prosperityfirst | Unsorted

Telegram-канал prosperityfirst - የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

1397

Subscribe to a channel

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በባሌ ሮቤ ያስገነባውን የዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናልን እያስመረቀ ነው።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ዋቆ ጉቱ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሃደ ሲንቄዎችና የአካባቢው መስተዳድር አካላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የቮልካኖ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደረስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በተቀናጀ ሁኔታ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የሟጓጓዝ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም በተደጋጋሚ መቀጠሉን ጠቅሰው÷ የቮልካኖ ፍንዳታ ዛሬ ተከስቷል፤ ንዝረቱም ከሰሞኑ ከፍያለ እና ጠንካራ ነበር ብለዋል፡፡

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሰዎች የነዱት ሰው ጸጸት

“ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!”

ብሮኒ በመጀመሪያ የምትተርከው ግሬስ ስለምትባል በታላቅ ጸጸት ውስጥ ስላለች ሴት ነው፡፡ ግሬስ ከሃምሳ አመታት በላይ በጋብቻ ሕይወት አሳልፋለች፡፡ ግሬስ ከልቧ ከምትወዳቸው ልጆቿ ከምታገኘው ደስታ ባሻገር “የአስራዎቹ” አመታት ወጣት የልጅ ልጆች ማግኘቷ የማይጠገብ የደስታ ምንጭ ሆኖላታል፡፡ ሆኖም፣ ይህ ደስታዋ ሙሉ እንዳይሆን ያደረገባት አንድ ጥቁር ነጥብ ግን በሕይወቷ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ የባለቤቷ ጉዳይ ነበር፡፡

አምባ ገነንና ጨካኝ የሆነው ባለቤቷ ባሳለፉት አመታት ውስጥ ጋብቻን አስቸጋሪ ያደረገባት ሰው ነበር፡፡ ወደጋብቻ ከመጡበት እለት ጀምሮ የቅስም ሰባሪ ቃላትና የተለያዩ የክፉ ተግባሮች ሰለባ አድርጓታል፡፡ ይህንንም ሁኔታውን ለማስተካከል መውሰድ የነበረባት እርምጃዎች እንዳሉ ብታውቅም፣ አንዱንም ምርጫ ለመውሰድ ድፍረቱ ሳይኖራት ለአመታት ተቀጥቅጣ ኖራለች፡፡ የባለቤቷ አስቸጋሪነት እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ ከጥቂት አመታት በፊት ከእርጅና የተነሳ በአረጋውያን መጦሪያ ማእከል በመግባቱ እርሷ ብቻ ሳትሆን ሁኔታውን የሚያወቁ ሰዎች ሁሉ ደስተኛ ነበሩ፡፡

ግሬስ በትዳር አመታቶቿ በሙሉ አንድ ቀን ከባሏ ክፉ ተጽእኖና ጨካኝ ሁኔታ ውጪ ሆና ደስተኛ ሕይወትን ለብቻዋ የምታጣጥምበትን ቀን እንደናፈቀች ኖራለች፡፡ አሁን በሰማኒያዎች አመታት ውስጥ ብትሆንም፣ ለእድሜዋ የሚመጥን መጠነኛ ጤንነትና የአካል ብቃት ነበራት፡፡ ወደማእከሉ ስትመጣ ወዲህ ወዲያ ለማለት የሚያበቃት አቅም ነበራት፡፡  

እድሜዋን በሙሉ “በድብደባ” ያሳለፈው አእምሮዋ አሁን ለዚህ ሁኔታ ከዳረጋት ባለቤቷ በመለየቷ ምክንያት የእረፍትን ጭላንጭል ያየ ይመስላል፡፡ ለብዙ ዘመናት የጠበቀችውን ይህንን ለብቻ የመሆንና ካለምንም የውጪ ሰው ተጽእኖ የማሰብ “ነጻነት” ባገኘች በአጭር ጊዜ ውስጥ በድንገት በጽኑ መታመም ጀመረች፡፡ ሕመሙ ከተሰማት ከጥቂት ቀናት በኋላ ብዙም እድሜ እንደማይኖራት የሚጠቁም ምልክት ተገኘባት፡፡ ሁኔታውን እጅግ ልብን የሚሰብር ያደረገባት፣ የህመሙ መንስኤ ለብዙ አመታት ባለቤቷ በቤት ውስጥ ሲያጨስ ከነበረው የሲጃራ ጭስ እንደሆነም ማወቋ ነው፡፡ የበሽታው ደረጃ እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ በአንድ ወር ውስጥ አቅሟን ሁሉ አጥታ የአልጋ ቁራኛ ሆነች፡፡

“ለምን ያንን ዘመን ሁሉ እኔ ያመንኩበትንና የፈለግሁትን ነገር አላደረኩም? ለምን እንደፈለገ እንዲገዛኝና እንዲያንገላታኝ ፈቀድኩለት?” የሚሉት ጥያቄዎች ካለማቋረጥ ከግሬስ አንደበት ሲወጣ ይደመጥ ነበር፡፡ ያመነችበትን ትክክለኛ ሕይወት ለመኖር ድፍረት ሳይኖራት ዘመኗ በማለፉ ምክንያት በራሷ ላይ እጅግ በጣም ትበሳጭ ነበር፡፡ ልጆቿም ቢሆኑ እንደፈለገ ባደረጋትና ባደረገባት ባሏ ምክንያት ስላሳለፈችው ከባድ ሕይወት በግልጽ ይመሰክሩ ነበር፡፡

