝደንት ወደ አስመራ አመሩ
ኘሬዝደንት ሃሰን ሼህ መሃሙድ ከደቂቃዎች በፊት ወደ አስመራ ማቅናታቸው ታውቋል።
የዛሬው ጉዞ በሶስት አመት ውስጥ ለስምንተኛ ጊዜ የተደረገ ነው።
ኘሬዝደንቱ በአስመራ ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት ያደረረጋሉ ።
ዋንኛው የውይይታቸው ትኩረትም በአንካራ የተፈረመው ስምምነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ይሆናሉ የተባለ ሲሆን ከፊርማው በኋላ በኘሬዝደንቱ የተደረገ የመጀመሪያው ጉዞ ነው።
በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የተደረሰው ስምምነት የአስመራ እና ካይሮ መንግስታት ያላስደሰተ መሆኑ ይታወቃል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ይካሄዳል!! - ክቡር አቶ አደም ፋራህ
2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።
በአንደኛው ታሪካዊ የብልጽግና ፓርቲ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎችን በመፈጸም በኩል አበረታች ሥራዎች መፈጸማቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል።
ባለፈው የፓርቲው ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ፣ በአሰባሳቢ ትርክት ማዳበር፣ በሰላም እና ደህንነት እና በመሰል ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመፈጸም ፓርቲው ለሕዝብ የገባቸውን ቃሎች በማክበር እና በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።
በኢኮኖሚው የሃገር በቅል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በተመተግበር ተጨባጭ ለውጥ የታየባቸው ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን ጠቅሰዋል።
የአቅም መገንባት ስራዎች መሰራታቸውን አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የማበረታቻ እና የእርምት እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።
ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ጠንካራ የፌደራል ስርዓት እንዲፈጠር መሰራቱን ጠቅሰዋል።
የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት አንጻርም አበረታች ሥራዎች መሰራታቸውን እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀርበው የሚነጋገሩበት ምህዳር መፈጠሩን አንስተዋል።
በሂደቱ ያጋጠሙ ከሰላም ከጽንፈኝነት ጋር የተያያዙ እና መሰል ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን በመቋቋም ሥኬቶች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል።
ለ2ኛው ጉባኤ ዝግጅትም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
#aa_prosperity
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ከጠቅላይ ሚንስተር ቢሮ!
የኮዲንግ ሥልጠና ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች!
በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ ይመዝገቡ፡፡
የኦንላይን ስልጠናውን በተሰጡት 8 ሳምንታት ለሚያጠናቅቁ ብቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትላቸዋል፡፡
ተሰጥዎን በማውጣት፤ ነገን እንለውጥ!!!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