“አንቺ ማድረግ የምትፈልጊውን ትክክለኛ ነገር ከማድረግ ማንም ሰው እንዲከለክልሽ አትፍቀጂለት” በማለት ለተንከባካቢዋ ለብሮኒ ደጋግማ ትነግራት ነበር፡፡ “እባክሽን ይህንን እኔ የሰራሁትን ስህተት እንዳትሰሪ ቃል ግቢልኝ” በማለት ታሳስባት ነበር፡፡ አንድ ቀን ግሬስ ይህንኑ ምክር ደግማ ከነገረቻት በኋላ፣ ብሮኒ በእሺታ ምክሯን ተቀብላ እንደምትተገብረው ቃል በመግባት፣ “ራስን የመቻልና ያመኑበትን ትክክለኛ ነገር የማድረግን ትምህርት ያስተማረችኝ እናት ስለነበረችኝ እድለኛ ነኝ” በማለት ለግሬስ ነገረቻት፡፡

“አሁን ያለሁበትን ሁኔታ ተመልከችው” አለች፣ ግሬስ በመቀጠል፡፡ “በመሞት ላይ ነኝ፡፡ በሞት አፋፍ! እንዴት ቢሆን ነው እነዚያን አመታት ሁሉ ነጻና ራሴን የቻልኩ ሆኜ ለመሆን ስጠብቅ ኖሬ፣ አሁን እዚያ የተመኘሁበት የሕይወት ምእራፍ ላይ የደረስኩ ሲመስለኝ ጊዜው ያለፈብኝ?” እነዚህን መራራ ቃላት የሰማችው ብሮኒ የግሬስ ሁኔታና ጸጸት እንድታስብ ያነሳሳትን እውነታ ማሰላሰል ጀመረች፡፡

የደረሰችበትም ድምዳሜ፣ “ማንኛውም ሰው የራሱን አመለካከት ማወቅ፣ ትክክለኛውን መንገድ መለየትና ያንንም ያመነበትን ትክክለኛ ጎዳና መከተል አለበት” የሚል ነበር፡፡ 

ግሬስ በውስጧ የምታምንበትንና የሚሰማትን ስሜት ሳይሆን የዚያን ተቃራኒ ገጽታን በውጪ እያንጸባረቀች ዘመኗን አባከነች፡፡ እድሜዋን በሙሉ እርሷ ያመነችበትንና ከነበረባት የጭካኔ ሰለባ የሚያወጣትን ሕይወት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ከእርሷ የሚጠብቁባትን አይነት ሕይወት ስትኖር ካሳለፈች በኋላ፣ አሁን በመጨረሻዎቹ አመቶቿ ምርጫው የእርሷ እንደነበርና፣ ፍርሃት ከትክክለኛው ምርጫ እንደገታት ተገነዘበች፡፡ ራሷን ይቅር የማለት አስፈላጊነት ቢነገራትም እንኳን አሁን ሌላ ምርጫ ያለውን ሕይወት ለመኖር ጊዜው ያለፈባት መሆኑን ስታስብ ከአቅሟ በላይ የሆነ ስሜት ይወርሳታል፡፡

ብሮኒ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች በሚኖሩበት ማእከል ውስጥ ስትሰራ ካጠናቻቸው የሰዎች ጸጸቶች ይህኛው፣ “ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!” የሚለው ጸጸት አብዛኛዎቹን ሰዎች የሚያጠቃውና ቀንደኛው ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የሕልማቸውን ግማሽ እንኳን ሳያጣጥሙ ዘመናቸው የሚያልፈው ያመኑበትን ትክክለኛ የሕይወት አቅጣጫ ለመከተል ምርጫ እንዳላቸው ካለማወቅና ወይም ትክክለኛውን ምርጫ እያወቁ ያንን ምርጫ ለመከተል ጉልበት ከማጣት የተነሳ ነው፡፡

ጊዜው ካለፈብህ በኋላ እዳትጸጸት ሰዎች ከአንተ የሚጠብቁትን ሳይሆን አንተ ራስህው ያመንክበትን ትክክለኛ ሕይወት የመኖርን ጉዳይ ዛሬውኑ አስብበት!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 63 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ ከተሞች ላይ ተሰምቷል።

የግድግዳ ላይ የተሰቀሉ ቁሶች የወደቁባቸው ቦታዎችም አሉ።

በአፋር አዋሽና አካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንብረት የወደመ ሲሆን ወገኖቻችንም መንቀጥቀጡ ካየለበት ስፍራ ሸሽተው ለመውጣት ተገደዋል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተትና ተከትሎ የሚመጣው ንዝረት ድግግሞሹ የቀጠለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ " ምንም ነገር አይፈጠርም ፤ ለምደነዋል " ብላችሁ እንዳትዘናጉ አደራ እንላለን።

አያድርገውና እጅግ የከፋ ነገር በሚመጣበት ጊዜ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ዘወትር አስታውሱ።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ብሪክስ 9 ሀገራትን በአጋርነት ተቀበለ!

ጥምረቱ በአጋርነት የተቀበላቸው ሀገራትም ቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ኩባ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ካዛኪስታን፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤኪስታን ናቸው፡፡

እ.አ.አ በጥቅምት ወር 2024 በሩሲያ ካዛን በተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ላይ 13 ሀገራት ጥምረቱን በአጋርነት እንዲቀላቀሉ ግብዣ ቀርቦላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ 

በሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ እና ብራዚል የተመሰረተው ብሪክስ፤ ደቡብ አፍሪካን እ.አ.አ በ2010፤ ኢትዮጵያን፣ ኢራንን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን እና ግብጽን ደግሞ እ.አ.አ በ2024 በአባልነት መቀበሉ ይታወቃል፡፡ እንደ ቻይና እና ሩሲያ ያሉ የዓለም ኃያላን ሀገራትን ያቀፈው ብሪክስ ከ3.5 ቢሊዮን የሚበልጥ ሕዝብን እንደሚወክል ዘ ሳውዝ አፍሪካን ዶት ኮም ዘግቧል

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ስሜታዊ ሆነው ለፍቅር አጋራቸው የላኩትን የእራቁት ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ  እንለቅባቸዋለን የሚል ዛቻ ወይም የሚለቀቅባቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው  እየጨመረ  ነው ተባለ 😭

በኢትዮጵያ የፍቅርም ሆነ የትዳር ግንኙነት ችግር በገጠመው ጊዜ በሰላሙ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ የተላላኩትን የራቁት ፎቶ በፌስ ቡክ እና በቴሌግራም  እለቅብሻለው የሚል ማስፈራሪያ ሴቶች እየደረሳቸው ነው። የተለቀቀባቸውም አሉ። እንዳይለቀቅባቸው ያለ ፍቃድ ወሲብ እና ገንዘብም የሚጠየቁ አሉ ሲል ሸጋ ሚዲያ ከቅርብ ሳምንት በፊት የሰራው የምርመራ ሪፖርት ያሳያል።


🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የፊዚክስ ሊቁ የ2025 ትንበያዎች - ከ30 ዓመታት በፊት 👇

ስመ ጥሩ እንግሊዛዊ ሳይንቲስት ስቴቨን ሃውኪንግ እ.አ.አ በ1995 ዓለም ከ30 ዓመታት በኋላ ምን ልትመስል ትችላለች የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፡፡

የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 2025 ዛሬ መግባቱን አስመልክቶ የፊዚክስ ሊቁን ትንበያዎች ከ30 ዓመት በኃላ በምልሰት እንቃኛቸዋለን፡፡

የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ሊቁ በ30 ዓመታት ውስጥ የሚጠበቁ ግዙፍ ለውጦች ብሎ ካነሳቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በየዘርፉ የቴክኖሎጂው መፍላት ነው፡፡ ሃውኪንግ የበይነ መረብ ጥቃት፣ የኮምፒዩተር ቫይረስ እና የመረጃ ምንተፋዎች እንደሚስፋፉ የተናገራቸው ትንበያዎች ባለ ጥቁር ምላስ ሊያስብሉት ይችላሉ፡፡

ሌላኛው ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የርቀት ህክምና አገልግሎት ትንበያው ሲሆን ሊቁ ስልጡን ሮቦት ሀኪሞችን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ብሎ ነበር፡፡ ይህ የሃውኪንግ ትንበያ ሙሉ በሙሉ ባይሳካም በተለያዩ የዓለም ሀገራት ጅማሮዎች ግን ተስተውለዋል፡፡

የሰው ልጅ ከህዋ ላይ ውድ ማዕድናትን ወደ ምድር ማጋዝ እንደሚጀምር በፊዚክስ ሊቁ የተሰጠው ትንበያ፤ ናሳን ጨምሮ የተለያዩ የጠፈር ምርምር ማዕከላት ከጨረቃ መጡ የተባሉ ድንጋዮችን በሙዚየም እስከማሳየት ቢደርሱም እስከ ማዕድን ቁፋሮ ስለመድረሳቸው ግን መረጃ ማግኘት አይቻልም፡፡

በህዋ ላይ ማዕድናት ያማውጣት ስራ ባይጀመርም፤ እድሉ ግን አሁንም እንዳለና በህዋ ላይ ያሉ ሰው ሰራሽ ቁሳቁሶች ለጠፈርተኞች እንቅስቃሴ እክል መሆናቸው ይገለጻል፡፡

ሳይንቲስቱ በትንበያው ከ30 ዓመታት በፊት ሊከሰት ይችላል በሚል ያቀረበው ሌላኛው ጉዳይ በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ገንዘብ ከባንክ መክፈያ ማሽን ማውጣት የሚቻልበት ቴክኖሎጂ በወደፊቱ የባንክ ዘርፍ ተግባራዊ ይሆናል የሚል ነበር፡፡

የሳይንቲስቱ ግምቶች እውን ሆነው ዲጂታል የባንክ አገልግሎት መስጠት፤ በጣት አሻራ እንዲሁም ስካን በማድረግ ደንበኞች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉበት ዘመን እውን ሆኗል፡፡

ቢቢሲ በዓለም አቀፍ ፕሮግራሙ ሳይንቲስቱ ስቴቨን ሃውኪንግ ያስቀመጣቸው ትንበያዎች በርካቶቹ እውን መሆናቸውን ቢገልጽም፤ የትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋትን መዘንጋቱን አስታውሷል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመከላከያ ተቋማት የኮሪደር ልማት አካል የሆኑ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ 

በጉብኝታቸውም በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ግቢ እና በሎጀስቲክስ ማእከሎች እየተሰሩ ያሉ የግንባታ ስራዎች እና ማዕከሎችን አረንጓዴ፣ ወብና ፅዱ የስራ አካባቢ ለማድረግ እተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡ 

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መከላከያ የሀገርን ሉአላዊነት ማስከበር ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ደህንነታቸው የተረጋገጠና ሰላማቸው የተጠበቀ እንዲሆን የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ እየፈፀመ መሆኑን መናገራችውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መረጃ ያመለክታል፡፡ 

ከዚሁ ጎን ለጎን በልማቱም ረገድ እንደ ሀገር የተቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ ዘርፈ ብዙ እና ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እና የልማት ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል። 

ይህ ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ርብርብ እየተተገበሩ ካሉት የኮሪደር ልማት ስራዎች አካል ሆኖ በተቀመጠው ዕቅድ መሰረት በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ እንደሆነ አረጋግጠው፤ ቀሪው ስራ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለተገነባበት አላማ እንዲውልም አሳስበዋል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኤርፖርቱ ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተመላከተ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመላክቷል።

ቋሚ ኮሚቴው በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አለምዓቀፍ አየር ማረፊያ ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎትና የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ኤርፖርቱ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በቀጥታ ወደ ሥራ በመግባት የክልሉን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ያደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል።

በአየር መንግዱ በመገንባት ላይ የነበሩ የአብራሪዎች ትምህርት ቤት እና የደኅንነት መሠረተ ልማት ግንባታዎች በመቋረጣቸው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል።

የበጀት ዕጥረትና የግብዓቶች አለመሟላት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና ማሳደሩን የአየር መንገዱ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

በክልሉ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በጋራ መሥራትና የበጎ ፈቃድና  ማህበራዊ አገልግሎቶችን በመሥጠት ማህበረሰቡን ማገዝ እንደሚገባው ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አቶ ገዱ በጠና ታመዋል 😭😭😭

ፈጣሪ ምህረትና ቸርነቱን ይላክልዎት

ለእኛ በመፀለያ ሰአትዎ እኛ ለእርስዎ እንፀልይ? 🤔🤔🤔 ጉድ እኮ ነው 🤔🤔🤔

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

"ሽኩቻው ስጋት ውስጥ ከቶናል" - ነዋሪዎች

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

#ኢዮሪካ_ጋርመንት

5 ቲሸርት በ1,500 ብር ብቻ 👌 ከኢዮሪካ ጋርመንት

- ቲሸርቶቹ ህትመት የሚቀበሉ ናቸው
- የገዙ ጥራቱን መስክረዋል።
- በፈለጉት ሳይዝ ሁሉም አለ።
- በብዛት ለሚገዛ ቅናሽ አለው ዴሊቨር እናደርጋለን።

ይደውሉ 👇👇👇
☎ +251984337091

አድራሻ 👇👇👇
መሪ 40/60 ኮንዶሚኒየም

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በህንድ የኮምፒውተር ባለሙያው ለአለቃው ስራ ማቆም እንደሚፈልግ ከመናገር ይልቅ አራት ጣቶቹን ቆረጠ

የ32 ዓመቱ ህንዳዊው ሰው በዘመድ ኩባንያ ውስጥ የኮምፒተር ኦፕሬተር ሆኖ ሲሰራ የነበረ ሲሆን የግራ እጁን አራት ጣቶችን እንደቆረጠ አምኗል።

አይሆንም ማለትን መማር ቀላል ይመስላል፣ ነገር ግን ለአንዳንድ ሰዎች፣ አይሆንም ወይም እምቢ ከማለት ይልቅ የገዛ ህይወታቸውን የበለጠ ከባድ አደጋ ላይ እስከ መጣል ሊሄዱ ይችላል። ለአለቃው ስራውን መልቀቅ እንደሚፈልግ ላለመናገር በግራ እጁ ላይ አራት ጣቶቸን እንዲቆረጥ ያደረገው የጉጃራቱ ሰው አደጋ እንደደረሰበት ሲያስመስል ቆይቷል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ማዩር ታራፓራ የግራ እጁ አራት ጣቶች መቆረጣቸውን ለማሳወቅ በትውልድ ከተማው ሱራት ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ አምርቷል። ሞተር ብስክሌቱን እየጋለበ ወደ ጓደኛው ቤት እየሄደ እንደነበር ተናግሯል።

ታዲያ በድንገት ራስን የማዞር ስሜት ተሰማው እና በመንገዱ ዳር ላይ መውደቁን ገልጿል። ከ10 ደቂቃ በኋላ ከእንቅልፉ ሲነቃ የግራ እጁ አራት ጣቶች ተቆርጠዋል። ፖሊሶች መጀመሪያ ላይ የሰውዬው ጣቶች ለጥቁር የአስማት የአምልኮ ሥርዓቶች እንደተቆረጠ በማመን እርሱ ከተናገረው ውጪ ተጠራጥረው ነበር። ነገር ግን ምርመራቸው ማዩር ላይ ጫን አድርገው ሲቀጥሉ ያልጠበቁት ሆኖ ተገኝቷል።አስገራሚው ጉዳይ ወደ ከተማው የወንጀል ቅርንጫፍ ከመዛወሩ በፊት በሱራት ፖሊስ ጣቢያ ተመዝግቧል። መርማሪዎች ተጎጂው እንደወደቀ በተናገረበት አካባቢ የክትትል ካሜራ ቀረጻ እና የዓይን እማኞችን ማጣራት ሲጀመር ግን እርሱ የተናገረውን መረጃ ማግኘት አልቻሉም።

ማዩር በዘፈቀደ የግራ እጁን ጣቶች ቆርጦ ከመመለሱ በፊት ብስክሌቱን ቀለበት መንገድ አጠገብ አቁሞ ይታያል። በተጨማሪም ማንም ሰው በመንገድ ዳር ሲያልፍ አይቶት አያውቅም። በፖሊስ ምርመራው ሲጠነክርበት ጣቶቹን እራሱን እንደቆረጠ አምኗል። ታራፓራ ስለታም ቢላዋ ከሱቅ እንደገዛ አምኗል ሲሉ የፖሊስ ባለስልጣን ለሂንዱ ጋዜጣ ተናግረዋል። ቢላዋን ከገዛ ከአራት ቀናት በኋላ፣ እሁድ ምሽት፣ ወደ አምሮሊ ሪንግ መንገድ በማቅናት ሞተር ብስክሌቱን ያቆማል። ምሽቱ 10 ሰአት ላይ አራት ጣቶቹን በቢላ ቆርጦ ከክርኑ አጠገብ ገመድ አስሮ ደም እንዳይፈስ አድርጓል። ከዚያም ቢላዋውን እና ጣቶቹን በከረጢት ውስጥ ካስገባ በኋላ ይወረውረዋል።

ማዩር ታራፓራ በዘመዱ የአልማዝ ኩባንያ ውስጥ መሥራት ስላልፈለገ የራሱን አካል ማጉደል እንደጀመረ ለመርማሪዎች ተናግሯል። ስራ መልቀቅን ሊነግራቸው እንዳልፈለገና ነገር ግን አራት ጣቶች ካጣ ሥራውን ለማቆም በቂ ምክንያት እንደሚሆንለትም ለፖሊስ ገልጿል።ፖሊስ የተቆረጡ ጣቶችን የያዘ ቦርሳ ለማግኘት ችሏል፣ነገር ግን አሁንም ይህን አስገራሚ ታሪክ በተመለከተ አንዳች የተለየ ጉዳይ ሊኖር ይችላል በማለት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ምርመራ ማድረግ መቀጠሉን አስታውቋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሃላፊነታችሁን ለዩ!

1.  ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እናንተ በፍጹም ሃላፈነትን መውሰድ የለባችሁም


እናንተ ከሰዎቹ ጋር ያላችሁን ግንኙነት በተቻላችሁ መጠን ጤናማ የማድረግ ሃላፊነታችሁነ ተወጡ እንጂ እነሱ ለሚሰማቸው ስሜት ተጠያቂው እናንተ እንደሆናችሁ በማሰብ በፍጹም እናንተ መሸከም የለባችሁም፡፡ እናንተም ብትሆኑ ለሚሰማችሁ ስሜት ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ የለባችሁም፡፡

2.  ሰዎችን ላላጠፋችኋቸው ነገር በፍጹም ይቅርታ መጠየቅ የለባችሁም፡፡

ሰዎችን አንድ ጥፋት ካጠፋችኋቸው፣ ይቅርታ የመጠየቅና ተግባራችሁን የማረም ሃላፊነት አለባችሁ እንጂ እናንተ ምንም ባላጠፋችሁት ጥፋት ገና ለገና እነሱ ስለከፋቸው ይቅርታ መጠየቅ የለባችሁም፡፡ እናንተም ብትሆኑ ሰዎችን በሆነ ባልሆነ በመኮነን ይቅርታ እንዲጠይቋችሁ መጫን የለባችሁም፡፡

3.  ደጋግመው ከሚጎዷችሁ ሰዎች ጋር አብሮነታችሁን እንደ ቀድሞው የማድረግ ግዴታ የለባችሁም፡፡

ሰዎች ከጎዷችሁ በኋላ ይቅርታን ቢጠይቋችሁ ይቅር ማለታችሁ በጣም ጤናማ አካሄድ ሆኖ ሳለ፣ ግንኙነታችሁን ግን እንደቀድሞው የማድረግ ግዴታ የለባችሁም፡፡ ይቅርታ የግንኙነት ጤናማነትን ሲያመለክት፣ አብሮነት ደግሞ የግንኙነትን አጋርነት ጠቋሚ ነው፡፡ ሰዎችን ይቅር በማለት ነገሩን መተው ይጠበቅባችኋል እንጂ ከእነሱ ጋር አብሮ መዋልና መስራት የለባችሁም፡፡ (ይህ ነጥብ የትዳር ግንኑነትን አይወክልም)

ሰዎች ለሚያስቡት፣ ለሚያደርጉትና ለሚሰማቸው ስሜት ሃላፊነት እንዲወስዱ መተውን ልመዱ፡፡ ያንን ስታደርጓቸው ሁል ጊዜ ለሰው በመጨነቅና የእናንተ ያልሆነውን ሸክም በመሸከም ከሚመጣ ከራስ ጋር የመለያየት አጉል ተጽእኖ ነጻ ትሆናላችሁ፡፡
  
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ከደቂቃ በፊት የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ የቤት እቃን ባነቃነቀ መልኩ መከሰቱን ከተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች የደረሰን መረጃ ያሳያል።

🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ፕሮግራም የስራ እድል አግኝተው ሲሰሩ የነበሩ ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገሩ 31ሺ 2 የከተማችንን ነዋሪዎች አስመርቀናል።

የከተማችን ነዋሪዎች ሰርቶ በመለወጥ፣ በትጋት፣ የተገኘውን እድል ወደ ድል በመቀየር፣ ኑሯቸውን በማሻሻል እና ከተረጂነት በመላቀቅ አምራች ዜጋ እና ተወዳዳሪ በመሆን ከራሳችሁ አልፋችሁ ለሌሎች ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ተተኪ የሌለው ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ አቀርባለሁ።

ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገራችሁ ነዋሪዎቻችን ኑሯችሁን በራሳችሁ አቅም በዘላቂነት ለመምራት በመቻላችሁ እና ለምረቃ በመብቃታችህ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ከጥር 1 ጀምሮ በመንግስት በጀት 154 ሺሕ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ሲሆን ማህበራዊ ፍትህን በማረጋገጥ ለብዙ ዘመን አንገት ያስደፋንን እና ለተረጂነት የዳረገንን ድህነትን በማሸነፍ በልተን ማደር ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋጥ በትጋት የምንሰራ ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ክብርት ከንቲባ አዴ አዴነች አቤቤ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

500 ኪ.ግ ሊሆን የሚመዝን የጋለ ብረት ከሰማይ መውደቁ ተነገረ

በአጎራባቿ ኬንያ 500 ኪሎ ግራም ሊመዝን የሚችል ብረት ከሰማይ ወድቋል ነው የተባለው።

ቀለበታማ ብረቱ የወደቀው ሙኩኩ በተሰኘች መንደር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብረቱ የ2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ወይም ዲያሜትር ያለው መሆኑ ተመላክቷል።

የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ሰሞኑን በአፋር ክልል በተከሰተው ርዕደ መሬት ተከትሎ ከሳይንሳዊ ምልከታ ውጪ የሚሰራጩ መረጃዎች መደናገር
እንደማይገባ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የሚከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ከቅልጥ አለት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ሰሞኑን በመዲናችን አዲስ አበባ ላይ የሚሰማው ንዝረት የከፋ ጉዳት እንደማያስከትል ህብረተሰቡ ሊገነዘብ እንደሚገባ የዘርፉተመራማሪዎች አሳውቀዋል።

በሳይንስ መሬት ሁልጊዜም በዕለት ከተዕለት እንቅስቃሴ ላይ በመሆንዋ የመሬት መንቀጥቅጥ፣ የመሬት መንሸራተት፣ እሳተ ጎመራና መሰል ተፈጥሮአዊ አደጋዎች የሚጠብቅ ክስተቶች ስለሆነ ዜጎች በተዛባ መረጃ መደናገር እንደሌለባቸውና መረጃውንም ከትክክለኛ ምንጭ ማግኘት እንደሚገባቸው የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢጃራ ተስፋዬ ገልፀዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በላሊበላ ከተማ እንግዶችን ለመቀበል 45 ሆቴሎች ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ተባለ፡፡

በላሊበላ ከተማ በድምቀት የሚከበረውን የገና በአል ለማክበር ወደ አከባቢው ለሚመጡ ቱሪስቶች 45 ሆቴሎች ዝግጅታቸውን አጠናቀው እንግዶችን በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ ሲል የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ አባይ መንግስቴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት  በከተማው የገና በአል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ሰርአቱን ጠብቆ እንዲከበር ከሀይማኖት አባቶች፣ከወጣቶች ፣ከአካባቢው ማህበረሰብ  ከሆቴል ማህበራትእና ከአስጎብኚ ማህበራት ጋር የተቀናጀ ኮሚቴዎች በማደራጀት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

የአካባቢው ማበረሰብም ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይኖር መሰራቱን እና የሚመጡ እንግዶች የፀጥታ ስጋት ሊኖርባቸው  እንደማይገባ ጠቅሰዋል፡፡

የንፁህ ውሀ መጠጥ አቅርቦት ችግር እንዳይከሰትም ሰፊ ስራ መሰራቱን አንስተዋል፡፡

በበአሉ እለትም እስከ 1.2 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ እና የውጪ ቱሪስቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡

ህብረተሰቡ በላሊበላ ከተማ በመገኘት በአሉን እንዲታደሙ እና የአከባቢው ማህበረሰብ በተለመደው የእንግዳ አቀባበል ልማድ ምእመኑን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን ስላጠናቀቀ ሁሉም ማህበረሰብ የገና በአልን  በቦታው በመገኘት እንዲያከብር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

አዲስ አበባ ፖሊስ ከኢትዮጵያ ፖሊሰ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በስሩ ለሚገኙ 155 ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሰጠ።

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለ 155 የአዲስ አበባ ፖሊስ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች ለ 3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ተጠናቀቀ። ስልጠናው በሀገረ መንግስት ግንባታ ሠላምና ፀጥታን ከማረጋገጥ አንፃር የፖሊስ ተቋም የሚኖረው ሚና እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ እና በሪፎርሙ ሂደት የፖሊስ ዋነኛ ተግባር ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

በስልጠናው መርሀ ግብር ላይ ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሪፎርም እና የአመራር ሚና (Ethiopian Federal Police Reform and Leadership Role) በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል።

ስልጠናውን ለመከታተል ሰንዳፋ በሚገኘው የኢትዩጰያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለታደሙ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መስፍን አበበ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በፌዴራል ፖሊስ ሪፎርም ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ አመራሩን በስልጠና በማብቃት ፖሊሳዊ ስብዕናው የተላበሰ ዘመናዊ እና ተናባቢ ብሎም ሀገራዊ ቁመና ያለው ተቋም ለማፍራት የአመራሩ ሚና ጉልህ መሆኑን በመገንዘብ ተቋሙ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ፖሊስ ዩኒቨርሲቲው ኢትዮጵያ በ2030 አፍሪካ ውስጥ ካሉ አምስት ምርጥ የፖሊስ ተቋም ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ ከዚህ ቀደም ሪፎርሙን ተከትሎ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን ገልፀው ተቋሙ አቅዶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል የመሪነት ብቃትና ክህሎት ባላቸው፣ በአመራር ሰጪነታቸው ፣ በእውቀታቸው እና በባህሪያቸው የተመሰገኑ የፖሊስ አመራሮች ለማፍራትና የተጀመሩ ለውጦችን ማስቀጠል መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ክቡር ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በስልጠና ራሱን እያበቃ የሚሄድ አመራር ለተቀበለው የተልዕኮ ስኬት ውጤታማነት መሠረታዊ ግብዓት መሆኑን ገልፀው መሪዎች የስልጠናውን ሐሳብ በየደረጃው ለሚገኘው አመራርና አባል ማውረድ እንደሚጠበቅባቸው የሥራ መመሪያ በመስጠት ለአሰልጣኞች እና ለስልጠና አስተባባሪዎች ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ የምስክር ወረቀትም አበርክተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ተቋሙ የተጣለበትን ራዕይና ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት ረገድ ስልጠናው ለተሻለ የስራ አፈፃፀም እንደሚረዳ ገልፀው የኢትዮጵያ ፖሊስ የሰነቀውን ራዕይ ከግብ ለማድረስ ወሳኝ መሆኑን ጭምር አብራርተዋል።

በተጨማሪም ከፍተኛ አመራሮቹ በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የፎረንሲክ ምርመራና የምርምር ልህቀት ማዕከል ጎብኝተዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በድጋሚ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበትን አድራሻ https://register.eaes.et/Online በመጠቀም በበየነ መረብ መመዝገብ ይችላሉ።

ይህ የበይነ መረብ ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ።

ከዚህ መልዕክት ጋር የተያያዙ መረጃዎች ተመዝገቢዎች በቀላሉ መመዝገብ እንዲችሉ አጋዥ ስለሆኑ ተጠቀሙባቸው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

የሩሲያ ጦር በ2023 ተቆጣጠሮ ከነበረው የዩክሬን መሬት ሰባት (7 ) እጥፍ ተጨማሪ መሬት በ2024 መቆጣጠሩ ተረጋገጠ

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ በሩሲያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚወድቅ የዩክሬን ግዛት በየአመቱ እየጨመረ መጥቷል።

አኤፍ ፒ ባወጣው ሪፓርት እአአ በ2024 የሩሲያ ጦር የተቆጣጠረው የዩክሬን መሬት 4,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መድረሱን አስታውቋል።

ይህም በ2023 ሩሲያ ተቆጣጥራ ከነበረው መሬት በሰባት እጥፍ የጨመረ ነው።

ሶስት አመታትን እየተጠጋ ባለው የሁለቱ ሃገራት ጦርነት አሜሪካ ፣ ጀርመን ፣ እንግሊዝን የመሳሰሉ አገራት ዩክሬን በመሳሪያ ጭምር እየደገፉ ቢሆንም የሩሲያን ጦር መመከት አልቻሉም።

እንደ ሪፓርቱ የሩሲያ ጥር የተቆጣጠረው የመሬት ስፋት መጠን የሃይል የበላይነቱ የሩሲያ መሆኑን ያመላክታል ።

ይበልጥ በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት ሩሲያ ጦር በዩክሬን ግዛት ጠልቆ በመግባት የተቆጣጠረው የቦታ ስፋት ከአንድ አመት በፊት ከነበረው በሰባት እጥፍ የበለጠ መሆኑ ፥ የዩክሬን ጦር በተጠናቀቀው የፈንጆች አመት እየተዳከመ መምጣቱን የሚያሳይ እንደሆነ ተገልጿል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢትዮጵያ በ AUSSOM ተልዕኮ ሰራዊት እንድታዋጣ ሶማሊያ መወሰኗ ተሰማ‼️

የሶማሊያ መንግስት ኢትዮጵያ በ AUSSOM ተልዕኮ ሰራዊት እንድታዋጣ መወሰኑን የሶማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ የምታዋጣው የሰራዊት ቁጥር የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ቀጣይ January 10, 2025 በዩጋንዳ በአካል ተገናኝተው እንደሚመክሩ ተዘግቧል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ኢ/ር ቢጃይ ናይከር ሽልማቱን ተቀበለ!

በኢኮኖሚ ዘርፍ የBIWs prize አሸናፊ ኢንጅነር ቢጃይ ናይከር በዛሬው ዕለት አዳማ በሚገኘው አንቴክስ ኢትዮጵያ በመገኘት የአስር ሚልዮን ብር ሽልማቱን ተቀበለ።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

Wal waaraansi qaaniidha; nageenyi qananiidha!
===
Nagaan jiruuf jireenya tasgabbeessa, hariiroo cimsa, guddinaafi misoomni biyyaa akka itti fufu taasisa. Nagaa badaan hin jiru.Akkasumas, waraanni gaariin  hin jiru. Kanaaf  wal waraansi qaaniidha; nageenyi ammoo  qananiidha. Bakka nageenyi hin jirretti homtuu jiraachuu hin danda’u.

Kanaaf gatiin nageenyaa waan hundarra qaaliidha. Dhabamuun nageenyaa lubbuu qaalii galaafata, jireenya balleessa, maatii bittinneessa, buqqaatii hordofsiisa, misooma mancaasuun guddina biyyaa qucarsa.

Kanaaf  qaamni kamuu nageenya biyyaatiif  dursa kennuun waan hunda olitti murteessaadha. Mootummaan naannoo Oromiyaa akka naannichaattis ta’ee akka biyyaatti nageenyi waaran akka jiraatuf, gola Oromiyaatti nagaaf tasgabbiin  bu’ee, uummanni sodaa nageenyaa malee nagaan bahee akka galuuf humna guutuun  hojjechaa jira.

Hojii gama kanaan hojjetamaa jiruunis injifannoo galmaa’aa jiru waan akka salphaatti ilaalamuu miti. Haa ta’u malee nageenya waaraa itti fufiinsa qabuufi yaaddoo nageenyaafi maraammartoo wal waraansaa guututti xumura itti gochuuf hirmaannan uummataa bal’aa daran murteessadha.

Oromoofi Oromiyaatti nagaa buusuuf  waamichi nagaa ummataafi mootummaan ammas itti fufiinsan taasifamaa jira. Qaamni kamuu kana hubachuun kadhaanna uummataafi harka nageenyaf mootumman diriirsetti fayyadamuun karaa nagaatti deebi’uun gaaddisa jalatti waliin mari’achuun Oromiyaan akka tasgabbooftuufi sagalee qawwee irraa bilisa  taatu gochuu keessatti hunduu qoodasaa bahachuu qaba.

Nagaan  hundaaf, hundis nageenyaf!

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ጎዳና ላይ የሚኖሩ ሕጻናት ቋሚ አድራሻ ስለሌላቸዉ ክትባት ለመስጠት አዳጋች መሆኑ ተገለጸ

የተለያዩ የክትባት አይነቶችን ጎዳና ላይ ለሚኖሩ ሕጻናት ለማድረስ አዳጋች መሆኑን፤ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የሕጻናትና ጨቅላ ሕጻናት ቡድን መሪ እና በጤና ሚኒስቴር የክትባት አስተባባሪ አቶ ደብረወርቅ ጌታቸው ለአሐዱ ገልጸዋል።

ለዚህም እንደዋነኛ ምክንያት የጠቀሱት ብዙ ጊዜ በጎዳና ላይ ኑሯቸውን ያደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቋሚ አድራሻ አለመኖሩ፤ ክትባቱን ለመስጠትና ሕክምናም ለማድረግ ተግዳሮት እንደሆነ ተናግረዋል።

አያይዘውም መድሀኒቱን መቀበል አለመፈለግና ተደጋጋሚ መውሰድ የሚገባቸውን አንድ ጊዜ ብቻ በመውሰድ የማቋረጥ ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ እንደሆነ አክለዋል።

በመሆኑም እንደ አራዳ፣ ልደታና ቂርቆስ አይነቶች መሀል ከተማ ላይ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች፤ የጎዳና ተዳዳሪ ልጆችን ብቻ ያማካለ ክትባት ሲሰጥ እንደነበር ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከከተማ ርቀው ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ጤና ጣቢያን በአቅራቢያቸው ማግኘት ለማይችሉ እንዲሁም፤ የጎዳና ልጆችን ጨምሮ በወር አንዴ በሚሰጠው ክትባት አገልግሎት ታሳቢ ተደርገው ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ መደበኛ ክትባቶችን ሲያገኙ እንደነበር አሳውቀዋል።

በመሆኑም ክትባቶች በአብዛኛው ወረርሽኝን የሚከላከሉ፣ መስፋፋትን የሚገድቡና ባለበት ማስቆም የሚችሉ በመሆናቸው በተለያየ ጊዜ በስፋት እንደሚሰጥ ገልጸው፤ በተለየ መልኩ ጎዳና ላይ የሚኖሩ አዋቂዎችን ጨምሮ ሕጻናት ለበሽታ እና ወረርሽኝ ተጋላጭ በመሆናቸው የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚሰሩ አክለው ገልጸዋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን ለጎበኙ የሚዲያና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ያስተላለፉት መልዕክት

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባ አንኳር ጉዳዮች ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ታኅሣሥ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባው በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች ላይ ተወያይቷል። ከውይይቱ በኋላ ባወጣው መግለጫም ቀጥሎ የተጠቀሱ አበይት ጉዳዮችን ይፋ አድርጓል።

የዋጋ ግሽበት 👇

ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት ባሳለፍነው ወርኅ ሕዳር ወደ 16.9 በመቶ በመውረድ ካለፉት አምስት ዓመታት ዝቅተኛው አሃዝ ተመዝግቧል፡፡ ምርታማነትና ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መተግበሩ ለዚህ በጅቷል። የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጥ እና አስተዳደራዊ የዋጋ ማሻሻያ ምግብ ነክ ላልሆነ የዋጋ ግሽበት ሲጨምር ምግብ ነክ ያልሆነ የዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር ከነበረው 11.6 በመቶ ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ጭማሪ አሳይቷል።

ዕድገትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ 👇

አብዛኞቹ አመልካቾች እንደሚያሳዩት፣ በዘንድሮው የ2017 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በግብርናው፣ ኢንዱስትሪው፣ አገልግሎቱ ዘርፎች ዕድገት እንዳለ አመላካቾች ያሳያሉ።

የገንዘብ አቅርቦት ሁኔታ👇

በ2017 በጀት ዓመቱ ጅማሮ ወዲህ በሁሉም የገንዘብ ዝውውር አመልካቾች ዘንድ በመጠኑ ከፍ ያለ ዕድገት ታይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ የገንዘብ አቅርቦት ዕድገት ቢኖርም፤ ከኢኮኖሚው ስፋት አንጻር የገንዘብ ዝውውር አመልካቾች የመቀነስ አዝማሚያ ታይቶባቸዋል፡፡ 

የፋይናንስ ዘርፍ መረጋጋት👇

የባንክ ሥርዓት ዝቅተኛ የተበላሸ ብድር፣ ከፍ ያለ የመጠባበቂያ ሂሳብና በቂ ካፒታል ያለው በመሆኑ ጤናማና የተረጋጋ እንደሆነ በኮሚቴው ተገምግሟል፡፡ በአንዳንድ ባንኮች ዘንድ ከፍ ያለ የጥሬ ገንዘብ አከል ንብረት እጥረት ተከስቷል፡፡

የፊስካል ሁኔታ👇

የበጀት እንቅስቃሴዎች ጥሩ አዝማሚያ አሳይተዋል፡፡ ይህም በዘንድሮው በጀት ዓመት ለበጀት ጉድለት ማሟያ ከብሔራዊ ባንክ ብድር እንዳይወሰድ ያደረገና የማዕከላዊ ባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ አቋም በእጅጉ የሚደግፍ ሆኗል፡፡

የውጭ ኢኮኖሚ ዘርፍ 👇

የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ለውጥ  ለውጭ ንግድ ዘርፍ ትልቅ መሻሻል ለገቢ ንግድ ግን መጠነኛ ቅናሽ ታይቶበታል፡፡ የንግድ ባንኮችም ሆነ የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በከፍተኛ ደረጃ አድጓል፡፡

ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች 👇

የዓለም ኢኮኖሚ የሀገር ውስጥ ሁኔታዎችን የሚነካው በዋናነት በሸቀጦች ዋጋ አማካይነት ሲሆን፤ አሁን ያለው የሸቀጦች ዋጋ በጥቅሉ ለሀገራችን ምቹ ነው ሊባል ይችላል፡፡

የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የቅርብ ጊዜ የዋጋ ግሽበት ሁኔታ አበረታችና በጥቅሉ የመርገብ አዝማሚያ ቢያሳይም፣ ጠበቅ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ተገንዝቧል፡፡ በዚህም ኮሚቴው የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን አቅርቧል።

የዋጋ ግሽበት ለመቀነስና የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ተመን መኖሩን ለማረጋገጥ ሲባል የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይ ማድረግ አንደኛው ምክር ሃሳብ ነው።

ሁለተኛው ምክረ ሃሳብ ደግሞ የባንክ ብድር ዕድገት ግብ የመጠቀም ሁኔታ እንዲቀጥል፤ ነገር ግን ለዚህ በጀት ዓመት የብድር ዕድገት ግቡ ከ14 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ነው፡፡

በመጨረሻም በብሔራዊ ባንክ ለባንኮች በሚሰጣቸው የአንድ ቀን የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት፣ በአንድ ቀን የብድር አገልግሎት ላይ የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ እና ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት የግዴታ መጠባበቂያ ተቀማጭ ሂሳብ በነበረበት እንዲቆይ ወስኗል፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በአፍሪካ ቁጥር አንዷ የዲፕሎማቶች መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት 2025 በደማቅ ሁኔታ ተቀብላለች።

የመዲናዋ ሰማይ ለ15 ደቂቃዎች ያክል በማራኪ የርችቶች ትእይንት ደምቋል።

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…

የመደመር ትውልድ 🇪🇹 🙏

በከተማችን አዲስ አበባ የምትኖሩ የአውሮፓውያኑን 2025 አዲስ ዓመት የምታከበሩ ሁሉ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ ፤ዓመቱ የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት !

Happy New Year 2025 to everyone around the world. May the New year bring peace, health, prosperity, and success to you and your loved ones.

ክብርት ከንቲባ አዴ አዳነች አቤቤ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Читать полностью…
Subscribe to a channel